ጥቅምት ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት። እስከዳር”  አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች። “ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ …

በግል ስልኩ የተቀረጸ የቪድዮ ምስል ይመልከቱ!

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 1  ቀን 2006 ዓ.ም. October 11, 2013)የሙስሊም ራዲዮ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄዎች ላይ ትንተናዎችን በመስጠት የሚታወቀው ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካን ሀገር ይፋዊ ያልሆነ ጎዞ ላይ ከሚገኙት የህወሃት ባለስልጣናት መሀከል አቶ ስብኃት ነጋን በአካል አግኝቶ በግል ስልኩ እየቀረጸ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥያቴ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ከሠላሳ ዓመታት በላይ አገልግለዋል ‹‹በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ይዞታ እንዳለን በታሪክ ሰፍሯል፡፡ ግብር ለመገበር አቅም ስላነሰን ዴር አብርሃምን ግሪኮች ወሰዱብን፤ ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፤ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብጾች ወስደው አጥፍተውታል፡፡›› ‹‹ግብጾች በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ ግብጾች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን፣ በመጪው ሰኔ ወር በብራዚል ለሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አፍሪቃን ወክለው ከሚገኙት 5 ቡድኖች አንዱ ሆኖ ለማለፍ ፣ከናይጀሪያ ጋር የቀሩት 2 የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ናቸው።

የአንድን ወይንም የራስን ሀገር፣ ቤተ መዘክር፣ ሀውልት፣ የህንፃም ሆነ ሌሎች ቅሪቶች እና የመሳሰሉትን በመጎብኘት ስለ ሀገር ታሪካዊ ቦታዎች እና ታሪክ ማወቅ ይቻላል። ለመሆኑ ወጣቱ ስለ ሀገሩ ታሪካዊ ቦታዎች ምን ያህል ያውቃል? ምን ያህልስ ማወቅ ይፈልጋል?

ደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ…ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ…ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን…ቢኖሩም…የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው – ‘ኢምንቱ’ ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!

ሙሉውን አስነብበኝ …

SHARE:

አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረዉን ቤት ‘ለወሔነት’ ባርና ሬስቶራንት ለፔንሲዮን አገልግሎት እንዲሚጠቀምበት ቢሆንም የፔንሲዮኑ ባለቤት የሆኑት አቶ በላቸዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ 3 አስተዳደር በግዴታ እንዲከራዩ የእያስገደዷቸዉ ሲሆን አቶ በላቸዉና የቤቱ ባለቤቶች እኛ ተገደን ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱን ለፓርቲ ጽ/ቤት እንዳይከራይ እየተከራከሩ ያሉት በአቶ ያለዉ እዉነቱ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሚመሩ የመስተዳድሩ አካላት መሆናቸዉ በይበልጥ ለፓርቲዉ ጽ/ቤትነት ለመጠቀም እንዳንችል መንግስት እጁ እንዳለበት መገንዘብ ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

በአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ህዝባዊ ንቅናቄ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ሁለት ደህንነቶች ዘላለም ደበበን ወደ ሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ በመዝለቅ በህገ ወጥ መንገድ ከወሰዱት በኋላ በማስፈራራትና ተራ የስድብ ቃላትን በማዝነብ በመጨረሻ ያለ ምንም ክስ መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ እንደሁልግዜው ማልዶ በስራ ገበታው የተገኘው ዘላለም በሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ቤተ መጻህፍት ለአዳዲስ […]

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡ የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን […]

SHARE:

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡

SHARE:

ሰማያዊ ፓርቲ ቀድሞ ከነበረበት ጽ/ቤት ወደ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ ፅ/ቤት ተከራይቶ ከቤቱ ባለቤቶች ጋር ለ2 ዓመት የሚቆይ ውል የተዋዋለ ሲሆን በውሉ እንደተገለፀውም ከዛሬ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ የሰማያዊ ፓርቲ በመሆኑ ቤቱን ለመረከብ በሄዱበት ወቀት ቤቱን እኛም ተከራይተንዋል በሚሉ ግለሰቦች ቤቱን በፖሊስ ሀይል ታግዘው ይዘውታል፡፡ የፓርቲው አመራሮችም ቤቱን በህጋዊ መንገድ እንደተከራዩትና ከዛሬ ጀምሮ የቤቱ ባለመብቶች እንደሆኑ ለፖሊስ ያስረዱ ሲሆን ይህ ዜና እስከደረሰን እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስም አብዛኛው የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ ጣቢያ እንደሆኑና በስልክም ማነጋገር አስቸጋሪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይነት የሚኖረውን ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን፡፡
(ፎቶ፡- ፓርቲው ከአከራዮቹ ጋር የገባው ውል)

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል። እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው እንደዘገበው  መላኩ ደምሴ  ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰዷል፡፡ ጋዜጠኛው ለጥያቄ የተወሰደው ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ …

መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል። ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት። የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ …

በአክሱም መንግሥት መደበኛ ቋንቋ እንደነበር ይነገራል፤ የግዕዝ ቋንቋ። ዛሬም ድረስ የግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ፤ በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ ይዉላል።

አጋቾች ኋላ ላይ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚንስትሩን ያገቱት፥ ዩናይትድ ስቴትስ በ1990 የናይሮቢና የዳሬ-ሰላም ኤምባሲዎቿን ካጋዩ «አሸባሪዎች አንዱ» ያለችዉን አቡ አነስ አል ሊቢን ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ አፍና ስትወስድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተባብረዋል በሚል ለመበቀል ነዉ።

ማይ አይኒ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ወደ ኢጣልያ ለመሻገር ሲሞክሩ ባለፈው ሳምንት የሞቱትን ኤርትራውያን ለማሰብ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ስደተኞቹ ካዘጋጁት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በኃላ ባካሄዱት ሰልፍ ብሶታቸውን ሲያሰሙ ነበር ።

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ፊታውራሪነት የአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን አሰራር ለመቃወም አፍሪካ መንግስታት በአዲስ አበባ ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል። ጠ/ሚ ሀይለማርያም ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርበው የወንጀል ፍርድ ቤቱን ተችተው ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር መሪዎችን ከጥቅምት 1 እስከ 2 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት እንደሚያደርግ ሪፖርተር ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር  በሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 በጀት ዓመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበርካታ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት እድገት መመዝገቡን አወድሰዋል። የግብርና ዘርፍ በ2005 በጀት ዓመት የ7 ነጥብ 1 በመቶ የአገልግሎት ዘርፉ  ደግሞ የ4 ነጥብ 9 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል። …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ አዲስ ፕሬዚደንት በመምረጥ የዚህን ዓመት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ፓርላማ በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ በንባብ የቀረበውን የመንግስት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫና ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀጣይ ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት በሚቀርቡ የድጋፍና የተቃውሞ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል፡፡ ፓርላማው በትላንት ውሎው መስከረም 27 ቀን 2006 ዓም አዲሱ ፕሬዚደንት ያደረጉትን …

  መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውይይታቸውን ያደረጉ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ጋዜጠኞች ሚዲያዎቹ በመንግስት የአፈና እና የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል።   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የባለሙያዎች የጥናት እና ምርምር ግኝት ስራዎች ላይ ተመርኩዞ ከባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በቀረቡት ጽሁፎች እንደተገለፀው የኢትዩጵያ ሚዲያዎች አዲስ የሚቋቋሙትም ሆነ ነባር …

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱፐር ኤግልስን ካሸነፉ መንግስት  እንደሚሰጣቸው ቃል የገባላቸው ቦነስ በቂ እንዳልሆነና ስሜታቸውን የሚያነሣሳ እንዳልሆነ ነው  ተጫዋቾቹ የተናገሩት። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀናት በፊት የ22ቱን ተጫዋቾች ስም ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነው ጌታነህ ከበደ በጉዳት ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም። በቀራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ ናይጀሪያን አሸንፈው ለዓለም ዋንጫ ካለፉ …

ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣ በባሌ/ሮቢ፣ በፍቼ፣ በአዳማ/ናዝሬት፣ በመቀሌ (በሙሉ ባይሳካም) ፣ በደሴም በባህር ዳርና ፣ በጎንደር የተደረገው የመጀመሪአዉ ዙር የሚሊየነሞች […]

ከ 318 ዓመታት በፊት ፣ እ ጎ አ በ 1705 ዓ ም መሆኑ ነው፣ ታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ና የሒሳብ ሊቅ አይዛክ ኒውተን፤ ስለ ስበት ኃይልና ስለብርሃን ምንነት ካደረገው ምርምር ውጭ ፣ ስለ ኅልፈተ ዓለም በማንሳት፤ እ ጎ አ በ 2060 ዓ ም፣

የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድ ጀርመን የሶሪያውን ቀውስ እንድትሸመግል እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ለአንድ የጀርመን መጽሔት እንዳሉት የጀርመን ልዑካን ሶሪያ መጥተው የሃገሪቱን አጠቃላይ ይዞታ እንዲመለከቱና በተጨባጩ ሁኔታ ላይ ከደማስቆ መንግሥት ጋር እንዲወያዩ ጠይቀዋል። ይሁንና የጀርመን መንግስት የአሳድን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

አፍሪቃ ውስጥ ሥራ እያላቸውም በልተው ማደር ያቃታቸው ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መዘርዝር ከሆነ 40 ከመቶ የሚሆን አፍሪቃዊ የሚተዳደረው በቀን ከ25 ብር በታች በሆነ ገቢ ነው።

በተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) ‹‹ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴ›ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉአሰፋ

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6 2013ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደ ቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨርኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ– አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፤ 19ኛ ዓመት ቁጥር 255፤ ነሐሴ 16 – ጳጉሜ 5 2004 ዓ.ም) ዲ/ን ታደሰ ወርቁ* ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ መንግሥታዊ አካላት የወጡ ሰነዶችና የሚሰሙ ንግግሮች ማኅበረ ቅዱሳንን የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት አክራሪዎች ማንጸርያ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው፡፡ ይህን የተሳሳተ አቻ ፈጠራ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን የራሳቸውን ፍላጎት ሲያራግቡበት ይታያል፡፡ ተከታዩ ጽሑፍ መንግሥት አቋሞቹን የገለጸባቸውን …


ከቅርብ ግዜ ወዲህ ፌስቡክ የወቅቱን ጨቋኝ ሕወሓትን ጥሎ የቀድሞዎቹን ጨቋኞች እነ ምኒልክን አንስቷል፡፡ ነገርዬው ሲተቹት በመሣሪያ መልስ ከሚሰጥ አካል ጋር ከመታገል፣ በሕይወት ከሌሉት ወይም ቀጥተኛ ተወካይ የሌላቸው ላይ መዘባበት ይሻላል በሚል ይሁን ወይም የጥያቄው አሳሳቢነት ስር ሰዶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም፡፡ በታሪካዊ ጭቆናዎች ትርክቶች ውስጥ ‹አንዱ በማፍረስ፣ አንዱ በመካብ፣ ሌላው ደግሞ በመገላገል› ሁሉም የያቅሙን የሞት ሽረት እያደረገ ነው፡፡

እነ አብይ አቶምሳ ‹‹የታሪክ ኢ-ፍትሐዊነት ላይ መተማመኛ ላይ ሳንደርስ ወደፊት ንቅንቅ የለም› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ትላንትና ዛሬ ደግሞ የኔም ወዳጆች በያዝ ለቀቅ የከረመውን ‹‹የይቅርታ ጉዳይ›› ቀለል አርገውም ቢሆን አንስተውታል፡፡ ናትናኤል ፈለቀ ‹‹የአባት ሀብት ወይም ዕዳ ለልጅ እንደሚተላለፍ ሁሉ የአባት ትውልድ በደል ለልጅ ትውልድ ይተላለፋልና፣ የበዳይ አባት ልጅ ትውልድ የተበዳይ አባት ልጅ ትውልድን ይቅር ቢል ምን አለበት?›› የሚመስል አማራጭ የመፍትሔ ጥያቄጠቁሟል፡፡ ማሕሌት ፋንታሁን ደግሞ ‹‹ነገሩን የተበዳይ ቦታ ሆኜ ብሆን ብዬ ሳስበው ከዚህ ትውልድም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ›› የሚል ጭብጥ ያለው የራሷን የይቅርታ መልዕክትአስነብባናለች፡፡
በኔ አመለካከት የጓደኖቼ ሐሳብ ለውይይቱ ጥሩ መንገድ ቢጠርግም፣ ይቅርታ መጠየቅ እና ምሕረት ማግኘት በአገራችን የብሔር ጭቆና ጉዳይ እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ግለሰቦች ‹‹ይቅር ለእግዜር›› የሚፈታ አይመስለኝም፡፡ በጭቆናው ጥልቀት እና አተረጓጎም ላይ እንኳን ገና መግባባት ላይ አልደረስንም፡፡ ስለሆነም እነዚህን መጠየቅ ይቀድማል ባይ ነኝ፤
  • ይቅርታ የሚጠያየቁት አካላት (የሚጠይቀው እና የሚጠየቀው) እነማን ናቸው?
  • ይቅርታ የሚጠየቅበት በደልስ የትኛው ነው?
  • ይቅርታ የሚጠየቀውስ እንዴት ነው?
  • ይቅርታው ያለካሣ ምሕረት ያገኛል ወይ?
  • ምሕረት የሚያስገኘው የካሣ ዓይነትስ ምንድን ነው?

‹አቢሲኒያውያን (በተለይ አማራ እንዲሁም ትግራይ) በተለይ ላለፉት 130 ዓመታት በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ (እና እንዲሁም በደቡብ ሕዝቦች ላይ) ‹‹ኢትዮጵያውነትን የመጫን›› (ወይም በሌሎች አነጋገር በኢትዮጵያ ክልል አጥሮ በማስገባት እና በጉልበት በማስገበር) ቋንቋቸውን፣ ባሕላቸውን፣ እምነታቸውን እና ጠቅላላ ማንነታቸውን የሚያጠፋ (ወይም በአማራነት የሚተካ – amharanize የሚያደርግ) በደል /ጭቆና/ አድርሰውባቸዋል› የሚለው ከሞላ ጎደል ጉዳዩን የሚገልጸው ቢሆንም በተለያዩ አካላት ግን የተለያየ አተረጓጎምና የቃላት አጠቃቀምም ጭምር ይኖረዋል፡፡

ብዙ የአማራ ልሒቃን የነበረው የማስገበር ሒደት አገር የማስፋት ነው እንጂ የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት ለማጥፋት የተደረገ ነገር የለም፡፡ የአማራውም የኦሮሞውም ገበሬ በነገሥታቱ ዕኩል ሲገብር፣ ሲዘረፍ እና ሲበደል ነው የኖረው ይላሉ፡፡ የኦሮሞ ልሒቃንም በበኩላቸው በሕዝባችን ላይ የደረሰው ‹የቅኝ አገዛዝ እንጂ ተራ ጭቆና አይደለም› ከሚሉት (ሌንጮ ለታ) አንስቶ ‹የነዳግማዊ ምኒልክ የማስገበር እርምጃ ነበር፤ አገር በዚያ መንገድ ነው የሚገነባው ቢሆንም የኦሮሞን ማንነት ግን ማጥፋቱ ፍትሐዊ አልነበረም… አሁንም ሒደቱ አልቆመም፡፡› እስከሚሉት (አቶ ቡልቻ ደመቅሳ) እንዲሁም ‹በኦሮሚያ የማንነት ጭቆናዎች ቢኖሩም የመደብ ጭቆናውን ያክል የከፋ አልነበረም፤ የኦሮሞ ባላባቶችም የኦሮሞ ሕዝብን በድለዋል› እስከሚሉት (ዶ/ር መረራ ጉዲና) እና ሌሎችም በከፊል የሚገናኙ እና በተለይ በአማራጭ መፍትሔዎቻቸው የሚለያዩ ማለትም ‹መገንጠል ነው መፍትሔው› በሚሉና ‹የለም ከሌሎች ጋር አብሮ በዕኩልነት ራስን ማስተዳደር› ይሻላል የሚሉ የተለያዩ አተረጓጎሞች አሉበት፡፡
ይቅርታ የመጠያየቅ አጀንዳ ሲመጣ በላይኛው አንቀጽ መሠረት አማራ በዳይ፣ ኦሮሞ ተበዳይ ለማለት የሚያስችሉ በርካታ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልገናል፡፡ የአማራ ባላባቶች (ወይም አማርኛ ተናጋሪዎች ማለትም ይቻላል – ምክንያቱም በተለይ የሸዋ ኦሮሞዎች የሚገባቸውን ያክል እንኳን ባይሆን በሥልጣኑ ውስጥ ቦታ ነበራቸው) በማስፋፋት፣ በነፍጠኝነት (ማለትም በኦሮሞ አካባቢዎች በነፍጥ ኃይል በመስፈር እና የአካባቢውን ነዋሪዎች ጭሰኛ በማድረግ) ለሠሩት በደል አማራ በጥቅሉ ተጠያቂ መሆን ይችላል ወይ? በወቅቱ ‹‹የጨዋው ልጅ አምስት መቶም አንሞላ›› የሚሉ ባላባቶች በነበሩበት ዘመን ብዙኃኑ የአማራ ተወላጅስ ቢሆን በጭሰኝነት እየገበረ የሚኖር ተጨቋኝ አልነበረም ወይ? ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦሮሞ መብት አራማጆች የሚያነሱት ወሳኝ መሟገቻ ‹የአማራ ብዙኃን ቢያንስ ማንነቱ አደጋ ላይ አልወደቀም፣ ይልቁንም ተስፋፍቶለት አሁንም ድረስ ስር ለሰደደው ተጠቃሚነት አብቅቶታል› የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ብዙኃኑ ተበዳይ በነበረበት ስርዓት ውስጥ በቋንቋ የሚመስሉት ሰዎች በደል በማድረሳቸው የእነርሱን በደል ተንተርሶ ይቅርታ መጠየቅ አለበት የሚለው ውኃ የማያነሳ መከራከሪያ ሊሆን ይችላል – አንዳንዶች ግን ‹‹ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሲባል ምን አለበት?›› ባዮች ናቸው፡፡
‹ይቅርታ ይጠየቅ – ጠያቂም አይጎዳም፣ ምሕረት አድራጊም አይከስርም› ቢባል ደግሞ ማነው የሚጠየቀው – በጥቅሉ የኦሮሞ ሕዝብ (እና ሌሎችም የደቡብ አካባቢዎች መኖራቸው እንዳይዘነጋ) ቢባል ማነው የሚጠይቅው – የአማራ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ ወካይ ፓርቲ (አለው?)፣ ክልላዊ መንግሥቱ (የያኔውን መንግሥት የመወከል ቅቡልነት አለው?) በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም፡፡ ይቅርታ የሚጠየቅበት በደልስ የትኛው ነው፣ የመስፋፋቱ ነው? በጭሰኝነትና ማስገበሩ ነው? ‹‹በቅኝ አገዛዙ ነው››? ወይስ አገር በቀሉን ስርዓት (እንበል ‹‹ገዳ››ን) በመተካቱ ነው?
ይቅርታው ተሳክቶ ተጠያየቁ እንበልና ከዚያ በኋላ የሚመጣው ምንድን ነው? ሁሉም ባለበት ይረጋል ወይስ እንደአዲስ ዕቅድ ማውጣት እንጀምራለን፡፡ ለደረሰው በደልስ ካሣው ምንድን ነው?
ሕወሓት ሕገመንግሥቱ በራሱ በደሉን ሽሮ ወደአዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ባይ ነው፡፡ በሕገመንግሥቱ የተገኘው ነገር የብሔር ፌዴራሊዝሙ ነው፡፡ ፌዴራሊዝሙ ተበዳይ ብሔረሰቦች ያለፈው በደላቸው ባይካሥም እንደአዲስ ግን ራሳቸውን በራሳቸው መገንባት የሚችሉበትን ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሎ ታምኗል፡፡ ሆኖም አሁንም የብሔር ጭቆናው ቀጥሏል ብለው የሚያምኑ ልሒቃን አሉ፡፡ በተለይ የኦሮምኛ ቋንቋ የፌዴራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት፤ ራስን በራስ የማስተዳደሩ ሚናም በእውነተኛ የኦሮሚያ ወኪሎች እንጂ በእጅ አዙር በሚገዙ ወኪሎች መሆን የለበትም የሚሉ (ይህ እንደተመልካቹ የሚለያይ እውነት ይሆናል) እና ከዚያም ባለፈ ደግሞ የተቀማነው ‹‹ነጻነት›› (ወይም ራስን የቻለ አገርነት) ካልተመለሰ ጭቆናው ቀጥሏል የሚሉም አሉ፡፡ ካሣው እንደየልሒቁ ይለያያል ማለት ነው፡፡ ምሕረቱም ምሕረት ላይሆን ይችላል፡፡

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ  የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው  የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ  ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል  እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር …

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እና በሊቢያ በልዩ ኮማንዶዎችዋ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ የወሰደችው የጥቃት ርምጃ ከአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖችዋ ይልቅ በልዩ ኃይል ላይ ያተኮረ ሥልት መከተሏን አመላካች ሆኖ ታይቶዋል።

ግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋ ምክክር አካሄዱ። ባለሥልጣናቱ ከአንዱ ቀን ውይይት በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ አፍሪቃ በአህጉሯ ለሚታዩ ውዝግቦች መፍትሄ ለማሰገኘት በምታደርገው ጥረትዋ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጾዋል።