ተጫዋቾቹ በርሊን ገቡ
የቡድኑ አባላት በግልፅ መኪና ተሳፍረዉ ከበርሊን አዉሮፕላን ማረፊያ ዋናዉ ድግሥ-ሥፍራ ብራንደርቡርገር ቶር እስኪደርሱ ድረሥም በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በመንገዶች ግራና ቀኝ በመሆን የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል
የቡድኑ አባላት በግልፅ መኪና ተሳፍረዉ ከበርሊን አዉሮፕላን ማረፊያ ዋናዉ ድግሥ-ሥፍራ ብራንደርቡርገር ቶር እስኪደርሱ ድረሥም በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በመንገዶች ግራና ቀኝ በመሆን የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል
ዩናይትድ ስቴትስ ሁለት የጀርመን መንግሥት ሠራተኞችን ለስለላ መመልመሏ ከተደረሰበት በኋላ በበርሊን የአሜሪካን ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት CIA ተጠሪ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጀርመን መጠየቋ በሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ጥላ አጥልቷል። የጀርመን መንግሥት ፖለቲከኞች ጀርመንም ለአፀፋ ስለላ እድትዘጋጅ እየጠየቁ ነው።
በኤቦላ ቫይረስ ወይም ተህዋሲ ከሚያዙ ሰዎች 90 በመቶዉ እንደማይተርፉ ነዉ መረጃዎች የሚያመለክቱት። ተህዋሲዉን የሚከላከልም ሆነ የሚያድን ክትባትም ሆነ መድሃኒት እስካሁን አልተገኘም። ኤቦላ ከዚህ ቀደም በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ጋቦን፣ አይቮሪኮስትና ዩጋንዳ በተደጋጋሚ ተከስቷል።
የጋዛ ግጭት ውዝግቡ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፣ ፍልሥጤማውያን ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን፣ የእስራኤል ጦርም ጋዛን ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል። በዚሁ መሀል እስራኤል እና
የብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ርዕሳነ ብሔር እና መራሕያነ መንግሥታት ከሁለት ቀናት በፊት የተጠናቀቀውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ባስተናገደችው ብራዚል ዛሬ የሁለት ቀናት ጉባዔ ይጀምራሉ።
መስፍን ሐብተማርያም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የወግ ፀሐፊ ነበር።በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ወጎችን የፃፈና ያሳተመ፤ ተርጓሚ፤ የሥነ-ፅሁፍ ሐያሲ እና አዲስ አበባና አሥመራ ዩኒቭርስቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ያስተማረ የሥነ-ፅሁፍ ሰዉ ነበር።
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. July 15, 2014)፦ ከአቶ ሀብተማርያም ሞገስ እና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም. የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በ71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ።
የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገ መንግስቱና የጸረ ሸብር አዋጁ በሚያዙት መሰረት እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባቸውና በቤተሰቦቻችውና በጠበቃቸው መጉብኘት መብታቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ጠበቆቻቸው ያልተሟሉላቸው መብቶች በፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ይከበሩ ዘንድ በዛሬው ዕለት ክስ መስርተው የማዕከላዊ አመራሮች ለቀረበባቸው ክስ በአካል በመገኘት ምላሽ […]
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በኖርዌይ የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ መሰጠት በእጅጉ አውግዘዋል። ከፍተኛ ቁጣ ባስተናገደው ተቃውሞ እንግሊዝ እየወሰደችው ያለው እርምጃ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል። በኖርዌይ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ደግሞ በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ለኢህአዴግ የደህንነት አባላት ተላልፈው የተሰጡትን የአቶ ኦኬሎ አኳይን …
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ እና እሁድ በጠቅላይ ሚኒስትር አዳራሽ የጸረ ሽብር ግብረሃይሉና የኢህአዴግ ባለስልጣናት በጋራ የመከሩ ሲሆን፣ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት 3 ሚልየን 400 ሺ ዶላር ወጭ ማድረጉን ገልጿል፡፡ “ኢሳያስ ቢያስፈልገን እርሱን የመያዝ አቅም ላይነን” በማለትራሱን ያሞካሸውግብረሃይሉ ፣ “ኢህአዴግንግስት ንቧን በመያዙየቀጣዩምርጫድልበርላይይገኛል” ሲልበሪፖርቱ አትቷል። ከሁሉምክልሎችየደህንነትሃይሎችአመራሮችበተካፈሉበትውይይትበቀጣይከግንቦትሰባትሊፈፀምይችላልየተባሉ ስጋቶችም ተነስተዋል። የመከላከያሃይሉልዩትዕዛዝተሰጥቶትየተዘናጋበትንክልልእንዲሸፍንናከፍተኛጥንቃቄእንዲወስድመመሪያእንዲሰጠው ተወስናል፡፡ “ግንቦትሰባትእስከጎንደርያለምንምእንከንቀድሞመግባትይችላል”የሚለው ሪፖርቱ፤የመከላከያሃይሉእናየደህንነትስራውየላላበመሆኑመጠናከርአለበትብሎአል። ይህንን ተከትሎም በተሰብሳቢዎች መካከል …
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደር ፀጥታ እና የፖሊስ ኮሚሺን በጋራ የ2006 ዓ.ምየ11 ወራት አፃፀም በገመገሙበት ውይይት የጎጃም ፤የጎንደር ፤የሺዋ እና የኦሮሞ አርሶ አደሮች ዛሬምበድብቅመሳሪያዎችንበነፍስወከፍበየቤቱይዘው እንደሚገኙያወሱሲሆን፣ አርሶ አደሩ የጦር መሳሪያውን እንዲመልስጥረትቢደረግምአልተሳካምብለዋል፡፡ አዲስህግእንዲወጣየጠየቁትየፀጥታሃይሎች በአርሶአደሩበህገወጥእጅየተሰገሰገውከ 4 ሚሊዩንበላይየሚገመትየተለያየየጦርመሳሪያ በአገሪቱ ለሚፈጸም ግድያ ዋና መንስኤ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዘመቻየጦርመሳሪያማስፈታትእናየቅጣትወሰንመመሪያእንደሃገርአለመኖርችግር መሆኑንበማንሳትየፊደራል መንግስት የህገወጥመሳሪያቁጥጥርአዋጅእንዲያወጣበሪፖርታቸውጠይቀዋል፡፡ የፌድራልፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው ከአማራ ክልል በመቀጠል አፋር እና …
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርላማ : ባህል ፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮምቴ ስብሳቢ 73ኛ የምስረታ ዓመቱን በቅርቡ ያከበረውን የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት በቁሙ እየሞተ መሆኑን በመጠቆም በራሱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይትችትአቀረቡ፡፡ የቋሚ ኮምቴው ስብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ዓርብ እና ቅዳሜ እለት በታተመ ቃለ ምልልሳቸው እንደተናገሩት የአዲስ ዘመን ፣ ኢትዮጵያ …
ከፍተኛ የአመራር አባሉ አቶ አብረሃ ደስታ ባለፈው ሣምንት መቀሌ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ ከተወሰዱ በኋላ የተወሰዱበትን ማወቅ አለመቻሉን አረና ትግራይ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት አስታውቆ ነበር፡፡
አባሉ የተያዙበትን እሥር ቤት ሰሞኑን ማረጋገጡን የገለጠው አረና ጠበቃ የማማከር ሕገመንግሥታዊ መብታቸው ግን ተነፍጓል ሲል ፖሊስን ከስሷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ሣምንት በተመሣሣይ ሁኔታ የተሠሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች የአንድነቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ እስከአሁን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን ድርጅቶቹ አስታውቀዋል፡፡
ተከሣሾች በ48 ሰዓታት…
“የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር አባላት የታሠሩት በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም እንዳይሆን ሥጋት አድሮብኛል” ሲል የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ኢዴፓ አስታወቀ፡፡
ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግሥት የታሣሪዎቹን መብቶች እንዲያከብር፣ ለኅብረተሰቡም ዝርዝርና ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ያላቸውን ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች በየቀጠሯቸው ዕለት ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡
Journalists and bloggers did not appear in Ethiopia’s court
Oppostion, detainees, edp
Opposition leaders, arrest in Ethioia, reaction
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑትን ወጣት ሀብታሙ አያሌውንና አቶ ዳንኤል ሺበሺን ለሰባት ቀናት አስሮ እስከ አሁን ፍርድ ቤት ያላቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ እና የመአከላዊ ወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኮማንደር ተክላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዘው የታሳሪዎቹ ጠበቆች ባቀረቡት ክስ መሰረት ነው፡፡ ዛሬ ሀምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት […]
ጀርመን በመከላከያና በስለላ ተቋሞቿ የሚሠሩ ሁለት ዜጎቿ ለዩናይትድ ስቴትስ መረጃ እንደሚያቀብሉ ከደረሰችበት ወዲህ ከአሜሪካ ጋ የነበራት ጠንካራ ግንኙነት ጥያቄ ላይ የወደቀ እንደመሰለ ነዉ።
በአንድነት ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አዘጋጅነት ትላንት ሀምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት “የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና የወጣቱ ተሳትፎ” በሚል ርዕስ ውይይት ተደረገ፡፡ በፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃም የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅራቢነት በተደረገው ውይይት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አበበ አካሉ ወጣቱ ኢህአዴግ እየፈፀመ ባለው እስር ሳይሸበር ትግሉን […]
በእሥራኤልና በጋዛው የፍልስጤማውያን ኃይል ፣ ሐማስ መካከል፣ በአየር ኃይል ድብደባና በሮኬት አጸፋዊ መልስ በተለይ በጋዛ የብዙ ሲቭሎች ሕይወት የተቀጠፈበት ፍልሚያ ከተጀመረ ሰባት ቀን ሆኖታል። ተኩስ ይቆም ዘንድ
ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ፣ ትናንት ማታ በፍጽሜ ግጥሚያ ጀርመን አርጀንቲናን 1-0 አሸንፋ ለ 4ኛ ጊዜ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቅታለች።
እግር ኳስ አፍቃሪው የጀርመን ሕዝብ ከልሂቅ
በሀምሌ 5 የሙዚቃ ቃና ፐሮገራም ምርጥ ምርጥ የሆኑ ዜማዎቸ የቀረቡበት ፕሮግራም ነው::
እንደ ጦርነት፤ ግጭት፤ሽብሩ ሁሉ ድርድር፤ ዉይይት፤የድርድር ዕቅድ ቃል ተስፋዉ በርግጥ ያን ምድር አልተለየዉም።የቤራንዲዶት ዕቅድ፤የሮጀር ዕቅድ፤የአሎን ዕቅድ፤የካምፕ ዴቪድ ዉል፤የፈሕድ ዕቅድ፤ የማድሪድ ጉባኤ፤የኦስሎ ስምምነት፤ እየተባለ በሥልሳ-ሰባት ዓመት ዉስጥ ሰላሳ-አንድ የሠላም ዕቅዶች፤ ሥምምነቶች ወይም የመፍትሔ ሐሳቦች ተሠንዝረዋል።
20ኛዉ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ዉድድር በጀርመን ድል ትናንት ተጠናቀቀ። ጀርመን ከምድቧ ማለትም ከምድብ G በአንደኝነት ነበር ወደቀጣዮቹ የግጥሚያ ዉድድሮች የተሻገረችዉ።
የጀርመን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከእርጀቲና ቡድን ጋር ባደረገው የዋንጫ ግጥሚያ አርጀንቲናን አንድ ለባዶ በመርታት የዋንጫ ባለቤት ሆነ። እስከ በመደበኛው የጨዋታ ጊዜ ፍፃሜ ሁለቱ ቡድኖች ባዶ ለባዶ ስለነበሩ ጨዋታው መራዘም ግድ ነበረበት። ከዚያም በ113 ኛ ደቂቃ ማርዮ ገትስ ባስቆጠራት ግብ ነበር ጀርመናውያን ድል ሊቀዳጁ የቻሉት።
‹‹ከቅዳሜ አራት ሰዓት ጀምሮ ደምበኞቼ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው መታወቅ አለበት ››
‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን››
የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ የሚመላለስ ጥያቄም ነበር፡፡ከዘጠኙ ታሳሪዎች መካከል ስምንቱን በፍርድ ቤት ሲወክሉ የቆዩት ጠበቃ አምሀም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቀደም ብለው ቅጥር ግቢው ተገኝተዋል፡፡
አራት ሰዓት እንደሚጀመር የተገመተው ችሉቱ እስከ አምስት ከሩብ ድረስ በሌሎች ጉዳዩች ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነፍጥ ባነገቱ ወታደሮች ታጅበው መምጣት የነበረባቸው ኪቦርድ አንጋቾች እስራት ያልበገረውን ተስፋቸውን እየዘሩ ሊመጡ አልቻሉም፡፡ሁኔታው አግራሞት የፈጠረባቸው የተወሰኑ ጋዜጠኞች ወደ መዝገብ ቤት በማምራት መረጃ ጠየቁ፡፡የተሰማው በግቢው ውስጥ የነበሩትን ጠበቃ አምሀን ጨምሮ ያስገረመ፣ ያሳዘነና ያሳፈረ ነበር፡፡ከጠበቃው ጋር ያደረግኩት አጠር ያለ ቃለ ምልልስ እንደወረደ እነሆ፡፡
ጥያቄ—ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመጡ በአእምሮዎ ያመላልሱት የነበረው ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ—ምናልባት ምርመራ ባለመጨረሳችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ይላሉ እያልኩ ነበር፡፡ይህንን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በምን አይነት መንገድ እንደሚመልስ ለማወቅም ፈልጌ ነበር፡፡የሆነው ግን በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ያመሩ ጋዜጠኞች ‹‹የልጆቹ መርማሪ ነኝ ያለ ሰው ምርመራዬን በመጨረሴ ለአቃቤ ህግ አስተላልፊያለሁ›› በማለቱ መዝገቡ እንደተዘጋ እንደተነገራቸው እንደነገሩኝ እውነት መሆኑን አጣርቻለሁ፡፡
ጥያቄ — ሁኔታውን እንደሰሙ ምን አደረጉ?
ጠበቃ አምሀ — እኛ ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብለን ግቢው ውስጥ ተገኝተን መርማሪው እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያቀርብ መስማት ነበረብን፡፡ በፍጹም እንዲህ አይነት መደረግ እንደሌለበት ቅሬታ እንደተሰማንና የተፈጸመው ነገር ህገ ወጥ መሆኑን ለዳኛው ተናግረናል፡፡
ጥያቄ — ህገ ወጥ የሆነው ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ –ለፖሊስ ልጆቹን ለተጨማሪ 28 ቀናት እንዲያስር ፈቅዶለት የነበረው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡እስካሁን ድረስ ደምበኞቼ የታሰሩት በፍርድ ቤት እውቅና ነው፡፡ከዛሬ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ደምበኞቼ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ እስራታቸው ህገ ወጥ ነው፡፡ፖሊስ ልጆቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ምርመራውን መጨረሱን ማስረዳትና ክስ የሚመሰርት ከሆነም ማሳወቅ ይገባው ነበር፡፡የሚመሰርተው ክስ ዋስትና የሚያስከለክልና የማያስከለክል መሆኑን መወሰን የነበረበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ይህ ሳይደረግ መዝገቡ ተዘግቷል መባሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
ጥያቄ — ከአሁን በኋላ ለደምበኞችዎ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ — ሰኞ ወይም ማክሰኞ የደምበኞቼ የአካል ነጻነት እንዲከበር ክስ እመሰርታለሁ፡፡ሰኞን የምንጠብቀው እንደተናገሩት ክስ የሚመሰርቱ ከሆነና የት እንደሚመሰርቱ ለማጣራት ነው፡፡
ጥያቄ –በ‹‹ሃፒየስ ኮርፐስ›› ደምበኞችዎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ክስ የምትመሰርቱት በየትኛው ፍርድ ቤት ነው?
ጠበቃ አምሀ –ክሱን የምንመሰርተው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው፡፡
ጥያቄ –ደምበኞችዎን በማዕከላዊ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ነገር ግን እስካሁን ድረስ አቤል ዋበላን ሰዎች ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርጋችኋል?
ጠበቃ አምሀ — ከዚህ በፊት ልጆቹን በሳምንት አንድ ቀን እንዳናግራቸው ይፈቀድልኝ ነበር፡፡በዚሁ ቀን ስምንቱንም ልጆች የማናገር ዕድል ነበረኝ፡፡ አሁን ግን በአንድ ቀን ማናገር የምትችለው አንዱን ደምበኛህን ብቻ ነው ብለውኛል፡፡እንግዲህ ስምንቱን ደምበኞቼን ለማግኘት አራት ሳምንት ያስፈልገኛል ማለት ነው፡፡ ይህም ፍጹም ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡ደምበኞቼ ከጠበቃቸው ጋር የመገናኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡
አቤልን በተመለከተ በተወሰነ ደረጃ ከመርማሪዎቹ ጋር ያልተስማማበት ነገር እንዳለ ሰምቼያለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ከእርሱ አንደበት ለመስማት እርሱን መጀመሪያ ማግኘት ይኖርብኛል፡፡
ጥያቄ –ደምበኞችዎ በምርመራ ወቅት የማያምኑትን ወይም ያልተሳተፉበትን ጉዳይ እንደተሳተፉበት አድርገው ቃላቸውን በሃይል እንዲሰጡ ስለመደረጋቸው ይነገራል፡፡በሀይል የሰጡት ቃል በፍርድ ቤት የሚኖረው ተቀባይነት ምን ያህል ነው? በተለይ በጸረ ሽብር አዋጁ?
ጠበቃ አምሀ — ለፖሊስ የሚሰጥን ቃል በተመለከተ የወንጀልና የሥነ-ስርዓት ህጉ በዝርዝር ይናገራሉ፡፡ለፖሊስ በሀይል እንደተሰጠ የተነገረበት የተጠርጣሪ ቃል ያን ያህል ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሰዎችም በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ ሊገደዱ አይገባም፡፡
ጥያቄ — ቀሪዎቹ ደምበኞችዎ የፊታችን ሰኞ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተይዞባቸው ነበር፡፡ ከዛሬው በመነሳት ሰኞ የሚቀርቡ ይመስልዎታል?
ጠበቃ አምሀ —- አይመስለኝም፡፡ እኛ ግን ቀጠሯችንን አክብረን በቦታው እንገኛለን፡፡
————– ታላቅ ምስጋና ለጠበቃ አምሀ ————-
ጎ…………ል! ጀርመን 1 አርጀንቲና 0 – ሃያኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ተጠናቀቀ፡፡ ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡
‹‹ከቅዳሜ አራት ሰዓት ጀምሮ ደምበኞቼ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው መታወቅ አለበት ›› ‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን›› የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ […]
World Cup; Argentina – Germany, Eskender Frew
ለዋንጫው አርጀንቲናና ጀርመን እየተፋለሙ ነው፡፡
ethiopia, journalists, bloggers, court
ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች መካከል ስድስቱ ትናንት ቅዳሜ፤ ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የአቶ አንዳርጋቸዉ መያዝ በተሰማ-በ16ኛዉ ቀን ባለፈዉ ማክስኞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሊቪዥን ጣቢያ ባሠራጨዉ መግለጫ ግን «የአሸባሪ ድርጅት አመራርና በጥብቅ የሚፈለጉ » ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ እና ሌሎች ሰዎች መታሰራቸዉን አረጋግጧል::
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
ዮሐንስ ታደሰ አካ የሚባል ወጣት ስደተኛ የተስፋው ነጸብራቅ የሚል መጽሐፍ እአአ በ2013 በጀርመን አገር አሳትሞአል፤ ሳይፈራ ሀሳቡን የሚገልጽ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም በታወቀው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያና በቃሊቲም ታስሮ ነበር፤ እሱ እንደሚለው ‹‹በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ውስጥ … የመሬት መሀንዲስ›› ተብሎ በ2000 ዓ.ም. ተቀጠረ፤ ከተቀጠረ በኋላ በቦዘኔነት ደመወዝ እየበላ ቆየ፤ ቀይቶ እንደተገነዘበው ‹‹… ለካስ እንኳንስ የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ ድርሻ ተለይቶ ሊታወቅ የመሥሪያ ቤቱም ሥራ አይታወቅም፤ መሥሪያ ቤቱም ሥራውን አያውቅም፤ የመሥሪያ ቤቱም ሃላፊዎች መሥሪያ ቤቱን አያውቁትም፤ ጉድ በል አዲስ አበባ! የምናወራው ስለዝነኛው አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነው።›› (ገ. 19)
Andargachew Tsigie, Wrap
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የብረቱ ትግል ከተጀመረ ከአንድ ዓመት ተኩል ገደማ በኋላም በብዙው የሀገሪቱ አካባቢ በቀድሞ ሙሥሊሞች የሴሌካ ዓማፅያን እና በአንፃራቸው በሚንቀሳቀሱት የፀረ ባላካ ሚሊሺያዎች መካከል ግጭቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሀገሪቱም ከግጭት አዙሪት መውጣት ተስኗታል። መንግሥትም ቀውሱን የማስቆም አቅም ተጓድሎት ይገኛል።