የአሜሪካ ሶማሊያውያን ስጋት

በኬንያው የናይሮቢ ግዙፍ የገበያ ማዕከል ውስጥ አሸባብ የፈፀመው ጥቃት የአሜሪካንንና የኬንያን የፀጥታ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል ። በሌላ በኩል በዚሁ ጥቃት ሶማሊያውያን አሜሪካውያን ተሳትፈዋል መባሉ በአሜሪካ የሚገኙ ሶማሊያውያንን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷል ።