ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ በደብዳቤያቸው ከዚህ ቀደም ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸውና ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጡ በመስጋታቸው ደብዳቤ ለመጻፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው “የፖለቲካ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊ ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር እየተጠናከረ መምጣት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙና አላማቸውን ፣ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያቀርቡ ማድረግ፣ ገዢው ፓርቲ መንግስታዊ መዋቅርን …

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመቃወም የተጠራው ሰልፍ የአገሪቱን ዋነኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢነርኬን ሽፋን አግኝቷል። ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በተጠራው ተቃውሞ፣ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ኖርዌይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽመው መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንድታቆም ጠይቀዋል።በኢትዮጵያ ለሚታየው …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

«በዘመናዊ አቅድ ስዕል ራሱ ሐሳብ ነው። የአንድ ነገር ሁኔታ የአንድ ነገር ትርጉምና ስሜት ነው…። ዛሪ ስው ራሱን ብቻ መመልከት ትቶ ዓለም ከብዙ ርቀት ከብዙ በኩል ሲታይ ምን አይነት ስሜት አንደሚስጥ – ዓለማዊ ዘላለማዊ የሆነውን ነገር በመተርጎም – በዓይን የሚታይ፥ የቀለም፥ የመስመርና የቅርጽ ሙዚቃ ለመፍጠር ይጥራል።»

የአዉሮፓ ኅብረት የጤና ሚኒስትሮች ኤቦላ ከተስፋፋባቸዉ የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የሚመጡ ተጓዦችን በየአዉሮፕላን ማረፊያዉ የሚቆጣጠሩበትን ስልት ባስቸኳይ ዳግም ለመከለስ ተስማሙ።

የአፍሪቃ የገበያ ቦታዎችን ወደዘመናዊ የገበያ ማዕከልነት ለማሻገር እንዲቻል በወጣ ዓለም አቀፍ የስነሕንፃ ንድፍ ዉድድር ሁለት ኢትዮጵዉያን የዘርፉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንድፍ ማሸነፉ ከወደፓሪስ ተሰምቷል። የንድፍ ዉድድሩን ያወጣዉ መቀመጫዉን በፓሪስ ፈረንሳይ

በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የኢቦላን ተኀዋሲ መስፋፋት መግታት ይቻል ዘንድ ባለሙያዎችን ያሠማራው የአፍሪቃ ሕብረት አዲስ ተስፋ መኖሩን አስታወቀ። የሕብረቱ ጽ/ቤትና የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽኑ በሕብረት በመሰለፍ፤ ተስፋው ፤

– ሕወሓት አልሸባብን ሽፋን አድርጎ ፍንዳታ ለመፈጸም እንዳቀደ መረጃዎች ያሳያሉ። – አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ላለማጣት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራች ነው። – አልሸባብ ላይ ማሳበብ ለምን አስፈለገ ? በምስራቅ አፍሪካ ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት የአሸባሪ ቡድኖች ስሙ በዋነኛነት የሚጠቀሰው አልሸባብ በቡድን ደረጃ የታጠቀ ሲሆ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የሕወሓት ቡድንም ሌላኛው ነው። እንዲሁም ሻእቢያ በግርግር መሃል ለመሹለክለክ […]

ኑፋቄያቸውና ሕገ ወጥ ጥቅማቸው እንዳይጋለጥ የሚሰጉ አካላት ያስተባበሩት ነው የብፁዓን አባቶች ስም እየተጠቀሰ የወረደው የስድብ ናዳ በእጅጉ አሳዝኖናል በፈቃዳችንና በነፃ የምንፈጽመውን የአገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው ግለሰቦቹ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ከቀጠሉ ማኅበሩ በሕግ ይጠይቃቸዋል *               *               * የስም ማጥፋት ድርጊቱን የፈጸሙበት ግለሰቦች÷ ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ …

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች በስፋት ተደረጉ። ባለስልጣናቱ፣ የሕዝቡ ሰላማዊ ተቃዉሞ አይሎ መምጣቱን ሲያዩ አፈገፈጉ። የተቃዋሚዎች ስብስብ በክልል ምርጫዉ ያገኙትን ምርጫ፣ ተቀበሉ። ሊበራል ዴሞክራቱ ዞራን ጂንጂች የአገሪቷ መዲና የቤል ግሬድ ከንቲባ ሆኑ።

ብዙም አልቆየም፣ በተቃዋሚዎች መካከል ችግር መታየት ጀመረ። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ ፓርቲና በዞራን ጂንጂች በሚመራዉ ፓርቲ መካከል ልዩነቶች ተፈጠሩ። መካረር መጣ። የሕዝብን ጥያቄ አንግቦ በጋራ መቆም ተሳናቸው። በአደባባይ መወጋገዝ ጀመሩ። በአመቱ አገራዊ የፕሬዘዳንት ምርጫ ሲደረግ የሚሎሶቪች የሶሻሊስት ፓርቲ በቀላሉ ስልጣኑን ጨበጠ። የተለፋበት፣ የተደከመበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሸፈ። አምባገነኖች አሸነፉ። በሕዝብ ትግል የተገኙ ዉጤት እንደገና ተቀለበሱ። ዞራን ጂንጂችም ከናካቴዉ ከተመረጡበት የቤልግሬድ ከንቲባነት ተነሱ።

በ1998 በየክልሉ ተማሪዎች «ኦትፖር» ( በሰርቢያን ቋንቋ እምቢተኝነት) በሚል ስም ከታች ወደ ላይ የሆነ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የተከፋፈሉ የፖለቲካ ደርጅቶች በአንድ ላይ እንደገና ተሰባሰቡ። ካለፉት ስህተቶች በመማር፣ ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለሚቀጥለው ምርጫ መዘጋጀት ጀመሩ። ከፍተኛ ጫና እየተደረገም ዝግጅቱ ተጧጧፈ። የገዥዉ ፓርቲ ደጋፊዎችን የመሳብ ሥራ በስፋት ተሰራ። በዚህም ምክንያት በርካታ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ጀመሩ። ኢቫን ስታምቦሊች ፣ የሚሎሶቪች አጋር የነበሩ ፖለቲከኛ ፣ ተቃዋሚዎች በመቀላቀላቸውም በሚሎሶቪሽ የደህንነት ሰራተኞች ታፍነው ተገደሉ።

ሴፕቴምበር 2000 ዓ.ም ምርጫ ተደረገ። የሚሎሶቪች ምርጫ ቦርድ፣ አሁንም የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት ይፋ አደረገ። ያንን አስከትሎ ኦክቶቦር 2000 ዓ.ም ፣ ትልቅ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። ምርጫ ቦርድ የምርጫዉን ዉጤት ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተገደደ። የተቃዋሚዎች እጩ የሆኑት ኮስቶኒሳ እንዳሸነፉ ተገለጸ። የሚሎሶቪች ስልጣን ፍጻሜ ሆነ። የሰርቢያ ሕዝብ የማይቀለበስ ድል ተቀዳጀ።

ይሄንን ያለ ምክንያት አይደለም ያመጣሁት። በሰርቢያ፣ በመጀመሪያዉ ምርጫ የተከሰተው፣ በኢትዮጵያም በምርጫ ዘጠና ሰባት ከተከሰተው ብዙ የሚለይ አይደለም። ያኔ በቅንጅት ጊዜ የሕዝብ ጉልበት አያሎ የወጣበት ወቅት ነበር። ነገር ግን በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠሩ ልዩነቶች፣ በቀላሉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ለመቆየት ቻለ። (በገዢው ፓርቲ የደረሰው ወከባ፣ ግድያ፣ እሥር፣ እንግልትን ጫና ቢኖርም፣ በዋናነት የተቃዋሚዎች ችግር ነው አገዛዙን ያቆየው ብዬ ነዉ የማምነው)

ሰርቦች ጠመንጃ አላነሱም። ሰርቦች ለዉጥ ማምጣት አይቻልም ብለው አላወጁም። ሰርቦች ተስፋ አልቆረጡም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ተስፋ ቆረጥን። ፎጣችንን መሬት ላይ ጥለን፣ አምባገነንነትን አሜን ብሎ የመቀበል አዝማሚያ አሳየን። «ተቃዋሚዎች አይረቡም። ያኔ ደግፈናቸው ጉድ አላደረጉንም እንዴ ? አርፎ መቀመጥ ይሻላል፣ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ….» የሚሉ ጨለምተኛና የሽንፈት አባባሎችን ማሰማት ጀመርን።
የገዢዉ ፓርቲ ሰዎችም፣ ስልጣን ላይ ለመቆት የሚያስችላቸው፣ ይሄዉ የተቃዋሚዎች መከፋፈልና የሕዝቡም ተስፋ መቁረጥ ስለነበረ፣ በሚቆጣጠሯቸው ሜዲያዎች፣ ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ የበለጠ ተስፋ እንዲቆርጥ፣ ከፍተኛና ሲስቴማቲክ፣ ተቃዋሚዎች የማጥላላትን የማሳነስ ዘመቻቸዉን አፋፋሙ። ጠንካራ የሚሏቸውን የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለ ርህራሄ አሰሩ። ብርቱካን ሚደቅሳን አሰቃይተውና ሰባብረው (ለስድስት ወራት ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር ጨለማ ቤት ዉስጥ እንዳስቀመጧት) ለስደት ዳረጓት። «እነርሱን ያየህ ተቀጣ» በሚል፣ በአንዱዋለም አራጌ፣ በእስክንደር ነጋ፣ በርዪት አለሙ፣ በዉብሸት ታዬ፣ በበቀለ ገርባ፣ በአብርሃ ደስታ፣ በሃብታሙ አያሌው፣ በዳነል ሺበሺ፣ በየሺዋስ አሰፋ፣ በተመሰገን ደሳለኝ፣ በዞን ዘጠኞች እንዲሁም በሌሎች ..ሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ፣ በተራ የዉሸት ሽብር ክስ፣ ኢፍትሃዊነትና ኢሰብአዊነት የተሞላበት ግፍ መፈጸማቸዉን ቀጠሉ። በሕዝቡ አይምሮ ዉስጥ፣ እነርሱን ማንም ሊነካቸው የማይችሉ፣ ግዙፎች (ኢንቪሲብል) እንደሆኑ ለመሳል መሞከርና፣ ሕዝቡ እርስ በርስ ተፈራርቶ እንዳይደራጅ፣ እንዳይነጋገር፣ እንዳይተማመን፣ በዘር፣ በኃይማኖት በጥቅም እንዲከፋፈል፣ ማድረጉን ተያያዙት።

ነገር ግን ኢትዮጵያዉያን መንቃት ያለብን ይመስለኛል። ከሰርቦች መማር ያለብን ይመስለኛል። አምባገነኖች ኃይለኛ የሆኑ ይመስላሉ እንጂ ሁልጊዜ ባዶ መሆናቸዉን መረዳት አለብን። ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሕዝብ ድጋፍ የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀ፣ ለሕዝብና ለዜጎች ከበሬታ የማያሳይ፣ ዜጎችን ሽብርተኞች እያለ የሚያሸብር፣ የበሰበሰ ድርጅት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነዉ።

እንግዲህ «ትላንት ወድቀናል ብለን፣ የትናንቱ ጠባሳችንን እያየን ወደፊት ከመራመድ መቆጠብ የለብንም» እላለሁ። ከስህተቶቻችን ተምረን፣ ያለፈው ታሪካችን በአይምሯችን እየፈጠረ ካለው ጎታች ጫና ተላቀን፣ ይሄንን ዘረኛና አምባገነን ስርዓት ለመቀየር በቁርጠኝነት መነሳት የግድ ነዉ። ቁልፉ በእጃችን ነዉ። በርግጥ ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። ጥያቄው «ፍላጎቱ አለን ወይ?» የሚል ነዉ።

እያንዳንዳች ወደ ራሳችን እንመልከት። እራሳችንን እንጠይቅ። «እስከመቼ ነዉ፣ በአገራችን እንደ ባይተዋር ፈርተን እና አንገታችንን ደፍተን የምንቀመጠው ?» ማለት እንጀመር። በየወረዳችን፣ በየአካባቢያችን፣ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶችን እንቀላቀል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ጠንካራና አገር ሰፊ የኢትዮጵያዊትነትና የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነዉ። በመቀሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ አዳማ ፣ አሶሶ …በአገርቷ ክፍሎች ሁሉ ብትሄዱ አንድነት በዚያ አለ። አንድነትን እንቀላቀል። አንድነትን እንደግፍ። የሰማያዊ ፓርቲ ፣ መኢአድ፣ ትብብር ..ሁሉም በፊናቸው የሕዝብን ጥያቄ እያሰተጋቡ ነው። እንቀላቀላቸው። እንደግፋቸው። ልዩነቶቻቸውንም አጣበው ፣ የበለጠ ኃይልና ጉልበት ኖሯቸው ሰላማዊ፣ የኢትዮጵያዊነት የሰለጠነን የፖለቲካ ትግል ይመሩ ዘንድ፣ እንዲሰባሰቡ፣ እንዲዋሃዱ እናበረታታቸው።

 

 

 

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃአውጭ ግንባር በካሉብ አካባቢ ሰሞኑን በርካታ ጥቃቶች ፈፅሜ ብዙ ጉዳት አደረስኩ ይላል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራው ድርጅት ሕልውናው ያከተመ ነው፤ የተፈፀመ ጥቃትም፣ የደረሰ ጉዳትም የለም ብሏል፡፡

 

 

 

የዘጠኙ አምደኞችና ጋዜጠኞች ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቤ ሕግ የበኩሉን ምላሽ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ከተከሳሾቹ መሃል ሁለቱ ሴት እሥረኞች ያቀረቡት አቤቱታ የሚመለከተው የማረሚያ ቤት ባለሥልጣን ሳይገኝ ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን ትዕዛዞች ጠቅሶ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ዘግቧል፤ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

 

 

አዋሽ ሞልቶ ባስከተለው መጥለቅለቅ ሳቢያ ከሰላሣ ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሏል፡፡

በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ፤ ለጊዜው መጠኑ ባልታወቀ ንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

ለውኃ ሙላቱ ምክንያት የሆነው በአካባቢው ደጋማ ሥፍራዎች የጣለውን ከባድ ዝናም ያስከተለው ጎፍርፍ መሆኑ ታውቋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዜጎቹ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አልሸባብ በቦሌ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። ኤምባሲው አዲስ መግለጫ እስከሚወጣ ድረስ ዜጎቹ ከሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የማምለኪያ ቦታዎች፣ ከገበያ ቦታዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲርቁ መክሯል። ጥቃቱ የሚፈጸምበት  ትክክለኛ ቦታ ባይታወቅም ፣ የአሜሪካ ዜጎች …

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩት ጸሃፊዎች እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። የተከሳሽ ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቢ ህግ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ይዟል። ተከሳሾቹ  ነጭ ልብስ ለብሰው መቅረባቸውን፣ በጥሩ መንፈስና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዘጋቢያችን …

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው ማህበሩ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ  ማህበሩ” በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት …

 #FreeZone9bloggers #Ethiopia

የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ውሎ

ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ በነሶልያና ሽመልስ የሽብር ወንጀል የክስ መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ቀጠሮ ችሎቱ ከ20 ቀን በኃላ እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቀቀ። 

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ። 

ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል። 

በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ። 

በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል። 

በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።

በቅርቡ ሐገሩን ጥሎ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ከትናንት በስተያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የጋዜጠኛ ሚሊዮን ባልደረቦች እና ጓደኞች እንደሚሉት ሚሊዮን ያረፈዉ ለሁለት ሳምንት ያሕል ከታመመ በሕዋላ ነዉ።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በዓለም ዙሪያ ፣ የዓለም የምግብ ዋስትና ዕለት ታስቦ ይውላል። በኢትዮጵያም በዋዜማው ይታሰባል። ጥቅምት 6 ወይም (Oct 16) የሚታሰበው ፤ በመጪው 2015 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 70 ዓመት የሚደፍነውን ፣ የተባበሩት መንግሥታትን የምግብና የግብርና ድርጅት ምሥረታ መንስዔ በማድረግ ነው።

በላይቤሪያ የተከሰተው የኤቦላ ወረርሽኝ ታማሚዎችን ብቻ ሳይሆን የጤና መኮንኖችዋን እና ሀኪሞችዋን ጭምር ስጋት ላይ ጥሎዋል። የጤና መኮንኖቹ እና ሀኪሞቹ በኤቦላ የተያዙትን ሰዎች በማስታመሙ ተግባራቸው ላይ

በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡባት የመን ዛሬም የተረጋጋች አትመስልም። ከሰንዓ የሚወጡ የተለያዩ የዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚለዉ በሁቲ አማፅያንና በአልቃይዳ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደዉ ዉጊያ ቢያንስ የ12 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል።

“ልዩነት የግድ ጥላቻን ወይም ድብድብን ማስከተል አለበት ብለው የሚያምን እና የሚያስብ በድርጊቱም የሚገፉ ካለ ከባድ ስዕተት ነው፡፡ ፣ልዩነትን በአንድ ጊዜና ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በሰለጠነና በሰከነ አካሄድ በውይይትና በሀሳብ ልውውጥ ማጥበብ ይቻላል፡፡” ለዚህም ይመስላል አንድነት ፓርቲ ውስጣዊ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ባይባልም መሠረታዊ ችግሩን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቻለው፡፡ የዚህም ጥሩ ማመላከቻ የሚሆነው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ […]

ይህ በአቶ ነሲቡ ስብሃት የተፃፈ መጽሓፍ በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ በነበረው አረመኔያዊ ሥርዓትና ሥርዓቱን ሲታገል በነበረው ኢሕአፓ የተመራው ቆራጥ ትውልድ መካከል የተካሄደው መራራ ትንቅንቅን በዝርዝር መረጃዎች አስደግፎ ያቀርባል። ስለሆነም፤ በዛን ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ማለት፣ በአንድ በኩል ላገርቷ አንድነት፣ ለህዝቧ ነፃነት፣ ፍትሕና እኩልነት ለመታገል ቆርጦ የተነሣ ትውልድ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝቡን ትግል አጨናግፎ የራሱ ፍላጎት በህዝቡ […]

ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡ …

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብስባ ዛሬ ይጀመራል፡፡ ዘንድሮ ለ፴፫ኛ ጊዜ የሚካሔደው ይኸው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ከጥቅምት ፭ – ፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሚቆይ ሲኾን ከ50 አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከ800 ያላነሱ ልኡካን ይገኙበታል፡፡ የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ ከኾነው ከአዲስ አበባ፣ የሀገረ ስብከቱን ተወካዮች ጨምሮ …

በስደት ላይ የሚገኘው የማራኪ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ሚልዮን ሹርቤ ባደረበት ህመም በትላንትናው እለት አረፈ።

ሚልዮን፤ “በኢትዮጵያ መንግስት ወከባ እየደረሰብን ነው፤” ባሉት ወከባ ሳቢያ በቅርቡ ከአገር ተሰደው ወደ ጎረቤት አገሮች ከኮበለሉ የመጽሔት አዘጋጆችና አሳታሚዎች አንዱ ነበር።

ሚልዮን የሕክምና እርዳታ ያገኝ ዘንድ በጓደኞቹ አማካኝነት በቀረበለት ጥያቄ መሠረት እገዛ ያደረገው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ የምሥራቅ አፍሪቃ ቢሮ ተጠሪ Tom Rhodes በጋዜጠኝነት ሥራ በተሰማሩበት በሚገጥማቸው ወከባ ሳቢያ አገራቸውን ጥለው ለመኮበልል የሚገደዱ ጋዜጠኞች ብዙዎቹ ለተለያዩ በሽታዎችና ለባሰ እንግልት ይጋለጣሉ፤ ይላል። አንዳንዱ በቀላሉ ሊታከሙ የሚችሉ የበሽታ ዓይነቶች ቢሆኑም እንዲህ እንዳሁኑ የከፋ ውጤት የሚያስከትሉበት ጊዜ ግን…

የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ። በጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል። ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ […]

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የተነሳ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በአሚባራና ዱላሳ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአሚባራ አካባቢ ከ5 ሺ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት መውደሙን፣ የ7 ቀበሌ ሰዎች በውሃ መከበባቸውንና ንብረታቸው በውሃ መወሰዱን እንዲሁም አንድ የእርሻ ምርምር ማእከል በውሃ መወሰዱን ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት የችሎት መቋረጥ በሁዋላ ስራ የጀመረው ፍርድ ቤቱ፣ አንድ ምስክር እንካ በአግባቡ ሳያዳምጥ መብራት ሄደ በሚል ምክንያት እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጿል። ሰኞ በነበረው ችሎት አቶ አህመድ ኡመር የተባሉ ምስክር እየተናገሩ ባለበት ጊዜ  ምስክርነታቸው ሳይጠናቀቅ መብራት በመሄዱ ለማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም ዛሬ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሁኔታ ችሎቱ ሳይካሄድ መቅረቱን ድምጻችን ይሰማ …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ” በሚል ወንጀል የተከሰሰው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሁዋላ፣ ውሳኔውን በእስር ላይ ሆኖ እንዲሰማ ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ እስር ቤት ተልኳል። ጋዜጠኛ ተመስገን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሲሰራ ” ድህረ ምርጫ 1997 ዓምን ተከትሎ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን …

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል። ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የሴቶችና እናቶችን የስነተዋልዶ ጤና ለማሻሻል ከሚረዱ እንቅስቃሴዎች አንዱ ነፍሰ ጡር እናቶች በሚገላገሉበት ጊዜ በተገቢዉ መንገድ በሰለጠኑ አዋላጆች መረዳት መቻላቸዉ ነዉ። ይህን እድል ያላገኙና የማያገኙ ደግሞ በተራዘመ ምጥ ምክንያት ለፊስቱላ ተጋልጠዉ የከፋ ህይወት ለመግፋት ይዳረጋሉ።