አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለመስከረም 19 ቀን 2006 ዓም አራዘመ
መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት የአዲስ አበባ መስተዳድር ከተማሪዎች ትምህርት መጀመር እና ከተለያዩ የአዲስ አመት በአላት ጋር በማያያዝ ፓርቲው ሰልፉን በሁለት ሳምንት እንዲያራዝም በተጠየቀው መሰረት፣ ጥያቄውን ተቀብሎ ለማራዘም ፈቃደኛ ሆኗል። መስተዳድሩ ፓርቲው ተቃውሞውን መስከረም 19 ማካሄድ የሚችል መሆኑን ከመስተዳድሩ ወረቀት አግኝቷል። አቶ ዘካሪያስ መስተዳድሩ ሰላማዊ ሰልፉን …
