የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ። “ሃሎ?” “ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?” “ነኝ፣ ምን ፈለግክ?” “ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።” “ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?” “99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!” “0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?” “አዎን […]

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ አዳዲስ ዜና ዘገባዎችን እና ካለፈው የቀጠለ የሰሃራ በረሃ ተጓዦች ትዝታን የሚያስቃኝ ትረካ ቀጣዩን ክፍል 3 እና 4 ይዘን ልናስደምጣቹ ተዘጋጅተናል::የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባዬ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጸጋዬ አላምረው ከስደት ካሉበት ያሳለፉትን የፖለቲካ ሕይወት እና የአንድነት ፓርቲን በተመለከተ ያደረጉት ቃለመጥይቅ በዚህ ፕሮግራም ይቀርባል:: ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ!!

ይሄ ሁሉ ናዳ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ እንደ ዝናብ ወርዶ የሚቀጠቅጠኝ ህሊናን አስቶ የሚደበድበኝ፤ ተስፋየን አሟጦ፡ በጭካኔ ረግጦ፤ ሙቀትና ብርዱ አዘቅቱ ንዳዱ፡ ችግር ቸነፈሩ ስቃይ ግርግሩ መከራው በርትቶ የሚያደናግረኝ ምንድነው ነገሩ? ግራ ግብት አለኝ!? እኮ ለምን ሆነ?በኔ ጠነከረ፤ ጥላቻና ክፋት እየተካረረ፡ ግድያና እስራት፡ ወከባና እንግልት፡ ምነው እንዲህ ሆነ? ተደጋገመብኝ፡ በረታ ጨክነ፡፡ ዘመኑን አርዝሞ፡ ክንዱን አፈርጥሞ፡ በላዩ […]

የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ተነፍጎ ባገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ አገዛዝ ስረ ወድቆ ፍዳውን እያየ ነው። ስርአቱ ላለፉት 24 አመታት በሃገራችን ውሰጥ በፈጠራቸው ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ቀውሶች ምክንያት ተተኪው ወጣት ትውልድ ባስደንጋጭ ሁኔታ በየጊዜው አገሩን ጥሎ ሲወጣ በባህር ውስጥ በመስመጥና፤ ከዛም የተረፈው በአፍሪካና በአረብ አገሮች እጅግ አሰቃቂ ለሆኑ ውርደት ስቃይና ግድያ ተጋልጧል። ከምርጫ ሂደት ጋር በተያያዘ፤ […]

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ከመቶ ዓመታት በላይ ነው። ይኼ ግንኙነት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የእኩልነትና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ እንደ ነበረ ታሪክ ያስታውሳል። መንግሥታት ቢለዋወጡም በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተመሰረተው የቆየ ግንኙነት አይፈርስም የሚል እምነት አለኝ። የኢትዮጵያ ስደተኞች አሜሪካን የመጀመሪያ መድረሻ አድርገን አሜሪካዊ የሆንንበትና ወደፊትም የምንሆንበት ዋና ምክንያት የአሜሪካ አስኳል እሴቶች–ነጻነት፤ የግለሰብ ክብር፤ ፍትህ-ርትእ፤ የሰብአዊ መብቶች […]

እንደወትሮው ከኢትዮጵያ የሚመጡ ዜናዎች አያስደስቱም፤ ሀገራችን ከጥፋት ማማ ላይ መድረሷን ያሳያሉ። ለአራት ጊዜ በሸፍጥ ተመርጫለሁ ብሎ ሥልጣን ላይ ቂጥ ያለው ወያኔ ለአምስት ጊዜ ሊያወናብድ እየተዘጋጀ ነው። በየጊዜው ጥቂቶች ብቻ በገሃድ የምርጫውን ሸፍጥነት ሲያጋልጡ ምዕላተ ሕዝቡ ግን ከሹሹክታ ያለፈ እንደ ቡርዲና ቡርኪነፋሶ ዳር እስከዳር በአደባባይ ወጥቶ ሲቃወም አይታይም፤ ዘንድሮ ግን ሌላ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ሣይጠብቅ እርሰ […]

“የተራቡትን መርጠን ከምንቸገር ያው የጠገበው ይሻለናል” የሚል መልክት ያላት ማዘናጊያ ሀሳብ በየፌስ ቡክ ላይ ተበትናለች። ሲጀመር በልቶ ጠገብኩ የሚሉ መቼ ነገሱብንና። በዛ ላይ ያለአባከና በሰፊው የለመደ ሆድ ለሌላ አምስት አመት ከበሉን ለመረጃ እንኳ አጥንታችንም አይጋኝም አትቀልዱ። የሚኖር አይመስለኝም እንጂ በዚህና “ድምጽ መሰረቁ ላይቀር” አይነት አንድምታ ባላቸው ምክንያቶች ተንተርሶ ለወያኔ ድምፁን የሚሰጥ ካለ በቁሙ የሞተ ነው። […]

ገዢው ፓርቲ በሰላማዊ ፓርቲዎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረገ ነው። የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ታስረዋል። የአንድነት ፓርቲን አግዶ እንደ ሰማያዊ ያሉትን እያዋከበ ነው። ነጻ ጋዜጦች ተዘግትዋል። ትግሉ የሕዝብ ጉዳይ እንጂ የድርጅት ጉዳይ ባለመሆኑ፣ የድርጅት መሪዎችን በማሰር፣ ድርጅቶችንም በማገድ፣ የህዝብንም ሆነ የታጋዮችን የነፃነት ፍላጎት መግታት አይቻልም። የአገዝዙን አፍናና በትር ለመቋቋም፣ ህዝቡን ወደአንድ አደረጃጀት ለማምጣትና በተናጥል […]

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ አዳዲስ ዜና ዘገባዎችን እና ካለፈው የቀጠለ የሰሃራ በረሃ ተጓዦች ትዝታን የሚያስቃኝ ትረካ ቀጣዩን ክፍል 3 እና 4 ይዘን ልናስደምጣቹ ተዘጋጅተናል::የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባዬ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጸጋዬ አላምረው ከስደት ካሉበት ያሳለፉትን የፖለቲካ ሕይወት እና የአንድነት ፓርቲን በተመለከተ ያደረጉት ቃለመጥይቅ በዚህ ፕሮግራም ይቀርባል:: ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊብያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በእንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት። መቼም ሼም የሚባል ነገር ከነሱ ዘንድ ጠፍቷል። በስራቸው ማፈር ሲገባቸው አይናቸውን […]

የዙሉ አክራሪዎች በኢትዮጵያዉያን እና ሌሎች የአፍሪካ ዜጎችን ላይ ኢሰብዓዊ ጥቃት በሚፈጽሙበት ጊዜ፣ እንደ ናይጄሪያ ያሉ አገሮች በዙማ መንግስት ላይ ጠንካራ አቋም ወሰዱ። ዙማ ተጽኖ ሲበረታባቸው፣ አስቸኳይ እርምጃዎች ለመዉሰድና ነገሮችን ለማረጋጋት ተገደዱ። ከነናይጄሪያ በደረሰው ግፊትና ጫና በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ለጊዜውም ቢሆን መረጋጋት ታየበት። በዚሁ ሁሉ ግን ሕወሃት/ኢሕአዴጎች የተከሰተዉን ቀውስ አሳንሰው በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያዉያን ጥብቅና የቆሙ ሳይሆን፣ […]

ለምርጫዉ ቅስቀስ ምርጫ ቦርድ ከመደበው ገንዘብ 15 ሚሊዮን ብር የሚሆን ለኢሕአዴግ ሲሰጥ፣ ለ 270 መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎችን ላሰለፈው መድረክ፣ 2 ሚሊዮን ብር፣ ለ165 እና ለ139 መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎች ላሰለፉት ኢዴፓና ሰማያዊ ወደ ስምንት መቶ ሺህ ብር የተመደበላቸው ተመድቦላቸዋል። ለትግስቱ አወሉ ቡድን ግማሽ ሚሊዮን ብር ተፈቅዶለታል። አንድ የፓርላማ ተወዳዳሪ ብቻ ያሰለፉ ድርጅቶች ወደ አምሳ ሶስት ሺህ ብር ድጋፍ […]

ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይደረጋል። ሆኖም ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ እንዳሸንፈ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ባስቀመጠው ሰነድ አሳወቀ። አርባ ሰባት የሚሆኑ ድርጅቶች እንደሚካፈሉ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን አርባ አምስት የሚሆኑት ለፌዴራል ፓርላማ ተወዳዳሪዎች አሰልፈዋል። መንግስት ለመቆጣጠር አንድ ድርጅት 274 የፓርላማ መቀመጫዎችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ ባሰፈረው ሪፖርት መሰረት፣ ኢሕአዴግ ለ501 የፓርላማ […]

በሊቢያ ቤንጋዚ አካባቢ ያሉ ወገኖቻችንን ወደ ግብድ ለመዉሰድ ታስቧል። እርሱ ላይ ችግር የለም። በትሪፖሊ/ሚስራታ ያሉትን ግን በሱዳን በኩል ለመዉሰድ ነው ኢሕአዴግ እየሰራ ያለው። ይሄ በጣም አደገኛ ነው። እዚህ ላይ ወገኖቻችን በሱዳን በኩል እንዲወጡ ቢደረግ 100% አይሰስ ይይዛቸዋል ማለት አይደለም። ምናልባት በወታደራዊ ኮንቮይ ታጅበው ይሆናል ለማስወጣት የታሰበው። ቢሆንም ትልቅ ሪስክ ነው እየተወሰደ ያለው። አንደኛ ከዚህ በፊት […]

ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል አንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም […]

የምድራችን ግፉአንና ምስኪኖች እንባና ጩኸት፣ ዋይታና ሰቆቃ ምድሪቱን ክፉኛ እየናጣትና እያናወጣት፣ እያስጨነቃት ነው፡፡ በዚህች ክፋት በሰለጠነባት፣ ዓመፃ በነገሠባት ዓለማችን ጆሮን ጭው የሚያደርግ፣ እግዚኦ የአንተ ያለህ! የሚያሰኝ ሌላ ክፉ ወሬን እያየን፣ እየሰማን ነው፡፡ ገና አንዱን ኀዘናችንን በቅጡ ሳንወጣው፣ እንባችን ‹‹የፍትሕ ያለ!›› በሚል በጉንጫን ላይ እየፈሰሰ ባለበት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቁ ኢዮብ የኀዘን መርዶን በላይ በላዩ እየሰማን፣ […]

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ […]

‹‹ሰይፍህን አንሣ፣ ክተት ሠራዊት፣ ዝመት ለፍቅር፣ ሰልጥን ለምሕረት፡፡›› (አርቲስት ዘሪቱ ከበደ) ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በቆንጨራ ለተጨፈጨፉ፣ በሚያሰቅቅና በሚዘገንን ኹናቴ እሳት በቁማቸው ለተለቀቀባቸው፣ ሀብት ንብረታቸው ለተዘረፈባቸውና ለጋየባቸው፣ የጦርነትና የእልቂት አውድማ በሆነችው በአገረ የመን ለሞቱና በጭንቅ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችንና በተለይም ደግሞ በሊቢያ በአይ ኤስ የአክራሪና ጽንፈኛ ቡድን የተሠዉትን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን አስመልክቶ በጥቂቱም ቢሆን የጥበብ ባለ ሙያዎቻችን በሥራዎቻቸው […]

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣ እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“ አገኘሁ እንግዳ ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት […]

በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው […]

ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ […]

“መንግስት በሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሰፋፊ ሰራዎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ቴድሮስ በቤንጋዚ ያሉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ መንግሰት በኩል፣ ትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ ከሱዳን መንግሰት ጋር በመተባበር ከሊቢያ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።” የሚል በዶር ቴድሮስ አዳኖም ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አነበብኩ። የዝግጅቱን ዝርዝር ባላውቅም ዝግጅቶች እየተደረጉ ሊሆኑ እንደሚሉ […]

የ24 አመታት ሂደቶች .. ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው እንዳይኖሩ የሆነበት…ለአንድ ወገን ያደላ እና በፓርቲ አባልነት ላይ የተመሰረተ አድልኦ የተንሰራፋበት … ጥቂት የፖለቲካ ቱጃሮች ብዙሃን ደሆች የፈሉባት … አምባገነንነት የነገሰባት ….ሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆቿን አቅፋ እንዳታኖር የተደረገበት እና ወደ ስደት የተበተኑበት … ይህንን ሁሉ ተሸክመን ከትከሻችን ለማውረድ የምንታገልበት ወቅት … ከትግሉ ፍሬዎች አንዱ ሰማያዊ ፓርቲ ነው::ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊነቱን […]

እማማ ኢትዮጵያ የሐዘን ማቅ ለብሳ በዋይታና በልቅሶ ተጨንቃ ልጆቿን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማች ትገኛለች!! አንገታችንን የሚያስደፋና በሐፍረት የሚያሸማቅቅ፣ ጆሮን ጭው የሚደርግ፣ የወላድ እናቶችን አንጀት የሚያላውስና በእንባ ጎርፍ እንዲታጠቡ የሚያደርግ ሌላ የሞት፣ ሌላ የውርደት፣ ማብቂያ የሌለው የሚመስል መሪር የሆነ የመርዶ፣ ሰቅጣጭና ክፉ ዜና ለእናት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ምድር፣ ከሊቢያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሀገረ የመን ተሰምቷል፡፡ ስለሆነም በቦስተን እና አካባቢዋ […]

የሃዘኑ ድባብ ከመብራቱ መቆራረጥ ጋር ተዳምሮ ጨለማውን አብሶታል። የአሁኑ መብራት መቋረጥ ግን ከወትሮ ፈረቃ ለየት ያለ ነው። ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል። ከጥቂት ስፍራ በስተቀር ሁሉም ቦታ በአንዴ እንዲጠፋ ነው የተደረገው። ከሬድዋን ሁሴን እና ከሃይለማርያም የቴሌቭሽን ዲስኩር በኋላ ሃገሩ ሁሉ ጨለማ እንዲሆን አደረጉ። ይህንን ለማድረግም በቂ ምክንያት ነበራቸው። ሃዘን ያልወጣለት ህዝብ አደባባይ ወጥቶ በአረመኔ ወታደሮች ሲቀጠቀት […]

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ከብዙ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣እንዲሁም ነጻ ከሆኑት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ ከፍሪደም ሃውስ፣ከሂውማን ራይትስ ዋች፣ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ከኢንተርናሽናል ሪቨርስና ከሌሎቹ ጋር በማበር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የፖለቲካ ቢሮ ም/ሃላፊ የሆኑት ዊንዲ ሸርማን በቅርቡ ባደረጉት የአዲስ አበባ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ወቅት በ16-04-2015 የሰጡት አስተያየት እውነትን የማያንቀባርቅ በመሆኑ ከማዘናችንም በላይ የአሜሪካንንም ሆነ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ጥቅም ሊያሰከብር የሚችል እንዳልሆነ […]

‹‹Leadership is Falling in Love with the People You Lead or Serve›› (ቀድሞዋ የማላዊ ሴት ፕሬዝዳት ጆሴ ባንዳ) ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ከትናንትና በስቲያ ከሥራ ወጥቼ ወደ ቤቴ ለመሄድ በተሳፈርኩበት ሃይገር ባስ ውስጥ ያጋጠመኝ እጅጉን ያሰዛነኝ ክስተት ነው፡፡ በተሳፈርኩበት ሃይገር ባስ ውስጥ ወጣቱ ሹፌር የይሁኔ በላይን የአገር ባህል፣ ሞቅ ያለ የበዓል ዘፈን እስከ ጣራው ለቆታል፡፡ […]

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የኢሕአዴግ መንግስት ላይ ወርደንበታል !!!! ጥሩ ነው ያደረግነው። በተለይም ትላንትና ህዝቡ ተቃዉሞዉን ማሰማቱ በጣም አስደስቶኛል። አርክቶኛል። ሕዝብ ሲናገር መስማት የመሰለ ትልቅ ነገር የለም። ምርጫ 2007 ትላንት የተደረገ ነው የመሰለኝ። በተለየም መሪዎቹ እዚያ ቆመው፣ የሕዝቡን ፉጨትና ጩኸት መስማታቸው ጥሩ ነው። ያለዉን የሕዝቡን ስሜት በአካል መረዳታቸው፣ ምናልባት አይምሯቸው ላይ የሚጭረው ነገር ሊኖር ይችላል። አፉን […]

በቦስተን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሊቢያ እና በተለያየ ቦታዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች በትናንትናው ምሽት የጸሎት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት፤ በደማቅ ስነ ስርዓት ተካሄደ!! የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጠራው የሻማ እና የጸሉት ስነ ስርዓት ላይ በቦስተን እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች፤ የመካነ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን […]

መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ በተገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ:: ፎቶች ይዘናል ይመልከቱ፤ የBBN ድምጽ ዘገባ እዚህ በመጫን ያዳምጡ ህዝቡ ካለማንም ነጋሪነት ካለማንም ተቃዋሚ ጣልቃ ገብነት ራሱ በራሱ የሚከተሉትን መፈክሮⶭ አስምቷል። * የፈሰሰው ደም የውሻ አይደለም * መከላከያ ስራህ ምንድነው * የወያኔ ጉልበት እኛ ላይ ብቻ * ና ና መንግስቱ ናና * አባረዋቸው አሳረድዋቸው […]

በማለዳው አነሳሴ እንደለመድኩት በስደቱ ዙሪያ ገብ የሆነውንና እየሆነ ስላለው ልሞነጫጭር ፣ ልብተከተክ አልነበረም … ከትናንት ከትናንት በስቲያ ጠዋት ፣ረፋድና ተሲያት ፣ ምሽት ፣ በደረቁ ሌሊት እያቅበጠበጠኝ ስልኬን አንስቸ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፒሊ ወደ ማትረጋው ቢንጋዚና ሚስራታ የደዋወልኳቸውን ስልኮች ተመለከትኩ ። ከወዳጆቸ የደረሱኝን ሁለት ሶስት አድራሻዎችና እዚህ ጅዳ ያለ ሊቢያዊ ጓኛየ አድራሻቸውን አፈላልጎ የሰጠኝን ሌሎች […]

በነገው እለት በመስቀል አደባባይ የሚደረገው ሰልፍ ላይ ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይወጣል ተብሎ ይገመታል። ከአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለ ህዝብ በነቂስ እንደሚወጣ የሚደርሱን መረጃዎች ይተቁማሉ። ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲንን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግፈውታል። አላማው በኢትዮጵያውያን ላይ አይሲስ የፈጸመውን ግድያ ለመቃወም ነው ተብሏል። በዛሬው እለት የታፈነው የአኢትዮጵያ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ድምጹን […]

‹‹. . . ዓይኔ በእንባ ደከመ፣ አንጀቴም ታወከ፡፡ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ አንጀቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ አቤቱ የሆነብንን አስብ፣ ተመልከት ስድባችንንም እይ . . .፡፡›› ሰቆ. ፪፣፲፩ ፤ ፭፣፩ ፡፡ ይህን ቃል የተናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ዘንድ ‹‹አልቃሻው፣ ባለ ሙሾው ነቢይ›› በመባል የሚታወቀው አይሁዳዊው ነቢዩ ኤርምያስ ነው፡፡ ይህንን ነቢይ እንዲህ እንደ ርኁሩኋ እናት አንጀቱን […]

ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በአዲስ አበባ ሰልፍ አድርገዋል። ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት ነበር ሰልፍ የወጣው። የተወሰኑ ቦታዎች የወያኔ ታጣቂዎች ሰልፈኛዉን ደብድበዋል። በብዙ ቦታዎች መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛው እንዳያልፍ ያከላከሉበትም ሁኔታ ነበር። ያው የታወቀ ነው። እነሱ የሚበረቱት ሁልጊዜ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው። የሕዝቡን ስሜት፣ ሐዘን እና ንዴት የተረዳው ወያኔ፣ ነገ «በበመስቀል አደባባይ ሰልፍ ይደረጋል» ብሎ […]