የተፈተነው ማነው?

እስኪ ይኼንን በአንድ ትምህርት ቤት ለሦስተኛ ክፍል ተማሪ የቀረበ ፈተና ተመልከቱት፡፡ አሁን የሚወድቀው ማነው? ተማሪው ወይስ ራሱ ትምህርቱ? እስኪ የስሕተቱን ብዛት እዩት? ወይ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ተምረን ጽንሰ ሐሳቡን አልተረዳነው፣ ወይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተምረን ቋንቋውን በሚገባ አላወቅነው፤ ከሁለት ያጣን ሆንኮ፡፡ ለመሆኑ ፈተናው እንዲህ ከሆነ ትምህርቱማ ምን ሊሆን ነው? እንዲህ እያስተማርንና እየፈተንንስ ምን ዓይነት ትውልድ ይሆን የምናወጣው? ‹አለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል› አለ ያገሬ ሰው፡፡