አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” […]

ኩራዝ ከጓሮ ማድቤት ተወሽቃ ትኖር ነበር፡፡ ለብዙ ዘመናት፡፡ ድንገት ሳሎን የምግብ ጠረጲዛ ላይ ታየች፡፡ ይህ ነገር ኮርኒስ ላይ የተንጠለጠለችውን አምፖል በእጅጉ አስገረማት፡፡

‹‹ኩራዝ፣ ዛሬ ከየት ከየት ተገኘሽ፡፡ እኔኮ እንደ ዳይኖሰር ዝርያሽ የጠፋ መስሎኝ ነበር›› አለች አምፖል እየተወዛወዘች፡፡

‹‹እናንተ የተጋደመ አታስተኙ፣ የተቀበረ አታስሞቱ›› አለቻት ኩራዝ ብል ብል እያለች፡፡ በዙሪያዋ የቤቱ ባለቤቶች ከብበው እራት ይበላሉ፡፡ ከተመጋቢዎቹ አንዱ ጭል ጭል በምትለው የኩራዟ ብርሃን በእንጀራው መሐል ያለውን ወጥ ፍለጋ ጠጋ ብሎ እያየ እንዲህ አለ፡-

‹‹ዛሬ ፌስ ቡክ ላይ ያየሁትን ግጥም ልንገራችሁ››

‹‹ምን ተባለ ደግሞ፡፡ ድሮ እረኛ ምን አለ? ነበር የሚባለው፡፡ ዛሬማ ፌስ ቡክ ምን አለ ሆነኮ፡፡›› አለችው የአባ ወራው ሚስት ወጡን ያገኘው ዘንድ ኩራዙን እያስጠጋችለት፡፡

‹‹እራትና መብራት ይባል ነበር ድሮ

እራቱም መብራቱም የት አለ ዘንድሮ›› አጨበጨበችለት፡፡ አምፖሏም ግርምቷን ይበልጥ በመወዛወዝ ገለጠችው፡፡ ኩራዝም ለመጎረር አስባ ትንሽ ኃይል ጨመረች፡፡ የሰውየውን ግጥም አጣጥማ ስትመለስም አምፖሏ ‹‹የጀመርሽውንኮ አልጨረስሽልኝም፡፡ የተጋደመ አታስተኙ፣ የተቀበረ አታስሞቱ ለምን አልሽን ›› አለቻት፡፡

‹‹እንዴ አዲስ አበባ ከተማ ላይ መብራት ከገባኮ መቶ ዓመት አለፈው፡፡ እኔ፣ ጧፍና ሻማ በቃን ብለን ጡረታ ወጥተን ነበር፡፡ ሻማና ጧፍም እንግዲህ ሲያረጁ ወደበተስኪያን ነው ብለው መንኩሰው በተስኪያን ገብተው ነበር፡፡ እኔም ባይሆን ስሜ እንኳን ለታሪክ ይቀመጥ ብል ስሜን ቀየራችሁት፡፡ ስሜ ከጠፋ እኔም ተረስቻለሁ ብዬ ሞቼ ነበር፡፡ እድሜ ለመብራት ኃይል እኔን ከተቀበርኩበት መቃብር፣ ሻማና ጧፍን ከመነኮሱበት ገዳም አመጣን፡፡ መቼም እናንተ ያለውን ከማክበር ይልቅ የሞተውን መቀስቀስ ትወዳላችሁ፡፡ ቆይ ግን አንቺና ፍሬቻ ልዩነታችሁ ምንድን ነው?››

‹‹ምን ልዩነት አለን፡፡ እርሱ መኪና ላይ እኔ ኮርኒስ ላይ ከመሆናችን በቀር፡፡ ያው ሁለታችንም ቦግ እልም ነው የምንለው፡፡ ሳንጠፋ ማብራት አይሆንልንም፡፡ ድሮ እኔ ሳቀው ቦግ እልም ብልጭ ድርግም የሚሉ ሦስት ነገሮች ብቻ ነበሩ››

‹‹ምን ምን ናቸው?››

‹‹አንድ መብረቅና፤ ከነ ድምጡ ብልጭ ብሎ ድርግም ይላል፡፡ ሁለት የገና መብራት፣ የገና ዛፍ ላይ ተጠብልሎ ቦግ እልም ይላል፡፡ ሦስት የዳንስ ቤት መብራት፣ ከሙዚቃ ጋር ተዋሕዶ በሙዚቃው ድምጥ ቦግ እልም ይላል፡፡ አሁን አሁንማ ወይ እንደ መብረቅ ነጎድጓድ የለኝ፣ ወይ እንደ ገና መብራት ዛፍ ላይ አልተንጠለጠልኩ፣ ወይ እንደ ዳንስ ቤት ሙዚቃ የለኝ እንዴው ብቻዬን ቦግ እልም ስል አመሻለሁ፡፡ አገልግሎቴኮ የሰዓት መቁጠሪያ ሆነ፡፡ መጀመሪያ መብራት የጠፋ ጊዜ፣ ሁለተኛ የጠፋ ጊዜ እየተባለ ሰዓት ይቆጠርብኛል፡፡ እንዴው ግን በናንተ ዘመን ሄደ መጣየሚባል ነገር ነበር እንዴ?››

‹‹ነበረ እንጂ›› አለች ኩራዝ፡፡ ‹‹ነጋዴ ሄደ መጣ፣ ወታደር ሄደ መጣ፣ እድሜ ሄደ፣ መሬት ሄደ መጣ፡፡ ስንት የሄደና የመጣ ነገር አለ፡፡››

‹‹መብራትስ ይሄድ ነበር››

‹‹መብራት መጣ፣ መብራት ሄደ አሁን እናንተ ስትሉ ነው የምሰማው፡፡ የመሠረተ ትምህርት ማስተማሪያ ላይ እንኳን አበበ ሄደ፣ ከበደ መጣ የሚል እንጂ መብራት ሄደ መብራት መጣ የሚል አላየሁም፡፡ እኛኮ በቅብዐ ኑግም ብትይ፣ በጥጥ ዘይትም ብትይ፣ በጉሎ ዘይትም ብትይ እንሠራ ነበር፡፡ ከባሰ ደግሞ ጤፍ የምታስለቅም ጨረቃ ትወጣለች፡፡ ያለበለዚያ ምድጃ ከብበሽ እሳት ዳር መብላት መጠጣት ነው፡፡ የእናንተኮ የሚገርም ነው፡፡ ዘይት መሥራቱን ኋላ ቀርነት ብላችሁ ተዋችሁት፡፡ ምድጃ ዳር እንዳትቀመጡ ሳሎናችን ለቴሌቭዥንና ለሶፋ ብቻ ነው አላችሁ፡፡ ከሁለቱም ያጣችሁ ሆናችሁኮ፡፡ እንደ ዘንድሮ ነጋዴኮ መከራ ያየ የለም፡፡ ገቢዎች፣ ጉምሩክ፣ ንግድ ቢሮ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ያወጣሉ፡፡ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ያስነግራሉ፡፡ ገና ማስታወቂያው ሲጀምር መብራቱ እልም፡፡ ተመዝገቡ ይባል፣ ክፈሉ ይባል፣ ተሰለፉ ይባል፣ ወረፋ ያዙ ይባል፣ ጥፉ ይባል፣ ሽሹ ይባል በምን ይታወቃል፡፡ ከዚያ ትቀጫለሽ ትባያለሽ›› ‹‹ምነው›› ያልሽ እንደሆነ ማስታወቂያ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ነግረን ነበር ይሉሻል፡፡ እነርሱ መናገራቸውን እንጂ እኛ አለመስማታችንን አያዩ፡፡ ቴሌቭዥንና ሬዲዮኮ ለራሳቸው እንጂ ለሁላችን የሚሆን ጀነሬተር የላቸውም፡፡ የስንቱ ሞያ ተበላሸ በእናንተ ምክንያት፡፡ ግማሽ በስሎ ግማሽ ሳይበስል የሚወጣ እንጀራ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?››

አምፖል መልሱን ለመስማት ጓጉታ ‹‹አላውቅም›› አለች

‹‹የመብራት ኃይል እንጀራ›› ይባላል፡፡

አምፖል በሳቅ ስትፈርስ በውስጧ የነበሩት ቀጫጭን ሽቦዎች ረገፉ፡፡ ደነገጠች፡፡

‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡

‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው››

‹‹እንዴት እንዴት››

‹‹ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡››

‹‹ መቃጠሌን ያወቁብኝ እንደሆነ ግን ከዚህ ቦታ መውረዴ ነው››

‹‹ተይ እባክሽ እዚህ ሀገር አንቺ ብቻ ነሽ እንዴ ስትቃጠይ የምትወርጅው፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየፓርቲው፣ በየእምነት ተቋሙ፣ በየግል ድርጅቱ ስንት የተቃጠለ አምፖል አለ አይደለም እንዴ፡፡ ማን አወረደው፡፡ መብራት ስለሌለ ማንም ሳይለየው የሚሠራ  አምፖል መስሎ ይኖራል፡፡ አየሽ ጨለማ ለአጭበርባሪ ይመቻል፡፡ በብርሃን ግን ሁሉ ይገለጣል፡፡ እንዲህ ጨለማ የምንሆነው ኤሌክትሪክ በሀገር ጠፍቶ መሰለሽ?››

‹‹ታድያ ለምንድን ነው?››

‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡›› ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡

‹‹በይ ደኅ እደሪ፣ እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል›› አለችና ቆርቆሮዋ ውስጥ ገብታ ተኛች፡፡  

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

ከክፍሉ ታደሰ መጽሐፍ በመዋስ በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እያልን የምንጠራው ትውልድ በ1966ቱ አብዮት ወቅት ወጣት የነበረውን ትውልድ ነው። አሁን በቅርቡ ከተጻፉት ውስጥ፣ (1) ዻንዲ — የነጋሶ መንገድ፤ (2) ሕይወት ተፈራ —   ‘Tower in The Sky’፤ (3) ዶ/ር መረራ ጉዺና — ‘የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች’፤ (4) ኢ/ር ኃይሉ ሻወል — ‘ሕይወቴና የፖለቲካ እርምጀዬ’ (?)፤ (5) ቡልቻ ዸመቅሳ—  My Life and My Vision ይገኙበታል። እዚህ ውስጥ ያልጠቃቀስኳቸውም ሌሎችም ብዙ አሉ። ሆኖም ማውራት ለምፈልገው የጠቀስኳቸው ይበቁኛል።

ከጠቀስኳቸው የ‘ያ ትውልድ’ ጸሐፍት ውስጥ የአሁኑ ፖለቲካ ውስጥ የሌለችው ሕይወት ተፈራ ብቻ ነች። ሆኖም ሁሉም የሚጋሩት አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል፤ የ‘ያ ትውልድ’ ፀሐይ እየጠለቀች መሆኑን በማመናቸው። ይህን ማመናቸውን በግምት ነው የምናገረው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የሕይወት ልምድን ማጋራቶች አንድም ከእርምጃዎቻቸውና ስህተቶቻቸው እንድንማር፣ አሊያም ደግሞ ሕልሞቻቸውን ከግብ እንድናደርስ ነው። የተጻፉት መጽሐፍት በቂ ባይሆኑም ‘ይህ ትውልድ’ ግን ያለበቂ ትምህርትም ቢሆን አገሪቱ እጁ ላይ መውደቋ አይቀርም። ትውልዱ ይህን አውቆ ተዘጋጅቷል?

“እናቸንፋለን” ወይስ “እናሸንፋለን”?

መጽሐፍ እየጻፈ ያለው ‘ያ ትውልድ’ ብቻ ሳይሆን ‘ይህ ትውልድ’ም ጭምር ነው። (ይህ ትውልድ የምለው ከሀያዎቹ አጋማሽ እስከአርባዎቹ አጋማሽ ያለውን ነው።) ለምሳሌ የልደቱ አያሌው ‘ሦስተኛው አማራጭ’፣ የግርማ ሰይፉ ‘የነፃነት ዋጋው ስንት ነው?’፣ የአንዱዓለም አራጌ ‘ያልተኬደበት መንገድ’ እና ሌሎችም እየወጡ ነው። የነዚህኞቹ ከነዛኞቹ የሚለየው አማራጭ መንገዶች ማመላከት ላይ ወይም ያልተኬደበትን መንገድ ማፈላለግ/ማመላከት ላይ ያተኩራል። የተሄደበትን ከያኛው፣ ያልተሄደበትን በይህኛው ማለት ነው።

‘ይህ ትውልድ’ ከ‘ያ ትውልድ’ ስህተት መውሰድ የሚገባው የመጀመሪያው ትምህርት በጥቂት ልዩነት ጎራ ለይቶ አለመቀጣቀጥን ነው ባይ ነኝ። ‘ያ ትውልድ’ በአንድ ርዕዮተ ዓለም፣ በአንድ ዓይነት ሕልም በቃላት አጠቃቀም ውስጥ ለውስጥ በአንጃነትና በሌላም በሌላም ሲከፋፈልና ሲቆራቆዝ እዚህ ደርሷል —  ቢያንስ እስከ ምርጫ 97። ልዩነትን አቻችሎና ተወያይቶ የመፍታት፣ ከነልዩነትም ቢሆን  (ከ“እናቸንፋለን”፣ “እናሸንፋለን” ዓይነት ትናንሽ የቃላትና አተረጓጎም ልዩነት ይልቅ) በዋነኛ አገራዊ ጉዳዮች (ዴሞክራሲ ማምጣት፣ ድህነትን ማጥፋት… የመሳሰሉት) ላይ ማተኮር ያስፈልጋል።

“እኔ ያልኩት ካልሆነ” የሚለው የቃል ሐረግ ካልሞተ የ‘ያ ትውልድ’ ፀሐይ ብትጠልቅም የ‘ይህ ትውልድ’ ፀሐይ አትወጣም።

እናሸንፋለንም፣ እናቸንፋለን

አንተ ወይም እኔ (እኔ ወይም ሞት) ሞቷል። አሁን ያለው አማራጭ እኔንም አንተንም አካታች የሆነ አማራጭ ብቻ ነው፤ አንዱ ሲያሸንፍ/ሲያቸንፍ ሌላው የማያጎድልበት፣ ሁሉም የሚያሸንፍበት/የሚያቸንፍበት ነው።

ይሄ ትውልድ በኔ እምነት ከያ ትውልድ ይሻላል። በቀኖና የሚነገሩት የ‘ያ ትውልድ’ ድርሳናት ‘ይህን ትውልድ’ የሚያጣጥሉት በያ ትውልድ መለኪያ እየመዘኑት ነው። ይህ ትውልድ የራሱ መንገድ አለው ብዬ አምናለሁ።  ስለአንባቢነት የሚወራውም ቢሆን ተጨባጩን እውነታ ያላገናዘበ ብዥታ ነው ብዬ የምረዳው። ብዙኃኑ ያኔም ሆነ አሁን ኖሮ አላፊ ነው። ልሒቁ ነው ለውጥ የሚያመጣው። ማንም ማንንም የማያጠፋበት የለውጥ መንገድ ደግሞ በዚህ ትውልድ እጅ አለ ብዬ አምናለሁ።

መልካም የለውጥ መንገድ!

21 ሰፕተምበር 2013 የግንቦት 7 ሳምንታዊ ርእሰ አንቀጽ በሚል ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2005 በኢትዮጵያዉያን አቆጣጠር ወያኔ በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የፈጸመዉን የመብት ጥሰት አስመልክቶ የወጣዉን ጽሑፍና አቶ ተክሌ በጽሁፉ ላይ ያቀረበዉን ትችት አንብቤአለሁ:: ወደ መሰረታዊ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት ግንቦት ሰባትም ሆነ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ከትግል ስልት ልዩነት በቀር ለአንድ አላማና ግብ ለሚታገሉ […]

በየሳምንቱ በዚህ ሰዓት የሚቀርበው ዓለም አቀፍ የስፖርት መሰናዶአችን እንሆ።በዝግጅቱ ከተካተቱት መካከል እግር ኳስ፤ አትሌቲክስና የአውቶሞቢል እሽቅድድም ይገኙበታል።

በኬኒያ መዲና ናይሮቢ ካሉት ግዙፍ እና ዘመናዊ የገበያ ማእከላት ኣንዱ እና ምናልባትም ዋንናው የሆነው WEST GATE የገበያ ማእከል ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በሳምንት ለሰባት ቀናት ከጡዋቱ 2 ሳዓት እስከ ምሽቱ 2 ሳዓት ለደንበኖቹ ክፍት ነበር

ሰማያዊ ፓርቲ ፣ በአቅዱ መሠረት ፣ ትናንት በመስቀል አደባባይ ሊያካሂደው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ እርምጃ መደናቀፉ ተነገረ።

በሚመጡት 4 ዓመታት ፤ ጀርመንን የሚመራትን የመንግሥት አስተዳዳሪና የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በተካሄደው ምርጫ ፣ ወግ አጥባቂዎች ሲቀናቸው ፤

የCDU እና የያኔዋ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ (ምዕራብ ጀርመን) መሥራች ኮንራድ አደናወር ከ1949 እስከ 1960 ድረስ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ-መንግሥትነት አገልግለዋል።ከአደናወር ቀጥሎ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ መንግሥትነት የመሩት ሔልሙት ኮል ናቸዉ።ሜርክል ጀርመንን ለሰወስተኛ ዘመነ-ሥልጣን በመምራት ሰወስተኛዋ ይሆናሉ

ላለፉት ሶስት ወራት ስኬታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የቆየው አንድነት ፓርቲ የመጀመሪያውን ዙር ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያጠናቅቃል፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው አካል የሆነው የበይነ መረብ ዘመቻ(online social media campaign) ከመስከረም 14-18 ቀን 2006 ዓ.ም ይደረጋል፡፡ ዘመቻው ትኩረት የሚያደርገው የሚሊዮኖች ድምፅ […]

የጀርመን ተፎካካሪ ፖለቲከኞች አሸንፈው ምክር ቤት ለመግባት ከፍተኛ የሆነ የምረጡኝ ዘመቻና ክርክር ሲያደርጉ ሠንብተዋል። ማን ይሳካለት ይሆን?

የጀርመን ፖለቲከኞች አሸንፈው ምክር ቤት ለመግባት ከፍተኛ የምረጡኝ ዘመቻና ክርክር ሲያደርጉ ሠንብተዋል። የሜርክል ፓርቲ አሸንፏል።እንዴት?

የተመ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኬንያ ናይሮቢ፤ ገበያ ማዕከል የተከሰተዉን ደም አፋሳሽ ጥቃት በጥብቅ አወገዘ። አሸባሪነት የዓለማቀፍን ሰላምና ጸጥታ የሚያደፈርስ ግዙፍ ጠንቅ ነዉ ሲል፤ በኒዮርክ የሚገኘዉ የተመድ ጽ/ቤት አስታዉቀዋል።

የጀርመን ተፎካካሪ ፖለቲከኞች አሸንፈው ምክር ቤት ለመግባት ከፍተኛ የሆነ የምረጡኝ ዘመቻና ክርክር ሲያደርጉ ሠንብተዋል። ማን ይሳካለት ይሆን?

የጀርመን ተፎካካሪ ፖለቲከኞች አሸንፈው ምክር ቤት ለመግባት ከፍተኛ የሆነ የምረጡኝ ዘመቻና ክርክር ሲያደርጉ ሠንብተዋል። ማን ይሳካለት ይሆን?

(ዕንቊ መጽሔት፤ ቅጽ 6 ቁጥር 101፤ መስከረም ፳፻፮ ዓ.ም) መንግሥት የተወሰኑ አክራሪዎች የሚላቸው አካላት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ እያወናበዱት ነው ሲል መግለጹ የሚታወቅ ነው፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ የተወሰኑ ሙስሊሞችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ይኸው አጀንዳ አሁንም የሙስሊሙን ማኅበረሰብ በሚያረካና ዘላቂ አገራዊ ሰላም በሚያመጣ ኹኔታ መቋጫ አላገኘም፡፡ ይልቁንም መንግሥት ‹‹ሚዛን ለመጠበቅ›› በሚመስል መልኩ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን …

ይድረስ ለአንዳርጋቸው ፅጌ ጥብቅና ለሻእቢያ ቁጥር 2 – ለቁጥር 2 ከአንበሳው ይብራ ([email protected]) አንዳርጋቸው ፅጌ ሁለተኛውን የኢሳት ቃለ መጠይቅዎንም አበጥሬ አንጠርጥሬ ሰማሁት ። ግሩም ደንቅ ነው መቼም ። ጠያቂው 2ኛውን ክፍል የሚጀምረው በባሕር በር ጥያቄ ነው ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ …

ጥብቅና ለሻእቢያ – ይድረስ ለአንዳርጋቸው ፅጌ Read more »

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት ከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡ ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ […]

ኢትዮጵያ ዉስጥ አምስት ዓመት ሳይሞላቸዉ የሚሞቱት ሕጻናት ቁጥር ባለፈዉ 20 ዓመት በሁለት ሶስተኛ መቀነሱ ተነገረ። በኢትዮጵያ ዉስጥ በየዓመቱ ከሚወለዱት ከ 1000 ህፃናት መካከል 5 ዓመት ሳይሞላቸዉ የሚሞቱት ሕጻናት ቁጥር፤

የፊታችን እሁድ ጀርመን ዉስጥ የምክር ቤት አባላት ምርጫ ይደረጋል። በምርጫ ሥልጣን የሚይዘዉ መንግስት ለሀገሪቱ ይሻላል የሚለዉን አዲስ የፖለቲካ መርህ ሲቀይስ፤ ጀርመን ስለ አፍሪቃ የምትከተለዉም መርህ በአዲስ ምዕራፍ ይቀጥላል።

የኤርትራ መንግሥት የዛሬ 12 ዓመት ካሠራቸው አሥራ አንድ ባለሥልጣናት በሕይወት የሚገኙት ሁለት ብቻ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ፓርላማዎች አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡

የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወደ አውስትራልያ ያመራሉ የሀ/ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች ማ/ክፍል ሓላፊ የታገደውን አመራር ለሁከት እየገፋፋ ነው በአመራሩ የቃለ ዐዋዲ ጥሰትና ሃይማኖታዊ ሕጸጽ ምክንያት የታሸገው የድሬዳዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት ተከፍቶ አገልግሎቱን በጊዜያዊ ሥራ አመራር ቀጠለ፡፡ ሰንበት ት/ቤቱ እንዲከፈት የተወሰነው የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ ከነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሲኾን ይህም …

ኤርትራ ውስጥ የፖለቲካ ተሳትፎንና የአመራር ብቃትን ለማጠናከር ሲባል መንግስታዊ መስርያ ቤቶች በአዲስ መልክ እየተዋቀሩ እንድሆነ የሀገሪቱ ፕረዚዳንት አስታውቀዋል።

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመተው ሰሞኑን ግንቦት 7ትን  ከተቀላቀሉት አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች መካከል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ተዋጊና አዛዥ የሆኑት ካፒቴን አክሊሉ መዘነ ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአንድ ወቅት በገናናነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር ሐይል አሁን ያለበት ደረጃ የሚያሳፍር መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ሰፍኖ አየር ሀይሉ ተመልሶ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 12 እና መስከረም 19 ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች በተከታታይ የጠሩዋቸው ሰልፎች በመስቀል አደባባይ እንደማይካሄዱ የአዲስ አበባ መስተዳድር ህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ክፍል አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ይህን ያስታወቀው ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት ካደረገ በሁዋላ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ” ህዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ለዜጎች ሁሉ …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቆላማና ከፊል  ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ  አርብቶአደሮች ባለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው በተደጋጋሚ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ጉስቁልና መዳረጋቸው ታውቋል። በቦረና ዞን ብቻ በ2005 ዓ.ም 30 ሺህ 216  እንስሳት  በድርቅ  ሲያልቁ፣  በ2004 ዓ.ም ደግሞ 10 ሺህ 609 እንስሳት አልቀዋል፡፡ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ የአካባቢ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት አቶ  አለባቸው …

መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣናቸውን በሀይል ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ግብጽ ሰላም ማግኘት አልቻለችም። የአገሪቱ  መንግስት የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊዎች ለማደን በሚያደርጉት ጥረት አንድ የፖሊስ ጀኔራል ተገድለዋል። መንግስት በርካታ የፕሬዚዳንቱን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲያስታውቅ፣ ደጋፊዎቹ ግን ራሳቸውን መሰራያ በማስታጠቅ መንግስት ለመፋለም ቆርጠው መነሳታቸው ይነገርላቸዋል። መንግስት በያዘው አቋሙ ከገፋበት ግብጽ ዳግም ሶሪያ ልትሆን …

ዛሬ እንግዳችን ጋሽ አበራ ሞላ በሚል ቅፅል ሥም ፤ የሚታወቀዉ አርቲስት ስለሺ ደምሴ ነዉ። አርቲስት ስለሺ ደምሴ፤ በባህላዊዉ የሙዚቃ መሣሪያ፣ ክራር ፤ ለየት ባለ ግርፉ ይታወቃል።

ዓረና ትግራይ ፓርቲ ፣በቅርቡ 3ኛ ዐቢይ ጉባዔውን ሲያካሂድ ፤ የቀድሞው የትግራይ ክፍለ ሀገር ርአሰ-መስተዳድርና የተጠቀሰው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት ሥልጣናቸውን ማስረከባቸው ተነግሯል። አቶ ገብሩ፤ ይህን ያደረጉት፤ ድርጅቱ፤ በቅርቡ

በሶማልያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በበላይ አለቆቻችን እየተበደልን ነው አሉ። አንዳንድ የሠራዊቱ አባላት፤ በ SMS መልእክት አማካኝነት ለ DW እንደገለጹት ከሆነ የውስጥ ነጻነታቸውን እየተነፈጉ ነው። የህክምና ፈቀድ በተለይ እንደነርሱ አገላለጽ