“ኢሕአዴግ አርጅቷል። የሐሳብ ድርቀት ደርሶበታል” ኢንጂነር ይልቃል “ለኢትይጵጵያ ሕዝብ ጥልቅ ፍቅር አለን። ፣ ትልቅ አክብሮትት አለን” ኢንጂነር ይልቃል “ኢሕአዴግ የአሁኑ ትዉል የሚመጥን አይደለም” አቶ ዮናታን ተስፋዬ “በኢሕአዴግ ክራይቴሪያ ማግኘት ይሻላል፣ በአካዳሚክ ከማግኘት እየተባለ ነው “ “የካቢኔ የካድሬ ወንድምና እህቶች የጠለበ ሥራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ድንጋይ ነው የሚፈልጡት! ዶር መራራ ጉዲና ዶር መራራ መልእክት ለኢትዮጵይ ሕዝብ “የኢሕአደግ […]

ተከራካሪ “ፓርቲዎች” ኢህአዴግ፤ አቶ አሰመላሽ ገ/ስላሴ እና አቶ ሬድዋን ሁሴን (ዋና ተከራካሪ ማን እንደሆነ ባይነገርም ይታወቃል) አትፓ፤ አቶ አሰፋው ጌታቸው መድረክ፤ ዶር መረራ ጉዲና ሰማያዊ፤ አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ ዮናታን ተሰፋዬ “አንድነት”፤ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግል ምልከታዬን ሲሆን፤ ሰዎች በተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በዘንድሮ ክርክር አንድ ጥሩ ነገር […]

የኢትዮጵያ ህዝበ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎችን በመጠቀምም ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል፤ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል። ምስሎቹ በማህበራዊ መድረኮች […]

ከእስክንድር ናፍቆት እስከ አንድነት ዘመነ፤ አይዞህ ወንድም አለም!! …ምስላቸውን ተመልክቸ ፣ ታሪካቸውን ሰምቸ ስሜቴን ካናወጡት ጥቂት ምስሎች መካከል ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቅምጥል ከታዳጊ ናፍቆት በቅርቡ አባቱን ከታሳሪዎች መካከል ሲያፈላልግ የተነሳው የፖለቲከኛው ዘመነ ምህረት ልጅ አንድነት ዘመነ ተናጋሪ ምስልን ከሃገር ውስጥ ካየኋቸው ስሜት ኮርኳሪ ተናጋሪ ምስሎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። … ከሃገር ወጣ ሲባል ደግሞ አስተማሪው በሞት የተነጠቀው […]

በእኔ እምነት እንኳን ‘አማራ’ ‘ኦሮሞ’ና ትግሬ . . . የሚባል ማንነትም የለም – በግድ በቋንቋ ‘አንድ ናቸው’ ካልተባለ በስተቀር (እሱም ቢሆን ዘየው የተለያየ ነው – የሀረሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ ከጂማው ኦሮምኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ በቋንቋ ደረጃ እንኳን ልዩነት አለው – እንደ አይሪሽ እና ስኮት አርጋችሁ አስቡት) በተመሳሳይ መልኩ የተንቤኑ ከአድዋው ትግርኛ ተናጋሪ በተለየ ቅላፄ እና ዘዬ […]

የኢህአዴግ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው በነገው ዕለት በቴለቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ይጀመራል፡፡ የነገው ክርክር ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ የተመለከተ ሲሆን ነገ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ተደርጎ ቀን ሙሉ ኢህአዴግ እማይጥመውን ንግግር በመቀስ ሲቆርጦው ከዋለ በኋለ ማታ ከ 2 ሰዓት ዜና በሁዋላ ይቀርባል ተብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና መድረክ በፌዴራሊዝም ላይ በሚደረግ ክርክር እናዳይከራከር ተከልክለዋል፡፡ ህዝብ ከህዝብ ጋር እያናቆረ ያለው […]

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ ሕዝባዊ ትንቅንቅ ከገዢው ፓርቲ ጋር ይዟል። ሰማያዊዎች የሚያደርጉት ትግል የነጻነት ትግል ነው። የሚተማመኑት በማንም አይደለም በሕዝቡ ነው። በሕዝቡ ብቻ ! በእኛና በእናንተ ። ገዢው ፓርቲ ሕወሃት የሰማያዊ ተወዳዳሪዎችን እያሰረ፣ ከምዝገባው እየሰረዘ፣ የቅስቀሳ መልእክቶቻቸውን ሳንሱር በማድረግ አልስተላልፍም እያለ፤ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ሲጠሩ እየከለከለ፣ ህዝቡ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሰማ ትልቅ ጫና እያሳደረ ነው። ይሳካለታል ወይ […]

የመከላከያ እና የደህንነት ግምገማዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ::ቀጣዩ ግምገማ ከዛቻና ማስፈራራት ወደ ልመና ሊዞር ነው::ባለፉት ሳምንታት በመከላከያ ሰራዊት በምድር ጦር እና አየር ሃይል እንዲሁም በደህንነት መምሪያ ሲደረጉ የነበሩ ግምገማዎች በስፋት ቀጥለው አባሎቻቸውን እያሰሩ እና እያስፈላሩ በመጭው ሳምንቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል:: በመፍረክረክ ላይ ያለው ስርአቱ ባደረበት ከፍተኛ ስጋት እና በገባበት አጣብቂኝ ተከትሎ በመከላከያ ውስጥ […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የሚል ስያሜ አግኝተዋል!! ጋዜጣዊ መግለጫ ዋሽንግተን ዲሲ፤ አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች በአንድነት በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና በፌስቡክ ገጻቸው የተናገሩትን አጸያፊ እና ሃላፊነት የጎደለው ውሸት እንዲያርሙ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመገናኛ ብዙሃን ታዳጊ ወጣት በሪቱ ጃለታ የተናገሩትን የ20 ሚልዮን ዶላር የፈጠራ ታሪክ እስካሁን […]

‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ […]

የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ ወያኔ በፈበረካቸው ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው:: የምንሊክ ሳልሳዊ የሳምንቱ መልእክት የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት አቶ ገረመው ገ/ጻድቅ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ከችሎት ውጭ በግላቸው መወሰናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የምዕ/ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ መዋቅር ዕጩዎቻችን ያለ አግባብ ተሰርዘውብናል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ የነበር ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ […]

ወንበዴው መንግስት ተብየው ሽፍታ ሽፍትነቱን ቀጥሎበታል፡፡ የፍትህ ስርአትን ፍርድ ቤትን እንደ መጨቆኛ መሳሪያ የሚጠቀመው መንግስት በሚዘውረው ፍርድ ሲሞግቱት፤ ሲሸነፍ መክሸፍ ልማዱ ሁንዋል፡፡ የፍትህ ስርአቱ የደረሰበት ቁልቁለት፤የስርአቱን እብለት በማጋለጥ በኩል ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ታላቅ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች የነ አብርሃ ደስታ ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በስራቸው የተለያዩ ዛቻዎች ማስፈራሪዎች በደህንነቶች፤በፖሊሶች፤ […]

᎐ተጨማሪ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል • ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ • ‹‹ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው›› የሺዋስ አሰፋ • ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፣ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› ዳንኤል ሺበሽ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እንዲሁም የዓረና ትግራይ ፓርቲዎች አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ […]

የምርጫ ጊዜ ነው ይሉናል። ባለው ሕግ መሰረት፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ በመሳሰሉት ሜዲያዎች መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ማድረግ መብታቸው ነው። በዚህ መሰረት የቅስቀሳ መልእክቶቻቸው እንዲተላለፉላቸው ይጠይቃሉ። ሆኖም ሜዲያዎቹ ፣ የቀረቡት መልእክቶች ሕወሃትን እና ሕወሃት ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠራቸውን ተቋማት የሚተቹ በመሆናቸው ሊያስተናግዷቸው ፍቃደኛ አልሆኑም። ሕወሃትን መተቸት ብቻ አይደለም፣ አረንጓደ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ያዘሉ መልክቶችም እንደ ወንጀል የተቆጠረበት ሁኔታ ነው […]

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ […]

ህዘባዊ እንቢታ ማለት ዜጎች የስርአት ለውጥን ሆነ መብታቸውን ለማስከበር በብዙ ቁጥር ሆነው በጋራ አንድን ነገር ማደረግ ወይ አለማድረግ ነው። አለቀ። ብብዙ ቁጥር ተቃውሞ አደባባይ መውጣት በጋራ ልናደርጋቸው ከምንችላቸው በትንሹ ከሺ ነገሮች ውስጥ አንዱ የህዝባዊ ተቃውሞ አካል ነው። ተቃውሟችንን ለመግለፅ በጋራ ልናደርጋቸው የሚቻሉን ነገሮች ሁሌ የግድ ከባድም አጋላጭም መሆንም የለባቸውም። በይበልጥም ስንጀምረው። ማወቅ ያለብን አምላክ የሰውን […]

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ በቅርቡ ‹‹ወገኔ›› በሚል ያወጣውን ዜማ ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን […]

የአባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው […]

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት። “ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!” አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት […]

የአቶ ኤርሚያስ ለገሰ እና የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የደብዳቤ ምልልሶች…ሶስቱም ደብዳቤዎች እዚህ ይገኛሉ ከአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመጀመሪያ ደብዳቤ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣ ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። […]

ልጄ አስራ ሁለተኛ ክፍል ስለጨረሰ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ… የሚል ግብዣ ደርሷችሁ አያውቅም? እናንተም ፋሽኮ ቪኖ ወይንም እናትና ልጅ አረቄ ይዛችሁ ድግሱን ለማድመቅ ሳትሄዱ አልቀራችሁም – የዚያን ዕለት ጎረምሶቹ የቀለጠ ፓርቲ ደግሰው እስኪነጋ ይጨፍራሉ አሉ… ይህስ ይሁን። ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ መሆኑን አንድም ቀን ሲናገር ሰምታችሁ የማታውቁት በቅርብ የምታውቁት ሰው ፣ እንዲያውም በመደበኛ ትምህርት ከስንተኛ […]

“ሸላሚም እኛ፣ ከሳሽም እኛ! “ አብርሃም ሰለሞን የ25 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ያሳደገው ኢሕአዴግ ራሱ (ወይም ዘመነ መንግስቱ) ነው፡፡ በቤተልሄም የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ IT መምህር ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ መልካም ዝና ነበረው፡፡ በ2006 በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ውድድር ላይ ይዞ በቀረበው የመምህራን ዳታ ቤዝ እና የመማሪያ ማኑዋል ዝግጅትን አሸናፊ መሆን ከቻሉ ሦስት ወጣቶች አንዱ ለመሆን […]

ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክ ኣባል ናቸው። በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሂወታቸው ልታልፍ ምንም ኣልቀረላቸውም ነበር። ይህ ድብደባ በ17/ 2007ዓ/ም ማታ 1 ሰዓት ኣከባቢ በ1ፖሊስ ድምብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የፈጥኖ ደራሻ ደንብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የመከላከያ ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች […]

ኢቢሲ የመኢአድን መልእክት ላለማስተላለፍ የሰጠው አንዱ ምክንያት፣ መልእክቱ የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን ይጻረራል የሚል ነበር።፡ “ ..የገዢ ፓርቲ ካድሬዎችና አመራሮ በፓርቲው መሪዎች፣ አባላቶችና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነና ግፍ የተሞላበት ድብደባ ፣ መሰደድና ሜታሰርና የመግደል ዕጣ ሲደርስባቸው ቆይቷል፤ ..” የሚለው የመኢአድ አባባ የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11፣ ንኡስ አቀንጽ 2ሀ ላይ የተመሰረተዉን ይጻረራል […]

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆነው አግባው ሰጠኝን ጨምሮ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮች ጠበቆች በፖሊስ ላይ አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ሊመሰርቱ ነው፡፡ ፖሊስ ዛሬ የካቲት 25/2007 ዓ.ም በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ላይ የመጨረሻውን ምርመራ ሊያሰማ ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም በቀጠሮው መሰረት አመራሮቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ባልቀረቡበት ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሻለሁ ብሎ መዝገቡን እንደዘጋ ለፍርድ […]

ብዙ ሰዎች ስለ እነ ትዕግሰቱ አወሉና ግብረ አበሮቹ መፃፍ ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡ ምክንያታቸውም ደረጃቸውን ከፍ ያደርገዋል የሚለው አንዱ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ከፍ ቢሉም ቢወርዱም እውነቱን ሰው አውቆት ፀሐይ ሞቆት መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሰለዚህ እፅፋለሁ፡፡ በቅርቡ የወጣ “የእኛ ፕሬስ ጋዜጣ ላይ አቶ ትዕግሰቱ በእርሱ ብሶ ቱግ ቱግ እያለ የሰጠውን ቅጥፈት የተሞላበት ቃለ መጠይቅ አይቼ […]

የአንድነት አባላትን ያካተተው የሰማያዊ ፓርቲ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ትራክቶችን በማሰራጨት ቅስቀሳ ዛሬ ጀምሯል። ለቅስቀሳ የተሰማሩ አባላቶቹ እየታሰሩ ነው። ያ ብቻ አይደለም። በቴሌቭዥን ክርክር እነ ዶር በየነና ሌሎች ሲቀርቡ፣ የሰማያዊ ፓርቲ እንዲቀርብ አልተደረገም። በራዲዮ የቅስቀሳ መልእክቶቻቸዉን ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንዲያቀርቡ በተጠየቀው መሰረት፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ኦዲዮ አዘጋጅቶ ቢልክም ፣ «ይሄ ካልተስተካከለ፣ ይሄን ካላወጣችሁ፣ ሙዚቃ ማድረግ አትችሉም ..» […]

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ የሳምንቱ ዜናዎች እና ዘገባዎች ይዘን እንኳን ለአንድ መቶ አስራ ዘጠነኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!እያልን ስለ አድዋ ልዩ ዝግጅት = ግጥም = ትረካ = በሙዚቃ ታጅቦ ቀርቦላቹሃል ያዳምጡት:: እንኳን ለአንድ መቶ አስራ ዘጠነኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም […]

በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ የተጀመረው እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ1957 በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን በ1955 የወጣውን ህገ -መንግስት መሰረት ያደረገ ንጉሱንና የላይኛውን ቤት ወይም ሴነቱን የማይመለከት ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት ኣባላትን መምረጥ ተጀምሮ ነበር። እማኞች ሲነግሩን ምርጫውና ቆጠራው ግን ሃቀኛ ነበር ኣሉ። ታዲያ ንጉሱ በነበሩበት ዘመን የነበሩት ምርጫዎች ጅማሪያቸው መልካም ቢሆንም ዓለም በማህበራዊ […]

በቅድሚ የኢሳት አድማጭ እንደሆንኩ ይታወቅልኝ። ኢሳት ከኢቲቪ ( 400 እጥፍ ይሻላል) “አሉ አሁንም ፖለቲከኞች አሉ የሚያወሩ። ስንሰባሰብ ሁሉ ጄነራል እንትና ይሄን አድርገው፤ እና ኮሎኔል እንትና …እኔ ስሙን ልከየት እንደሚያመጡት አላወቅም። እንትን ሬዲይ ይጎረጉራሉ። አገር ቤት ጠዋት ተነስትው አንድ ወንድም ትልቅ የ እግዚባሄር ሰው ነው ፣ እኮ ተነስቶ ዜና ልሰማ ነው አለ። የምን የአገር ቤት … […]

በከፊል የተቀዳውን የፓስተሩን ንግግር የሰማሁት “ሰልማ” የተሰኘውን ፊልም አይቼ እንደተመለስኩ ነበር። በዚህ አመት ለአራት የኦስካር ሽልማት የበቃው “ሰልማ” ፊልም ኦፕራ ዊንፍሬን ጨምሮ ምርጥ አክተሮች ይተውኑታል። ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ1965 በዩናይትድ ስቴትስ የጥቁሮች የመምረጥ መብት ገፈፋን ተከትሎ፣ ዶክተር ማርቲን ሉተር ይህ መብት እንዲከበር የሚያደርገውን ትንቅንቅ ያሳየናል። ፓስተር ሉተር ለዜጎች የመምረጥ መብት እንዲከበር ያለማቋረት በመስበኩ ሲደበደብ፣ ሲንገላታና ሲታሰር […]

መግቢያ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ ስሞችን፣ መርኆዎችን፣ ተግባራትን፣ ባጠቃላይም ማንነትን ተከናንቧል። ይህ ማለት፤ በሂደቱ እየተቀያየረ የሄደ ድርጅት ነው። ሲነሳ፤ አሁን የያዘው እምነት፣ ግብና አሠራር አልነበረውም። እግረ መንገዱን ለዕለቱ የሚረዳውን የፖለቲካ አቋም እየውለበለበ ተጓዘ እንጂ፤ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ አቋም አልነበረውም። ይህ የሚነግረን፤ ይህ ድርጅት፤ አጋጣሚዎችን ተጠቃሚነትን፣ ሥልጣንን፣ ቂምና በቀልን፣ የሕልውናው መሠረቶች አድርጎ የተጓዘ […]

ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል። የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም […]

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንምካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካና የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የምንሻኮተው ብዙዎቹ ጎሳዎች/ነገዶች ስማችንየለም፡፡ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከተለያየ […]

በአሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ጥንቃቄ በሚያስፈልገው ጊዜ ትገኛለች፡፡ ሃላፊነት እሚሰማው ተቃዋሚ ፓርቲ እና ለህግ ተገዢ የሆነ ጥበበኛ ገዚ ፓርቲ ትሻለች፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በብሄር ፍትጫ የተወጠረች እና ልትበጠስ ትንሽ የቀራት ስስ ክር ሆናለች፡፡ አገሪትዋ በአንድ በኩል ኢህኣዴግ እሚባል ላፀደቀው ህግ ደንታ የሌለው ጠበንጃ አምላኪ ጉጅሌ ስትታመስ በሌላ በኩል ደግሞ ኢህኣዴግን በማንኛውም መንገድ ከስልጣን ለማውረድ ብቻ […]

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም […]

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ […]

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን […]

በዓለማዊው ህይወታችን ሳያዩ ማመን ከባድ ነው፡፡ ባሌ እባብ ሊሆን ይችላል ብሎ መኖርም ከባድ ነው! እርግጥ፤ “አንድ ቀን ቤተ መንግሥት ውስጥ እነቃለሁ” ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ግን ድካም አለበት፡፡ በቀስት ተጭሮ እንደመንቃት ቀላል አይደለም፡፡ ቃልኪዳንን መጠበቁን ይጠይቃል፡፡ ለማወቅ ጉጉት ለከት ማበጀትም ይፈታተናል፡፡ በልጦ መገኘትን ጠንቅቆ መቻል እንደው ያለጥረት የሚገኝ፣ ክብሪት እንደመጫርም የቀለለ፣ የዘፈቀደ ነገር አይደለም፡፡ በሀገራችን ተፎካካሪን […]

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡ ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ‹‹መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ›› እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ […]

የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አሳወቁ:: ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ባለመስራቱና የገዢውን ፓርቲ ዓላማና ፍላጎት የሚያስፈጽም ተቋም ሆኖ በምርጫ መወዳደር ለተቋሙ ኢ-ፍትሃዊ ተግባር እውቅና መስጠት ነው ያሉት በአቶ አበባው መሐሪ የሚመራው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ስብስብ የህዝብ ግኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋሁን አለምነው እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ መኢአድ እንደ ፓርቲ በምርጫው የሚሳተፍ […]

ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት ሴቶችን በሚመለከቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን […]