ሚሊዮኖች ድምጽ – ለመጋቢት 28ቱ ሰልፍ በአዲስ አበባ ቅስቀሳ ተጀምሯል
መጋቢት 28 የሚደረገዉን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ፣ የአንድነት አባላቶችንና ደጋፊዎች በአራት የከተማዋ አቅጣጫዎች በመሰማራት በራሪ ወረቀቶችን ለሕዝብ ሲያደርሱ እንደነበረ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በአዲስ አበባ መንገዶች ሲሰራጩ ከነበሩ በራሪ ወረቀቶች መካከል ፡
መጋቢት 28 የሚደረገዉን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ፣ የአንድነት አባላቶችንና ደጋፊዎች በአራት የከተማዋ አቅጣጫዎች በመሰማራት በራሪ ወረቀቶችን ለሕዝብ ሲያደርሱ እንደነበረ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በአዲስ አበባ መንገዶች ሲሰራጩ ከነበሩ በራሪ ወረቀቶች መካከል ፡
መጋቢት 20/ 2006 ዓ.ም የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሶዶ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ምንም አይነት ምክንያት ሳይሰጥ ሰብስቦ እንዳሰራቸው ከአካባቢው የፓርቲው ተወካዮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ ድል በትግል በተባለው የፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም እስር ላይ ከሚገኙት መካከልም፡- 1. ወጨፎ ሳዳሞ የወላይታ ዞን ምክትል ሰብሳቢ 2. ታደመ ፍቃዱ […]
«በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውም ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ፣ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል» ሲል ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ […]
ጉባኤዉ ገና ሳይጀመር በፊት የአዉሮጳ ሕብረት የአፍሪቃ ሕብረት አባል ያልሆኑትን የአፍሪቃ መሪዎች ጋብዞ አባል ከሆኑት አንዳንዶቹን አለመጋበዙን የተቃወሙ የአፍሪቃ መሪዎች በጉባኤዉ አልተሳተፉም
ኢንተርኔት ፤ በአሁኑ ዘመን ችላ የማይባል የዕለታዊ ህይወት አንድ አካል ነው ከተባለ፣ አባባሉ ሢሦውን የዓለም ሕዝብ ብቻ ነው የሚመለከተው። አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበው መረጃ መሠረት የኢንተርኔት ተጠቃሚ
የሰሃራን ምድረ በዳ አቋርጠው በጀልባ አውሮፓ ለመግባት የሚጥሩ አያሌ ወጣቶችና ጎልማሶች በየጊዜው ስለሚያጋጥሟቸው አያሌ ሕልውና ተፈታታኝ ተግዳሮቶች ያልተነገረበት ጊዜ የለም። ቀደም ባሉት ጊዜያት ከሰሜን ምዕራብ አፍሪቃ በጀልባዎች ወደ ካናሪ ደሴቶች
ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል
የዕለቱ ዜና
#udj@addisabeba የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባዎች ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላቀረበላቸው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ደብዳቤ ህገ ወጥ ምላሽ በመስጠታቸው ፓርቲው ደብዳቤውን የተቃወመበትን የህግ አግባብ በመጥቀስ ደብዳቤ ልኮላቸው ነበር፡፡ አቶ ማርቆስ በጽ/ቤታቸው በአካል የተላከላቸውን ደብዳቤ ምስክሮች ባሉበት ‹‹አልቀበልም ብትፈልጉ ክሰሱኝ››በማለት በህጋዊ መንገድ የቀረበላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም በማለት መልሰዋል፡፡አንድነት ፓርቲ […]
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በዛሬው ዕለት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ የሚቀለበስ ሰላማዊ የትግል ስልት ባለመኖሩ የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበለት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ምላሹን እንዲሰጥ በአክብሮት እንጠይቃለን››ብሏል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ በመጻፍ ሰልፉን ማከናወን አትችሉም ማለቱ ከህግ በላይ ነኝ የሚል መንፈስ እንዳለው እንደሚያሳይ የገለጸው […]
የኢትዮጵያ ሬዲየና ቴሌቪዥን ድርጅት ከኅዳር 16 እስከ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. በተከታታይ ሦስት ክፍሎች ‹‹አኬልዳማ›› በሚል ባቀረበው ዘጋቢ ፕሮግራም፣ክብርና ዝናን የሚያጠፋ በድምፅ፣ በምስልና በጽሑፍ በተቀነባበረ መንገድ ስሙን እንዳጠፋው በመግለጽ፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በመሠረተበት የፍትሐ ብሔር ክስ ተረታ፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ዘጠነኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት መጋቢት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. […]
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
“ማሕበረ–ወያኔ”
በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ቢደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል። የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል።
አንድነት በቅርቡ ይፋ ባደረገው የሚሊዮን ድምጽ ንቅናቄ አሥራ አራት የተመረጡ ቢሆንም፣ ከአሥራ አራቱ ከተሞች ዉጭ ያሉ ሌሎች ከተሞችና ወረዳዎች ም «ለምን እኛ ጋር አልተደረገም ?» የሚሉ ጥያቄዎች እያነሱ እንደሆነ ይነገራል። ከነዚህ ቦታዎች አንዱ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ የምትገኛው የደራሼ ልዩ ወረዳ፣ የምትገኘው የጊዶሌ ከተማ ናት። በወረዳው ያሉ ነዋሪዎች ፣ «የትግሉ መሪ እኛ ነን ። እባካችሁ በአደባባይ […]
እንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የፊታችን እሁድ መጋቢት28 ቀን 2006 ዓ.ም፣ በታላቋ የደሴ ከተማ፣ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለማረጋገጥ ችለናል። አስፈላጊው ባለስልጣናትን የማሳወቅ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ አንድነት በደሴ እና በአካባቢዋ ያሉ ነዋሪዎች በሙሉ፣ በነቂስ እንዲወጡና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል። በከተማዋም ቅስቀሳ፣ በጥቂት ቀናቶች ዉስጥ ይጀመራል ተብሎ ይገመታል። ከስድስት ወራት በፊት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ […]
«አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፣ ዛሬ ባካሄደው ልዩ አስቸኳይ ስብሰባ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ‹‹የእሪታ ቀን››በሚል መሪ ቃል የተጠራው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ማወቅ ለሚገባው አካል ሁሉ የማሳወቅ ስራው የተጠናቀቀ በመሆኑ፣ የአደባባይ ቅስቀሳ ስራው ከነገ ማለትም መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም፣ ጀምሮ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል እና ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ምክር […]
መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል።
የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመስማማት ከፈለገ ምንም ቂምና ቁርሾ የምንይዝበት ነገር አይኖርም ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ 20 ሺ ኤርትራውያን ስደተኞችን ታስተምራለች የተባለውም የተጋነነና ቁጥሩ ከ1800 እንደማይበልጥ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ እነዚህ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንደማይሆኑና አስፈላጊው ምርመራ ተካሂዶባቸው ትምህርት እንደጀመሩ ገልጸዋል።
ከኤርትራ ስደተኞች ይልቅ የጸጥታ ስጋት የሚፈጥረው የኢትዮጵያ ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህን ወጣት መከታተል የጸጥታ ችግሮችን እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።
በንግግራቸው መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ባይከብርም የመክፈር ፍላጎት እንዲኖረው በማድረጋችን ጸጥአየትኩረት አቅጣጫውን ለማስቀየር ችለናል ብለዋል።
የጅቡቲ ወደብን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ፣ ለጅቡቲ ወደብ የምንከፍለውን ኪራይ የጅቡቲ መሪዎች ቤተሰቦች የሚቀራመቱት በመሆኑ አገሪቱ ወደብ ትከለክለናለች ብለን አንሰጋም ሲሉ መልሰዋል።
በመብራት መቆራረጥ የሚሰቃየው የኢትዮጵያ ህዝብ “እፎይ” የሚልበትን ቀን ሁሉም ይናፍቃል። የአባይ ወንዝ ከተገደበ በኋላ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ከኢትዮጵያ አልፎ ለሱዳን እና ለግብጽ እንደሚበቃም ይነገራል። ከዚህ ግድብ በተጨማሪ የግልገል ጊቤ 2 እና 3 ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የሚኖራት የመብራት ሃይል በአስር እጥፍ እንደሚጨምር የዘርፉ ሙያተኞች ይመሰክራሉ። በዚህ አጋጣሚም በመብራት መቆራረጥ እና እጦት የሚሰቃየውም ህዝብ የሚካስበት አጋጣሚ ይፈጠራል። […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ኢቲቪ ተመጣጣኝ የማስተባበያ አየር ሰዓት ለአንድነት ፓርቲ እንዲሰጥ ታዟል የዘገየ ፍትህ እንደተሰጠ ባይቀጠርም በአንድነት ፓርቲ እና በኢትጵያ ቴሌቪዥን መካከል “አኬልዳማ ዘጋቢ ፊልምን አስመልክቶ ለነበረው 3 አመታትን ለፈጀ ክርክር ለአንድነት ፓርቲ ፈርዶ መቋጫ ሰጥቶታል በመሆኑም ኢ.ቲ.ቪ የአንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ ተመጣጣኝ የማስተባቤ አየር ሰዓት ለአንድነት እንዲሰጥ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ችሎቱን የተከታተለው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ […]
ችሎቱ በተከሳሽ በእነ አቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ቃልም ማድመጥ ጀምሯል ። ዛሬ የአንዱን ተከሳሽ ቃል ያደመጠው ችሎቱ የተቀሩትን 18 ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ለማዳመጥ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል ።
በጎርጎሮሳውያኑ 2013 ጀርመን ተገን እንድትሰጣቸው የጠየቁ ስደተኞች ቁጥር በኢንዱስትሪ በበለፀጉ ሌሎች ሃገራት ካመለከቱት ቁጥር ጋር ሲነፃጸር ከፍተኛ ነው ። ሆኖም አብዛኛዎቹ ጀርመን እንድትቀበላቸው የጠየቁ አመልካቾች የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ባለሞያዎች ይናገራሉ ።
በኬንያ መዲና፣ ናይሮቢ በተጣሉ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና 25 መቁሰላቸውን የኬንያ ሀገር አስተዳደር ባለሥልጣናት አስታወቁ። ትናንት ማታ የተጣሉት ጥቃቶች ዒላማ ያደረጉት በብዛት
አቶ አስራት ዛሬ በጠበቃቸው በኩል ለልዩ ችሎቱ ባቀረቡት ይግባኝ በአንድ የግል መፅሄት ላይ ፍርድ ቤቱን በመድፈርና በመተቸት ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የተጣለባቸው የ2 ዓመት ገደብ እንዲነሳላቸው ጠይቀው ነበር ።
የአፍሪቃ መሪዎች ስምምነቱን ላለመቀበል የሚያቅማሙበት ብዙ ምክንያት አላቸዉ።ቀድሞ የሚጠቀሰዉ ግን ማርቲን እንደሚሉት አዉሮፖች ለአፍሪቃ ምርቶች ቀረጥ ሳይጠይቁ ገበያቸዉን ክፍት ካደረጉ፤ አፍሪቃዎችም በምላሹ ለአዉሮጳ ሸቀጦች ቀረጥ ሳያስከፍሉ ገበያቸዉን ክፍት እንዲያደርጉ መጠየቃቸዉ ነዉ።
አዋጁን-።«ለማስከበር እና ቦኩ ሐራምን ለማጥፋት» ተብሎ የዘመተዉ ጦር ሕዝቡን መዉጪያ መግቢያ አሳጣዉ።የጠረጠረዉን በመደዳ-ያስር፤ያሰረዉን ይገርፍ፤ ያሰቃይ፤ እስራት-ስቃዩን ለማምለጥ የሞከረዉን እያሳደደ-ይገድለዉ ያዘ።አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ ይሕ የሁለቱ ሐይላት እርምጃ ከጦር ወንጀል የሚቆጠር ነዉ።
ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ሕገ ወጥ ተግባራት መካከል÷ ያልተፈቀደላቸው ሰባክያን ስምሪትና የኅትመት ውጤቶቻቸው፣ የአስመሳይ ባሕታውያንና መነኰሳት ነውረኛ ድርጊቶች፣ ሕገ ወጥ ልመና፣ የአጥቢያ አስተዳደር ሙስናና የወጣት ሱሰኝነት ይገኙበታል፡፡ ማዕተብ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምእመን በተለይም ወጣቱ ከሱስ ነጻ መኾን አለበት፤ መስቀሉን አንጠልጥሎ በየባንኮኒውና በየዳንኪራው ከመታየት መጠበቅ አለበት፤ ዶግማውን፣ ቀኖናውንና ትውፊቱን ያወቀና የጠነቀቀ፣ በኢኮኖሚያዊና ፋይናንሳዊ አቅሙም ጠንካራና እርስ በርሱ መደጋገፍ ይገባዋል፡፡ …![]()
Genet Zewdie, Solomon Kifle
(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 22/2006 ዓ.ም፤ ማርች 31/2014. PDF)፦ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳንን ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገው ትርምስ ተጀምሯል። ይሁዳ ለ30 ዶላር እነዚህ የዘመናችን ሰቃልያን ደግሞ “ማኅበሩ ያፈራውን ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል። በዚህም በዚያም ክህደት እና ስቅለት።
ግለሰቡ “የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች”የሚልና ስለ ዝርፊያው ጥልቅ ምንነት አይን ገላጭ የሆነ ማስረጃ ያቀረቡ ናቸው። ዝርፊያው ምን ያህል የጎላ መሆኑን ሲያብራሩ ያሉትን እናክል፦ የመንግስት ባለስልጣናት የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል ሙስና ኮሚሽን አማሯል።
ኢትየጵያ ውስጥ አሁን ያለው የሙስና መጠን ትናንትና ከነበረው እጥፍና ከእጥፍ በላይ አሻቅቧል፡፡ አሁን አገሪቷ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ወደላይ እንዲያሻቅብ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱም የሙስና ጣርያ መንካት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አሳሳቢ መሆኑን መግለጽ ቀርቶ የእገሌን አገር ደረጃ አያክልም የሚለውን አባባል የኢትዮጵያ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡በአሁኑ ወቅት ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቷል፡፡ ባለጉዳይም ጉቦ ካልሰጠ ጉዳዩን እንደማያስጨርስ፤ ጉዳይ ፈጻሚም ገንዘብ ካላገኘ ጉዳይን ማስጨረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በገሃድ በሚታይበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በጉምሩክ፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሆስፒታሎች፣ በኢሚግሬሽን፣ ወዘተ ጉዳይን ለማስጨረስ ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡
ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡ ጉቦ የማይቀበል የማይረባና የማይጠቅም ተብሎ የሚሰየምበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን እያንዳንዱ ሰው በሚገባ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህ በመሰለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም ሲባል ምን ማለት ነው? መረጃው የተገኘውስ ከየት ነው? ከተበዳይ ወይስ ከበዳይ?
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢዎች አነስተኛም ይሁኑ ትላልቅ የፕሮጀክት ጨረታዎች ያለኮሚሽን ክፍያ የተፈጸሙ ናቸው የሚል ጥናት ፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ምንልክሳልሳዊበአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግዢዎችና ጨረታዎች ሕጋዊነትን ለማስያዝ ብቻ የሚካሄዱ ካልሆነ በስተቀር፣ አስቀድሞ ከታቀደውና ከታለመው ሰው ወይም ድርጅት ውጭ ማንም እንዲገባ በማይፈቀድበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የዋህ ሰው ሳይቀር በሚገባ የሚረዳበት ደረጃ ላይ እኮ ነን ያለነው፡፡ ግዢዎች ሲፈጸሙ ወይም ጨረታ በሚወጣበት ጊዜ የሚደረገውን ለአብነት እንይ፡፡
እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡
የጨረታ ዶክመንት ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ሰው ከሳምንታት ወይም ወራት በፊት አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱ (ቴክኒካል ስፔስፊኬሽኑ) በአጫራቹ ድርጅት አማካይነት በተመረጡና በታመኑ ሰዎች እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ ይህ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ግዥ በሚፈጽሙ ተቋማት ውስጥ በግልጽ እንደሚደረግ ግልጽ ነው፡፡ ፀሐይ የሞቀውም ነው፡፡ ለጨረታ ወይም ለግዥው የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ለጨረታ የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ አስቀድሞ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከተሰጠ በኋላ፣ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖረው ተፈላጊው ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዲያቀርብ ተደርጎ ተመራጭ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ምንልክሳልሳዊበአንዳንድ ግዥዎች አሸናፊ እንዲሆን የሚፈለግ የተጫራች ድርጅት ስፔስፊኬሽን እንዳለ የጨረታ ዶክመንት ሆኖ እንደሚቀርብ በግልጽ በሚታወቅበት ደረጃ ላይ ነን፡፡
በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ያሉ ግዥዎችና ጨረታዎች ከፍተኛ ሙስና እየተፈጸመባቸው የሚካሄዱ መሆኑ ቢታይም፣ ሕጋዊነትን ተከትለው እንደተፈጸሙ ስለሚቀመጡ (በወረቀት፣ በአካሄድና በአሠራር) እጅግ የረቀቁና ሥር እየሰደዱ የመጡ ሙስናዎችን ለማየት ግን አዳጋች አይደለም፡፡ ምንልክሳልሳዊአንድ ድርጅት ከሁለት በላይ የተለያዩ ስም የያዙ የድርጅት ስሞችን ይዞ በመቅረብ አንዱ አሸናፊ ሌሎች አጃቢዎች ሁነው እንደሚቀርቡ በግልጽ ይታወቃል፡፡ የጨረታ ጊዜዎችን እጅግ በማሳጠር አሸናፊ እንዲሆን ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ግን አስቀድሞ መረጃውን በመንገርና ተዘጋጅቶ እንዲቆይ በሚደረግ፣ የሌሎች ተጫራቾችን ጊዜ በማሳጠርና የዝግጅት ጊዜ እንዲያጡ በማድረግ የሚፈጸሙ ግዥዎችና ጨረታዎች ናቸው እየተካሄዱ ያሉት፡፡ምንልክሳልሳዊ
አንዳንድ ቦታ ጨረታ በሚዘጋጅበት ወይም በሚካሄድበት ጊዜ ተጫራቾቹ በአጫራቹ ድርጅት ግለሰቦች ስም የሚጠሩበት አጋጣሚ እንዳለም በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡ ማን አሸነፈ ሲባል የአጫራቹ ግለሰብ ስም እየተጠራ እገሌ አሸነፈ ተብሎ በሚነገርበት ደረጃ ላይ እንዳለን ለማንም ባልተሰወረበት ሁኔታ ላይ ነን፡፡ እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጨረታ በኋላ አሸናፊው ድርጅት በፕሮጀክቶች ክትትልና በዕቃ ርክክብ ከሚፈለገው ደረጃና ብቃት በታች አፈጻጸም ያሳያል፡፡ ከሚፈለገው ዕቃ ውጭ አቅርቦቶች ሲካሄዱ ዝም እየተባለ የሚፈጸሙ የፕሮጀክቶች ግዥዎች ከበስተጀርባቸው ትልቅ ሙስና እንደሚካሄድባቸው ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ምንልክሳልሳዊ
ለዚህ ትልቅ ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ በመንገድ ግንባታ፣ በትላልቅ ግድቦች ግንባታ፣ በውኃ ሥራዎች፣ በቴሌኮም ፕሮጀክቶች፣ በቤቶች ግንባታና ማጠናቀቂያ ላይ ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ በእጅጉ ይታወቃል፡፡ እንደ ምሳሌ ለማቅረብ ከኤርፖርት እስከ መስቀል አደባባይ እየተሠራ ያለው መንገድ ቀደም ብሎ ለሌላ ድርጅት ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኋላ ግን ተቀይሮ ለሲአርቢሲ ተሰጥቷል፡፡ የመጀመርያው ተጫራችና አሸናፊ ድርጅት አቅም ሲመዘን እንኳን በዚህ ትልቅና አስቸጋሪ መንገድ እንዲሳተፍ በገጠር መንገድም ለማሳተፍ የሚያስችል ብቃት እንደሌለው ግልጽ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ድርጅት አሸናፊ እንዲሆን ተመርጦ የነበረው አላስፈላጊ ግንኙነት በመመሥረቱ ነበር፡፡ የዚህ ዓይነት መሰል ገጠመኞች ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ባንኮች ብድርና የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት በግልጽ ኮሚሽን በሚቀበሉበት አገር ላይ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ አይደለም እንዴት ይባላል?
የፀረ ሙስና ኮሚሽን አንዳንድ ሰዎች አሳሳቢ የሚባል የሙስና መረጃ ሲያገኙ፣ በተለይ ከሀብታም ነጋዴዎች ጋር የሚያያዝ ከሆነ ቀድመው ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ከሚጥሩ ይልቅ ለግልግል በሚሯሯጡበት አገር ላይ እያለን፣ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ነው እንዴት ይባላል? በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሮች ድረስ በሀብታም ተፅዕኖ ሥር በወደቁበት፣ ጉቦ በመቀበል የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡበት፣ ሀቅን በገንዘብ በሚለውጡበት፣ በጠራራ ፀሐይ ብሉ ሌብልና ቪኤስኦፒ በካርቶን በሚጫንበት፣ የሰው ሕይወት በገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት፣ ዓይን ያወጡ ሙሰኞች በሰፊው ሕዝብ ፊት ደረታቸውን ነፍተው ጉራቸውን በሚነፉበትና ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ወቅት መሆናችን እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም እንዴት ይባላል?
ትናንትና ለሀቅ፣ ለዲሞክራሲና ለአገራቸው ብልጽግና ሲሉ የወጣትነት ዕድሜያቸውን በረሃ የወጡ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ቀብረው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ጀግኖች በሙስና ተነክረው ሀብታም ሥር በተንበረከኩበት ወቅት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ቅጥረኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሠራርና መመርያዎችን ጥሰው በኔትወርክ በተሳሰሩበት ወቅት፣ እርስ በራሳቸው እሳትና ጭድ ሁነው በማይተማመኑበት ወቅት፣ ለሕዝብ ህልውና ዋስትና በታጣበት ወቅት፣ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሳስብ አይገባም ተብሎ እንዴት ይነገራል?
ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ፣ ከአሳሳቢነቱ በላይም ጊዜ የማይሰጠውና ወረርሽኝ በሆነበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይም ሙሰኞች የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ወሬዎች በሚናፈሱበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንዱ ቅንጣት ጥፋት የሌለው ይመስል ከራባቱን አስሮ ‹‹ሙስናን እንዋጋ›› የሚለው ከበስተጀርባው ትልቅ ጥፋት ተሸክሞ ነው፡፡
እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ምንልክሳልሳዊ

ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል:
(አዲስ አድማስ መጋቢት 20 2006 ዓ.ም)
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡
የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኗን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በዚህም መሠረት ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ አሠራሮችን ለማረምና ለማስተካከል ጥረት እያደረገች ቢኾንም ባለሥልጣናቱ ከማን ጋር መሥራት እንዳለባቸው በትክክል አለመለየታቸውንና ግንኙነቱም ሙሰኞችን በአይዟችኹ ባይነት የሚያበረታታ እንደኾነ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡
ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን በዚህ መልኩ ለባለሥልጣናቱ ለማቅረብ ያስገደዳቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎቹ፣ ‹‹ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ ያነሣሣል፤ በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ባሉት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁበት መግለጫቸው ነው፡፡
የመንግሥት የተለመደ እገዛ እንዳላቸው በአጽንዖት የጠቀሱት አስተዳዳሪዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፣ መንግሥት በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ገለልተኛ ኦዲተር መድቦ በማኅበሩ ላይ የሀብትና ንብረት ቁጥጥር የማካሔድ ድጋፉ እንዳይለያቸው ያስተላለፉት ጥሪ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና የቀረበ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ መንገድ ማከናወን በሚገባት ተግባር ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የሚጋብዝና ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥ እንደኾነ ተመልክቷል፡፡
በመንበረ ፓትርያርኩ ከተገኙት የመንግሥት ሓላፊዎች ጋራ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንደተካሔደ በተገለጸው የኹለትዮሽ ውይይት፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በመቃወም ሰበብ የወጣው የአስተዳዳሪዎቹ መግለጫ ዋነኛ ዓላማ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ወስና የምታካሒደውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ሒደት መጋፋት ነው ተብሏል፡፡ መላውን የሀገረ ስብከቱን አድባራት አገልጋዮች ለመወከል የማይበቁ ጥቂት ግለሰቦችን በመያዝ ይደረጋል የተባለው ይኸው እንቅስቃሴም ‹‹የት እንደሚያደርስ እናየዋለን›› የሚሉ ንግግሮች ጭምር ከሊቃነ ጳጳሳቱ የተሰሙበት እንደነበር ምንጮቹ አስታውቀዋል፤ ጉዳዩም በመጪው ግንቦት በሚካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓቢይ መነጋገርያ መኾኑ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡
ከሀገረ ስብከቱ አድባራት የተውጣጡ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎች ያደረጉት ስብሰባ፣ አስተባባሪዎቹ ከፓትርያርኩ ተሰጥቶናል ከሚሉት ፈቃድ በቀር በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዘንድ በይፋ የታወቀና የተፈቀደ እንዳልነበረ ምንጮቹ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን በሁከትና ሽብር ለሚከሱ በቂ ሕጋዊነትና ውክልና የላቸውም ለተባሉ አካላት ፓትርያርኩ የሰጡትን የስብሰባ ፈቃድ፣ በቅርቡ ማኀበሩ አገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ እንዳያካሒድ ከተጣለበት እገዳ ጋር ያነፃፀሩ ታዛቢዎች፣ ሁኔታው የፓትርያርኩን ርምጃዎች መርሕ አልባነት የሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር መተዳደርያ ደንብ ያለውና ግልጽ ተልእኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር፣ህልውናና አገልግሎት በግልጽ አስተዳደራዊ ጫና ውስጥ መግባቱን እንደሚያመለክት ታዛቢዎቹ ያምናሉ፡፡
ከመዋቅር፣ ከሀብትና ንብረት ቁጥጥር ጋራ በተያያዘ በማኅበሩ ላይ የሚቀርቡት ውንጀላዎች፣ በፀረ አክራሪነት ስም የሚናፈስበትን ፕሮፓጋንዳ በማጠናከር ፖሊቲካዊ ርምጃ እንዲወሰድበት ፍላጎት ያላቸውን አካላት ምኞት በጉልሕ እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡ ማኅበሩ ሃይማኖቱን የሚጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያኑን የሚከባከብና ሀገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ያለውን ዓላማ የሚረዱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናንና የመንግሥት አካላትም የተቃዋሚዎቹን አቋምና መግለጫ በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ትውፊት ውጭ ነው በተባለ የሌላ እምነት አስተምህሮ የተነሳ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መካከልና በደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተገለጸ ነው፡፡
ከኮሌጁ ውጭ ከሚገኙና በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋር የዓላማና የጥቅም ግንኙነት መሥርተዋል በተባሉ ጥቂት ደቀ መዛሙርት አማካይነት በኮሌጁ ውስጥ ከመንጸባረቅ አልፎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው የተባለው ይኸው አስተምህሮ፣ አስተዳደራዊ መፍትሔ እንዲበጅለት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት ጥር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ለኮሌጁ አስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ እስከ አሁን ምላሽ አለማግኘቱ ውጥረቱን የበለጠ እንዳባባሰው ለአዲስ አድማስ የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡
የአስተምህሮው ውዝግብ አፋጣኝ መፍትሔ አለማግኘቱ ከደቀ መዛሙርቱ አልፎ የምክር ቤት አባላትን ለሁለት እንደከፈለ ተገልጧል፡፡ ኮሌጁንና ደቀ መዛሙርቱን በቅንነትና በትጋት ለማገልገል በደቀ መዛሙርቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠውና ከፍተኛ ሓላፊነት የተጣለበት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት፣ ‹‹ከልማቱ ጥፋቱ አመዝኗል›› ያሉት ጸሐፊውና አንድ የአመራር አባሉም ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡
‹‹ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ትውፊት ውጭ የኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲዘራ ድምፀ ተዓቅቦ ከማድረግ ባሻገር ችግር አለባቸው ከሚባሉት ደቀ መዛሙርት ጎን ተሰልፈው ኮሌጁንም ኾነ ሓላፊነት የሰጠንን ደቀ መዝሙር በቅንነት እንዳናገለግል የአንዳንድ መማክርት አባላት ተግባር አውኮናል›› ያሉት ሁለቱ አባላት፤ በዚህ ሳምንት ለኮሌጁ ዋና ዲን ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ የችግሩ ተባባሪ በመኾኑ ከሓላፊነቱ ታግዶ ጉዳዩ እንዲጣራና እምነታቸውና ሥነ ምግባራቸው በተመሰከረላቸው ደቀ መዛሙርት እንዲተካ ጠይቀዋል፡፡
‹‹የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ፣ በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት የሚያራምዱ›› ያሏቸውን ወገኖች አጥብቀው እንደሚቃወሙ የገለጹ የደቀ መዛሙርት ተወካዮች በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ለመጠበቅና ለማስፋፋት የቆመ በመኾኑ አስተዳደሩ፣ በቃል፣ በድምፅና በጽሑፍ የሚቀርቡለትን ማስረጃዎች መርምሮ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡
ባልደረባችን ሰሎሞን ክፍሌ ባለቤቱን አጥቷል፡፡
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የአፍሪቃ ህብረት እና የአውሮጳ ህብረትየፊታችን ረቡዕ እና ሀሙስ፣ እአአ ሚያዝያ ሁለት እና ሦስት በብራስልስ ጉባዔ ያካሂዳሉ።
የአሜሪካን ባለስልጣናት ኢህአዴግን በተመለከተ የሚጠቀሙት ቃልና የድምጻቸው ቃና ተቀይሯል::
ጎልጉል ፦ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።
ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
አቶ መለስ በጓዶቻቸው ቋንቋ “ተሰው” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ተቸግሮ ነበር። ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ፖሊስና ዋንኛ የአገሪቱን ተቋማት ጠቅልሎ የያዘው ህወሃት በቀጥታ አሜሪካ ባደረገችው ጫና ሳይወድ በግዱ አቶ ሃይለማርያምን በጠ/ሚኒስትርነት ለመሰየም ተገደደ። የስልጣን ክፍተቱን በተመለከተ አቻ ድርጅቶችና ህወሃት ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበር “ምደባ” በሚል ኢትዮጵያ በደቦ የሚመሯት አራት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሰየሙላት።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት እንዳሉት አሜሪካ ስጋት የገባት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር። መለስ እንዳለፉ ልዩ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሁኔታውን በመገምገም ስራ የጀመረችው አሜሪካ አሁን አሁን በህወሃት ስትራቴጂ የተሰራው ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ዋንኛ የችግር ምንጭ ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየመከሩበትና የመፍትሔ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው።
“We cannot afford to lose Ethiopia” አሜሪካ ኢትዮጵያን ልታጣት አይገባም በማለት ለጎልጉል የዋሽንግቶን ዘጋቢ የተናገሩት የዲፕሎማት ምንጭ “የአሜሪካን ባለስልጣናት ኢህአዴግን በተመለከተ የሚጠቀሙት ቃልና የድምጻቸው ቃና ተቀይሯል” ሲሉ የጉዳዩን ክብደት አመላክተዋል።
በዋሽንግቶን የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ኢህአዴግን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል። አዲስ አበባም ተወካይ በመላክ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በግል እየተነጋገሩ ነው። በያዝነው ሳምንትም ለተመሳሳይ ስራ አዲስ አበባ የተጓዙ አሉ። እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ የህወሃት ሰዎች ውስጣዊ ችግር እንዳለ አይቀበሉም። በግል ያነጋገሯቸው የሌሎች ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ግን ኢህአዴግ ውስጡ አለመረጋጋትና ስጋት የተሞላው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ አንድ ችግር ቢፈጠር ለማረጋጋት አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ ህዝቡ በተለይ በህወሃቶች ላይ የሚያሳየው ጥላቻ እየተካረረ መምጣቱ፣ በአገሪቱ የሚፈጸመው ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት፣ አፈናውና ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ ተግባራት ተዳምረው ህዝቡን ክፉኛ ማስቀየሙ ያልታሰበ ችግር ሊቀሰቅስ እንደሚችል አሜሪካ መገንዘቧን ያወሱት ዲፕሎማት፣ “ህወሀቶች የቀጠናው የሰላም ምንጮች ስለመሆናቸው ለራሳቸው ምስክርነት ለመስጠት ቢሞክሩም በተግባር የሚታየው ግልባጩ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ላይ የተተከለው የጎሳ አገዛዝ እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ዲፕሎማት “በጎሳ አስተሳሰብ የተዋቀረው ኢህአዴግ ችግሩ ከገነፈለ ሊቆጣጠረው የሚችል ባለስልጣንና መሪ የለውም። አስተዳዳራዊ ማዕከላዊነት አይታይበትም። በግል የሚወስን ባለስልጣንና ርምጃ የሚወስድ አካል የለውም” ሲሉ የስጋቱን ግዝፈት ያሳያሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ችግሩ ቢከሰት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰቡ አዳጋች እንደማይሆን ይጠቁማሉ። አያይዘውም “አሜሪካ ቸል ብላ ስትመለከተው የነበረውን ጉዳይ አጽንኦት ብትሰጠው አይገርምም” ብለዋል። አሜሪካ ይህንን የምታደርገው ለራሷ ስትል እንደሆነ ያልሸሸጉት ዲፕሎማት አንድ ጥያቄም ጠይቀዋል። “እናንተስ ለራሳችሁ ስትሉ ምን እየሰራችሁ ነው?” ከረጅም ፈገግታ ጋር።
አልቃይዳን ከምንጩ ማድረቅ በሚለው የመለስ ስትራቴጂ ለኢህአዴግ ግብር ስታስገባ የነበረችው አሜሪካ ግብሯን ስትገብር የኖረችው በፔንታጎን ወታደራዊ ውሳኔ መሰረት ነበር። ኢህአዴግም ግብሩ እንዳይቆምበት በአዲስ አበባ ታክሲ ላይና ህዝብ በሚያዘወትርባቸው ቦታዎች ፈንጂ በማፈንዳት ሲጫወተው የነበረውን ድራማ ዊኪሊክስ (ሹልክ ዓምድ) አምባሳደር ያማማቶን ጠቅሶ ማጋለጡ አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ይመስላል ኢህአዴግ የቀድሞውን ጨዋታ የመጫወት እድሉ እንዳከተመ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ባደባባይ የመለስን ስብዕና በመዝለፍ ባልተለመደ መልኩ ተናግረው ነበር።
ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ዲፕሎማት “እናንተስ” በሚል ለሰነዘሩት ጥያቄ ማብራሪያ ተጠይቀው “እኔ ኢትዮጵያዊ ብሆን አገሬን አስቀድማለሁ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። አሜሪካ አማራጭ ማጣቷንም እንደ አንድ ችግር አንስተዋል።
በዲፕሎማቱ አስተያየት ላይ ገለልተኛ ወገኖችን አነጋግረናል። ያሰባሰባንቸው አስተያየቶች “አሜሪካ እዚህ ደረጃ ከደረሰች፣ ኢህአዴግም በዚህ ደረጃ ከተመደበ ተቃዋሚዎች የግል ጉዳያቸውንና ፕሮግራማቸውን ለህዝብ ውሳኔ በመተው ለመጪው ትውልድና ለአገር ሲሉ ከመቧደን በሽታ ሊፈወሱ ይገባል” የሚል ይገኝበታል።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀናጅቶ መበተን፣ ተደራጅቶ መፍረክረክ፣ ተደላድለው መስለል በተለያዩ ወቅቶች ህዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገዋል። የሚፎካከሩትን ፓርቲ ትተው እርስ በርሳቸው ለተራ ጉዳይ ሲሻኮቱ ዓመታት አሳልፈዋል። በዚህም የተነሳ “አማራጭ የለም” በሚል ኢህአዴግን ማንገስ ግድ እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎች “የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህንን አስተሳሰብ ሰብረው አገር መምራት እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ ህብረት መፍጠር ይገባቸዋል። ይህም ካልሆነ የርስ በርስ ውዝግባቸውን ማቆምና የራሳቸውን የቤት ስራ መስራት ላይ ማተኮር ግዳጃቸው ይሆናል” ብለዋል።
ምሁራን ከተደበቁበት ሊወጡ እንደሚገቡም ያሳሰቡ አሉ። አገር የመምራት፣ በህዝብ የመታመን፣ የህዝብን ይሁንታ ማግኘት እንችላለን የሚሉ ከፊት ለፊት፣ አሁን ከፊት ያለውን ችግር በመጥረግ የወደፊቷን ኢትዮጵያ በመገንባትና መጪውን ትውልድ በማዳኑ ስራ አጋዥ ሃይል ለመሆን መወሰን እንደሚገባቸው በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል። ከሁሉም በላይ ግን “አሁን ካለው ህዝብን ካገለለ ዘመናዊ የመሳፍንት ስርዓት ኢትዮጵያንና ህዝቧን ማሻገር የሚችል ሞገሰ ሙሉ፣ ቅን፣ ከጥላቻ የጸዳ፣ ከሥልጣን ይልቅ የወደፊቷን ኢትዮጵያ አሻግሮ መመልከት የሚችል መሪ ወደ ፊት ወጥቶ በግልጽ ለህዝብ የሚተዋወቅበትን መንገድ የማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ድረገጾች፣ ሬዲዮኖች አገር ወዳድ የመገናኛ አውታሮች አጀንዳ አድርገው ሊወያዩበት ይገባል” የሚለው አስተያየት ሚዛኑን የደፋ ሆኗል።
“…የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም::” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ምላሹን አልቀበልም በማለቱም በፖስታ ቤት ተልኮለታል ህገ መንግስቱ እውቅና የቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ሳይሸራረፍ መተግበሩን እንዲከታተል በአዋጅ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ዓ.ም መነሻውን ፓርቲው ከሚገኝበት ቀበና በማድረግ በአራት ኪሎ አደባባይ በመዞር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በአዋጅ የተሰጠውን ጊዜ ገደብ አሳልፎ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ኦፊሰሩ በደብዳቤያቸው ‹‹በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና ፣የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡››ብሏል፡፡ የአገሪቱ ፓርላማ ‹‹ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ባወጣው አዋጅ ‹‹የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ግዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም››(አዋጅ ቁጥር 3/1983 )በማለት ያወጀውን በአዋጁ ስር የተቋቋመው ጽ/ቤት በማን አለብኝነት በመሻር የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም ብሏል፡፡
አንድነት አዋጁን የጣሰውን ደብዳቤ እንደማይቀበል በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ በመጻፍ በአካል ቢሯቸው በመገኘት ለመስጠት ቢሞክርም በአስገራሚ ሁኔታ ኦፊሰሩ ደብዳቤውን አልቀበልም ብለዋል፡፡
የኦፊሰሩ ድርጊት ህገ ወጥ መሆኑን የተገነዘበው ፓርቲያችን ደብዳቤውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትቶ ከመውጣቱም በላይ በሪኮማንዴ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡ ኦፊሰሩ እየሰሩ የሚገኙት ነገር ህገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘቡም ለፌደራል ፖሊስ፣ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በግልባጭ ደብዳቤው እንዲደርሳቸው መደረጉን የአንድነት የአዲስ አበባ ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው ተናግረዋል፡፡ በህገ ወጥ ደብዳቤ የሚሰረዝ ሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ባለመኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ እንደሚደረግ አቶ ነብዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ Finotenetsanet

ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ዘረኝነት ባታራምዱ የተሻለ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ / ሕወሓት/ ነው፡፤ ዋናው ትግላችንም ሕወሓትን ማስወገድ ነው። እናንተ የትግራይ ህዝብ ላይ አተኩራችሁ አቃቂር ስታወጡ ሕወሓት እናንተን እንደማስረጃ እየተቀሰ በትግራይ ውስጥ ጥላቻን እየዘራ ነው። ስለዚህ ዘር እየጠሩ ዘመቻ አያዛልቅም ለህዝቦች አንድነት እና ፍቅር ተባብረን ብንነሳ መልካም ነው።
በቅኝ አገዛዝ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በአምባገነን ስር አት ውስጥም ባንዳዎች ይፈለፈላሉ ። ይህ የታወቀ ነገር ንው። ውዴታዊ ባንዳነት እንዳለ ሁሉ ግዴታዊ ባንዳነት ከዛ መላመድም እንዳለ ታሪክ ስናገላብጥ አንብበናል። ቢሆንም መልካም የህዝቦችን ታሪክ እየያዝን ለክፉው ታሪክ መቃብር እየማስን እየቀበርን በትግል ወደፊት በመገስገስ በኢትዮጵያ ላይ የተጫነውን የሕወሓት አምባገነናዊ ጁንታ መንግለን መጣል አለብን ።
እደግመዋለሁ !!! ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ድርጅት ይወልዳል ያድጋል ይሞታል፣ህዝብ ግን ለዘላልም ይኖራል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!!ምንሊክ ሳልሳዊ
ያኔ-ከ21ዱ የወታደራዊ ሁንታዉ አባላት ሁሉ ወጣት ነበሩ።ያን ሚስጥር-በመናገራቸዉ የካይሮ ሠልፈኞችን በቁጣ፤ የመብት በተለይም የሴቶች መብት ተሟጋቾችን በዉግዘት ከማንጫጫቱ ባለፍ፤ ድምፀ ለሥላሳዉ ወጣት ጄኔራል የሚፈልጉትን ለማደረግ-የፖለቲካዉን ትኩሳት የለኩበት መግለጫ መሆኑን ያሰበ-ያስተዋል አልነበረም።
በደሴ ከተማ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ስፍራው የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ ድብደባና ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ በደሴ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕራት በልተው ሲወጡ ታርጋ የሌለውና መስታወቱ ጥቁር በሆነ ኮብራ መኪና አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ከውጪ ሁለት ሰዎች […]
በርካታ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የርቀት ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ2005 ዓም ትምህርታቸውን ቢጨርሱም፣ ጊዚያዊ ዲግሪያቸውን ፣ ማለትም የዲግሪያቸውን ቅጂ ባለማግኘታቸው በስራ ፍለጋ ጥረታቸው ላይ እክል እንደደቀነባቸው በምሬት ገልጸዋል።
የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ሰሞኑን ደቡብ ሱዳንን እና ማሊን ጎብኝተውዋል። ሚንስትሩ ወደ ሁለቱ ሀገራት የተጓዙት በቦታው በመገኘት በዚያ ስላለው የመሠረተ ልማት ግንባታ፣
የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሰልፍ እንደሚያደርግ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 15 ቀን ያሳዉቃል። «የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ሥነ-ሥርዓት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርሲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀዉን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደሩ ከ48 ሰዓታት በኋላ መጋቢት 17 ቀን ምላሽ ይሰጣል። […]
ትናንት እሁድ መጋቢት 21, 2006 ዓም ዓረና ከእንደርታ ህዝብ ጋር ለመወያየት በኲሓ ከተማ ሐየሎም አዳራሽ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል። ለስብሰባው በስፒከር ለመቀስቀስ ሞክረን እንደተከለከልን፣ የአመራር አባሎቻችንም መታሰራቸው እንደዉጤቱም የቅስቀሳ ሂደቱ መተጓጎሉ ጠቅሼ ነበር። ሁኖም ግን የዓረና አማራጭ ሐሳብ የያዘ በራሪ ወረቀት ለኗሪዎች በማደል የተወሰነ ቅስቀሳ አድርገናል። ከሌሎች አከባቢዎች ለየት ባለ መልኩ በእንደርታ ወረዳ በስፒከር እንዳንቀሰቅስ የተፈለገበት […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ