‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ››
መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፡፡
አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋዕትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም፡፡ አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም፡፡
ትግሉ ሰላማዊ እና ሰላማዊ ብቻ እንዲሆን ከአንድ ወገን ብቻ (ከተቃዋሚዎች በኩል) እየተደረገ ያለውን ጥረት ኢህአዴግ እንደፈሪነት እየቆጠረው በትዕቢት ተወጥሮ ያስራል ይገላል፡፡ ነገም ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ነገር አያደርግም፡፡
ፓርቲያችን አንድነትን ለጀሌዎችህ ስትሰጣቸው እጃችንን አጣጥፈን ዝም ብለን አናይህም በሚል ነገ የአንድነት አባላቶች እና ደጋፊዎች ሰልፍ ሲወጡ ወያኔ እንደለመደው ያስራል፡፡
ዛሬ በልሳኑ ኢቲቪ/ኢቢሲ ደግሞ ሰማያዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እሰራለሁ አመፅንም እጠራለሁ ብሏል ሲል በሬ ጥጃ ወለደ ዲስኩሩን ደስኩሯል፡፡
አንድነትን ለእነ ትዕግስቱ አወሉ ሰጥቼ እውነተኛ አመራሮቹንም አስሬ አፈርሰዋለሁ፤ ሰማያዊን ደግሞ አመፅ ሊጠራ ነው በሚል ፓርቲውን አግዳለሁ አመራሮቹንም አስራለሁ በሚል ስሌት እየሰራ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኗል፡፡
እንግዲያው ፓርቲዎችን ከዘጋ፣ ህጋዊ አመራሮችንም ካሰረ እና ሰላማዊውን መንገድ ከዘጋው የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን ይቀይራል፡፡
ጓዶቹ የታሰሩለትን ፓርቲ፣ አላማ እንዲሁም ትግል ወደጎን ትቶ የሚሄድ የለምና አሁን ትግሉ ሞትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ እና ነፃነትን የመሻት ነው፡፡ ‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ›› እንዲል ጋዜጠኛው ነቢዩ፡፡

አንለያይም ሞትም ቢመጣ!!!
‪#‎እናቸንፋለን‬ Eyasped tesfaye

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት በምርጫው ለመወዳደር መወሰኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዴግ እያደረጉት ያለውን ስውር ደባ እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቢቆይም መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምክንያት ‹‹መብታችንን ለማስከበር አንለምንም›› በማለት በነገው እለት ማለትም ጥር 17/2007 ዓ.ም በ5 ከተሞች የጠራውን …

የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት የነገው የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ውሳኔ አስተላለፈ Read more »

ወደ አስራ አንድ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች አንድ ኮሚቴ አዋቀሩ። ይህ ኮሚቴ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ዶር ሰለሞን ተርፋና ዶር ስብሐት የሚመራ ነበር። ይህ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የነበረው አለመረጋጋት አገሪቷን ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይወስዳት፣ በወቅቱ ይገዛ ከነበረው ከኢሰፓ/ደርግ እንዲሁም ከሽምቅ ተዋጊዎች (ሻእቢያና ወያኔ) የተወጣጣ ፣ የሽማግሌ ጊዚያዊ መንግስት እንዲቋቋም የሚጠይቅ ነበር። “ይቅር ለ እግዚአብሄር “ በሚል መንፈስ መቀባበል እንዲመጣ ነበር ምሁራኑ የጠየቁት። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ወያኔ ከትግራይ ፣ ሻእቢያ ደግሞ ከከረን አላለፉም ነበር። ያ ማለት ወታደራዊ የበላይነት የነበረው ደርግ ነበር ማለት ነው። ምሁራኑ ይሄንን የእርቅ ሐሳብ ሲያቀርቡ የሽምቅ ተዋጊዎችን ጥንካሬ በማየት ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ደርግ በሕዝብ እየተተፋ መምጣቱን በማየታቸው፣ አገሪቷም እንደ ላይቤሪያና ሶማሊያ እንዳትሆን በመፍራት ነበር።

አርብ ከሰዓት በኋላ ነው። መስሪያ ቤቶች የተዘጉ ይመስላል። ሁሉም በየቤቱ ገብቷል። ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ለሕዝብ ንግግር ሊያደርጉ ነው። በፊታቸው ለነርሱም መዉጭ መንገድ፣ ለሽምቅ ተዋጊዎችም እንደዚሁ የሚበጅ፣ የመፍቴሄ ሀሳብ ቀርቧል። “ኮሎኔሉ ለዚህ ቀና ሐሳብ ምን ይመልሱ ይሆን?” ብለን መጠባበቅ ጀመርን። አራት ሰዓት ሙሉ ተናገሩ። “የአገር ጉዳይ የባልና የሚስት ጉዳይ አይደለም፣ በይቅር ለእግዚአብሄር የሚፈታው” ብለው እነ ፕሮፌሰር መስፍንን ወረፏቸው። አንድ የብነመር ሰው የሰጠኝ ብለው አንድ ጊራጌ መዘዙና አሳዩን። አይ ፉከራ !. አይ ጀብደኝነት !!!!!

ብዙም አልቆየም፣ ሰራዊቱ እየተከፋፈለ፣ እየከዳቸው ፣ ሽምቅ ተዋጊዎችም ተዋግተው ሳይሆን እንደ ማራቶን እየሮጡ፣ ጎንደር፣ ወሎ …እያሉ አዲስ አበባ አካባቢ ደረሱ። እንደ አጼ ቴዎድሮስ እስከመጨረሻው ጥይት ጠጥቼ እሞታለሁ ያሉት ኮሎኔሉ ፈረጠጡ። “ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት” ብለው ራሳቸውን የጠሩት ወያኔዎችም፣ ስኳር እየቃሙ በጢቢጢቢ ጫማ፣ አዲስ አበባን ተቆጣጠሩ። የኢሰፓና የደርግ አመራሮች ከያሉበት እንደ ጥንቸል ታድነው ተያዙ። የነበራቸውን ነገር በሙሉ አጡ። ወደ ወህኒ ተወረወሩ።፡አይወድቁ አወዳደቅ ወደቁ።

አሁን ሕወሃቶች፣ ተመሳሳይ ጀብደኝነት እያሳዩ ናቸው። ህዝብ እየተፋቸው ነው። ሕዝብ በደርግ ላይ ከነበረው የበለጠ ጥላቻ በነርሱ ላይ እያደረበት ነው። ብዙ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች አገዛዙ ወደ ብሄራዊ መግባባት እንዲመጣ እየመከሩና እየተማጸኑ ነው። ሆኖም ሕወሃቶች ልባቸው በጣም አብጧል። ማሰብ ተሰኗቸዋል። የትላንትናዉን ረስተዋል። ኢትዮጵያዉያን ወደ አመጽና ጦርነት እየገፋፏቸው ነው። “እስቲ ወንድ ከሆናችሁ ኑና በጦርነት ግጠሙን” እያሉ ነው። የሰላም በሮችን በሙሉ እየዘጉ ነው። ከነርሱ የተለያ ሐሳብ ያላቸው በሚቆጣጠሩት ሜዲያ፣ ትላንት ደርግ የፍየ ወጠጤ እያለ ሲፊከርና ሲያስፈራራ እንደነበረው፣ ዶኩመንተሪ ምጥርቅሾ እያሉ፣ እያስፈራሩ ነው። ዜጎች በአገራቸው ተሸማቀው እንዲኖሩ እያደረጉ ነው። በአጭሩ አባባል ዳግማዊ ግራዚያኒ እየሆኑ ነው።

በአገር ዉስጥ በምርጫ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ህዝቡ የፈለገውን እንዲሽርና እንዲሾም የሚደረግበት ሲስተም ከሌለ፣ ሌላው አማራጭ ጦርነትና አመጽ ነው። “የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ” እንዳለው አብርሃ ደስታ። በአገር ቤት ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ፓርቲ በማገድ፣ የፓርቲዉን ሕጋዊ ሰርተፊኬት፣ እነርሱ ራሳቸው ላደራጁት ተለጣፊ አንድነት ለመስጠት ወስነዋል የሚል መረጃ አለ። የአንድነት ፓርቲም ይሄን በመቃወም ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ እሁድ ሰልፍ ጠርቷል። ለአስተዳደሩ አሳዉቋል። ሆኖ አገዛዙ በሜዲያ መዛቱን ቀጥሏል። አንድነቶ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስዱም፣ ዳኞች ፈርተው ጉዳዩን ለማያተ ፍቃደኛ አልሆኑም።

እንግዲህ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚደረገው ትግል ጫፍ ላይ ደርሷል። ሕወሃት ተጠንቆ እርምጃ እንዲወስድ እመክራለሁ። በአንድነት ፓርቲ ላይ ማናቸዉንም አይነት ሕግ ወጥና አምባገነናዊ እርምጃ ቢወስድ፣ አመራር አባላቱ ቢታሰሩ፣ በአገራች ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዳከተመ፣ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የመታገል በር ሙሉ በሙሉ እንደተዘጋ የሚገልጽ አዋጅ እንዳወጀ ነው የሚቆጠረው።

ወያኔዎች አዲስ አበባ ሲቆጣጠሩ «ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት» ነበር ያሉት። ልክ እንደያኔውም ብሶት፣ የግፍ ቀንበር፣ ጭቃና፣ ባርነት እጅግ በጣም ብዙ ሰራዊቶችን ይፍጥራል። ስለዚህ ረጋ ብለው እንዲያስቡ የኮሎኔል መንግስቱ አይነት ስህተትን እንዳይሰሩ እመክራለሁ። ጀብደኝነት ለማንም አይጠቅምም። እነርሱም ጥብቆ እንደታጠቁት ሌላው ጥብቆ ታጥቋል። ለሁላችንም ሰላምና መግባባት ይበጀናል። እሁድ የአንድነት ሰልፍ በሰላም ተጠናቆ (ለምን ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ነውና) ምርጫ ቦርድም በአንድነት ላይ የከፈተውን ዘመቻ አቁሞ፣ ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን ሥራ ይጀመር። አለበለዚያ ግን እነርሱ ራሳቸው በለኮሱት እሳት መጥፊያችውን እንዳወጁ ይወቁ።

“አቶ በላይ በዝረራ ነው የጣለኝን ፣ ጨብጬም ስሜዋለሁ” ትግስቱ አወል

ይህ በአቶ ትግስቱና በአንድ የአንድነት ደጋፊ መካከል ከተደረገ ልዉውጥ የተወሰደ ነው። በዚህ ልዉውጥ አቶ ትግስቱ ለፕሬዘዳንትነት ሲወዳደሩ ፣ በምክር ቤቱ አንድ ድምጽ ብቻ በማግነት (እርሱም የርሳቸው ብቻ ድምጽ) በተሸነፉበት ጊዜ ስለ አቶ በላይ ፍቃዱ የተናገሩት ይገኝበታል።

ደጋፊ

“ቃለ መሐላ ሲያደርጉ የሚይሳይ ፎቶ አየሁ። የአንድነት ሊቀመንበር ነኝ ብለው እየተናገሩ ነው። ስልጣን የሚወዱ ሰው እንደሆኑ ብዙዎች ይናገሩ ነበር። የምርጫ ቦርድ ያሰናከለዉን የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት ቢሳካ ኖሮ፣ ዉህዱን ፓርቲ በፕሬዘዳንትነት ለመምራት ራስዎትን እጩ አደረጉ። ዉህደቱ እንደማይሆን ሲታወቅ ኢንጂነር ግዛቸው እንደገና ካቢኔያቸውን ሲያዋቅሩ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ። ለጊዜው የስልጣን ጥሞትን ትንሽ አረኩ። ዉች ካሉ ደጋፊዎችም ጋር መገናኘት ጀመሩ። ኢንጂነር ግዛቸው ከሃላፊነት ሲለቁ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴያቸውን በተኑ። ለጥቂት ሳምንታት ያገኙት ስልጣን በማጣትዎት ተከፉ። በምክር ቤቱ በሕጉ መሰረት አዲስ ሊቀመነበር መመረጥ ስላለበት፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እጩዎች ቀረቡ። እርስዎም እንደጋና እጩ ሆነው ቀረቡ። ከምክር ቤት አባላት አንድ ሰው ለርስዎ ድምጹን ሳይሰጠ ቀረ። አንድ ድምጽ ብቻ እርሱም እርስዎ ለራስዎት የሰጡትን ድምጽ ብቻ አገኙ። በአባላት ባለመመረጥዎት የተነሳ ራስዎትን መጠየቅ ሲገባዎት አኮረፉ። በዉስጥዎት በአንድነት ፓርቲ ላይ ቂም ቋጠሩ። አንድነት ደንቡን በማሻሻል የኮረም ቁጥር ማስገባት አለበት የሚል ሕገ ወጥ ጥያቄ ባቀረቡበት ጊዜ፣ አንድነት በትንሽ ነገር ግብግብ አያስፈልግም በሚል፣ ለአባላት ስልጠና ለመስጠት በማሰብ የጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ። እርስዎም በጉባኤ ተገኝተው ፣ እርስዎ አንድ ድምጽ ሲያገኙ 26 ድምጽ፡ያገኙትን የአቶ በላይን አመራር ተቃዉመው ጠቅላላ ጉባዔው አመራሩን እንዲመርጥ ጠየቁ። ጠቅላላ ጉባኤ በርስዎ ፊት ምክር ቤቱ በደንቡ መሰረት ሊቀመነበሩን መምረጡን ትክክል እንደሆነ አረጋገጠ። በድጋሚም የአቶ በላይን ምርጫ አጸደቀ። እርስዎም አፈሩ። በዲሞክራሲና በሐሳብ ተሸነፉ።”የተማሩ ኖት። የማስተርስ ዲግሪ አልዎት። እንደ አዋቂ ቢያስቡና ቢያስተዉሉ ኖሮ ፣ ሌላ ጊዜ የአባላትን ድጋፍ በማግኘት ወደ ስልጣን ለመምጣት ይሰሩ ነበር። ሆኖም እልህ ተሞሉ። ህዝብን እያሸበረ ካለ ቡድን፣ ጋር ከሕወሃት ጋር አበሩ። “

አቶ ትግስቱ

ተወዳድረህ ሰው አልመረጠህም ያልከኝ፤ እውነት ነው፤ በዴሞክራሲያዊ ሂደት የሚጠበቅ ነው ። በመሆኑም እኮራለሁ እንጂ አላፍርበትም፡፡ በእለቱም በዝረራ የጣለኝን አቶ በላይ ፈቃዱን ጨብጬ ስሜዋለሁ ምርጫው ዴሞክራሲዊ እንደሆነ ገልጬ መልካም ምኞቴን ገልጫለሁ፡፡ በመቀጠልም በበላይ ክብኔ ስር ምክትል ሃላፊ ሆኜ እስከ ታህሳስ 3ቀን 2007 ጉባኤ እስከተደረገበት ድረስ አብሬ ነበር፡፡ እኔ ከፓርቲው ሳይሆን በሃሳብ ከነበላይ የተለየሁት በጉባኤው ወቅት ይህ ዛሬ በምርጫ ቦርድ የቀረበው ጥያቄ እንዳይመጣ በማሰብና ፓርቲዬን ለማዳን ያቀረብኩትን ደንባዊ አስተያዬት በእውቀት ሳይሆን በስሜት በ……… ጩኸት ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በጩኸት የሚደረግ ውሳኔ ዴሞክራሲያዊ ተደርጎ በየዋሆች ሊወሰድ ስለሚችል፡፡ በድምፅ ተቃወምኩት፡፡ ከጉባኤው በኃላ በ ………… ፊታውራሪነት አንድነት የአባላቱ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች አክሲዮን በሚመስል መልኩ አመራሩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ስገነዘብና በተለይ ……………. የፓርቲውን አባላት በንቀት ሲመለከትና የአመራሩ መታበይ ምክንያት የእነ አቶ አየለ ስሜነህን ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ትግል ተቀላቀልኩ፡፡”

እንግዲ እዚህ ላይ አቶ ትግስቱ ሐሳባቸውን ጠቅላላ ጉባኤው እንዳልተቀበለው አስቀምጠዋል። በአቶ በላይ በዝረራ እንደተሸነፉ ይናገራሉ። በዲሞክራሲ እንደሚያምኑም ጽፈዋል። አድንነትን ከምርጫ ቦርድ ከሚመጣ ችግር ለማዳን ስል፣ አቶ አየለ ስሜነህ የሚመሩትን ቡድን እንደተቀላቀሉ ይናገራሉ።

አቶ አየለ ስሜነህ በምርጫ ቦርድ የሚደረገው ደባ ስላልተመቻቸው በምርጫ ቦርድ በኩል በሕወሃት የሚደረገውን በሜዲያ በይፋ አጋልጠዋል። አቶ ትግስቱ ግን በምርጫ ቦርድ ገጸ በረከት የአንድነት ስርተፊኬት ለመቀበል፣ በምርጫ ያላገኙትን በምርጫ ቦርድ ስጦታ ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው። አንድነትን ከምርጫ ቦርድ ለማዳን ሳይሆን የምርጫ ቦርድ መሳሪያና “ሰራተኛ” ሆነው አቶ ትእግስቱ ትልቅ ታሪካዊ ስሀተት እየሰሩ ነው።

በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው ውዝግብ ግንባር ቀደም ሚና ያላቸው አቶ አየለ ስሜነህ የአሰላለፍ ለውጥ አደረጉ፡፡ የእነትእግስቱ አወልን ቡድን በማደራጀት ቀዳሚ ሚና የነበራቸው አቶ አየለ፤ ሰልፋቸውን ቀይረው የነበላይ ፈቃዱን ቡድን መቀላቀላቸውን ትላንት የአንድነት ልሳን ለሆነው ለ‹‹ፍኖተ-ነፃነት›› በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡ አቶ አየለ የቅሬታቸው መነሻ የሆኑት ጉዳዮች ያልተመለሱ ቢሆንም ወቅቱ የምርጫ በመሆኑ እና ፓርቲውን ከአደጋ ለማዳን ሲሉ የአሰላለፍ ለውጥ እንዳደረጉ ገለጸዋል፡፡ ‹‹ፍኖተ-ነፃነት›› የለቀቀውን የአቶ አየለ ስሜነህ መግለጫ ቪዲዮ ከታች ይመልከቱ፡፡ *********** More from Horn Affairs AmharicAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫበደቡብ ሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስታቸው እንዲታደጋቸው ይሻሉAudio | በኦሮሞ ተማሪዎች ስለተካሄዱት ተቃውሞዎች የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘገባVideo | ዳንኤል ብርሃነ እና ፋኑኤል ክንፉ የትግራይ ጉብኝትን አስመልክቶ በኢቢሲ የሚዲያ ዳሰሳ ፕሮግራም ላይኢ/ር ይልቃል:- የብሔር ብሔረሰብ መብት የሚባለው በጥራዝ ነጠቅ ያመጡት ነገር ነውምርጫ 97 ነፃ ነበር ከአሁኑ ይሻላል የሚለው ተቀባይነት የለውም – ፕ/ር መርጋ በቃና

የብረታ ብረት ማቅለጫን ጨምሮ 15  የማምረቻ ፋብሪካዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን የትግራይ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ   አስታወቀ። ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል መድቧል። የኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የተለያዩ ክብደት ያላቸው ብረት ብረት ማቅለጥ የሚችሉ ስድስት ፋብሪካዎችን በ6 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ከክልሉ ጋር መስማማቱን አስታውቋል። በክልሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሓላፊ አቶ ጥላሁን ታረቀኝ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት የክልሉን የተፈጥሮ ሃብት ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ  የማምረቻ ፋብሪካዎቹ  በዘንድሮ ዓመት ይገነባሉ። ”ፋብሪካዎቹ የግብርናውን ምርት ለማቀነባበር የሚያስችሉና ለኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው”ብለዋል። የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት መሰረት በማድረግ ትልልቅ አራት የማምረቻ ፋብሪካዎች በአላማጣ፣ መቀሌ፣አድዋና ሁመራ ይገነባሉ ሲሉም ተናግረዋል። ባለፈው በጀት ዓመትም ክልሉ በ223 ሚልዮን ብር ወጪ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ፋብሪካዎች የፕሮዳክሽን ስራዎች ሊያሰሩ የሚችሉ ማሽኖች ያቀፉ አምስት የማምረቻ ፋብሪካዎች መገንባት መቻሉንም አስታውሰዋል። ከአምስቱ የማምረቻ ፋብሪካዎች በተገኘ ተጨባጭ ልምድና  በተፈጠረ ፍላጎት መነሻነት ከክልሉ በተገኘ የገንዘብ ምንጭ እነዚህ ትልልቅ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ለመገንባት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል። ከግንባታ እስከ አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ያሉት ስራዎች በዋናነት በኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን  እንደሚከናውን የገለፁት አቶ ጥላሁን  የገንዘብ  አቅርቦቱን ታዛ በተባለው የክልሉ የካፒታል ዕቃ የፋይናንስ አክስዮን ማሕበር እንደሚሸፈን ገልጸዋል። የአክስዮን ማሕበሩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አማኑኤል ገብረ ትንሳኤ በበኩላቸው አገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ […]

(ጥላሁን ካሳ) በአቶ በላይ ፍቃዱ ቡድን የሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የምጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የለም አለ። ጠቅላላ ጉባኤ አካሂጄ የፓርቲውን መሪ መርጫለሁ ሌላው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የከፈተብኝ ዘመቻ ነው ሲልም ነው የገለፀው። ይህንንም የቦርዱን ዘመቻ ለመቃወም ለእሁድ ሰልፍ ጠርቻለው ብሏል። ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለት የተከፈሉት እና በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው የአንድነት ቡድን ከነገ በስቲያ እሁድ አካሂደዋለሁ ያለውን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ እንደማይችል ነው ዛሬ የገለፀው ። የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ቡድኑ ሰላማዊ ሰልፉን እንዳያካሂድ የተከለከለው ሰለማዊ ሰልፍ ሲካሄድ መሟላት ያለበትን አስፈላጊ ቅጽ ባለማሟላቱ ነው ብለዋል። እንደ ሀላፊው ቅፁ የሚጠይቃቸው በሰልፉ ላይ የሚያዙ መፈክሮችን እና ሰልፉ ከየት ተነስቶ የት እንደሚጠናቀቅ የሚገልፁ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄጃ መስፈርቶችን አላሟላም። ከዚህ ቀደም መንግስት አስፈላጊውን የሰላማዊ ሰልፍ መመሪያዎች ተከትለው ለተንቀሳቀሱ ሰላማዊ ሰልፎችን የማካሄድ ፍቃድ መሰጠቱን የተናገሩት ሃላፊው፥ በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው ቡድን የፊታችን እሁድ ለማካሄድ ያሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ግን የወጣውን መመሪያ ያልተከተለ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ የማይሰጠው መሆኑን ገልፀዋል። ሌላኛውን የአንድነት ቡድን ወክላለው የሚሉ ግለሰቦች የእሁዱ ሰልፍ በአንድነት ፓርቲ ስም ሊካሄድ አይገባም ብለው በመቃወም ተፈራርመው ለአስተዳደሩ ማስገባታቸውንም ነው ሀላፊው የጠቆሙት። ሌላኛውን የአንድነት ፓርቲ ቡድን በአሁን ወቅት በፕሬዚዳንትነት እየመሩ የሚገኙት አቶ ትእግስቱ አዎሎ በአቶ በላይ ፍቃዱ […]

(ጥላሁን ካሳ) በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠኝን የቤት ሰራ ቀደም ሲል አጠናቅቂያለሁ ከዚህ በኋላ የምጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የለም አለ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ማክሰኞ ጥር 19 ከአመራር ምርጫ ጋር ያሉበትን ችግሮች ፈቶ ሪፖርት እንዲደረግለት ነበር ከሁለት ሳምንታት በፊት አስገንዝቦ የነበረው። የቦርዱ ጥቅል መልዕክት ፓርቲው ላወጣው ህግ ይገዛ የሚል ይዘት ያለው ነው። ፕሬዝዳንትና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳነት ሆነው በጽህፈት ቤት የቀረውን ፓርቲ የሚመሩት አቶ ማሙሸት አማረ እና ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለ ከፓርቲው የተባረሩ እና በፓርቲው ደንብ መሰረት መዋጮ ያልከፈሉ መሆናቸውን በቀዳሚነት ተጣሰ ለተባለው ህግ ምክንያት ናቸው በማለት ጠቅሷል። ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ናቸው የሚባሉት ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ያልነበሩ በመሆናቸው ራሱ ፓርቲው እገዛበታለሁ ብሎ ለቦርዱ ካሳወቀው አንቀጽ 7 ነጥብ 4 እና 4 ነጥብ 2 ውጪ መሆናቸውንም ቦርዱ ቀደም ሲል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል። ፓርቲው በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሌላ ደንብ መጣሱንም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በጋዜጣዊ መግለጫቸው ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ፕሮፌሰሩ ፓርቲው ቀደም ሲል የጣሳቸውን ደንቦች አስተካክሎ ለየብቻ የተከፋፈሉ ክንፎች አንድ ላይ ሆነው እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው የውስጥ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠቱንም በድጋሚ አብራርተዋል። በተሰጣቸው የሁለት ሳምንታት ጊዜ የመኢአድ ሁለቱም ክንፎች አንድ ላይ ሆነው የውስጥ ችግሮቻቸውን በመፍታት፥ እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራትና ውጤቱን ሪፖርት […]

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ካርድ እጥረት አልቋል እንደተባሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ምንጮቹ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ ባመሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ካርድ እንደሌለ ተገልጾላቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ በተለያዩ አደረጃጀቱ በመጠቀም ኢህአዴግን ይመርጣሉ ብሎ ያሰባቸውን ዜጎች …

የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ‹‹ካርድ አልቋል›› እየተባሉ እንደሆነ ገለጹ Read more »

(ዳዊት መስፍን) የቀድሞው የአንደነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ዋና እና ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቶች የፓርቲው አባላት የቡድን ፓለቲካ የወለደውን የአንድነት መከፋፈል በጋራ ጉባኤ እንዲፈቱት ጥሪ አቀረቡ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በሴራ ፓለቲካ ህልውናው አደጋ ውስጥ የወደቀውን ፓርቲ ሊያድኑ የሚችሉት ህጋዊ አባላቱ ናቸው ብለዋል። አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚሉት ኢንጅነር ግዛቸው፥ የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን በመፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኢንጀነር ዘለቀ ረዲም የፓርቲው አባላት በሁለቱም ጎራ በቆሙት ህገወጥ አመራሮች ላይ ጫና በመፍጠር ወደ ውይይት መድረኩ እንዲያመጧቸው ነው ጥሪ ያቀረቡት። የፓርቲው የ2000 እና የ2004 ውስጠ ደንብ ለአንድ ወር ፓርቲው በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቱ ይመራ ይላል። በወቅቱ ወንበሩ ላይ እንዲቀመጡ ደንቡ ይፈቅድላቸው የነበረው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ ይህ እንዳልሆነ አንስተዋል። ከአንድነት ፓርቲ የስልጣን ወንበር ጀርባ ያለውን ሹክቻም ፕሬዝዳንቱን አስለቅቆ ቀጠለ ያሉት ኢንጅነር ዘለቀ፥ የእሳቸውም በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንትነት መዝለቅ በደባ ተገዝግዞ እንዳጋደለ ተናግረዋል። በፓርቲው ውስጥ ያለው ሴራና ሽኩቻ እጅግ ስላሳዘነኝም ስልጣኔን በይፋ ልለቅ ችያለሁ ነው ያሉት ኢንጂነር ዘለቀ። ኢንጅነር ግዛቸው በፕሬዝዳንትነት ዘመኔ ለፓርቲው ድጋፍ ከውጭ ሀገራት የሚመጣው ገንዘብ በግለሰብ የሂሳብ ቁጥር መሆኑ ቀርቶ በፓርቲው የባንክ ደብተር ይሁን ማለታቸውንም አውስተዋል። የቀድሞቹ አመራሮች የተጎነጎነው ሴራ ከእኛ አልፎ ፓርቲውን ጠልፎ እንዳይጥለው ስንል ቀዳሚውን እና ተከታዩን የፓርቲውን የስልጣን […]

የኢህአዴግ ሴራ ከሸፈ::
አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡

የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው::ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ጻፍኩለት ያለውን አየለ ስሜን አጥቷል :: ምርጫ ቦርድ ለአቶ አየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ደብዳቤ መስጠቱን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ከዚህ ቀደም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ዛሬ በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ከእነ አቶ አየለ ቀደም ብለው የተወሰኑ ወጣቶች ከፓርቲው ውጪ ይሰበስቧቸው የነበሩ ሰዎችን የጥፋት ተልዕኮ በመረዳት መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡
በእኔ እምነት ከዚህ ቀደም በፓርቲው ውስጥ በተደረገ ምርጫ ለራሳቸው የሰጡትን ድምጽ ብቻ ያገኙት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ብቻቸውን ከመቅረታቸው በፊት እነ አየለ ስሜን በመከተል ይቅርታ እንደሚጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
Image

የሃገሪቱን አንጡረ ሃብት ለስለላ በመመደብ ሕዝብ ላይ ሽብር ታውጇል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ኢሕአዴግ ውስጥ በተነሳው የብሩህ ተስፋ ክሽፈት የመጣ በባለስልጣናቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት አመራሮችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። ባለፉት 24 አመታት በህዝብ እና በሃገር ላይ የተደረገው ከፍተኛ የሆነ በደል እና ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ እንዳስነከሰባቸው እና መጪው ጊዜ ይጨልምብናል ብለው ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው በአራት ቡድኖች የተከፋፈለ በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ እና በመላው ሃገሪቱ የተበተነ የድህንነት እና የስለላ ሃይል ማሰማራታቸው ታውቋል።

የለውጥ ሃይሎች እና የዲያስፖራው ህዝባዊ ተቃውሞ በርትቶ እና ገኖ መውጣት፣በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣የካድሬዎች እንቢተኝነት፣ የውጪ ሃይሎች ጫና፣ የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ የሃገሪቱን እና የሕዝቡን አንጡረ ሃብት ስድሳ ከመቶውን ካለምንም እውቅና በዘፈቀደኝነት ለደህንነት እና ለስለላ ተግባር የመደቡት ከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን እንደገና መዋቀሩን ታውቀዋል።በሕወሃት የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ዳግም የተዋቀረው በየአከባቢው ከመንደር እና ቀበሌ ጀምሮ እስከ ከተሞች የገጠር ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በወያኔ ላይ ደባ ይሰራሉ ይፈጸማሉ ይመከራሉ የተባሉ እያንዳንዱን የዜጎች እንቅስቃሴዎች ሪፖርቶችን በትጋት በመሰብሰብ ወደ መሃል አገር በመላክ መታፈን ያለባቸው መገደል ያለባቸው ደብዛቸው መጥፋት ያለባቸውን ሰዎች በተመለከተ ከበላይ በሚተላለፍለት ትእዛዝ መሰረት መፈጸም ዋናው ስራው ነው።

ወያኔ የሚጠራው መጪው ምርጫ ሕዝቡ በ1997 እንዳደረገው አሁንም እንዲሁ ቂሙን በካርድ ይገልጽብናል በማለት የሚሰጋው ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እርምጃ በመጠቀም ለማክሸፍ የሚያስችለው በየትኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሊሆን እንደሚችል ስለላውን ተያይዞታል፤በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች የካድሬዎች እንቢተኝነት የውጪ ሃይሎች ጫና የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ ማጣፊያው አጥሮት የሃገሪቱን ግማሽ በጀት የሚሆነውን ለደህንነት እና ለስለላ ተግብር በማዋል ከፍተኛ የሆነ አደጋ በሃገር ላይ አውጆ ሕዝብን እያሸበረ ይገኛል።

Image

ተቃዋሚ ሃይሎች ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ሰብረው በመግባት ስርአቱን ማፍረስ ያለባቸው ወቅት ነው::
Minilik Salsawi : ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የፖለቲካ የምጣኔ ሃብት እና የማሕበራዊ ቀውስ እና ውጥረት ተከትሎ የባለስልጣናት አረመረጋጋት ታክሎበት በገዢው መደብ የተዋቀረው የደሕንነት ተቋም መናጋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ የላኩት መረጃ ጠቁሟል::እንደውስጥ አዋቂ ምንጮች ዘገባ ከሆነ የደህንነት አባላቱ ቡድን እና ብሄር በመለየት በሃላፊዎቻቸው ላይ ያላቸውን ጥላቻ እና ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን ለአንድ ብሄር ብቻ ተለይቶ የሚደረገው የበላይነት አድሎአዊ አሰራር ፍትሃዊነትን ሳይሆን የበታችነታችሁን ያሳብቅባቹሃል የሚሉ ጠንካራ ቡድኖች ከኢሚግሬሽን እና ደህንነት መምሪያ አከባቢ መከሰታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል::

የደህንነት አባላቱ በዜጎች መካከል በሚደረግ አድሏዊ አሰራር ለሃገር ይጠቅማሉ የተባሉ አባላትን በየክፍለ ሃገሩ በማዘዋወር ከችሎታቸው እና ከሰለጠኑት የደህንነት ሙያ ጋር የማይገናኝ ስራ ላይ በመመደብ መረጃ አምጡ ማለት የስርአቱን ዝቅጠት ከማሳየቱም በላይ በቀበሌ ካድሬዎች እና በመንደር ጆሮ ጤቢዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን አሜሪካ እና እስራኤል ሰልጥነው በመጡ የአማራ እኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የደህንነት አባላት ማሰለል ስር አቱ ምን ያህል መዋቅሩን እንደሳተ እና በሰለጠኑ ዜጎች ላይ ሃገራዊ እምነት እንዳሌለው ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል::

በውጭ አገር ሰልጥነው የመጡ የደህንነት አባላት ወደ ሃገራዊ የደህንነት መረጃ ሃይሎች እና ጉዳዮች እንዳይጠጉ የሚደረግ ሲሆን በቦታው ከዚህ ቀደም የተመደቡም ቢሆኑ በመረጃ መውር ውስጥ እንዳይሳተፉ ሲደረግ የአንድ ብሄር ተወላጆች በዚህ ላይ እንዲቀሳቀሱ መደረጉ ለስር አቱ ሰዎች አደጋ እና የመዋቅር መናጋት የፈጠረ ሲሆን አንዳንድ የሕወሓት አባላት አብረውን ውጪ አግር ሰልጥነው የመጡ አባሎቻችን የት ሄዱ ለምን አብረውን አይሰሩም በማለት በመዋቅሩ ውስጥ አደጋ ሆነው በመገኘት መናጋቱን እንዳጦዙት ታውቋል::

እንደ ምንጮቹ ከሆነ በአሁኑ ውቅት በሰራዊት ውስጥ እና በደህንነቱ ውስጥ የመዋቅር መናጋት አለመተማመን እና የእርስ በርስ ፍትጊያዎች በስፋት እየታዩ በመሆኑ በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች ይህንን ክፍተት እና የመዋቅር መናጋት እንዲሁም የውስጥ ሽኩቻን ተገን በማድረግ ሰርገው በመግባት ለስርአቱ መውደቅ ተጨማሪ ሃይል ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል::

የዛሬው የጥምቀት በዓል እንዲህ ሰማያዊ ሆኖ ነው የተከበረው፡፡ አዘጋጆቹ የቲሸርቱን ቀለም እንዲቀይሩ በደህንነቶችና በፖሊስ ወከባና ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም ‹‹የምንለብሰውን ልብስ ቀለም አትመርጡልንም›› ብለው ሰማያዊውን ቲሸርት ለብሰውት ውለዋል፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲ እና  ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፍራው የአንድነት አባለት ለፓርቲው ህልውና ሲሉ የተፈጠረውን ችግር በሰከነ መንፈስ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ:: የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ በሚመራው ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት ግርማ ሰይፉ በኩል ከፓርቲው  መሪነት የተነሱት ፓርቲውን የመምራት እና ጫናን የመቋቋም አቅም ስላልቻሉ ነው መባላቸውን በታህሳሱ ምርጫ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር አቶ ግርማን  በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ማሸናፋቸውን በማንሳት ኃሳቡን አጣጥለውታል። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ቀን ተሸናፊው አቶ ግርማ ራሴን ያየሁበት ውድድር ነው። ውጤቱም እንኳንስ ፓርቲ ወረዳ  መምራት የማልችል መሆኔን የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ያስታወሱት ኢንጅነር ግዛቸው ስልጣኔን ያስረከብኩት ፓርቲው በቡድን ፓለቲካ እንዳይፈርስ ለህልውናው በማሰብ ነው ብለዋል። አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚል አስተያየት የሰነዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን መፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት የከፈሉት አመራሮች ችግራቸውን በጋራ በውይይት እንዲፈቱ የሁለት ሳምንት ግዜ መስጠቱ ይታወሳል። ********* ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 09-2007 More from Horn Affairs Amharic‘የእነበላይ ፍቃዱ አንድነት’ መግለጫ:- ‹‹የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው››ሰንደቅ ጋዜጣ:- ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በሠነዘሩት አሉባልታ ሊከሰሱ ነውAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫበኦሮሚያ ክልል በዩንቨርስቲዎች ስለተከሰቱት ግጭቶች ከመንግስት የተሰጠ መግለጫየመኢአድ ውዝግብ በድጋሚ አገረሸበመጪው ምርጫ ከፖለቲከኞቻችን፣ ከፖለቲካቸው እና ከህዝቡ ምን ይጠበቃል?

የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳይፈጠር የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው፡፡ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ/አንድነት/ የተሰጠ መግለጫ የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ […]

(ፋኑኤል ክንፉ) ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሳባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፈጸማቸውን የሕግ ጥሰቶች በመመርመር እስከ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ በሕጉና እና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አሟልቶ እንዲያቀርብ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል። ይህን የቦርዱ ጥያቄ ባይሟላ ቦርዱ የመጨረሻ ሕጋዊ እርምጃ በፓርቲው ላይ እንደሚወስድ በደብዳቤ ቁጥር አ/573/ፓ4/ጠ405 በተፃፈ ደብዳቤ መግለጽን ለማወቅ ተችሏል። የቦርዱን ማሳሰቢያ ከግምት በመውሰድ አንድነት ፓርቲ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የሕግ እና የውስጥ ደንብ ሁኔታዎችን የመመርመር ሥልጣን ያለው ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን ጠቅሶ፣ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ቀበና መድሐኒዓለም አጠገብ በሚገኘው ጽ/ቤት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለማድረግ መወሰኑን ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ አስታውቋል። በሌላ መልኩ ምርጫ ቦርድ ግልባጭ እያለ ለሚያሳውቃቸው “የእነአቶ አየለ ስሜነህ” የአመራር ቡድን በበኩላቸው፣ ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሳሬም ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያደርጉ በደብዳቤ ለቦርዱ አስታውቀዋል። ከላይ የሰፈሩት ሁለቱ አካሎች በተለያየ ቦታዎች ጉባኤ እንደሚያካሂዱ ማሳወቃቸውን አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልፃ፣ ምርጫ ቦርድ በሁለቱም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ታዛቢ ሳይልክ ቀርቷል። ዝግጅት ክፍላችን ከላይ የሰፈረው ውዝግብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት ያጠናከረውን ዘገባ እና በእነአየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡትን ፕሬዝደነት ቃለ ምልልስ ይዞ ቀርቧል። ዘገባው […]

* ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለጉዳቱ መባባስ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያን ተጠያቂ አድርገዋል * “ቃጠሎው ከጃዝ አምባ አልተነሳም” የጃዝ አምባ ዋና ሥራ አስኪያጅ * እሣቱ ከጣይቱ ኪችን አለመነሳቱን አረጋግጣለሁ – አቶ አያሌው ታደሰ የጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ * አጋጣሚው ምትክ የማላገኝላቸውን ነገሮች ያጣሁበት ክፉ አጋጣሚ ነው – የፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤት ባለፈው እሁድ ማለዳ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል እሣት መነሻ እያወዛገበ ነው፡፡ ፖሊስ እሳቱ የተነሳው በጃዝ አምባ አዳራሽ ውስጥ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች መጠላለፍ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ቢገለፅም እሳቱ ከጃዝ አምባ አለመነሳቱን የጃዝ አምባ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ ፋንቱ ገልፀዋል፡፡ የጃዝ አምባ የኤሌክትሪክ ሲስተም አዲስና ደረጃውን የጠበቀ በመሆኑ ለእንዲህ አይነት አደጋ የሚጋለጥበት ምንም ምክንያት እንደሌለና ላለፉት አራት ዓመታት ምንም ዓይነት ችግር አጋጥሞ እንደማያውቅ የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ፤ ፖሊስ እሳቱ የተነሳው ከጃዝ አምባ ነው ማለቱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ “ከሙዚቃ መሳሪያ ጋር በተገናኘ እሳቱ ተነስቷል እንዳይባል እንኳን እሁድ ጠዋት የጃዝ አምባ ሰራተኛ የሆነው ልጅ ገብቶ መድረኩን ለቴአትር ዝግጁ ለማድረግ ሁሉንም የሙዚቃ መሳሪያ አነሳስቶ ነበር” ብለዋል፡፡ ሌላው እሳቱ ከጃዝ አምባ እንዳልተነሳ እርግጠኛ የሆኑበትን ምክንያት አቶ ኤርሚያስ ሲናገሩ፤ የህብረት ባንክና የጃዝ አምባ ሲስተም አንድ መሆኑን ጠቁመው፣ እሳቱ ተነስቶ ከጀርባ በኩል ጭስ ሲታይ ሰዎች ከኤቲኤም ማሽን ብር እያወጡ እንደነበር አስታውሰው፣ እሳቱ ከጃዝ አምባ ቢነሳ ኖሮ ኤቲኤም ማሽኑ አይሰራም ነበር  ሲሉ እሳቱ […]

Image

አለመተማመኑ እና ክፍፍሉ እየሰፋ መቷል::የእርስ በርስ መወነጃጀሉም ተጧጡፏል::Minilik Salsawi

ሕወሓት በራሱ መልክ እና ቅርጽ የፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ስር ካለው ከጦር ሃይሎች መኮንኖች የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው የወያኔ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እርስ በራሳቸው መወነጃጀላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ በመግባት በግምገማ እየተፋተጉ መሆኑን ታውቋል::በዘረፋ እና መረጃ በመሸጥ:አሳልፎ ለጠላት ወገን በማስተላለፍ ወንጀል መፈራረጅ የጀመሩት የጦር መኮንኖቹ አብዛኛዎቹ የመንደር ጎጥ ለይተው ሲጠቋቆሙ እና ሲመሰካከሩ የታየ ሲሆን ለእረፍት ከሃገር ውጪ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች በአስቸኳይ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ተጠይቋል::

በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ ከንፈራቸውን የነከሱ በርካታ ከኮሎኔል በታች ያሉ የጦር መኮንኖች በቀጥዩ ግምገማ ላይ በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚገልጹበት መድረክ እንደሚዘጋጅ የተነገረ ሲሆን ላለፉት ሁለት ቀናት የተደረገው እና አሁንም በቀጣይነት በመኮንኖች ክበብ እና በተለያዩ የመምሪያ አደራሾች ውስጥ በከፍተኛ መኮንኖች እና የጦር መምሪያ ሃላፊዎች ላይ የቀጠለው ግምገማ ውጠቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የሆነው ሌ/ጄ. ሳሞራ የኑስ ዋናው አትኩሮ ሲናገር የነበረው በሙስና እና በመረጃ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የጦር መኮንኖች ምስጢራችንን አሳልፋችሁ ሸጣችኋል እና ብትጠነቀቁ መልካም ነው ካልሆነ እርምጃ እንወስዳለን ሲል የዛተ ሲሆን እርምጃ የሚወሰድባቸው ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ተናግሯል::

ከጦር ሰራዊቱ ውስጥ ከአስረአምስት ቢሊዮን ብር በላይ አላግባብ ባክኗል የተባለው የሙስና ግምገማ በመኮንኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የቃላት አተካሮ እና አለመግባባት እየፈጠረ መሆኑን ምንጮቹ ለምንልክ ሳልሳዊ ተናግረዋል:: ይህንን ተከትሎ አንዳንድ አደገኛ የተባሉ የጦር መኮንኖችን ለማባረር በጡረታ ለማሰናበት እና ለማሰር የታቀደ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው በሰራዊቱ ውስጥ ተከስቶ ያለውን አለመተማመን እና ክፍፍል ተከትለው ከስርአቱ በተጻራሪ ወገን ቆመዋል ጥያቄ ያበዛሉ የተባሉ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ምንጮቹ አክለው::

ተጨማሪ መረጃ (EDIT) : የሃገሪቱን አንጡረ ሃብት ዘርፈው ሃገሪቱን በውጪ ብድር ዪመራሉ ብድሩም ከዘረፋ አልተረፈም:: የሚገርመው እያንዳንዱ የጦር መኮንን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመዝረፉም ባሻገር ለውጪ ሃይሎች መረጃ በመሸጥ ወያኔንን እርቃኑን አስቀርቶታል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰላም አስከባሪ ስም የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በሚሊዮቾች ዶላሮች በኢትዮጵያ የጦር አለቆች ተጭበርብሬአለሁ የሚል ስሞታ አሰምቷል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image

ቅዳሜ ጥር 9/2007አዲስ አበባ ዛሬ ሌሊት በትግሉ መፈክሮች አሸብርቃ አደረች! ተቃውሞውን እና ለትግሉ ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ የቆየው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እየገለፀ ይገኛል።

የግራፊቲ መፈክሮቹ በቦሌ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በመካኒሳ፣ በቺቺኒያ፣ በአየር ጤና፣ በጦር ሀይሎች በሚገኘው መጅሊስ ቢሮ አካባቢ፣ በላንቻና በጎተራ፣ እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተፅፈው ያደሩ ሲሆን የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎችም በሁኔታው መደናገጣቸውን ማወቅ ተችሏል።

በግራፊቲው ከተፃፉት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:–

«የጨለማ ፈራጆች!»
«ኮሚቴው የህዝብ ነው!»
«ሂጃብ መለያችን!»
«ትግሉ ይቀጥላል!»
«ፍትህ ለኮሚቴው!»

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ሰማያዊ ቀለም በኢህአዴግ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል›› ምክትል ሳጅን መላኩ
• ‹‹አብዮት እየጠራ ያለው ኢህአዴግ ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
Image
በትናንትናው ዕለት ፖሊስ የጥምቀትን በዓል ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡ የበዓሉ አስተባባሪዎችን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን ስላስገባ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳትለብሱ›› ሲል ማስጠንቀቁን ተወካዮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ያስጠነቀቁት የቀጨኔ ማዘዣ የወረዳ 4 ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ሳጅን መላኩ የጥምቀት በዓልን ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡትን 150 ያህል ወጣቶች ‹‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል፣ ቲሸርቶቹ አዲሱ ገበያ አካባቢ እንደሚገኙ መረጃ አግኝተናል፡፡ ማንም ሰው ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለብስ፡፡ ትዕዛዙ ከበላይ አካል የመጣ ነው›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ተወካዮቹ ለጥምቀት ያዘጋጁዋቸው ቲሸርቶች ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸውና ከመልበስም እንደማይቆጠቡ በመግለጻቸው ጉዳዩ ባለመግባባት ተቋጭቷል፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ፍቅረማሪያም ፖሊሶቹንና የበዓሉን አስተባባሪዎች ለማስታረቅ ጥረት ቢያደርጉም ፖሊሶቹ ‹‹ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ በመሆኑ እኛ የምንወስነው ነገር የለም፡፡›› በማለታቸው ባለመግባባት ተጠናቅቋል፡፡ ከቲሸርት በተጨማሪ ሰማያዊ ዣንጥላም እንዳይያዝ ፖሊሶቹ መከልከላቸውን የበዓሉ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ስለ ሁኔታው ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ኢህአዴግ ህዝቡን ስለማያምነው የማያስደነግጠው ነገር የለም፡፡ በደነገጠ ቁጥር ህዝብን የሚከለክለው ለዚህ ነው፡፡ አብዮት እየጠራ ያለው ራሱ ኢህአዴግ ነው፡፡ ምን ያህል ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ በሩ ዝግ እንደሆነ፣ ይህንም ሰብሮ ለመውጣት የተዘጋጀ ኃይል እንዳለ፣ ከዛ ውስጥ ሰማያዊ አንዱ መሆኑን ያውቀዋል፡፡›› ሲሉ የኢህአዴግን የስጋት ምንጭ ከምን እንደመነጨ ገልጸውልናል፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን በሆነ ባልሆነው ለማሸማቀቅና ለመከልከል ቢሞክርም ለውጡ እንደማይቀር፣ ፓርቲያቸው ይህንን ለውጥ ለመምራት የተዘጋጀ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ እንዲህ ከሰጋም ‹‹አዲሱ ገበያን እንዳያቃጥለው እሰጋለሁ›› ብለዋል አቶ ዮናታን፡፡

በሌላ ዜና የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ሰማያዊ ቲሸርት (የደንብ ልብስ) ተሰርቶ መጥቶላቸው የነበር ቢሆንም በቀለሙ ምክንያት እንዳይለበስ በመከልከሉ ቢጫ ቀለም ያለው ሌላ ቲሸርት እንደተሰራላቸው ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን›› ካሰራቸው ቲሸርቶች መካከል ሰማያዊ ቀለም ያላቸው እንዳይለበሱ መከልከሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

Image

ክርስቲያኖች ለሀገር መሪዎችና ለሰላም እንድንጸልይ ታዘናል።እርቅን፥መግባባትን ማወጅ ሃላፊነታችን ነው፤የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው ተብሎ ተጽፏልና::

በቅርቡ በሀገራችን ምርጫ ይካሄዳል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፉክክር፥ክርክር፥ውድድር ይኖራሉ።አንዳንዴም በሌላውም ዓለም እንደሚታየው መረር ያሉና መስመር ሊያስለቅቁ የሚችሉ ሽኩቻ ስድብና በጥላቻ ላይ የተመሰረታ ዘመቻ ይታያል።ከዚህም በፊት በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሞቱበት አሳዛኝ ሁኔታ ተከስቶ ነበር።ያ እንዲደገም አንፈልግም።ለሰላምና ለመግባባት እንጸልያለን።

ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ውድድር ማድረግ እንዲችሉ ሜዳውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ማመቻቸት ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ፥ፍርድ ቤትና ሚዲያው ሁሉንም እኩል የሚያስተናግዱ ሊሆን ይገባል።ኢትዮጵያ የምታድገው የተለያዩ ሃሳቦች ተፋጭተው ከውድድር በሚገኝ የነጠረ አስተሳሰብ ነው።ተቃዋሚ ሲኖር ለገዢው ፓርቲ መስተዋት ይሆናሉ፤ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋሉ፤ሙስናን ሌሎች ህገወጥነትን ያጋልጣሉ።ተወዳድረው ከተመረጡ ደግሞ ሀገር የመምራት እድል ያገኛሉ።

የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እንግልትና እስራት በተለያዩ ባለስልጣኖች ይደርስባቸዋል።እነዚህ በአግባቡ ታይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል።ወንጀል የሰሩና ያልሰሩ መለየት አለባቸው።ባልተጣራ ሁኔታና በግል ቂም በቀል ንጹህ ሰው በፍጹም መንገላታት የለበትም።

መንግስት ምንም አላደረገም ማለት አይቻልም።ሀገሪቷ ከቀደሙት መንግስታት የተሻለ የዲሞክራሲ ብልጭታ ታይቶባታል።ሆኖም ግን ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።

ሰሞኑን በአንዳንድ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ መካከል ያለው መቃቃር በሰላምና በመግባባት እንዲያልቅ እንጸልያለን።
እነዚህ ፓርቲዎች ክፍተኛ ዝግጅት አድርገው ለመወዳደር ተነስተዋል፤አንዳንድ ግድፈቶች አሉ ከተባለ በማለፍ በተቻለ መጠን ምርጫውን እንዲካፈሉ መንግስት መጣር አለበት።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመካከላቸው የሚነሱትን ልዩነቶች ብስለት በተሞላበት መንገድ በውይይት መፍታትና አንድነት መፍጠር ሀገራዊ ግዴታቸው መሆኑን በውሉ ሊያጤኑት ይገባል። በአንዳንዶች የምናየው ስር የሰደደ ጥላቻ፥ስድብ፥የሰውን ስብእና ማዋረድና ዘረኝነት መግባባትንና እርቅን ይጎዳልና በአስቸኳይ መቆም አለበት።

በሀገራችን የዲሞክራሲ ግንባታ ትልቅ ሚና የሚጫወቱና ባሁን ሰአት ካሉት ፓርቲዎች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ላይ ካሉት ከአንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል። ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።እነዚህም ፓርቲዎች በሰላማዊ ትግል ላይ ተስፋ ይቆርጣሉ።እነርሱ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት(Civil Disobedience) እንገባለን እያሉ ነው፤በዚህም ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ የምትገባ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚካሄዱትን የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያዳክም ይችላል።

ዛሬ በኢትዮጵያ አንዱ የጎደለው ነገር ቅንነት ነው።ቅንነት ከሌለ መጨቃጨቅ፥መካሰስ፥ፍርድ ቤት መንከራተት ብቻ ይሆናል።አንዱ አንዱን ለማጥቃት ሰበብና ምክንያት ብቻ ነው የሚፈልገው፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱትም አይነሳምና። ስለሆነም ችግሮች ሁሉ የሚፈቱት በመነጋገርና በመከባበር ነው።ያለፈውን በደል ይቅርታ በመጠያየቅ ህዝባችን ከድህነት የሚወጣበትን መንገድ ማፋጠን እንጂ እኛ ለስማችንና ለክብራችን ስንከራከር ህዝብ ማለቅ የለበትም።

እግዚአብሔርም ይሄን አይወድም፤ይቅር ተባባሉ፥ተከባበሩ፥ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አትሸነፉ ነው ያለው።ሌላ አማራጭ የለም። “እርስ በርስ መግባባት፥ሀገርን መገንባት” መርሃችን ይሁን።

አብያተ ክርስቲያናትና የሃይማኖት ተቋማት እውነትን በፍቅር የመናገር ሃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ቅንነት ለኢትዮጵያ!
ፍቅርና ፍትህ ለኢትዮጵያ!

ዳንኤል ጣሰው

ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ

የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ ያለምንም ጠንካራ ተቀናቃኝ ብቻውን ሮጦ ብቻውን እንዲያሻንፍ የሚያደረግ ተቋማዊ ሴራ ቦርዱን በታሪክ ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ዘላቂ ሰላም ላይ ለሚፈጠረው አደጋ ቦርዱ ከተጠያቂነት እንደማይድን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረግ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ሳምንታትም በመንግሰትና በቦርዱ ላይ ጫና ማሳደሩን እንደሚቀጥልበት እያረጋገጥን አንድነት ፓርቲ ወደ ህገወጥነት የሚወሰደውን “የጋራ ጉባዔ” አካሂዱ የሚለው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የማንቀበለው መሆኑን ለመላው አባላትና ደጋፊውች ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 8/2007
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/

Image
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ
በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል፡፡የታሪኩ ስለ ሁኔታው የገለጸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡
ስምንት አንድን ሰው በደም እስኪታጠብ ድረስ በርግጫ፣ በጥፊና በሰደፍ መደብደብ፣ በእጁ ላይ የሚገኝውን ብርና መፃሀፍ መንጠቅ፣ ስልኩን መስበር…. ይህ ድርጊት በሌሊት አንድ ሰው ላይ በሌቦች የተፈፀመ ሳይሆን ትላንት ከረፋዱ በ 5 ሰዓት ላይ በዝዋይ እስር ቤት ግቢ ውስጥ በኔ ላይ የተፈፀመ ነው፤
ነገሩ እነዲህ ነው የሆነው፣ እንደልማዴ ዝዋይ የደረስኩት በማለዳ ነው፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስፈትሼ እንደጨረስኩ የሬዲዬ መገናኛ የያዘ መቶ አለቃ እንደሆነ የሚገልፅ ማዕረግ ያለው ወታደር እየገላመጠኝ “ለምን መጣህ?” አለኝ፤ “እዚህ የታሰረ ወንድም አለኝ እሱን ለመጠየቅ ነው” ስል መለስኩ፡፡ ቀጥ ብለህ ወጣ ተከተለ “አንተ ወንድምህን መጠየቅ አትችለም” ሲለኝ “ምክኒያቱ ይነገረኝ” ብዬ ብናገር ከጉዳይም አልቆጠረኝም “እሺ እኔ ባልገባ እንኳን ያመጣሁት ምግብን አድርሱልኝ” ብል ስሚ አጣሁ፡፡ አንገቴን ደፍቼ ልወጣ ስል መቶ አለቃው በሬዲዬ እያወራ አንድቆም በእጁ ምልክት ሲሰጠኝ ልገባ ነው ብዬ ደሰ አለኝ፡፡ መቶ አለቃው በፍጥነት ወደኔ በመምጣት ያዙት አለ፡፡ በዙሬያዬ ወደ ስምንት የሚጠጉ ወታደሮች ከበቡኝ፡፡ የመቶ አለቃው “የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ነህ?” አለኝ፡፡ የተመስገን ወንድም መሆኔን በአንገቴም በአፌም “አዎ ነኝ” ከማለቴ ጥፊ ጆሮዬ ላይ ጮኽ፡፡ ከዛም አንደኛው በከስክስ ጫማ ሌላኛው በሰደፍ ተቀባበሉኝ፡፡ ደምቼ መሬት እስክወድቅ ድረስ ደበደቡኝ….ደበደቡኝ፤ ወደኩኝ፡፡ ከነደሜ አነሱኝ የያዝኩትን ብርና መጽሐፍ ነጠቁኝ ያመጣሁትን ምግብ መሬት ላይ ደፉተው እየገፈታተሩ ከግቢው አስወጡኝ፡፡ እስር ቤቱ ፊት ለፊት አቧራው ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ ተሜን በዓይን ርቀት ያህል ብቀርበውም መጠየቅ ባለመቻሌ አለቀስኩኝ፤ ደሜን አፍስሼ ወንድሜን ሳላይ ተመልሻለሁ … ተሜ ለኔ አንተን አለማየት የማይቻል ሽክም ነው፡፡ ይሄንንስ እነዴት ልንገርህ?!

Image
ሬዲዩ ፋና፣ ‹‹አንድነት ከአሸባሪ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል›› በማለት ወነጀለ ::አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አያይዘው ገልፀዋል፡፡

አንድነት እየቀረበበት የሚገኘው ውንጀላ መሰረተ-ቢስ መሆኑን የገለፁት አመራሮቹ፣ ፓርቲው አሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስብ እና ለዚህም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የአንድነት ደጋፊዎች፣ በፓርቲው እውቅና ተሰጥቷቸው የድጋፍ ሰጪ ቻፕተር ማቋቋማቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ሰዎች ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ›› የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በበኩላቸው የፓርቲው የፋይናንስ አሰራር ግልፅነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፣ በየዓመቱም ኦዲት እንደሚደረግና ምርጫ ቦርድም ለተከታታይ ዓመታት የፓርቲውን የፋይናንስ አሰራር ግልፅነት የሚታይበት እንደሆነ ጠቅሶ ለፓርቲው ሰርተፍኬት መስጠቱን› አቶ ግርማ አውስተዋል፡፡ የራዲዮ ፋና ውንጀላም ከዚህ አንፃር ተገቢነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡ ይህን መሰሉን ውንጀላ የአንድነት አባል ነን የሚሉ ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት በሬዲዮ ፋና ላይ ቀርበው ያሰሙ ሲሆን የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ የሚል ብሩክ ከበደ፣ የተባለ ግለሰብም ይህን መሰሉን ውንጀላ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ሰይፉ እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ በሬዲዮ ፋና “ሞጋች” በተባለ ፕሮግራም ላይ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረቡበት ወቅት የገዢው ቡድን ተጠሪ የሆነው ብሩክ ከበደ ፣ “አንድነት ፓርቲ በሽብር ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይሰበስባል” የሚል ውንጀላ ሲያቀርብ እንደነበር የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት አስረድተዋል፡፡

ገዢው ፓርቲ አሰርጎ ባስገባቸው ሰዎች “የደንብ ጥሰት አለ” የሚል ውንጀላ ሲቀርብበት የነበረው አንድነት ዛሬ ላይ ደግሞ ውንጀላው በህዝብ ስም በተቋቋሙት ሚዲያዎች አማካኝነት “በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል” በሚል ሌላ ውንጀላ እየቀረበበት ይገኛል፡፡
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ገዢው ቡድን “አንድነት ፓርቲ ከግንቦት ሰባት 1 ሚሊዮን ብር ተቀብሏል፡፡” የሚል ክስ በተላላኪዎቹ በኩል ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የሚያጋልጥ መረጃ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡

Image
• ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል
የአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በቀጣዩ ምርጫ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራውን አመጽ መቆጣጠር እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ ምንጮች በተለይ ፖሊስና ፀጥታ ጉዳይ ከ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› ጋር በመተባበር የደፈጣ ውጊያን ለመከላከል ‹‹የደፈጣ ውጊያ ስምሪት›› በሚል አጭር ስልጣና እየወሰዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም አገር ውስጥ አመጽ ያነሳል ተብሎ ከሚፈራው ህዝብ በተጨማሪ መሳሪያ ያነሱ ተቃዋሚዎች በምርጫው ወቅት ጦርነት ይከፍታሉ የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ በደብረማርቆስ ውስጥ ስልጠናውን የሚወስዱት ሰልጣኞች ማታ ማታ የተኩስ ልምምድ እንደሚያደርጉ አንድ የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርጫውን ተከትሎ ይከሰታል ከተባለው አመጽና ታጣቂ ቡድኖች ያደርሱታል ተብሎ ከሚፈራው ጥቃት በተጨማሪ የጥምቀት በዓል ላይ አመጽ እንዳይነሳ መከላከል፣ ከተነሳም መቆጠጠር የስልጠናው የአጭር ጊዜ ግብ ነው ተብሏል፡፡

በስልጠናው ወቅት በተለይ ፖሊሶች ‹‹ልዩ ኃይልና ፌደራል ፖሊስ በስራችን ጣልቃ ስለሚገቡ ነጻነት የለንም፣ ፖሊስ የህዝብ ነው እየተባለ ህዝብ ግን ይጠላናል፣ በህገ መንግስቱ መሰረት የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ሲገባን እርምጃ እንድንወስድ ከበላይ አካል እንታዘዛለን፣ ከፖለቲካው ገለልተኛ አይደለንም›› የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎችንና ጥያቄዎችንም አንስተዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፖሊሶች በቂ ደመወዝና ዩኒፎርም አይቀርብልንም የሚል ቅሬታ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስልጠናው ወቅትም በተለይ ፖሊሶች ጠንካራ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን መሰንዘራቸው ተከትሎ ሁሉም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንድ የደረጃ እድገት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ተብሏል፡፡ ጥር 12007 ዓ.ም የጀመረው የ‹‹ፀጥታ ኃይሎች›› ስልጠና ቅዳሜ ጥር 9/2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጥር 7/- ጥር 11/2007 ዓ.ም ለሚሊሻዎች አመራሮች ተጨማሪ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጾአል፡፡

በታህሳስ ወር የታቦት ማደሪያው ለባለሀብት መሰጠት የለበትም በሚል የባህርዳር ከተማ የክርስትና እምነት ተከታዮች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማታቸው እንዲሁም በደብረማርቆስና በሌሎች የክልሉ ከተሞች ስልጠና ላይ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው በ‹‹ፀጥታ ኃይሎች› ስልጠና ወቅት መወያያ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ሁለቱ ክስተቶች የአማራ ክልል አስተዳደር በዚህ አመት አመጽ ይነሳል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆነዋል ተብሏል፡፡

በምድራችን ላይ የሚገኘው ሀብት ውስን (አላቂ) መሆን እና በአንፃሩ የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ አልባነት፣ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ነገር በፈለገበት ሰአት እና ቀን እንዳያገኝ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ለየትኛውም ግለሰብም ሆነ ሀገር ትልቁ ፈተና ከእጥረት ጋር የተያያዘ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በሌላ በኩልም አንድ ሰው የፈለገውን ነገር በፈለገበት ሰአት እና ቀን አለማግኘቱ የተገደበ (ውስን የሆነውን) ገቢውን፣ ሰአቱን እና ሀብቱን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው መሰረታዊ ነገሮቹ እንዲያውል ይገደዳል፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት እንደ ሀገር ትልቁ የኢኮኖሚ ዳራ በዋነኛነት ከእጥረት ጋር የተገናኘ ቢሆንም፤ በአለም ላይ ያሉ ሀገራት የየራሳቸውን ባህል፣ ሀብት (ቁሳዊም ሆነ ሰዋዊ)፣ ታሪክ ወዘተ ያገናዘበ የኢኮኖሚ ስርአት በመከተል፤ ከእጥረት ጋር የተገናኘውን ኢኮኖሚያዊ ዳራ ለመወጣት እንደሞከሩ እና እንደሚሞክሩ የኢኮኖሚ ታሪክ ላይ ትኩረት ያደረጉ ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ኢኮኖሚስቶች አራት አይነት (ባህላዊ፣ የእዝ፣ የገበያ መር እና ድብልቅ) የኢኮኖሚ ስርአት እንዳለ ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ ከእጥረት ጋር በተገናኘ ያለውን የኢኮኖሚ ዳራ ከመፍታት እና ከመቀነስ አኳያ የትኛው የተሻለው ነው የሚለው ላይ አንድ አይነት አቋምም ሆነ ስምምነት የላቸውም፡፡ መንግስታት የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል በሚል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ሊመጣ የሚችለው የሚፈሰው ሀገራዊ ሀብት በአንድ በኩል ከወቅታዊው የሀገሪቷ ህዝብ ችግር አኳያ፣ ከዘለቄታዊ ጥቅሙ አኳያ በሌላ በኩል ለመጪው ትውልድ ከሚያስረክበው ተራፊ ሀገራዊ ሀብት አኳያ ከተገናዘበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት የመምጣቱ ዋስትና በመንግስታዊ ስርአት ባህሪ ላይ የተንጠለጠለ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም በእኔ እምነት ኢህአዴግ የሚለፍፍለትን የኢኮኖሚ እድገት በአንድ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ማሳያ ተብለው የሚቀርቡትን የልማት እንቅስቃሴዎች እንደ ህዝብ ካለብን ድህነት እና የምግብ ዋስትና ማጣት አንፃር፣ ድህነታችንን በመቅረፍ የምግብ አንፃር ያላቸውን ፋይዳ፣ ዘለቄታዊ ጥቅማቸውን የሚፈስባቸውን ሀገራዊ ሀብት ማእከል ባደረገ መልኩ፤ ኢህአዲጋዊውን የልማታዊ መንግስት ስርአት መፈተሸ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

በልማታዊ መንግስት ስርአት ውስጥ የህዝብ ሚና እስኬት ድረስ ነው?

የልማታዊ መንግስት ንድፈ ሀሳብ፣ በዋነኛነት ማእከል የሚያደርገው መንግስት በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ባለው የቁጥጥር እና የተሳታፊነት ስፋት መጠን ላይ ብቻ ነው፡፡ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቃት በኋላ የጃፓን እና የምስራቅ ኤሽያ ሀገራት መንግስታት በሀገራቸው ኢንደስትሪን ለማስፋፋት ኢኮኖሚ ስርአቱን ተከላካይ በሆነ መልኩ በመምራትም ሆነ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ተሳታፊ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1980 ዓ.ም የላቲን አሜሪካ ሀገራት የብድር ቀውስ እና ከ1997 ዓ.ም የምስራቅ ኤሽያ ሀገራት የገንዘብ ቀውስ፣

ከአለም- አቀፋዊነት መስፋፋት እንዲሁም ኢኮኖሚን ከማረጋጋት፣ ትምህርት፣ ጤና እና መሰረተ-ልማቶችን ከማስፋፋት አንፃር መንግስት የሚኖረውን ሚና በተመለከተ በዋሽንግተኑ መግባቢያ ሰነድ ላይ የርዕዮት አለም ልዩነት ከመፈጠሩ ጋር በተያያዘ የልማታዊ መንግስት ስርአት በ20ኛው ክፍለ ዘመን እውቅና አግኝቷል፡፡ በሌላ በኩል ከልማታዊ መንግስት ጋር አንድ አይነት የሆነ ስርአት፣ ሆላንድን የመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት በ 17ኛው እና በ18ኛው ክፍለ-ዘመን ስለመተግበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ልማታዊ መንግስት በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ፣ አንዳንዶች እንደሚሉት እና እንደሚያምኑት የልማታዊ መንግስትን ንድፈ ሀሳብ ኢህአዴግ የፈጠረው አለመሆኑን ነው፡፡ ‘እከሌ የሚባለው ሀገር በልማታዊ መንግስት መርህ ነው ያደገው፣ እከሌ ኒዮ-ሊበራሊስት ነው እከሌ ልማታዊ ነው’ የሚለውን የአላዋቂ ክርክር ወደጎን ትተን፣ በልማታዊ መንግስት መርህ ኢኮኖሚያቸውን በጠንካራ መሰረት ላይ በመገንባት ህዝባቸውን ከድህነት ያወጡ ሀገራትን ታሪክ እነዚህ አገራት ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ሀብታቸውን መነሻ በማድረግ እና የፖለቲካ ልዩነትን ወደጎን በመተው አሳታፊ የሆነ ፖሊሲ በመቅረጽ ስለተንቀሳቀሱ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዋነኝነት ግን ህዝባዊ ቅቡልነት ስለነበረው መሆኑ አይካድም፡፡

የአለም ሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ እንደሚያሳየን መንግስታዊ ስርአቱ አንባገነን መንግስት በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርገው ጣልቃ-ገብነት፣ ውስን በሆነው ሀገራዊ ሀብት የሚከናወኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉት የመንግስቱን ባለሟሎች እና ከመንግስታዊው ስርአት ጋር ተለጣፊ የሆኑትን የግል ባለሀብቶችን ብቻ ይሆናል፡፡ የአንባገነኑ ሙጋቤን ሀገር ዚምባቡዌ እና የአንባገነኑ ፒኖቼ ሀገር ቺሊ (በፒኖቼ አመራር ስር በነበረችበት ወቅት) ተመክሮ ለዚህ በቂ ማሳያ ይመስለኛል፡፡ መንግስት፣ በኢኮኖሚው ውስጥ በሚሣተፍበት የልማታዊ መንግስት ስርዓት ስኬት እና ውድቀት፣ ልማታዊ መንግስቱ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓትም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ ተቋማት እንዲኖሩ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ የፖለቲካ ስርአቱን ለኢኮኖሚ እድገት አጋዥ ለማድረግ፣ ለመድብለ ፖርቲም ሆነ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት፤ እንዲሁም ለነፃ እና ለገለልተኛ ተቋማት መኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያደርግ የልማታዊ መንግስት ስርአት፤ በአስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡ የልማታዊ መንግስትን መርህ በሚከተሉ ፖርቲዎች አማካይነት አሁን ላሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ የበቁትን የሆላንድን እና የጃፓንን ታሪክ በማሳያነት ማቅረብ ይቻላል፡፡

ኢህአዴግአዊው ልማታዊ መንግስትስ ?

ኢሕአዴጋዊው ልማታዊ መንግስት፣ ድህነትን ለመቅረፍ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ረጅም የስልጣን ዘመን የግድ ነው የሚለውን ሀሳብ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ስርዓት ጋር በመግመድ ብልፅግናን አመጣለሁ የሚል ስርዓት ነው፡፡ በእንደእኛ አይነቱ ደሀ ሀገር ከላይ በጠቀስኩት መልኩ ልማታዊ መንግስትነትን ለአንድ ፖርቲ ብቻ ተለቆ ቢቀጥል የሚቀነሰው የህዝቡ ድህነት ነው ወይስ የባለስልጣኖቹ እና ሸሪኮቻቸው ድህነት ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳት ማየት ተገቢ ነው፡፡

አፍሪካ በኒዮ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ ኢኮኖሚዋ ከማደግ ይልቅ አዙሪት ውስጥ መግባቱን በመተንተን ከዚህ አዙሪት ለመውጣት አፍሪካ የኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብን አሽቀንጥራ በመጣል፣ የልማታዊ መንግስን ስርአት መከተል እንዳለባት፣ ልማታዊ መንግስት ህዝቦችን ከድህነት በማውጣት እና በማነቃቃት ድህነት ቀራፊ ፖሊሲ የሚነድፍ እና የሚተገብር፣ ለረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚቆይ ፓርቲ አስፈላጊ ስለመሆኑ በመግለፅ ይህ ለረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚቆየው ፓርቲ ረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ ለመቆየት ዋስትናው በሀገሪቷ በየጊዜው የሚያስመዘግበው የኢኮኖሚ እድገት መሆኑን የኢህአዴግ ጭንቅላት የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “African Development the dead ends and the new beginning” በሚለው የዶክትሬት ዲግሪ ሟሟያ ጥናታዊ ፅሁፋቸው ላይ ያትታሉ፡፡ አቶ መለስ፣ ኢህአዴግ ለሚከተላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዋነኛው ነዳፊ እንደመሆናቸው መጠን ከላይ የጠቀስኩት ጥናታቸው የስርዓቱን የልማታዊ መንግስት ትርጓሜና አፈፃፀም በግልጽ ያሣያል፡፡

እውቁን ኢኮኖሚስት ፕሮፌሰር ማርክ ኦንልሰን፣ አንባገነን መንግስታት ለልማት በሚል የሚያፈሱት ሀገራዊ ሀብት ቅድሚያ ስሌቱ የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ሳይሆን ለስርአቱ ከሚያስገኘው ገቢ እና ለህልውናው ካለው ፋይዳ (ወተትን ለማግኘት እንጂ ለላሚቷ በማሰብ ሳር ከማይሰጣት ግለሰብ ጋር በተመሳሰለ መልኩ) አንፃር በመሆኑ አንባገነን መንግስታት የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ የሚያሻሽል አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጡ አይችሉም’ ይላል፡፡ ይህን የኦንልሰን ንድፈ ሀሳብ መነሻ በማድረግ የሀገራችን ግብርና ዘርፍ ልማታዊ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ፤ ከሀያ ሶስት አመት በሁአላም በሀገራችን ዋነኛ የግብርና ምርታማነት ግብአት የሆነው ማዳበሪያ ብቸኛ አቅራቢ እራሱ መሆኑ፣ ለግብርና ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የሚመድበው በጀት ሲታይ፣ የሚከተለው የመሬት ፖሊሲ ከገበሬው ይልቅ ሹመኞችን መጥቀሙ ወዘተ የኢህአዴግ ልማታዊ መንግስትነት ፋይዳው ለማን እንደሆነ የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡
ኢህአዴግ፤ ‘ልማታዊ መንግስትነኝ’ ከማለቱ ጋር በተገናኘ ልማት በሚል የዳቦ ስም ሀገሪቷ ላይ የሚፈሰው የሀገሪቷ ሀብት፣ ከሀገሪቷ ህዝብ ወቅታዊም ችግርም ሆነ ከዘለቄታዊ ጥቅም አኳያ የህዝብ የምግብ ዋስትና በመሆኑ፣ ለግብርና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ኢህአዴግ ለግብርና ትኩረት አለመስጠቱ ከላይ ከጠቀስኩት የግብርናችን ተግዳሮት በተጨማሪ የግብርና ምርቶች የዋጋ ንረት ማሳያ ይመስለኛል፡፡ ኢህአዴግ በሚመራዊ ኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ የሚታየውን ፖሊሲ ከመሸጥ (ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለግለሰቦች ማሳወቅ) እስከ ፖሊሲን ለሸሪኮች ማመቻቸት፤ ኢኮኖሚያዊ ስርአቱን ለፓርቲው ሰዎች ብቻ ምቹ ማድረግን እንዲሁም መንግስታዊ ሌብነትን መነሻ በማድረግ ከግብርና ውጪ ባሉ የኢኮኖሚ ክፍሎች ላይም የሚፈሰውን ሀገራዊ ሀብት ለህዝቡ ከሚያስገኘው ዘለቄታዊ ጥቅም አንፃር ሲታይ መንግስት በኢኮኖሚያዊ እድገት የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ የሀገሪቷ ሀብት በጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚዘውሩት የኢኮኖሚ ኢምፖየር እንዲገነባ አድርጓል፡፡

የሃገራችን ማህበረ-ፖለቲካዊ አውድ ከድሮ እስከ ዘንድሮ፣ ከግለሰባዊነት ይልቅ ማህበራዊነት ያጠላበት ነው፡፡ ብዙዎቻችን ስንወድ ስንጠላ፣ ስንደግፍ ስንቃወም የጀማውን አዝማሚያ አይተን ነው፡፡ በግላችን የምናቀርበው ክርክር በጀማው ዘንድ ተቀባይነት ካጣ፣ በግል እምነታችን ከመፅናት ይልቅ ተሸማቀን የምናፈገፍግበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ትክክለኛነታችንን የምንለካው፣ በተከተለን መንጋ ብዛት እንጂ በአመክንዮአችን ጥንካሬ አይደለም፡፡

ይህ አንደህዝብ የምንጋራው በጎ ያልሆነ እሴታችን ነው፡፡ መንግስት ደግሞ የህዝብ ነፀብራቅ ነውና በተለያየ ወቅት ሃገራችንን የመሩ መንግስታትም ከዚህ የተዋጁ አይደሉም፡፡ ገዥዎቻችን፣ ብዙሃኑ ህዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እየተገዛላቸው፣ ጥቂት የተለየ ሃሳብ ያነሱ ዜጎችን ከምድር በታች ካላደረጉ እንቅልፍግ የማይወስዳቸው ለዚህ ነው፡፡ ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሃገሬው “ስዩመ እግዚአብሄር” እያለ ይሰግድላቸው የነበሩት አፄ ኃ/ስላሴ፣ ገርማሜ ነዋይን የመሰለ ባለ አእምሮ የገመድ ራት ያደረጉት በዚህ አግባብ ነው፡፡ የነ ልጅ እያሱ፣ በላይ ዘለቀ፣ ጥላሁን ግዛው አሳዛኝ ፍፃሜ የዚሁ የንጉሱ በደቦ የመግዛት ፍላጎት ክፉ ውጤት ነው፡፡ ዱላ ተቀባዩ ወታደራዊው መንግስትም ኢትዮጵያ ትቅደም፣ የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም፣ የእድገት በህብረት የእውቀት እና የስራ ዘመቻ፣ ሁሉም ነገር ወደጦር ግምባር፣ የቀይ ኮኮብ ዘመቻ ወዘተ እያለ በየጊዜው የሚያመጣቸው ግን ደግሞ እርሱ እራሱ በቅጡ ያልተረዳቸውን ፍልስፍናዎች በደቦ ያልደገፈውን ሁሉ ደም ከማፍሰስ ወደኋላ አይልም ነበር፡፡ የዚህ አካሄዱ ማጀቢያም “ከእኛ ጋር ያልሆነ ከጠላታችን ጋር ነው” የሚል የደመ-ነፍስ መርህ ነበር፡፡

ተተኪው ኢህአዴግም መውደድ መጥላቱን፣ አድናቆት ውግዘቱን ከዘጠና ሚሊዮኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በደቦ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ ያፈነገጠን ሁሉ የዲያቢሎስ አምሳያ የሃገር ጠላት አድርጎ ያብጠለጥላል፡፡ ይህን የደቦ አባዜውን፣ ከሃገሬው ህዝብ አልፎ እስከ ባህርማዶ የምዕራባዊያን ግለሰቦች እና ተቋማት ድረስ ያዘልቀዋል፡፡ ከሚያስተዳድረው ህዝብ አልፎ ባዕዳንም በደቦ የወደደውን እንዲወዱ የጠላውን እንዲያወግዙ ይፈልጋል፡፡

የፍቅር ደቦ -1

በ1977 ዓ.ም በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ረሃብ ሰበብ፣ የምዕራባዊኑን ዶላር ጣዕም የቀመሰው ህወሃት የምዕራባዊያኑ ንዋይ የህይወት መስመሩን የሚያረዝም መሆኑን የተረዳው ገና ጫካ እያለ ነበር፡፡ ሸማቂው ቡድን፣ “ቆምኩለት” በሚለው ድሃው የትግራይ ህዝብ ስም የመጣውን የእርዳታ ገንዘብ አያሌ ድርሻ፤ በአቶ መለስ ፊታውራሪነት ለማሌሊት መመስረቻ እና ማጠናከሪያ እንዲውል እንደተደረገ፣ አልፎ ተርፎም ሱዳን ላይ ለድርጅቱ ትላልቅ የእርሻ መሬት ተገዝቶ ሰሊጥ እያመረቱ ይቸበችቡ እንደነበር በወቅቱ የድርጅቱ በጅሮንድ የነበሩት አቶ ገ/መድህን አርአያ፤ በአንድ ወቅት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል፡፡ይህ ተግባር አሳፋሪ ቢሆንም፣ በዚሁ መንገድ የመጣው ረብጣ ገንዘብ ሕወሓትን በወቅቱ ከነበሩ ሃብታም ሸማቂዎች መካከል እንዲመደብ አድርጎታል፡፡ ነገሩ ድርጅቱን ከምዕራባዊያኑ ጋር ከአንጀት ባይሆንም ከአንገት በላይ በሆነ ፍቅር እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም የሸማቂነቱ ዘመን አብቅቶ መንግስት ሲሆን የምዕራባዊያኑን ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፈለግ እንደሚከተል ይገልፅ ጀመር፡፡ በፖለቲካው ረገድ፣ በምዕራባዊያኑ ዲሞክራሲ ስም በመማል በመገዘት፣ በኢኮኖሚው በኩል ደግሞ “የምከተለው ነጭ ካፒታሊዝምን ነው” ሲል ያመሽ ያነጋ ነበር፡፡ ዓለም-አቀፍ የሰብዐዊ መብት አንቀፆችን የህገ-መንግስቱ አካል በማድረግ፣ ለምዕራባዊያኑ ሊብራሊዝም ፅንሰ-ሃሳብ እና አጠቃላይ ርዕዮተ-ዓለም ያለውን ታማኝነት ለማስመስከር ሞክሯል፡፡ የጣለውን የደርግ ስርዓት ያብጠለጥል የነበረውም የዜጎችን ሰብዐዊ መብት በመርገጥ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን ባለመቻሉ ያጠፋቸውን ጥፋቶች በማነሳሳት ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የምዕራባዊያኑ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ፈለግ፣ በኢሕአዴግ ዘንድ ብቸኛ የድኅነት መንገድ ተደርጎ ይወሰድ ነበርና ከዚህ ሃሳብ መለየት ለማንም አልተፈቀደም ነበር፡፡ የተለየ ሃሳብ አለኝ የሚል ቢገኝ እንኳ መጠሪያው የደርግ ርዥራዥ፣ “የዲሞክራሲ ጠላት” የሚል ይሆናል፡፡

የፍቅር ደቦ -2

ሕወሓት ከውልደቱ ጀምሮ በሻዕብያ ፍቅር ክፉኛ የተመታ ነበር፡፡ ይህ ጣራ የነካ ፍቅር በሚገርም ሁኔታ እናት ሃገርን ቅኝ ገዥ አድርጎ እስከማሰብ እና ቀኝ ተገዥዎችን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት እናት ሃገርን እስከ መውጋት አድርሶታል፡፡ ህወሃት፤ ከሻዕብያ ጋር የወደቀበት ሃያል ፍቅር፣ ወዳጅ ጠላቱን ለመለየት ሳይቀር ዋና መለኪያው፣ ያ ወገን የኤርትራን ጉዳይ የሚረዳበትን መንገድ እስከ ማድረግ ደርሶ ነበር፡፡ ለምሳሌ ህወሃትን ከኢህአፓ ጋር ያቃቃረው፣ ኢህአፓ የኤርትራን ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ለማለት ባለመድፈሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም የህወሃት ፍቅር፣ ከራሳቸው ከኤርትራዊያኑ ታጋዮች የበለጠ ለኤርትራ ያገባኛል እንደማለት ስለሚሞክረው ለወሬ የማይመች የሚሆንበት ጊዜም ነበር፡፡ አቶ መለስ፣ ጫካ በነበሩበት ወቅት የትክክለኛ ኤርትራዊነትን መስፈርቶች እስከማውጣት ደርሰው እንደነበር የአስራት አብረሃም “ከሃገር በስተጀርባ” መፅሃፍ ያስረዳል፡፡ አቶ መለስ፣ በዚሁ መስፈርታቸው በኢትዮጵያዊነት ስር ሆኖ የኤርትራ ጥያቄ ይመለስ የሚሉ፣ ኢትዮጵያ የኤርትራ እናት ሃገር ነችና መገንጠሏን አንቀበልም የሚሉ፣ ከደርግ ጋር ተደራድረው ኤርትራን ለመገንጠል የሚደረገውን ትግል ለማስቆም የሚከጅሉ ኤርትራዊያን፤ ከኤርትራዊነት የጎደሉ እንደሆኑ አምርረው ይናገሩና ይፅፉ ነበር፡፡ በአቶ መለስ መስፈርቶች ከተሰፈሩ፣ አንድ ሁለት ጊዜ ከደርግ ጋር ለመደራደር መለስ ቀለስ ብለው የነበሩት ኢሳይያስ አፈወርቂ ራሳቸው ኤርትራዊነት የሚጎድላቸው ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚወዱት እውቁ ኤርትራዊ ምሁር ፕ/ር ተስፋፅዮን መዳኔ፣ ከኤርትራዊነት ፀዳል የጎደሉ እንደሆኑ አቶ መለስ “የኤርትራ ህዝብ ትግል የቁልቁሊት አይደፋም” የሚል መፅሃፍ እስከመፃፍ በደረሰ ሙግት ሲያስረዱ ነበር፡፡
ይህ ከጠዋቱ ህወሃትን የተጣባው የሻዕብያ ፍቅር፣ ሸማቂ ቡድኑ አድጎ ኢህአዴግ በሚል ሰፊ ድርጅታዊ ማዕቀፍ ውስጥ ገብቶም፣ የመንግስትነት ሰገነት ላይ ወጥቶም የሚብስ እንጅ የሚበርድ አልሆነም፡፡ ሸማቂ ቡድኑ፣ ወደ አዲስ አበባ በሚያደርገው ግስጋሴ ሁሉ ቆምኩለት ከሚለው ኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እና ፍላጎት ይልቅ የሻዕብያ አመራሮችን ፍላጎት ያስቀድም ነበር፡፡ አዲስ አበባ ገብቶ የታላቋን ሃገር የኢትዮጵያን እጣ-ፋንታ አንድ ደረጃ ሳያደርስ፣ የኤርትራን መገንጠል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የተባበሩት መንግስታትን ሹማምንት እረፍት በነሳ ውትወታ ተጠምዶ ነበር፡፡ የመገንጠሉ ሂደት ሚጢጢዋን ኤርትራን ያለ አግባብ ባለ ሁለት ወደብ ሲያደርግ ኢህአዴግ ታገልኩላት የሚላትን ታላቋን ሃገራችንን ወደብ አልባ ማድረጉ፣ በኤርትራ ፍቅር አይነ-ልቦናው ለታወረው ህወሃት ነገሬ የሚባል ጉዳይ አልነበረም፡፡

ይህ ምንጩን ለማወቅ የሚያስቸግር ህወሃት የወደቀበት ሃያል ፍቅር፣ ወደ ሁሉም ኢትዮጵዊ በደቦ ሰርጎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኤርትራን ጉዳይ ቀዳሚ እንዲያደርግ የመፈለጉ ዝንባሌ ራሱ ከወደቀበት ፍቅር ብርታት የበለጠ የሚገርም ነበር፡፡በወቅቱ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት የፈለገውን ያህል በኤርትራ ፍቅር ሊወድቅ ቀርቶ፣ የኤርትራን ሃገርነት ለመቀበልም እንኳ ዝግጁ አልነበረም፡፡ በተቃራኒው ህዝቡ ኤርትራ የተገነጠለችበትን ሪፈረንደም አግባብነት እና የኢትዮጵያ ሁለት ወደብ አስረክቦ ወደብ አልባ መሆን እያስቆጨው ነበር፡፡ ይህ የአብዛኛው ዜጋ እምነት ታዲያ ለህወሃት መሪዎች የደርግ ቅሪት፣ የነፍጠኛው ስርዓት ርዝራዥ፣ የነፃነት ጥያቄ የማይገባው ትምክህተኛ፣ የተስፋፊነት አባዜ የተጠናወተው፣ የጎረቤት ሃገር ሉአላዊነት የማይዋጥለት ጦረኛ …. የሚል መጠሪያ ይሰጠው ነበር፡፡ “ስለ ኤርትራ አንዳች ክፉ የሚናገር ቀድሞ የሚጣላው ከእኛ ጋር ነው” የሚለው የህወሃት አባባል፤ ሽርክናው ወደ መሸካከር ተቀይሮ፣ በሁለቱ ሃገራት መሃከል ከፍተኛ ደም መፋሰስ ከሆነ በኋላም የቀጠለ ነው፡፡

‘የኤርትራ መገንጠል የነፃነት ምልክት ነው ከተባለ ይሁንና የኤርትራ አካል ያልሆነው የአሰብ ወደብ እንኳን ለሃገራችን ይትረፍ’ ማለትም በህወሃት መንደር የሚያስቀስፍ ሃጢያት ነበር፡፡ የወደብ እጦቱ ድህነቱን ያባባሰበት የኢትዮጵያ ህዝብም የአሰብን ወደብ ያለአግባብ ለኤርትራ መሰጠቱን በደቦ እንዲቀበል አልፎ ተርፎም ህገ-መንግስቱ ያመጣው የነፃነት ትሩፋት ነው ብሎ እንዲያምን ይጠበቅበታል፡፡ ህወሃት፣ ኤርትራን በተመለከተ የያዘውን አስገራሚ አቋም እንዲይዝ ባደረገው ፍቅር የተለከፈበት በሚናገረውም ሆነ በማይናገረው የራሱ ምክንያት ሆኖ ሳለ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ያለ ምክንያት ተገቢ ያልሆነውን የሚቀበልበት እና ከህወሃት ጋር የፍቅር ደቦ ገብቶ ‘ከኤርትራ ያስቀድመኝ’ የሚልበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ሆኖም ደቦ ወዳዱ ህወሃት፣ እርሱ በወደቀበት የኤርትራ ፍቅር የኢትዮጵያም ህዝብ እንዲወድቅ ይጠብቃልና የወደቡ አንሶ ቡናው፣ ጤፉ፣ ገብሱ፣ ስንዴው …. ወደ ኤርትራ ሲጋዝ ከልቡ ደስ እንዲለው ሲፈርድበት ኖሯል፡፡

የፍቅር ደቦ-3

የመገንጠል መብትን የህገ-መንግስቱ አካል ያደረገው ኢህአዴግ፣ ህገ-መንግስቱ በፀደቀ ማግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በደቦ በመገንጠል ፍቅር እንዲወድቅ፣ የመለያየት መዝሙር እንዲዘምር፣ ከሃገራዊነት ይልቅ ወንዘኝነቱን እንዲያጠብቅ፣ መገንጠልን የነፃነት ቁንጮ አድርጎ እንዲያስብ መፈለጉ አልቀረም፡፡ በሌላ በኩል በዘውዳዊው ስርዓትም ሆነ በወታደራዊው መንግስት ዘመን ለተቆጠሩ ረዥም አመታት በጋብቻ፣ በጉርብትና እና መሰል ማህበራዊ መስተጋብሮች አንድነቱ ሲያጠብቅ ለኖረው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ይህ በቀላሉ የሚዋጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከጠዋቱ የሃገር አንድነትን በነፍጠኛ አማሮች ብቻ የሚቀነቀን ክፉ አባዜ አድርጎ ይቆጥር ነበርና እርሱ በወደቀበት የመነጣጠል ፍቅር ያለመመታት፣ የትምክህተኝነት ምልክት ተደርጎ ይወገዛል፡፡ የሚገርመው ይህን የሚለው ኢህአዴግ መገንጠልን አልመው የሚንቀሳቀሱ የብሄር ፓርቲዎችንም በጠባብነት ይከሳል፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ አተያይ፣ የመገንጠል ጥያቄ የነፃነት ትግል የሚሆነውም የሚሳካውም ሻዕብያ ሲያነሳው ብቻ ነው፡፡ በተረፈ ስለመገንጠል ቀርቶ ስለአንድ ብሄር መብት ጥያቄ ማንሣት የጥበት ምልክት ነው፡፡ ይህን ግራ የተጋባ የገዥው ፓርቲ አቋም፣ በደቦ መከተል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ግዴታ ነው፤ ካልሆነ የተለመደው ውግዘት ይከተለዋል፡፡

የፍቅር ደቦ – 4

ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ‘ዲሞክራሲያዊነቱን ትቼ ልማታዊ ሆኛለሁ’ ያለው ኢህአዴግ፣ ይህን ሲል ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ ሲዘምርለት የኖረውን የምዕራባዊያን ዲሞክራሲ በልማታዊ መንግስት ርዕዮት ተክቶ ነው፡፡ “ሩቅ አሳቢ” ሲል የጠራውን የልማታዊ መንግስት እሳቤ፣ ‘የእስያን ሃገሮች ኢኮኖሚ እንደ ነብር እንዲፈተለክ ያደረገ ብቸኛ መድህን ነው’ ሲል አወዳድሶ፤ ቀድሞ ሲያሞካሸው የነበረውን የምዕራባዊያኑን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የርዕዮት አለም ዘይቤ ደግሞ፡- “በአሸናፊነት መንፈስ አለቅጥ የሰከረ፣ ለአፍሪካ ፈፅሞ የማይበጅ” ሲል አጣጥሎ ነው፡፡ የኒዮ ሊብራል ቀሳውስት ዶግማ የሚለውን የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ዘይቤ በተለይ “የዘበኛ መንግስት የመመስረት ህልም ያለው” ሲል ያራክሰዋል፡፡

በዚህ ቅፅበትም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲዘምርለት የኖረውን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ህልም ወዲያው ረስቶ፣ ከኢህአዴግ ጋር በቻይና ፖለቲካዊ ርዕዮት ፍቅር እንዲወድቅ፣ ስለሱው እንዲዘምር፣ በአንድ አውራ ፓርቲ ስር መሆንን ፀዳል ድንቅነት እንደያወድስ፣ ስለሰብዐዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ አያያዝ ሁኔታ ትንፍሽ ሳይል ስለቁሳዊ እድገት እና እንዲሁ በደቦ የልማታዊ መንግስትን መስመር ተከትሎ ስለሱው ትሩፋቶች ብቻ እንዲነጋገር ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ የደቦ አስተሳሰብ የሚያፈነግጥ የልማት አደናቃፊ፣ የህዝብ ጠላት የሚሉ ተቀፅላዎች ይንጠለጠሉበትና ጉዞው ወደቃሊቲ ይሆናል፡፡

ከላይ ለማሳያነት የቀረቡት የኢህአዴግ የደቦ ጉዞ ፍላጎቶች፣ በምክንያታዊነት ለሚያምን እና የራሱ አተያይ ላለው ዜጋ ክፉ ፈተና የሚደቅን ነው፡፡ ሌላው የዚህ ከመንግስት በኩል የሚፈለገው የደቦ ጉዞ ችግር፣ ራሱ ለደቦ የሚጋብዝበትን ሃሳብ ይዞ የመሰንበት ዝንባሌው አናሳ መሆን ነው፡፡ ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደተሞከረው ገዥው ፓርቲ ትናንት በፍቅር ወድቆለት ሌት ተቀን ሲያነሳሳው ህዝቡንም ለደቦ አድናቆት ሲጋብዝበት የነበረውን ርዕዮተ አለምም ሆነ መመሪያ፣ ከመቅፅበት ቀይሮት ጠላት ሲያደርገው ይስተዋላል፡፡ የምዕራባዊያኑ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እሳቤ፣ ከኤርትራ ጋር የነበረው ወዳጅነት፣ የመገንጠል ጥያቄን የሚያስተናግድበት ሁኔታ ወ.ዘ.ተ ለዚህ አባባል በማሣያነት ሊቀርቡ የሚችሉ አብነቶች ናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ የደቦ ጉዞውን ለመቀበል ለተዘጋጀ ሰውም ቢሆን የኢህአዴግ አካሄድ አስቸጋሪ እና ግራ አጋቢ መሆኑ አይቀርም፡፡ በዚህ ሁኔታ ለመያዝ ለመጨበጥ አስቸጋሪ የሆነው የኢህአዴግ አካሄድ አስቸጋሪ ሆኖ ሳለ፣ መንግስት ለፍቅሩ ብቻ ሳይሆን ለጠቡም ደቦ የመፈለጉ አካሄድ ደግሞ ሌላው ከባድ እና ግራ አጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

የኢህአዴግ የፍቅርም ሆነ የጠብ ደቦ ፍለጋ፣ የዜጎችን እጣፈንታ የሚወስን እየሆነ መምጣቱ ይብስ አሳሳቢው ጉዳይ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ኢህአዴግ የወደደውን መውደድ የጠላውን መጥላት ብቻ ሳይሆን አብሮ ማውገዝ ከሁሉም በመንግስቱ ጥላ ስር የሚኖር ዜጋ ግዴታ ወደመምሰሉ እየሄደ መጥቷል፡፡ በዚህ የማይስማማ እጣ-ፈንታው ሁለት ነው ወይ ቃሊቲ መውረድ ወይ መሰደድ፡፡ እለት እለት እየጨመረ የመጣው የተሰዳጅ እና የታሳሪ ቁጥርም በአመዛኙ ከዚሁ ከኢህአዴግ የልብ ሃሳብ ጋር የመመሳሰል እና ያለመመሳሰል ጉዳይ ነው፡፡ ለፍቅርም ሆነ ለጠብ ከመንግስት ጋር እኩል ማሰብ ደግሞ ተፈጥሯዊም አይደለምና ለዜጎች ትልቅ ፈተና ነው፡፡ የፈተናውን ክብደት የሚያሳዩ የኢህአዴግ የጠብ ደቦ ፍላጎቶችን ለማሳየት ሳምንት እመለሳለሁ፡፡

*የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት ተልኳል፡፡ በትናንትናው ዕለት አንድ ከሴራሊዮን የመጣ ግለሰብ በኢቦላ ሕመም ተጠርጥሮ ምርመራ ቢደረግለትም ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አስታወቁ፡፡ ታማሚው በሴራሊዮን በአንድ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጀት በኩል ተቀጥሮ የአካባቢ ቁጥጥር ባለሙያ በመሆን  ይሠራ የነበረ  ሲሆን፥ ከሴራሊዮን ከተመለሰ በ15ኛ ቀኑ በትኩሣት ራሱን በመሳቱ በተደረገለት የደም ምርመራ ፋልሲፓረም የተባለ የወባ በሽታ የተገኘበት በመሆኑ ለዚሁ አገልግሎት ባዘጋጀችው ላብራቶሪ ለኢባላ የደም ምርመራ ተደርጎለት ውጤቱ ከበሽታው ነፃ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በላብራቶሪ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ብንሆንም ታካሚው ሴራሊዮን ደርሶ ከመመለሱ አንፃር የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት መላኩንና ከ48 እስከ 72 ሰዓታት ውስጥ ውጤቱ እንደሚታወቅ ነው የተመለከተው። በውጤቱ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ በቀጣይ ሚኒስቴሩ እንደሚያሳውቅ ዶክተር ከሰተብርሃን ገልጸዋል፡፡ ታካሚው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ ሕይወቱ ማለፉንም ነው ያስታወቁት፡፡ የተላከው ናሙና ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ከተጠርጣሪው ጋር ቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ላይ የባለሙያ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ኢቦላን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አረጋግጠዋል፡፡ ******** ምንጭ፡- ፋና – ጥር 6፣ 2007 More from Horn Affairs Amharicበአሶሳ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ተከሰተ – ክልሉ ኢቦላ አይደለም ይላልየኬሚካል ክምችትና የአደጋ ስጋት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችዓለማየሁ አቶምሳ – ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ የታገለና ያታገለኢትዮ-ቴሌኮም በ75 የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር ፈታሁ […]

ምርጫ ቦርድ አንድነትና መኢአድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ውሳኔ አስተላለፈ

• ለሰማያዊ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውስጥ ችግራቸውን መፍታት አልቻሉም በሚል በዛሬው ዕለት ውሳኔ እሰጣለሁ ብሎ የነበረው ምርጫ ቦርድ ሁለቱ ፓርቲዎች በሁለት ሳምንት ውስጥ የውስጥ ችግራቸውን ፈትተው ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ የመጨረሻ ጊዜ ሰጥቻቸዋለሁ ሲል ገልጾአል፡፡ ቦርዱ ዛሬ ከሰዓት በሰጠው መግለጫ በአንድነትና መኢአድ ስም የተለያዩ ጉባኤዎች በመደረጋቸው ሁለቱ ፓርቲዎች ጥር 3 ያደረጉትን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አለመገኘቱን፣ አንድነት የ2004 ዓ.ም እንዲሁም የመኢአድን የ2001 ዓ.ም ደንብን እንጅ ከዛ በኋላ ያሉትን የፓርቲውን ደንቦች እንደማያውቅ በመግለጽ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ችግራቸውን እንዲፈቱ የመጨረሻ ጊዜ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል መድረክ ረግጦ በመውጣት፣ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲያድሙ በማድረግ፣ ቦርዱ የማያውቀው ትብብር በመመስረት በሚል በምርጫ ቦርድ ክስ የቀረበበትና ይቅርታ እንደማይጠይቅ በደብዳቤ ለገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ ማስጠንቀቂያውን የማያከብር ከሆነም ቦርዱ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

የቦርዱ ባለስልጣናት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን ህገ ወጥ ትብብር በመመስረት ስትከሱ ሌሎቹን የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ለምን አልከሰሳችሁም?›› በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ‹‹ፓርቲዎቹ 9 መሆናቸውን የሰማሁት አሁን ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹እስካሁን ሌሎች ትብብሮችን ምርጫ ቦርድ አያውቃቸውም ብላችሁ ከሳችሁ አታውቁም›› በሚል የ9ኙን ፓርቲዎች ትብብር ህገ ወጥ ነው ካሉ ገዠው ፓርቲ ከአጋሮቹ ጋር ያለውን ግንኙነትን ለምን ህገ ወጥ ነው እንደማይሉ ለቀረበላቸው ጥያቄም ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ‹‹ኢህአዴግ እንደገዥ ፓርቲ አጋር ፓርቲዎች ሊኖሩት ይቻላል፡፡ እንደ ገዥ ፓርቲ ከአጋሮች ጋር መስራት ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ነገሮችን ቦርዱ አይመለከተውም›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

አንድነትና መኢአድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ችግራቸውን እንዲፈቱ ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቻለሁ ያለው ምርጫ ቦርድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔውን ያሳውቃል ብሏል፡፡

አንድነት ፓርቲን ለማፍረስ የተወጠነው ሴራ በዶክመንተሪ ፊልም ተቀናበረ::
በነሀብታሙ አያሌው እና የአንድነት አባላት ላይ ለመመስከር ስምምነት ተደርሷል::

የኢህአዴግ ሰርጎገብ የሆኑትና አንድነትን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱት(በትግስቱ አወሉ የሚመሩት) አካላት በምርጫ ቦርድና ጽ/ቤት ለብሄራዊ ደህንነት አባላት በቪዲዮ በሰጡት የሃሰት ምስክርነት አንድነት ፓርቲ በግንቦት7 ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት እየሰራ ነው የሚል መረጃ መስጣታቸው ታወቀ፡፡ ሰርጎገቦቹ የአንድነት አባላት በሆኑትና አሁን በእስር ላይ በሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው ላይም የሀሰት ምስክርነት ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡

ዳንኤል ሙላት፤ኤዶም ሰይፉ፤ደረጀ ጣሰው እና ገዛሀኝ ንጉሴ በነሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሺ ላይ ለተመሰረተው ክስ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው ለመቅረብ የውል ስምምነት ፊርማቸውን በትላንትናው እለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ሊግ ቢሮ አኖሩ፡፡ፓርቲውም ለነሱ ተላልፎ እንደሚሰጣቸው አልያም ሊዘጋ እንደሚችል ቃል ተገብቶላቸዋል ፡፡

Image

ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::

Minilik Salsawi ህዝብን ያዘናጋ እየመሰለው የተዘናጋው ህዝብን ያፋጀ እየመሰለው ያፋቀረው ወያኔ እንደት እንደሚሳካለት ባለማወቁ እየዳከረ ነው::ህዝባዊ ጥያቄዎች እየበረቱበት የመጣው ወያኔ መላወሻ በማጣቱ የሚያደርገውን እስካለማወቅ ደርሷል:: ከእነዚህም ድንብርብሮች አንዱ ከአባቱ ሻእቢያ እንደወረሰው የፈጠራ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ነው:: እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ያስረሱልኛል ጭንቅላት ይሰርቃሉ የሚል እደምታ ያለውን ፈጣን ዘገባ ማሰራጨት ቅርሶችን እና የሃገር እና ሕዝብ አትኩሮት ይስባሉ የተባሉ ነገሮችን ማውደም የህዝብን አንግት ለመስበር እና ህዝብን ሃዘን ለማስቀመጥ ማለም ሃሳብን ሰርቆ አቅጣጫ በማስቀየር የማሰቢያ ጊዜ እንዲያገኝ መትጋት ስራዬ ብሎ ይዞታል::

ባለፉት 24 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ወያኔ ስልታዊ የሆኑ ያልሰለጠኑ እና ጫካዊ ብልሃቶችን ለመፍጠር እና ሲነቁበትም አለማቀፍ ሽብርን ይፈጥራሉ የሚለውን ወንጀል በዜጎች ላይ በመላከክ የትግል መሪ ሃሳቦችን ወደ አንድ አቅጣጫ ሊነዳቸው ይፈልጋል:: የህዝቦችን የመብት እና የነጻነት ጥያቄ መመለስ ያቃተው ወያኔ በሚፈጥራቸው የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡን ለማደንዘዝ እና ለማዘናጋት እየዳከረ ይገኛል::የስርኣቱን ንዝህላልነት እና እየደከመ ለመውደቅ መንገዳገዱን እንዳያሳብቅበት ይመስላል የተለያየ ዘዴ በመፍጠር እና በማስወራት ራሱን ለትዝብት ዳርጓል:: ህዝብን አዘናጋለሁ ብሎ ራሱ በመዘናጋት በሽታ የተጠቃው ወያኔ ለህዝባዊ ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ የተሻለ ይሆናል:: የዛኔ ህዝብን ማዘናጋት ይቻላል::

የራሳቸው ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች በሃገር ውስጥ ያለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች….. የኑሩ ውድነት የመዘዋወር መብት የሃይማኖት እና የህግ ጉዳይ ጥያቄዎችን አንግበው ተነስተውባታል ወያኔ ላይ:: በምንም ነገር ህዝብን በማዘናጋት ትግልን ለማሰልሰል የተደረጉ ሙከራዎች አይሳኩም ህዝባዊ ጥያቄዎች ሲመለሱ የዛን ጊዜ …የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሲፈቱ ያን ሰአት …ህዝብ ጠግቦ ሲያድር…መልክም አስተዳደር ሲሰፍን ሰው በእውቀት ሲሰራ ጎሳ መቁጠር ሲቆም …ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ በሃገሪቱ ሲሰፍን ጠላትነት እና የጎሳ ተኮር ፖለቲካ ሲወገድ የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ ሲኖር ፍርድ ቤቶች/ዳኞች ከመንግስት ባለስልጣናት መዳፍ ወተው በነጻነት ሲሰሩ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሲመለሱ ህዝብ አርፎ ይቀመጣል::

የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ጥያቄና የተቃውሞ ሰልፍ፣ የተቃዋሚወች ጫጫታ፣ የኢኮኖሚው ድቀት፣ የስራአጥነት ብዛት፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን እንዲአሰፋና የዜጎችን መብት እንዲጠብቅ በምእራቡ ዓለም የሚደረግበት ግፊትና ተጽእኖ ወዘት ከአቢዮታዊ ዴሞካራሲ ጋር በቀጥታ የሚላተምበት ስለሆነ ብዙ ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አያጠራጠርም:: በሰላም ሊአስገዛው የሚችል አይሆንም:: ተቃውሞው በዓይነት በመጠንና በስፋት እየጨመረበት ይሄዳል:: የህዝብ ተቃውሞ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የመንግስት አፈናም እይተባባሰ ይሄዳል::ይሕም ወደ ሕዝብ አመጽ ይሸጋገራል::ህዝባዊ ጥያቄዎች ታዝለው ግን ረዥም ማንገድ መሄድ አደጋ ስላለው የተዘናጋው ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::

ከያኒ አስቴር በዳኔ “ተራራ አንቀጥቃጩን” ጠመንጃ ሳትይዝ ፣ ጥይት ሳተኩስ በለሰለሰ አንደበት በተባ አማርኛ ብቻ ስታንቀጠቅጠውና ስታስጨንቀው በሃሳብ ፣ ታየችኝና ቀናሁባት። “ጀግና አልባሌ ነው” ሲባል እሰማ ነበር ፣ ዛሬ ደሞ እውን መሆኑን በሷ አወኩት።

‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ በአጥቂነት ቦታ ተሰልፎ እየተጫወተ ነው››የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር
ትብብሩ ምርጫ ቦርድ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን በር ለመዝጋት እየተጋ መሆኑን አስታወቀ
Image
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን በር ለመዝጋት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል ቅሬታውን ገለጸ፡፡ ትብብሩ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ምርጫ ቦርድ ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ የፓርቲዎችን ትብብር ‹ህገ-ወጥ› በማለትና በአባል ፓርቲዎቹ መካከል ‹አሰባሳቢና ተሰባሳቢ› እንዳለ በማስመሰል አለመተማመን ለመፍጠር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
ትብብሩ የትብብሩ አባል ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ‹‹ትብብር በሚል ማሰባሰብን›› እንደ ጥፋት ቆጥሮ ይቅርታ እንዲጠይቅ ደብዳቤ መጻፉ ተገቢነት የሌለውና ትብብሩ የሚያወግዘው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ቦርዱ በአደባባይ ‹‹ፓርቲዎችን በእኩል ዓይን ነው የምመለከተው፣ በሆደ ሰፊነት እያስተናገድኩ ነው›› ቢልም፣ በፓርቲዎች መካከል አድሎ እንደሚፈጽም በማስረጃ ማስረዳት እንደሚችል የገለጸው ትብብሩ፣ የሚከተሉትን ነጥቦች በዋቢነት አንስቷል፡፡
1. ገዥው ፓርቲ/መንግስት ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚለው ፕሮግራማችን ህገ-መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን የጠራናቸው የአደባባይ ስብሰባዎችና ሰልፍ በማፈን ህገ-ወጥ እርምጃ ሲወስድ ቦርዱ ‹‹ህገ ወጥና እኔ የማላውቀው ትብብር ነው›› በሚል ክስ ማቅረቡ፣
2. ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች በማበላለጥ አሰባሳቢና ተሰብሳቢ፣ የሁከት ጠንሳሽና ጀሌ፣ በማለት ያለ መተማመን ስሜት በመፍጠር ለመከፋፈል ያደረገው ሙከራን መጥቀስ ይቻላል ብሏል በመግለጫው፡፡
ፓርቲዎች በትብብር የጋራ አቋም ለመውሰድም ሆነ የጋራ ተግባር ለመፈፀም የቦርዱ እውቅና እንደማያስፈልግ፣ ከዚህ በፊት ለበርካታ ጊዜያት ፓርቲዎች በጋራ የጠሯቸውን ሰላማዊ ሰልፎች፣ በህጋዊ ሰውነታቸው የመሰረቷቸውን ግንኙነቶች (የኢተፓዴኀ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ መኢአድ፣ ኦብኮ፣ ደቡብ ህብረት ኀብረትና አማራጭ የመሰረቱትን ‹ትዲኢ›› እና 33ቱ) አውቀው መርሳታቸው፣ ገዥው ፓርቲ አምስት ክልሎችን ከሚመሩ ፓርቲዎች ጋር አጋር በሚል የሚያደርገው ግንኙነት ከእኛ ትብብር ቀርቶ በግንባር ከተደራጁ ያለፈና የጠነከረ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ለዘመናት በዘለቀበትና አንድም ቀን ጥያቄ ባላነሳበት፤ ቦርዱ በአዋጅ ባልተሰጠው ሥልጣን ለገዥው ፓርቲ ‹አጋር መልማይ› ወይንም የህወሓት/ኢህአዴግ ‹‹ገንዘብ አዳይ ሆኖ ለተለዩ ፓርቲዎች ዳረጎት በሚሰፍርበት እውነታ ውስጥ ሆኖ ትብብሩ ላይ ጣት መቀሰሩን በማሳያነት አንስቷል፡፡
በመሆኑም ‹‹ትብብራችን በገዥው ፓርቲ ላይ የፈጠረውን የፍርሃት ስሜት የትብብራችን የጋራ እንቅስቃሴም ለገዥው ፓርቲ ሥጋት መፍጠሩን ለዚህም ምርጫ ቦርድ ይህን አይነቱን ህገ-ወጥ ፖለቲካዊ ድጋፍ በመገናኛ ብዙሃን በማሰራጨት ህዝቡ የሚሰጠንን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመግታት ወይንም ፈሪ ከተገኘ ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ የሚደረግ ተራ ፕሮፖጋንዳ ነው›› ብሏል፡፡
በአጠቃላይ ቦርዱ እየፈጸማቸው ያሉትን ተግባራት በህገ-መንግስቱና የምርጫ ህጉንና ሌሎች የአገሪቱ ህጎች ከተጣለበት ከባድ የዳኝነት ኃላፊነት ወጥቶ ለገዥው ፓርቲ በአጥቂነት ቦታ ተሰልፎ የሚጫወት መሆኑንና ይህም በሕገ-መንግሥት የተቀመጠውን የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሂደት ከደረሰበት ወደኋላ የሚመልስ አካሄድ ነው ሲል ገልጹዋል፡፡
በመጨረሻም ትብብሩ ህገ-መንግስቱን አክብሮ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ በትብብር ከመስራትና የጋራ ህጋዊና ሰላማዊ ትግል ከማድረግ ለአፍታ እንደማያቆም አስታውቋል፡፡