ሉሉ ደበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)


አንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውንእየገመገሙናራሳቸውንእያረሙ፤ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርእድል ይሰጣቸዋል ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን  ብሎ ድንገት  እየተጯጯኽ  ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገንደሳለኝ)

…‹‹የጣር ቀጠሮው ስንት ነው
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው
ላይችል ሰጥቶት ለሚያስችለው
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?…››
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ‹‹እሳት ወይ አበባ›› የግጥም መድብል)
እነሆም ለቅስቀሳ ሳይሆን፣ አንተንም እራሴንም እወቅስ ዘንድ ብዕሬን እንዲህ አነሳሁ፡- ‹‹ ገሬ መከታዬ፣ መኩሪያዬ…›› ከምትላት እናት ኢትዮጵያ ምንድር ነው የምትፈልገው? …ዳቦ፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ ፖለቲካዊ ነፃነት፣ ቤት መስራት፣ መማር-አለመማር፣ መደገፍ-መቃወም፣ መተኛት-መነሳት፣ ፈጣሪን ማምለክ-መካድ፣ መስራት-አለመስራት፣ መምረጥ-አለመምረጥ፣ አደባባይ መዋል፣ ሰፈር መዋል፣ መደራ ት-አለመደራ ት፣ ማልቀስ-መሳቅ፣ መፃፍ፣ መናገር፣ መጮኽ-መመሰጥ፣ የግል መብት፣ የቡድን መብት?
ይህ ይሆን ዘንድ ከወዴት ትሻለህ? …ከሙት መንፈስ፣ ከውርሱ ድንዛዜ፣ ከሰማይ፣ ከምድር፣ ከፀሐይ፣ ከጨረቃ፣ ከርዕዮተ-ዓለም ወይስ….?

ሙሉውን አስነብበኝ …

 በክንፉአሰፋ

 “የአሲምባ ፍቅር” – መጽሃፍ ቅኝት
በክንፉ አሰፋ
ደራሲ፣ ካሕሳይ አብርሃ ብስራት
ብዛት፣ 446 ገጾች
በተስፋዬ ወልደዮሃንስ አዲስ አበባ ታትሞ የተሰራጨ
* ከስር በስእሉ እንደሚታየው ኢሲምባ 3250 ሜትር ከፍታ ላይ በትግራይ ውስጥ ያለ ተራራ ነው። አሲምባ በዚህ ከፍታው ሳቢያ ሌሊት ላይ በጉም ይሸፈናል። አሲምባ “ቀይ አንባ” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አውሮፕላኑ ወደ ምድር ዝቅ እያለ መሆኑን አስተናጋጇ በመናገር ላይ ናት፡፡ የምናርፈው ባንዳር ሰሪ ባጋዋን የሚባለው የብሩናይ ዓለም ዐቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ነው፡፡ ብሩናይ እስከ ዛሬ ስሟን እንኳን ሰምቻት የማላውቅ ትንሽ የደቡብ እስያ (ኦሺንያ) ሀገር ናት፡፡ ወደ እርሷ ለመድረስ ከዱባይ ተነሥተን የ8 …

ጉዞ ወደ ምድር ጥግ (ሦስተኛ ክፍል) Read more »

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ ከጥቁር አንበሳ እንደገለጸው በዛሬው ድብደባ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተደብድበዋል፣  እየታፈሱም ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ተግዘዋል። ኢሳት በራሱ ዘጋቢዎች ባያረጋገጥም፣ ያነጋራቸው ሰዎች አንድ ነፍሰጡርና አንድ ታዳጊ ልጅ መሞታቸውን ጠቁመዋል።  

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢው በከፍተኛ አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ አርፍዷዋል፡፡በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።  የደሴ ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማወቅ በፊድራል ፖሊስ ሐይሎች ሆስፒታሎች በመከበቡ ለማወቅ አልተቻለም። በደሴ የሚኖሩ ሙስሊሞች 2 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት ተናግረዋል በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፤ እና መርሳ አካባቢ ክፍተኛ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በሙስሊሙ እና …

በወላይታ የአንድነት ሰብሳቢ ታሰሩ በደቡብ ክልላዊ መስተዳደር ወላይታ ዞን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሰብሳቢ ታሰሩ፡፡ ሰብሳቢው አቶ ወኖ መንዓሳ ትናንት ነሐሴ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የዞኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑትንና ባለፈው ሳምንት ሐምሌ27 የታሰሩትን ወ/ሮ ሀዲያ መሐመድን ለመጠየቅ ከሚኖሩበት በዴሳ ወረዳ ወላይታ ሶዶ ከተማ ደርሰው ሊመለሱ ሲሉ ከአውቶቡስ ተራ ተይዘው መታሰራቸውን የዞኑ […]

የኢትዮጵያ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ በተለያየ አቅጣጫ ጥፋት እየፈጸመ መሆኑን፤ በሕገ ወጥ ቅርስ አቀባዮች የሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ወደ ዉጭ እየተጋዘ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ።

1434ኛው የእድ አል ፈጥር በዓለ ዛሬ በሙሥሊም ሀገራት ተከበረ። ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሙሥሊሙ ህብረተሰብ አባላት በአዲስ አበባ ስቴድየም የተካሄደውን የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓት ወደዚያ በመሄድ እና በዙርያው በመገኘት ተከታትለውታል።

በሳውዲ ዐረቢያ ፣ በየመን እና በዩኤስ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙሥሊሞች ዕለቱን እንዴት እንዳከበሩት ከጄዳ፣ ከሰንዓ እና ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪሎቻችን ጋ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርገናል።

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድምጻችን ይሰማ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው መንግስት ፣ በካድሬዎቹ አማካኝነት ” የአገርህ ባንዲራ ተደፍራለችና ስልፍ ውጣ እያለ” ትናንት ህዝቡን ሲያስፈርም መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። አንዳንድ ካድሬዎች “ጊዮርጊስ አድዋ ድረስ ሄዶ ተዋግቷል፣  አንተም አገር ሊያጠፉ የመጡትን ተነስትህ ተዋጋ”የሚሉ ቅስቀሳዎችን መዋላቸውንም እነዚሁ እማኞች ተናግረዋል። በእድሜ ለገፉት ደግሞ አሸባሪዎችን …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ባልጨመረበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ብቻ የኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በ0.16 ሳንቲም ከፍ በማለት በሊትር 18 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ የንግድ ሚኒስቴር መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው የዓለም የነዳጅ ዋጋ የመዋዥቅ ሁኔታ ማሳየቱን ተከትሎ ጭማሪ ለማድረግ መገደዱን ይግለጽ እንጂ በዓለም ገበያ በዚህ ወቅት ነዳጅ …

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለቀላል ባቡር ፕሮጀክቱ ግንባታ በሚል ሰበብ ከዚህ ቀደም እንዲፈርሱ ከተደረጉት ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ የሚዘልቀው መንገድ የመሀል ክፍልና ከደሴ ሆቴል ወደ ፑሽኪን አደባባይ ከተዘረጋው አዲስ ከፊል የአስፓልት መንገድ በተጨማሪ ፣ ከ192 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጐበት ከሾላ ገበያ በለም ሆቴል እስከ አንበሳ ጋራዥ የተገነባው መንገድ የተወሰነ ክፍሉ በቅርቡ እንደሚፈርስ ሪፖርተር …

የአፍሪካ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች
አጎአ በሚል ምኅፃር በሚጠራው አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በቀለለ ሁኔታ ለመናገድ እንድትችል መንገድ በሚጠርገው የንግድና የገበያ ተጠቃሚነት ዕድል መርኃግብር የአፍሪካ ሴቶች እንዳልተጠቀሙ ተገልጿል፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥም የአፍሪካን ሴቶች አቅም ማጎልበት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበር አሳስቧል፡፡

ማኅበሩ አዲስ አበባ ላይ አዲስ ቢሮ ከፍቷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምኃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሰኔ 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ እየተካሄደ ያለው የፀረ ሽብር ህጉን የመቃወም እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከእስር ቤት ሆና ባስተላለፈችው መልዕክት ጠየቀች፡፡ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ጋዜጠኛ ርዩት አለሙ ገዥው የኢህአዴግ መንግስት የፀረ ሽብር ህጉን ለስልጣኑ ማራዘሚያነት ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ እየተጠቀመበት እንደሚገኝ ገልጻ እየተደረጉ ያሉት …

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ በትላንትናው እለት የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ህግና የተጠርጣሪ ጠበቆች በጋራ ተስማምተው ንብረቱን የሚያስተዳድር አካል እስከ መስከረም 22 ቀን 2006 ዓ.ም. እንዲያቋቁሙ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ንብረታቸው በገለልተኛ አካል እንዲተዳደር ፍርድ ቤት የወሰነባቸው ንብረትነቱ የአቶ ሰማቸው ከበደ የሆነው ባለ 5 ኮከብ ኢንተርኮንተነንታል ሆቴል እና ዲ ኤች ሲሜክስ …

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በትላንትናው ዕለት የህዝበ ሙስሊሙን የተቃውሞ ስልፍ በመፍራት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከበረውን በአል በልዩ የመግቢያ ካርድ እንዲሆን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመግቢያ ካርዶችን እንዳዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁንና ዛሬ የፌደራል መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ልዩ ትዕዛዝ በመስጠት ሁኔታው እንዲቆም ማድረጉ ታውቋል፡፡ የፌደራል መረጃና ደህንነት ተወካዮች በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተማ የሚገኙ …

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታዋቂው የአበበ ቢቂላ 81ኛ ዓመት የልደት በዓል በማስመልከት ታዋቂው የድህረ ገጽ ቋት የሆነው ጉግል የአበበ ቢቂላን ፎቶ በፊት ገጹ ላይ በማስቀመጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አስበውት እንዲውሉ አደረገ፡፡ የጉግል አካል የሆነውና ጉግል በአርማነት የሚጠቀመው ጉግል ዶድል ድረ ገጽ ላይ የመጀመሪያው የሰብ ሰሀራ ኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነው አበበ ቢቂላ እንደዚህ አይነት …

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሁኔታው ያሳሰበው የአውሮፓ ህብረት የማልታ መንግስት ያለምንም መዘግየት በእንግልት ላይ የሚገኙትን ሰዎች ወደ ድንበሩ ገብተው ሰብአዊ መብት እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ ማረፊያ ያጣችው መርከብ በውስጧ አራት እርጉዝ ሴቶችን፣ አንድ የተጎዳች ሴትና የ5 ወር ህጻን መያዟን የአውሮፓ ህብረት አስታወቋል፡፡ በላይቤሪያ መንግስት ንብረትነት የተመዘገበችው ጀልባ በግሪካዊ ኩባንያ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረች ሲሆን 120 …

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን v  በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ v  ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ v  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችኹ v  በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ v  የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ     ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ የተወደዳችኹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን÷ እግዚአብሔር አምላክ …

ዓለም አቀፉ አጥኚ ተቋም ICG እንደሚለዉ ልዩነቱን ለማስወገድ መሠረታዊዉ ነገር የሁለቱ ፖለቲካዊ ራዕይ ነዉ።አርቆ ማስተዋሉ ካለ ዉክልና ወይም ሥልጣን መጋራት፥በጋራ ጉዳዮች በጋራ መወሰን አካባቢዉን ማልማት፥የሕዝቡን ኑሮ ማሻሻሉም አይገድም።

የኮት ዲ ቯር የፍትሕ ሚንስቴር በእስር ከሚገኙት የቀድሞው የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሎውሮ ባግቦ ደጋፊዎች መካከል የቅርብ ረዳቶቻቸው ናቸው የሚባሉትን 14 ሰሞኑን በጊዜያዊ ሁኔታ ፈታ። ግለሰቦቹ የተፈቱበት ርምጃ በሀገሪቱ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት ዓቢይ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ቢገምቱም፣ የባግቦ ደጋፊዎች በቂ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።

ረሃብን ለመቅረፍ በሽታን ለመከላከል፣ መሠረተ ልማትን በሰፊው ለመዘርጋት ፣ በአጠቃላይ ኑሮን ለማሻሻል፤ ዕውቀት ወሳኝ ነው። ዕውቀት የሚስፋፋው ፤ የሚዳብረው ፣ በመመራመርና ከሌሎች ጋር የሐሳብ ልውጥ በማድረግ ነው። ይህን በማከናወን ቀዳሚውን ቦታ

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በተለያዩ አካባቢዎች፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ፤ አካኺደው እንደነበረ የሚታወስ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሻሻመኔ አካባቢ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ፤

የMDC ሥሌት መረጃዎቹ ሕጋዊ መሠረት ካገኙ የዉጪ ሐይላት በተለይም የአፍሪቃ ሕብረት እና የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ (SADC) በፕሬዝዳት ሙጋቤ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ይጠቅማሉ ነዉ።ከተሳካ አዲስ ምርጫ።

ወያኔ እንደ ቆሰለ አውሬ. . . ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) ዘመንኑ ያለቀበት ስርዓት፣ መዋቅሩ የፈረሰ ስርዓት፣ ሁለመናው እኩይ በሆነ በሕዝብና ሃገር ጥላቻ የተተበተበ ስርዓት፣ የእድሜ ዘመኑ እያለቀና የማስተዳደርና የመምራት አቅም ማጣት ሲጀምር ለስልጣኑና በስልጣን ዘመኑ የመዘበረውን የሕዝብና የሃገር ሃብት ለማስጠበቅ የውር ድንብሩን ዪዳክራል፡፡ ይህው በመቃብር አፋፍ ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት በሕዝብና […]

በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ የህዝብ አውቶብሶች አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተበላሹ ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ያመረታቸው እና የገጣጠማቸው የከተማ እና  አገር አቋራጭ  አውቶብሶች አመት ሳይሞላቸው ለጉዳት ተደርገዋል። አውቶብሶቹ ከግማሽ በላይ አካላቸው በሀገር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የተመረተ ቢሆንም በውጭ ሃገር ግዥ …

መዋቅሩና ምደባው ለመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያናችን ተልእኮ ትኩረት የተሰጠበት፣ ድጋፍ ሰጪው በባለሞያ ብቻ የሚመራበት፣ ሠሪውና ተቆጣጣሪው የተለየበት ነው የቁጥጥር አገልግሎቱ ሥልጣን ከሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በላይ ኾኖ ተጠሪነቱ ለመንበረ ጵጵስናው ሀ/ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ኾኗል፤ የጸሐፊ ሥራ መደብ ቀርቷል ራሳቸውን ከለውጡ ጋራ የሚያራምዱ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በሥራ አፈጻጸማቸው የሚመዘኑበት፣ በዕድገትና ሥልጠና የሚበረታቱበትና የሚታገዙበት ኹኔታ ተመቻችቷል በተለያዩ ዓላማዎች …

ጀርመን ውስጥ በተለይ በምሥራቅ ጀርመን ዘረኝነት ከቀድሞው እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን አንድ ጥናት አስታውቋል ። የጀርመን መንግሥት ምስራቅ ጀርመን ውስጥ በሚገኙ ፌደራል ግዛቶች ዘረኝነትን ለመከላከል ተግባራዊ ያደረገው መርህም ለውጥ አለማምጣቱ በጥናቱ ተገልጿል ።

የወጣቶቹ ማሕበር በጠራዉ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የሕክምና ባለሙያዎችና የሐይማኖት መሪዎችም ግብረ-ሰዶማይነትን ያስፋፋሉ ባላቸዉ ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ጠይቀዋል

በደቡብ ሶማልያ የምትገኘው የኪስማዮ ከተማ አስተዳደር ለሶማልያ ማዕከላዊዉ መንግሥት እንዲሰጥ ሀሳብ ቀረበ። ይህንን ሀሳብ ያቀረቡት በሳምንቱ መጨረሻ በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ የአንድ ቀን ምክክር ያካሄዱት ያካባቢ ሀገራት መሪዎች ናቸው። ይህ የቀረበው ሀሳብ በተግባር ሊተረጎም መቻል አለመቻሉ የሚመለከታቸውን ወገኖች ብዙ እያነጋገረ ነው።

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።