ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ እና የጋራ ብልጽግና መስሪያ ቤት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ማርክ ሲሞንድ  የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከእንግሊዝ መንግስት የኮንሱላር ምክር የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚጠይቅ ደብዳቤ ለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጽፈዋል። ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሰጠው መልስ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ የተባለ ድርጅት …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ሃላፊዎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በሰንዳፋ እና በኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛዎች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፣ የሰልጠና ተሳታፊዎች የሚያነሱዋቸውን  ጥያቄዎችን አሰልጣኞች መመለስ አለመቻላቸውን በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ ፖሊሶች ለኢሳት ገልጸዋል። ፖሊሶቹ ” መንግስትበተለይከሙስሊምሃይማኖትተከታዮችየሚነሳውንዲሞክራሲያዊየሆነጥያቄለምንአይመልስም?  ለምን በፖሊስተቋምላይየስራጫናእንዲበዛ ይደረጋል?ህዝቡበፖሊስላይያለውጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣እኛህብረተሰቡን በተገቢውመንገድማገልገልእንፈልጋለንና …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በጎንደር ዩኒቨርስቲ የምረቃ ስነስርአት ላይ የተገኙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከከተማውና ከአካባቢው ህዝብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ህዝቡ በድፍረት ያሉበትን የመልካም አስተዳደርና ልማት ችግሮች ዘርዝሮ አቅርቧል። አንድ አስተያየት ሰጪ፣ “ከጎንደር አየር ማረፊያ እስከ አዘዞ ያለው መንገድ እናንተ ትማጣላችሁ ተብሎ በአፈር ተደለደለ እንጅ መኪና አያሳልፍም ነበር” ብለዋል። “ውሃንም …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በሙስሊም ኢትዮጵያውያውያን ላይ ያደረሱትን ኢ ሰበአዊ እርምጃ ተከትሎ በአካባቢው ስትንቀሳቀስ ተገንታለች በሚል ሰበብ የተያዘቸው የሰማያዊፓርቲብሄራዊምክርቤትናየሴቶችጉዳይአባልወይዘሪትወይንሸትሞላለሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጠራለች፡፡ ወይንሸትጭንቅላቷ አካባቢ የተመታች ሲሆንእጇም በፋሻ እንደታሰረበስፍራው የነበሩ ጓደኞቿ ለኢሳት ገልጸዋል። ችሎቱን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ካቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አቤልኤፍሬም በፖሊሶች …

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስራኤል ኦር ይሁዳ የሚኖሩ ጓደኛሞች በራስ ተነሳሽነት ተሰባስበው ለኢሳት ያሰባሰቡትን ከ6 ሺ ዩሮ በላይ ገንዘብ አስገብተዋል። ገንዘቡን በማሰባሰብ በኩል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው በየነ ቀጸላ ፣  በልጁ በእዮብ አንደኛ አመት የልደት ቀን ኢሳትን የመርዳት ሃሳብ እንደመጣለትና በበአሉ ላይ የተገኙት ጓደኞቹ ከፍተኛ የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጿል። ኢሳት በአገራችን ስላለው ሁኔታ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኢትዮጵያ የበርካታ ባህልና የታሪክ ቅርሶች መገኛ ብትሆንም በአንፃሩ በተለያዩ መንገዶች ቅርሶቿ ከሀገር የሚወጡባቸዉ አጋጣሚዎች ብዙ ናቸዉ። እርግጥ ነዉ አንዳንድ ከሀገር የሚወጡ ቅርሶችን የማስመለስ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ቢታይም አሁንም በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች በተለያዩ ሃገራት ቤተ መዘክሮችና ግለሰቦች እጅ ላይ መገኘታቸዉ አልቀረም።

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ […]

የተመድ የልማት መረሃ ግብር በምህፃሩ UNDP የ2014 ዓመታዊ ዘገባ ሥራና ማኅበራዊ ዋስትና፤ ለአፍሪቃ እድገት ያመጣል ይላል። ይህች አህጉር ግን አሁንም ቢሆን አደጋ የተደቀነባት ናት። ድርጅቱ በመጀመርያ ገጹ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ ተስፋ ይሚሰጥ ነዉ።

በደቡባዊ ጣሊያን በሲሲሊ ግዛት የካታኒያ ከተማ ፖሊስ ከሊቢያ ወደጣሊያን ያቀኑ የነበሩ ስደኞችን የጫነች ጀልባ ዉስጥ ስደተኞችን ገድለዉ ባህር ዉስጥ በመወርወር የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታዉቋል።

በመቀሌ አንዳንድ ጓደኞቼን «የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ትፈልጋላቹህ ? ለምን ገብታቹህ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አታደርጉም ? » ስላቸው «ዝም ብለን ለምን እንለፋልን። እንደተለመደው ይዘርፉታል። የህዝብ ድምጽ አይከበርም» አሉኝ። በጣም ገረመኝ ። ምክንያቱም ድሮስ አንባገነን ስርዓቶች ፍትሓዊ ምርጫ እንዲካሄድ ይፈልጋሉ እንዴ? አንባገነን መንግስታት በሚመሩት ሃገር ነጻ፣ ፍትሓዊ እና ተአማኒ ምርጫ ይካሄድ ዘንድ አስገዳጅ ሁኔታ መፈጠር አለበት። አለበለዚያ አንባገነኖች […]

ለረዥም ጊዜ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ሲያቀርቡ በነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ህውሓት/ኢህአዴግ የወሰደውን የኃይል እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን ፡፡ እንደ መኢአድ እምነት ለጥያቄዎቻቸው ተገቢውን መልስ መስጠት ሲገባ በግልባጩ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ያሳዘነና ያስቆጣ የኃይል እርምጃ መወሰዱ የህውሓት/ኢህአዴግን ማንነት በተግባር ያሳየ ድርጊት ነው፡፡ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም የእስልምና እምነት ተከታዮች በአንዋር መስጊድ በፀሎት ሥነ-ሥርዓታቸው ላይ […]

በአንቀጽ 19፣ ንኡስ አንቀጽ 3፣ የአገሪቷ ሕገ መንግስት፣ ዜጎች ሲታሰሩ በ48 ሰዓት ዉስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል። ክሱ በግልጽ ችሎት መሰማቱን ተከሳሾች የማይፈልጉ ከሆነ፣ ወይንም በአገር ደህንነት ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ ካልታሰበ በቀር፣ በአንቀጽ 20 ፣ ንኡስ አንቀጽ 1 እንደተቀመጠው፣ ዜጎች በግልጽ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው። አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 2፣ በጥበቃ ሥር […]

መኢአድና አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ካንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ አዲስ ፓርቲ መመስረታቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

የሁለቱ ፓርቲዎች መሪዎች የቅድመ-ውህደት ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ውህደቱን ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ስራዎች እየሰሩ መቆየታቸውን የፓርቲዎቹ መሪዎች ይፋ አደረጉ።

የህጻናትን ሕይወት ለማዳን መንግስታት ወይንም በአገሮች መካከል ያንን ያህል ምርጫ እንደማያደርጉ ቁጥር አንድ የዓለማችን ባለጸጋ ቢል ጌትስ ተናገሩ።

ድርጅታቸዉ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ በሰራዉ ሥራ እንደተደሰቱና ተጨማሪም መርሃ ግብር ለመዘረጋት እንዳሰቡ የገለጹት ቢል ጌትስ፤ ቀደም ብሎ ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሰጣቸዉን የክብር ድግሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ እጅ ተቀብለዋል።

ገትስ ማምሻዉ ላይ ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ ተንተርሶ የተጠናቀረውን ዘገባ ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።

ለአንድ ወር ያህል ተቋርጦ የቆየው የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የሰላም ድርድር ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ እንደሚጀመር የምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ማህበር ኢጋድ አስታወቀ።

ተቀናቃኝ ወገኞች ድርድሩን ለመቀጠል ፈቃደኛ መሆናቸውንም ኢጋድ አመልክቷል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የደህንነት አባላት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰራዊቱን አባላትና ከባድ መሳሪያዎችን በምሽት ወደ ሽሬ፣ ተከዜ፣ ወልቃይት፣ መተማ፣ አርማጭሆ በመሳሰሉት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያጓጓዘ ነው። ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ጋር በተያያዘ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የታው የህዝብ ቁጣ ያስደነገጠው መንግስት፣ ማንኛውም አይነት ተቃውሞ ቢነሳ በሚል …

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቱ ተከብረው ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እያካሄደባለውቁርጠኝነትየተሞላበትሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልናየኢህአዴግአምባገነናዊአገዛዝ የሕዝባችንንየመብትጥያቄዎችአፍኖለመግዛትእያካሄደ ባለው የማይሳካለት ጥረት መካከል ያለው ቅራኔ እየሰፋና እየተባባሰበ መምጣቱ ለረጅም ጊዜ በአምባገነናዊ አገዛዝ ለመቀጠል የነበረው ምኞትስጋት ውስጥ እንደወደቀ የተረዳውኢህአዴግለመብታቸውጠንክረውየሚንቀሳቀሱትንሰላማዊ ታጋዮችበሽብርተኝነትእየወነጀለበማሰርና በማሰቃየትላይይገኛልሲልመድረክአስታወቀ። የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክሰሞኑን ‘ሰላማዊተቃዋሚዎችንበሽብርተኝነትበመወንጀል ሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልንመግታትናሕገ-መንግስታዊ መብቶችንረግጦመግዛትአይቻልም!!!’ በሚልርዕስ ባወጣውመግለጫኢህአዴግበዚሁአካሄዱበየጊዜውበሚወስዳቸውየተሳሳቱእርምጃዎችዜጎችበሕገ-መንግስቱ የተረጋገጡትንመብቶችበአግባቡእንዳይጠቀሙግራየሚያጋባውዥንብርእየፈጠረይገኛል።በዚህየኢህአዴግተግባር የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክ የአመራርአባላትናደጋፊዎችእንደዚሁምየሌሎችተቃዋሚ ፓርቲዎችየአመራርአባላትናአባላትሰለባእየሆኑይገኛሉብሏል። የመድረክአባልየሆነውየአረናትግራይለዴሞክራሲናሉአላዊነትፓርቲየሥራአስፈፃሚኮሚቴ አባልናየመድረክጠ/ጉባዔአባልየሆኑትናየገዥውንፓርቲኢ-ሰብአዊናፀረ-ዴሞክራሲያዊ …

ናይጀሪያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቦኮሃራም በሰሜን ምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል ከሚገኘዉ ቦርኖ ግዛት ከ200 የሚበልጡ ታዳጊ ሴት ተማሪዎችን አግቶ ከወሰደ 100 ቀን ሞላዉ። ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2009ዓ,ም ጀምሮ ከ10,000 ሕዝብ በላይ ከፈጀዉ ከዚህ ቡድን እስካሁን ልጆቹን ማስለቀቅ ባለመቻሉ የናይጀሪያ የጦር ኃይል ይተቻል።

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባዉ የኃይል ማመንጫ ግዙፍ ግድብ የአባይ ተፋሰስ ሃገራትን ብቻ ሳይሆን የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ፕሮጀክት ነዉ። ግድቡ ሲጠናቀቅ 6,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል።

ድብደባ እና ህግ አስከባሪው ፖሊስ ሚና

ድብደባ ከድሮም ባህላችን የነበረ ባል ሚስቱን መደብደብ፣ አባት ልጁን መግረፍ፣አስተማሪ ተማሪውን መጠፍጠፍ፣ለኛ ኢትዮጵያውያን የታዘዘልን ባህላዊ ህክምናዎች ኣንዱ ይማስለኛል፣ በሀሳብ እና ንግግር ችግርን ክመፍታት ይልቅ ጉልበት አለኝ የሚለው አካል በሀይል አስገድዶ የራስን ፍላጎት መጫን በመሀበረሰባችን ውስጥ ያለ እውነታ ነው። እናስ መንግስት የማህበረሰቡ ውጤት ነውና ክድሮም ጀምሮ በተለያዩ ገዢዎቻችን ስንጠፈጠፍ ኖረናል አሁንም አለም ስለ ሰብአዊ መብቶች የተሻለ ግንዛቤ አለባት በምንልበት ወቅትም እኛና ድብደባ ላንፋታ የተጋባን ይመስል የድብደባ ሌጋሲያችንን እያስቀጠልን ነው። በቅርቡም ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ የሶስተኛ ማእረግነት አግኝተናል እንዲሁም፣ በቅርቡ በመንግስት በኩልም በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን እና ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በጅምላ በፌድራል ፖሊስ ለመደብደብ ታቅዶ ታልሞ የሰለጠኑ በሚመስል ሁኔታ ብዙ ሺህ ሰዎች ፅሎት ሊያደርጉ በሄዱበት እንዲሁም ነጋዴዎች እና ገበያተኞች እንደ አንበጣ ወረሽኝ በድንገት ተወረው ተደብድበዋል።
Image

አድማ መበተን ወይስ ድብደባ

እንደ ፈረደብን ሌላ ሀገር ምሳሌ ላርግና ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲኖሩት ሰልፍ መውጣት የተለመደ ነው። ነገሩ ከፍቶም ችግር ከተፈጠረ አድማ በታኝ ፖሊሶች መተው ሰልፉን መበተን እንዲሁም ከተቃውሞ አድራጊዎቹ ወገን እንደ ድንጋይ እና ሀይል መጠቀም ከተጀመረም በተለያዩ መንገዶች መበተን አዲስ አይደለም። ነገር ግን ባለፈው አርብ በአንዋር መስጊድ እና መርካቶ አካባቢ የታየው ሁኔታ ግርም የሚል ነው።

ምክንያት፡~
1 ድብደባው የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፉ ሳይደረግ በፊት እየተሰገደ ነበር።
2 የተቃውሞ ስልፈኞቹ መሀል በገቡ ደህነነቶች እና ምልምል ካድሬዎች ሰልፉ ሰላማዊ እንዳይሆን አስቀድመው ህዝቡ መሀል ድንጋይ በመወርወር እንዲረበሽ አስደርገዋል።
3 በሌላ ሀገር እንደምናየው ህዝቡ እንኩዋን ከፖሊስ ሀይል ጋር ሊጋጭ ይቅርና አንድ ፖሊስ በያዘው ዱላ ብቻ እስክ ሀምሳ ሰዎችን የሚሆኑ እያሩዋሩዋጠ ሲዥልጥ ነበር።ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ያደረገው በአለም የምንተወቅበትን እሩጫ ብቻ ነበር።
4 እናም የፖሊስ ተልእኮ አድማ መበተን ሳይሆን መግረፍ ይመስል ነበር።
5 መርካቶ አካባቢ ደጅ ላይ በልብስ ስፌት የሚተዳደሩ ወጣቶች ስራቸውን እየሰሩ ባሉበት ሰአት ከየት እንደመጣ እንኩዋን ያላዩት የፖሊስ መንጋ መቶ አናት አናታቸውን ሲፈልጣቸው ማሽናቸውን ጥለው እግሬ አውጪኝ ሲሉ ባለሱቆች ሱቃችሁን አልዘጋችሁም ተብለው እንግልት እና ድብደባ ተደርጎባቸዋል።

ፖሊስ መታሁ ስትል የሰማሁዋት አንዲት ልጅ ብቻ ነች ምክንያትዋን ስታስረዳም” መስጊድ ውስጥ ታግተን እንዳለ አንዱ ፖሊስ መጣና ከአጠገቤ የቆሙትን አሮጊት በያዘው ዱላ ወገባቸውን ሲላቸው አላስቻለኝም ለምን እኔን አይመታም እንዴት እኝህን ሴትዮ አልኩና ጫማዮን አውልቄ አናቱን ብየው ወደ ህዝቡ ውስጥ ስገባ ቆይ በሁዋላ ላግኝሽ እያለኝ ተሰወርኩበት። ” በተረፈ አንድ ተጎድቶ የተኛ የፖሊስ ምስል እዚሁ ፌስቡክ ላይ የተለቀቀ አይቻለሁ እሱንም በግርግሩ መሀል መኪና የገጨው መሆኑን ተረድቻለሁ።

ከአንዋሩ ድብደባ በሁዋላ መስጊድ ውስጥ የታገቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ ታግተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች በትልልቅ መኪኖች እንደ ሰርዲን ታጭቀው ተወስደዋል።

በየማቆያ ጣቢያዎቹ የነበረው ሁኔታም የተለያየ ነበር በጉለሌ አካባቢ የታሰሩት ሰዎች በተለያዩ ኮማንደሮች ልማታዊ የምክር አገልግሎት ተሰጥቶዋቸው የተወሰደባቸው ሞባየሎቻቸው ተመልሶላቸው ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ተለቀዋል።

ወደ ኮልፌ ያለው የፌድራል ፖሊስ ማሰልጠኛ የተወሰዱት ግን ያዩት አበሳ አሳዛኝና ዘግናኝም ነበር የሴቶችን መከናነቢያ ማቃጠል ለሊቱን ሙሉ የሰልጣኝ ፌድራል ፖሊሶች ድብደባ እንዲሁም ሞባየሎቻቸውን ቅሚያም ነውር አልነበረም። ሞባየል ሲነ’ጥቁ ቆምንለት ከሚሉት የህግ ማስከበር አላማ በተፃራሪ እንደቆሙ የሚያገናዝብ ህሊናም አልነበራቸውም። እንዲሁም ድብደባው ይደረግ የነበረው ቀጥታ አናት አናት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ደግሞ ሰዎቹ ጭንቅላት እና ከበሮን መለየት ይችላሉ ወይ ያስብላል።

አንዱ ሽማግሌ ሲያጫውቱኝ እኔ ስብሰባ ይሁን ምን የማውቀው ታሪክም አልነበረም በቃ ከባንክ የሰው አርባ ሺ ብር ቼክ አውጥቼ በዛው ልሰግድ አንዋር ሄድኩ የገጠመኝ ግን ድብደባና ዝርፊያ ነበር። በግርግሩ መሀል ስሮጥ ብሩ ተበተነ ካጠገቤ የደረሱትም ፖሊሶች “የአሸባሪ ብር ፥የአሸባሪ ብር “እያሉ ብሩን ወደ ኪሳቸው መዶል ጀመሩ እኔንም አንዴ አናቴን ሲሉኝ ነብሴን ለማዳን ፈረጠጥኩ።እንዲሁም ልጆቻቸው የታሰረባቸው ቤተሰቦችን አንዳንድ ፖሊሶች ልጆቻችሁን እንድናስለቅቅላችሁ እያሉ እስከ ሁለት ሺ ብር መጠየቅም ተጀምሮ ነበር።

እናም ህግ አስከብራለሁ የሚለው ፖሊስ እና መንግስት አሸባሪ ሆነው ህዝቡ ደግሞ ሲሸበር ዋሉ ለማጠቃለያም የዛሬ አመት እንዲሁ በኢድ ሰላት ላይ ድብደባ ተደርጎ ነበር፣ እናም አንድ ገጠመኝ አጫውቼያችሁ ልሰናበት ልጁ ፖሊሶች እንደ ለመዱት አናት አናቱን በዛ ዱላቸው ሲያራውጡት የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ሆኖበት “ወላሂ እኔ ክርስትያን ነኝ” አላቸው።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ በአለው አቅምና ችሎታ አነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ይጥራል፤ ይህ ቀላል አይደለም፤ ቀላል የማያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ
ከአምስት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ፡፡ በሞያው ውስጥ ሰንበት ብያለኹና ከአብዛኞቹ የጣቢያው ዘጋቢዎች ጋራ እንተዋወቃለን፡፡ ጥሪው የደረሰኝም በላይ ኃድጎ ከተባለ ከማውቀው ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ለሥራ ጉዳይ በስልክ ሳይኾን በአካል መገናኘት እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ ባለመመቻቸት ሳንገናኝ ቀናት ቢቆጠሩም በመጨረሻ ተገናኘን፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትልቁ የዓለማችን ባለ ጸጋ ቢል ጌትስ የክብር ድግሪ ሊሸልም ነው።

በኢትዮጵያ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ለታየው የህጻናት ሞት መቀነስና አገሪቱ በጤና ዘርፋ ላሳየችዉ ማሻሻል የሚሊንዳ ጌትስ ድርጅት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተዘግቧል።

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማን ለማሸነፍ ቆርጦ የነተሳው ኢህአዴግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ነዋሪዎች ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በማምጣት መታወቂያዎችን እያደለ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል። ብዛት ያላቸው በተለይም ከትግራይ ክልል የመጡ የህወሃት አባላት የ13 ቱም ክፍለ ከተሞች የመኖሪያ መታዎቂያዎች እየታደሉዋቸው ሲሆን፣ በምርጫው እለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን የመርሃ ቤቴ ወረዳ አለም ከተማ እና የሚዳ ወረሞ ወረዳ መራኛ ከተማን እንዲሁም አዋሳኝ የደራ ወረዳን ጨምሮ 24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት እንዲሰጥ በአለም ከተማ የሚገኘውን ዋና የመብራት ማሰረጫ ትራንስፎርመር ተነቅሎ  ወደ አቃስታ የመብራት ስቴሽን ጣቢያ ለማዛወር  የነበረው  እቅድ በህዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ መክሸፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፊታችን አርብ በቤልጂየም ብራሰልስ በሚደረገው ተቃውሞ በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ያወግዛሉ። የተቃውሞ ሰልፉ  በብራሰልሰሹማንአደባባይ እኤአ ጁላይ 25 ቀን ከቀኑ 13 ፡30 እስከ 17 ሰአት ይካሄዳል። ነገ ረቡዕ ደግሞ በጀርመን በርሊን እንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚኖር ታውቋል። ይህ በእንዲህ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ የሆኑት ሬክማቻር በናስር በተባለው ከተማ እንደ አዲስ በተነሳው ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮችንና ንብረቶችን ማውደማቸውን ሲገልጹ የናስር ከተማን ደግሞ  በእጃቸው ማስገባታቸውን እየተናገሩ ነው። ሬክማቻር ምንጮቻቸውን ጠቅሰው እንደተናገሩት  3 የሚሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎችን አውድመው በመቶዎች የሚቆጠሩ(100) የመንግስት ወታደሮችን መግደላቸውን ሲናገሩ የመንግስቱ የጦር አዛዝ የሆኑት ፓል ማሎንግ አዋን ማስተባበላቸውንና …

እስከፊታችን ዓርብ በሚዘልቀው የሜልቦርኑ ጉባዔ ላይ “Living in the Shadow” – (ተደብቆ መኖር) በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምፅ – ቪኦኤ የተዘጋጀ ጥናታዊ ፊልም ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ታይቷል፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ሁለት ሣምንታትን ያስቆጠረው የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ድረስ አልተቋረጠም። በፍልስጥኤም በኩል ከ600 በላይ፣ ከእስራኤል ወገን ደግሞ ወደ 30 የሚጠጉ አይሁዶች መገደላቸው ተዘግቧል። የአረብ ሊግ እና የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ የተመድ ብሎም ዩናይትድ ስቴትስ ግጭቱን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል።