ሰበር ዜና፤ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ታሰሩ – ፍኖተ ነጻነት
የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና ብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፣ተክሌ በቀለ፣ ዳንኤል ተፈራ፣ አበበ አካሉ፣ ስዩም መንገሻ፣ሀብታሙ አያሌው፣ብሩ ብርመጂ የተባሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አራዳ በሁለት የፖሊስ ፒካፖች ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ እገታውን የሚያሳየውን ቪዲዮ ከደቂቃዎች በኋላ እንለቃለን፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በእስር ላይ ቢገኙም የፓርቲው አባላት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሜጋፎን በመታገዝ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እያደረጉ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው በራሪ ወረቀትም በመሰራቸት ላይ ይገኛል፡፡ millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ