ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው! ግርማ ሞገስ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ […]
‹‹የሰባት ወይራ ሆቴልን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዳይወስድብን ለመለመን›› በሚል በደብሩ አስተዳደር ያስወሰኑትን ግማሽ ሚልዮን ብር፣ ሢመተ ጵጵስናውን ይቃወማሉ የሚባሉ አባቶችን የማግባባት አቅማቸውን እንደሚያጠናክሩበት ጠቁመዋል፡፡ ከቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በተፃራሪ በሥልጣን ላይ የቆዩትና በአስተዳዳሪው ውሳኔ እስከ 7000 ብር በወር የሚከፈላቸው አብዛኞቹ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላት እና የጽ/ቤቱ ሠራተኞች፣ በአስተዳዳሪው የግማሽ ሚልዮን ብር ጥያቄ እንዲስማሙ በ‹ጥቅማቸው› መገደዳቸው ታውቋል፡፡ …![]()
UDJ leadership arrested and released
ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለሰአታት ታግተው አርፍደዋል። ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ ለፓርቲው ፈቃድ ቢሰጥም ፣ ፖሊስ በበኩሉ ፓርቲው ቅስቀሳ ለማድረግ ከፈለገ …
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ታስረው የነበሩ 40 ሰዎች ተፈቱ። አስተባባሪ ናቸው በሚል የታሰሩት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ ግን ሳይፈቱ ቀርተዋል። ሰዎቹ ከ3 ወራት በፊት ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ውሳኔ ቢያስተላልፍም ፖሊስ በራሱ ስልጣን አልፈታም ብሎ መቆየቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ እስረኞቹ በትናንትው እለት ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው …
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል። መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል። በጉዳዩ ዙሪያ …
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የያዘውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ወደሁለት ዓመት ካጠፈ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ያለውን መልሶ ማልማት ሥራ በሰፊው እንደሚያከናውን አስታውቆአል፡፡ በዚህ የመልሶ ማልማት ሥራ በመሃል ከተማ የሚገኙ በርካታ ቁልፍ ቦታዎች የሚፈርሱ ሲሆን ነዋሪዎችም የመፈናቀል አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ …
መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ከጀርመኑ ባዉሃዉስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊመር እና ከደቡብ ሱዳኑ ጁባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ተማሪዎች አማካይነት በ10 ቀናት ውስጥ የባለ አንድ ፎቅ ተገጣጣሚ ሕንጻ ገነባ፡፡ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነውን ቴክኖሎጂ በነገው ዕለት ይፋ ለማድረግ ፕሮግራም ተይዞአል፡፡ …
ከአራን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ ጋር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ መነጋገራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስታወቁ፡፡
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ዓመራር አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ኣበባ ላይ ለጠሩት ሰልፍ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዳልቻሉ ኣስታወቁ በኢትዮፕያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ የፓርቲው ዓመራሮች ዛሬ ለተወሰኑ ሳዓታት በፓሊሶች ታግተው መለቀቃቸውን ፓርቲው ኣስታውቋል ።
ያን ፊሊፕ ቫይል ተወልዶ ያደገው በክሬፌልድ ከተማ ጀርመን ሀገር ሲሆን ጀርመናዊው ወጣት ገና የ14 ዓመት ልጅ ሳለ ነው ከጓደኛው ጋ በመሆን ለኢትዮጵያ ገንዘብ ማሰባሰብ የጀመረው። ይሄው ወጣት በአሁኑ ሰዓት «ኤምራ እና ዳቦ» የሚል ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ በመቅረፅ ላይ ይገኛል።
በኬንያው የናይሮቢ ግዙፍ የገበያ ማዕከል ውስጥ አሸባብ የፈፀመው ጥቃት የአሜሪካንንና የኬንያን የፀጥታ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል ። በሌላ በኩል በዚሁ ጥቃት ሶማሊያውያን አሜሪካውያን ተሳትፈዋል መባሉ በአሜሪካ የሚገኙ ሶማሊያውያንን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷል ።
ወለላዬ
ሰፈራችንን መሀል ለመሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው መንገድ በስተቀኝ ሃያ አንድ መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ቤቶች ነዋሪዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የስጋ ዝምድና አለን። በተለይ በአንድ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ስምንት ቤተሰቦች ደግሞ የቅርብ – በጣም የቅርብ ዘመዳሞች ነን።
አብርሃም ያየህ
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊና የድርጅቱ ያመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ከቅርብ ቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለመጠይቅ አማካኝነት በሰነዘሯቸው የተለያዩ አብይ ሃሳቦችና፣ ከቃለ-መጠይቁ ውጭ ነገር ግን ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች፣ መሰረት በማድረግ ለመወያየት ወስኛለሁ።
የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዛሬም ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ አብረዋቸው የታሰዩት አመራሮችና አባላት እንደሚከተለው እንዘረዝራለን በፖለስ የታሰሩ አመራሮችና አባላት በከፊል ========================= ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የተከበሩ ግርማ ሰይፉ – የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ስዩም መንገሻ – የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት […]
የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና ብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፣ተክሌ በቀለ፣ ዳንኤል ተፈራ፣ አበበ አካሉ፣ ስዩም መንገሻ፣ሀብታሙ አያሌው፣ብሩ ብርመጂ የተባሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አራዳ በሁለት የፖሊስ ፒካፖች ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ እገታውን የሚያሳየውን ቪዲዮ ከደቂቃዎች በኋላ እንለቃለን፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በእስር ላይ ቢገኙም የፓርቲው አባላት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሜጋፎን በመታገዝ የቤት ለቤት […]
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው ደመራ በአል በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። በአዲስ አበባ የሀይማኖቱ አባቶች ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የውጭ አገር ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተከብሮአል።
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል። በቅርቡ በወልድያ …
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደልጊ አካባቢ ከግጦሽ ሳር ጋር በተገናኘ በተነሳ ግጭት የአካባቢው ኗሪዎች በወሰዱት የመከላከል እርምጃ የፖሊስ አዛዡ ህይወት አልፏል፡፡ የፖሊስ አዛዡ ነዋሪዎችን “ መሬት የመንግስት በመሆኑ በተከለከለ ቦታ ላይ ከብቶችን ማሰማራት እንደማይችሉ መናገሩን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ” መሬት የኛ መሆኑን ነው የምናውቀው፣ መሬት የህዝብ እንጅ የመንግስት አለመሆኑን ነው …
(ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር) የመስቀል በዓል ትውፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመስቀል ያለውን የጠለቀ ዕውቀት ያሳያል የመስቀል በዓል አከባበር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያልደረሰችበት፣ ወንጌል ያልሰበከችበት የኢትዮጵያ ክፍል እንዳልነበረ አመልካች ነው የመስቀል በዓል አከባበር መንፈሳዊነቱንና ባህላዊ ገጽታውን ሳይለውጥ ለዘመናት የቀጠለበት ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትምህርት በሕዝቡ ዘንድ እንዲሠርጽ ካደረገችው ጥረት ይመነጫል የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ የሚከበረው ከየትኛውም …![]()
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የኮምኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ከቻይና ከህዝብ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሁለቱም ልማታዊ መንግስታት በመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀን ረገድ የሚሰሩት ብዙ ስራዎች አሉዋቸው ያሉት አቶ ሬዲዋን፣ የቻይናን ብሄራዊ ቴሌቪዥንና የዢኖዋን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። ቻይና …
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ዲቪ 2015 በፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 1 ተጀምሮ ኖቬንበር 2 ይጠናቀቃል ብሎአል።
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተከል ዞን በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በአዊ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ መብራት እንደተቋረጠባቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። በፓዊ የኤሊክትሪክ ሐይል መቆጣጠሪያ እና ማከፋፋያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙት እና የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወረዳዎች፤ወንበራ ፤ ጉባ ፤ድባጢ ፤ ግልገል በለስ ፤ፓዊ ፤ ዳንጉር ፤ ማንኩሺ ፤ማንዱራ ፤ ማንቡክ፤ …
አማኑኤል ዘሰላም
በደሴ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ፍቼ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ሮቢ/ባሌ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዳ፣ ጂንካ፣ አርባ ምንጭ … ሰላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። በአዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ወሊሶ፣ አሶሳና ጋምቤላ፣ እቅዱ ውስጥ የነበሩም ቢሆንም በገንዘብ አቅም ምክንያት ለጊዜው ሰልፎች ሊካሄዱ አልቻሉም።

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ “የአላዊት ጎሳ” ይባላል። አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው። በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል። እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም። አላዊቶችም ቢሆኑ “አልሸሹም ዞር አሉ” ናቸው።
ግርማ ሞገስ
በክፍል አንድ እንዳነበብነው የዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ ተርቦ ከመሞቱ በፊት የሚቀልቡት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ነበሩት። የፖለቲካ ኃይል ምንጮቹ መድረቅ ተርቦ እንዲሞት አድርገውታል። እንደ ዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ መንግሥትም የፖለቲካ ኃይል ምንጮች አሉት።
ኬንያ፤ በመዲናዋ በናይሮቢ ዌስትጌት በተባለው ግዙፍ የገበያ ህንጻ ውስጥ ፣ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሶማልያው አሸባብየአሸባሪዎች ቡድን፤ ቢያንስ72 ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ ፣የ 67 ቱ ሰለባዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል ። የ3 ቀን የኀዘን ጊዜም ታውጆ ተግባራዊ በመሆን
የዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም የበርካታ ድምጻውያንን ዜማዎች እና ሙዚቃ ነክ ዜናዎችን ያስተናግዳል፡፡
የፖለቲካ ኃይል ምንጮች (ክፍል አንድ/2)
ግርማ ሞገስ
የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል።
«መስቀል አብርሃ!–»
የዘንድሮው ፤ የ 2006 ዓ ም፣ የደመራ በዓል ፣ ከቀትር በኋላ ፣ ማምሻውን ተክብሯል።
በንግሥት ዕሌኒ ትእዛዝ ተቆፍሮ ፤ በኢየሩሳሌም የተገኘው ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሠቀለበት መሥቀል፣ የሚታሰብበት በዓል፣ ሃይማኖታዊ፣
ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)
የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም ሀገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው።
የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ ኣበባ ከተማ
ለማካሄድ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማጨናገፍ መንግሥት ከወዲሁ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሰልፉን
ግን ከማካሄድ ወደኃላ እንደማይል የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ርነጋሶ ጊዳዳ አስታወቁ ።
እንደ ምክትል ሚኒስትሩ የዓለም ኃያላን መንግሥታት በህጉ መሠረት የኢራን የኒዩክልየር መብት እስካከበሩ ድረስ ለኒዩክልየር ውዝግቡ መፍትሄ ማግኘቱ አዳጋች አይሆንም ።
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
ከሀገር ርቀዉ፤ በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሀገራቸዉን ቋንቋ ባህልና የማንነታቸዉን መለያ ለልጆቻቸዉ እንዴት እና በምን ዘዴ ያወርሳሉ?
የዓለም ዜና 260913
አንድነት እና የ33 ፓርቲዎች በጋራ የጠሩትን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ለቅስቀሳ ዛሬ ማለዳ ወደ ፈረንሳይ አካባቢ ተንቀሳቅሶ የነበረ መኪና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እውቅና ለተቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገውን ቅስቀሳ ለመቅረጽና የህዝቡን ስሜት ለመመልከት ካሜራና ላፕ ቶፕ በመያዝ ከቀስቃሽ ቡድኑ ጋር የተጓዘው የፍኖተ ነጻነት ጋዜጠኛ አሸናፊ አሳምነው ከሌሎቹ የተለየ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ በስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ […]
በደሴ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ፍቼ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ሮቢ/ባሌ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዳ፣ ጂንካ፣ አርባ ምንጭ …ሰላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። በአዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ወሊሶ፣ አሶሳና ጋምቤላ፣ እቅዱ ዉስጥ የነበሩም ቢሆንም በገንዘብ አቅም ምክንያት ለጊዜዉ ሰልፎች ሊካሄዱ አልቻሉም። መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም ትኩረቱ አዲስ አበባ ፊንፊኔ ይሆናል። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የጀመረዉ የመጀመሪያዉ ዙር የሶስት ወራት እንቅስቃሴ የሚደመደምበት ! […]
(ተመስገን ደሳለኝ)
ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አ ንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
Hailemariam Desalegn, UNGA, ICC
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ሽሮ ሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ከገለጹ ከሰአታት በሁዋላ ፣ ሊቀመንበሩ ማምሻውን ተፈትተዋል። አንድ ግለሰብ “የፓርቲው የሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ግብረሀይል አባላት ያለፍላጎቴ ፎቶግራፍ አንስተውኛል” በሚል ክስ መመስረቱን ተከትሎ ፣ የቅስቀሳ አባላቱ መያዛቸውንና …
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል። ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ …
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አክራሪነት የመንግስትን ተቋም በማፈራረስ እና ተከታዮቹ ነፍጥ አንስተው …
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡ በኢህአዴግ ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡ ይህ …
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ከቀኑ 14 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ጭምር በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የኢሳት 3ኛ ዓመት በዓል ላይ ‘ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ኢሳት ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደደረሰ በስፋት ያብራሩት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ፤ኢሳት ለወደፊቱ መድረስ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተሰነቀውን ራዕይ ጠቁመዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች …
Hailemariam Desalegn, Speech, UNGA