እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም
በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ እሳት መነሣቱን የገዳሙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ እሳቱ የተነሣው ከደኑ አካባቢ ሲሆን ወደ ገዳሙ ገና አልደረሰም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት መድረሱ ተሰምቷል፡፡ አባቶች እሳቱን ቆርጦ ለመከላከል እየሞከሩ ነው፡፡ በሰው ኃይል ለመከላከል የማይቻል ከሆነ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክልሉ ገልጦላቸዋል፡፡
ዳጋ እስጢፋኖስ አጼ ፋሲልና ሌሎችም ታላላቅ የኢትዮጵያ ነገስታት የተቀበሩበት ቦታ ነው።