ሰበር ዜና: አጠቃላይ ጉባኤውን ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም ለማስያዝ ፓትርያርኩና ጥቂት አማሳኞች በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ ጫናቸውን አጠናክረዋል

Zekarias Addis a day light robber

  • አማሳኞቹ በአጠቃላይ ጉባኤው የሚሳተፉት በታዛቢነት ብቻ ኾኖ ሳለ የውይይት መድረኩን ተጠቅመው የፓትርያርኩን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው!›› ቅስቀሳ ለማጠናከርና ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ እንዲወጣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የሚያደርጉት ጫና እንደማይወክላቸው የአዲስ አበባ ልኡካን እየገለጹ ነው፡፡
  • ‹‹ሰሞኑን መቅሠፍት አለ›› በሚል ከንቱ ማስፈራሪያ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ከመፍጠር አልፈው አካላዊ ጥቃት ለማድረስም እየተሰናዱ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ የአማሳኞች እንቅስቃሴ አይወክለንም ያሉት ብዙኃኑ የአ/አ ገዳማትና አድባራት ልኡካን ለአጸፋ እንቅስቃሴ እየተዘጋጁ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡
  • በኹሉም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ኹለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት ከፍተኛ ዕውቅና በተሰጠበትና ይህም በጉባኤተኞች ደማቅ ድጋፍ በተረጋገጠበት እንዲኹም በማኅበሩ ላይ አንዳችም ተቃውሞ ባልተሰማበት ኹኔታ፣ አጠቃላይ ጉባኤው ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም እንዲይዝና በጋራ መግለጫው እንዲያካትት ጥቂት አማሳኞች የሚያደርጉት ጫና ፓትርያርኩን የበለጠ ከማዋረድ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው ታምኖበታል፡፡