ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መድረክ ባወጣው መግለጫ  በሀገራችን የምርጫ ሂደት የነበሩ ጉድለቶችንና በተለይም በ2002 የሀገራችን የምርጫ ሂደት የወረደበትን አዘቅት በሚገባ በጥልቀት ገምግሞ እነዚህን ቀደም ባሉት ምርጫዎች የነበሩ ጉድለቶችን ማረምና ማሰተካከል ለ2007 ምርጫ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ መሆን የምኖረውን ወሳኝ ሚና በግልጽ ቢያስቀምጥም፣ ይህንን እውነታ በአግባቡ መገንዘብ ያልቻሉና ከ1997 እና ከ2002 ምርጫዎች ደካማ …

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 10 /2007 ዓ.ም ለአምስት ሰዎች ሞትና ለበርካቶች አካል መጉደል ምክንያት በሆነው የተቃውሞ ሰልፍ ዙሪያ የገዢው መንግስት አስቸኳይ  መግለጫ እንዲሰጡ ያስገደዳቸው የኃይማኖት አባቶች በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ላይ የቀረበውን ጥያቄ በደስታ እንደተቀበሉት በመግለጫቸው መስጠታቸው እና ምዕመኑን እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር ማግለላችው እንዳበሳጫቸው በትላንትናው ዕለት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ከ100 000 ሺ በላይ ስደተኞች አውሮጳ በተለይ ኢጣሊያ መግባታቸው፣ የቀኝ አክራሪዎች-የውጭ ሃገር ዜጎች ጥላቻ መባባስ፣ ብሎም በአውሮጳ ምክር ቤት አሸናፊ ሆነው መውጣት እንዲሁም ሌሎች አበይት ነጥቦች በዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ጥንቅራችን ተካቷል።

የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በተገባደደዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት የተሻለ የሰብል ምርት መገኘቱን በቅርቡ ይፋ አድርጓል። በተቃራኒዉ በመላዉ ዓለም ወደ805 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ በቂ ምግብ እንደማያገኝም ጠቁሟል። ከአየር ንብረት ለዉጥና ከለዉጡ መዘዞች በመታገል የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጥረቶች በተለያዩ ሃገራት እየተሞከሩ ነዉ።

«የምዕራብ ፀረ-እስልምና የአውሮፓ አርበኞች» በጀርመንኛ ምህፃሩ ፔጊዳ የተሰኘዉ ኅብረት ፤ የጀርመን ዋና የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰነበተ። ህብረቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም ትናንት 10ኛውን የተቃውሞ ሰልፍ በድሬስድን ከተማ አካሂዷል።

የኢቦላ ተሐዋሲን ጨምሮ በአፍሪቃ የረሀብ አደጋም ስጋት እንደፈጠረ ተገለጠ። ከአፍሪቃ ጋር የሚደረግ የንግድ ግንኙነት ኅብረተሰቡን በማይጎዳ መልኩ መሆን እንደሚገባው የጀርመን መራሒተ-መንግሥት የአፍሪቃ ልዕክ ተገልጧል። የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ኢቦላን ለመዋጋት ለሚያደርጉት ጥረት ጀርመን የምትሰጠው ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የደቡብ ሱዳንን ቀውስ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ማዕቀብ የመጨረሻው አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አመለከቱ። ከዚህም ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራቸው ተጨማሪ ጦር ወደ ሶማሊያ ለማዝመት ዝግጁ እንደሆነች መግለፃቸዉንም የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

መኢአድ (የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) አንጋፋ ድርጅት ነው። ከመስራቹ ከፕሮፌሰር አስራት ጀመሮ የዚህ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። ብዙዎች ሞተዋል፤ ብዙዎች ታስረዋል። ከማንም ድርጅት ባልተናነሳ ገዢው ሙሸት አማረ በሚመራዉና በአቶ አበባው በሚመራው ቡድን መካከል ያሉ ልዩነቶች በአሁኑ ወቅት መኢአድ ትንች በተጠናከረ መልኩ ወደፊት እንዳይሄድ አድርጎታል። የነዚህ ሁለት ቡድኖች ዉዝግብ ገና አልተፈታም። ሕጋዊዉ የመኢአድ […]

“ለነፋስ ተርባይኖች” ግዢ በሚል ሰበብ በየአመቱ እንደዘበት የሚባክነው የቢሊዮን ብሮች ሃብት ሲታይ፣ በእርግጥም በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የማይገኝለት ቅሌት ነው ማለት ይቻላል። በየትኛውም አገር ቢሆን፣ በበለፀጉት አገራትም ጭምር፣ ከፍተኛ ሃብት በከንቱ እንዲባክን ማድረግ አሳፋሪ ተግባር ነው። አብዛኛው ህዝብ ችግረኛ በሆነባት፣ ሩብ ያህሉ ካለምፅዋት ሕይወቱን ማቆየት በማይችልባትና ገና አንገቷን ቀና ለማድረግ በምትውተረተር ደሃ አገር ውስጥ፣ በፈቃደኝነት ሃብት […]

Image

“ካልመለሱልኝ በውጊያ አስመልሰዋለሁ::” የደነገጠው ወያኔ
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::

ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል:: http://andargachewtsige.com/?p=383 ) አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::

በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::

ቁም ነገር ቅጽ 13 ቁጥር 193 ታህሣስ 2007

ለሶደሬ

መነሻ

በሀገራችን የኪነ ጥበብ ሙያ ውስጥ በሙያው አንቱ የተባለ አንድ አርቲስት ከዓመታት በፊት በአንድ ፊልም ላይ እንዲተውን ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ ጥያቄውን ተቀብሎ…

ትግራይ ክልል ላይ የሚፈፀሙትን ጭቆናዎች ሳይታክት አጋልጧል። ዘረኝነትን ፣ አምባገነንነትን ፣ ሙሰኝነትን ፣ ኢ-ፍትሐዊነትን አውግዟል። ሰብአዊነትን በማስቀደም ሰውን በሰውነቱ የሚለካ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው-አብርሃ ደስታ፡፡ አብርሃ ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሰዎችን ቀልብ ለመሳብ ከመቻሉም በላይ ፤ “ፌስቡክን” ከፌዝ-ቡክነት በመታደግ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን ሲያቀብለን ነበር፡፡ በመግቢያችን ላይ በአጭሩ እንደተገለጸው ይህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፣ የአሁኑ የፖለቲካ እስረኛ […]

ጓድ ቆምጬ አምባው በስማቸው የሚነገሩትን ጨዋታዎች በኔ ስም የተፈጠሩ ተረቶች ይሏቸዋል፡፡ ሰውዬውን በቅርበት የሚያውቁት ግን በርሳቸው ስም የተፈጠሩት ጨዋታዎች ከፊል እውነታ እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡ በርካታ ሰዎች ጨዋታዎቹን እያወሱ የሰውዬውን ጅልነት ሊያሳዩ እንደሚፈልጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ቆምጬ አምባው ነገር የገባቸው ብልጥ ነበሩ እንጂ በጭራሽ ጅል አይደሉም፡፡ ይህንን ለማሳየት እንዲቻለንም በርሳቸው ስም ከሚነገሩት ጨዋታዎች መካከል ጥቂቶቹን እንጽፍላችኋለን፡፡ ***** በደርግ […]


ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
በህይወት እስካለን ድረስ ተረት መተረታችንን አናቆምም፡፡ እነሆ ለዛሬም በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል እየተደጋገሙ የሚነገሩ ሁለት ትራጄዲ ተረቶችን አዘጋጅተንላችኋል፡፡
===የተንኮል ገበቴ===
እናት አንድ ልጅ ብቻ ነበራት፡፡ ይህንንም ልጅ በብዙ ልፋት ካሳደገችው በኋላ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ዳረችው፡፡ ታዲያ የልጁ ሚስት እናትዬውን የምትወድ አልነበረችም፡፡ በብዙ አድራጎቷ ትበድላታለች፡፡ ይብስ ብሎ ደግሞ እናትየዋ ታወረች፡፡ ሚስትም በደሏን አጠናከረች፡፡ በተለይም ሴትዮዋን በጣም የምትበድለው ለእናትዮዋ በምታቀርበው ምግብ ነው፡፡
 ለምሳሌ ለእራት ገንፎ ስታቀርብላት ባሏም ሆነ ሌላ ሰው ዐይኑን እንዳይጥልበት በገንፎው ላይ ቅቤ ትጨምርበታለች፡፡ ነገር ግን ቅቤው ወደ መሬት እንዲፈስ ገንፎው የሚቀርብበትን ገበቴ በአንድ በኩል በስታዋለች፡፡ ልጁ እናቱ ገንፎ በቅቤ የበላች ስለሚመስለው ሚስቱን አይናገራትም፡፡ ሆኖም ገንፎው ቀስ እያለ ወደ መሬት ስለሚፈስ እናትዮዋ አታገኘውም (እናትዮዋ ዐይነስውር መሆኗን አስታውሱ)፡፡
ዘመን አለፈ፡፡ የልጁ እናትም አረፈች፡፡ ልጅየውም ካገባት ሚስቱ አንድ ልጅ ወልዶ ሞተ፡፡ የትናንትናዋ ሚስት የአዲሱ ልጅ እናት ሆነችና ከልጇ ጋር መኖር ጀመረች፡፡ ልጇ ለአቅመ አዳም ሲደርስ እርሷም በተራዋ ከአንዲት ወጣት ጋር በጋብቻ እንዲጣመር አደረገችው፡፡ ሶስቱ ሰዎች በአንድ ላይ መኖር ጀመሩ፡፡ እናት ስታረጅ እንደ ትልቋ እናት (የሞተችው የቧላ እናት) ታወረች፡፡ አንድ ቀን ምግብ ሲቀርብላት ገንፎው ቅቤ የሌለው ሆነባት፡፡ ወዲያውኑ የሆነ ነገር ትዝ አላትና ገበቴውን መዳበስ ጀመረች፡፡ በርግጥም እንደጠረጠረችው ገበቴው በአንድ በኩል የተበሳ ሆኖ አገኘችው፡፡ እናም ድሮ ስትፈጽመው የነበረውን በደል በማስታወስ ከልቧ አዘነች፡፡ እንዲህም አለች፡፡
“አይ ገበቴ! አይ ገበቴዋ! ከምኔው ዞረሽ ወደኔ መጣሽ?!! ግድ የለም፡፡ የእጄን ነው ያገኘሁት፡፡ ያኔ የባሌን እናት ባልበድል ኖሮ ዛሬ ምግቤ እኔ በቀደድኩት ገበቴ ባልተሰጠኝ ነበር”
የሴትዮዋ ንግግር ከልጁ ሚስት ጆሮ ጥልቅ አለ፡፡ እናም ሚስት በሰማችው ነገር ሽምቅቅ አለች፡፡ “ለካስ የኔም የወደፊት እጣ በዚህች ገበቴ መብላት ነው?” እያለች አሰላሰለች፡፡ ወዲያውኑ የባሏን እናት ይቅርታ ጠይቃ ያቺን የተንኮል ገበቴ እንክትክት አድርጋ ሰባበረቻት፡፡ እናትም ምግባቸው በጤነኛ ገበቴ ይቀርብላቸው ጀመር፡፡
===ሁለቱ አባቶችና ሁለቱ ልጆች===
ልጅና አባት አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ አባት ልጁ ትዳር እንዲይዝ ካደረገው በኋላ ሁሉንም ነገር አስረከበው፡፡ ለራሱም ጡረተኛ ሆኖ ከልጁ ቤት ጀርባ ከነበረች አንዲት አነስተኛ ጎጆ መኖር ጀመረ፡፡ ይሁንና አባትዬው በጸባዩ ነጭናጫ ነው፡፡ በተለይ ልጅ ለስራ ወደሌላ ቦታ በሚሄድበት ጊዜ የልጁን ሚስት በሆነ ባልሆነው ይነዘንዛታል፡፡ ሚስትም በንጭንጩ ተማረረችና ባሏ ሲመጣ “ወይ አባትህን ከዚህ ቤት አርቅልኝ፤ ወይ ደግሞ ፍታኝ” አለችው፡፡
ልጁ ወደ አባቱ ሄደና “አባቴ! እዚህ ቤት ስትኖር አፍህን ዝጋልኝ!! ካልሆነ ግን ወደ ገደል እወረውርሃለው” በማለት አስጠነቀቀው፡፡ አባትም “አረ አትወርውረኝ! ከእንግዲህ አፌን እይዛለሁ” በማለት ተማፀነው፡፡ በመሆኑም አባት ከነርሱ ጋር መኖሩን ቀጠለ፡፡ ነገር ግን አባት ቃሉን ሊያከብር አልቻለም፡፡ ልጁ ከቤት እስኪወጣ ጠብቆ ሚስትዬውን ይጨቀጭቃት ገባ፡፡ በዚህ የተናደደችው ሚስት ወደ ባሏ ሄዳ “ነገ አባትህን ከዚህ ቤት ካላስወጣህልኝ እሄድልሃለሁ” አለችው፡፡ ባልም “ግድ የለም! ነገ ገደል ውስጥ እጥለዋለሁ” አላት፡፡
በንጋቱ ልጅየው ሽማግሌ አባቱን ወደ ገደል ሊወረውረው ተነሳ፡፡ ከገደሉ ጫፍ ላይ ካደረሰው በኋላም “አባቴ! ብትፈልግ ገደል ግባ! ብትፈልግ የፈለግከውን ሁን፡፡ አባቴ ስለሆንክ ግን በራሴ እጅ አልወረውርህም፡፡ ትዳሬንም እወዳለሁና ከቤቴ እንድትመለስ አልፈቅድልህም” አለው፡፡ አባትየውንም እዚያው ትቶት ሄደ፡፡
ዘመን አለፈ፡፡ የድሮው ልጅ በተራው አባት ሆነ፡፡ ልጁም አገባ፡፡ አባትም ከልጁ ጋር መኖር ጀመረ፡፡ ታዲያ እርጅና ሲመጣ ይህኛውም  አባት ልክ እንደ ድሮው አባት ጨቅጫቃ ሆነ፡፡ የልጁን ሚስት በረባ ባልረባው ይጨቀጭቃት ጀመር፡፡ ልጁም ጭቅጭቁ ሲሰለቸው አባትዬውን ወደ ገደል ሊወረውረው ተሸክሞት ተነሳ፡፡ ረጅም ርቀት ከተጓዙ በኋላ የታዘለው አባት ልጁን እንዲህ አለው፡፡
  “እዚሁ ጋ ብትተወኝ ይሻለኛል፤ እኔም ያኔ አባቴን ከዚህ አላሳለፍኩትም”፡፡
*****
  አያድርስ ነው ወገን! “ሁሉም የዘራውን ነው የሚያጭደው” የሚለው ምሳሌ አሁን ላይ የማይሰራ ቢመስልም ጊዜው ሲደርስ እውነት መሆኑ አይቀርም፡፡ አላህ ከእንዲህ ዓይነት ክፋት ይጠብቀን፡፡
በነገራችን ላይ የመጀመሪያውን ተረት የነገሩን ጎረቤቴ የነበሩት “ሀቦ ኑሪያ” ናቸው፡፡ ሁለተኛውን ተረት የአባቴ የቅርብ የስጋ ዘመድ ከሆኑት ሼኽ ሙሐመድ ሑሴን ቲርሞ የሰማሁት ነው (በኋላ ላይ ስብሐት ገብረእግዚአብሄር ጽፎት ባነበውም ተረቱን በቅድሚያ የሰማሁት ከሼኽ ሑሴን አንደበት ነው)፡፡
——
አፈንዲ ሙተቂ
ግንቦት 26/2006
አዳማ!!
—–
Afendi Muteki is a researcher and author of the ethnography and history with special focus on the peoples of East Ethiopia. You may follow him on his blog and his facebook page by clicking the following links

ከመከላከያ ሰራዊት እንዲባረሩ የታሰቡ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ለስርአቱ ደህንነት ሲባል በቦታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ታወቀ::

ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰራ የነበረው ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ባለፈው አመት ከቦታው መባረሩ ተከትሎ መባረር አለባቸው ተብለው ውስጥ ለውስጥ የተጨረሰላቸው በርካታ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ቢኖሩም፤ ከኋላ ሊነሳ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት በተደረገው ግምገማ ላይ በማስጠንቀቅያ ብቻ እንዲታለፉ መደረጉን ታውቋል::

መባረር አለባቸው ተብለው ከተቀመጡት ከፍተኛ መኮነኖች አብዛኛዎቹ የሌተናል ኮረኔል ማእረግ ያላቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የጄኔራል አበባው ተከታዮች ስለሆኑና እንቅፋት ስለሚፈጥሩብን ተብለው እንዲባረሩ የተወሰነባቸው ቢሆንም፤ በመጪው ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በህዝቡ መሃል ገብተው ኢህአዴግን ለመጣል ሊያነሳሱ ስለሚችሉ ግምገማ በማድረግ በማሰጠንቀቂያ እንዲታለፉ መደረጋቸውን መረጃዎች አምልክተዋል::መረጃዉም አያይዞ እንደጠቀሰው ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስልጠና ልምምድ እያደረገ የነበረ አንድ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ተዋጊ ሄሊኮፍተር ከሃዲው አብራሪ ቴክኒሻኑንና ረዳት አብራሪውን በማስገደድ ኤርትራ ማረፉን የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ  ሄሊኮፍተሩ ባፈው አርብ ከጧቱ 2 ሰዓት ከ35 ጀምሮ በመደበኛ የስልጠና ልምምድ ላይ ነበር፡፡ …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን ኤም አይ 35 የተባለ የውጊያ ሄሊኮፕተር ይዘው በመጥፋት ወደ አልታወቀ ስፍራ የተጓዙት ሁለቱን አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሻንን ለመፈለግ አየር ሃይል በተለያዩ አካበባዎች  አሰሳ ሲያደርግ ቢቆይም በመጨረሻ ፍለጋው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ፍለጋው እንዲቋረጥ የተደረገበት ዋና ምክንያት አብራሪዎቹ ሆን ብለው መጥፋታቸውና ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው ትብብር ባወጣው መግለጫ የባህርዳር ከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት መቅጠፉን አስታወሶ፣  ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል …

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር በቀጥታ እየተገናኙ የሀገራችንን ጥቅምና ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አሉ ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን አስመልክቶ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አሸባሪ ከሚባሉ ቡድኖች በቀጥታ እየተገናኙና እያቀዱ ሀገር …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

በባህር ዳር ከተማ ዓርብ ታኅሣሥ 10 ቀን 2007 ዓም ድንገት በተቀሰቀሰ ግጭት ከሦስት እስከ አምስት ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰማ። በርካቶችም መቁሰላቸው ተጠቅሷል። ሆኖም የደረሰዉን የጉዳት መጠን በትክክል የሚያረጋግጥልን የመንግስት አካል አላገኘንም።

ለዋሽንግተን ሐቫና ግንኙነት አሮጌዉ ዓመት አዲስ ተስፋ ፈንጥቋል። ከአፍሪቃ በስተቀር የሌላዉን ዓለም አበይት ክንዉኖች በሁለት ክፍሎች ቃኝተን፤ የማላላን ገደኛ፤ የማሌዥያን ፈሪሰኛ ግን ጉደኛ ዓመት እንሸኘዉ፤

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የእምነት ነጻነትን በመጋፋት ፣ ታቦት ቢወጣበትና የጥቅምት በዓል በሚከበርበት በባህር ዳር የመስቀል አደባባይ “ልማት” በሚል ስም ለባለሃብቶች ቦታዎች ሊሰጥ ማሰቡን ተከትሎ ሕዝቡ ለአስተዳደሩ ብሶቱን በደብዳቤ ለማስገባት፣ በቦታው ሄዱ ለማነጋገር ቢሞክር፣ ለሕዝብ ጥያቄ ደንታ የሌላቸው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ቦታውን ለባላሃብቶች ለመስጠት በመወሰናቸው፣ ሕዝቡ የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር ባለስልጣናት ዉሳኔያቸዉን እንዲቀለብሱ ለማድረግ፣ በራሱ አነሳሽነት ፣ በሺሆች […]

Image

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰዉን በድልና ጭቆናን በመቃወምና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችአስመልክቶ በዋሽግተን ዲሲ የሚገኘዉ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን የ አቋም መግለጫ አወጣ
ባለስድስት ነጥብ የሆነዉ የ አቋም መግለጫ የ ኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮች ያጠቃለለ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚያደርሰዉን በደልና ጭቆና ለመታደግ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን አገራዊ ሐላፊነቱን ለመወጣት የሚጠበቅበትን ሁሉ እደሚያደርግ የ አመራር አካላቱ ለ ቢቢኤን ገልጸዋል። የአቋም መግለጫዉም እንደሚከተለዉ ይነበባል፦

• ሆን ተብሎ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ መንግስት ሲፈፅም የቆየዉን ኢሰብአዊ ድርጊት ባዲስና በከፋ መልኩ የጀመረዉን እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

• ሙስሊም እህቶቻችንን የእምነት ነፃነት በመንፈግ ባአዲስ አበባ ዩኒፈርሲቲና በሌሎች የትምህርት እንዲሁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ሂጃባቸዉን እንዲያወልቁ የማስገደዱ ጉዳይ ሙስሊም ሴቶችን ከእምነታቸዉና ከትምህር እንዲሁም ከእምነታቸዉና ሰርተዉ ከመኖር ምረጡ እየተባሉ የሚደረግባቸዉን ተፅእኖን አጥብቀን እናወግዛለን

• በግፍ ታስረዉ ባሉት የሙስሊም መሪዎች ቤተሰቦች ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ ገብታችሁ ወዳጆቻችሁንን መጠየቅም ሆነ ምግብ ማቅረብ አትችሉም ተብለዉ የሚደርስባቸዉን መጉላላት በጥብቅ የምናወግዝ መሆናችንንም እንገልፃለን

• እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካንድ ጠቅላይ ሚንስቴር በማይጠበቅ አፀያፊ አነጋገር ጨዋዉንና ታታሪ ሰራተኛዉን የስልጤን ብሄረ ሰብ መዝለፋቸዉን አጥብቀን እንቃወማለን

• በቪዎች የሚቆጠሩትን ካገርና ከወገን ተለይተዉ ቤተሰቦቻቸዉንና ዘመዶቻቸዉን ለመርዳት የሚደርስባቸዉን ያካልና የመንፈስ ተፅእኖን በመቇቇም ለሚያደርጉት መስዋእትነት መመስገንናና መደነቅ ሲገባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ባልተገራ አንደበታቸዉ እህቶቻችንን ገረዶች ብለዉ አንቇሸዉ መጥራታቸዉ እጅጉን አስከፍቶናል። የኢትዯዽያ ህዝብንም ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ እናሳስባለን።

• በተጨማሪም በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች ላይና እንዲሁም ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣዉ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን ኢሰብአዊ መንግስታዊ እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

“ፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን የኢትዯዽያ መንግስት ከቀን ወደቀን የህዝቡን ሰብአዊ መብት እየጨፈለቀ መቀጠሉን አጥብቀን እንደሚያወግዝና ሌላዉም የሰዉ መብት ያገባኛል የሚል ስብእና ያለዉ ሰዉ ያወግዝ ዘንድ ጥሪዉን ያቀርባል” በሚል የጥሪ መልክት የ አቋም መግለጫዉ ተቋጭቷል። የፈርስት ሒጅራህ የአመራር አካላት መጠነ ሰፊ የሆነዉን ጭቆናና በደል ለመታደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንደሚሰሩ በመግለጽ በቀጣይነትም የሚያከናዉኗቸዉ የተቃዉሞ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

የአሸባሪ ሚስት ድሮም አሸባሪ ናት ሂጃብ አውልቂ ከተባለች ለምን አታወልቅም አይደለም ሂጃብ ይቅርና ካስፈለገን ቀሚሳቸውን አሶልቀን እናያቸዋለን (አቶ አምባዬ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ) አቡ ዳውድ ኡስማን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ኡስታዞቻችን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዚህ ሳምንት የጀመረውን ሙስሊም ሴቶችን ሂጃባችሁን አውልቃችሁ ሳንፈትሻቹ አትገቡም የሚለውን ክልከላ አስመልክቶ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ሃላፊ ላቀረቡት አቤቱታ በማረሚያ […]

አምርረህ ልትታገልበት የሚገባ በቂ ምክንያት ካለ አላማው አንድና አንድ “ማሸነፍ” የሆነ ትግል እንጂ የትግል አይነት የሚባል ነገር የለም። አዎ ያለው ትግል ነው። ቢቸግር ነው እንጂ ችግሩ “አይነት” የሚለው ቃል ችግር ሆኖ አይደለም። ትግሉ ላይ ሲሆን አጠቃቀማችንና አረዳዳችን ግን በጣሙኑ ግራ ያጋባል። “ምግብ” ለሚለው ያጋራ መገለጫ ስር ጨጨብሳ፤ ሙዝ ፤ ወተት የመሳሰሉ ምግቦች እንዳሉ ለማሳያት ሳይሆን […]

በህይወት እያሉ ተረት ለመሆን የበቁትና በጎጃም ክፍለ ሀገር የደብረ ወርቅ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ “ቆምጫ አምባው” በዚህ ፎቶግራፍ የምትመለከቷቸው ሰውዬ ናቸው፡፡ አቶ ቆምጬ በአሁኑ ወቅት በትውልድ ከተማቸው በጥብቅና ሙያ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ (ፎቶ፡ ዘ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ)

Image



(አፈንዲ ሙተቂ)
—-
   በምስሉ ላይ ያለውን ሰውዬ ታውቁታላችሁ አይደል?… ህንዳዊ የሲኒማ አክተር ነው፡፡ በትክክለኛ ስሙ “ሚቱን ቻክራቦርቲ” ይባላል፡፡ የሀገራችን የሲኒማ አፍቃሪዎች ግን “Disco Dancer” በሚባለው ፊልም ውስጥ በሚጠራበት ስሙ ነው የሚጠሩት፡፡

አዎን! “ጂሚ” ነው፡፡ ያ “እኔ እኮ የዲስኮ ዳንሰኛ ነኝ” እያለ የሚሞላቀቀው ጆሊ!!
  I am a disco dancer
 ዘንደኪ ሜራሃና!
 ሜንዲሽቲ ከቲቫና
ኮቹሞ ሀነቾ
ሀ ሜሪ ሰቲ ነቾ
 
  አዎን!!  እርሱ እኮ ነው፡፡ (ዲስኮ ዳንሰርን በዚህ ሊንክ ላይ ተመልከቱት https://www.youtube.com/watch?v=7JdEZoffm-Q   )
 “ጂሚ ጂሚ ጂሚ… አጃ.. አጃ” እያለች የምታለቅስለትን ልጅስ አስታወሳችኋት?… ወይ ስታዝን!… ጂሚ በኤሌክትሪክ ጊታር ተቃጥላ የሞተችበት የእናቱ ሐዘን ቅስሙን ሰብሮት ሙዚቃውን እርግፍ አድርጎ ስለተወ ሽልማቱን ሊያጣ ደርሶ ነበር፡፡ በመሆኑም ነው ልጅቷ  “ጂሚ.. ጂሚ.. አጃ.. አጃ.” እያለች የተለማመጠችው፡፡
በልጅነታችን Disco Dancer የሚባለውን ፊልም ሳናየው በፊት በቪዲዮው ውስጥ ያሉት ዘፈኖች የተሰበሰቡበት ካሴት በጣም ተወዳጅ ሆኖ ነበር፡፡ በመሆኑም በሰርግ ቤትም ሆነ በወላጆች ቀን በዓል ቀዳሚ ምርጫ ሆኖ ይከፈት የነበረው እርሱ ነው፡፡ እርሱ በደንብ ከተደመጠ በኋላ ነው የማይክል ጃክሰን “ትሪለር” በሁለተኛ ደረጃ የሚከፈተው (በሶስተኛ ደረጃ የ“ቦኒ ኤም” ዳዲ ኩል ነው የሚመረጠው)፡፡
   ታዲያ ዕድላችን ተቃንቶ የህንድ ሲኒማ በ1978 ወደ ከተማችን ሲመጣ ጂሚን በውኑ ያየነውን ያህል ነው የፈነጠዝነው፡፡ ጂሚን የማየት የዘመናት ጥማታችንን የተወጣንበት የመጀመሪያው ፊልም  “Jimmy and His Elephant” የሚል ርዕስ የነበረው ይመስለኛል (በአማርኛ “እኔና ዝሆኔ” ይሉት ነበር)፡፡ በርግጥም ጂሚ በፊልሙ ውስጥ ከዝሆን ጋር ጉደኛ ዳንስ ይደንሳል፡፡ ዝሆኑ እንደ ጥሩምቦንና እንደ ሳክስፎን “ፓፓፓ” እያለ ድምጽ አውጥቶ ይሞዝቃል፡፡
    ከሁለት ዓመት በኋላ (በ1980) ጂሚ በጣም የታወቀበት `Disco Dancer”  መጣ፡፡ ማን ይቻለን!! አቤት ፌሽታ!! የፊልሙ ፖስተር (በያኔው አጠራር “ሌክራም”) በከተማችን ማዕከላዊ ስፍራ ላይ በነበረው የአቶ ዋጋዬ ይደነቃል ሱቅ ግድግዳ ላይ ሲለጠፍ እርሱን ለማየት የነበረው ግርግር እስከ አሁን ድረስ ይታወሰኛል፡፡ ማታ በ12፡00 ሰዓት ለሚታየው ፊልም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ነው የተሰለፍነው፡፡
   ፊልሙ ተጀመረ፡፡ ጂሚ በልጅነቱ Goron Ki Na kalon Ki እያለ ከሚዘፍነው ዘፈኑ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ ልባችን እየተሰቀለ አየነው፡፡ በርሱ ዳንስና እናቱን በገደለበት ተንኮለኛ ሙጅሪም (በኛ አጠራር “ፋሩቅ” የሚባል)መሀል እየተወዛወዝን አጣጣምነው፡፡ ፊልሙን ባየንበት ማግስት ወሬው እርሱ ብቻ ሆነ፡፡ በየሆቴሉ፣ በየሻይ ቤቱና በየጥናት ቤቱ የጂሚ ፖስተሮች ተለጠፉ!!
—-
በ1981 ደግሞ ጂሚ ሌላ ተአምር ይዞ መጣ፡፡ Kassam Paida Karne Wale Ki (በአጭር አጠራር Kassam Paida) የሚባል ፊልም ውስጥ ያየነው ጂሚ ድሮ ከምናውቀው ጂሚ በእጥፍ ጨመረ፡፡ ይህኛው ጂሚ በሙዚቃው ብቻ ሳይሆን በአለባበሱም ከሌላ ፕላኔት የመጣ መልአክ መስሎ ነው የታየን፡፡ በዳንሱና በአለባበሱ በጣም ስላፈዘዘን “ከጂሚና ከማይክል ጃክሰን ማን ነው የሚበልጠው?” የሚል ውርርድም ተጀምሮ ነበር (በነገራችን ላይ Kassam Paida የሚባለው ፊልም በአማርኛ “ጂሚ እንደ ማይክል” ተብሎ ነው የሚጠራው፤ በፊልሙ ውስጥ ጂሚ የሚዘፍነው አንዱ ዘፈን ዜማው ከማይክል ዘፈን ስለተኮረጀ ይመስለኛል እንደዚያ የተባለው፤ ደግሞም ማይክል Thriller በተሰኘው ዘፈን እንዳደረገው ሁሉ ጂሚም ሙታንን ከመቃብር አስነስቶ አስደንሷል)፡፡
   ከሁሉም በላይ Kassam Paida ውስጥ የተወነው ጂሚ በጣም ያስደነቀን  በድራም አመታቱ ነው፡፡ በፊልሙ ውስጥ አብራው የተወነችው Salma Agha የተባለች ፓኪስታናዊት አክትረስ ናት፡፡ ይህቺ አክትረስ Joom Joom Joom Ba Bah እያለች የምትጫወተው ዘፈን አለ፡፡ በዚያ ዘፈን ላይ በሙዚቃ መሳሪያ ካጀቧት ሙዚቀኞች መካከል አንዱ ጂሚ ነው፡፡ ጂሚ ድራሙን ሲያተረማምሰው አፍ ያስከፍታል፡፡ በተለይም አንድ ቦታ ላይ “ሳልማ” (በፊልሙ ውስጥ የምትጠራበት ስም “ኒና” ነው) ዘፈኑን እያስኬደችው ታቆመውና ወደ ጂሚ ዞራ የዐይን ምልክት ትሰጠዋለች፡፡ ይሄኔ ጂሚ ድራሙን ይቀውጠዋል፤ እያርበደበደ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ ዲም..ዲም ዲም.. ዲም….ተራራም.. ዲም…..ዳም ዳም…ኪሽ…ኪሽ…..!!  እንዲያው እኮ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ማሽን ነው የሚመስለው!!
 
  ጂሚ ድራሙን እንደዚያ አተረማምሶ ሲወቃው በአዳራሹ የነበረው የከተማችን የሲኒማ ተመልካች በሙሉ ከመቀመጫው ተነስቶ በጭብጨባ አድናቆቱን ገልጾለታል፡፡ በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ነገር እንደተከሰተ ተነግሮኛል፡፡
 (ያንን የድራም ምት ለማየት ካሻችሁ ይህንን የዩቲዩብ ቪዲዮ ተመልከቱ፡፡ http://www.youtube.com/watch?v=IFjKnIgd9js  )
——-
“ጉድና ጅራት በስተመጨረሻ ነው” አሉ!! ሰሞኑን የሆነ ነገር ፈልጌ You Tubeን ስጎረጉር የጂሚን የቆዩ ቪዲዮዎች አገኘሁ፡፡ ያኔ በልጅነታችን ሲያስጨበጭቡን የነበሩት የዲስኮ ዳንሰር እና የKassam Paida ዘፈኖች በመደዳ ተደርድረዋል፡፡ “ወይ ጂሚ! ከየት ተገኘህ ደግሞ” አልኩኝና አንድ ሁለቱን ከፍቼ አየኋቸው፡፡ ጂሚ አሁን ያለበትንም ሁኔታ የማወቅ ጉጉት ስላደረብኝ ኢንተርኔቱን የበለጠ ጎረጎርኩት!!
መቼም ይህ ኢንተርኔት የሚባለው “የሸይጣን ድር” አቃጣሪም አይደል? የአሁኑን ጂሚ ብቻ ሳይሆን የያኔውን ጂሚ ጭምር ቁልጭ አድርጎ አሳየኝ፡፡ “ዳንሱም የውሸት፣ ሙዚቃውም የውሸት፣ ዘፈኑም የውሸት ነው፤ ጂሚ ሌላ ሰው በዘፈነው ሙዚቃ ነው እንደዚያ ሲያጭበረብራችሁ የነበረው”- ይላል ኢንተርኔቱ!!
ይገርማል!! ከዚህ በፊት “የህንድ ፊልም የእውነት ነው” ስንል እንደነበር ጽፌአለሁ፡፡ በሂደትም በፊልም ውስጥ የውሸትና የእውነት ትዕይንቶች ተቀላቅለው እንደሚቀናበሩ ማወቃችንንም ነግሬአችኋለሁ፡፡ በመሆኑም የህንድ ፊልምም የውሸትና የእውነት ቅንብር ነው ብዬ ነበር የማምነው፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር የውሸት ሆኖ ቁጭ አለ! አይ እዳ!!
    ይህ ጂሚ አናደደኝ !! የምሬን ነው በጣም ነው ያቃጠለኝ!! በውሸት ምት እነ ሳምሶን መላጣን ከጣሪያ ወደ መሬት እያንከባለለ ሲያጭበረብረን የነበረው ሳያንሰው በውሸት ዘፈንና ዳንስ ያታልለናል እንዴ?!! አሁን ያቺ ምትሃተኛ ድራም የውሸት ናት?… በውሸት ነው እንደዚያ ከሳልማ ጋር እየተቀባበሉ “በዘበዛ” ሲያደርጉን የከረሙት?… እኛስ አስመሳዩን ሰውዬ ነው ከማይክል ጃክሰን ስናስበልጠው የነበረው?…
ይገርማል!! የሆሊውድ አክተሮችም በሙዚቀኛና በሙዚቀኛነት ህይወት ላይ ያተኮረ ፊልም ይሰራሉ፡፡ ነገፍ ግን ምዕራባዊያኑ በፊልም ውስጥ የሚዘፍኑት ዘፈንና የሚደንሱት ዳንስ በአብዛኛው የእውነት ነው (ለምሳሌ ጆን ትራ ቮልታን መጥቀስ እንችላለን)፡፡ ጂሚ ሆዬ በውሸት ዘፈንና በውሸት የሙዚቃ መሳሪያ አጨዋወት ስልት ሲያስለፈልፈን ከረመ!! ይኼ ቦንባ!! ይሄ ጉረኛ!!
—-
ደግነቱ እኛ ብቻ አልነበርንም፡፡ “ጂሚ” በመካከለኛው ምስራቅ፣ በምስራቅ አውሮጳ ሀገራትና በሶቪየት ህብረትም ጭምር ነው ዝነኛ የሆነው፡፡( በዚያ ዘመን ከሆሊውድ የመጣ ፊልም በሶቪየት ህብረት አይታይም፤ የህንድ ፊልሞች ግን ይፈቀዳሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ የህንድ ፊልሞች እንደ አሜሪካ ፊልሞች ሶቪየት ህብረትንና የሶሻሊዝም ስርዓትን ስለማያጥላሉና ስለማይተነኩሱ ነው)፡፡  በመሆኑም የኛ መሸወድ የተለየ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ ያ እንደዚያ ስናጨበጭብለት የነበረው ጂሚ እኛ ምኑንም ባላወቅነበት ወቅት በካሜራ ጥበብ ቢያታልለንም ዛሬም እናደንቀዋለን!!
ከመልከ መልካሙ ጂሚ ጋር ወደፊት!!
—-
ጳጉሜ 5/2006

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ካድሬዎቹ በባህር ዳር የተደረገውን ግድያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል::
Minilik Salsawi – ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::

እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ ካድሬዎቹ ሕዝብን ማሳመን የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል::ንጹሃን በአደባባይ መግደል የፖለቲካ ትርፉ ምንድነው የሚሉ እና በባህር ዳር የተደረገው ድርጊት በመጭው ምርጫ ላይ ከባድ ተጽእኖ ያጠላበታል ሲሉ አስተያየታቸን እና ጥያቄዎቻቸውን ሰንዝረዋል::ይህንን ድርጊት ፖሊሶቹ እንዲፈጽሙ ለምን ከፌዴራሉ ትእዛዝ መቀበል አስፈለገ? የክልሉ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ በሰላም ለመበተን ያደረገው ጥረት ምንድነው ማብራሪያ እንፈልጋለን ሲሉ ካድሬዎቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ለውይይት የተጠራው ስብሰባ ወደ ጫጫታ ተለውጧል::

ካድሬዎቹ እንደሚሉት ማንኛውንም ጥያቄ በሃይል እየደፈጠጥን በምርጫው ወቅት ስንሸነፍ ሽንፈታችንን ተከትሎ በህዝብ ላይ ላለመተኮሳችን ማረጋገጫው ምንድነው ይህ ከባድ አደጋ ስለሆነ ባህር ዳር ላይ ለተፈጸመው ግድያ እና ድብደባ የክልሉ መንግስት እና መሪ ድርጅቱ ኢሕአዴግ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው::ሌሎች አስፈላጊውን ሮሮ ሳያሰሙ ለጉዳተኞች ካሳ ሊከፈል ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
የካድሬዎቹ ውይይት ከመጭው ምርጫ ላይ ያላቸውን ስጋት እና በህዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥፋት በመናገር ያላቸውን ስጋት የገለጹ ሲሆን እንደ አባልነታቸው ደህንነታቸው ላይ ያለውን ጉዳይ በተመለከተም ጥያቄ አንስተዋል:: ለ 6 ሰአታት ያህል የዘለቀው ስብሰባ በስተመጨረሻ በምክክር ተጨማሪ ስብሰባዎች ይኖሩናል በሚል ካለመስማማት በጫጫታ መበተኑን ምንጮቹ ለምንሊክሳልሳዊ ገልጸዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ካድሬዎቹ በባህር ዳር የተደረገውን ግድያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል:: – ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ ካድሬዎቹ ሕዝብን ማሳመን የማንችልበት ደረጃ ላይ […]

እስካሁን ሦስት ተከታታይ አልበሞችን አሣትሟል። በቅርቡ ለአድናቂዎቹ ጆሮ ያደረሰው ሲዲ «አስታራቂ» ይሰኛል። ዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ መሣሪያ ተጨዋች እና ድምፃዊ ነው። አርቲስት አብነት አጎናፍር።

የዚያኑ ያክል ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበት ሃኛ ዓመት ከመከበሩ ከአንድ ቀን በፊት አዲስ አበባ ዉስጥ ለተቃዉሞ ሠልፍ አደባባይ ለመዉጣት የሞከሩ የከተማይቱ ነዋሪዎች፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና አባላት በፀጥታ አስከባሪዎች መደብደብ፤መዋከብ፤ በጅምላ እየታፈሱ መታሰራቸዉ ተዘግቧል።

 ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ።የት እንደገቡ እስካሁን አልታወቀም። ለኢሳት በደረሰው መረጃ የ ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሻምበል ሳሙ ኤል ግደይ እና መቶ አለቃ ቢልልኝ መኮንን ትናንት ጧት ለልምምድ እንደወጡ ነው ጠፍተው የቀሩት። አብራሪዎቹ ከ 30 ደቂቃ በላይ እንዲቆዩ ከማይፈቀድላቸው የበረራ ራዲየስ በመውጣት የሚያበሯቸውን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ይዘው […]

ዬኤስ አሜሪካ ጓንታናሞ ኪዩባ በሚገኘዉ ወታደራዊ እስር ቤቷ የያዘቻቸዉን አራት የአፍጋኒስታን ዜጎች በነፃ ለቃ ወደ ሃገራቸዉ መላክዋን ዋሽንግተን የሚገኘዉ የዩኤስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

“ ቅ/ ሲኖዶሱ በአድባራት ሓላፊዎች ላይ ያሳለፈው ሕገመንግሥቱን የሚፃረር ነው ” /ፓትርያርኩ/
Image

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል ፓትርያርኩ ማገዳቸው ተገለጸ፡፡
ፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር 30 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመንበረ ፓትርያርክና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሾች በተካሔዱት ስብሰባዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም አስተዳደርና ወቅታዊ ችግሮች የተመለከቱ የጉባኤተኞች አስተያየቶችና ሐሳቦች መቅረባቸውን በደብዳቤያቸው ያስታወሱት ፓትርያርኩ፤ ተሰብሳቢዎቹ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ መናገራቸውና አሉ የተባሉ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ መጠየቃቸው ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃም ኾነ በሀገራችን ለሕዝብ የተፈቀደ ዴሞክራሲያዊ መብት መኾኑ አያጠያይቅም›› ብለዋል፡፡ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ ያቀረቡ ሰዎችን መገሠጽና መውቀስም ሕገ መንግሥቱን እንደሚፃረር ጠቁመዋል፡፡
ጉባኤዎቹ በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት የተካሔዱ እንደነበሩና ተሰብሳቢዎቹም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣ አገልጋዮችና ሠራተኞች መኾናቸውን ፓትርያርኩ ጠቅሰው÷ የጎደለው እንዲሟላ የጠመመው እንዲቃና ያላቸውን አስተያየት በማቅረባቸው ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹የስብሰባ ነፃነትንና መብትን ነፍጎ ሐቁ እንዳይነገር›› የሚከለክልና ውጤቱም ‹‹ጊዜ ያለፈበትን አፈና በማንገሥ ችግሮች ተባብሰው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ነው›› ብለዋል፡፡ “በውይይቱ ወቅት ‹‹የዳኅፀ ልሳን ወለምታ›› አጋጥሞም ከኾነ በወቅቱ ማብራሪያና ማስተካከያ ይሰጥበታል እንጂ እንደ ከባድ ጥፋት ተቆጥሮ ሰዎች ሊገሠጹበትና ሊወቀሱበት አይገባም፤ ሕግም አይፈቅድም፡፡” ሲሉ ገልጸዋል – በደብዳቤያቸው፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ያላቸው አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹ሕግንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር›› ብቻ ሳይኾን ‹‹ትልቁን ጉባኤ በታሪክና በሕግ ዐዋቂዎች ዘንድ ግምት ውስጥ የሚጥለው እንዳይኾን አቡነ ማትያስ አስጠንቅቀው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉዳዩን እንደገና በጥልቀትና ከሕግ አንጻር ፈትሾ እንዲያጤነው በማለት አፈጻጸሙ እንዲቆይ አስታውቀዋል፡፡
በሕገ ቤተክርስትያን ት/ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ፓትርያርኩ የማገድ ሥልጣን እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከተጠቀሰበት አግባብ አኳያም፣ “ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕግጋት አሏት፤ እነዚህ ሕግጋት ማዕከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤” ሲልም ቅ/ሲኖዶሱ አሳስቧል፡፡
ባለፈው መስከረም መጨረሻ “የቤተ ክርስቲንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ” በሚል መርሕ በተካሔደው ስብሰባ አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ‹‹ፈጣሪ የለም ይላል፤ አሸባሪና አክራሪ ነው፤›› በማለት ቤተ ክርስቲያኗ ዕውቅና የሰጠችውን ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ ጽንፈኞች ጋራ እያመሳሰሉ መወንጀላቸው ተገቢ እንዳልኾነና የማኅበሩ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ እንደኾነ ቅዱስ ሲኖዶሱ አረጋግጧል፡፡
‹‹ቆራጣ ደብዳቤ ይበቃዋል፤ ከመንግሥት ጋራ በመተባበር እስከ ጫፍ አድርሱልን፤ በቶሎ ቁረጡት›› እያሉ መጠየቅ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱንም “ከፈለጉ ቆባቸውን አስቀምጠው ወደዚያው ይግቡ” እያሉ መዝለፋቸውስ በምን መመዘኛ ነው ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ የሚኾነው በማለት የሚገልጹ የስብሰባው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ፓትርያርኩ የውሳኔውን አፈጻጸም ማገዳቸው፣ አድሏዊ እንደሚያደርጋቸውና በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ መንፈሳዊ አባትነታቸውንና ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው እንደሚኾን ጠቁመዋል፡፡

ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ የፌደራል ፖሊሶች እቃቸው በድንገት እንደተበረበረና እንደተወሰደ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ቃሊቲ እስር ቤትና አካባቢው በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ተከቦ እንደነበር የገለጹት ምንጮቹ ባልታወቀ ምክንያት የሁሉም እስረኞች እቃ በድንገት የተበረበረ ሲሆን በተለይም ፖለቲካ ነክ ጽሁፎች የሰፈሩባቸው ማስታወሻዎችና ሰነዶች መወሰዳቸውን ከእስረኞቹን ጠይቀው እንደተረዱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ብርበራም የታዋቂው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከ30 በላይ ገጽ የፖለቲካ ትንታኔ ጽሁፎች፣ እንዲሁም የአንዱ ዓለም አራጌ ማስታወሻዎች መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ ማስታወሻዎችንና ሌሎቹንም የእስረኞቹን ንብረቶች እያስፈረመ የወሰደ ሲሆን እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ እስር ቤቱ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
Image