በሽግግር ጊዜ አደረጃጀትና አሠራር በተዋቀረው የአ/አ ሀ/ስብከት የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ ተካሄደ
- መዋቅሩና ምደባው ለመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያናችን ተልእኮ ትኩረት የተሰጠበት፣ ድጋፍ ሰጪው በባለሞያ ብቻ የሚመራበት፣ ሠሪውና ተቆጣጣሪው የተለየበት ነው
- የቁጥጥር አገልግሎቱ ሥልጣን ከሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በላይ ኾኖ ተጠሪነቱ ለመንበረ ጵጵስናው ሀ/ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ኾኗል፤ የጸሐፊ ሥራ መደብ ቀርቷል
- ራሳቸውን ከለውጡ ጋራ የሚያራምዱ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በሥራ አፈጻጸማቸው የሚመዘኑበት፣ በዕድገትና ሥልጠና የሚበረታቱበትና የሚታገዙበት ኹኔታ ተመቻችቷል
- በተለያዩ ዓላማዎች ዙሪያ በሀ/ስብከቱ የሚንቀሳቀሱ መንፈሳውያን ማኅበራት በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እና ማኅበራት ማደራጃ ክፍል አማካይነት ይደራጃሉ፤ ክትትልና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፤ የክህነት አሰጣጡ ከአጥቢያ እስከ ሀ/ስብከት ጥብቅ ተዋረዳዊ ቁጥጥር ይደረግበታል
- በሀ/ስብከቱ ተጧጡፎ ከቆየው ብልሹ አሠራር አንጻር ራሳቸውን ከገቢያቸው በላይ ያበለጸጉ ግለሰቦች በዝውውርና ከደረጃ ዝቅ በማድረግ ሳይኾን በግልጽ የሚጠየቁበት የመማማርያና እርምት መድረክ እንዲመቻች እየተጠየቀ ነው
- በቀጣይ÷ አብያተ ክርስቲያን ደረጃ ይወጣላቸዋል፤ የሰው ኀይልና ደመወዝ ስኬል፣ ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር ለአብያተ ክርስቲያን በሚወጣው ደረጃ መሠረት ወጥነት ይኖረዋል፤ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የተመጣጠነ አቅም ባላቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲደራጁና በውድድር መንፈስ እንዲሠሩ ይደረጋል
- እስከ ጥቅምት ወር ፳፻፮ ዓ.ም በሚቆየው የሽግግር ወቅት የሚቀሰሙ ተሞክሮዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፤ ለዘላቂው የሀ/ስብከቱ አደረጃጀትና አሠራር የሚያገለግሉ ፖሊሲዎችና ዝርዝር የሥራ መመሪያዎች ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ዝግጅቱ ከሕገ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዐዋዲው ማሻሻያ ቀድሞ/ጎን ለጎን መካሄዱ እንዴት ይታያል?
ዝርዝሩ ይቀጥላል