ዩክሬን ከማይዳን አብዮት እስከ ባይደን ጉብኝት DW Amharic November 24, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ ወዲሕ በተለያዩ ሐገራት የተለያዩ የአደባባይ ሠልፍ-አመፆች ተደርገዋል።አስር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ሁለት መንግሥት በአደባባይ አመፅ የፈረሰባት ሐገር ግን አንድ ናት።ዩክሬን።ዛሬም ቢያንስ ምሥራቃዊ ግዛቷ ደም በሚያራጭ አመፅ እየወደመች፤ ምስራቅ ምዕራቦችን ከ25 ዓመት በኋላ ዳግም እንዳፋጠጠች ነዉ።