ኅዳሴ ግድብ እና የዓለምአቀፉ ቡድን ሪፖርት

​ አቶ ምኅረት ደበበ - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ​​ ኅዳሴ ግድብ እና የዓለምአቀፉ ቡድን ሪፖርት ታዋቂ የሆኑ ጋዜጦችና የዜና ወኪሎች ስለናይል ወይም ስለአባይ ወንዝ እና ስለኅዳሴ ግድብ እየፃፉ ነው፡፡ የኒው ዮርኮቹ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብሉምበርግ፣ ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል፣ ዘ ናሽናል ከእነዚያ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ​ ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል በረቡዕ፣ ጥቅምት 6/2006 ዓ.ም ዕትሙ ባሠፈረው ዘገባው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በመጭው ሣምንት ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12/2006 ዓ.ም እንደሚሰበሰቡ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምንጭነት ጠቅሶ ፅፏል፡፡ Ethiopia, Sudan, Egypt, Eritrea ​​ ይህ ስብሰባ የሚካሄደው በሦስቱ ሃገሮች የተመሠረተው የኤክስፐርቶች ቡድን የቅኝት ሪፖርቱን ካስገባ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ...