ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው መደብደባቸውን ለቢቢኤን ሬድዩ ተናገሩ!
ወንበዴው መንግስት ተብየው ሽፍታ ሽፍትነቱን ቀጥሎበታል፡፡ የፍትህ ስርአትን ፍርድ ቤትን እንደ መጨቆኛ መሳሪያ የሚጠቀመው መንግስት በሚዘውረው ፍርድ ሲሞግቱት፤ ሲሸነፍ መክሸፍ ልማዱ ሁንዋል፡፡ የፍትህ ስርአቱ የደረሰበት ቁልቁለት፤የስርአቱን እብለት በማጋለጥ በኩል ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ታላቅ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች የነ አብርሃ ደስታ ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በስራቸው የተለያዩ ዛቻዎች ማስፈራሪዎች በደህንነቶች፤በፖሊሶች፤ በዳኞች ሲፈጸምባቸው ቆይተዋል፡፡ ከዚያም አልፎ ተርፎ የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም ክስ ተመሰርቶባቸዋል፡፡ የጥብቅና ፍቃድህ እንሰርዘዋለን የሚል ማስፈራሪያም ደርሶባቸዋል
እርሳቸው ግን ይህ ሁሉም ደርሶባቸው እውነትን ከማፍረጥረጥ፤ የአምባገነኑን የፍትህ ስርአት ሸፍጥ ከማጋለጥ አልቦዘኑም፡፡ በዚህ ድርጊታቸው የተበሳቸው መንግስት በዛሬው እለት ታስቦበትና ታቅዶበት በሚመስል መልኩ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶም ለቢቢኤን አስረድትዋል ቢቢኤን የዛሬ የመጋቢት 1 ፕሮግራም
ቢቢኤን High Quality like emoticon
Low Quality like emoticon http://goo.gl/UsS5lu
ይህ በርግጥም ስርአቱ በራሱ ፍርድ ቤት እየደረሰበት ያለውን ሽንፈትና ክሽፈት የሚያሳይ ነው፡፡ ወንበዴ መንግስት ይሄው ነው ሰበብ ፈልጎ ያስረሃል ያለ ስምህ ስም ይለጥፍብሃል ለማሰር አልመቸው ካልክ በዱርየ ያስደበድበሃል!