የግንቦት7 አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው
ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት …


