የሊቢያ የርስበርስ ጦርነት
በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ የአየር ማረፊያ አቅራቢያ የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው።
በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ የአየር ማረፊያ አቅራቢያ የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ በኧዤን ከተማ በኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ቀናት በተካሄደው እና ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ፌዴሬሽን የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሦስተኛነትን ደረጃ አግኝታ ተጠናቋል።
በአሁኑ ጊዜ ምዕራባውያንን፣ በተለይም ፣ አውሮጳን እያሳሰበ ያለው ፈተናም ውስጥ የጣለው የዩክሬይን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ከሩስያ ጋ የገቡበት እሰጣ ገባ እና የፖለቲካ ፍጥጫ ነው።
በጎርጎሪዮሳዊዉ 1990 እና 1992ዓ,ም በቢሊዮን ይገመት የነበረዉ ለምግብ እጥረት የተጋለጠዉ ሕዝብ አሁን ወደ 842 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ አንድ ነገር ነዉ ቢባልም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉን ወገኖች አሁን የሚያሳስበዉ የተደበቀ ወይም ስዉር ረሃብ መኖሩ መሆኑን ያመለክታሉ።
#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw
የኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለዞን9 ጦማርያን ሽልማት አበረከተ
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በእስር ለሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ያልተዘመረላቸው ጀግኖች በሚል በአራተኛው አመታዊ ክብረ በአል ላይ ሽልማትን አበርክቶላቸዋል፡፡
በየአመቱ በሚደረገው በዚህ ክብረ በአል መዝጊያ ስነስርአት ላይ የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበበ የዞን9 ጦማርያን ከፍተኛ መስዋእትነትን የሚከፈልበትን ሃሳብን አገር ውስጥ ሆኖ እውነትን የመናገርን ሃላፌነት ወስደው እየከፈሉት ላሉት መስዋእትነት እውቅና መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
ይህ ያልተነገረላቸው ጀግኖች በሚለው ምድብ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከዚያ በተጨማሪ ሁለት ተሸላሚዎች ከአገረ አሜሪካን ሽልማት ወስደዋል፡፡
የዞን9 ጦማርያን በታሰሩ ጦማሪ ጓደኞቻችን እና ጋዜጠኞችን ስም ለተሰጠው እውቅና ሽልማት ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
የመን ውስጥ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጡትን የግንቦት ሰባት የፍትህ ነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ዓለም አቀፋዊና ሕጋዊ መብት መነሻ ያደረገ ዝግጅት ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ “የትጥቅ ትግል ያወጀ ነው፤” ሲል ድርጅታቸውን ግንቦት ሰባትንና አቶ አንዳርጋቸውን በአሸባነት ይወነጅላል።
“ለጥያቄዎ መልስ” በሳምንታዊ ቅንብሩ፥ ተንታኝ ባለ ሞያው መልስ የሚሰጡባቸውን የበርካታ አድማጮችን ጥያቄዎች አስተናግዷል።
ለመሆኑ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ሕግ የሁለቱን ጉዳይና የየመንን አሳልፎ መስጠት እንዴት ይመለከቱታል? ዝርዝሩን ከዝግጅቱ ይከታተሉ።
የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን እቅድ በመቃወም ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ በመንግሥት ኃይሎች ተፈጽሟል፤ ያሉትን ግድያ፥ ድብደባና እሥራት በመቃወም፥ እዚህ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት፥ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ለሦሥት ቀናት የዘለቀ የረሃብ አድማ አድርገዋል።
“መንግሥት በዜጐቹ ላይ እያደረሰ ያለው ችግር ተባብሶ ቀጥሏል፤” የሚሉት በWhite House ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት ለሦስት ቀናት በረሃብ አድማው የተሳተፉ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች፥ ዓላማቸው ሁኔታውን ለአሜሪካና ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ መሆኑን ይናገራሉ። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ።
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-1 ሺህ 435ኛው የኢድ አልፈጥር በመላው የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም የነበረው ክብረበአል በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ድምጻችን ይሰማ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይካሄድ ባዘዘው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀርቷል። የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል …
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ …
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በከተሞች የሚገኙ አውራጅና ጫኝ፤ሊስትሮ፤ሱቅ በደረቴ፤ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን፤ በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችን እና በአደረጃጀት ያልታቀፉ ሌሎች ወጣቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀው ሰነድ ፣ “የጥፋት ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ በመላ የከተማችን ሰላም ወዳድ ወጣቶች የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ እንዲከሽፍ ካልተደረገ በመላ ቀልቡ ወደ ልማቱ የገባው ህዝባችን በተለይ …
ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢውን ጎብኝተው የተመለሱት የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መከሰቱን ጠቅሰዋል፡፡ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ በሰብአዊነት ስም እጠይቃለሁ በማለት ዋጻ ጸሃፊው ተናግረዋል። የኢድ አል ፈጥርን በአል ምክንያት በማድረግ ሁለቱም ሃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ አለማቀፍ ማህበረሰቡ የጠየቀ ሲሆን፣ ሃማስ የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በመጣስ በእስራኤል ላይ ተወንጫፊ …
EDP, Ethiopia, investigation
President Barak Obaman and his young African guests
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበጋ ወራት ፍልሚያ ሊጀመር የቀሩት 19 ቀናት ግድም ነው። የዓለም ታላላቅ የእግር ኳስ ቡድኖች የተጨዋቾች ዝውውር ላይ ተጠምደዋል። በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የወጣቶች ፉክክር ኢትዮጵያ ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች።
አብዱረዛቅ ሙደሲር በቦንና ኮለን መካከል በምትገኘው ብሩህል ይኖራል። በጀርመን አስራ ሁለት ዓመታትን ለኖረው አብዱረዛቅ የዘንድሮው ረመዳን እንደወትሮው አይደለም። በአውሮጳ የሚታየው የበጋ ረጅም ቀን እንደ አብዱረዛቅ ረመዳንን ለሚጾሙ ፈታኝ ጊዜ ነው።
ሐማስ የግብፁ የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበር ቅርንጫፍ ወይም ጥብቅ ወዳጅ ነዉ።በግብፅ ሕዝብ የተመረጡትን የሙስሊም ወንድማማቾቹን ፖለቲከኛ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲን ከሥልጣን ያስወገዱት ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ የሙስሊም ወድማማች ጠላት ናቸዉ።ሐማስ ድሮም-ዘንድሮም የእሥራኤል ጠላት ነዉ። አልሲሲና እስራኤል ምን እና ምን ናቸዉ?
ታሪክማ ሊረሳ አይገባም ታህሣሥ 7 ቀን 1966 ዓ.ም የነጌሌ ጦር አባሎች ለአዛዦቻቸው ላለመታዘዝ ወሰኑ። የምድር ጦር አዛዥ የነበሩት ሌተና ጄኔራል ድረሴ ዱባለ አማፅያኑን እንዲያረጋጉ በታዘዙት መሠረት የመንግሥት ልዑካን ይዘው ታህሣሥ 23ቀን 1966 ዓ.ም ነጌሌ ጦር ሠፈር ገብተው ሠራዊቱን ሲያነጋግሩ የተጠበቀውን መልስ ስላልሰጡ እርሳቸውም ከነተከታዮቻቸው ታገቱ፡፡ በ27/4/66 በአየር ኤታማጆር ሹም በጄኔራል አበራ ወልደማርያም የሚመራ የዓፄው ልዑካን […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ግብጽ አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ ግድቡ ወደ ሃገርዋ በሚገባው የውሃ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳያደርስ ያቀረበችው ጥያቄ እንዴት እንደሚፈታ እያጠያየቀ ነው
ቦኮሐራም የተሰኘው የናይጀሪያ እስልምና አክራሪ ታጣቂ ቡድን ካሜሩን ውስጥ ሰርጎ በመግባት የካሜሩን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ባለቤትን አግቶ መሰወሩን የካሜሩን መንግስት አስታወቀ።
‹‹የነጻነት ትግሉ በአፈና ስር ቢወድቅም ትግሉ ለአንድ አፍታም አይቆምም›› በማለት ኮንፈረንሱን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ይህ ኮንፈረንስ በአይነቱ ልዩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ ልዮ ኮንፈረንስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚደረግ እና በመዝጊያው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትና የወረዳ አመራሮች በአጠቃላይ የአንድነት የአዲስ አበባ አባላት በሚታደሙበት የአቋም መግለጫ […]
በመክፈቻው ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሴቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ የሴቶች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በእጅጉ አሳስቦአችሁ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘታችሁ በአንድነት ፓርቲ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ ካሉ በኋላ እንዲሁም የጽሑፍ አቅራቢ ወ/ሮ አልማዝ ሰይፉ ለሴቶች እንቅስቃሴና የእኩልነት ጥያቄ ትምህርት ለመስጠት በመሀከላችን በመገኘቷ በናንተና በፓርቲው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርብላታለሁ፡፡ ሴቶች በቀን ከ12 – 16 […]
ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡ ሙስና ከስልጣን ጋር ተጋብቶ እንደ ሸረሪት ድር ተወሳስቧል፡፡ ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋፍቶ መንግስታዊ ሽብርተኝነትን አማክሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕዝብ ዋይታ፣ ለቅሶ ለመሆኑ በቅቷል፡፡ ቢሮክራሲው በሙስና ተዘፍቆ ለስራ ሂደቶች ማነቆ ሆኗል፣ የልማት እንቅስቃሴዎች በመንግስት ሹመኞች ሙስና ተሰነካክለዋል፣ ይህ ነው ለማለት በሚያዳግት ደረጃ ሙስናን […]
ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው ከሁለት ዓመታት የፖለቲካ እረፍት በኋላ የአንድነት ፓርቲ አመራር ሆነው እንዲሰየሙ ጥሪ ሲደረግላቸው ጥሪውን የተቀበሉት ‹‹ወጣቶችን ለአመራርነት ለማብቃት›› ከሚል ውስጣዊ ቅንነት ጋር እንደነበር መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ኢንጂነሩ ከዶክተር ነጋሶ የተረከቡት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን የውህደት ድርድር በማስቀጠልና ተቃዋሚዎች እየተዋሃዱ አንድ አቢይ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲመሰርቱ በመርህ ደረጃ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በእኔ እምነት ኢንጂነሩ ፓርቲውን ለመምራት የቀረበላቸውን […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ተቀናቃኝ ወገኖች ባለፈው ረቡዕ የተፈራረሙት የተኩስ አቁም ስምምነት ዘላቂነት እያጠያየቀ ነው። የፈረንሳይ ራድዮ፣ «ኤር ኤፍ ኢ» ባለፈው ሀሙስ እንደዘገበው፣ ስምምነቱን ተፋላሚዎቹ ወገኖች
በእስራኤል እና በሃማስ ቡድን መካከል ለዛሬ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተከብሮ የዋለ ይመስላል። የነፍስ አድን ሠራተኞችም ይህንን የ12 ሠዓታት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠቅመው ሌሎች 35 አስክሬኖችን ከጋዛ ሰርጥ ፍርስራሾች እንዳወጡ ተገልጿል።
“የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” በያዘነው ሳምንት መጀመሪያ በህግ የተፈቀደለትን ሰማኒያ ከመቶ ጊዜ አጠናቆ ተዘግቷል፡፡ ስራውን እንጂ ግዜውን አላልኩም፡፡ በቀረው 20 ከመቶ በሚሆነው ጊዜ ባለፉት አራት ዓመታት ያከናወናቸውን ዓይነት ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት ኢህአዴግ፣ በገዢነት በማንኛውም መንገድ ሊቀጥል እንደሚችል እርግጠኛ ቢሆንም፤ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ግን መቀጠል አለመቀጠላቸውን የሚያረጋግጡበት ግልፅ የሆነ አሰራር ባለመኖሩ ስጋት ላይ እንደሚወድቁ ስለማውቅ ነው፡፡ ይህ ስጋት ካሁኑ መታየት ጀምሯል፡፡ ስለዚህ አብዛኞቹ የምክር ቤት አባላት፣ አሁን በቀጣይ ዕጣ-ፋንታቸው ላይ የሚወሰነውን የሚጠባበቁበት እና በግላቸውም ቢሆን አማራጭ የሚመለከቱበት ጊዜ ነው፡፡
እነዚሁ የምክር ቤት አባላት የአራተኛውን ዓመት ጊዜ ለማጠናቀቂያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቧቸው ከደርዘን የሚበልጡ ጥያቄዎች መካከል፤ ገዢው ፓርቲ ያቀደውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ክፍተት እንዳለበት ማሳለቁ አያቋርጥም፡፡ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡትም መልስ ‹‹ያሉትን ችግሮች ተቀብሎ ቢሆንም›› በሚል ማገናኛ ቃል በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሰረት ዕድገት አስመዝግበናል የሚል ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ አንድ አንድ ነጥቦችን አንስተን እንመልከት፡፡
መንግስት፣ በዘመቻ ከሚሰራቸው የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ግንባታዎች ጋር በተያያዘ እየተፈጠሩ ያሉ እድሎች ወደፊት ዘላቂ ሊሆኑ የሚችሉት፤ በምርቱ ዘርፍ የግል ባለሀብቱ ሲሳተፍ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ዘርፍ ግን በሚፈለገው መጠን የስራ እድል ሊፈጥር በሚችል ሁኔታ እየተስፋፋ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀብለውታል፡፡ ይህም ቢሆን የሀገራችን ኢኮኖሚ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሰረት በሁለት አሃዝ ማደጉን ግን አላቋረጠም፡፡ የምርቱ ዘርፍ የስራ እድል ቢፈጥርም ባይፈጥርም፣ ኢኮኖሚያችን ማደጉን ለነገሩ ኢትዮጵያዊያን አስማተኞች ሳንሆን አንቀርም፡፡ ስራ ቢኖረንም ባይኖረንም በልተን/ቀምሰን ማደርና ጠዋት ለስራ-ፈትነት አርፍዶ መንቃት የለመድን ይመስለኛል፡፡
መንግስት የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ፤ ስግብግብ ነጋዴዎች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይገባቸው በተደጋጋሚ ከመገለፁ በተጨማሪ አሁን የሚመጣ የዋጋ ጭማሪ ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንደሌለው እንድናምን እየተነገረን ነው፡፡ የኢኮኖሚክስ “ሀሁ” እንደሚነግረን ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ማለት የአቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም ሲሆን፣ የኢኮኖሚክሱ “አቦጊዳ” ደግሞ እነዚህ ሁለቱን የሚያሳልጠው የገንዘብ አቅርቦት ተመጣጣኝ አለመሆን እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ክፍተት መኖሩን አምነው፣ ይህ ክፍተት የሚዘጋው፣ የበለጠ የከፈለ ያገኛል በሚለው መርህ መሆኑን እርሱት እያሉን ነው፡፡ ይህ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ካልሆነ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክንያት ለምን ሌላ እንደሚፈልጉ ለእኔ ግልፅ አይደለም፡፡ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር መንግስት በመሰረታዊ ዕቃዎች ላይ ድጎማ በማድረግ ዋጋ እንደሚያረጋጋ የነገሩን፣ በቂ አቅርቦት በሌለበት ድጎማ ዋጋ እንደማያረጋጋ ለማወቅ የኢኮኖሚ ሊቅ መሆን አይጠይቅም፡፡ በዚህ ጊዜ የሚኖረው በኮታ ማደል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለጥቁር ገበያ እና ለከፍተኛ ዋጋ ንረት መንገድ ይከፍታል፡፡
ለማንኛውም በደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በሚፈጠር የዋጋ ንረት ሃላፊነቱን የሚወስዱት “ጥቂት ስግብግብ ነጋዴዎች” ስለሆኑ፤ እነሱን ለመታገል በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቀመጠው አቅጣጫ “ተደራጁ” የሚል ነው፡፡ በእኔ እምነት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር፣ አሁን ባለው ሁኔታ የሚያዋጣ ስላልሆነ በየመስሪያ ቤታችን የዋጋ ንረትን በጋራ ለመቆጣጠር መደራጀት ሊኖርብን ነው፡፡ ይህን ኃላፊነት ግን ለምን አሁን ያለው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት አይረከበውም? ይህ አደረጃጀት፤ አንደኛ መንግስት በትክክል መደጎሙን ይከታተላል፤ እግረ-መንገዱንም ከ“ስግብግብ ነጋዴዎች” ጋር ግብይት እንዳናካሂድ አድማ ለማድረግ ይጠቅመናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “በነፃ ገበያ” ስርዓት ዋጋ ጨመርክ ተብሎ ማሰር ስለማይቻል ነው አድማ ማድረግን ያመጣሁት እንጂ አብዮት ለመቀስቀስ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስጠይቀው በሸማቾች ህግ ሳይሆን በፀረ-ሽብር ህግ ነው፡፡
መንግስት፣ በዕቅድ ደረጃ ስምንት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከውጭ ንግድ ለማግኘት አቅዶ ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ለዚህም ዋና ዋና የተባሉት እና በመንግስትም እንደችግር ከተጠቀሱት ውስጥ ቡና ማልማት ከሚችለው መሬት አንፃር ከሃምሳ በመቶ በታች፣ ከምርታማነት አንፃር ገና አንድ ሶሰተኛው አካባቢ ላይ መሆናችን ነው፡፡ በዕቅድ ዘመኑ የቅባት እህሎች ለማምረት ወደ ተግባር እንደሚገቡ የታሰቡት ክልሎች ወደ ስራ ያለመግባታቸው፤ የገቡት የአማራና የትግራይ ክልልም ቢሆኑ፣ ምርታማነታቸው ከሃምሳ በመቶ በታች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት የምርት ዘርፉ ገና ያልተጀመረ መሆኑ፣ በማዕድን ዘርፍ የወርቅ ዋጋ መቀነስ ብቻ ሳይሆን በባህላዊ አምራቾች ሊገኝ የታሰበው ያለመሳካቱ፣ እንዲሁም እጅግ ብዛት ያላቸው የንግድ ሰርዓት ማነቆዎች በመኖራቸው ምክንያት ዕቅዱ አልተሳካም፡፡ ይህን የሚያህል ሀገራዊ ዕቅድ ባልተሳካበት ሁኔታ፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት አንድ መድህን ግን አልጠፋም፡፡ ይኽውም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለዘመዶቻቸው የላኩት ገንዘብ ከዕቅድ በላይ ተሳክቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን የሀገሪቱ አጠቃላይ እድገት በሁለት አሃዝ ከማደግ የከለከለው አንድም ምድራዊ ሀይል አልተገኝም፡፡ የውጭ ምንዛሬ ግኝታችን ከስልሣ በመቶ በታች ቢሆንም እድገታችን ግን ካቀድነው ፍንክች አላለም፡፡
የአንድ ሀገር እድገት የሚለካው ዜጎች በትምህርት በሚያገኙት ክህሎት እና ይህንንም ክህሎት እሴት ለመጨመር ሲያውሉት እንደሆነ ይታመናል፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ግብ ከትግራይ ክልል በስተቀር ያለመሳካቱ ጉዳቱን ያዩበት አቅጣጫ ምቾት ሰጥቶኛል፡፡ ልጆች ትምህርት ቤት በሚሄዱበት ወቅት ከትምህርት ገበታ ከተገለሉ ለጉልበት ብዝበዛ የሚጋለጡበት ሁኔታ እንዳለ አስረድተውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያለ እድሜ ጋብቻ እና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚወድቁ መሆኑን ደምረን ስናየው፤ የዚህ እቅድ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ጉልህ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትምህርት ዘርፍ ወደ ስልሳ ሁለት ከመቶ ለማድረስ የታቀደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋን ያልተሳካ መሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢታመንም፤ በእድገታችን ላይ አንድም ነጥብ ለመቀነስ ግን በቂ አይደለም፡፡
መንግስት፣ በገጠር ከተሞች እና ማዕከላት ለማስፋፋት አቅዶት የነበረው የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም፤ በባለሞያ ዕጥረት እና አንዳንድ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ባለመቻሉ እንደታሰበው ሊሄድ እንዳልቻለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምነዋል፡፡ መቼም የመብራት አስፈላጊነት ጨለማን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን መብራት በሚገባላቸው አካባቢዎች የሚፈጥረውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ታሳቢ በማድረግ ጭምር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አንዳንድ ሰዎች መብራት በሌለባቸው አካባቢዎች የወሊድ ምጣኔም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡ በእኛ ሀገር ግን ይህ እቅድ በታሰበው መጠን ባይሳካም፣ አጠቃላይ እድገታችን ላይ ምንም ጫና የለውም፡፡ ለዚህም ይመስላል በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሁለት አሃዝ ያደግነው፡፡
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አራተኛ ዓመት ማገባደጃ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ አንድ የቱሪዝም ምክር ቤት ተመስርቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በክልሎችም፣ በክልል መስተዳድሮች የሚመራ የቱሪዝም ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ ከስምምነት ተደርሷል ብለውናል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት ለመጠቀም አቅጣጫ የሚያሳይ የተባለለት ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ገለፃ መሰረት ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሴክትር ያላትን አቅም የሚያህል አንድም የአፍሪካ ሀገር የለውም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ልንጠቀም እንዳልቻልን ይስማማሉ፡፡ ይህን ባናደርግም ግን እድገታችንን ከሁለት አሃዝ ማን ሊያወርደው ይችላል? የሀገር እድገት በእምቅ ሀብት ሳይሆን በተግባር ላይ በዋለ ምርት የሚለካ ቢሆንም፣ ‹‹ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ›› የሚሉት ሹሞች ግን ‹‹አድገናል›› እያሉን ነው፡፡
የምክር ቤት አባላት ካቀረቡት ጥያቄ አንዱ ‹‹የኦዲት ሪፖርትን መሰረት ያደረገ ተጠያቂነት ለምን አይኖርም?›› የሚል ነበር፡፡ ክቡርነታቸው መልስ ሲሰጡ ዋናው ነገር ሪፖርት አቅራቢ መስሪያ ቤቶች ያለውን እውነት ማሳየታቸው ነው ብለውናል፡፡ ሌላው በሂደት የሚደረስበት ነው ማለታቸው ነው፡፡ ችግሮቹን ለመሸፈን የሚደረግ ጥረት ቢኖር አሳሳቢ ይሆን ነበር፡፡ ይህ አቅጣጫ መቼም የመንግስትን ሀብትና ንብረት ተገቢ ባልሆነ መስመር ለሚጠቀሙ ሰዎች፣ ጥሩ አረንጓዴ መብራት ይመስለኛል፡፡ ዘራፊዎቹ ዘረፋ ይቀጥላሉ፤ ሀብት ይባክናል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የሀገሪቱን እድገት ከሁለት አሃዝ የሚያወርድ አይሆንም፡፡
በመጨረሻም በግሌ ያነሳሁት የግል ባንኮች ተሳትፎ በሚኖርበት ሁኔታ የማኑፋክቸሪንግን ዘርፍ ለማስፋፋት መንግስት ማበረታቻ ማድረግ ይኖርበታል የሚል ነበር፡፡ ለዚህ ጥያቄ የተሰጠው መልስ ለግል ባንክ የምንሰጠው ገንዘብ የለም የሚል ነው፡፡ የግል ባንኮች ገንዘብ መሰብሰብ ያለባቸው ከደንበኞች ቁጠባ ነው የሚል ሃረግም አክለውበታል፡፡ በግሌ ያቀረብኩት ሃሳብ፤ መንግስት ለግል ባንኮች ገንዘብ ይስጥ ሳይሆን፤ መንግስት ከግል ባንኮች የሚወስደውን ሃያ ሰባት በመቶ ያቁምና እራሳቸው ብድሩን ለግል ሴክተር ይስጡ ነው፡፡ መቼም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ባይጠፋቸውም፣ አጠቃላይ አድማጩን ህዝብ ለማሳሳት በሚመስል መልኩ ጥያቄውን ወደሌላ አቅጣጫ መርተውታል፡፡ አሁንም የግል ተሳትፎ እንዲጎለብት የግል ባንኮች ተሳትፎ መኖር አለበት ብንልም አይሆንም ብለዋል፡፡ የግል ሴክተሩ ለኢኮኖሚው ሞተር ነው እያሉ ሞተሩ የሚነሳበትን ባትሪ በመንቀል እንዳይሰራ እያደረጉት ነው፡፡ የግል ሴክተሩ ቢሳተፍ ባይሳተፍ በሁለት አሃዝ ማደጋችን ግን ይቀጥላል፡፡
አንድ ጥያቄ አለኝ! መንግስት የዚች ሀገር እድገት ሊቀንስ የሚችለው ምን ምን ሁኔታዎች ሳይሳኩ እንደሆነ ሊገልፅልን ቢችል እኛንም ከመደናገር ያድነናል ብዬ አምናለሁ፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ውስጥ ይህ እቅድ እንዲሳካ ታሳቢ ተብለው የተቀመጡት ነገሮች በአብዛኛው በታሰበው መሰረት አልነበሩም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን እድገቱ በታሰበው መሰረት ቀጥሏል …… የጉድ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሚባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚገኙት፣ መኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ ዉህደት በቅርቡ ይፈጽማሉ ተብሎ ይገመታል። በዚህ ዙሪያ፣ ይችን ሰሞን በሶሻል ሜዲያዎች፣ አንዳንድ ጤናማ ዉይይቶችን እያነበብኩኝ ነው። የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ከመኢአድ ጋር ሲዋሃድ ፣ መጀመሪያ የአንድነት እና የመኢአድ ጠቅላላ ጉበኤ፣ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ባሉበት በተናጥል ይደረጋሉ። ለዉህዱ ፓርቲ የሚቀርቡ ተወካዮችን እና ዉህዱ ፓርቲን የሚመሩ እጩ […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥ በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ …
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ለመጪው ምርጫ ይረዳቸው ዘንድ በተለያዩ የአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የህዝብ ተወካዮችን እየዞሩ በማነጋገር ላይ ሲሆኑ፣ የህዝቡ ተወካዮች ግን ችግሮቹን ሳይፈራ እያቀረበ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “የኢትዮጵያ መብራት ዝናብ የሚፈራ ነው” በሚል ዝናብ በዘነበ ቁጥር መብራት እንደሚጠፋባቸው ተናግረዋል። “ቋራ …
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት እስራኤል በሃመስ የሚወነጨፉ ሮኬቶችን ለማውደምና መሬት ለመሬት የተሰሩ መተላለፊያዎችን ለመዝጋት በሚል ምክንያት ጦሯን ወደ ጋዛ መላኩዋን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ ነው። እስካሁን ድረስ ከ800 በላይ ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው አብዛኛው ሟቾች ህጻናትና ሴቶች ናቸው። በእስራኤል ወገን ደግሞ …
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ሁለት በመፅሀፍ ንግድ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ናቸው። አንዱ በአደባባይ ሌላኛዋ ደግሞ በኢንተርኔት መፅሀፎችን ለአንባቢዎቻቸው ያቀርባሉ። ስለሁለቱ ወጣቶች የመፅሀፍ ንግድ እና ከዚህ ጋር ሳይነሳ የማያልፈው የማንበብ ፍላጎት እና ባህል፤ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ምን እንደሚመስል አንድ የከፍተኛ ተቋም መምህርን ጠይቀናል።
የፓርቲዉ መሪዎች ዛሬ ለጋዘጠኞች በሠጡት መግለጫ እንዳሉት ማሻሻዉ በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የክፍለ ሐገር አከላላል እንዲቀር፤ መሬት በግል እንዲያዝና ብሕራዊ ቋንቋ እንዲኖር የሚጠይቁ ሐሳቦች ተካተዉበታል።
ዛሬም እንደሳምንቱ መብታችንን እያሉ ኢትዮጵያዊያን በየመስጊዱ ተሰብሰበዋል። በየቀኑ በየቤተክርስትያኑ ጸሎታቸውን ያደርሳሉ። በየትምህርት ቤቱ በራቸው ተንኳኩቶ እንዳይወሰዱ ተደብቀው ያጠናሉ። መምህራን በፍራቻ፤ ለተማሪዎቻቸው ሳይሆን ለካድሬዎቹ ይሽቆጠቆጣሉ። አርሶ አደሮች ለሚያርሱበት መሬት፣ ለማዳበሪያና ለካድሬ ሲሉ አንገታቸውን ደፍተዋል። ላብ አደሮች የሥራ ዋስትና አንገታቸውን አንቆ ወገባቸውን አጉብጦታል። ነጋዴዎች ከኤፈርት ጋር ውድድሩ ራቁታቸውን አስቀርቷቸዋል። ጋዜጠኞች ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እኔ የምላችሁን ካላደረጋችሁ ተብለው እስር […]
ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ የማውቃቸው አንድነትን ከመቀላቀሌ ቀደም ብሎ ነው። የመድረክ ስራ አስፈፃሚ ሆኘ በምስራበት ወቅት የባለራዕይ ወጣቶች ሀያ ሁለት አከባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል አድርጎት በነበረው ስብሰባ ለመገኘት በሄድኩ ጊዜ ነበር ሀብታሙን ለመጀምሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት። የባለራዕይ ወጣቶች እንዲያ ተሰባስበው ስለሀገገር ጉዳይ ሲመክሩ ስመለከት ተስፋ ነበር የታየኝና ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር። አዲሱ ትውልድ በራሱ ጉዳይ […]