በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው – VOA


በጎንደር፣ በአዴት፣ በዳንግላና ሌሎችም ሥፍራዎች የታሠሩ ሰዎች መኖራቸውንና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊም እየተፈለጉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ስለሁኔታው መረጃ እንደሌላቸው የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻገር የሚሠሩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፀጥታና የደኅንነት ኃላፊ አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ዳንግላ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ – መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ዐይናለም ተይዘው ዳኛ ፊትም ሳይቀርቡ፣ ክሥም ሳይመሠረትባቸው ለአሥር ቀናት መታሠራቸውን ባለቤታቸው ገልፀዋል፡፡

አዴት ላይም የፓርቲው የይልማና ዴንሣ ወረዳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ስመኘው ገሠሠ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተኩል ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ተይዘው መታሠራቸውና ወደ ብር ሸለቆ መወሰዳቸውን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎችም በርከት ያሉ የጅምላ እሥራቶች እየተከናወኑ ሲሆን እንቅስቃሴዎቹ የተሣሣቱ ወጣቶችን ለማስተማር፤ በወንጀል ተጠያቂ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያለባቸውን ደግሞ ሕግ ፊት ለማቅረብ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አስረድተዋል፡፡

ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ → listen

2 Comments on “በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው – VOA”

  1. ትኩስ ሰበር ዜና የማይቀር
    ኢሐዲግ ለ 4 ተከፈለ በንጉሡ ሞቱማ ጀግና ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ቡድን ስነጣጥቆ በኢሕአዴግ ውስጥ ገባ። መስከረም 12 ቀን 2009 ዘመቻ ከደረሰ ኢሕአዴጎችን እንቅልፍ ነሳቸው።
    በዚህ ሣምንት እርስበእርሳቸው ተጨራርሰው ከህዝቡ የሚቀላቀሉ ቡድን ታሪክ ሰረዎች በተግባር እናያለን።
    መስከረም 3 ቀን 2009

  2. ወያኔ ጠላቶች ናቸው ብሎ የሰየማቸው
    1- አማራ
    2- የኦርቶደክስ እምነት
    3- የሙስሊም እምነት
    4- ምሁራን
    5- የሃገር ሽማግሌዎች
    6- አንድነት ኢትዮጵያ የሚል/የሚሉ ሰው/ሰዎች
    7- ጥረው ግረው ሃብትና/ሃብታም/የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን
    8- እውነተኛ ጋዘጤኛ
    ሞላ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*