የመስተዳድሩን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የከተማይቱን እቅድ ማሸጋሸግ ያስፈለገው ከፌደራሉ የእድገት እና ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) እቅድ ጋር ለማጣጣም ነው ተብሏል።

ጀርመን በቅርብ ዘመን ታሪኳ፣ ንጉሣዊ፤ የዘውድ አገዛዝ ሥርዓት ፤ ፋሺስታዊ አምባገነንና ጨቋኝ ኮሙዩኒስታዊ አገዛዝን አስተናግዳለች።

የአደጋ ደራሽ ሰራተኞች ካገኙት 82 አስክሪን መካከል በርካታ ሴቶች እና ሁለት ህጻናት ይገኙበታል። እንደ ከተማዋ ከንቲባ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ዛሪ ማለዳ በጀልባዋ ዋ ላይ ሳሉ እሳት ከተነሳ በኋላ፤ ለብዙ ሰዓታት ባህሩ ዉስጥ ነበሩ።አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ከኤርትራ እና ከሶማልያ እንደሆኑ ፖሊስ ተናግሯል።

(ከወልደሚካኤል መሸሻ)

ውድ አንባቢያን ይህን ጽሑፍ ጀምሬ ያጠናቀቅሁት ወደ እ . ኤ. አ በ2012 መጀመሪያ ነው። ለምን እስከአሁን አቆየኸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው ታዲያ። ተገቢ ጥያቄ ነው። የተለያዩ አቅጣጫዎችን የማየትና የማሰላሰል ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ ደግሞ በአነሰኛ መጽሐፍ መልክ ባሳትመውስ የሚል አሳብ እየተደቀነብኝ መጥቶ ነው። ሁለቱም ተራ በተራ ተፈታተኑኝ። የትኛውን እንደምመርጥ ማውጣት ማውረዱን ቀጠልሁ። ጽሑፍን እንድያዩትና አሳባቸውን እንዲሰጡኝ ለጥቂት ወዳጆቼ ላክሁ። አንዳንዶቹ ቶሎ ጽሑፉ እንዲወጣ የሚገፋፋ አሳብ ሰጡኝ። አንዳንዶች ከማስጠበቅ ውጭ ላያልፉ ሆኑ። በዚህ ላይ እያለሁ ለጽሑፉ መሠረት የሆነው የእምዬ ጠላት በመርዘኛ ብዕሩ ብቅ ማለቱን ሰማሁ። ወዳጆቹ ከወዲህ ወዲያ እያሉ መሆኑንም አዳመጥሁ። እርሱም የእምዬ ልጆችን የማባላቱን ሥራ ማጠናቀቁን ከወብሳይቱ ተመለከትሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዛሬዋ ቱርክ ኢያዞሎክ፣ በጥንታዊቷ የኤፌሶን ከተማ ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህች ከተማ እጅግ የታወቀች፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች አማንያን የሚጎርፉላት፣ ምስሏን የሚሠሩ አንጥረኞች ብር በቁና የሚያተርፉባት አርጤምስ የምትባል ጣዖት ትመለክ ነበር፡፡ ጳውሎስ እዚህ ከተማ ገብቶ ወደ አርጤምስ ቤተ መቅደስ በመጓዝ ‹‹አርጤምስ አምላክ አይደለችም›› ብሎ አስተማረ፡፡

ይህን ሲሰሙ የአርጤምስ ወዳጆች፣ ምስሏን በመሥራት የሚያተርፉት አንጥረኞችና፣ አርጤምስን ለመሳለም ከሚመጡ አማኞች ጠቀም ያለ ትርፍ የሚያገኙ ነጋዴዎች በከተማዋ ሑከት አስነሡ፡፡ ከተማዋ ተደበላለቀች፡፡ ከየአቅጣጫው ሕዝቡ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ጎረፈ፡፡ የሐዋርያት ሥራ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ብዙዎች ወዲያና ወዲህ እያሉ ይጮኻሉ፡፡ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ፣ የሚበልጡት ስለምን እንደተሰበሰቡ እንኳን አያውቁም ነበር፡፡››

አርጤምሳዊነት ባልተረዱት፣ ምስክርነት በማይሰጡበት፣ በማያውቁት ጉዳይ ላይ ሌሎች ስላደረጉት ብቻ፣ ወይም ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ሲያከናውነው ስለታየ ብቻ መደገፍ ወይም መቃወም፣ ወይም ያንኑ መሥራት ማለት ነው፡፡ የሚሰበሰቡበትን ምክንያት ሳያውቁ መሰብሰብ፣ የሚደግፉበትን ምክንያት ሳያውቁ መደገፍ፣ የሚቃወሙበትን ምክንያት ሳያውቁት መደገፍ፣ የሚወዱበት ምክንያት ሳይኖር መውደድ፣ የሚጠሉበትንም ምክንያት ሳይረዱት መጥላት ነው፡፡

ለምን? ሲባል ‹‹እኔ ከሰው እለያለሁ እንዴ›፣ ሰው ሁሉ እንዲህ እያደረገኮ ነው፣ መቼም አንድ ምክንያት አይጠፋም ብዬ፣ እነ እገሌ ሲሄዱ ሄድኩ፣ ዝም ብሎ ያስጠላኛል፣ እንዲሁ ጥሎብኝ እወደዋለሁ፤ ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ሆኖ፣ አህያ ሲጭኑ ሦስት ሆኖ ስለሚባል፣ እየተባለ ዝም ብሎ መደገፍና መቃወም ነው አርጤምሳዊነት፡፡

መመሪያ ስለሆነ፣ አድርጉ ስለተባልን፣ አሠራር ነው፣ የተለመደ ነው፣ በኛ ጊዜ አልተጀመረም፣ ድሮም የነበረ ነው፣ ምን ይደረግ ታዝዘን ነው፣ እኔ ከማን እበልጣለሁ፣ እኔ ከማን አንሣለሁ፣ ከበላይ የመጣ ነው፣ ውጡ ስለተባልን ነው፣ የሚሉ ነገሮችን የምትሰሙባቸው መሥሪያ ቤቶች ካሉ እነዚህ መሥሪያ ቤቶች በአርጤምሳውያን የሚመሩ ወይም የተሞሉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ይፈርማሉ፤ ለምን? ማብራራት አይችሉም፤ ይሰበሰባሉ፤ ለምን ተሰበሰባችሁ? ሳትሰበሰቡ ማድረግ አትችሉም ነበር ወይ? ሲባሉ ምክንያት ያለው መልስ የላቸውም፡፡ ይውደም ይላሉ፤ ማንን እንደሆነ አያውቁትም፡፡ ይቅደም ይላሉ ማን እንደሚቀድም ግን አልወሰኑም፡፡

አንዳንዶች ጓደኞቻቸው ያደረጉት፣ የተከተሉት፣ ያወሩት፣ የወደዱት፣ የጠሉት፣ የደገፉት፣ የተቃወሙት ሁሉ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ፡፡ አመክንዮ የላቸውም፡፡ የተደረገውን ከመድገም በቀር፡፡ ከዚህም አልፈው ከራሳቸው አእምሮ ይልቅ በሰው አእምሮ ያስባሉ፡፡ ሌላውን ሰው መከተል እንጂ የት ይወስደኛል፣ ለምን አከተለዋለሁ፣ ትክክል ነው ወይ? እኔ የተሻለ ሃሳብ የለኝም ወይ? ብለው አይጠይቁም፡፡ እንዲሁ ይከተላሉ፡፡

አርጤምሳውያን ሰውን እንጂ ሃሳብን አይከተሉም፡፡ ሰውን እንጂ ሃሳብን አይቃወሙም፡፡ ለእነርሱ ቁም ነገሩ እነማን አሉበት? የሚለው እንጂ ምን ነገር አለበት? የሚለው አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ድልድይ ላይ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ተሰብስበውም ወደ ድልድዩ ሥር ይመለከታሉ፡፡ እኔ ማዶ ቆሜያለሁ፡፡ ቀስ በቀስ ድልድዩ ላይ ቆመው የሚመለከቱት ሰዎች ቁጥራቸው እየበዛ መጣ፡፡ በኋላም በድልድዩ ላይ መኪና ማለፍ እስኪያቅተው ድረስ በሰው ተሞላ፡፡የምጠብቀው መኪና መጣልኝና በድልድዩ ላይ ለማለፍ ከሌሎች መኪኖች ኋላ ወረፋ ያዝን፡፡ መኪኖቹ በሕዝብ በተጣበበው ድልድይ ላይ እንደ ዔሊ እየተንፏቀቁ ነበር የሚጓዙት፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ነገሩ ሲጀመር አካባቢ ድልድዩ ላይ ያየሁትን ሰው አገኘሁትና የመስኮቱን መስተዋት አውርጄ ‹‹ምንድን ነው ጉዳዩ?›› ብዬ ጠየቅኩት፡፡

እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ትከሻውን እያራገፈ ‹‹የሆነ ነገር ሳይገባ አይቀርም›› አለኝ፡፡

‹‹አንተ አላየኸውም›› አልኩት፡፡

‹‹አላየሁትም፤ አንዳንዶች ከብት ነው ይላሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሰው ነው ይላሉ›› አለኝ፡፡

‹‹አንተ ምን ትላለህ›› አልኩት

‹‹እኔ እንጃ›› አለ፡፡

‹‹ይህንን ካላጣራህ ታድያ ለምን መጣህ››  አልኩት

‹‹ሰው ሲሰበሰብ ጊዜ ዝም ብዬ ነው የመጣሁት›› አለኝ፡፡

ቢያንስ ከሠላሳ ደቂቃ በላይ ቆሟል፡፡ እንዲህ ሰው ሳይጨናነቅ ነበር የመጣው፡፡ የመጣበትን ምክንያት ግን አያውቀውም፡፡ ሰው ተሰበሰበ፣ እርሱም አብሮ ተሰበሰበ፡፡ ሰው ወደ ድልድዩ ሥር ያያል፤ እርሱም ያያል፡፡ ምን እንደሚያይ ግን አያውቅም፡፡ ብቻ ያያል፡፡ አርጤምሳዊ፡፡

አርጤምሳውያን ነገሩ ሳያስቃቸው ነው የሚስቁት፡፡ የተሰበሰበው ሰው ከሳቀ ይስቃሉ፡፡ ቀልዱ ግን ላይገባቸው ይችላል፡፡ ባይገባቸውም ያጨበጭባሉ፡፡ ከዐዋቂ መካከል ከተቀመጡም ራስ ሲነቀነቅ ሲያዩ ይነቀንቃሉ፡፡ የሆነ ወረቀት ሲታደል ካገኙ ይቀበላሉ፤ ግን አያነቡትም፡፡ ማስተዋሻ ሲሰጥ ካዩ ተስገብግበው ይወስዳሉ፤ ግን አይጽፉበትም፡፡ የሆነ ምዝገባ ነገር ከተመለከቱ ወደ ሲኦል ለመሄድ ቢሆን እንኳን አያጣሩም፤ ብቻ ይመዘገባሉ፡፡ የሆነ ኮሚቴ፣ ማኅበር፣ ቡድን ሲመሠረት ዘለው ይገባሉ፤ ዓላማው፣ አሠራሩ፣ ማንነቱ አይመለከታቸውም፡፡ ዓላማቸው መቀላቀል ብቻ ነው፡፡

ኢሜይል አላቸው፣ የሚገናኙት ሰው የለም፤ ፌስ ቡክ አላቸው የሚለጥፉት ነገር የለም፡፡ ትዊተር አላቸው፣ የሚያስተላልፉት ነገር የለም፡፡ በሞባይላቸው ይቀዳሉ፣ እነርሱስ ከማን ያንሳሉ፡፡ ግን የቀዱትን አያዳምጡትም፡፡ እንዲያውም በቀጣዩ ደምስሰው ሌላ ይቀዱበታል፡፡ በሞባይል ፎቶ ያነሣሉ፤ ደግመው ግን አያዩትም፡፡ አርጤምሳውያን፡፡

አርጤምሳውያን ቤት የሚገዙት፣ መኪና የሚገዙት፣ ድርጅት የሚከፍቱት፣ ልብስ የሚገዙት፣ ውጭ የሚሄዱት፣ ርዳታ የሚረዱት፣ ድግስ የሚደግሱት፣ ሞባይል የሚቀይሩት፣ ምክንያት ስላላቸው አይደለም፡፡ እገሌ ስላደረገው፣ የዘመኑ ፋሽን ስለሆነ፣ ሰው እጅ ላይ ስላዩት፣ የሆነ ሰው ሲያወራለት ስለሰሙ ብቻ ነው፡፡  

አንድ ሰው መንገድ ዳር ቆሞ ይለምናል፡፡ ‹‹አግኝቼ ያጣሁ ነኝ›› ይላል ደጋግሞ፡፡ ከሚያልፉት መንገደኞች አንዱ ጠጋ አለውና ‹‹እውነት አንተ አግኝተህ ያጣህ ነህ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ይለምን የነበረው ሰውም ‹አዎ›› ሲል መለሰ፡፡ መንገደኛውም ‹‹ለመሆኑ ከዶሮ ብልቶች በጣም ጣፋጩ ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ሲለምን የነበረው ሰውም ‹‹ቆዳው›› ሲል መለሰለት፡፡ መንገደኛው ሰው ‹‹እውነትም አንተ አግኝተህ ያጣህ ነህ›› ብሎ ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጠው፡፡

ከጎኑ ቆሞ ሲያይ የነበረ አንድ ሰው ቀበል አደረገና ‹‹አግኝቼ ያጣሁ›› ማለት ጀመረ፡፡ 
ሌላ መንገደኛም ጠጋ ብሎ ‹‹አግኝተህ ያጣህ ከሆንክ ከበግ ሥጋ የሚጣፍጠው ምንድን ነው›› ሲል ጠየቀው

‹‹ቆዳ›› አለ አሉ፡፡

  © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።

ሊብያ ውስጥ የሚገኙ ከአምስት መቶ ሃምሣ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ሰሃራ በረሃ ውስጥ በሚገኝ እሥር ቤት መታጎራቸውንና እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለፅ አማርረዋል፡፡

Libya, refugees, Ethiopians, Eritreans

በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲዎች እጣ እያነጋገረ ነው
«የኢሕአዲግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ እንዲኖርና ሌሎች እንዲጠፉ የሚፈልግ ነው፣» ሲሉ አንድ የቀድሞ የቀድሞው የአረና ትግራይ ሊቀ-መሪ ተናገሩ።

አንዲት የሕወሃት ባለሥልጣን በበኩላቸው «ፓርቲዎቹ ይህን የሚሉት፣ ህብረተሰቡ ስለማይቀበላቸውና ድክመታቸውን ለመሸፈን ነው፤» ሲሉ መልስ ሰጡ። ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የድሃ ድሃ ተብለው ተመርጠው ኑሮቸውን በጉስቁልና የሚመሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከደርግ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድርስ በቀበሌ ቤቶች ሲገለገሉ ቢቆይም ያለ አግባብ በባለስልጣናት እየተቀሙ መሆኑ ለከፍተኛ ችግር እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት ደሀዎችን “ተተኪ ቦታና ቤት ይሰጣችሁዋል” በማለት ቤቶችን እየቀሙ ለባለሐብቶች እና ለራሳቸው በሊዝ እየገዙ አዳዲስ ህንጻዎችን …

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው በተዝረከረከ የንብረት አስተዳደር ሥርዓት ምክንያት ለብክነት፣ ለምዝበራ እና ለብልሽት የተጋለጡ ንብረቶችን ለመታደግ ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መጥፋቱን፣ የመስሪያ ቤቱ ባለስልጣናትም ያለጠያቂ በሙስና መዘፈቃቸውን  የፌድራል የስነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሺን ገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውስጥ የDCI እና የDN  የቧንቧ መገጣጠሚያዎች ቁመታቸው እና ውፍረታቸው …

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ ክልል ከ300 ሺ ሄክታር ያላነሰ መሬት በነጻ በሚባል ዋጋ የተረከበው የህንዱ የእርሻ ኩባንያ ካራቱሬ ፣ በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ስራ አለማከናወኑንና የባንክና ሌሎች እዳዎችን ለመክፈል አለመቻሉን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት የሆኑት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለጋዜጣው  እንዳስረዱት ፣ ካራቱሪ …

መስከረም ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ያደረገውን ግምገማ ውጤት ተከትሎ ማንኛውም የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኝ ከጥቅምት1 ቀን 2006 በፊት በማናቸውም የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ትምህርት እንዳይጀምሩ አስጠነቀቀ፡፡ ዛሬ ይፋ በተረደገው የጥናት ውጤት መሰረት ከ58 የማሰልጠኛ ተቋማት ዝቅተኛውን መስፈርት …

በአዲሱ የጥናት ውጤት መሠረት ፣ የየብስ የመሬትና የከባቢ አየር ሙቀት መጠን ፣ ከተተነበየው በላቀ ሁኔታ በሲሦ ይጨምራል ነው የተባለው። እ ጎ አ እስከ 2100 ዓ ም፤ ውቅያኖሶች፤ ከባህር ልክ በላይ ከ 26 -82 ሴንቲሜትር ከፍታ ይኖራቸዋል ማለት ነው።

የመራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ክርስቲያን ዲሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ፓርቲው በቅርቡ በተካሄደው የጀርመን የምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ አብላጫውን ድምፅ ቢያገኝም፤ ሀገሪቱን በጥምረት አብሮ ሲመራ የቆየው FDP ለምክር ቤት በቂ ድምፅ ባለማግኘቱ ከሌሎች የተቃውሞ ፓርቲዎች ጋር ለመጣመር ድርድር በማድረግ ላይ ይገኛል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር አሰምተዋል። ንግግራቸው በተለይ በኢራን እና በኑክልየር መርሀግብር ላይ ያነጣጠረ ነበር።

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ፣ በምሕፃሩ ኤራፓ፣ የብሔራዊ መግባባትን ጉዳይ አስፈላጊነትን ለማጉላት በአዲስ አበባ ለፊታችን እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶዋል። ኤራፓ ሰልፉን በመሥቀል አደባባይ ለማድረግ ቢያቅድም፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ እና

ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቋሚ ሲኖዶሱ የሚያጤነውን የአካዳሚክና አስተዳደር ዲኖች ሹመት አጽድቀዋል የመምህራኑ የመብራትና ውኃ አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ወር ሊሞላው ነው ደመወዛቸው እንደታገደ ነው ከሥልጣናቸው ተገልለው እንዲቆዩ በተወሰነባቸው ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እየተመራ ያለው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር÷ በሕንጻ እድሳት አመካኝቶ በኮሌጁ ቅጽር የሚኖሩ መምህራን ቤቶቻቸውን ለቀው እንዲወጡ ያስተላለፈው ትእዛዝና ቤቶቹን ካለቀቃችኹ በሚል በመምህራኑ ደመወዝ ላይ የጣለው እገዳ ውድቅ …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጫ ከወራት በፊት የነተሳውን ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል 40 ሰዎች በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ቢያዝም ፖሊስ አልፈታም በማለቱ ሰዎቹ ለተጨማሪ ወራት ከታሰሩ በሁዋላ ከቀናት በፊት መፈታታቸው ይታወቃል። ይሁንና የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ወደ መስሪያ ቤታቸው ሲያቀኑ ለ14ቱ የስራ ስንብት ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል። …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን  በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ውስጥ ስላለው የንብረት አስተዳደር አሰራር ስርዓት ጥናት አካሒዶ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መገኘቱን አረጋግጧል። በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው ችግር እቃዎች ተገዝተው ወደ ንብረት ክፍል ከመግባታቸው በፊት ንብረት ክፍሉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደረግ የሚያስችለውና ወጥነት ያለው የማሳወቂያ ስርዓት አለመሰራት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ግዥዎች ከተፈጸሙ …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሮፌሰር ባደግ በቀለ የሚመራውና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በተለይም የአመራር ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥ በማስተማር የሚታወቀው ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንሰቲትዩት  በትምህርት ሚኒስቴር ስር ካለው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ  ታውቋል። የሁለቱ አካላት ውዝግብ መነሻ ምክንያቱ ተቋሙ ሳይፈቀድለት በዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር በመጀመሩ ነው፡፡ የከፍተኛ ትምህርት …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የሪፐብሊካን እና የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በአዲሱ በጀት ላይ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ሳቢያ  በርካታ መስሪያ ቤቶችና  ተቋማት በከፊል እየተዘጉ ነው።  ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባላት በጀቱን ለማጽደቅ  የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ   የህክምና ፖሊሲ ማሻሻያ፤ በእግሊዝኛው አጠራር “ሄልዝ ኬር ሪፎርም” ሊዘገይ ይገባል  የሚል አቋምን እንደ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል። በዚህም ምክንያት …

መስከረም ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአገሩ የተመደቡ የትኬት ሽያጭ ወኪሎች የተሸጡና ያልተሸጡ ቁጥሮችን በመለየት እስከ ኦክቶበር 8፣ በስልክ ወይም በኢሜል እንድታስታውቁ እንጠይቃለን። ትኬቱን እስካሁን ያልገዛችሁ ውድ የኢሳት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች የቀሩትን ጥቂት ቀናት በመጠቀም ከአካባቢያችሁ ካሉ ወኪሎች ወይም በኦን ላይን ትኬቶችን መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንደወዳለን። ትኬቶችን ሽጣችሁ የጨረሳችሁ ደግሞ በኢሳት አካውንት ገንዘቡን ገቢ …

በዮናይትድ እስቴትስ ሬፑብሊካኖች እና ዲሞክራቶች የሀገሪቷን በጀት በተመለከተ አንድ የጋራ አቋም ላይ ሊደርሱ አልቻሉም።

መስከረም 12 2006 ዓም የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ተካሂደ አሸናፊውና ተሸናፊው ቢለይም እስካሁን ግን አዲስ መንግሥት አልተመሰረተም ። አሸናፊዎቹ እህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች አሁንም ተጣማሪ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው ።

ከአራት ዓመት በፊት በአፍሪቃ በተደረገ ጥናት መሰረት የህዝቡ ቁጥር 1 ቢሊዮን ማለፉ ተመልክቷል። ይህ አሃዝ ከ 35 ዓመት በኋላ በእጥፍ እንደሚያድግ ተተንብይዋል።

በጎ አ 2011 ዓ,ም በግብፅ የተቀጣጠለ አብዮት፤ ዋና ዓላማ በሲቢሉ ላይ የሚደረገዉን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም ነበር። ነገር ግን ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዛሪም፤ ወታደሩ በሲቢሉ ላይ የሚያካሂደዉ የሃይል እርምጃ እንደቀጠለ ነዉ። የሰላ ብዕር የያዙ ጋዜጠኞችም፤ ሥራቸዉን እንዳይሰሩ ይታፈናሉ።

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Obamacare analysis – Dr. Bisrat Hailemesqel

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው አመራሮች በዛሬው እለት ተሰብስበው ትናንት እሁድ ፓርቲው የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ውጤት ገምግመዋል። መስቀል አደባባይ ብንሄድ ኖሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል የተናገሩት አቶ ደንኤል፣ በከፍተኛ አፈና ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከ80 ሺ በላይ በሆነ ህዝብ መካሄዱ የተሳካና ለሚቀጥለው ሰልፍ ፍንጭ የሰጠ፣ ህዝቡ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንና ከፓርቲያቸው …

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው። የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት …

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው። ብሮችን የሚቀብሩ …

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሣምንቱ መገባደጃ ላይ የተከናወኑ ዓበይት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች በተለይም የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ዋነኛ ትኩረታችን ይሆናል። የጀርመኑ ቡንደስሊጋ እና የበርሊኑ ማራቶን ውጤቶችን የሚመለከቱ ዘገባዎችንም አጠናቅረናል።

የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሳይሆን በፈረንሳይኛ፥ በእንግሊዝኛ ወይም በሌላ የአዉሮጳ ቋንቋ ለሚዘግቡት አልጠፉም።