የምርጫ ቅስቀሳ እገዳ – ባንዲራ ማዉለብለብ ወንጄል ሆኗል – ግርማ ካሳ

የምርጫ ጊዜ ነው ይሉናል። ባለው ሕግ መሰረት፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ በመሳሰሉት ሜዲያዎች መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ማድረግ መብታቸው ነው። በዚህ መሰረት የቅስቀሳ መልእክቶቻቸው እንዲተላለፉላቸው ይጠይቃሉ። ሆኖም ሜዲያዎቹ ፣ የቀረቡት መልእክቶች ሕወሃትን እና ሕወሃት ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠራቸውን ተቋማት የሚተቹ በመሆናቸው ሊያስተናግዷቸው ፍቃደኛ አልሆኑም።
ሕወሃትን መተቸት ብቻ አይደለም፣ አረንጓደ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ያዘሉ መልክቶችም እንደ ወንጀል የተቆጠረበት ሁኔታ ነው ያለው። አይገርማችሁ ? እነ በላይ ዘለቀ የተፋለሙበት፣ እነ አጼ ዮሐንስ ደማቸውን ያፈሰሱበት ሰንደቅ የረከሰበት ዘመን ነው።
1. አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ኢትዮጵያን አይወክልም ነው ኢቢሲ እያለን ያለው።
ኢቢሲ የሰማያዊ ቅስቀሳ መልእክቶችን እንደማያስተላለፍ ከላካቸው ስድስት ደብዳቤዎች በአንዱ የሚክተለው ይገኝበታል፡
«በላካችሁት የምርጫ ቅስቀሳ መልእክት፣ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልእክታችሁ ዉስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው የሰንደቅ አላማ ምስል፣ የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክል፣ የሕግ መግስቱን አንቀጽ 3 እና የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 16 እና አንቀጽ 23 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2ን የሚጻረር ሆኖ አግኝተነዋል»
2. ግፍ በአገዛዙ ታጣቂዎች ደርሶብናል ብሎ መናገር አይቻልም
መኢአድ በቅስቀሳ መልእክቶቹ በአባላትና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርሰዉን ግፍ ለሕዝብ ለመግልጽ « የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና አመራሮች በፓርቲው መሪዎች፣ አባላቶችና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነና ግፍ የተሞላበት ድብደባ፣ መሰደድና የመታሰርና የመግደል እጣ ሲያደርሱባቸው ቆይተዋል » ይላል።
የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች ነፍሰ ጡር ሴቶች ሲደበድቡ፣ ብእር ያነሱ ሰላማዊ ኢትዮጵያዉያን መሬት አስተኝተው አጥንቶቻቸዉን ሲሰባብሩ በግልጽ በአደባባይ የተመለከትነው ነው። ሆኖም ኢቢሲ ለምን በሕዝብ ላይ ግፍና ጭካኔ የሚፈጽሙት ጨካኝ የሕውሃት ካድሬዎችና ታጣቂዎች ተነኩ በሚል ነው መሰለኝ፣ የስነ ምግባር ኮድ የሚሉትን በመጥቅስ መልክቱን ለማስተለፍ ፍቃደኛ አልሆነም።
«ይህ መልዕክት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11፣ ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ ላይ የተመለከተውን የሚጻረር ሆኖ አግኝተነዋል» የሚል ምላሽ በመስጠት ነው የፓርቲዎችን የመቀስቀስ መብት የረገጠው።
3. ምርጫ ቦርድና ፍርድ ቤት መተቸት አይቻልም
ምርጫ ቦርድ የሕወሃት ቅርንጫፍ እንደሆነና በቀጥታ ከሕወሃት በሚሰጥ መመሪያ እንደሚሰራ የታወቀ ነው። በአንድነት ፓርቲ ላይ የተወሰደው ኢ-ሕገ መንግስታዊ እርምጃ እንኳን ተራው ኢትዮጵያዊ፣ ራሳቸው የአገዛዙ ደጋፊዎችን ሁሉ ሳይቀር አፍ ያዘጋ፣ ምርጫ ቦርድን መሳቂያ ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቶችን በተመለከተ፣ በአብዛኛዉ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው። ዳኞች ለምን ፍርድ ቤቱን ተቻችሁ በሚል የሰባት ወራት እሥር የሚበይኑ፣ ከ20 ጊዜ በላይ ዜጎችን ፍርድ ቤት እየተመላለሱ የፍርድ ሂደቱና ክርክሩ እንዲቀጠል ማድረግ የተሳናቸው ፣ መጨረሻ ላይ ከሕወሃት አመራር ይሄን በይኑ የተባሉትን ወጥተው የሚያነቡ፣ ለሆዳቸው ያደሩ፣ ጥቁር ካባ የለበሱ ካድሬዎች መሆናቸውን አገር ሁሉ ያውቀዋል።
መድረክ፣ በምርጫ ቦርድና በፍርድ ቤቶች ያላቸው ችግር “ ..እስከአሁን ድረስ በታዩት የምርጫ ሙከራዎች እና ምርጫ ነክ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በሃገራችን የኢሕአዴግን ፍላጎት ከማስፈጸም ያለፈ ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አልታየም ..የዳኞች ምልመላ እና ሹመት በሕግ እወቀት፣ ልምድና ሃቀኝነት መመስረቱ ቀርቶ ለገዥው ፓርቲው ባለ ቅርበት እና የ እርሱን ፍላጎትና ተጽእኖ ለመቀበል ፈቃደኝነት ኡእተመሰረተ በመሄዱ የዳኝነት ሰርራቱ ነጻነት የለም ከሚባልበት ደረጃ ላይደርሷል ..” በማለት ነበር በቅስቀሳ መልእክቱ ያቀረበው።
ሆኖም « እነዚህ መልእክቶች በሕግ መንግስቱ የተቋቋሙ የዲሞክራሲ ተቋማትን ሕልዉና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ፣ ህዝቡ በፍትህ አካላት ላይ አመኔታ እንዲያጣና መረጋጋት እንዲጠፋ የሚያደረጉ መልእክቶች በመሆናቸውና ሕገ መንግስቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ-ምግባር ሕጉን አንቀጽ 11/2 ሐንና 29/1 እንዲሁም የድርጅታችንን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚጻረር ሆነው አግንተናቸዋል » ሲል ኢቢሲ/ኢቲቪ የመድረክን መልእክት አላስተናግድም በማለት የመድረክን ሕጋዊ መብት ረግጧል።
እንግዲህ እንደምናየው ገዢው ፓርቲ መልእክት እንዳያስተላልፉ እያገደ ያለው በዋናነት ሰማያው ፓርቲን ሆኖ ፣ በተወሰነ ደረጃም መድረክ እና መኢአድ መሆኑን እያየን ነው።
ሰማያዊም ሆነ ሌሎች እንደ ኢቢሲ ያሉትን ተቋማት ባይፈትሹ ኖሮ፣ የነዚህ ተቋማት እርቃን ባልወጣ ነበር። ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ አገር ሁሉ እያወቀው ነው። እየተመዘገበ ነው። አላወቁትም እንጂ ሕወሃት እየቀለለና እየወደቀ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተተፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው። በራሳቸው እንደማይተማመኑ፣ ህዝቡን እንደሚፈሩአን እንደደነገጡ አመላካች ነው። ምናልባት አሁን የሚያደርጉትን በዚህ በዚያ አሸንፈን ካለፍነው ለማንሰራራት ይረዳናል ብለው ይሆናል።፡ሆኖም በሚያስገርም ሁኔታ ምርጫው እየጎዳቸው ነው።11033173_788905021194434_841547304513731900_n