ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተካሄደ ያለውን የሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ የማፈን ተግባርን በመቃወም ነገ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ አካላት ለኢሳት ገለጹ፡፡ የአርብ የፀሎትና የስግደት ስነ ስርዓትን ተከትሎ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በሀገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የመንግስት እርምጃ ለማውገዝ ያለመ እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሰይድ …

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ …

የሶሪያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ፈፅሟል የተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት በተባበሩት መንግስታት ፈታሾች በመጣራት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ምዕራባውያን መንግሥታት በሶሪያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር የተዘጋጁ ይመስላል ከህግ አንፃር ሲታይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ዓለም ዓቀፉን ህግ የሚጥስ እርምጃ ነው ።

በአዲሱ የትምሕርት ዘመን ላይቤሪያ ዩኒቨርስቲ ያመለከቱ 25 ሺህ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን መውደቃቸው የላይቤሪያ የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን እንደሚያመለክት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ሳይቀሩ አምነዋል ።

ቀሬ ቤተእስራኤላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የትናንቱ ጉዞ የመጨረሻው እንዳይደለ ቤተ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ትንናት እስራኤል የገቡት ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እጎአ በ2010 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቀሪ የቤተ እስራኤል ወገኖች በ 3 ዓመት ውስጥ ተጠቃለው እስራኤል እንዲገቡ በታቀደው መሠረት የተከናወነ ነው።

ይኽው መፀሀፍ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ ለቀሪው ትውልድ የሚያቆይ ታላቅ ቅርስ መሆኑን በመፀሃፉ ምረቃ ላይ ተገልጿል ። መፀሃፉ ለህትመት የበቃው ደራሲው ተስፋዮ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ ነው ።

ፎቶ አንሽው ሚካኤል ፀጋዬ በተለያዩ አገሮች አውደ ርዕይ አሳይቷል። ከዚህ ባሻገር ፎቶዎቹ በታዋቂው ሳምንታዊ የጀርመን መፅሄት «ዴር ሽፒግል» ታትመው ወጥተዋል። ሮይተርስን እና ብሉምቤርግን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙኋንም በፎቶዎቹ ተጠቅመዋል።

አስተዳደሩን ይሰበስባሉ፤ ሠራተኛ ያባርራሉ፤ ቢሮ ያሽጋሉ፤ ደመወዝ ይከለክላሉ መምህራኑን ለዓመታት ከኖሩባቸው የኮሌጁ ቤቶች ለቀው እንዲወጡ አዝዘዋል እስከ ነሐሴ ፴ መኖርያ ቤቶቹን የማይለቁ መምህራን ደመወዛቸው ይታገዳል ‹‹ለጥያቄዎቻችን ሥር ነቀል ምላሽ አላገኘንም፤ ይብሱኑ በቀልና ተደጋጋሚ በደል እየተፈጸመብን ነው›› ያሉት መምህራኑ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አቤት ብለዋል በጊዜያዊ ሓላፊነት የተመደቡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ድምፃቸውን አጥፍተዋል   ቅዱስ ሲኖዶስ …

ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥ 1) የፓርላማ አባል የተከበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ እና 2) የአንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይ ፈቃዱ በረዳ – በኢትዮጵያችን በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች […]

ሞቃዲሾና ጁባ ተስማሙ
የሶማሊያ ፌደራል መንግሥትና የጁባ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ በአዲስ አበባ በኢጋድና ሌሎች አህጉራዊና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላት ባስተባበሩት ድርድር እርቅና መተማመንን ለመገንባት የታለመ ስምምነት ተፈራራሙ።

ስምምነቱ በምሳሌነት ሊወሰድና ለጥቅም ሊውል እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ይህን የተናገሩት በመካሄድ ላይ ባለው የሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች መንግስት “ትእግስቱን አብዝቶታል፣ እርምጃ ይውሰድልን” እያሉ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አቶ በረከት ” መንግስት ሀይሉ እንዳለውና መታገሱ ጠቃሚ መሆኑን” ተናግረዋል።  “ይሁን እንጅ” ይላሉ አቶ በረከት “የተፈጠረው ችግር ጊዜ …

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ …

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት ስር በአለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር እና ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ ናቸው ሲል አለም አቀፉ ድርጅት አስታውቋል፡፡ ዩኔስኮ  ባቀረበው ጥናት ቅርሶቹ ባለፉት አርባ አመታት በተለያየ መልኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሺ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል ብሎአል፡፡ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ …

ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበሽር አላሳድ መንግስት በሲቪሎች ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል ሰበብ ምእራባዊያን ሀይል እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው። እንግሊዝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አንድ ህግ ረቂቅ ያዘጋጀች ሲሆን ረቂቁም አገሮች በሶሪያ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መብት ይሰጣል። የአየር ላይ ጥቃታቸውን ለመሰንዘር እየተዘጋጁ ያሉት አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ …

(ተመስገን ደሳለኝ)

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም”

ሙሉውን አስነብበኝ …

(እየሩሳሌምአርአያ)

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት /አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶመለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የዕለት- ከዕለት ዓለም አቀፍ የአየር ጠባይ መዝጋቢዎች ፤በዓለም ዙሪያ ስለተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የሙቀት መጠን መግለጽ አይሳናቸውም። ለምሳሌ ያህል፤ የኢትዮጵያ መዲና ፣ አዲስ አበባ ፤ ዛሬ ያለው የሙቀት መጠን ፣ ቢበዛ 19 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው።

ቱሪዝም በርከት ባሉ ታዳጊ ሃገራት በያመቱ በብዙ ሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስገኝ ጠቃሚ የኤኮኖሚ ዘርፍ ነው። በሌላ በኩል ይሄው ዘርፍ ሙስናና ቀውስ የተጣባው መሆኑም ይታወቃል። ተጠቃሚዎቹ እጅግ ጥቂት በእጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

የአሜሪካ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩት ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂዉ ንግግራቸዉን ያደረጉበት 50ኛ ዓመት ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ እየተከበረ ይገኛል።

አራት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዉያን ለዓመታት ሲያልሟት ወደነበረችዉ ምድር በዛሬዉ ዕለት ተሸንተዋል። ቀሪዎቹን ደግሞ ይህ ጉዞ የመጨረሻዉ ነዉ መባሉ እንዳሳዘናቸዉ የቤተ እስራኤላዉያን ማኅበር ገልጿል።

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል። በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት …

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ እና አልሙ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁም በአማራ ክልል ቻግኒ እና አካባቢው መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤ ነዋሪዎች ለኢሳት ባደረሱት መረጃ እንዳሉት በመብራት እጦት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተናል ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዩጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሺ ከአቅም በላይ ሁኖብኛል ሲል ተናግሮዋል፡፡ ድሃ …

በኢትዮጵያና በኬንያ የድንበር አካባቢዎች ከከትናንት በስተያው ቅዳሜ ወዲህ በተፈጠሩ የጎሣዎች ግጭቶች ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኬንያ ራዲዮ ጣቢያ ዘገበ፡፡

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳ ሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል፡፡ ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም […]

ለተከበሩ ኢንጂነር ይልቃል፣ ለክቡራን ከፍተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በቅድሚያ ሰላምታዬ ባላችሁበት ቦታ ይድረሳችሁ! ጤና ይስጥልኝ። ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት አለኝ። የግራዚያኒ ሃዉልትን በመቃወም ያደረጋችሁት ሰልፍን ተከታትያለሁ። በብዛት ግን ሰው ያወቃችሁ፣ በአዲስ አበባ በጠራችሁት ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ያኔ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት። አኩርታችሁኛል። ብዙ ደጋፊዎችም በአጭር ጊዜ ዉስጥ አግኝታቹሃል። ያኔ የጠራችሁትን ሰልፍ አብዛኞቻችን ብንደግፈውም፣ ሌሎች ድርጅቶችን […]

የአገሬ ሰው “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጎዳም”የምትል አባባል ነበረችው።ግፍ በተለያየ ምክንያት ሊውልብህ ቢችልም የግፉ ደራሲ ግፉን ሲፈጽምብህ ወይም እየፈጸመብህ መርዘኛ በሆነ ፀያፍ አነጋገር በሕሊናህም ላይ ጠባሳ ካልተወ በጊዜ ብዛት የደረሰብህን ግፍ ችላ ልትል፤ ከቶውንም ግፈኛውንም ይቅር ልትል እንደምትችል ለማመላከት ይመስለኛል። “ስልጣን ያባልጋል፤ፍፁም ስልጣን ደግሞ ፍፁም ያባልጋል” የሚለው አባባል ደጋግሞ በታሪክ እንዳሳየን አምባገነኖችና ጀሌዎቻቸው ግፍ […]

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

የግብፅ ጦር ሐይል በሐገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝዳትን ከሥልጣን ማስወገዱ፥ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ወገኖችን መግደል፥ ማሰሩ ብዙ ሲያነጋግር፥ሕዝባዊ አብዮት ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀጣጠለባት አምባገናናዊዉን ሥርዓት በምርጫ የተኩት የቱኒዚያ ፖለቲከኞች እርስ በርስ እየተወዛገቡባት ነዉ

ባለፈዉ ሳምንት ደማስቆ ዉስጥ ደርሷል ለተባለዉ የአደገኛ ኬሚካል መሳሪያ ጥቃት የአረብ ሊግ የሶርያ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ። በመቶዎች የተገመቱ ሰዎችን ሕይወት ያሳለፈዉ የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት ተጠያቂዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ድርጅቱ ጠይቋል።

የፊታችን መስከረም ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ይረዳል ባሉት መንገድ የመራጩን ህዝብ ቀለብ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

ችግሩ የውጭ ግንኙነት መምሪያውን አፋጣኝ ትኩረት ይሻል የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አስተዳደር ላይ በወጣው ዘገባ ዙርያ ከሚደርሱን አስተያየቶችና ትችቶች የሚበዙት ከደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ምእመናንና አገልጋዮች የሚላኩልን ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙበት ፲፱፻፺፯ ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ለስምንት ዓመታት የቆዩበት ደቡብ አፍሪቃ መንበረ ሊቀ ጵጵስናው እና የአህጉረ …

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም በዓለም ዙሪያ በወባ በሽታ 660 ሺ ሰዎች ማለቃቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ማለትም 90 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት ደግሞ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። የዛሬ ሶስት ዓመት በወባ በሽታ 220 ሚሊዮን ሰዎች ተይዘዉ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ።

አሁን አብዛኛው አውስትራልያ የገባ ኢትዮጵያዊ በሚገኝባት የሜልበርን ከተማ ውስጥ አበሻው ሰብሰብ ብሎ በሚኖርባትና በሚሠራባት ፉትስክሬይ በተባለችው መንደር እንገኛለን፡፡ ይህች የሜልበርን ምዕራባዊ ቀበሌ የሆነች መንደር ጥንት የኤስያውያን መናኸርያ ነበረች ይባላል፡፡ ዛሬ ግን ዋናዋ የአፍሪካውያን ስደተኞች መሰባሰቢያ ናት፡፡ በዚህች ከ74000 ትንሽ ከፍ የሚል ሕዝብ በሚኖርባት መንደር ውስጥ ከ135 ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ይኖሩባታል፤ ከ85 ቋንቋ በላይ ይነገርባታል፡፡ እንዴው መርካቶ በሏት፡፡

በአውስትራልያ ታሪክ የመጀመሪያው የእንጀራ መሸጫ ሱቅ የተከፈተው እዚህ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እዚህ ሀገር እንጀራ በዋናነት ከስንዴ ወይም ከሩዝ ዱቄት ተቦክቶ የማሽላ ዱቄት ይቀላቀልበታል፡፡ የታደሉት ደግሞ ከሀገር ቤት የመጣ የጤፍ ዱቄት ለአመል ይጨምሩበታል፡፡ ስፋቱ የአገር ቤት እንጎቻ የሚያህል ሲሆን ውፍረቱ የሰንበት ቂጣ ታናሽ ወንድም ነው፡፡ ኮከብ የመሰለ ዓይን ባያገኝም፣ ሞጭሟጫ ከመባል ለጥቂት ይተርፋል፡፡ በብዛት የሚጋገረው ከብረት በተሠራ ምጣድ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከሀገር ቤት የሸክላ ምጣድ የሚያመጡ አሉ፡፡ ሳይሰበር ከደረሰላቸው፡፡

በፉት ስክሬይ ከደርዘን በላይ የኢትዮጵያውያን ሱቆች፣ ከአምስት በላይ ምግብ ቤቶች እንዳሉ ይነገራል፡፡ በአካባቢው ስትዘዋወሩ ቢያነጥሳችሁ ‹ይማርህ› የሚል አታጡም ይባላል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ስለሚዘዋወሩበት፡፡ በርግጥ ወጣቶቹና ጎልማሶቹ እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም፡፡ የሚገርማችሁ እንዲያውም እዚህ አካባቢ አበሻና አበሻ ሲገናኝ ቁጣ እንጂ ሰላምታ አይሰጣጥም፡፡ ሁለቱም ፊታቸውን ኮስተር አድርገው ነው የሚተላለፉት፡፡ እኔ እንዲያውም ‹እዚህ ሀገር የመጣው ያኮረፈው ተመርጦ ነው እንዴ› ብዬ ነበር፡፡

በፉት ስክሬይ የሚጠፋ ቅመማ ቅመም የለም፡፡ በተለይም ሕንድ ሱቅ ውስጥ በሀገራችን የጠፋው ቅመም ሁሉ ይገኛል፡፡ ሞያ በሜልበርን በሽ በሽ ነው፡፡ በርበሬ ከሀገር ቤት ለማስመጣት የአውስትራልያ የምግብ ሕግ ሲያስቸግር እዚሁ ሌላ በርበሬ ተፈጥሯል፡፡ ከሕንዶች ሱቅ የሚገዛ የሚያቃጥል ቀይ ቃሪያ አለ፡፡ እርሱን በኮረሪማ መፍጫ መፍጨት ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ቅመማ ቅመሙን ለብቻ ፈጭቶ መጨመር፡፡ በመጨረሻም አውስትራልያ ሠራሽ ምርጥ ድልህ ይሆንላችኋል፡፡

 አንድ ወዳጃችን ‹ሽሮ እኛን ስላሳደገች በክብር ጡረታ ወጥታ ትቀመጥ› ቢልም ከሀገር ሲወጡ አንዱ የሚናፍቀው ግን ሽሮ ነው፡፡ በአውስትራልያ ልዩ የሆነ የሽሮ አዘገጃጀት ተፈጥሯል፡፡ የባቄላው ዱቄት ከሕንድ ሱቅ ይገዛል፡፡ ከዚያም አመስ አመስ ይደረጋል፡፡ ለቅመማው አስፈላጊ የሆነውን ቅመምም ሕንዶቹ ያመጡታል፡፡ እርሱንም በቡና መፍጫ ፈጭቶ በመጠኑ ማመስ ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱን በባለሞያ እጅ ደባልቆ ምርጥ የውጭ ሀገር ሽሮ ማግኘት፡፡ ችግር ብልሃትን ይፈጥር የለ፡፡

   ለኢትዮጵያውያን እዚህ አንዱ ፈተና ከሀገር ቤት ባህላዊ ምግቦችን ማስመጣት ነው፡፡ የሀገሩ ሕግ ጥብቅ ስለሆነ፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ግን እንደ ካልዲ(የቡናን ፍሬ ያገኘው እረኛ) አዳዲስ ቅጠላ ቅጠሎችን የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን እዚህ ሞልተዋል፡፡ አንድ ቀን ነው አሉ፡፡ መቼም እኛ ታሪክን በጊዜና በሰዓት የመመዝገብ ችግር አለብን፡፡ (ተረቱም ታሪኩም ከዕለታት በአንድ ቀን ብሎ ነው የሚጀምረው) አንዲት የሀገሬ ሰው በግቢዋ ውስጥ ስትዘዋወር አንድ የምታውቀውን ቅጠል የሚመስል ነገር ታያለች፡፡ ጠጋ ብላ ቆረጠችውና መዳፏ ላይ አሸችው፡፡ ልክ ነው፤ እርሱ ነው፡፡ ወስዳ ለጓደኛዋ አሳየቻት፡፡ ሁለቱም ርግጠኞች ሆኑ፡፡ ጉዳዩን ወደ ልጅቱ እናት ‹ሪፈር› አደረጉት፡፡ እርሳቸውም እየተገረሙ ‹እርሱ ነው› አሉ፡፡ ለካስ ጌሾ ኖሯል፡፡ ጠላ ለመጥመቅ ችግር የነበረው ጌሾ በአውስትራልያ ምድር በቅሎ ተገኘ፡፡ ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ግቢ ውስጥ ጌሾ በቅሎ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

በዚህች ምድር በቅሎ የተገኘው ግን ጌሾ ብቻ አይደለም፡፡ መቼም አገር ደግ ነገር ብቻ አታበቅል፡፡ አንድ ወዳጃችን ሁል ጊዜ አንድ ቦታ እየሄደ ቅጠል ሸምጥጦ ሲወጣ ይታያል አሉ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ማንም ከቁም ነገር አልወሰደውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ሸምጣጩ በዛ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ግራ ገባቸው፡፡ በከተማዋ ውስጥም ወሬው ተባዛ፡፡ የሚሸመጠጥበት ቦታም በአንዳንድ ሰዎች መዘውተር ጀመረ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከሥሩ እየነቀሉ ወስደው በጓሯቸው ተከሉት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአውስትራልያ ፖሊሶች ጉዳዩን ሰሙትና ክትትል አደረጉ፡፡ ለካስ ያ በወፍ ዘራሽ በቅሎ አገር እየተራኮተ የሚሸመጥጠው ጫት ኖሯል፡፡ ፖሊሶቹ እዚያ ቦታ የነበረውን መድምደው አጠፉት፡፡ ችግሩ ግን እነርሱ ሳይደርሱ በፊት በየግቢው ተዛምቷል፡፡ አንዳንድ ቤት ስትሄዱ ጫት በኩራት በቅሎ ታዩታላችሁ፡፡

ፉት ስክሬይ በአበሾች ዘንድ ከምትታወቅበት ሀብቷ አንዱ ምርጥ የሆነ ቁርጥ ሥጋ መሸጫ ስለሆነች ነው፡፡ መቼም ቁርጥ እየበላን ቁርጥ ነገር አለመቻላችን የሚገርም ቢሆንም የሀገሬ ሰው የትም ቦታ ቢሄድ፣ ምንም ዓይነት ትምህርት ቢማር ሊያጣው የማይፈልገው ነገር ቢኖር ቁርጥ ሥጋ ነው፡፡ ከነአባባሉም ‹የተማረ ሰውና የተሳለ ቢላዋ ሥጋ አያጣም› አይደል የሚባለው፡፡ እዚህ ከተማ በጥሬ ሥጋ ሻጭነታቸው የታወቁ ቤቶች አሉ፡፡ ነጭ፣ ቀይ፣ ጎድን፣ ዳቢት፣ ሻኛ፣ ለቁርጥ፣ ለወጥ እያሉ የሚያስተናግዱ፡፡ እነርሱ ጋ ገብቶ አለበለዚያም ደግሞ ሰፈር ይዞ መጥቶ ቁርጥ በኅብረት መብላት እዚህ የተለመደ ነው፡፡ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ አውስትራልያ ዘመድ ለመጠየቅም ሆነ ለመዝናናት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያ ቁርጥ ፍቅር ተነድፈው ነው የሚመለሱት፡፡ አንዳንድ የአውሮፓና የአሜሪካ ወዳጆቼ ጋር ስንጻጻፍ እንዲያውም ‹የአውስትራልያን ቁርጥ ሳትበላ እንዳትመጣ› ይሉኛል፡፡ እስቲ ቀምሼ እመሰክርለታለሁ፡፡

‹አይ እኔ ማን እንደነካው የማይታወቅ ሥጋ አልበላም› ለሚሉ አለያም ደግሞ ‹የተሸረፈ ጥርስ፣ ደልደል ያለም ላት አይቶ መርጦ ተከራክሮ መግዛት› ለሚያምራቸው ወደ ገጠሩ ክፍል ወጣ ማለት ነው፡፡ ከበግ አርቢ ገበሬዎች ጋር ምን የመሰለ የደብረ ብርሃን በግ ይገኛል፡፡ ማረዱን ባይፈቅዱላችሁም መባረኩን ይፈቅዱላችኋል፡፡ እነርሱ ደግሞ ገፍፈውና ቆራርጠው ይሰጧችኋል፡፡ ከዚያ በኋላማ ‹አቤት ባለፈው ለፋሲካ የገዛሁት ምን የመሰለ በግ› እያላችሁ ሾላ ገበያ የሄዳችሁ ማስመሰል ነው፡፡ 

ሜልበርን አውስትራልያ፡፡

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፍቼ ከተማ እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፈ ላይ የገዢው ፓርቲ አፈና በግልጽ የተነጸባረቀበት እንደነበር የፓርቲው የምክርቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል በባሌ ሮቤ ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ሀይል የሀይል እርምጃ ለመውሰድ በማቀዱ ሳይሳካ መቅረቱን በስፍራው የተገኙት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት ገዢው ፓርቲ በተቃውሞው ላይ …