ወባ ዛሬም ገዳይ በሽታ ነዉ በተለይ በአፍሪቃ። በበሽታዉ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቁት ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች መሆናቸዉን የህክምና ባለሙያዎች ያመለክታሉ። በወባ በሽታ በዓለማችን በየዓመቱ ከሚያልቀዉ ህዝብ ቁጥር 80 በመቶዉ የሚገኘዉ አፍሪቃ ነዉ።

በቅርብ ጊዜ የአውሮፓ የጀልባ ስደተኞች ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ነው ። ባለፈው ሃሙስ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በእሳት ከተያያዘች በኋላ ሰጥማ የደረሰው አደጋ ። እንደ እድል ሆኖ 155ቱ ቢተርፉም የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 274 ከፍ ብሏል ።

የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልከፋበትም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አለ በቂ ምክንያት ሰዎችን እንዳያስቀይም ወይም ለማስደሰት ብቻ አለ በቂ ምክንያት እንዳያስደስት በማደርገው ሀበሻዊ ይሉኝታ አዘል ጥንቃቄ ወረቀት ላይ የሚቀመጠው ነገር አንዳንዴ ለራሴም ስሜት አልባ የሚሆንብኝ አጋጣሚ አለ – ይህንን ስል ግን ተናድጄ የምጽፈው ሁሉ ቱሪናፋ ነው ማለቴ እንዳልሆነ ግንዛቤ እንድትወስዱ […]

‹ዛሬ በናትሽ ዳጎስ ያለ ሰነድ ወይም መጽሐፍ ወይም ዶሴ መብላት አማረኝ›› አለች አንዲት ነጭ አይጥ ለጓደኛዋ፡፡
‹‹ለምን አንዱ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አልወስድሽም›› አለቻት ጥቁሯ አይጥ፡፡

‹‹እኔን ለማስደብደብ ነው እንዴ ፍላጎትሽ›› አለቻት ነጯ

‹‹ማነው ደግሞ የሚደበድብሽ››

‹‹ሠራተኞቹ ናቸዋ››

‹‹ስለ ሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አታውቂም ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥኮ አንድ ነገር የሕዝብ ነው ከተባለ ሁለት ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ወይ የማንም አይደለም፤ ወይም የጥቂቶች ብቻ ነው፡፡ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ማለት የማንም ያልሆነ ቤተ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡ በጀት የለው፤ ተቆጣጣሪ የለው፤ ባለቤት የለው፡፡ ማዘጋጃ ቤት የባህል ቢሮ ነው ይለዋል፤ የባህል ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው ይለዋል፤ ኮሙኒኬሽን ጽ/ ቤት የወጣቶች ሊግ ነው ይለዋል፤ የወጣቶች ሊግ የሕዝብ ነው ይለዋል፡፡ ስንትና ስንት የጥንት መጽሐፍ ባለቤት ስላጣ ማንም ዘወር ብሎ አያየውም፡፡ ይልቅ ተነሽ እንሂድ››

ተያይዘው ሄዱ፡፡ ገቡ፡፡ አንድ አስነባቢ ገቢያቸውን ለብሰው ጠረጲዛ ላይ ክንዳቸውን ተንተርሰው ሸለብ አድርገዋል፡፡ አይጦቹ በበሩ ሲገቡ እንኳን አላዩዋቸውም፡፡

‹‹ያንን መጽሐፍ አውርጂው›› አለቻት ጥቁሯ፡፡ ነጯ አይጥ ሄደችና አወረደችው፡፡ ዳስ ካፒታል የሚለው የማርክስ መጽሐፍ ነው፡፡ ‹‹ለእኔ ደግሞ እዚያ ማዶ ያለውን አምጭልኝ›› አለቻት፡፡ ኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ነው፡፡ ሁለቱም ተቀምጠው መቆርጠም ጀመሩ፡፡

አስነባቢው የሆነ ድምጽ ስለሰሙ ቀና አሉና መልሰው ተኙ፡፡

‹‹እንዴ በሙሉ የድሮ መጽሐፍ ብቻ ነው እንዴ›› አለች ነጯ አይጥ፡፡

‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡፡ አታይም ሠላሳ ሺ ሕዝብ የሚይዝ ኮንዶሚንየም ሲገነባ በግ ማረጃ እንጂ ቤተ መጻሕፍት ተገንብቷል? ለመጠጥ ቤት፣ ለጫት ቤት፣ የሚሆን ቦታ ግን ሕንጻዎቹ ሥር ተሠርቷል፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቹ በየቢሮው ያሉት ከዕውቀት የጸዱ፣ ከሆድ የተዛመዱ ናቸዋ፡፡ ያለ አእምሮ ልማት ቁሳዊ ልማት ከየት ይመጣል፡፡ መገንባት ብቻውን አያለማምኮ፡፡ የገነባሽውን በሚገባ የሚጠቀም፣ የሚከባከብ፣ እድሜውን የሚያረዝም፣ እሴት የሚጨምርም ዜጋ ያስፈልጋል፡፡ በጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው፡፡ ከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤  ኪነ ጥበብ ከማይበረታቱ ኢንዱስትሪዎች መደብ በተመደበባት ሀገር ምን ትጠብቂያለሽ›› አለች ጥቁሯ፡፡

‹‹ባለፈው አንዲት ጓደኛዬን ለአዲስ ዓመት ወጣ ብለን እንዝናና ስላት የት እንደወሰደችኝ ታውቂያለሽ››

‹‹ዱከም ወስዳ ሥጋ ጋበዘችሽ››

‹‹ኧረ አይደለም፤ አቃቂ››

‹‹አቃቂ ደግሞ ምን አለ?››

‹‹ድሮ በደርግ ጊዜ ኩራዝ አሳታሚ እያለ ሊታተሙ የተሰበሰቡ ረቂቆች አሉ ብላ ይዛኝ ሄደች፡፡ አንድ ትልቅ የቆርቆሮ መጋዘን ውስጥ ተከምረውልሻል፡፡ እዚያ ይዛኝ ገባች፡፡ እዚህ ሀገር የታወቁ ደራስያንን ሥራ ስንከሰክስ ስንከሰክስ ዋልንልሽ፡፡ አንዳንዱ ታርሟል፤ አንዳንዱ አልፏል የሚል ተጽፎበታል፡፡ አንዳንዱ ማኅተም አለው፡፡

‹‹ዝም አሏችሁ››

‹‹ማንም ዝር አይልም ከአይጥ በቀር አሉ የለመዱትማ ሲነግሩን››

‹‹ወይ ይህቺ ሀገር፣ ከገዛ ታሪኳና ቅርሷ፣ ከገዛ መዛግብቷና ሰነዶቿ ጋር የምትጣላ ሀገር፡፡ ባለፈው የባድሜ  ጉዳይ በዓለም ፍርድ ቤት ሲዳኝ አንዱ የተጠየቅነው ሰነድ ነበር አሉ፡፡ የተቆረጠ ደረሰኝ፣ የተሰጠ ሹመት፣ ከዚያ አካባቢ የተጻፈ ነገር፣ የሐኪም ቤት ካርድ፣ ያ ቦታ የኢትዮጵያን እንደነበረ የሚያሳይ ዶሴ አምጡ ተብሎ ነበር አሉ፡፡ እዚህ ሀገርኮ ስንቱ ፋይል፣ ስንቱ ዶክመንት፣ ስንቱ ደብዳቤ፣ ስንቱ መረጃ አሮጌ ነው እየተባለ ተጥሎ በየቆርቆሮው ቤት ታሽጎበታል መሰለሽ፡፡ ለኛማ ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ እርሱን እየበላን እንኖራለን፡፡ ሀገሪቱ ግን ታሳዝናለች፡፡››

‹‹ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት የሚባል ድርጅት አለ አይደል እንዴ››

‹‹አንድ ለእናቱ የሆነውን ነው የምትይኝ? ይኼው ሰማንያ ዓመት ሆኖታል አንድ ለእናቱ ነው፡፡ እስኪ ክልል ውረጅ አንድ የመዛግብት ማዕከል ታገኛለሽ? በተለይማ ባለፉት ሥርዓቶች የነበሩ መዛግብት የጠላት ገንዘብ ተደርገው የማንም መጫወቻ ሆነዋል፡፡ ወይ ቆርቆሮ ቤት ገብተዋል፤ ወይ ተቃጥለዋል፤ ያለበለዚያም በኪሎ ተሸጠዋል፡፡››

‹‹ይበላቸው እባክሽ፤ እነርሱ በዘመናቸው እኛ ድርሽ እንዳንል ድመት ለሚያረባ ሰው የድመት መሬት እየሰጡ አሳድደውናል፡፡ይኼው ዛሬ የሀብታም መሬት እንጂ የድመት መሬት የለ፡፡እንደልባችን ታሪክ ስንበላ እንውላለን፡፡››

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ በሽታ መቼ ተከሰተ፣ የት የት ቦታ ተከሰተ፣ ምን ያህል ሕዝብ ተያዘ፣ ምን ተደረገ፣ መቼ ጠፋ? ብለሽ ብትጠይቂ መልሱ ያለው የት እንደሆነ ታውቂያለሽ?››

‹‹ጤና ጥበቃ ነዋ››

‹‹ተሳስተሻል፡፡ እኛ ሆድ ውስጥ ነው፡፡ የሆስፒታል የድሮ ካርዶችኮ እንድንበላቸው ተፈቅደውልን የተከፋፈተ መጋዘን ውስጥ ተጥለዋል፡፡ እንደ ጓያ ነቃይ የዛሬን እንጂ የነገን የሚያስብ የለም፡፡ አሁንኮ ሀገሪቱ ስላደገች የወዳደቀ ትራፊ ሳይሆን አልፎልን ታሪክና መረጃ ነው የምንበላው፡፡ አንዳንድ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን አሉ ጋዜጠኞች፡፡ የሚደርሰውኮ ወደኛ ነው፡፡›› 

‹‹አንድ ነገር አስታወስሽኝ፡፡ ከሆነ ዓመት በፊት አንድ ትልቅ ባለ ሥልጣን የተናገረው ነገር፡፡ ኢሕአዴግ ባሕርዳር ሲገባ እነርሱ የኢሠፓ ጽ/ቤት ነበር ያደሩት፡፡ ብርድ ስለነበር ሌሊቱን ፋይል እያነደዱ ሲሞቁ፡፡ በመካከል የአንድ ደራሲን ልቦለድ አግኝቶ እንዳነበበውና አዲስ አበባ ፈልጎ እንደሰጠው ሲናገር ነበር፡፡ አሁን ሰነድ ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው?ሰዎቹ ናቸው እንጂ ኢሠፓ ፋይሉኮ ኢሠፓ አይደለም፡፡ ፋይሉማ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡››

‹‹የኢትዮጵያን ዕቃ ገዥ ከሌላው ዓለም ገዥ የሚለየው አንዱ ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?››

‹‹አላውቅም››

‹‹ሌላው በተራ ወረቀትና ፌስታል ዕቃውን ይጠቀልላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በታሪካቸው ስለሚኮሩ በታሪካዊ መዛግብትና ሰነዶች፣ በታሪካዊ ደብዳቤዎችና ፋይሎች ዕቃቸውን ይጠቀልላሉ፡፡ በየሱቁ ከምትገዥው ስኳር በላይ ባለ ሱቁ የጠቀለለበት ፋይል ዋጋው ውድ ነው፡፡

‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››

ቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡

‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡

‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡

ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም

ታሪክ እንበላለን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልጠላውም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አመዛዛኝ ይሆንና ሁሉንም አለ በቂ ምክንያት ላለማስቀየም ወይም አለ በቂ ምክንያት ላለማስደሰት በማደርገው ጥረት ወይም ጥንቃቄ የምጽፈው ነገር ለራሴም ስሜት ያጣብኛል፡፡ ተናድጄ ስጽፍ ግን ስሜቴን እንደወረደ ወረቀት ላይ አየዋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – ተናድዶ መጻፍ ‹ሪስክ› አለው፡፡ ሰዎችን ልታስቆጣ ትችላለህ፡፡ በሌላም በኩል […]

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሦስተኛው  የ ኢህአዴግ ፕሬዚዳንት በመሆን በ አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ምትክ ተሾሙ። የኢህአዴግ/ኦህዴድ አባል የሆኑት  ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን በመተካት ሁለተኛው ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ በስፋት የተወራ ቢሆንም፤”ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚመረጠው ሰው የማናቸውም ፓርቲ አባል ያልሆነ ገለልተኛ ሰው መሆን …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በክልሉ ከመልካም አስተዳደር እና ከሰዎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የሚታየው ችግር እየተባባሰ በሚገኝበት ሁኔታ የክልሉን ባለስልጣናት ለመምረጥ በአዋሽ አርባ ታንከኛ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄ ነው። ከፍተኛ የህወሀት ድጋፍ አላቸው የሚባሉት የአቶ እስማኤል አሊሴሮ ደጋፊዎች በአንድ በኩል ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሰዎች በሌላ በኩል ሆነው በስብሰባው …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በ2006 ዓም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፣ ሽብርተኝነት እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ትምህርት ለመስጠት የጀመረውን እቅድ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀምሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር። …

 መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢሳት እንደገለጹት በክልል ከተሞች ስኳርን በቀበሌዎች ለማከፋፈል የተደረገው ሙከራ  በአላመስራቱ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ለልጆቻችን ሻሂ እና ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን ማዘጋጀት አልቻልንም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ቀደም ብሎ በቀበሌ በኪሎ 15 ብር ይሸጥ የነበረውን ስኳር፣ በ30 ብር ማግኘት እየተሳናቸው መምጣቱን ተናግረዋል። መንግስት  ላለፉት 2 አመታት ዘይትና ስኳር …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለማቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ማህበር ባወጣው መረጃ በአለም ካሉ አገራት ጊኒ ቢሳው፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማእከላዊ አፍሪካና ኒጀር የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በተቀራኒው ደቡብ ኮሪያ፣ ስዊድን፣ አይስላንድ፣ ዴን ማርክ፣ ፊንላንድ ፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድስ እንግሊዝና ሆንግ ኮንግ ከ አንድ እሰከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን …

በግብጹ ካይሮ ዩኒቨሲቲ የኢንጂኔሪንግ ፋከልቲ የመስኖና የሀይድሮሊክስ ክፍል ፕሮፌሰሮች “The Group of the Nile Basin”የሚል ቡድን መስርተው በታላውቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የሀገራቸውን መንግስት በማማከር ለመርዳት ተነሳሱ።

አኤአ ጥቅምት 5 የተዋቂው አይርላንድዊ ሙዚቀኛ Bob Geldof የተወለደበት ቀን ስለሆን በዛሬው ፕሮግራም የእሱን ዜማዎች እና ሌሎች ዜማዎችን ከሙዚቃ ነክ ዜናዎችን ጋር ያስተናግዳል፡፡

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌደሬሽን ም/ቤት በዛሬው ዕለት ፣ አዲስ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት መርጠዋል። የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት፤ ቃለ መሃላ መፈጸማቸውንም፣

ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት እሳቸዉም ሆኑ ዛሬ የአስራ-ሁለት ዓመታት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ያበቃዉ አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊዮስ እንደፕሬዝዳትነት የሚጠበቅባቸዉን አላደረጉም።ዛሬ በፕሬዝዳትነት የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመም ከእስካሁኖቹ የተለዩ ይሆናሉ ብለዉ አይጠብቁም።ምክንያት?

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ፤ ዛሬ ከበርሊን በሰጠው መግለጫ ላይ ፤ የመን በሚገኘው ኤምባሲው አንድ የኤምባሲው የፀጥታ ጉዳይ ባለሙያ መገደላቸውን አረጋግጧል። አምባሰደሯ ወ/ሮ ካሮላ ሙዑለር ሆልት ኬምፐርን አፍኖ

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6፣ 2013። ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨር-ኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ-አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል። ያን ሰሞን በኢትዮጵያ ድረ-ገጾች፣ በተለይ ደግሞ በፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ መድረኮች ላይ የውይይት ርእስ ሆኖ ሰነበተ። የታማኝ […]

እጎአ በ2000 ዓም 189 ሃገራትእጎአ እስከ 2015 ለመተግበር ቃልየገቧቸው Millennium development goals ወይምየተባበሩት መንግሥታት የአምዓቱ የልማትግቦችየተቀመጠላቸውየጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 2 ዓመትገደማ ብቻ ነውየቀረው።

SHARE:

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መንግስት በሚያስተዳድረው ሐገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን፣ ተቋማትን፣ የሀገር ሉዓላዊነትን፣ ታሪክን፣ ባህልን፣ የእምነት ነፃነትንና ደህንነትን ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት ወድሟል፡፡
እጅግ የሚያሣዝነው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡ ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡ በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲያችንን ከልብ አሳስቦታል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት፡-
1. አንጋጫ ኪ/ምህረት 2. ዳገት ሚካኤል 3. የደርበን ሚካኤል
4. ዋሻ መድሀኒዓለም 5. መንክር ማሪያም 6. ቀዝቀዝ ገብርኤል
7. ደማም እየሱስ 8. ምስለ ዋሻ ጊዮርጊስ
አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ የወደሙ ሲሆን የተወሰኑት በአካባቢው ሕብረተሰብ ጥረት በከፊል ተቃጥለው የተወሰነ ንብረት ሊተርፍ ችሏል፡፡ ፓርቲያችን በህግ ተመዝግቦ ህጋዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተወዳደሮ የመንግስት ሥልጣን ከመያዝ በተጨማሪ በተለያየ ጊዜ በሐገርና በህዝብ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን መከታተልና በሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረት ማደረግ ስለሆነ በመንግስት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የቃጠሎው ምክንያት ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀመው አካል በህግ ተጠያቂ እንዲሆንና ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለፅ እያሳሰብን እንዲህ ዓይነቱ በሕዝብ አመኔታ የሚጣልባቸው ተቋማትን የማውደም ተግባር ወደፊትም እንዳይደገም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
መስከረም 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አምስተርዳም ጉባዔ ላይ ለጥናት የቀረበ ጽሁፍ! 1.0 መግቢያ የታሪክ ግዴታ ሆኖ የሰው ልጅ እንደማህበረሰብ ከተደራጀና፣ ስልጣንና ሀብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ከጀመረ ወዲህ የአንድ ህዝብ ዕድልና የወደፊት ጉዞው፣ ታሪክ የመስራትና ያለመስራት ችሎታው በመጀመሪያ ደረጃ ሊወሰን የሚችለው ስልጣንን በቁጥጥራቸው ውስጥ ባስቀመጡ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው። በታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ ከአንድ አገዛዝ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ […]

መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም […]

ከሶስት ቀናት በፊት ቀትር ላይ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ ። አንድ እዚህ ጅዳ የሚገኝ ወዳጀ ነበር ። ይህ ወዳጀ በስደተኛ ዜጎቻችንና በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የከፋ ግፍ ሲፈጸም ፣ ዜጎች በራሳችን መንግስት ተወካዮች በጅዳና ሪያድ መጠለያዎች ፍዳቸውን ሲያዩ ፣ ኢትዮጵያውያን ሲያመን ህመሙ ዘልቆ ሲያመው እና የአረቡ መገናኛ ብዙሃን ስማችን አጉድፈው ክብራችን ቀንሰው መረጃ ሲያሰራጩ በስጨት ብለው […]

በኢጣልያ የባህር ክልል አካባቢ ሐሙስ፣ መስከረም 23 ቀን፣ 2006 ዓም ወደ አውሮጳ ለመግባት በሞከሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ እንደገና ዘግናኝ የመሰመጥ አደጋ ከደረሰ በኋላ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የህብረቱ የስደተኞችና እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ፖሊሲ ሰብዓዊነት እንዲታከልበት እና ለስደተኞች ደህንነት

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ ካናዳ)

የኛ ነገር፡ ክፍል 16፤ ከኔ ማእዘን፤

 

እንደ መግቢያ

 

1.       ይህ ጽሁፍ ሲታሽ፤ ሲሰቃይ እዚህ የደረሰ የቁጭት ጽሁፍ ነው፡፡ ወዲህም ግንቦትሰባትየምወደውበሱ ግን ደስ ያላለኝ ፓርቲስለሆነና፤ ዲባቶ ብርሀኑ ጋ ለኢሳት ዝግጅት ወደቶሮንቶ ስለሚዘልቅ፤ ያንዳንዶቻችንን ቁጭትና ጭንቀት ለመገለጽ የተሰናዳ ጽኁፍ ነውቀደም ያሉት የራስን የሆነን አካል የተቸሁባቸው ጽሁፎቼ ባንዳንድ ወዳጆቼ ዘንድ ቅሬታ ፈጥረዋል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ወዳጅን የሚያስቀይመውን ንጥረ ነገር ለመሽረፍ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ቀድሞውንስ በግል መንገሩ አይሻልም ወይ ለምን መጸፍ አስፈለገ ለሚሉት መልሱን ወደመጨረሻ እሰጣለሁ፡፡ ደግሞስ ፖለቲከኞች ወደ አደባባይ ሲወጡ ለመተቸት ተዘጋጅተው አይደለምን? ስለዚህ የሌሎችን ሀሳብ እተቻለሁ፤ የእኔም እንዲተች እነሆኝ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዩሱፍ ያሲን

በየታሪክ መጋጠሚያው የሚወጥር ጥያቄ

በተለያዩ የሀገራችን ወሳኝ የታሪክ ምዕራፎች ኢትዮጵያ ለመፃኢ እድሏ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆነ መስቀለኛ የታሪክ መጋጣሚያ ላይ ትገኛለች ሲባል ደጋግመን ሰምተናል። በርካታ ጊዜያት መንታ መንገድ ላይ ናት ተብሎ ሲነገር እንሰማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል። በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል …

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምዘና ፈተና ጋር በተያያዘ በተማሪዎችና እና በዩኒቨርስቲው አስተዳደር መካከል በተፈጠረ ልዩነት ከ3 ሺ በላይ ተማሪዎች ዩኒቭረስቲውን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው በቤተክርስቲያናትና በሰዎች ቤት ተጠልለለው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ከእረፍት በተመለሱበት ማግስት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ የምዘና ፈተና ውሰዱ መባላቸውን ተቃውመው ተጨማሪ የጥናት ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ችግር መፈጥሩን ገልጸዋል። …

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉበርግ የአለማቀፍ አጥኚዎች ቡድንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው መንግስት በማስገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ መሰረቱ ችግሮች ሊኖሩበት ስለሚችል መንግስት እንደገና እንዲያስጠና መክሯል። ግድቡ በታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በደንብ መጠናት አለበት ሲሉ የባለሙያዎቹ ቡድን አስተያየቱን ሰጥቷል። የግድቡን መሰረት ለማጠንከር መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ያስፈልጋል በማለት ያመለከቱት ባለሙያዎች፣ “ድክመት …

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ደሴት አካባቢ በጀልባ መስጠም ከሞቱት መካከል የ11 ሰዎች አስከሬን ቢገኙም፣ ከ200 በላይ ሰዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም። ፖፕ ፍራንሲስ በስፍራው ተገኝተው አደጋውን ከተመለከቱ በሁዋላ ሀዘናቸውን ገልጸዋል፣ ችግሩን ዝም ብለው የሚያዩትን አገራትም ወቅሰዋል። ብዙ የጣሊያን ባለስልጣናት የህጻናቱን አስከሬን እያዩ ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ሲያለቅሱ ታይቷል። እስካሁን …

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽንን የሥራ ሂደት ለማስተዳደር አንድ የህንድ ኩባንያ ተመረጠ፡፡ ፖወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ኦፍ ኢንድያ የተባለው ኩባንያ የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ሀይል ለማስተዳደር የሁለት ዓመት ኮንትራት ተሰጥቶታል፡፡ መንግስት ድርጅቱን ለውጭ ኩባንያ መስጠት የወሰነው በድርጅቱ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉና የተሻለ ስራን በሀገሪቱ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት …

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ብሔራዊ መንግስት መስተዳደር በክልሉ ያሉ ከተሞችን አስመልክቶ ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራት ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 19 ሚሊዮን ብር ለመፍቀድ ስብሰባ መቀመጡን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ በፖለቲካ ውሳኔ ለመንግስታዊው ዋልታ የመረጃ ማዕከል ሊሰጥ የታቀደው ፕሮጀክት የደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሀንን ቅር ማሰኘቱ ታውቋል፡፡ የክልሉ መገናኛ ብዙሀን በቂ መሳሪያና የሰው ሀይል እያለው ስራውን …

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበሪያ ሀላፊ ከነበሩት ግለሰብ ሰባት ነጥብ አራት ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብ መያዙን የፌደራል ስነ ምግባር ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጹ፡፡ ሀላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ስዩም 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል የሚል …

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን 500 አፍሪካውያ ስደተኞችን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የእሳት አደጋ በትንሹ 130 ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸው ተሰማ፡፡ ከአቅሟ በላይ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ጣሊያን የሚሄዱ ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ በመጨናነቋ ከተሳፋሪዎች አንዱ እርዳታን ለማግኘት ሲል በለኮሰው እሳት ጀልባዋ መቀጣጠሏን አሶሼትድ ፕሬስ ከጣሊያን ዘግቧል፡፡ የእሳት ምልክትን ከሩቅ አይተው ሰዎች ለእርዳታ ይደርሱልናል በሚል የተለኮሰው እሳት …

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ከጀመሩ ሁለት ወራት ያስቆጠሩት ምክትል ሚንስትሯ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው በአፍሪቃ በተለይም በቀፍሪቃ ቀንድን የሚከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አብራርተዋል።

ምስራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የምድር ባቡር የቀን ሰራተኞች በቀን ክፍያ በደል ደርሶብናል እያሉ ነው። እነዚሁ በምዕራብ ሃራርጌ ዞን አሰቦት አካባቢ የሚገኙ የምድር ባቡር ሰራተኞች እንደሚሉት ሌላ ቦታ ለተመሳሳይ ስራ በቀን የሚከፈለው ከ50 እስከ 100 ብር ሲሆን እነሱ ግን 25 እና 30 ብር ብቻ እየተከፈላቸው ነው።

ሄኖክ የሽጥላ (ገጣሚ)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፣ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ? ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በኢጣልያ ደሴት፤ ላምፔዱዛ አቅራቢያ ፣ ትናንት በእሳት ከተያያዛች በኋላ በሰጠመችው ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ደብዛቸው የጠፋውን ፍለጋ ዛሬም ቀጥሏል ።ከሊቢያ የባህር ጠረፍ 500 የሚሆኑ ስደተኞች አጭቃ ላምፔዱዛ የባህር ዳርቻ የደረሰችው ይህችው ጀልባ የኤርትራ እና የሶማሊያ ስደተኞች ነበር ያሳፈረችው ።

ዩናይትድ ስቴትስ ለሩዋንዳ የምትሰጠዉን ወታደራዊ እርዳታ እንደምታቆም አስታወቀች። የዋሽንግተን አስተዳደር እንዳለው እርዳታው የሚቋረጠው ሩዋንዳ ፣ ህፃናትን በውትድርና በማሰለፍ የሚከሰሰውን

በቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረት ሰፍነውና በቢሮክራሲዋ ውስጥ ተሰግስገው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለሚያራምዱ ድርጅቶች ተልእኮ አስፈጻሚና የቅስቀሳ ኃይል የኾኑ ሕገ ወጥ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመመከት በኦርቶዶክሳዊ ቀናዒነትና በበጎ ፈቃድ ተሰባስቦ በጥቅምት ወር ፳፻፫ ዓ.ም አገልግሎቱን የጀመረው የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት÷ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ወቅታዊ ጉዳዮችን የገመገመበትንና ቀጣይ የአገልግሎት አቅጣጫዎችን የተለመበትን የግማሽ ቀን …