ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንዋር መስጊድ እጅግ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በተካሄደው ተቃውሞ ፣ መንግስት “መጅሊሱን ለህዘበ ሙስሊሙ እንዲያስረክብ እንዲሁም የታሰሩትን መሪዎች እንዲፈታ” ጠይቀዋል። “ትግሉ የጽኑዎች ነው፣ ፍትህ ይስፈን፣ የእምነት ቤቶቻችን ይከበሩ፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ የትግላችንን መነሻ እናሳካው የማነፍርበት የትግል መዳረሻችን ነው፣ አፈና ግፍና ማስገደድ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን በረመዳን ጾም …

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ የሌሎች አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው፣ በቴፒ ከተማ ኤግዢቢሽን አዳራሽ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎች በምግብ እና በውሃ ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው ታውቋል። እስካሁን ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ግጭቱ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ተነግሯል። ልዩ ፖሊስና የወረዳው ፖሊስ፣ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁት የሸኮና መዠንገር ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ታውቋል። ሸኮና መዠንገር …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኢንተርኔት አማካይነት በቀላሉ የሚገኙ መረጃ እና አገልግሎቶችን ተጠቅሞ እውቀትን እንዴት ማዳበር ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎች ከሰኞ እስከ እሮብ በቆየው እና ዶይቸ ቬለ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው።

የእስራኤል ፖሊስ ኢየሩሳሉም ዉስጥ ከፍልስጤም የተቃዉሞ ሰልፈኞች ጋ መጋጨቱ ተሰማ። ፍልስጤማዉያኑ በፅንፈኛ እስራኤላዉያን ሳይገደል እንዳልቀረ በሚገመተዉ ፍልስጤማዊ ታዳጊ ወጣት ቀብር የተሰባሰቡ እንደሆኑ አሶሲየትድ ፕረስ ከስፍራዉ ዘግቧል።

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ ቻይናን ይጎበኛሉ። ሜርክል የጀርመን ከፍተኛ የንግድና ባንክ ባለስልጣናትን አስከትለዉ ለአራት ቀናት በቻይና በሚያደርጉት ጉብኝት ከፕሬዝደንት ሺ ቺ ፒንግና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪጂንግ ጋ ይነጋገራሉ።

ዶይቸ ቬለ በዚህ ሳምንት ያስተናገደው ሰባተኛው የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መድረክ ትናንት ተጠናቀቀ። በጉባዔው ከ100 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ወደ 2,000 የሚጠጉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚው

“የተፈጠረው ሁናቴ እጅግ ቢያሳዝንም ይህንን አለማቀፍ ህግ የሚጥስ አገዛዝ ለመጣል ሁላችንም ቆርጠን እንድንነሳ ያደርጋል” አቶ ነአምን ዘለቀ

 

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ ላይ የነበሩትና የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት የወረዱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዛው የመን ታግተው ከቆዩ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ ስጋቱ አይሏል

ኤርትራዊያኖች የየመን አየር መንገድን እንዳይጠቀሙ ማስተባበር ያስፈልጋል አቶ ዳንኤል ጥላሁን (የህግ ባለሙያ)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለጉዞ መሸጋገሪያ የመን ከገቡ ጀምሮ በአገሪቱ ደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አስመልክቶ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ሲሆን በተለይ የየመን አየር መንገድን በመቃወም ኤርትራዊያን የጉዞ ማእቀብ እንዲያደርጉ አንድ ተቀማጭነቱን ካናዳ ያደረገ የህግ ባለሙያ ጥሪ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም” በሚል ርእስ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋዩን እንዲለቅ” አስጠንቅቋል።  ይህ ባይሆን ግን ይላል የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ  የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላ አገሪቱ የስልክ መልእክቶችን በመደወል ለአቶ አንዳርጋቸው ጀግንነት ድጋፋቸውን የሚገልጹ፣ በእርሱ መታሰር የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ስሜት የሚገልጹና ስለቀጣዩ ህዝባዊ እርምጃ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካታ የስልክ መልእክቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። “እድሜየ 50ዎቹ አጋማሽ ነው፣ ከስራ ውየ ስገባ የሰማሁት ዜና አስደንግጦኛል፣ ስሜቴን መቆጣጠርም አልቻልኩም፣ ቤተሰቤን ልጆቼን ትቼ ትግሉን ለመቀላቀል ወስኛለሁ” በማለት …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአፓ የየመን የጸጥታ ሃይሎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የወሰዱትን እርምጃ በጽኑ አውግዞ፣ የአገሪቱ መንግስት በአስቸኳይ እንዲለቀው ጠይቋል። አንዳርጋቸው በአምባገነኖች ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሶ ሞት የተፈረደበት በመሆኑ፣ ተላልፎ ቢሰጥ ለከፋ ስቃይና ሞት ሊዳረግ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር አደገኛ የሆነ አሰራር የሚፈጥር በመሆኑ ድርጊቱ በጽኑ ሊኮነን ይገባዋል ሲል ኢህአፓ …

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው የሽብር ድርጅቶች ጥቃት ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ለመሆናቸው አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል። ይህን ተከትሎም በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎችም አገራት አየር መንገዶች ላይ የሚታየው ጥበቃ ተጠናክሯል”” ኡጋንዳም በአየር መንገዷ ላይ ሽብር ሊፈጸም ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገች ነው።

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ […]

ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው) (ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን መቀጠላቸዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ «ዩ ኤን ኤች ሲአር»

«ሃሳብ አልጠል ሲል፤ በልብ የያዙት፤ በጭንቅላት የሚጉላሉት፤ በቀለም ቡሩሽ፤ በስዕል መልክ አልወጣ ሲል፤ ቃላት ቋጥሮ ግጥምን የመደርደር ባህላችን የቆየና የሚኖር ነዉ። የሥነ-ጥበብ ቤተሰቡ ሥነ-ግጥም በከፍተኛ ደስታ እና ኃዘን እንዲሁም ፍቅር ግዜ ሃሳባችንን በቃላት አምቀን የምንተነፍስበት ዘዴ ነዉ» ይሉናል፤ ሰዓሊና ገጣሚ እሸቱ ጥሩነህ

የሰውነት አካላትን እያደማ ለሞት የሚዳርገው የኤቦላ ተኀዋሲ (ቫይረስ) ሥርጭት በምዕራብ አፍሪቃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በጊኒ በላይቤሪያ እና በሴራልዮን 467 ሰዎች በኤቦላ ተይዘው መሞታቸውን የዓለም የጤና ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ «ዳብል ዩ ኤች ኦ» አስታውቋል ።

ኤርትራ ዉስጥ በእስር ላይ የሚገኘዉን የጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ አስመልክቶ ከዚህ በፊት በአፍሪቃ የሰብዓዊ ጉዳይ ኮሚሽን ጥያቄያቸዉ እንዲታይላቸዉ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሶስት የሕግ ባለሙያዎች በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ ክስ አቀረቡ።

የአፍሪቃ መሪዎች ባለፈዉ ሳምንት ባካሄዱት ጉባኤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እያለ ክስ እንዳይመሠረትበት መስማማታቸዉ ትችት አስከትሏል። የአፍሪቃ የፍትህና የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የተሰኘዉ መድረክ ስልጣን ላይ የሚገኙ መሪዎችና ባለስልጣናትን መክሰስ እንዳይችል የታገደ ነዉ።

ፕሮ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን  ማገቱን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። አላማጣ አካባቢ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ  ” የየመን መንግስት ያገተው አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በዚህ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ አንድ ነገር ቢደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ …

ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ታፍኖ የተወሰደ የፍልስጤም  ወጣት መገደሉን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። የ17 አመቱ ወጣት ሙሃመድ አቡ ካድር በመኪና ታፍኖ ሲወሰድ የአይን ምስክሮች ማየታቸውን ተናግረዋል።  ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ የእስራኤሉ መሪ ቤንጃሚን ናታንያሁ  ግድያውን አውግዘው፣ የእየሩሳሌም ከንቲባ የህዝቡን ቁጣ እንዲያበርዱ አሳስበዋል። የፍልስጤም መሪዎች በበኩላቸው እስራኤል 3 ወጣቶች …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በያመቱ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሞቃት ወራት ፣ በሳይንስ የኖቤል ሽልማት ያገኙ ጠበብት ከታዳጊ ሳይንቲስቶች ጋር ተገናኝተው ሐሳብ የሚለዋወጡበት ጉባዔ ዘንድሮም ፣ ባለፈው እሁድ በደቡባዊቷ የቦደን ሴ (ቦደን ባህር ) ጠረፍ ከተማ ተጀምሮ እስከፊታችን

ከዓለማችን 162 ሃገራት በሰላም ረገድ ኢትዮጵያ 139 ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አንድ መዘርዝር አመለከተ። ጎረቤት ኬንያ ደግሞ 132ኛ ናት። ይኸዉ መዘርዝር ከሽብር ስጋት አኳያ ኢራቅን በአንደኛ ደረጃ ሲያሰፍር፣ አይስላንድ በዓለም ሰላም የሰፈነባት ሀገር ብሏታል። ኢትዮጵያ ከ157 ሃገራት 37ኛ ናት።

ግንቦት ሰባት እንደሚለዉ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ የመን አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አስከባሪዎች ከተያዙ በኋላ ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ አይታወቅም

የዩክሬይን ጦር በምሥራቃዊ የሀገራቸው ከፊል በሚንቀሳቀሱት መፍቀሬ ሩስያ ሚሊሺዎች አንፃር የጥቃት ዘመቻቸውን ማጠናክራቸውን አስታወቁ። የዜና ምንጮች እንዳመለከቱት፣ የዩክሬይን ፕሬዚደንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ

ሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ?ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡

እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን ዕቃ ይዞ ላጥ አለ፡፡ መንገድ ላይ ያዩት ሰዎች የሚያውቁትን ዕቃ አንድ ሰው ይዞ ሲሸመጥጥ በማየታቸው ይጠራጠሩና ያስቆሙታል፡፡ ፖሊስም በነገሩ ይገባበታል፡፡ ሰውም ከዚህም ከዚያም ይወርድበታል፡፡

ግርግሩ በዚህ መልክ እየቀጠለ ዕቃቸው የተሰረቀባቸው ሰዎች ኡኡ እያሉ ይደርሳሉ፡፡ ሲደርሱም የቤት ዕቃቸው በአንድ በማያውቁት ሰው ትከሻ ላይ ያገኛሉ፡፡ ግርግሩን ሰንጥቀው ይገቡና ‹‹ሞላጫ ሌባ›› እያሉ ሌባውን በጥፊ ሲመቱት ሌባው ተናድዶ ዕቃውን ያወርድና ጥፊውን በጥፊ ይመልሳል፡፡ ፖሊስ በድርጊቱ ተገርሞ ከዚያ ሁሉ ሰው ይልቅ ለባለቤቶቹ ጥፊ ለምን መልስ እንደሰጠ ሲጠይቀው ‹‹ቤታቸውን ከፍተው እየሄዱ ሰው ሌባ ያደርጋሉ›› አለ ይባላል፡፡

የሰሞኑ ሁኔታም ይህን ነገር እንድናየው የሚያደርግ ነው፡፡ ለመጭበርበርና ለመታለል የሚችል አሠራር፣ አካሄድና አፈጻጸም የዘረጋነው እኛው ነን፡፡ ነገሮችን በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመርኩዘን ከመወሰን ይልቅ በሚወራ ወሬ፣ በሚገነባ ገጽታና ከሚዲያ በምንሰማው ነገር ላይ ብቻ የመመራትን አሠራር ያሰፈንነው እኛው ነን፡፡ ዛሬ ቀን ጥሎት የተጋለጠው ሰው ላይ በወደቀ ዛፍ ላይ የሚበዛውን ምሣር ሁሉ እናዘንብበታለን እንጂ ሌሎች ወደፊት እንዳይከሰቱ የሚያደርግ አደረጃጀት፣ አሠራርና አስተሳሰብ ግን አልዘረጋንም፡፡  

እንዲያውም የዚህን ሰው በዚህ መልኩ መምጣት ለሀገራችን ተቋማትና ኃላፊዎች ‹በረከተ መርገም› የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ‹ዓመት ባል ካልመጣ ሁሉ ሴት፣ ክረምት ካልመጣ ሁሉ ቤት› የሚባል አባባል አለ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ባይኖሩ የኃላፊዎቻችንን፣የምሁሮቻችንንና የመሥሪያ ቤቶቻችንን የተዝረከረከ አሠራር እንድናይ ማን ያደርገን ነበር፡፡ እዚህ ሀገር ምን ዓይነት ሰዎች ምን ዓይነት ቦታ እንደሚይዙ አሳይቶናል፤ ሴትዮዋ ‹አፍ ያለው ያግባሽ ከብት ያለው› ስትባል ‹‹አፍ ያለው ያግባኝ፣ አፍ ያለው ከብቱን ያመጣዋልና›› ያለችው እውነቷን ነው እንድንል አስችሎናል፡፡ አፍ ካለ፣ መናገር ከተቻለ፣ መስጠት ከተቻለ፣ እዚህ ሀገር ውስጥ ዕድሉም መንገዱም ወለል ብሎ እንደሚከፈት አይተናል፡፡ ሚዲያዎቻችንም የማጣረት፣ የመመርመርና ከግራ ቀኝ የማየት ዐቅማቸው የት ድረስ እንደሆነ አሳይቶናል፡፡ ‹ማን ምን አለ› እንጂ ‹ያለው ልክ ነው ወይ?› ብሎ ለማረጋገጥ ጥቂት እርምጃዎች መሄድ የሚችሉ ሚዲያዎች እንደዋልያ ‹ብርቅዬ ድንቅየ›› መሆናቸውን ተምረንበታል፡፡

እንዲህ ያለ ሰውማ ይምጣ፡፡ እዚህ ሀገር ድፍረት እንጂ ዕውቀት፣ ትውውቅ እንጂ ዕውውቅ፣ ዘመድ እንጂ ችሎታ፣ ቅልጥፍና እንጂ ጉብዝና ዋጋ እንደሌላቸው እናይ ዘንድ፡፡

እኔን ምን አገባኝ የሚሉት አጉል ወግ

እርሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ

የሚል ግጥም ልጽፍ ተነሣሁኝና

ምን አገባኝ ብዬ ተውኩት እንደገና

ብሎ የጻፈውን ባለ ቅኔ እውነት እንድናየው አድርጎናልና እንዲህ ያለ ሰውማ ይኑር፡፡

ምሁሮቻችን ያላስተማሩት ተማሪ ከፊታቸው ቆሞ አስተምራችሁኛል ሲላቸው፣ ተማሪዎቹ ብቃት አንሷችሁ እኔን ማየት ሳትችሉ ቀርታችሁ ነው እንጂ አብሬያችሁ ተምሬ ነበር ሲላቸው፣ የዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደሮች ረስታችሁኝ ነው እንጂ ሸልማችሁኝ ነበር ሲላቸው፣ በቅቼ ተሠውሬ ነው እንጂ አብሬያችሁኮ ነው የምሠራው ሲላቸው፤ የቤተ መንግሥት ሰዎች በእሳት ሠረገላ ገብቼ አላያችሁኝም እንጂ ከአቶ መለስ ጋር አብሬ ነበርኩኮ ሲላቸው ዝም ያሉት ‹ዝምታ ወርቅ ነው›› ብለው አይደል፡፡ የዝምታችን ነገር የት ድረስ እንደሚደርስ፣ ስሕተትን የመቻል ዐቅማችን የት ድረስ እንደሆነ፣ የተበላሸን ነገር የመሸከም ችሎታችን ምን ያህል እንዳደገ፣ ውሸትን የመቀበል ብቃታችን ጨምሮ ጨምሮ እዚህ መድረሱን በሚገባ አሳይቶናል፡፡ ኑርልን ባክህ፡፡

ባለፈው ጊዜ በዓለም ዋንጫ ጉዟችን አንድ ተጨዋች ሁለት ቢጫ ካየ በኋላ እንደገና ተሰልፎ በመጨዋቱ ፊፋ ቀጣን፡፡ ይህ ቅጣት ብዙ ሰዎችን አሳዘነ፡፡ ያ ቅጣት ግን ብናውቅበት ኖሮ በረከተ መርገም ነበር፡፡ የፌዴሬሽናችንን አሠራር ቁልጭ አድርጎ በአደባባይ ያሳየን፡፡ እንኳንም ተጨዋቹ ተቀጣ፣ እንኳን ፌዴሬሽኑም ተዝረከረከ፡፡ ያንን ዝርክርክነት እንዴት አድርገን እናየው ነበር፡፡ ከዚያ በፊትምኮ ከዚያ የባሱ ዝርክርክ አሠራሮች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በድብብቁ አሠራራችን ምክንያት ‹ሽል ሆነው ከመግፋት ይልቅ ቂጣ ሆነው እየጠፉ› ሳናያቸው ኖርን፡፡ ያንን አጋጣሚ ማለፍ ግን አልተቻለም፡፡ ዓለም ያወቀው፣ ዓለም ሊያውቀውም ግድ የሚለው ጥፋት ነበረና፡፡

የሚገርመው ነገር እንዲያ ዓይነት አገርን አንገት ያስደፋን ጥፋት ሲሆን እንዳይፈጸም፣ ካልሆነም እንዲታረም የሚያደርግ አሠራር ባለመዘርጋታችንና አመለካከታችንንም ባለማስተካከላችን በሴቶች እግር ኳስ ላይ ተደገመና የፓስፖርት መጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባትን ተጨዋች ለማሰለፍ ሜዳ ውስጥ እስከማስገባት ደረስን፡፡ ይኼኛውን ዝርክርክነት ለማወቅ የቻልነው ለማወቅና ለመታወቅ የግድ የሚለው ዓለም አቀፋዊ አሠራር በመኖሩ የተነሣ ነው፡፡

ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው) ‹በረከተ መርገም› በሚለው ግጥሙ ላይ ‹ድኻው ምን አረገ ሊቆቹን ነው መርገም› ይላል፡፡ አሁን መረገም ያለበት ተቋማዊ አሠራራችን፣ አስተሳሰባችን፣ የመረጃ አያያዛችን፣ ነገሮችን በንሥር ዓይን ከማየት ይልቅ በተወራውና በተባለው ብቻ መመራታችን፣ የዘመድ አዝማድ አካሄዳችን፣ የተጠጋጋውን ሁሉ የሚያምነው አሠራራችን ነው፡፡ መረገም ያለበት ለመታለል፣ ለመሞኘት፣ ለመሸወድ፣ ለመጭበርበር እጅግ ቀላልና እጅግም ዝግጁ የሆነው ቢሮክራሲያችን ነው፡፡

ይህን መሰል ሰዎች መምጣታቸው በሀገራችን እጅግ ተወዳጁ ምግብ ‹ምላስና ሰንበር› መሆኑን እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከውን ተናገር – ትሰማለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከውን ነኝ በል – ትታመናለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ የፈለግከው ቦታ ደርሻለሁ በል – ትደነቃለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ እንደ ኢዲ አሚን ሁሉንም መዓርግ ለራስህ ስጥ – ትሞገሳለህ፤ ምላስና ሰንበር ካለህ ዐዋቄ ኩሉ ነኝ በል – ተከታይ ታገኛለህ፡፡ የዚህን መሰል ሰዎች መነሣት ይህንን አሳይቶናል፡፡ እንኳንም ተነሣችሁ፡፡

ደግሞስ እነርሱ ባይኖሩ ይህንን መሰሉን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የተወካዮች ምክር ቤት፣ ዋናው ኦዲተር፣ ያልደረሰባቸውን የተበላሹ አሠራሮች እንዴት እናያቸው ነበር? ኧረ እንኳን ኖራችሁ፤ ለኛ በረከተ መርገም ናችሁ፡፡ 

 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

    ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ትላንት ጥዋት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለተሰለፉ ከአንድ ሺሕ ለማያንሱ ካህናትና ምእመናን አስታውቀዋል፤ የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ የካህናቱንና ምእመናኑን ቀጣይ ርምጃ ይወስናል፡፡     ፓትርያርኩ በጥቂት አማሳኞች ምክር ላይ የተመሠረተ የሙስና ክሣቸውን በማስረጃ አስደግፈው እንዲገልጹላቸው የተማፀኗቸውን፤ ለአቤቱታ በሕዝብ ማመላሻ አውቶቡሶች፣ ታክሲዎችና የቤት …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባልና የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘርፍ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የየመን የጸጥታ ሃይሎች አቶ አንዳርጋቸውን በአስቸኳይ ይለቁት ዘንድ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ከመጻፍ ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበትን መንገድ እያመቻቹ ነው። ግንቦት7 ለየመን ፕሬዚዳንት ፊልድ ማርሻል አብዱ …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመንአቶአንዳርጋቸውጽጌንማገቷሌላአደገኛናበጣምአሳሳቢክስተትነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል። ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ …

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸው እንደታወቀ የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው በሃማስ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቁዋን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል። የአገሪቱ መሪ ጠ/ሚ ናትኒያሁ ” ወጣቶቹ በሰው እንስሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” ተገድለዋል ያሉ ሲሆን፣ በሃማስ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። ይህን ተከትሎም ማምሻውን እስራኤል በሃማስ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች