በደቡብ ኢትዮጵያ የመድረክ አባል ተደብድበው መገደላቸውን ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በደቡብ ክልል አንድ የምርጫ አስተባባሪው አርብለት ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲም በምርጫ 2007 ዙሪያ የዛሬውን ጨምሮ 4 አባላቱና ደጋፊዎቹ መገደላቸውን አስታውቋል። በዚህ ሳምንት እንደተገደሉ ተቃዋሚዎች ከገለጿቸው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው አጠቃላይ ቁጥር ስድስት ደርሷል። በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የተገደሉት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ በትናንትናውለት በሁለት […]
ሌላስ ምን እናድርግ ? ? ?
++++++++++
እኛ መጋደልን:-
ስላየነው ሞተን፤
ስንቱ ተሰውቷል እኛ ብቻ ቀርተን::
ይህን አገር ያውቃል አለምም ሰምቶታል:-
ታሪክም በሰው-ደም ለትውልድ ፅፎታል::
እንደገና ይሄው ጉጅሌዎች ደግሞ;-
ሳይማሩ ቀርተው ደደቡ ፈፅሞ::
እንኳንስ ሰው ቢሞት;ቢጋደልም ሕዝቡ:-
ደንታ የላቸውም ብር ብቻ ይሰብስቡ::
የደም-እምባ ሲፈስ እኛ ስንጠርግ;-
እንዼት እንደሚድን:-
ሌላስ ምን እናድርግ::
በባንዳዎች እንዳናመር ሕዝቡ ላመፅ እንዳያብር፤
ሰላም ይቅደም ተብለን በአድርባይ ትግሉን ስንቀብር።
ሃያ አራት ዓመታት ተቆጠረ፣መቶ በመቶ ተዘርፈን፤
የስቃይ ግድያ ጀምሮ የታጋይ ሬሳ ታቅፈን።
እንግዲህ ምን ቀረ ያልሆነ፣”እግሬን እየበላኝ ነው…”ካላልን፤
ኢትዮጵያዊነትን-ዝምታ-ውጦት ለዜግነታችን ካልታገልን።
የሰላም መንገድ ለማይገባው ፣በሥልጡንነት ለማያይ፤
መግደል ምላሹ ለሆነ፣በቅንነት ለማይወያይ፤
እስከመቼ ነው እንዲገለን የምንፈቅደው? ? ?
ሕዝብ እንዳያምፅ በሰላም ሥም የምንወደው።
ዝም የምንል ሰልፍ ብቻ፤
እንሙት ሆነን መጫወቻ?
ዛሬም ላመፅ « በቃ!!! »አትሉም፤
በአንድነት ሥም አትምሉም? ? ?
የሕዝብ አመፁ ተነስቶ፣የታጠቀው እንዲጠርግ፤
በተጠንቀቅ ከመጠበቅ፣
እኛ ሌላስ ምን እናድርግ? ? ?