ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ በሐምሌ ወር አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ከአፍሪካ ኅብረት አመራሮች ጋር እንደሚመክሩ፣ ዋይት ሀውስ አስታወቀ፡፡

በሥራ ላይ ያለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ጎብኝቶ አያውቅም፡፡

የበርካታ አገሮች መሪዎች ይታደሙታል ተብሎ የሚጠበቀው ከሐምሌ 5 እስከ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚካሄደው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ጉባዔ ባራክ ኦባማ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይሁንና የዋይት ሀውስ መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ለዚሁ ጉባዔ ስለመምጣታቸው የሚያወሳው ነገር የለም፡፡ 

ጉባዔው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀውን የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብን ይተካል የተባለለት ዘላቂ የልማት ግቦችን ለመተግበር የሚያስችሉ የፋይናንስ ምንጮች ላይ ይመክራል፡፡ ይህንኑ ጉባዔ ለመከታተል ከ5,000 በላይ የአገር መሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የግል ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበራትና የሚዲያ ተወካዮች አዲስ አበባ እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡

የዋይት ሀውስ የፕሬስ ጉዳዮች ኃላፊ ጆሽ ኧርነስት የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት አሜሪካ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከርና በአፍሪካ ኢንቨስት የማድረግ ቁርጠኝነት ያላት መሆኑን ለማሳየት ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮችና ዜጎች ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲያመጡ፣ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲገቡና የደኅንነት ይዞታቸውን እንዲያጠናክሩ አሜሪካ የምታደርገው ጥረት አካል እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡ 

ፕሬዚዳንት ኦባማ በኬንያ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ጉባዔ ከተከታተሉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ታውቋል፡፡ የባራክ ኦባማ አባት ኬንያዊ ቢሆኑም ይህ ጉዟቸው እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ ነው፡፡   

 

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ምስማር ለማምረት ከሚያገለግለው ስታፋ ብረት (ዋየር ሮድ) ለዓመታት የቆየውን ታሪፍ ከለላ እንዲነሳ ማድረጉ ውዝግብ አስነሳ፡፡

የታሪፍ ከለላው መነሳት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የምስማር ንግድ፣ አንድ ኩባንያ ብቻ በሞኖፖል እንዲቆጣጠር በር ከፍቷል የሚሉ ምስማር አምራች ኩባንያዎች ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወስደውታል፡፡

ስታፋ ብረት ላይ የታሪፍ ከለላ በመነሳቱ ቅሬታቸውን ካቀረቡት 76 ፋብሪካዎች መካከል 46 የሚሆኑት ትላልቅ የምስማር ፋብሪካዎች፣ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኘው ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከምስማር አምራቾች በተጨማሪ በታሪፍ ከለላ መነሳቱ በትግራይ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ለውኃና ለአፈር ጥበቃ የሚያገለግለው ጋብዮን (በሽቦ የተሠራ መረብ) የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ይገኙበታል፡፡ 

ሚኒስቴሩ ሚያዚያ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባስተላለፈው መመርያ የስታፋ ብረት ከውጭ ሲገባ፣ 20 በመቶ የጉምሩክ ታክስና አምስት በመቶ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ እንዲከፈል አድርጓል፡፡ ሚኒስቴሩ እዚህ ውሳኔ አይ የደረሰው በአገር ውስጥ ስታፋ ብረት በብቸኝነት የሚያመርተው ስቲሊ አርኤምአይ ኩባንያ ለመጥቀም ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ምስማር አምራቾች ስታፋ ብረት ከስቲሊ አርኤምአይ በመግዛት ሥራቸውን እንዲያካሂዱ ለማድረግ የታሪፍ ከለላውን አንስቷል፡፡

ቅሬታ አቅራቢ ምስማር አምራቾች የተላለፈው መመርያ አንዱን ወገን ማለትም ጥሬ ዕቃውን ማምረት ለጀመረው ስቲሊ አርኤምአይ ኩባንያ ለመደገፍ የወጣ እንጂ ፍትሐዊነት የሌለው አሠራር ነው በሚል ይተቻሉ፡፡

“በስታፋ ብረት ላይ የሁለተኛ ደረጃ ታሪፍ ከለላ መነሳቱን ይበልጥ አስቸጋሪ ያደረገው የስታፋ ብረት አገር ውስጥ ማምረት የጀመረው እስቲሊ አርኤምአይ እህት ኩባንያ የሆነው አስመን ላለፉት 15 ዓመታት የምስማር ገበያን 65 በመቶ ድርሻ የያዘ በመሆኑ ነው፤” በማለት ቅሬት አቅራቢ ኩባንያዎች ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ ተገልጿል፡፡

ስቲሊ አርኤምአይ እና እህት ኩባንያው አስመን የስታፋ ብረትና የምስማር ዋጋ በሞኖፖል ለመወሰን እንዲችሉ ከፍተኛ አቅም ይሰጣል በማለት፣ የሚኒስቴሩን መመርያ አግባብነት የሌለው እንደሆነ የቅሬታ አቅራቢዎቹ ደብዳቤ ጨምሮ ያስረዳል፡፡ የስቲሊ ኤምአርአይ የኦፕሬሽንና ፖሊሲ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ለማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ስታፋ የሚሸጥበት ዋጋ ለሁሉም አምራች ኩባንያዎችም ሆነ ለእህት ኩባንያ አንድ ነው በማለት ምሳሌ ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡ ደብዳቤው ሚኒስቴሩ መመርያውን ካስተላለፈ ከጥቂት ወራት በኋላ ጉዳዩን የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ እንደነበርም ያስታውሳል፡፡ ኮሚቴውን የንግድ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አህመድ ኑሩ የመሩ ሲሆን፣ ኮሚቴው ባካሄደው ጥናትም ስቲሊ አርኤምአይ የስታፋ ብረት በበቂ መጠንና በሚፈለገው ጥናት እያመረተ መሆኑን፣ የቀረበው የሞኖፖሊ ሥጋትም “በአሠራር ማስወገድ እንደሚቻል” በመጥቀስ የታሪፍ ማሻሻያው ተገቢ መሆኑን አስተያየት ሰጥቷል፡፡

የብረት አምራቾች ግን ይህንን ሐሳብ በፍፁም አልተቀበሉትም፡፡ የታሪፍ ከለላው የተነሳው ስቲሊ አርኤምአይን ሆን ብሎ ለመጥቀም ነው በማለት መከራከርያቸውን ያቀርባሉ፡፡ ይህ ውሳኔ የኢንቨስትመንት ፈቃድና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ በተሰጣቸው በርካታ አምራቾች ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖ አልታየም፡፡ ስቲሊ አርኤምአይ ከሚያመርታቸው ልዩ ልዩ ምርቶች አንዱን በመነጠልና በአንዱ ምርት ላይ ያነጣጠረና በርካታ አምራቾችን ከገበያ የሚያስወጣ ነው በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይናገራሉ፡፡ 

የበለጠ እሴት ጭማሪ ያለውና ከፍተኛ የሰው ኃይል የሚቀጥረው የምስማር ፋብሪካ ከውጭ በሚያስገባው የስታፋ ብረት ላይ የተነሳው የታሪፍ ከለላ በጥልቀት ያልታየና በጥናት ላይ ያልተመሠረተ ነው በማለት፣ ቅሬታቸውን በጽሑፍ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅርበዋል፡፡ 

የምስማር ፋብሪካዎቹ እንደሚሉት የታሪፍ ከለላ በመነሳቱ ስታፋ ብረት ከውጭ በማስገባት ምስማር ማምረት አዋጭ አይደለም፡፡ ከስቲሊ አርኤምአይ ስታፋ ብረት ገዝቶ ምስማር ማምረትም አዋጭ አይደለም ይላሉ፡፡

አዋጭ ያልሆነበት ምክንያት ሲያብራሩ፣ በተወሰደው ዕርምጃ የጥሬ ዕቃ መግዣና የምርቱ የመሸጫ ዋጋ በዋናነት የሚወሰኑት ስቲሊ አርኤምአይ እና እህት ኩባንያው አስመን ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ለብዙ ዓመታት በሥራ ላይ የቆዩ የምስማር አምራች ኩባንያዎች፣ ‹‹ከሥራ እንድንወጣ እያደረገን ነው›› በማለት ቅሬታቸውን አስተጋብተዋል፡፡ “በተቀመጠው አቅጣጫ ጥሬ ዕቃ ከስቲሊ በመግዛት ሥራችንን እናስቀጥል ብለው የጀመሩ አንዳንድ የምስማር ፋብሪካዎችም ቢሆኑ፣ በዋናነት በስቲሊና በአስመን እየተፈጠረ ባለው የዋጋ መዛባት ሥራውን በተገቢው መንገድ ለመቀጠል ተቸግረዋል፤” በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በደብዳቤ ይገልጻል፡፡ 

በአቶ አህመድ የሚመራው ኮሚቴ በምስማር አምራቾቹ የቀረበው የሞኖፖሊ ሥጋት በአሠራር ማስወገድ እንደሚቻል የገለጸ ቢሆንም፣ የሞኖፖሊ ሥጋት እንዴት እንደሚወገድ የሚገልጽ የአሠራር ዘዴ ግን አያይዞ አላቀረበም በማለትም ይወቅሳሉ፡፡ 

“በስታፋ አምራቹ ስቲሊ አርኤምአይ እና በምስማር ምርት ትልቁን ድርሻ በሚያመርተው እህት ኩባንያው አስመን የሞኖፖል አሠራሮች ለማስወገድ የሚያስችል አሠራር ተቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ ሲገባ፣ አንድ ወገን ብቻ በማየት የተወሰነው ውሳኔ በዋጋ ላይ እንደተጠበቀው ከፍተኛ ችግር ያስከተለ መሆኑንና እንዲያውም አንዳንድ ፋብሪካዎች ከነጭራሱ እስከ መዘጋት ደርሰዋል፤” በማለት ቅሬታ አቅራቢ የምስማር ፋብሪካዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባቀረቡት ቅሬታ ይገልጻሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት ስቲሊ አርኤምአይ በስታፋ ብረት የነበረው ከለላ ሲነሳ፣ የምስማር ፋብሪካዎች የስታፋ ብረት ከውጭ ሲያስገቡና የምስማር ነጋዴዎች ያለቀለት ምስማር ከውጭ ሲያስገቡ የሚከፍሉት የጉምሩክ ቀረጥና ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ተመሳሳይ ስለሚሆን፣ ስታፋ ብረት ከውጭ አስገብቶ ምስማር ከማምረት ይልቅ ያለቀለት ምስማር በተመሳሳይ ቀረጥ ከውጭ አስመጥቶ መሸጥ የቀለለ እንደሆነ፣ የምስማር አምራቾች ከአስመጭዎች የተሻለ ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

ነገር ግን የጥናት ቡድኑ “ይህ ጉዳይ ወደፊት ሊጠና ይገባል” በማለት ጉዳዩን በቀላሉ እንዳለፈውም ይጠቁማሉ፡፡ በምስማር ፋብሪካዎች የተነሱት ሥጋቶችና ችግሮች ከከለላው መነሳት ጋር ተያይዘው ካልተመለሱ የታሪፍ ከለላ ብቻ ማንሳቱ ለአንዱ ወገን ያደላ መሆኑን፣ ይህም የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ፍትሐዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ ነው በሚል ኩባንያዎቹ የቅሬታቸውን ስፋት በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ የተወሰደው ዕርምጃ ያስገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው ፋይዳ አንፃር ሲታይ ያስከተላቸው ችግሮች ሚዛን የደፉ በመሆናቸው፣ ወደ ተግባር ሲለወጥም የተገመቱ ሥጋቶችን ለመከላከል አስቸጋሪ ስለሆነና እንዲሁም በውሳኔው ችግሮች ሲከሰቱ ለመፍታት የሚያስችል ሥርዓት አብሮ ያልታየ በመሆኑ፣ በብዙ መመዘኛዎች ሲታይ በስታፋ ብረት ላይ የተነሳው ከለላ እንደገና ሊጠና ይገባል በማለት ምስማር አምራች ኩባንያዎች ቅሬታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅርበዋል፡፡

ስቲሊ አርኤምአይ በመስከረም 1997 ዓ.ም. በ486 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የብረት ማቅለጥና የሮሊንግ ፋብሪካ በማቋቋም ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ኩባንያው አቅሙን በማሳደግ በአገር ውስጥ የሚመረት ስታፋ ብረት ባለመኖሩ በ726 ሚሊዮን ብር ወጪ ታኅሳስ 2006 ዓ.ም. አዲስ ፋብሪካ አቋቁሟል፡፡ ድርጅቱ በአጠቃላይ ሦስት ፋብሪካዎች አሉት፡፡ እነዚህ ፋብሪካዎች በዓመት 30 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም የአርማታ ብረትና ስታፋ ብረት ያመርታሉ፡፡ ስቲሊ አርኤምአይ ያቋቋመው አስመን ኩባንያ በበኩሉ ስታፋ ብረት በመጠቀም የተለያዩ ምስማሮችን ያመርታል፡፡ ስቲሊ አርኤምአይ ለሪፖርተር በሰጠው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ የግል ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪ ልማት ቀድመው ለሚገቡ ባለሀብቶች መንግሥት ሰፊና ጠንካራ ድጋፍ እንዳደረገለት አስረድቷል፡፡ “ይህ ከለላ የተሰጠው ለስቲሊ ሳይሆን ለብረት አምራች ኢንዱስትሪ ስለሆነ የኋልዮሽ የእሴት ጭማሪ አድርገው መዋለ ንዋያቸውን ላፈሰሱ ባለሀብቶች የተሰጠ ነው፤” በማለት አቶ ተፈራ ገልጸዋል፡፡ “በዚህ መሠረት ወደ ኢንዱስትሪው ቀድመው ለሚገቡም ሆነ የምርት ሰንሰለቱን ጠብቀው ለሚሠሩ፣ የታክስ ከለላና ሌሎችንም ማበረታቻዎች ይሰጣል፤” በማለትም መንግሥት ያደረገለትን ድጋፍ አስረድቷል፡፡ ኩባንያው በመቀጠል መንግሥት እነዚህን ማበረታቻዎች የሚሰጠው ባለሀብቶች በእነዚህ ማበረታቻዎች ተበረታተው በሰፊው ወደ ልማቱ እንዲገቡና በአገሪቱ የተያዘው የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ እንጂ፣ የተወሰኑ ሰዎችን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት አይደለም ብሏል፡፡ 

ኩባንያው የቀረበበትን ክስ በሚመለከት እንደገለጸው፣ ከአሁን በፊት ስታፋ ብረት ከሚጠይቀው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ፣ ዕውቀትና ከፍተኛ የካፒታል መጠን ምክንያት በአገሪቱ የማይመረት ነበረ፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ስቲሊ አርኤምአይ ለአርማታ ብረት እንደተደረገው ሁሉ የስታፋ ብረት በአገር ውስጥ በመመረቱና ምንም እንኳ ስታፍ ብረት ከአርማታ ብረት ጋር ሲነፃፀር የሚጠይቀው የማምረቻ ሒደትና የሚፈጀው ወጪ ከፍተኛ ቢሆንም፣ ለአርማታ ብረት ከተሰጠው የታክስ ከለላ እኩል ከለላ እንዲሰጠው መንግሥት ወስኗል፡፡ ይህም ምስማር ፋብሪካዎች ያቀረቡት በዘርፉ ውስጥ ለአንድ ዓይነት ምርት ብቻ ከለላ ተሰጥቷል የሚለው ትክክል አለመሆኑን ያስረዳል ሲሉ አቶ ተፈራ ተናግረዋል፡፡ 

“ይህ ማለት ከአሁን በፊት ለምስማር ጥሬ ዕቃነት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ሲገባ የነበረው የስታፋ ብረት ላለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ሲደረግለት የነበረው የታክስ ከለላ ተነስቶ ቀረጥ እንዲቀረጥበት አደረገ እንጂ፣ ከውጭ ማስመጣት አልተከለከለም፤”  በማለት የስቲሊ አርኤምአይ መረጃ ይተነትናል፡፡

“ይህ የመንግሥት ውሳኔ የስታፋ ምርት በከፍተኛና በብዛት አገር ውስጥ የሚመረት በመሆኑ ካለው የኢንዱስትሪ ፖሊሲና የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ቁጠባ ከማጎልበት አንፃር ተመልክቶ የወሰነው ጉዳይ ነው፡፡ ውሳኔውም የተሰጠው ለእኛ ድርጅት ሳይሆን ለምርቱ የተሰጠ ዕውቅና ነው፤” በማለትም አክሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአንድ ወገን ስቲሊ አርኤምአይ በሌላ ወገን ደግሞ በርካታ ምስማር አምራቾች በከፍተኛ ደረጃ በመወዛገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ውዝግብ ለመፍታት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያዳረጓቸው ጥረቶች ያልተሳኩ በመሆናቸው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ መንግሥት በመስከረም 2005 ዓ.ም. ባሳተመው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ሰነድ ላይ በተዘረዘረው መሠረት ልንስተናገድ ይገባል በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጉዳያቸውን መውሰዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

 

ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዛሬ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አቀወ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችሁ እሰሩልን›› ያሉ አስተዳዳሪዎች የፖሊስ እና የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት ወቀሱ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን እንደተቋም መወንጀል አትችሉም፤ ፖሊስ የእናንተ ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› /ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም/ የቅድመ ውይይት ምክክሩና ውይይቱ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን ማኅበረ ካህናትን፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮችን ሊያካትት ይገባል፡፡ (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፭ ቁጥር ፰፻፭፤ …

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በደቡብ ክልል አንድ የምርጫ አስተባባሪው አርብለት ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲም በምርጫ 2007 ዙሪያ የዛሬውን ጨምሮ 4 አባላቱና ደጋፊዎቹ መገደላቸውን አስታውቋል። በዚህ ሳምንት እንደተገደሉ ተቃዋሚዎች ከገለጿቸው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው አጠቃላይ ቁጥር ስድስት ደርሷል። በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የተገደሉት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ በትናንትናውለት በሁለት […]

ወደ ሚኒስቴሩ ካመሩት 25 አለቆች 20 ያኽሎቹ በዋና ሥራ አስኪያጁ በተደረገባቸው ጫና ያለፍላጎታቸው እንዲሔዱ መገደዳቸውን እየተናገሩ ነው በየሰንበት ት/ቤቶቹ የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ መነሣሣት ማኅበረ ቅዱሳንን ወንጅለዋል፤ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› /ኃይሌ ኣብርሃ/ ‹‹እንዴት አድርገን መከላከል እንዳለብን አሠልጥኑን እንጂ ስለ ሰላም መወያየት ምን ያደርግልናል?›› /የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ/ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን …

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ በ67 ዓመታቸው አረፉ ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ – ግንቦት 13 ቀን፣ 1983 ዓ.ም. የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት፤ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም አገር ለቀው ሲወጡ ዜናውን ያነበበው ጋዜጠኛ ነበር። • ስርዓተ ቀብራቸው ነገ ሰኔ 14 ቀን 2007ዓ.ም በፈረንሳይ ለጋሲዮን ጉራራ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 6፡00 ስዓት ይፈፀማል፡ መልክት ሼር በማድረግ ሀዘኑን አድርሱ፡፡ Filed under: NEWS

በባህርዳር ከተማ ትምህርታቸው ጨርሰው መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ወጣቶች ቦዞኔ እየተባሉ በጸጥታ አካላት ተገፈው ቤሻንጉል ወደሚገኘው የመንግስት እርሻ እንዲሰሩ መወሰዳቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ። ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ስራ ያላገኙት ወጣቶች እለታዊ ንሮአቸውን ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ስለተገኙ ብቻ በስርዓቱ ካድሬዎችና የፀጥታ ሃይሎች ቦዞኔ ተብለው እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ ምንም ዓይነት የምግብና የህክምና አቅርቦት […]

በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት ያልተፈለጉትን ለማሰናበት ተብሎ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ወታደሮች አገልግሎታችን ግዜ ያበቃ በመሆኑ መሰናበት አለብን በማለታቸው የተነሳ ስብሰባው እንደተቋረጠ ታወቀ። ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት- በሰሜን እዝ በክፈለ ጦሩ አዛዦች ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለና ብርጋዴር ጀነራል ማዓሾ በየነ የተመራው ስብሰባ ግንቦት 21 2007 ዓ/ም የተካሄደ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙዎች ዘንድ አስቂኝ ተብሎ የተተቸውን የ2007 ዓም ምርጫ ተከትሎ በኦሮምያ ብቻ ከ640 በላይ የመድረክ ደጋፊዎች ሲታሰሩ፣ 66 በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣7 አባለት በጥይት ቆሰልዋል፣ 2 አባላት ደግሞ መገደላቸውን መድረክ አስታውቋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በሺዎች እንደሚቆጠር መረጃዎች ያመለክታሉ። መድረክ እንዳለው በምርጫ 2007 ማግሥት በመድረክ …

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክረምቱ ወቅት 119 የሚሆኑ የብአዴን አባላት በድሬዳዋ ከተማ የደህንነት እና መረጃ መሰብሰብ ስልጠና ተሰጥቷቸው በክልሉ ከተሰማሩት መካካል አንዱ የሆነው ሰራተኛው እንደገለጸው፣ ማንኛውም ደህህነት ሰራተኛ የስለላ ሪፖርቱን ተክሌ ለተባለ የደህንነት ሰራተኛ ሲያቀርብ መቆየቱን ለኢሳት ተናግሯል። ስልጠናውን ከወሰዱት የደህንነት ስራተኞች መካከል አንዳንዶች በምስራቅ ጎጃም ደብረማርቆስ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ …

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የማህበራዊ ጥናት መድረክ በቅርቡ ባካሄደው ጥናት በአዲስአበባ የግሉ የጤና ዘርፍ ከፍተኛ የጥራት መጓደልን ይዞ የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ እየጠየቀ መሆኑን ገልጿል። ጥናቱ በአዲስአበባ ከሚገኙ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች መካከል በ34ቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን አገልግሎት ክፍያ (ዋጋን) በተመለከተ በመንግስት ሆስፒታሎች የካርድ ክፍያ አማካይ ዋጋ 5 ብር ሲሆን፣ በግል ክሊኒኮች …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት አካላት ናቸው ብሎአል። ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ብሎ እንደማይጠይቅም አስታውቋል። “ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምርጫው በአሳፋሪ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የመድረክ ደጋፊዎችን ቤቶች መቃጠላቸውን፣ መደብደባቸውንና ማሳደዳቸውን የአርባምንጭ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ በላካ ቀበሌ ብዙ ሰዎች አካላ ጎደሎ ሆነዋል፣ ቤቶቻቸውም ተቃጥሎባቸዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የቀበሌ አመራሮች ከሰኔ 15 በሁዋላ መግቢያችሁን ፈልጉ እየተባሉ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዳዊት ጉበዜ እና አዛውንት እናቱ ወ/ሮ …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ ቦርድ የታገደው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ማሙሸት አማረ ከሳምንታት እስር በሁዋላ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢያስተላልፍም፣ ውሳኔው ለሁለተኛ ጊዜ በፓሊስ ተጥሶ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ግንቦት 26/2007 ቦሌ የሚገኘው ችሎት አቶ ማሙሸት የቀረበባቸው ክስ እንደማያስከስሳቸው …

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ሰበብ አስባቦች የሚጣልብን ቅጣትና እገዳ ተገቢ አይደለም በሚል ሰኔ 8፣ 2007 ዓም ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ አድርገው የነበሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ሾፌሮች፣ ፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸውን የሚሰማ እና መፍትሄ የሚሰጥ አካል ይኖራል ብለው ሲጠብቁ፣ በተቃራኒው ከስራ መታገዳቸውን ተናግረዋል። ሾፌሮች እና ባለሃብቶች እንደሚናገሩት “የመንግስትን ትእዛዝ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

“ለማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለለሃገሬና ለነፃነት ነው፡፡ በአካል ብታሰርም ህሊናዬ አይታሰርም፡፡ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት፤ ጉዞአችን ጎርባጣ፤ መድረሻችን ነፃነት፤ ታሪካችን ዘላለማዊ ነው፡፡” ሳሙኤል አወቀ ፊስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ሰኔ 8/2ዐዐ7 ዓ.ም፡፡ ምስራቅ ጎጃም ግንደ ወይን 1978 ዓ/ም ተወልዶ – በህግ የዲፕሎማ እና ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ ሣሙኤል አወቀ የሠማያዊ ፓርቲ […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡ አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት […]

የሳሙኤል አወቀ ስርዓተ ቀብር ላይ ደርሰው ወደ ደብረማርቆስ ሲመለሱ የነበሩት ለቀስተኞች ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ወደ ደብረማርቆስ እንዳይመለሱ መታገታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለቀስተኞቹ በመኪና እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ከቢቸና ወደ ደብረማርቆስ 80 ኪሎሜትር አካባቢ የምትገኝ የትመን የተባለች ቦታ ላይ ፖሊሶች ያስቆሟቸው ሲሆን ‹‹በዚህ ሰዓት መንቀሳቀስ አትችሉም›› በሚል የሾፌሩን መንጃ ፈቃድ ከቀሙ በኋላ ለሚሊሻ አስረክበዋቸው ሄደዋል፡፡ ለቀስተኞቹ […]

Originally posted on ሐራ ዘተዋሕዶ:
በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔና በፓትርያርኩ ቡራኬ ያጠኑትን በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች ብለዋቸዋል የሰ/ት/ቤቶችን፣ ከኮብልስቶን ሥራ ይልቅ ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋት የሚነጥቁ በሚል ዘልፈዋል በሒሳብ አያያዝ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ያተኮረ ሥልጠና ተጀምሯል አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ሒሳብ ሹሞችን ጨምሮ የሀ/ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎች ይሳተፋሉ ያለበቂ ዝግጅት የተጀመረው ሥልጠና ከወሬ ያላለፈ በሚል በተሳታፊዎች ክፉኛ ተተችቷል ለሥልጠናው ድጋፍ ከንግድ…

በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔና በፓትርያርኩ ቡራኬ ያጠኑትን በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች ብለዋቸዋል የሰ/ት/ቤቶችን፣ ከኮብልስቶን ሥራ ይልቅ ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋት የሚነጥቁ በሚል ዘልፈዋል በሒሳብ አያያዝ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ያተኮረ ሥልጠና ተጀምሯል አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ሒሳብ ሹሞችን ጨምሮ የሀ/ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎች ይሳተፋሉ ያለበቂ ዝግጅት የተጀመረው ሥልጠና ከወሬ ያላለፈ በሚል በተሳታፊዎች ክፉኛ ተተችቷል ለሥልጠናው ድጋፍ ከንግድ ባንክ የተገኘው ብር …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ለመብት የሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና የጸረ ሽብር ግበረሃይል አባላት በከተማዋ ተገኝተው እጃቸው አለበት ብለው የጠረጠሩዋቸውን የቴፒ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 7 ፖሊሶችን ይዘው አስረዋል። ባለስልጣኖቹ የከተማውን ህዝብ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በነጻነት እጦት እየተሰቃየ መሆኑንና ወጣቶች እርምጃ የሚወስዱት ከዚህ ተነስተው …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንት በፊት አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል በቡርካባ ግዛት ጃሚዮ በሚባል ቦታ ላይ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ከ30 በላይ ወታደሮችን ከገደለ በሁዋላ፣ በርካታ ቁስለኞች ሞቃዲሹ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ቁጥር ሁለት ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። አሚሶም በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የሰፈረው የአፍሪካ ህብረት ጦር በአልሸባብ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በጋምቤላ እርሻ ስራ ተሰማርተው የሚፈለግባቸውን የመሬት ኪራይ እዳ ባልከፈሉ 150 ባለሀብቶች ላይ ያወጣው የማሳሰቢያ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ የጋምቤላን መሬት የተቀራመቱት ከ90 በመቶ የሚልቁት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከ2006 እስከ 2007 ሰኔ ወር ድረስ ያለባቸውን ውዝፍ እዳ አጠቃለው እንዲከፍሉ በወጣው የማስጠንቀቂያ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ አንድ ተጀምሮ ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ ከፍተኛ አመራሮችን፤አዛዦችን እንዲሁም ተራ የፖሊስ አባሎችን አካቷል። ከጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የግምገማው ይዘት በፖሊስ ስነምግባር ዙሪያ ነው። በግምገማው ወቅት አንድ ባለ ሳጅን ማዕረግ ያለውና አንድ ኮንስታብል ፖሊስ በስልካቸው ውስጥ የግንቦት ሰባት፤የሰማያዊ ፓርቲና የሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶች መረጃዎች በስልካቸው ውስጥ …

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ 2007 ቅስቀሳን ተንተርሶ በህዝቡ ዘንድ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢህአዴግ፤ በከተማዋ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች ለረዢም አመታት ለኖሩ የይዞታ ባለመብቶች ከምርጫው በፊት ሰጥቶት የነበረውን በባለ ቀለም የብአዴን አርማና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መልሶ በመውሰድ ውሳኔውን ለመሻር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ “በየክፍለ …

ጴትሮስ አሸናፊ በቅዱስ መጽሐፍ በአለማችን ረጅሙን እድሜ ማቱሳላ( 969 ዓመት )መኖሩን አንብበናል። (ዘፍ 5፣27) ከዚያም ለጥፋት ውሃ ምክንያት በሆነው የሰው ኃጢአት ምክንያት 120 መድረሱን ብናነብም ይስሐቅ 180 ዓመት መኖር ችሏል። ከዚያም ወርዶ 70 ከበዛም 80 ዓመት ሲሆን ይህንን ካለፈ ትርፉ ድካምና መከራ እንደሆነ ነግሮናል። «የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና […]

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአረና ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው አምዶም ገብረስላሴ በፌስ ቡክ ገጹ እንደጻፈው ፣ የ48 አመቱ አቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገድለዋል። አቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ …

(ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፲፤ ረቡዕ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደር እና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ አስተምህሮ እና ሥርዐት እንዲጠበቅ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ውሳኔ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ አስታወቀ፡፡ የሰንበት ት/ቤቶቹ፣ በአማሳኝ የአስተዳደር ሓላፊዎች እና በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ …

አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ […]

ባሳለፍነው እሁድ ናይሮቢ ኢስሊ የተበለ ቦታ የከተሙ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰማራቸው ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ግለሰቦቹን በተመለከተ ሲያቀርቡት የነበረው ጥቆማ በመጨረሻ ሰሚ ጆሮ በማግኘቱ የኬንያ የጸረ ሽብር ግበረ ሀይል ግለሰቦቹን ከያሉበት ለቃቅሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ስደተኞቹን አስደስቷል፡፡ታሳሪዎቹ በቀጣዩቹ ቀናቶች ፍርድ ቤት […]