የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የማሊ ፪ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ። ምንም እንኳን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይወጣም በኬይታ አንፃር የተወዳደሩት የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ሱማይላ ሲሴ ሽንፈታቸውን በመቀበል ትናንት ከተፊካካሪያቸው ኬይታ ጋ በመገናኘት የእንኳን ደስ ያልዎት ምኞታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ – /ፎቶ – ፋይል/ ​​
አጎአ እንዲሰፋ ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠየቁ
ዩናይትድ ስቴትስ ከሠሃራ በስተደቡብ ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች ያወጣችው በምኅፃር አጎአ የሚባለው ከቀረጥ ታሪፍ ነፃ የመናገድ፤ የአፍሪካ የዕድገትና የንግድ ዕድሎች ተጠቃሚነት ሕግ ረዘም ላሉ ዓመታት መቀጠል እንዳለበት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠይቀዋል፡፡
አጎአ – አዲስ አበባ – 2013 ​​
አዲስ አበባ ላይ በተከፈተው የአጎአ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ጠቀሜታው ሊሰፋ፤ ከገበያ ዕድልም ሊያልፍ ይገባዋል ብለዋል፡፡

የአሜሪካው የንግድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ማይክል ፍሮማን በበኩላቸው አጎአ አሜሪካና አፍሪካን በንግድና በምጣኔ ኃብት የሚገኛኙበትን ሁኔታ በእውነት የቀየረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አጎአ – አዲስ አበባ – 2013 ​​
ዝርዝሩን …

ሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ላይ እየተካሄደ ባለው 14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ድል በዓለሙ ሠንጠረዥ ሁለተኛ ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሕዝበ ሙስሊሙን ከ18 ወራት በላይ የዘለቀ እንቅስቃሴ በኃይል ለማፈን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየወሰደ ያለው እርምጃ በሙስሊም አባላቱ ዘንድ ቅሬታ ማሳደሩ የግንባሩን ከፍተኛ አመራር ስጋት ውስጥ እንደጣለ የውስጥ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አብዛኛዎቹ የግንባሩ ሙስሊም ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ አመራር አባላት መንግስት በሙስሊሙ ጥያቄ አፈታት …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሰዎችን ማሰሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል 6ቱ ሴቶች ናቸው። ባለፈው ሐሙስ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መደብደባቸውን የሚያመለክት ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በብዛት በማቅናት ሰዎችን በማሰር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ መረጃዎችን በማቀባባል የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በክልሉ ባሉ የአስተዳደር ቢሮዎች ባካሄደው ቅኝት የመልካም  አስተደዳር ችግር በክልሉ ተባብሶ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ በተለይም በፍትህ ፤ በፖሊስ ፤ በማረሚያ ቤቶች ፤ በመሬት ፤ኢንቨስትመንት፤ መብራት እና ውሃ ደግሞ የችግሩ መለያ ቦታዎች መሆናቸውን ለክልሉ ካቢኔ የቀረበው ሪፖርት የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን ያወሳል፡፡ በክልሉም ከጊዜ …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል። በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን አብየ ግዛት የሚገኘው የጥምር ኮሚቴ ስብሳቢዎች አንዱ የሆኑት አልከሄር አል ፋቲም አማጺ የሆነውን የሱዳን አብዮታዊ ግንባር በአካባቢው መኖሩ እያወቀ በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር በዝምታ በማለፉ ክፉኛ ወቅስዋል:: አልከሄር አል ፋቲም ሰሜን ሱዳንን ወክለው የሚገኙ ሲሆን እንደሳቸው ገለጻ አማጺው ሃይል በምስራቅ አብየ ሰፍሮ እንደሚገኝ ገልጸዉ የኢትዮጵያን ጦር ዝምታ ግን …

አገርን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሚወስኗቸው ዉሳኔዎች፣ አገርን በማልማትም ሆነ በማጥፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። ብዙዎች በአፋቸው «ፖለቲካን አንፈልግም። ፖለቲካ ውስጥ የለንበትም» ቢሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን፣ የፖለቲካዉ አካል ናቸው። ፖለቲካዉ የማይነካዉ ማንም ዜጋ የለም። የፖለቲካ ስልጣን የያዙ በሙስና ከተጨማለቁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ሊያገኝ የሚገባዉን አገልግሎት በሚገባ አያገኝም። ፖለቲካዉ ዜጎችን በዘር ከፋፍሎ ፣ «የዚህ […]

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ-ህዝብ ጠበብት ጥናታዊ ትንበያ እንደሚጠቁመው ከሆነ ፣ ምድራችን፣ እ ጎ አ እስከ 2100 ዓ መተ ምኅረት፤ 11 ቢሊዮን ያህል ዜጎችን ማስተናገድ ግድ ሳይሆንባት አይቀርም። አሁን የዓለም ህዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን ነው።

ትምህርት ቤቶች ለረዥም ጊዜ የሚዘጉበት የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በርካታ የጀርመንና የእስራኤል ወጣቶች የልምድ ልውውጥ መርኀ ግብር የሚያካሂዱበት ወቅት ነው ። ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ጀርመናውያን ወጣት በጎ ፈቃደኞች በእስራኤል ማህበራዊ አግልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው

አሁን ሶስተኛው ትውልድ ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው፤ አልቃይዳ። የመጀመሪያው ትውልድ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ከመስከረሙ የ2001 ዓም ጥቃት በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ ይጠቀልላል። ሁለተኛው ትውልድ ደግሞ የአልቃይዳው ዋና ሰው ቢን ላደን እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ የነበሩትን ሁነቶች ያካትታልል። ሶስተኛው ትውልድ የቢን ላደን መገደልና የአረብ

አገርን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሚወስኗቸው ዉሳኔዎች፣ አገርን በማልማትም ሆነ በማጥፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። ብዙዎች በአፋቸው «ፖለቲካን አንፈልግም። ፖለቲካ ውስጥ የለንበትም» ቢሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን፣ የፖለቲካዉ አካል ናቸው። ፖለቲካዉ የማይነካዉ ማንም ዜጋ የለም። የፖለቲካ ስልጣን የያዙ በሙስና ከተጨማለቁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ሊያገኝ የሚገባዉን አገልግሎት በሚገባ አያገኝም። ፖለቲካዉ ዜጎችን በዘር ከፋፍሎ ፣ «የዚህ […]

ዩኤስ አሜሪካ እና አፍሪቃ፣ «አፍሪካን ግሮውትስ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት» በምሕፃሩ «አ ጎ አ» በሚል ውል ባነቃቁት የንግድና የኤኮኖሚ ትብብር ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር ማካሄድ ጀመሩ።

አንባገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውን እየገመገሙና ራሳቸውን እያረሙ፤ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርም እድል ይሰጣቸዋል ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን ብሎ ድንገት እየተጯጯኽ ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት። ይህ አባይን የመሰለ ብሄራዊ ጉዳይ ባልታሰብ ሁኔታና ጊዜ ድንገት ያነሳው ቡድን፤ ኢትዮጵያን እንደሀገር ሊያቆዩአት […]

የሀገርን ክብር ከፍ የሚያደርጉ፣ ጽናትንና ብርታትን የሚሰብኩ፣ አልበገር ባይነትንና ተጋድሎን የሚያውጁ፣ ለዓላማ ቁርጠኝነትንና ትጋትን የሚናኙ የተባረኩ እግሮች፡፡ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው እንዲያ ተከበሽ ስትሮጭ፣ ምን ነበር ይሆን የምታልሚው እንዲያ ሀገርሽ አንድ ወርቅ እንኳን አጥታ ስሟ ከሠንጠረዡ ሲጠፋ፤ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው የእነ አበበና የነ ማሞ፣ የነ ምሩጽና የነኃሌሌ፣ የነ ቀነኒሳና የነ ገዛኸኝ ታሪክ ወደ ተረትነት ሲለወጥ፤ ተንታኙ ሁሉ እንዲህ ነበሩኮ የሚለንን ስትሰሚ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው፡፡

የሮጥሽውን እንጂ ያሰብሽውን አላየነውም፡፡ ያደረግሽውን እንጂ የወሰንሽውን አልተመለከትነውም፡፡ ወደየት ነበር የሮጥሽው? ምን ነበር ከፊት የሚታይሽ? አበበ ነው ወይስ ኃይሌ? ባንዲራሽ ነው ወይስ ሕዝብሽ? መቼም ምንመ ሳታይ እንዲያ አልተፈተለክሽም፡፡ ምንስ ነበር የምትሰሚው? መቼም የሞስኮን ሕዝብ ጩኸት አይደለም፡፡ በማያውቁት ቋንቋ የሚነገር ጩኸት ምች እንዲያ ያስሮጣልና፡፡ ሂጂ፣ ሂጂ፣ ሂጂ ጥሩነሽ ሩጭ፤ ታሪክ ተረት ሆኖ እንዳይቀር ለሀገርሽ ወርቁን አምጭ› ‹ሂጅ አብረንኅ እየሮጥን ነው፣ ብቻሽን ከቶ አይደለሽም፤ ምሩጽ ቀድሞ ሰባብሮታል፣ ይህ አየር ለኛ አዲስ አይደለም› የሚለው የሕዝብሽ ድምጽ ነበር በሹክሹክታ የተማሽው? አርምሞኮ ቋንቋ ነው በውስጥ ከነፍስ ጋር የሚያወሩት፡፡

እነዚያ እግሮችሽ እንደ ሲላ ሲወረወሩ፣ እንደ ንሥር ሲበርሩ፣ እንደ አቦ ሸማኔ ሲፈተለኩ፣ እንደ ሚግ ሲምዘገዘጉ፣ እጆችሽ እንደ መልአክ ክንፍ አየሩን ሲሰነጥቁ፣ ደረትሽ እንደ ሚሳይል እየከፈለው ሲተኮስ፤ እንደታቀፈች ሰጎን ዓይኖችሽ ምድር ምድር ሲያዩ፣ ከአየር ጋር ስትሟገች፣ ከድል ጋር ስትጠራሪ፣ ከእልክ ጋር ተወራርደሽ፣ ከእምቢ ጋር አብረሽ ስትሮጭ፤ ልብና እግሮችሽ ተስማምተው እየተማከሩ ሲነጉዱ፤ ዓይንና እጆችሽ ተፋቅረው የርቀት መጠን ሲለኩ፤ እንደ ንብ አውራ ታጅበሽ፣ እንደ ንብ ንግሥት ስትከንፊ፤ ምነ ነበር ያኔ የምታስቢው?

ሀገር ነበረች ከኋላሽ፣ ሀገር ነበረች ከፊትሽ፤ እንዳንች ማልያ አጥልቀን፣ እንዳንቺ ሞስኮ ባንጓዝ፤ እንዳንቺ ሀገር ወክለን እንዳንቺ በመም ላይ ባንከፍ፤ ልባችን ካንች ጋር ነበር፣ ሁሉንም ዙር አብሮ ዞሯል፤ ኅሊናችንም ካንቺ ጋር ለአምላክ ሥዕለቱን አቅርቧል፡፡ እንዴት ደስ ይላል መሰለሽ አገር አስከትሎ መሮጥ፤ እያባረርሽን አልነበረም፣ እየተከተልንሽ እንጂ፣ በእጅሽ መሣሪያ አልያዝሽም፤ ውርደትን ቀዘፍሽው እንጂ፡፡ ሀገርን ሊያኮራ የሚሮጥ፣ ድሮም ሕዝብ አብሮት ይሮጣል፣ እግሮቹ ብሩካን ናቸው ብሎ ከጥንቱ መርቆታል፡፡ በሞስኮ አፈር ላይ አይደለም በብሩካን እግሮችሽ የሮጥሽው፣ በሚወድሽና በሚሳሳልሽ ሕዝብ በልቡናቸው ውስጥ ነው፡፡


አብረንሽ ባንሮጥ ኑሮ ድል ስታደርጊ ለምን አብሮ ደስ አለን? ድል አደረግን ሲሉንኮ አብረናቸው ያልተደሰትን ብዙዎች አሉ፡፡ ድሉ የራሳቸው ብቻ የሆነ፤ ብቻቸውን ያሸነፉ፤ ድላቸውን ያልገዛንላቸው፡፡ አንዳንዶች ወርቅ ከሀገራቸው ሲያወጡ አንቺ ግን ወርቅ ወደ ሀገርሽ አመጣሽ፤ ስለዚህ አብረንሽ ሮጥን፡፡ አብረንሽም ስለሮጥን አብረንሽ ተደሰትን፡፡ ሞስኮ ላይ ያዩሽ ሁሉ፤ ምሩጽ አልሞተም አሉ፡፡ አረንጓዴው ጎርፍ ቢደርቅም አረንጓዴ ወርቅ አላቸው አሉ፡፡ ሁሉንም የሚግባባ ሃሳብና ፕሮግራም፣ አስተዳደርና አመራር፣ አካሄድና መዋቅር በጠፋበት ጊዜ ምሥራቅ ከምዕራብ ሰሜን ከደቡብ አስተባብረሻልና የመግባቢያ ሰነዳችን ሆነሻል፡፡ በየጎራው የቆሙትን፣ በየተቃራኒው የተሰለፉትን ሁሉንም ሞስኮ አምጥተሸ አንድ አድርገሻቸዋልና የአንድነት ዓርማ ሆነሻል፡፡ 

ማጭበርበር በሌለው ምርጫ ተመርጠሻል፤ የምረጡኝ ዘመቻ ሳያስፈልግሽ በተግባር ሕዝብ አሰልፈሻል፤ ዙፋን ሳያስፈልገሽ ነግሠሽ፣ ሉል ሳያስፈልግሽ ገዝተሻል፡፡ ስም ወደ ግብር ይመራልና ጥሩነሽ ጀግና ሆነሻል፡፡

እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡ 

የግጭት አፈታት ​​
የግጭት አፈታት
በአንድ ቡድን ወይም በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር ግጭት ቋሚ መፍትሔ የሚያገኘው በድርድርና በውይይት አንዱ የሌላውን ጥያቄ ግንዛቤው ውስጥ ሲጨምር መሆኑን የግጭት አፈታት ስልት ምሁሩ አቶ ሰለሞን ጥላሁን ገልፀዋል። የግጭት አፈታት ​​​​ አቶ ሰለሞን ከትዝታ በላቸው ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ግጭት ተወልዶ እስከሚሞት እንዲባባስ ስለሚያደርጉትና ስለሚያረግቡት፣ እንዲሁም የማጥፊያው መንገዶች በሰፊው ተንትነዋል፡፡

ባለሙያው በማብራሪያቸው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ ተመጣጣኝ ያልሆኑ ግቦች ወደ መግባባትና ወደ ግጭት ሊያደርሱ እንደሚችሉም አመልክተዋል፡፡
የግጭት አፈታት ​​
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮች ከተለያዩ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የልማት ርዳታ ያገኛሉ። ኢትዮጵያ አፍሪቃ ዉስጥ ከፍተኛ የልማት ርዳታ ከሚያገኙ ሃገር ግንባር ቀደሟ ናት

በምደባ ቅር የተሰኙ ሓላፊዎች በየሆቴሉና ሬስቶራንቱ የዐመፅ ምክክር ይዘዋል ‹‹የቋሚ ሲኖዶሱ ምደባ በአተገባበር በደላሎች ተጠልፏል›› የሚል ቅሬታ አላቸው የረዳት ሊቀ ጳጳሱና ጽ/ቤታቸው ድርሻ የቋሚ ሲኖዶሱን ምደባ ማስፈጸም ብቻ ነው በዘላቂው የሀ/ስብከቱ መዋቅር ስፍራ የሚኖራቸው በጊዜያዊ ምደባቸው ብቃት ያሳዩ ሓላፊዎችና ሠራተኞች መኾናቸው ተገልጧል የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት ለዘረጋው የሽግግር ጊዜ መዋቅር …

አንድነት በመብራት ሃይል አዳራሽ በአጭር ጊዜ የጠራው ስብሰባ በድምቀት እና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ በመብራት ሐይል በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ የፓርቲው አመራር አባሎች እና ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ በተለይ ዛሬ ለስብሰባው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በህገወጥ መንገድ የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ተለቀው ወደስብሰባ አዳራሹ በማመራት ስበሰባውን መሳተፍ ችለዋል፡፡ ከነሱ መሀል […]

በማሊ ዛሬ 11.08.2013 ፪ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።
በምርጫው የሚወዳደሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ እና የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ሱማይላ ሲሴ ናቸው።

በናይጀሪያ የምክር ቤት እንደራሴዎች ለአካለ መጠን ያለደረሱ ሕፃናት ሴቶች ሊዳሩ ይቸላሉ የሚለውን ሕግ ወደፊትም ሊሰራበት ይችላል ካሉ በኋላ በሀገሪቱ ሰፊ ክርክር ተነስቶዋል። ሰሞኑንም በኤኮኖሚ መናኸሪያ በሆነችው በሌጎስ ከተማ አደባባይ በመውጣት «ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት እንጂ ለሙሽራነት አልደረሱም » የሚል መፈክር አሰምተዋል።

አንድነት ፓርቲ ነገ ነሃሴ 5, 2005 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው የመብራት ሃይል አዳራሽ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 12 የፓርቲው አባላትና ሁለት መኪኖች መስቀል አደባባይና ሳሪስ አካባቢ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችም አባሎቹ ወደ ታሰሩባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች አምርተዋል፡፡ ቀደም ሲል አዲሱ ገበያ አካባቢ 3 አባላት ተይዘው የነበረ ሲሆን እስከ አሁኗ ሰአት ድረስም 15 […]

አንድነት ፓርቲ ነገ በመብራት ሃይል ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ባልቀ ከመንግስት የአዳራሽ ፍቃድ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ቢሰጥም ገና የመከና ላይ ቅስቀሳ በጀመሩ በፖሊሶች ክልከላ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ በአዲሱ ገበያ አካባቢ ሲቀሰቅስ የነበረው መኪና ላይ የነበሩት ሶስት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት ማዕከላዊ (3ኛ ፖሊስ ጣቢያ) ታስረዋል፡፡ የታሰሩት አባላት ሰፊው መኮንን፣ አቶ ኃይሉ ግዛው እና ወርቁ ፡፡ […]

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። […]

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት በ ኢድ አል ፈጥር እለት የፌደራል ፖሊሶች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ ሌሊቱንና ዛሬም በርካታ ሙስሊሞች ከቤታቸው እየተወሰዱ ታስረዋል። በአሁኑ ጊዜ በትክክል የታሰረውን ህዝብ ቁጥር ለማወቅ ባይቻልም   በሺዎች እንደሚቆጠር ይገልጻሉ። በዛሬው እለትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር ተፈተዋል።  ድምጻችን ይሰማ …

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ነው። ሶቭየት ሰራሹ አንቶኖቭ አውሮፕላን መሬት ላይ እንደወደቀ በእሳት ጋይቶ 4 ቱን አብራሪዎች ገድሎአዋቸል። አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከሳምንት በፊት አንድ የመከላከያ ንብረት የሆነ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል።

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በወረዳው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በትናንትናው እለት አልፋ እየተባለ ወደ ሚጠራው ቀበሌ ያመሩ የፖሊስ አባላትና ካድሬዎች ምሽቱን መደብደባቸውን የተመለከተ መረጃ የደረሰው ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በዛሬው እለት በዙሁ ቀበሌ ያለው ውጥረት የጨመረ ሲሆን፣ በካድሬዎቹ እና በፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም …

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኮሪያ ዘማች ቤተሰቦች ተውጣጥው ወደ ደቡብ ኮሪያ ለትምህርት ከተላኩት 59 ኢትዮጵያውያን መካከል 38ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለ8 ወራት የተሰጣቸውን ስልጠና ሊያጠናቅቁ የቀናት እድሜ ሲቀራቸው ነው ጥገኝነቱን የጠየቁት። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት፣ ወጣቱ በአገሩ የሚሰራበት ሁኔታ ሊመቻች ባለመቻሉ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደተገደዱ ወጣት ሲሳይ ወልደገብረኤል ለኢሳት ገልጿል።

የዩጋንዳ የተቃውሞው ወገን የአገሪቱ ፓርላማ ፤ የህዝብን የመሰብሰብ መብት የሚያርቅ አዲስ ህግ ፣ ከትናንት በስቲያ ማጽደቁን አስመልክቶ ፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረ-ሰብ ጣልቃ ይገባ ዘንድ ተማጽኖ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተነገረ። በአዲሱ ህግ መሠረት፤ ማንኛውንም

ከአንድ አመት በፊት ነበር «ጋንግናም ስታይል» በገበያ ላይ የዋለው።ደቡብ ኮሪያዊው አቀንቃኝ ፕሳይ በዚህ አዝናኝ የዳንስ ቪዲዮ በአለም አቀፍ እውቅናን አገኘ። ቢንያም ዳና ደግሞ «የኛ እስታይል» ሲል ተጫውቶታል።

ሙስሊም ወገኖቻችንን መግደል፣ ማሰርና መደብደብ ሕገ-ወጥነት እንጅ መፍትሔ አይደለም!! ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሁለት ዓመት ለመሙላት ጥቂት ወራት የቀረውን የሙስሊም ወገኖቻችንን ሠላማዊ የመብት ጥያቄ እንዲያከብር፣ መንግሥት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ያነሷቸውን ጥያቄዎች በአስተውሎት በማየት እንዲሁም ወደ ውይይት በመምጣት ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ ሲያሳስብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ የመንግስት ሚዲያዎችና አንዳንድ የገዢው […]