የተቋማዊ ለውጥ ጥናቱን የደገፉ አለቆች በቀል እየተፈጸመባቸው ነው፤ የደ/ሰላም ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ፣ ካህናትና ምእመናን ዛሬ ለቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት አቤቱታቸውን ያቀርባሉ

St.Urael church bld00

ፓትርያርኩ እና አማሳኝ አማካሪዎቻቸው÷ ለቅዱስ ሲኖዶሱ የመልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጋራ የተቋማዊ ለውጥ ጥናቱን በመደገፍ በቅርበት የሠሩት ውጤታማው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ክብሩ ገብረ ጻድቅ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ በሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ላይ ግፊት አድርገዋል – ‹‹ታዝዤ ነው፤ የፓትርያርኩ ጭቅጭቅ አላስቀምጥ አለኝ፡፡›› (ዋ/ሥ/አስኪያጁ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን)

 

  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ይኹንታ የሰጠው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱ በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት እንዳይከናወን ተቃዋሚ ነን ባይ አማሳኞችን ያስተባበሩት ዘካርያስ ሐዲስና ኃይሌ ኣብርሃ በውጤታማው አስተዳዳሪ ላይ ‹‹አንተን ካልሠራንልኽ›› በሚል ሲዝቱባቸው ቆይተዋል፡፡
  • በተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው እና የአመራር ክህሎታቸው ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙት ውጤታማው አስተዳዳሪ፣ አንድ ዓመት ባልሞላ ቆይታቸው ከሙስናና ምዝበራ እንዲጠበቅ ያደረጉት የደብሩ ተቀማጭ ገንዘብ ከኻያ ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡
  • ውጤታማው አስተዳዳሪ ከተቆጣጠሯቸው የደብሩ ነባር ድጋፍ ሰጪ ጥቅመኞች ጋራ ቁርኝት በመፍጠር ሲዙቱባቸው ከቆዩ የአማሳኞች መሪ አንዱ ኃይሌ ኣብርሃ በምትካቸው ለመመደብ ለመመደብ መታቀዱ ተመልክቷል፡፡ ከደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል ከ13.3 ሚልዮን ብር በላይ በመመዝበር በፈጸመው የከፋ ሙስና ከእልቅና ከተወገደ በኋላ በደ/ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ያለተጠያቂነት የተመደበው አማሳኙ፣ እንደለመደው በልማት ስም ኻያ ሚልዮን ብሩን ለመመዝበር አሰፍስፏል!!! ‹‹ሳይገባው በውዝግብ የተመደበበትን የአስተዳደር ሓላፊነት ትቶ ራሱ በሚሾፍረው ሚኒባስ ከመገናኛ – ጣፎ – ሰንዳፋ እየሸቀለ ያመሻል፡፡›› /ታዛቢዎች/
  • በሐምሌ ፳፻፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከውጤታማው አስተዳዳሪ ጋራ በመግባባት ሓላፊነቱን በአግባቡ የተወጣውና የአገልግሎት ዘመኑን እያጠናቀቀ የሚገኘው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ በስኬት የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት ባለፈው እሑድ በተከበረው የቅ/ዑራኤል ወርኃዊ በዓል ላይ በዝርዝር በማቅረብ ተቃውሞውን በይፋ ገልጧል፡፡
  • ልማደኛ አማሳኞች በውጤታማው አስተዳዳሪ የተገታባቸውን ሕገ ወጥ ጥቅም ለማስቀጠል አለቃውን ከሓላፊነት ከማሥነሳት ባሻገር፣ እስከ ልዩ ጽ/ቤት በተዘረጋውና 22 ሚልዮን ብር ያኽል በዘረፉበት የምዝበራ ኔትወርካቸው አማካይነት ቀጣዩን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምርጫ ሒደት ለመቆጣጠር ቋምጠዋል፡፡
  • የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በመዋጋትና በአዲስ አበባ ደረጃ ለተቋቋመው የማኅበራት ኅብረት ምሥረታ ቀዳሚ አስተዋፅኦ ያደረገው የቅዱስ ዑራኤል አካባቢ መንፈሳዊ ጎልማሶችና ወጣቶች ማኅበር ውጤታማው አስተዳዳሪ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸውን ተቃውሟል፤ የዐሥር ቀበሌዎች አንድነት የኾነውና ከኹለት ሺሕ በላይ ወጣቶችን ያቀፈው ማኅበሩ፣ አጥቢያውን ከአማሳኞች ኔትወርክና ከልማደኛ መዝባሪዎች ለመጠበቅ ተዘጋጅቷል፡፡