በታዬ ዘሐዋሳ
በሃገራችን በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም አመለካከት የተነሳበርካታ ኢትዮጵያውያን በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል:: የሚኖሩበትም ሃገር ብዛትና ስብጥር በራሱ ከሌሎች ሃገራት ዜጎች የተለየን ያደርገናል ብዬአስባለሁ:: እንደ ሃገራቱ ስብጥር እና ብዛት ሁሉ የሃበሻ አመለካከትም እጅግብዙ ነው:: ይህ ብዛት ያለው ስብጥር ደግሞ ወጥ የሆነ አመለካከት እንዳይኖረን አድርጓል:: ክፍፍላችንም እንደዚያውብዙ ነው:: ፍረጃችንም ጭምር:: የዛኑ ያክልም ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራለመፈራረጅ ወይምለመሞጋገስ ከንፋስየፈጠነ ነው:: ፍረጃው ከተለያዩ አካላት ይጀመር እንጂ አብዛኛዎቹን ፍረጃዎች በማዳነቅና በማሟሟቅ ረገድ የሁሉም ድርሻ አለበት:: አንዲት የፌስቡክ ወዳጅ ስለፍረጃዎች ብዛትእና ጥልቀት ትዝብቷን አካፍላን ነበር:: ከነዚህ የርስ በርስ ፍረጃዎች ውስጥ የሚከተሉት በስፋትየምናስተውላቸው ናቸው:-
. ኢቲቪ ወይም ኢሳት
. ኢህአዴግ ወይም ተቃዋሚ
. አይጋፎረም ወይም ኢትዮጲያን ሪቪው
. አዲስዘመን ወይም ፍትህ
. ኢትዮጲያወይም ሞት ወይም ገንጣይ ተገንጣይ
. እምየሚኒሊክ ወይም አፄ ዮሃንስ
. ኢትዮጲያፈርስት ወይም ኦሮሞ ፈርስት
. ልማትወይም ሰብአዊ መብት
. ንኡስከበርቴ ወይም ደሃ
. ኪራይሰብሳቢ ወይም ልማታዊ
. ሰለፊስትወይም አህባሽ
. የውጪሲኖዶስ ወይም የሃገር ውስጥ ሲኖዶስ
. የምርጫትግል ወይም የትጥቅ ትግል
. ጠባብወይም አገር ወዳድ
. ባንዳወይም ጀግና
. የባንዳልጅ ወይም የጀግና ልጅ
. X ወይምY እያለ ይቀጥላል::
ይህን የፍረጃ ብዛት እና አይነት ለግዜው በዚህ እናብቃው:: የፅሁፌ መነሻ ርዕሥ በርካታ ሃሳቦችን ማስነሳት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራንበተመለከተ የተለያዩሃሳቦችን ማንሳትና ማወያየት እንደሚችል ግልፅ ነው:: አነሰም በዛም እነዚህን ሃሳቦች እያነሱ መወያየትም ሆነ መተራረም ስለ ድክመታችን አውቀን የማስተካከያ እርምጃ እንድንወስድ ይረዳናል:: ድክመቱን በገደምዳሜ እያየንየምናልፈው ከሆነግን ለሃገራችንም ሆነ ለህዝባችን ፋይዳ አናመጣም:: መፅሃፉ እንዳለውም አስቀድሞ በአይናችን ያለውን ምሰሶ ማውጣት ስንችል ነው የጓደኛችንን ጉድፍ ማየት የምንችለው:: ነገርግን የኛ ዳያስፖራ እሱ ያለው እንጂ ሌላው የሚለው ትክክል አይደለም ብሎ የማሰብ አዝማሚያ ያሳያል:: እናም ምናልባት የኔ ሃሳቦች ከተወደደው ዳያስፖራሃሳብ ጋር ካልተስማሙ የማይስማሙበትን ሁኔታ ለመስማት ዝግጁ መሆኔን አስቀድሜ ልግለፅ:: የባህርያችንን ጥልቀት ለማሳየትም ይመስላል “ኢትዮጵያየገባ አንድ ፀሃፊ በማግስቱ ስለ ኢትዮጵያውያን ከአንድ በላይ መፅሃፍ ሊፅፍ ይችላል:: በሁለተኛው ቀን ምናልባት ከተሳካለት ለጋዜጣየሚሆን መጣጥፍ ሊፅፍ ይችላል:: ሳምንት ሲቆይ ግን ያ ሰው ስለ ኢትዮጵያውያን አንድአረፍተ ነገር እንኳ መፃፍ አይችልም” አለየሚባለው:: ለማንኛውም ለዛሬ የሚከተሉትን “እዛም እዛም የረገጡ” ሃሳቦችንላንሳ:: ነገር ግን የማነሳቸው ሃሳቦች ከጥቂት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችጋር ግንኙነት የሌላቸው እና እንደማይመለከታቸውም ባውቅም ብዙሃኑን ይወክል ዘንድ እነዚያን ጥቂቶችም የፅሁፌ አካል አድርጌያቸዋለሁ:: ለዚህአስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ::
1) የእርስ በእርስ ፍረጃ መፍትሄ ይሆነናል?
ፍረጃ በማንኛውም ልኬትቢለካ ወደምንፈልገው የልማት ግብ ሊያደርሰን አይችልም:: ክፍፍሎችንና ፍረጃዎችንእየተከተልን ስንጨቃጨቅእና ስንፈራረጅ ዓለም ጥሎን መሄዱ አይቀርም:: የፍረጃችንን ጥልቀትየሚያሳይ አንድ ትዝብት ላንሳ:: አንዱ የውጭ ሃገር ዜጋ ስለኛ ክፍፍል እና ፍረጃ ከሃበሻ ጋር ሲወያይ “እናንተኢትዮጵያውያን በእስካሁኑሂደት በብሄር፤ በጎሳ፤ በቋንቋ፤ በሀይማኖት እናበመሳሰሉት ተከፋፍላችኋል:: አሁን የቀራችሁ ነገር ቢኖር በስማችሁ ፊደል ቅደም ተከተል መከፋፈል ነው፡፡” አለየሚባል መራራ የቀልድ እውነታ አለ:: በብዛት እንደምንታዘበውም አብዛኛውስለወቅታዊው ፖለቲካየሚያወራልን ኢትዮጵያዊሁሉ አንድነትን ወይም ህብረትን የሚሰብክልን የራሱብሄር ከፍታ ቦታ ላይ ሊሆን እንደሚችል ካሰበ ብቻ ነው:: የርሱን ብሔር የተመለከተ ሌላ ታሪክ ወይም ድርጊት ከተነገረ ከርሱ በላይ የዘር ፖለቲካን አራማጅ የለም:: ፍረጃውም በአይነት በአይነት ተደርድሮ ይቀርባል:: ይህንን አይነት አካሄድን የሚያሳየን ደግሞ በተለያዩ ግዜያት ጣል በሚደረጉ አመለካከቶች ስር የሚሰጡ አስተያየቶችን መመልከትስንችል ነው:: እንደዚህ አይነት አመለካከትና አካሄድምናልባት የምንፈራውን ከማፋጠን ያለፈ ፋይዳ የለውም:: ስለ አንድነት ሲሰብክ የነበረ ኦሮሞ ስለ ኦሮሞ እርሱ የማያምንበት ተፅፎሲያነብ ለዛ ፅሁፍ መልስ ወይም ማስተካከያ እና መከራከሪያ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ የፀሃፊውን ዘር እያነሱ ጥንብ እርኩሱን በማውጣት ፍረጃ የሚያወጣለት ከሆነምኑን ስለ አንድነት ሰበከው? ስለዘር ፓለቲካ ጎጂነት አሳምሮ አቀነባብሮ የሚሰብከንሰው ስለትግሬ መጥፎነት በማውራት እና በመፈረጅ ካጠናቀቀው የቱላይ ነው አንድነትን የሚያሳየው? አንድነት ሃይል ነው እያለ የሚያስተምር ሰውስለ አማራ ጨቋኝነት እያነሳ እና አማራውን እየፈረጀ ሌላው ብሄር አማራን እንዲጠላ ከሰበከ የቱ ላይ ነው አንድነቱ ያለው? አንድ ነን እያለ ትግሬን አትመኑ ካለን፣ አንድ ነን እያለ አማራ በድሎናል በማለት ያለፈ ታሪክ ካወራ፣ አንድ ነን እያለ ኦሮሞ የመጣው ከዚያ ነው ካለ የቱ ጋር አንድነቱ ያለው? የሚወራው አንድነትስ የማን ነው? አንድነቱ ከግለሰቦች ካልጀመረ እንዴትስ አንድነት ይሆናል? ይህን ትዝብት ለግዜው እዚህ ልግታዉና ወደ ቀጣይ ሃሳብ ላምራ::
2) ምን ያህል ዳያስፖራዎች ናቸው ሃገራቸውን የሚወዱት?
የግሌ መልስ “ምናልባት20% የሚሆኑት ይወዱ ይሆናል” ባይነኝ:: ሃገርን የመውደድ ልኬቱ በኔና በነሱ ሊለያይ ይችላል:: ለኔ ሃገርን መውደድ ማለት የግል ፍላጎትን እና ምቾትን ለሃገር አሳልፎ መስጠት ነው:: ሃገርን መውደድ ማለት እራስን አሳልፎ እስከመስጠት ማለት ነው:: ሃገርን መውደድ ማለት መከራን እና ችግርን መሸሽ አይደለም:: አንድ ሰው ፖለቲከኛ ሲሆን ለግል ጥቅሙ ሳይሆን ለህዝብና ለሃገር ሊሰራ ቆርጦ ተነሳ ማለት ነው:: ሆኖም ግን አንድ ችግር ሲያጋጥመው የሚኮበልልከሆነ ቀድሞውኑ የተነሳው ለራሱ ግላዊ ጥቅም እንጂ ለሃገርና ለህዝብ አልነበረም ማለት ነው:: ከዚህ የፖለቲከኞች ቁማር ጋር በተያያዘ የበርካቶችን ታሪክ ማንሳት ይቻላል:: ነገር ግን ከዚህ በፊትም ብዙ ስለተባለ ልለፈው:: በኔ አመለካከት ፖለቲከኛ ለያዘው አላማ ሞትን የሚጋፈጥ እንጂ የሚሞዳሞድ ወይምወደ ባእድ ሃገር የሚፈረጥጥ አይደለም::
ሌላው በዚህ ርዕስ ስር የማነሳው ሃሳብ ሰልፍን ይመለከታል:: በተለያዩሃገሮች ላይ ሃበሾች ሰልፍ ሲወጡ ይታያሉ:: ለምንድን ነው ሰልፍ የሚወጡት? ሀገራቸውን ስለሚወዱወይስ በሌላ ምክንያት? ከላይ እንዳልኩት 80%ቱምክንያታቸው ሌላነው:: ሃገሩንና ህዝቡን የሚወድ ሰው በሩቁ ሆኖ “ሊመታችሁነው ተጠንቀቁ” “ሊገላችሁ ነው ሽሹ” ወይም“ገደላቸው ገረፋቸው” እያሉ በባዶ ሜዳ መፈክር ማሰማት አይደለም:: ሃገሩን የሚወድ ሞትንም ቢሆን ተጋፍጦ ለሃገሩ ለውጥ ያመጣል እንጅ በተንደላቀቀ ኑሮ ላይ ሆኖ እንዲህ እኔ እንደምጽፈው መፈክር እያዘጋጁ መሰለፍ አይደለም:: ከተሰላፊዎቹ መካከልበርካታ የሃገሪቱ አንጡራ ሃብት ፈሶባቸው በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ ነገር ግን ብር Read more ›