Tag: ethiopian news in amharic
‘አሸባሪ ብዕሮች’
ክንፉ አሰፋ
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።
አሸባሪ ብዕሮች
ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።
አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ ጠባቂም እየሆነ የህዝብን በደልም ይፋ አድርጓል። ይህን የተቀደሰ ተግባር ማከናወን እንደወንጀል፤ ጠንከር ሲል ደግሞ እንደ ሽብርተኝነት የሚቆጠርበት ሃገር ሆናለች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ።
መብትን ማወቅ እና ማሳወቅ፤ ‘ህዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ማድረግ፤ ወይንም በስራዓቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ነው’ ተብሎ ከተተረጎመ ደግሞ ጋዜጠኛን በአሸባሪነት መፈረጁ ብዙ ሊደንቀን አይገባም።
ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት-አመታት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በቁጥር አንደኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሃገር ናት። አሁን ይህንን ደረጃዋን ለቃለች። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑን ተከትሎ ከመጡት ለውጦች አንደኛው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የአንደኝነት ደረጃዋን ያጣችው ታዲያ ትራንስፎርሜሽኑ ይዞት በመጣው መሻሻል አይደለም። ነጻ ፕሬሱ ከሃገሪቱ እንዲጠፋ በተደረገ ሁለገብ ጦርነት እንጂ። አብዛኛው ጋዜጠኛ ተሰድዷል፣ ጥቂቶቹ ታስረዋል፣ አንዳንዶቹም አቅማቸው ተሟጦ አልቆ፤ ዝም ብለው እንዲቀመጡ ተደርገዋል። ለነጋሪ የተረፉትንም እስከዛሬዋ እለት ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ።
ከጅምሩ በፕሬሱ ላይ የተከፈተው የገዥው ፓርቲ ውግያ ቀላል አልነበረም። ፕሬሱ ግን እለት ተዕለት የሚያርፍበትን የአንባገነኖች ጡጫ ሁሉ ችሎ ብዙ ተጉዟል። እየተንገዳገደ፤ እየወደቀና እየተነሳ የህዝቡን የህሊና ንቃት እንዲሰፋ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዲዳብር ነጻው ፕሬስ ተግቶ ሰርቷል። የህትመት ዋጋ እስከ 500% እንዲጨምር ቢደረግም ፕሬሱ አልቆመም ነበር። ጋዜጠኞች እንደጥጃ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተሰቃዩም ስራቸውን ላለማቋረጥ መትጋታቸውን አላቆሙም። በካድሬ ዳኞች ፍርደ-ገምድል ፍትህ ሲሰጣቸው፤ ያለ አግባብ በእስርና በገንዘብ ሲቀጡም ሰራቸውን አላቋረጡም…
የአሜሪካው ፍሪደም ሃውስ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎች ኢትዮጵያን ፕሬስ (Status: NOT FREE) “ነጻ ያልሆነች” ሃገር ሲል ፈርጇል። የፕሬስ አዋጁንም ፍጹም አፋኝ ሲል ይከሳል። የፈረንሳዩ ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፣ የኒውዮርኩ ሲ.ፒ.ጄ. እና የብራስልሱ አይ.ኤፍ.ጄ. በሽብር ክስ የተያዙ የጋዜጠኖችን ሰነድ እያከታተሉ አሳፋሪነቱን ቢገልጹም አፍ እንጂ ጆሮ ከሌለው ስርዓት ያገኙት የስድብ ምላሽ ብቻ ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችም አፈናውን ይፋ ማድረጉን ተያይዘውታል። ከገዥው ፓርቲ የሚያገኙት ምላሽ “የኒዮ ሊበራል” አቀንቃኞች የሚል ስድብ እና ዛቻ ብቻ ነው።
ከምርጫ 97 ነኋላ ግን የህወሃት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን፤ ጫን ያለ ነገር ይዞ ብቅ አለ።
ሽብርተኝነት!
ከዚህ በኋላ ጋዜጠኛ በህገ-መንግስት ሳይሆን፤ ህጉን በሚጻረረው አዋጅ መዳኘት እንዳለበት ተነገረ። ስርዓቱም በባሩድ ሳይሆን ይልቁንም በብእር ጫፍ እንደሚሸበር አረጋገጠ።
ይህ የሽብርተኝነት አዋጅ ቃል በቃል የተቀዳው ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ መንግስታት ሰነድ መሆኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ድንቅ ነው። ሰውየው ግን ምን እየተናገሩ እንደሆን የሚያውቁት አይመስልም። በዚህች በሙት መንፈስ የምትመራ ሃገር ሌላም ብዙ እንግዳ ነገር እንሰማለን። የቡሽ አስተዳደር ከቶኒ ብሌየር ጋር አልቃይዳ የተባለውን አደገኛ ሽብርተኛ ለማጥፋት የነደፉት ይህ ሰነድ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማጥፋት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው የሚነግሩን። የፈረንጆቹ ሽብርተኝነት (terrorism) ሲተረጎም፤ “በሃይማኖት ወይንም በርዕዮተአለም ጥላ ስር ተደራጅቶ አመጽን የማድረግ ተግባር” እንደሆነ ይነግረገናል።
በሽብርተኝነት ተወንጅለው በየእስር ቤቱ የተጣሉት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ የትኛውን ርዕዮተ-አለም ወይንም ሃይማኖት ተንተርሰው አመጽ እንደፈጠሩ፣ የትኛውን አውሮፕላን እንዳስጠለፉ፣ የትኛውን ህንጻ እንዳፈረሱ፣ የትኛውን ንጹህ ዜጋ እንደገደሉ አልተነገረንም።
እርግጥ ነው። የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እየተቹ ይጽፋሉ። ትችቱ ታድያ ለውጡ ላይ አይደለም። የለውጡ አቅጣጫ ላይ እንጂ። አቅጣጫው ትክክለኛ መስመር መያዝ እና አለመያዙን መተቸት “ወንጀል ነው” ሲባል ለቀረው አለም አዲስ ነገር ሊሆን ይችላል። ከዚያ የባሰም አለ። ገዢውን ፓርቲ መተቸት እና ስለ ለውጥ አስፈላጊነት መጻፍ በሽብርተኛነት ያስከሰሰ ወንጀል ሆኖ ሰማን። አስቂኙ ነገር፤ አዋጁ ለኦሳማ ቢን ላደን ሽብር በምእራባውያን ሀገሮች የረቀቀ የጸረ-ሽብር ህግ መሆኑ ነው።
ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ሲፈረጁ ነው ነጻው ፕሬስ በኢትዮጵያ አፈር የለበሰው። ይህ የመጨረሻ ጥይታቸው መሆኑ ነው። አለማቀፍ የጋዜጠኞች ተሟጋች ተቋማት ሳይቀሩ ተስፋ የቆረጡ እስኪመስል ድረድ በዘንድሮ አመታዊ ዘገባቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ ችላ ብለውታል። እነዚህ ተቋማት በየአመቱ ስለኢትዮጵያ ፕሬስ ሁኔታ የሚያወጧቸው ዘገባዎች የሚዘገንኑ ነበሩ። ወያኔን የማይማር፣ የደነዘዘ እና የማይለወጥ ስርዓት አድረገው ስላዩት ችላ ያሉት ይመስላል። ሃያ አመት የማይሰማ፣ ያሃ አመት የማይሻሻል፣ ሃያ አመት የማይማር ስርዓት… ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ሆነባቸው።
በምርጫ 97 ሰሞን በርካታ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ቃሊቲ ተወርውረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዲያሬክተር ከነበሩት ዶ/ር ማርቲን ሂል ጋር ስናወራ አንድ ጥያቄ አነሱልኝ።
“ለመሆኑ ሰርካለም ፋሲል ላይ ለምን እንዲህ ጨከኑባት? ” የሚል ነበር የማርቲን ጥያቄ። እኝህ ታላቅ ሰው ይህን ጥያቄ ለምን እንዳነሱልኝ አሁን ነው የተገለጠልኝ።
የሰርካለም ፋሲልን ጉዳይ ማንሳቱ የኢትዮጵያን ፕሬስ የሰቆቃ ጉዞ በከፊልም ቢሆን ይገልጸዋል።
ሰርካለምን ከባለቤትዋ እስክንድር ነጋ ጋር አፍነው ወደ ቃሊቲ ሲወስዷት ነብሰ-ጡር ነበረች። የመውለጃዋ ቀን ሲደርስም ከእስር አልለቀቅዋትም። በምጥ ስቃይ፣ ነብስ ውጭ፤ነብስ ግቢ ሁኔታ ውስጥ ሆና እንኳን አሳሪዎችዋ ርህራሄ አላሳዩዋትም ነበር። በመጨረሻ እዚያው ቃሊቲ እስር ቤጥ ናፍቆትን ተገላገለች። በዚያ የጭንቅ ወቅት የሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣ ስርዓት ምን እያደረገ እንደነበር እንኳን በውል አየውቀውም። “የመንግስት ጠላት” የሚል ታፔላ ተለጥፎለት የሚንቀሳቀስ ጋዜጠኛ፤ ሊወድቅ ከሚንገዳገድ ስርዓት ከዚህም በላይ ሊደረግበት እንደሚችል ለማስረዳት ሞከርኩ።
ነብሰ-ጡርዋ ሰርካለም የተከሰሰችው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ እና ለማፍረስ፣ ጥላቻን የምታስፋፋ፣ ጥርጣሬን የምትነዛ… ተብላ ነበር። በ “ምህረት” ከእስር እንደተፈታች ወደ ኬንያ ተሰደደች። በኋላም ሀገር ሰላም የሆነ ሲመስላት ከስደት ተመለሰች። ይህች ወጣት እትብትዋ ወደተቀበረባት ሃገርዋ ብትመለስም እንደዜጋ የመኖር ዋስትናዋ ግን በአንባገነኖች መዳፍ ስር ሆነ። በኑሮዋ እና በትዳርዋ ዙርያ ካለፈው የባሰ ችግር መጣባት። ባለቤትዋ እስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት ተከሶ በፍርደ-ገምድል ዳኛ ለአመታት ተፈረደበት። ቤት ንብረታቸውም በግፍ ተቀማ። ከዚህ በኋላ በመኖር እና ባለመኖር የሚደረግ ምርጫ ውስጥ መግባት ግድ ሆነባት። እናም ባለቤትዋን ወህኒ ቤት ጥላ ዳግም ተሰደደች። እስዋም ሆነች በሰቆቃ የተወለደ ልጅዋ በመንገድ ከመወርወራቸው በፊት ያላቸው አማራጭ ይህ ብቻ ነበር። የሚወዷት ሃገራቸውን ጥለው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኛ ጋዜጠኞችን ተቀላቀሉ። እንደቀልድ የሚነገር ሌላም እውነታ አለ። ከ”ሽብርተኛ” ጋር በስልክም ሆነ በአካል ያወራ፣ አብሮ የታየ፣ አብሮ ሻይ የጠጣ፣ የተነካካ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ እንደሆነ አዋጁ ይደነግጋል። ሰርካለም እና ናፍቆት በእስር ያለው እስክንድር ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ሽብርተኛ ተብለው ሊወነጀሉም ይችሉ ነበር።
በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ፍርሃት ውስጥ እንዳሉ ግልጽ ነው። በጋዜጠኛ የሚናድ ሀገ-መንግስት ይዘው ስንት አመት ሊዘልቁ እንደሚችሉ ባናውቅም፤ አሁንም ጋዜጠኞችን ሲያስሩ ይህንንኑ ዘፈን ይደጋግሙታል። 99.7 በመቶ በህዝብ የተመረጠ መንግስት መራጩን ሕዝብ ከቶውንም መፍራት አልነበረበትም። ነገሩ ስላቅ ነው። ይህ ቀልዳቸው ግን የህዝቡን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመጣ ይሁን እንጂ ጉዳዪ ሌላ ነው። አንባገነኑ ናፖሊዮን ቦናፓርት ብሎታል። ከሺ ሳንጃ አንድ ጋዜጠኛ ያስፈራል። የጭቆና እና የአፈና ስርዓት ገንብቶ ለረጅም አመት የቆየ አንባገነን በታሪክ አልታየም።
የፈቀደውን መምረጥ የሚችልን ህዝብ አዲስ ዘመንን ብቻ እንዲያነብ መምከራቸው ብቻ አይደለም በሕዝብ ላይ ያላቸው ንቀት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለበቀል የሚዘረጋ እጃቸው አድርገው ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት ሲጠቀሙበትም እጅግ ያንገበግባል። የህግ የበላይነትን እንዲህ እያደረጉ ናዱት።
ኢሕአዴግ የፕሬስ ነጻነትን ለህዝቡ እንዳጎናጸፈ ይመጻደቃል። ይህ ስህተት ነው። መናገር፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ፣ መጻፍ፣ … ወዘተ መብት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጸጋ እንጂ አንድ ስርዓት የሚያጎናጽፈን ጉዳይ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀው ስርዓት እነዚሁኑ መብቶች እየጨፈለቀ እነሆ ሃያ ሶስት አመታትን ዘልቋል።
ነጻ ፕሬሱን ለምእራባውያን የዲሞክራሲ ማሳያ አድርጎ እንደተጠቀመበት እርግጥ ነው። የአለም ባንክ እና ለጋሽ ሃገሮች በኢትዮጵያ የሳንሱር አዋጅ እንደጠፋ ነው የሚነገራቸው። የእርዳታና ብድር እጃቸውን የሚዘረጉልንም ከቀድሞው የተሻለ የመጻፍና የመናገር ነጻነት አለ ብለው ስለሚያምኑ ይመስላል። ግና ይህ የሳንሱር አዋጅ በአእምሮ ሳንሱር መተካቱን የምናውቀው እኛ ብቻ ነን። ሳንሱር ቢኖር ይህ ሁሉ ጋዜጠኛ ባልታሰረ፣ ባልተንከራተተ እና ባልተሰደደ ነበር።
ምርጫ መጣ! ጋዜጠኛ ይውጣ! እንዲሉ… በቅርቡ በስድስት ነጻ ፕሬስ ህትመቶች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር በተያያዘ አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ለስደት መብቃታቸው ተዘግቧል። በጭላንጭል የነጻነት ድባብ ይንቀሳቀሱ የነበሩት፤ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አፍሮ ታይምስ እና እንቁ ጋዜጦች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ጋዜጠኞቹም በአሸባሪነት ሽፋን ተከስሰው እስከ አስራ ስድስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበይኖባቸው የነእስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙ እጣ ይደርሳቸዋል። እነዚህ ጋዜጠኞች የነበራቸው አማራጭ የሽብር አዋጁ ሰለባ መሆን አልያም አገር ለቀው መሰደድ ነው። ተሰደዱ። የስደተኛ ጋዜጠኛውን ቁጥር ወደ 210 አሳደጉት።
ውንጀላው ግን በተያዘለት መርሃ-ግብር ቀጥሏል። ሰሞኑን “ያልተገሩ ብዕሮች” በሚል ርእስ በኢቲቪ የቀረበውን “ዘጋቢ ፊልም” ያስተውሏል? በአንድ በኩል የጋዜጠኖቹ ጉዳይ በህግ የተያዘ እንደሆነ ይነግሩናል። በሌላ በኩል ደግሞ “ልማታዊ” ተዋንያን እና የስርዓቱ አጎብዳጆችን በመገናኛ ብዙሃን አቅርበው ፍርድ እንዲሰጡ ያደርጓቸዋል። በእርግጥ በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አንድ ተጠርጣሪን በወንጀለኝነት መፈረጅ አዲስ ነገር አይደለም። የፍትህ አካሉ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ተጠርጣሪው በኢቲቪ የፖለቲካ ፍርድ ይበየንበታል። ከዚያም እንደ “ዳኛ” ልዑል አይነት የሲቪል ሰርቪስ ምርቶች ውሳኔውን ያጸኑታል።
በዚያ የኢቲቪ ቅንብር ሃይሌ ገብረስላሴም ተዋንያን ነበር። የሚናገረውም የትዬለሌ። “ትልቁ የጦር መሳርያቸው ፕሬስ ነው።… ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል… ” ይለናል ሃይሌ ገብረስላሴ። “ዘጋቢ” ፊልሙም የእነ እስክንድር ነጋን ፎቶ፣ የእነ ተመስገን ጽሁፎች ያሳየናል። የዚህ ድራማ ሌሎቹ ተዋንያን ከሙያው ጋር የተያያዝን ነን የሚሉ አድርባዮች ናቸው። ሃይሌ ግን ምን ቤት እንደሆነ ግልጽ አይደለም። በየትኛውስ እውቀቱ ነው ፍርድ ሊሰጥ የደፈረው? “አንድ ጋዜጣ የውሃ አምራች ድርጅትን እንዲዘጋ አድርጓል።” ሲል ሃይሌ በዚያ “ዘጋቢ ፊልም” ይወነጅላል። አንድ ጋዜጠኛ እውነትን ጽፎ የንግድ ድርጅትን ወይንም የመንግስት ተቋምን ማፍረስ ወይንም በተቋማቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ከቻለ እንዲያውም ጀግና ነው የሚባለው። ጋዜጠናው የሚጽፈው ውሸት ከሆነ ደግሞ ፍርዱን ለህዝቡ ለምን አይተውለትም?
አብራሃ ደስታ ሌላው በአሸባሪነት ሽፋን የተከሰሰ ጋዜጠኛ ነው። አብርሃ አሸባሪ መሆኑ የተረጋገጠው ፍርድ ቤት ሲገባ እና ሲወጣ ነው። ሲገባ በጭብጨባ ሲወጣ በጭብጨባ ተሸኝቷል። ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ኣብርሃ ጀግና! የነፃነት ታጋይ! እንወዳሃለን፤እናከብርሃለን ሲለው እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ የት ነበሩ?
ያልተገራ አንደበታቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሲከፍቱ የነበሩት እነዚህ ተዋንያን የሚነግሩን እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። አጠቃላይ ይዘቱ በመንግስት ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም የሚል እንድምታ አለው። የህወሃትን አንባገነናዊነት መተቸት፣ የስርዓቱ ፖሊሲዎች መንካትና በባለስልጣናቱ ላይ ጥርጣሪ እንዲኖር ማድረግ… ስርዓቱን ያፈርሰዋል ነው እያሉን ያለው። ህግ አውጭው ከህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ በሌለበት ሃገር ነጻው ፕሬስ ከዚህ ውጭ ምን ይስራ ነው የሚሉት? ፕሮፓጋንዳ?
ለፕሮፓጋንዳውማ በርካታ አማራጮሽ አሉ። አዲስ ዘመን ጋዜጣም አለልን። ለ90 ሚሊዮን ህዝብ የቀረው ጋዜጣ። አዲስ ዘመን በቁጥር ስንት ሺ እንደሚታተም ባናናውቅም በኪሎ እየተሸጠ የሸቀጥ እቃ መጠቅለያ ሆነ እንጂ። ‘የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመረቁ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ሄዱ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ተመለሱ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ 11 እጅ እንደሚያድግ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።’ …. የሚሉ ዘገባዎችን እየያዘ ከሸቀጥ እቃ መጠቅለያነት ውጭ ለሚመጻደቁለት እድገት ምንም እንዳልፈየደ እንኳ አያውቁትም።
የመገናኛ ብዙሃን አፈናው በነጻ ፕሬሱ ላይ ብቻ አልተገደበም። በኢትዮጵያ የመረጃ መረቦችም ታፍነዋል። ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ በኢንተርኔት ይዞታ እና አገልግሎት የመጨረሻዋ ሃገር ናት። ኢንተርኔቱን የሚቆጣጠረው መንግስታዊው ቴሌኮም ስርዓቱን የሚተቹ ድረ-ገጾችን በቻይና ቴክኖሎጂ እንዲዘጉ አድርጓል። የዜጎችን ስልክ በህገወጥ ማንገድ መጥለፍ የተለመደ ተግባር ነው። እንዲሁም ስካይፕ እና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ። እንዲህ እያሉ በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም እንዳደረጉት የአሜሪካው ሂዩማን ራይትስ ዋች ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያን ወደ ጨለማ ዘመን እየወሰዳት ያለው ይህ የህወሃት ስርዓት የኢንተርኔት ተጠቃሚው እንዲያሽቆለቁል እየጣረ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። በተለይ የፌስቡክ አብዮትን ለመግታት ስለሚሻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማዳከሙ ላይ ጥብቅ አቋም ይዟል። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣ ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት። በዚህ ቀላል ቴክኖሎጂ እንኳን ከሶማልያ በታች ሆኖ ስለ እድገት መመጻደቃቸው ሊያፍሩበት ይገባል።
እጅግ የሚያሳዝነው ይህ ስርዓት ለፈጸመው ለዚህ ሁሉ በደል ለሽልማት መብቃቱ ነው። ልማታዊው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በአርቲስቶች ስም ለሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር የወርቅ ብዕር ነበር ያበረከተላቸው። ብዕር ትልቅ ትርጉም አለው። ብእር የሚሸለም ሰው ለፕሬስ ክብር ያለው፤ ፕሬስን የሚያከብር ሰው ነው። ሰራዊት የወርቅ ብዕር እንዲሸልም አርቲስቶች አልወከሉትም ነበር። ይህንን ሲያደርግ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እስር ቤት ውስጥ ይንገላቱ ነበር። ሰራዊት ይህንን ሲያደርግ የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ጠ/ሚኒስትሩን የፕሬስ አፈና በእጅጉ ያወግዝ ነበር። እንደ ሰራዊት ያሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ብዙ አይደሉም። ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ሲሉ እንዲህ አይነት ስራ እየሰሩ በሰው በቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳሉ። ታዲያ እንደነዚህ አይነቶቹ አድርባዮችም ለፕሬሱ መጥፋት ሚናቸው ቀላል አይደለም። የማያልፍ የለም። ሁሉም ያልፋል። መንግስትም እንደ አንሶላ ተጠቅልሎ ይሄዳል። ይህ ቀን አልፎም ለትዝብት ያበቃናል።
ማን ነበር “ፕሬስ የሌለው መንግስት ከሚኖረን መንግስት የሌለው ፕሬስ ቢኖረን እንመርጣለን።” ያለው? እርግጥ ነው። ያለ ፕሬስ የሚኖር ህዝብ በጨለማ ነው የሚጓዘው። ያለ ነጻ አስተሳሰብ እና ያለ ነጻ ፕሬስ፣ እድገት ይመጣል ማለት አይታሰብም። እንዲያው የህዝብን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ መመልከት ይሆናል እንጂ።
ኢቦላና የሙከራ ሕክምናና ክትባቶች
መላውን ዓለም እያሳሰቡና ያንኑም ያህል እያነጋገሩ ካሉ ሰሞንኛ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ ነው።
የኢቦላ ወረርሽኝና የሕክምና ጥረቶች፥ ይልቁንም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በዩናይትድ ስቴትስ የታዩ ሁኔታዎች ይዳስሳል።
በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው የኢቦላ ታማሚ የሆኑትን የላይቤሪያዊውን የMr Thomas Eric Duncan’ን በትላንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ተከትሎ ለህልፈታቸው ምክኒያት የሆኑት ጉዳዮች እያነጋገሩ ነው።
ከኢቦላ ቫይረስ ጠባይ፤ በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተባቸው የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ውጭ የመዛመት ሁኔታ፤ እስከ መከላከያና የሕክም ጥረቶቹ ድረስ የወረርሽኙን ሁለንተናዊ ገጽታዎች ከሚዳስሱት ተከታታይ ቅንብሮች፤ በተለይ ሙከራ ሕክምና ጥረቶቹ ላይ ያተኮሩትን ከዚህ ያድምጡ፤
መንግስት የባንዲራ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ጀምሯል።
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከሚፈስባቸው የመንግስት ክብረ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የባንዲራ ቀን ዘንድሮም ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓም በአዲስአበባ ስታዲየም በድምቀት እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል። “በሕዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯን እና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር!” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ጊዜ …
በአዋሳ አንድ ባለሀብት ጠበቃ ገድለው ተሰወሩ
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ …
በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች በመሰረተ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኋላ መቅረታቸውን የወረዳ አመራሮች በግልጽ በማቅረባቸው ከክልልና ዞን ባለስልጣናት ግሳጼ እንደደረሰባቸው ተናገሩ፡፡
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ህብረተሰቡ ምን ይለናል የሚለውን ለማዳማጥ ከሰሜን ጎንደር ከተሰባሰቡ የወረዳ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ የወረዳ አመራሮች በንባብ እንዲያሰሙት ከየዞን ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ማስታወሻና አቅጣጫ ወደጎን በመተው መንግስት እንዲያስተካክላቸው በጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ምክንያት ከስብሰባው በኋላ ወከባና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦክተውበር 09, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ወቀሣ፣
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ፣ ከተቀናቃኙና ተፋላሚው ኃይል ጋር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርድ ፤ በኢጋድ ሸምጋይነት የሰላም ውይይት በመካሄድ ላይ ቢሆንም፣ የመንግሥት ለውጥ እንዲደረግ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያና ኖርዌይ የሚያደርጉትን ጉትጎታ ዋናው ሸምጋይ
በሶስት የግል መፅሔቶች ላይ የተላለፈው ብይን እና ውግዘቱ
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በሶስት የግል መጽሄቶች ባለቤቶች ላይ በሌሉበት ውሳኔ ማሳለፉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል። እንደዘገባዉ ፍርድ ቤቱ መጽሔቶቹ ሎሚ፤ አዲስ ጉዳይ እና ፋክት የተሰኙት ሲሆኑ ውሳኔው በአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ጀርመን አፍሪቃዊትዋ የምዕተ ዓመቱ የታሪክ መስካሪ
የ 90 ዓመትዋ ደራሲ ሩት ቫይስ እትብታቸዉ የተቀበረበት ሀገረ ጀርመንን የሚያዉቁት እጅግ በጥቂቱ ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ ግን አዛዉንቷ በሥነ-ጽሑፍ ስራቸዉ እጅግ ታዋቂና የተከበሩ ናቸዉ፤ ምናልባትም ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሩት እጅግ ታዋቂዋና ብቸኛዋ የጀርመናዊት ጋዜጠኛ ናቸዉ ማለትም ይቻላል።
የኢትዮጵያ ኤኮኖሚና የ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዘገባ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት « አይ ኤም ኤፍ» የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአሁኑ 2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት አድጓል ሲል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ እና የዓ/አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዘገባ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት « አይ ኤም ኤፍ» የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአሁኑ 2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት አድጓል ሲል አስታወቀ። ይኸው የኤኮኖሚ ዕድገት በዋናነት በከፍተኛ የግብርና ምርት፤ በመንግሥትና በውጭ መዋዕለ ንዋይ የታገዘ መሆኑን የተቋሙ
ስጋት ያጠላበት የየመን የፀጥታ ይዞታ
በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በዛሬዉ ዕለት በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና ከ70 በላይም መጎዳታቸዉን የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የጠቀሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ኤቦላን ለመታገል ተፈላጊው ዓለም አቀፍ ትብብር፣
ከላይቤሪያ የተመለሰው አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመምተኛ ቶማስ ኤሪክ ዳንከን ትናንት በዳላስ ቴክስስ ካረፈ ወዲህ ይህን አደጋና በሽታ ለመታገልና ለመግታት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያሻ በመነገር ላይ ነው።
ኢህአፓን አንድ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቋመ
Read here. iframe
ኢትዮጵያዊያኑ ደጋፊና ተቃዋሚ ሠልፈኞች ብዛታቸው እንዲስተካከል ቪኦኤን ጠየቁ – ኦክተውበር 08, 2014
Ethiopians supporter and opposition demonstrations 10-18-14
“ሰራዊታችን ህብረብሄር ሆኗል” ሲል ኢህአዴግ ገለጸ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ” በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት …
ነዋሪዎች የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት ተቃወሙ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በአዲስአበባ ባለፈው ዓመት 22ሺ ያህል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 22ሺ ያህል ቤቶች ቀደም ሲል ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች …
ማህበረ-ቅዱሳን አደጋ አንዣቦበታል።
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››ሲሉ የኢትዮፐያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተናሩ። ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህን ያሉት ፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት …
በአማራ ክልል የተደራጁ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት መክሰራቸውን አስታወቁ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተው ፤በየቀኑ ላባቸውን እያፈሰሱ የሚደክሙ የድሃ ድሃ እናቶች እለቅሶ ርቆ እየተሰማ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ነጋዴዎችን አነጋግራ የሰራቸው ዘገባ ያመለክታል 33 በእድሜ የገፉ እናቶች ” በመንግስት ሌቦች ተዘርፈናል ሲሉ ” እያለቀሱ ብሶታቸውን ገልጸዋል። በአማራ ክልል በስራ አጥ እና የድሃ ድሃ ከተደራጁ 31 ሺ 549 ማህበራት …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦክተውበር 08, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የኡሁሩ ኬንያታ በ«አይ ሲ ሲ» መቅረብ
የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።
ፀረ ሰብል መርዛማ ንጥረ ነገርን የተመለከተ ምክክር
ሰብል በመስክ ላይ እያለ ወይም በሚደርቅበት፣ በሚከማችበት ወይም በሚጓጓዝበት ጊዜ በሚፈጠር ሻጋታ ውስጥ የሚገኘው አፍላቶክሲን የሚባለውን መርዛማ ንጥረ ነገር በአፍሪቃ በቆሎን እና ለውዝን የመሳሰሉ የግብርና
የኡሁሩ ኬንያታ «አይ ሲ ሲ» መቅረብ
የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።
በሳይንስ የዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚዎች
ከሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ወደ ደቡብ እስከ ምድር ሰቅ የሚዘልቁና ወደመጡበት ሳይደናገሩ የሚመለሱ አእዋፍ ምንቃራቸው አጠገብ በቀኝ በኩል አቅጣጫ አመላካች የተፈጥሮ «ኮምፓስ» አላቸው። የሌሊት አእዋፍ ፣ ዓይን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ አቅጣጫ ጠቋሚ አላቸው።
አሳሳቢው የኤቦላ ወረርሽኝ እና ማከላከያው ጥንቃቄ
በምዕራብ አፍሪቃ ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በተከሰተው እና በዓለም እስከዛሬ አስከፊ መሆኑ በተነገረለት የኤቦላ ወረርሽኝ የ3,431 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱን፣እንዲሁም፣ በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴየራ ልዮን ወደ 7,470 ሰዎች ደግሞ በኤቦላ አስተላላፊ ተሀዋሲ መያዛቸውን የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አስታውቋል።
የሶማሊያ ጦር ግሥጋሤና የአሸባብ እጣ
የሶማልያ ብሄራዊ ጦርና የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል ‘አሚሶም’ከአሸባብ አክራሪ ኃይል ጠንካራ ይዞታዎች መካከል አንዷ ነች የተባለችውን የባራዌ የወደብ ከተማ ከቀናት በፊት ነፃ አዉጥተዋል። ለበርካታ ዓመታት ከሶማልያ ማዕከላዊ መንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆና የቆየችው የባራዌ ከተማ ለአሸባብ ዋንኛ የገቢ ምንጭም ነበረች።
አርሴማ
|
ዐጽሟ ያረፈበት አርመን የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን
|
![]() |
|
በመቃብሯ ላይ የሚገኘው ሥዕል
|
ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም አሜን በኤፍሬም ማዴቦ
ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ […]
በዋሽንግተን ዲሲ ጥቂት የወያኔ ኢምባሲ ሠራተኞች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በየፊናቸው ሰልፍ ወጡ!! – (ዘ-ሐበሻ)
ጥቂት የሕወሓት የዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ሠራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ በሚሰጣቸው የስኮላርሺፕ ገንዘብ የደለቡ የስርዓቱ ደጋፊዎች በሰለሞን ተካልኝ መሪነት በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ ዛሬ ሰልፍ ወጡ። በተመሳሳይም የአሜሪካ መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት ኢምባሲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰውን የስርዓቱን ተላላኪ ከሃገሩ በማባረሩ ለዚህም ምስጋና ለማቅረብ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመንት ተመሳሳይ ሰልፍ አድርገዋል። ሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን […]
የአቶ ፈቃዱ ደሪሎ አጭር የሕይዎት ታሪክ
አቶ ፈቃዱ ደሪሎ ከአባቱ ከአቶ ደሪሎ ተክለማሪያምና ከናቱ ከወ/ሮ ጥሩነሽ ደረሳ መስከረም 6 ቀን 1948 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ።
አቶ ፈቃዱ በበረራ መሐንዲስነት ከ20 ዓመታት በላይ እጅግ የላቀ የሥራ ልምድ ነበረዉ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በ1964-65 ዓ/ም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተግባረዕድ ት/ቤት ገባ። የሙያ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በሰኔ 15 ቀን 1965 ዓ/ም ዝነኛ በነበረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀጠረ። የበረራ ፈቃድ በመያዝ በቦዪንግ 707/720 እና 727/737/767 ((Boeing 707/720 b/727/737/767) ላይ አገለገለ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉስጥ በመሥራቱ ወደ ተለያዩ የአዉሮፓ፤ ኢስያ፤ ኩባና አፍሪቃ አገሮች የመዘዋወርና የመሥራት ዕድል አገኘ። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እድሜ ልኩን እጅግ የሚወዳቸዉን ጓደኞች አተረፈለት።
በ1985 ዓ/ም ሂትሮ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ለቦዪንግ 76 ጥገና በመመደብ በሎንዶን ከተማ እስከ 1990 ዓ/ም ድረስ ሠራ። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በርክሼር ዉስጥ ላነግሌይ በሚባል ቦታ ከኖረ በኋላ በ1989 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከተማ ከቤተሰቡ ጋር በመዞር በምሥራቅ አክቶን ተቀመጠ። በነዚህ ዘመናት ከርሱ ጋር ያሳለፉትን ደስታ ቤተሰቦቹና ኋደኞቹ እስካሁን ያስታዉሳሉ።
ለተለያዩ ኩባኒያዎች የሠራ ሲሆን በመጨረሻ የሠራዉ ለኤየርክራፍት ሴርቪስ ኢንተርናሺናል ግሩፕ (Aircraft Service International Group) ነበር።
አቶ ፈቃዱ ከወ/ሮ አይናለም በሻህ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የተጋባዉ በ1974 ዓ/ም ነበር። በ1985 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከመላኩ በፊት ኑሮዉም ሥራዉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቤተሰቦቹ መጥተዉ ተቀላቀሉት።
አቶ ፈቃዱ ተወልዶ ያደገዉ ጠንካራ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሆኑት ቤተሰቦች መሃል ነዉ፤ ይሄም ለመልካም የዕድገት ደረጃና ጠንካራ አምልኮት አድርሶታል። በየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ በሄደ ቁጥር ቤተሰቦቹንና ኋደኞቹን ከማየቱ በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀሎት ያደርስ ነበር። ጊዜዉን በደስታ የሚያሳልፈዉ ከቤተሰቦቹ ጋር እቤት ዉስጥ በመሆን ነዉ፤ ሰፖርት ፕሮግራሞችን ይመለከታል፤ የተሌቪዥን ጥያቄዎች ይከታተላል፤ የበረራ መጻሕፍትን ያነባል፤ መኪናዉን ያጥባል፤ ይጠግናል።
መልካም ባል፤ ጥሩ አባትና ቆራጥ አያት ነበረ። ቅርቡ የሆኑት የሥራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ ዝምተኛነቱንና ተቖርቋሪነቱን ይመሰክራሉ።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ አቶ ፈቃዱ በሰላም በተኛበት ቦታ በ65 ዓመቱ ማክሰኞ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዐለም በሞት ተለየ፤ ሞቱም በተፈጥሮ ምክንያት መሆኑ በአጣሪዎቹ ኮሮኔሮች ተረጋግጧል።
ቤተሰቦቹም የሚከተሉት ናቸዉ፤ ባለቤቱ ወ/ሮ ዓይናለም፤ ሁለት ልጆቹ ዮናስና እዮብ፤ የልጅ ልጆቹ፤ ረዲኤት፤ አቤልና ሲሳይ ሲሆኑ 6 ወንድሞቹና እህቱ ግርማ፤ ሙሉ፤ ታምሩ፤ ታደለ፤ ብርሃኑና አክሊሉ ናቸዉ።
ቸሩ አምላካችን ነፍሱን በመንግሥተ ሰማያት ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቹና ወገኖቹ በሙሉ ጽናቱን ይስጥልን አሜን።
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በሦሥት አሳታሚ ድርድቶች ኃላፊዎች ላይ የእስራት ቅጣት በየነ
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በሦስት አሳታሚ ድርጅቶች መሪዎች ላይ የእስራት ፍርድ በየነ።
የፌዴራል አቃቤ ሕግ ዩፋ ኢንተርቴይንመንትና የፕሬስ ሥራዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ዳዲሞስ ኢንተርቴይንመንትና ሮዝ አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተሰኙ ድርጅቶችና በዋና ስራ አስኪያጆቻቸው ፋጡማ ኑርዬ፣ አቶ ግዛዉ ታዬ ኦርዶፋና አቶ እንዳልካቸዉ አድጉ ላይ ባቀረበዉ ክስ መሰረት፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት “ጥፋተኛ” ናቸው ሲል ወስኖባቸዋል። ሶስቱም ተከሳሾች ቀደም ብሎ አገር ጥለው የኮበለሉ ሲሆን፤ የእስራት ቅጣቱ የተፈረደባቸው በሌሉበት ነው።
ዛሬ በዋለዉ ችሎት ፍርድ ቤቱ በእያንዳንዳንዱ ተከሳሽ ላይ ከ3 አመት ከ3 ወራት እስከ 3 ዓመት ከ11 ወራት የሚደርስ እስራት ፈርዷል።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የዳዲሞስ…
የቦስተኑ ሮቤል ፊሊጶስ የችሎት ውሎ
የቦስተን ማራቶኑ የቦምብ ጥቃት አድራሾች ጓደኛ ትውልደ ኢትዮጵያ ሮቤል ፊሊጶስ አደጋው በተጣለ ሰሞን ስለነበረው ሁኔታ አንዱን ቅዳሜ ሙሉ ዕፀ-ፋሪስ ሲያጤስ ስለዋለ አደንዛዡ ዕፅ ባደረሰበት የማስታወስ ችሎታ መታወክ ምክንያት በዕለቱ ምን እንደተፈፀመ ማስታወስ አልቻለም እንጂ የዋሸው አንዳች ነገር የለም ሲሉ ጠበቆቹ ለፍርድ ቤት መከራከሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የሮቤልን ጉዳይ የተመለከተው የቦስተን ችሎት የተሰየመው – ሰኞ ትናንት ነበር፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የቦስተኑ ሮቤል ፊሊጶስ የችሎት ውሎ – ኦክተውበር 07, 2014
Robel Philipos, Court
በአሣታሚዎች ላይ ፍርድ ተሰጠ – ኦክተውበር 07, 2014
Ethiopia, Publishers sentenced
ደጋፊና ተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰልፍ ወጡ – ኦክተውበር 07, 2014
Ethiopians – demonstration in front of State Department
ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ የኢቦላ ምርመራ ልታደርግ ነው – ኦክተውበር 07, 2014
Additional US ebola screening measures
በአሜሪካ ሁለት የተለያዩ ተቃውሞች ተካሄዱ
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሞ ለማሰማት በሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው ሰለሞን ገብረስላሴ፣ በ48 ሰአታት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በሁዋላ የመንግስት ደጋፊዎች የአሜሪካን እርምጃ ለመቃወም የጠሩትን ተቃውሞ ለማክሸፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተመሳሳይ ተቃውሞ አዘጋጅተዋል። የመንግስት ደጋፊዎች አሜሪካ ለኢምባሲው በቂ ጥበቃ አላደረገችም በሚል ሲቃወሙ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች …
አቶ በረከት ስምኦን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችን ማሰልጠናቸውን ቀጥለዋል
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው አገሪቱ ለሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለኢህአዴግ አባላት የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና የዩኒቨርስቲ መምህራንም እንዲወስዱ በመገደዳቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን በቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር እና በአሁኑ የጠ/ሚ የፖሊሲ አማካሪ በአቶ በረከት ስምኦን እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው። ስልጠናውን የሚወስዱት በታሪክ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣ በሶሺኦሎጂ፣ በጆግራፊ፣ በፊዚክስ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች …
የመካከለኛው ምስራቅ እና የምእራብ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖታዊ ሽኩቻ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ተችሎአል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ስልጠና በመውሰድ ላይ ላሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው። አቶ በረከት በምእራባውያን እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ገንዘብ በሃይማኖት ስም የፖለቲካ አላማ ለማራመድ በሚል ወጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ትርምስ እንዲፈጠር ይፈልጋሉ ያሉዋቸውን …
የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተመራቂ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው ዲን በደመወዝ ከፍያ ምክንያት ባለመግባባታቸው ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኙ ምንጮች አመለከቱ፡፡
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው እስከ 200 የሚደርሱ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎች በመመረቂያ አመታቸው ላይ እንዳሉ ሲመረቁ የሚከፈላቸውን የደመወዝ ግማሽ የሚከፈላቸው ሲሆን የውዝግቡ ዋነኛ ምክንያት የሚከፈላቸው ግማሽ ክፍያ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መሰረት አለመሆኑ ነው፡፡ የህክምና ተማሪዎቹ ለአካባቢው አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው የፓለቲካ አመራሮቹ “ቅሬታችሁ ተገቢ ነው” የሚል መልስ ቢሰጡዋቸውም የዩኒቨርስቲው ዲን ተማሪዎቹን …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦክተውበር 07, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በደቡብ ጀርመን የሚገኙ ስደተኞች እጣ
በሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየሳምንቱ በሊቢያ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ። የአንዳንዶቹ እጣ ፋንታ በሜዲትሪያን ባህር ሰምጦ መሞት ሲሆን በህይወት የተረፉት ደግሞ በስፓኝ፣ በማልታ፣ በግሪክ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በኢጣሊያ አድርገው ወደሰሜን አውሮፓ ለመግባት ይሞክራሉ።


