በይዘቱ ወቅታዊ የቴሌ-ኮንፍረንስ ስብሰባ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የሰሜን አሜሪካ አንድነት ፓርቲ ደጋፊ ግብረ ኃይል
ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥
1) የፓርላማ አባል የተከበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ እና
2) የአንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይ ፈቃዱ በረዳ – በኢትዮጵያችን በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ስለሚያደርጉ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል። የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ። በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥ 1) ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ 2) ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮሪቪው እና ሌሎች 3) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ከረንት አፌር ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥ –
ቀን፥ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. (Saturday, August 31, 2013) – ከሁለት ቀኖች በኋላ!
ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Estern Time)
በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ 267-507-0240 ይደውሉ እና 201820 ኮድ ይጠቀሙ
