ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጣና ሞባይል የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ደንበኛ ከሆነው ከቻይናው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ዜድ.ቲ.ኢ  ጋር በጋራ ለመስራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በ2003 ዓ.ም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ በባህርዳር ከተማ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ማምረቻ ፋብሪካ በመክፈት ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ፋብሪካው ባልታወቀ ሁኔታ  ከቀጠራቸው ሠራተኞቹ መካከል ወደ 70 የሚጠጉትን …

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 …

ምሥራቅና በደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ በኤድስ ላይ ተጨብጧል የሚባለውን ግዙፍ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መርኃግብር ባለሥልጣናት አሞግሰውታል፡፡

ከኤድስ ጋር የተያያዘው የሞት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን እና ለኤችአይቪ እየተጋለጠ ያለው ሰው ቁጥርም በብዙ እየወረደ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ጠቁሟል፡፡

ይህ ክስተት መድኃኒት በብዛት የመገኘቱ ውጤት ነው የሚለው ይህ ሪፖርት ፈተናዎቹ ግን እንዳሉ እንደሚቀጥሉ አሳስቧል፡፡

ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ላይ በተካሄደው የአህጉሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከጋምቤላ በስተቀር በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች የኤችአይቪ ሥርጭት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር …

የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ የጀመረው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዜጎች ህገ መንግስቱን በመጨፍለቅ በጸረ ሽብርተኝነት ሽፋን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣ጋዜጠኞችንና የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የሚቃወሙ ዜጎችን በሽብርተኝነት በመወንጀል ወህኒ እያወረደ ያለውን የጸረ ሽብር አዋጅ በመቃወም እንዲሰረዝ ፊርማቸውን በፓርቲው ጽ/ቤት በመገኘት በተዘጋጀው የፊርማ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ለህዝቡ ማሰራጨት […]

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከሀገር እንዳይወጡ በቅርስ ጥበቃ ረገድ መስሪያ ቤታቸዉ ከሌሎች ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለዶቼ ቬለ ገለጹ።

በግጥም ምሽት የኪነጥበብ አድናቂዎችን ሲያዝናኑ ወራት አስቆጥረዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ የካንሰር ታማሚ ህፃናትን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ስለበሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ ለማስፋት እየጣሩ ነዉ።

በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።

የዛሬ ዓመት በቁልቢ በዓል ሲባርኩን የነበሩት የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በአፀደ ስጋ ተለይተውን በሌሉበት አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተገኙበት የቁልቢን ባዕልን አክብረናል፡፡ በቁልቢ ገብርኤል ቅፅር ጊቢ ከአውደ ምዕረቱ ጀርባ ባለው መግቢያ ተሰቅለው ከነበሩት የቀድሞው ፓትርያርክ ምስሎች አንደኛው በፍፁም ደብዝዞ ሌላኛው በመስታውት ተሸፍኖም ቢሆን ግርማ ሞገስ ርቆት ቢታይም በሌላ በኩል ደግሞ በረጅም ተፅፎ የነበረውን የማዕረግ ስም […]

በመቀሌ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ መንግስት እየሞከረ ነው በመቀሌ ከተማ የፊታችን እሑድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ለሚደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት ከፍተኛ አመራር አቶ የማነ አበራ ስልክ ተቀምተዋል፡፡ የመቀሌ የፀጥታ ኃይሎችና ደህንነቶች ከአቶ የማነ ከቀሙት ስልክ ላይ የተመዘገቡ የግል አድራሻዎች መዝግበው ሰጥተዋቸዋል፡፡ አመራሩ ለሰላማዊ ሰላፍ ቅስቀሳና ማስተባበር ስራ ወደስፍራው ያቀኑ ሲሆን የከተማው የፀጥታ ኃይሎችና […]

ከ15 – 20 ዓመት በሚያስቀጡ ቅርስን የማፍረስ፣ ከባድ የእምነት ማጉደል እና ሐሰተኛ ሰነድ የመፍጠር የወንጀል ተግባራት ይፈለጋሉ ‹‹ተራማጁ እና ልማታዊው›› በሚል የሚሞካሹት ቆሞሱ በመንበረ ጵጵስና ብፁዕ አቡነ ቄርሎስን የመተካት ምኞት ነበራቸው፤ በቀድሞው ዘመነ ፕትርክና ሁለት ጊዜ በሲሞናዊ መንገድ ለኤጲስ ቆጶስነት ለመታጨት ሞክረዋል፤ በውጭ ጉዟቸው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውን ሲኖዶስ ማኩረፊያ አድርገውት ይኾን? ሙሰኝነታቸውንና የአስተዳደር …

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


በከበደ ሚካኤልኛ እንዲህ ይተረካል፡፡
አንዲት ግልገል በቅሎ እናቷን እንዲህ ብላ ጠየቀቻት፡፡ ‹‹እማዬ እኔ ግን ማነኝ››
እናቷም ገረማትና ‹አንቺማ በቅሎ ነሽ፤ ግን ለምን ጠየቅሽኝ››
ግልገሏም ጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ‹‹መጀመሪያ ግን አህያ ነበርኩ ወይስ ፈረስ›› አለቻት፡፡ እናቲቱም አንገቷን ነቅንቃ፡፡ ‹‹እንስሳ ነሽ ልጄ፤ እንስሳ፡፡ ፈረስም አህያም እንስሳ ነው፡፡ ስንፈጠር እንስሳ ነበርን፡፡ የቤት የዱር፣ የሸክም የግልቢያ፣ የእርሻ የሜዳ፣ የንጉሥ የባሪያ የሚለው በኋላ የመጣ ነው፡፡ አዳምኮ ሲፈጠር ቤት አልነበረውም፡፡ ስለዚህ የቤት እንስሳ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ሁላችንም ይህቺን ምድር እንደልባችን እንጠቀምባት ነበር፡፡ ነገር የመጣው በኋላ ነው፡፡ ለመኖር የሚደረግ ትግል ነው ይህንን አሁን ያለንበትን ሁኔታ የፈጠረው፡፡››
‹‹ጓደኛዬ የአንቺ አያቶች ጨቁነውናል አለኝ፡፡››

 ‹‹እንዴት አድርገው ነው የጨቆኑት፤ ለመሆኑስ የአንቺ አያቶች ስንት ናቸው? እርሱ የተነገረውን ብቻ ነው የሚያውቀው፤ ያልተነገረውስ? ከታሪካችንኮ በጣም ጥቂቱ ነው የተጻፈው፤ ከተጻፈውም በጣም ጥቂቱ ነው የተነገረው፡፡ ባልተጻፈው ታሪካችን ውስጥ ማን ምን እንደነበረ ማን ያውቃል? ለምሳሌ በሀገረ እሥራኤል አህዮች እጅግ የሚወደዱ የቤት እንስሳት ነበሩ፡፡ ነገሥታቱም፣ ካህናቱም፣ ነቢያቱም ዘመኑ ዘመነ ሰላም ሲሆን በአህያ ነው ይሄዱ የነበሩት፡፡ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ የተሰደደችው በአህያ ነው፡፡ በጥንታውያን ግብጾች ዘንድ አህያ የመኳንንትና የነገሥታት ሀብት ማሳያ ነበር፡፡ የናርማር ወይም  ሖር – አሃ መቃብር እንደሆነ በሚታመነው ቦታ ላይ በተደረገ ቁፋሮ አህዮች ከነገሥታቱ ጋር በክብር ተቀብረው ተገኝተዋል፡፡ በዚያ ጊዜ አህዮች የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየተመገቡ፣ በቤተ መንግሥቱም እየተሸለሙ ኖረዋል፡፡ በሌላው ዘመን ደግሞ ይህንን ፈረሶቹ ወስደውታል፡፡››

‹‹ወደ ኋላ ተመልሰሽ ሁሉን እንስሳት ብታያቸው ታሪካቸው እንደዚሁ ነው ልጄ፡፡ በዘርሽ አትጨቁኝም፤ በዘርሽም አትጨቆኝም፡፡ የጭቆና መሠረቱ ኃይልና ሥልጣን ነው፡፡ አቤልን የገደለውኮ ቃየል ነው፡፡ የአንድ ማኅፀን ልጆች ናቸውኮ፡፡ ቃየል አቤልን የገደለው ለጥቅም ሲል ነው፡፡ እስኪ የሰዎችን ታሪክ እይው አፍሪካውያንኮ በራሳቸው በአፍሪካውያን ይጨቆኑ ነበር፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ሰው መሰሎቹን ይሰበስብና ሌሎቹን የሀገሩን ልጆች ይጨቁናል፡፡ መጀመሪያ የገዛ ወገኖቻቸውን ለዐረቦች በባርነት ሲሸጡ የነበሩት የሀገራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ አፍሪካውያን በባርነት ተሽጠው አሜሪካ ሲሄዱ ደግሞ ነጮቹ ጥቁሮቹን መጨቆን ጀመሩ፡፡ አየርላንዳውያን በእንግሊዞች መከራቸውን አይተዋል፡፡ ዓረቦች በዓረቦች ተሰቃይተዋል፡፡
አየሽ ቤተ መንግሥቱ ላይ ስትቀመጭ ሌላውን ለማግለል ሳጥን ትከፍቻለሽ፤ ከዚያ ሁሉንም በየሳጥኑ ታስቀምጭዋለሽ፡፡ የእምነት፣ የዘር፣ የመልክ፣ የአካባቢ፣ የቋንቋ ሳጥኖችን ከፍተው ሁሉንም እዚያ ስላስቀመጧቸው ተቀማጮቹ ሳጥኑን እንዳለ ተቀበሉት፡፡ ማንነታቸውም አደረጉትና ሳጥኑን ለማስቀረት ከመታገል ይልቅ ራሳቸውን ብቻ ከሳጥኑ ለማውጣት ይታገሉ ነበር፡፡ በሳጥኑ ዛሬ አህዮች ይገቡበታል፤ ነገ ፈረሶች፣ ከነገወዲያ ግመሎች፣ ከዚያም በጎች፣ ከዚያም ፍየሎች እየገቡበት ይቀጥላል፡፡ እኛም ዛሬ ያለሳጥን መኖር ከማንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ እኔን ሲያገኙኝ እንስሳ መሆኔን አይደለም የሚያዩት፤ የትኛው እንስሳ? ይላሉ፡፡ – ፈረስ፡፡ በዚህ አያቆሙም፡፡ ከዚያ ደግሞ የትኛው ፈረስ? የዱር ወይስ የቤት? ይቀጥላል፡፡ -የቤት፡፡ ለጭነት ወይስ ለግልቢያ? መቋጫ የለውም ልጄ፡፡ በትልቁ ሳጥን ውስጥ ራሳችን የሠራናቸው ትንንሽ ሳጥኖችም አሉ፡፡ በእነዚያም ውስጥ ሌሎች ትንንሽ ሳጥኖች አሉ፡፡››
‹‹ ለአንድ የገጠር ጉዞ በእኔ ላይ ይሄድ የነበረ አንድ ሰው ሲናገረው የሰማሁትን ታሪክ ልንገርሽ፡፡ ሰውዬው የከባድ መኪና ሾፌር ነበረ፡፡ ድሮ አሰብ እየተመላለሰ ዕቃ ይጭን ነበር፡፤ አንድ ጊዜ ወደ አሰብ ሲሄድ በረሃው ላይ መኪናው ይበላሽበታል፡፡ ከዚያም እዚያው ማደር ስለነበረበት ለምግቡ የሚሆን ፍየል ከአካባቢው የአፋር ሰው ይገዛል፡፡ አፋሩ ሰውዬው ፍየሏን መሸጥ ብቻ ሳይሆን አርዶ፣ ጠብሶ ያቀርብለታል፡፡ ሾፌሩ ምግቡን እየበላ የሸጠለትን የአፋር ሰው ‹‹እንግዲህ ትቼህ መብላቴ ነው፤ እንብላ እንዳልልህ የክርስቲያን ሥጋ አትበላም ብዬ ነው›› ይለዋል፡፡ አፋሩ ሰውዬ ይገርመውና ‹‹እኔው አዋልጄ፣ እኔው አሳድጌ፣ እኔው አርጄ፣ እኔው ጠብሼ ያመጣኋትን ፍየል ምንጊዜ ክርስቲያን አደረግካት?›› አለኝ ብሎ ሲያወራ ሰማሁት፡፡ አየሽ ሌላን ማግለል ስትፈልጊ የሆነ ነገር ትፈጥሪያለሽ፡፡ ማቅረብም ስትፈልጊ እንደዚያው፡፡››
‹ብዙ ዓይነት ነጻ አውጭዎች አሉ፡፡ እኔ አሁን የፈረስ ነጻ አውጭ ውስጥ ልግባ ወይስ የአህያ? ወይስ የበቅሎ?›› አለቻት ግልገሏ፡፡
‹‹የእንስሳት ነጻ አውጭ ካለ እዚያ ግቢ፡፡ አንቺ እንስሳ ነሽ፡፡ የቀረው ከመኖር የመጣ ስም ነው፡፡ እንስሳት ሁሉ ነጻ ሳይሆኑ በቅሎ ተለይታ ነጻ ልትሆን አትችልም፡፡ አንድን አካቢ ብቻውን ንጹሕ ማድረግ አትችይም፡፡ ምክንቱም ዝንቧ ከወዲያኛው ማዶ ትመጣለችና፡፡ ከእኛም ወገኖችኮ ሜዳ በመኖራቸው የተነሣ ‹የሜዳ ፈረስ›› ተብለው የቀሩ አሉ፡፡ እኛ ከሰው ተጠግተን ‹የቤት ፈረስ›› ለመሆን ቻልን፡፡ ‹‹የቤት አህዮች›› አሉ፡፡ ‹‹የሜዳ አህዮች›.ም አሉ፡፡ የስም ጉዳይ ነው፡፡ የአኗኗር ጉዳይ ነው፡፡ በቤተ መንግሥት ከነገሥታት ጋር የሚኖር አንበሳ ነበርኮ፡፡ የነገሥታቱ ዙፋን እንዲያውም የአንበሳ ቅርጽ ነበረው፡፡ በዚያው ዘመን ግን ንጉሡ ጫካ ወጥተው ሌላ አንበሳ ገድለው እየተዘፈነላቸው ይመጣሉ፡፡ ጀርባሽን ለመጋለብ ምቹ ካደረግሽው ምንጊዜም የተሻለ ተወዳጅ ትሆኛለሽ፡፡ እንግሊዞች ‹‹Better to ride on ass that carries me, than on a horse that throws me – የምትገለብጠኝን ፈረስ ከምጋልብ፣ የምትሸከመኝን አህያ ብጋልብ ይመረጣል›› ይላሉ፡፡
ቤት የቀረው ውሻ ዱር ከቀረው ውሻ ጋር በመለያየታቸው ዛሬ አንዱ አንዱን እንደ ጠላት ያባርረዋል፡፡ ሰው ብልጥ ነው፡፡ አንዱን ወደራሱ አቅርቦ ውሻ አደረገውና ‹‹ቦቢ›› እያለ በማቆላመጥ ነጻ የወጣ አስመሰለው፡፤ ሌላውን ደግሞ ቀበሮ፣ ተኩላ ብሎ ጫካ ተወውና እርሱን መግደል ጀግንነት እንዲሆን አደረገው፡፡ አሁን ውሾቹ የሠለጠኑና ነጻ የወጡ መስሏቸው ተኩላና ቀበሮ ሲያብርሩ ይኖራሉ፡፡ አየሽ ጉዳዩ የዘር አይደለም፡፡ በዘር ከሰው ተኩላ ለውሻ ይቀርበዋል፣ ቀበሮ ይዛመደዋል፡፡ ጉዳዩ የጥቅም ጉዳይ ነው፤ የመደብ ጉዳይ ነው፡፡ ከቀበሮውና ከተኩላው መካከል ደግሞ የተወሰነውን ይወስዱና ፓርክ ውስጥ አስገብተው ያለፈለት ያስመስሉታል፡፡ እርሱም ማግኘት የሚገባውን ሳይሆን ራሱን ከጫካው ኑሮ ጋር ስለሚያነጻጽር ‹ተመስገን› እያለ ይኖራል፡፡››
‹‹ነጻነት የፍጡር ሀብት ነው፡፡ ለእነ እገሌ ተብሎ የሚቆረስ አይደለም፡፡ ጨቋኙም ተጨቋኙም ነጻ ካልወጣ ሙሉ ነጻነት አይገኝም፡፡ ጨቋኝነት ከአስተሳሰብ ባርነት የሚመጣ ነው፡፡ ከአመለካከት ድህነት የሚከሰት ነው፡፡ ሙሉ ነጻነትን ለማግኘት እርሱን ነጻ ማውጣት አለብሽ፡፡ ካልሆነ ግን ጉዞው አንዱን ጨቋኝ በሌላ ጨቋኝ መተካት ነው የሚሆነው፡፡ አፍሪካውያንኮ ራሳቸውን ከአውሮፓውያን ነጻ ማውጣት አላቃታቸውም፡፡ ያቃታቸው ራሳቸውን ከራሳቸው ነጻ ማውጣት ነው፡፡ ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተኩ፡፡ ቅድም እንዳልኩሽ ሳጥኑን ካላጠፋሽው ታግሎ ከሳጥኑ የወጣው ሁሉ በፋንታው የተሸነፈውን እርሱ ወደወጣበት  ሳጥን መክተቱ የማይቀር ነው፡፡
‹‹ደግሞስ ለምን በማትቀይሪው ነገር ጊዜሽን ታጠፊያለሽ? አሁን አንቺ በቅሎ ሆነሻል፡፡ አለቀ፡፡ ከእንግዲህ አህያ፣ ፈረስ፣ አንበሳ፣ ጅብ ፣ ድመት ልትሆኝ አትችይ? መሆን ለምትፈልጊው ነው መታገል ያለብሽ? በእጅሽ ላይ ላሉት ዕድሎች ነው መታገል ያለብሽ፤ ልትለውጫቸው ለምትችያቸው ዕድሎች ነው መታገል ያለብሽ፤ ልታሸንፊያቸው ከምትችያቸው ነገሮች ጋር ነው መታገል ያለብሽ፡፡ ትናንትን በነገ ለመቀየር ታገዪ፤ ትናንት ውስጥ ገብተሸ ግን እቀይረዋለሁ አትበዪ፤ መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ከትናንቱ ውጭ፤ ያ ያለፈ ነገር ነው፡፡ ታሪክ አይታረምም፤ ሆኗልና፡፡ በታሪክ ውስጥ የተፈጠረ ችግር ግን በቀጣይ ታሪክ ይታረማል፡፡ ምን ሆነ? የሚለው አይለወጥም፤ ምን ይሁን? የሚለውን መለወጥ ግን ይቻላል፡፡ ዛሬ ላይ ሆነሽ የመጣሽበትን ማስተካከል አትችይም፤ የሚትሄጅበትን ግን ትችያለሽ፡፡ ብዙዎቹ ነጻ አውጭዎች ትናንትን ነጻ ለማውጣት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ አንቺ መግባት ያለብሽ ነገን ነጻ ሊያወጣ የተቋቋመ አካል ከተፈጠረ ብቻ ነው፡፡
‹‹አፍሪካውያን ‹‹until the lions have their own historians tales of hunt will always glorify the hunters- አንበሶች የራሳቸው ታሪክ ጸሐፊዎች እስኪኖሯቸው ድረስ ስለ አደን የሚጻፈው ታሪክ ሁሉ ምጊዜም አዳኞችን የሚያገንና የሚያከብር ይሆናል›› ይላሉ፡፡ ዛሬ ከአንድ ወገን ብቻ እየሰማን የምንፈርዳቸው ፍርዶች በታሪክ ተሠሩ ከምንላቸው ስሕተቶች በላይ እንድንሳሳት የሚያደርጉን ናቸው፡፡ የማናውቃቸውና ያልሰማናቸው፤ ምናልባትም ወደፊትም ልንሰማቸው የማንችላቸው ታሪኮችም አሉን፡፡ ትናንት ያለፈ በመሆኑ ለፍርድ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰሎሞን ዴሬሳ የተባለ ሰው ‹አንተ ዘርህ ምንድን ነው?› ሲባል ‹‹በቅድመ አያቴ ደጅ ማን እንዳለፈ እኔ ምን ዐውቃለሁ›› ይል ነበር፡፡ በአንቺስ ቅድመ አያት በር ማን እንዳለፈ ምን ታውቂያለሽ? መጠኑና ዘመኑ ይለያያል እንጂ ‹ሌላ› የሚለውን አካል ሳይገድል፣ ሳያጠፋ፣ ሳይጨቁን፣ ሳይቀማ እዚህ የደረሰ የለም፡፡ ግን ታሪክ እንደተራኪው ነው፡፡
‹‹ሁላችንንም መከራውና ግፉ፣ ጭቆናውና የደረሰብን ነገር ሁሉ አስተባብሮናል፡፡ በየዘመናቱ ቤተ መንግሥቱን የተጠጋ ተሸልሟል፡፡ አምሮበታል፡፡ ሌላውን ለማስገበርም ዘምቷል፡፡ እኛ አህዮች፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ነንኮ ሌሎች እንስሳት እንዲታደኑ አብረን ከሰዎች ጋር የዘመትነው፡፡ በእኛ ዘምተው ሌላ ሀገር የሚገኙ ፈረሶችንና አህዮችን እንዲዘርፉ አድርገናልኮ፡፡ ከዘመቻው በኋላ ለእኛ የተሻለ ነገር ጣል ሲደረግልን እነርሱ ግን በባዶ ሜዳ አድረዋልኮ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ለእኛ እነርሱ ይቀርቡን ነበር፡፡ ነገር ግን ቤተ መንግሥቱን ስትጠጊ እንዲህ አታስቢም፡፡ በታሪካችን ውስጥ የደረሱብንንና ያደረስናቸውን ብንቆጥራቸው ከምንለያይበት የምንመሳሰልበት ይበልጣል፡፡ ግን ምን ያደርጋል ከሳጥኑ ወጥቶ የሚያስብ የለም፡፡ ሳጥኑ ውስጥ ስትሆኚ ደግሞ ያንቺ ብቻ ነው የሚታይሽ፡፡
‹‹መቼም በእንስሳት ታሪክ ቀደምት ከሚባሉት አንደኛዎቹ ቲቤታውያን ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ ‹‹አንጥረኛው ጥበበኛ ከሆነ ብረትና ነሐስ ሊዋሐዱ ይችላሉ››፡፡ አሁንም እኛ አንድ ልንሆን ያልቻልነው አንድ የሚያደረግን ነገር ስለሌለ ሳይሆን አንድ የሚያደርገን ጥበበኛ አንጥረኛ ስለሌለ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቺው፤ ቤተ መንግሥት የኖረውን አንበሳኮ ነው ‹‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጨዋቻ ይሆናል›› የሚሉት፡፡ ታድያ ከጫካው አንበሳ ምን የተለየ ነገር አገኘ? የቤት አህያም ሆነ የጫካ አህያ ሲያረጁ ሁለቱንም አውሬ ይበላቸዋል፡፡ ቤት ውስጥ የኖረውም ውሻ ሲያረጅ ዞር ብሎ የሚየው የለም፡፡ ስለዚህ ልጄ አሁን የሚያስፈልገን የእገሌ ነጻ አውጭ ድርጅት ሳይሆን ‹የአስተሳሰብ ነጻ አውጭ ድርጅት›› ነው፡፡ አስተሳሰብሽ ነጻ ሲወጣ ‹‹መጀመሪያ እኔ እንስሳ ነኝ ወይስ በቅሎ?›› የሚለውን ጥያቄ ራስሽ ትመልሽዋለሽ፡፡
ሲድኒ፣ አውስትራልያ

አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአምስት የክልል ከተሞች ለሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊውን የማሳወቅ ተግባር እንደጨረሰ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በመጪዎቹ ቀናት በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በመቀሌ፣ በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ከዋናው የአንድነት ጽ/ቤት እና ከየዞኑ የተውጣጡ ቡድኖችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሚደረግባቸው […]

ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል እያከናወነ በሚገኘው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር መሰረት፣ ሐምሌ 28 ቀን 2005 በጂንካ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን በበራሪ ወረቀትና ፖስተሮችን በመለጠፍ ህዝቡን ሲያነቃቃ ቆይቷል፡፡ ዝርዝር ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ

ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም የሰላማዊ ሰልፍ «የአሸባሪዎች ተላላኪ ናችሁ። የመቀሌ ህዝብ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ አይፈልግም» በማለት አንድነት ፓርቲን የሚመለከት በራሪ ወረቀት የመበተንም ሆነ የቅስቀሳ ስራ የሚያከናውን ሰው ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ እየዛቱ ነዉ። ሆኖም በመቀሌ የሚገኙት የአንድነት አመራሮች ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለአከባቢው ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡ ዝርዝር ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት አከባበር ሥነ ሥርዓት ጋር  በተያያዘ ሠራተኞቹን በየደረጃው ማወያየት ጀመረ፡፡ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ከመሰልቸቱ ጋር ተያይዞ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሽፋናቸው እንዲቀንስ ተደርጎ የነበሩት የአቶ መለስ ርዕሰ ጉዳይ- ሙት ዓመታቸውን ተከትሎ እንደገና አዲስ አጀንዳ ሆኗል፡፡ የአስተዳዳሩ ምንጮች እንደገለጹት የአቶ መለስን …

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው። ሰዎቹ በምን ምክንያት ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ አሳት ወደ አኳባቢው ፖሊስ  በመደወል ላቀረበው ጥያቄ፣ ፖሊስ ሰዎቹ ተገድለው መገኘታቸውን አረጋግጦ፣ ስለአሟሟታቸው ምክንያት ማጣሪያ እያደረገ መሆኑና ምርመራውንም እንደጨረሰ መረጃውን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። ኢሳት በጉዳዩ …

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያአዘ በቅርቡ በጋሞጎፋ ዞን በቁቻ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት በርካታ ሰዎች መካከል 13ቱ ዛሬ በዋስ የተለቀቁ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ደግሞ ለሀምሌ 25 መቀጠራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በቅርቡ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የከተማዋ አገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል ።

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለጉዳዮቹ  የከፍተኛው ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ከነበረው የቀበሌ ፍርድ ሸንጐ ማነሱንና በጥራትም በብቃትም እጅግ መውረዱን ገልጸዋል:: የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብና የንብረት ክርክሮችን የሚዳኝ ሲሆን አልፎ አልፎ የወንጀል ጉዳዮችን ይመለከታል:: ይህ ፍርድ ቤት የተሟላ የህዝብ መጸዳጃ የሌለውክመሆኑም በላይ መብራት ሲቋረጥ ጀነሬተር ባለመኖሩና የፍርድ ቤቱ የድምጽ ቀረጻ ስለሚስተጎገል …

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ግርማ በህይወት ዘመናቸው ለሚወዷት ሀገራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተለያዩ ሀርፎች ያገለገሉ ሲሆን ወደ ፖለቲካው በመግባትም ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ ሲል አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። አቶ ግርማ ወደ ተቃውሞ ጎራው ትግል የገቡት ለ1984 ዓ/ም ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋር በመሆን መአህድን በመመስረት ነው። የመኢአድ …

የኢትዮጵያው ንጉሥ አፄ ኃይለሥላሴ ለአፍሪካ ያበረከቱትን አስተዋፅዖ የፈተሸ ውይይት ባለፈው ቅዳሜ፤ ኀምሌ 20/2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ፤ የሰቆጣና አካባቢዋ ኑዋሪዎች ከላሊበላ -ሰቆጣ እንደሚሠራ ቃል የተገባልን አስፋልት መንገድ ተግባራዊ ይሁን በማለት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

የሀዘን መግለጫ፤ አቶ ግርማ ወ/ሰንበት በ1984 ዓ.ም. መዐህድን በመመስረት፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) የብሄራዊ ም/ቤት አመራር አባል በመሆን ታግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓርቲያችን አንድነት ከፍተኛ አመራር ሰጭ በመሆን ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን ለማሳካት ግንባር ቀደም አርበኛ በመሆን ሲታገሉ የቆዩ ብርቅዬ […]

ሰበር ዜና፤ በጂንካ ነዋሪዎች ለእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ መዘጋጀታቸውን ገለፁ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል እያከናወነ በሚገኘው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር መሰረት ሐምሌ 28 ቀን 2005 በጂንካ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን በበራሪ ወረቀትና ፖስተሮችን በመለጠፍ ህዝቡን ሲያነቃቃ ቆይቷል፡፡ የጂንካና የአካባቢው ነዋሪዎችም በዕለቱ አደባባይ በመውጣት የታፈነ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ለአንድነት የጂንካ አመራሮችና አባላት […]

በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር በማሊ፣ እንደተፈራው ሳይሆን የትናንቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰላም ነው የተከናወነው። የዶቸ ቬለ ባልደረባ ፣ ካትሪን ጌንትስለር፣ ከማሊ የላከችው ዘገባ እንደሚጠቁመው፣ከ 27 ቱ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል፤

የኢትዮጵያን አብያተ ክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሶችን በሥርዓት ለመጠበቅ ባለመቻሉ፣ የሚያስጠብቅም ባለመኖሩ ፣ ባለፉት አያሌ ዓመታት እጅግ በዛ ያሉ ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ ቅርሶች ወደ ውጭ እየተጋዙ ገበያ ላይ መዋላቸው እንግዳ ነገር አልሆነም።

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ፤ ትልቅ ሥም ያላቸውን ፤ ገጣሚ ፣ ደራሲና ደራሴ ተውኔት ፤ የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅንን የህይወት ታሪክ፣ በሚዳስስ መጽሐፍ ላይ ፤ ሜሪላንድ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ውይይት ተካሄደ።

የአዉቶማቲክ ጠመንጃ ተኩስ ይሰማናል።ተቃዋሚ ሠልፈኞቹ (እኛ እንዳንመታ) ዙሪያችንን ከበዉ ሠብአዊ ጋሻ ሠሩ።ጥይቶችና የሲ ኤስ ጋሶች ይተኮሱብናል።አየሩ በጢስ ታፍኗል።ሰዎች ያስታዉካሉ።የመስክ ሆስፒታሎቹ ወለል ደም ተንጣሎባቸዋል።—“

ሰበር ዜና፤ አቶ ጌታቸው ገ/ስላሴ የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣አቶ ወልዳይ የተባሉና የመቀሌ ዞን የፀጥታ ኃላፊ እንዲሁም ከመቀሌ ወጣቶች ማህበር ተወከልኩ ያለ ግለሰብ የአንድነት አመራሮቸን በመጥራት “መንግስት አጠቃላይ ግምገማ ላይ ስለሆነ የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብለዋቸዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም መልሳቸሁ ህግ የተከተለ አይደለም፤ እኛ ህገመንግስታዊ መብታችንን ጠይቀናል በየትኛውም ሁኔታ ሰልፉን አንሰርዝም፡፡” የሚል […]

በታዬ ዘሐዋሳ
በሃገራችን በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም አመለካከት የተነሳበርካታ ኢትዮጵያውያን በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል:: የሚኖሩበትም ሃገር ብዛትና ስብጥር በራሱ ከሌሎች ሃገራት ዜጎች የተለየን ያደርገናል ብዬአስባለሁ:: እንደ ሃገራቱ ስብጥር እና ብዛት ሁሉ የሃበሻ አመለካከትም እጅግብዙ ነው:: ይህ ብዛት ያለው ስብጥር ደግሞ ወጥ የሆነ አመለካከት እንዳይኖረን አድርጓል:: ክፍፍላችንም እንደዚያውብዙ ነው:: ፍረጃችንም ጭምር:: የዛኑ ያክልም ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራለመፈራረጅ ወይምለመሞጋገስ ከንፋስየፈጠነ ነው:: ፍረጃው ከተለያዩ አካላት ይጀመር እንጂ አብዛኛዎቹን ፍረጃዎች በማዳነቅና በማሟሟቅ ረገድ የሁሉም ድርሻ አለበት:: አንዲት የፌስቡክ ወዳጅ ስለፍረጃዎች ብዛትእና ጥልቀት ትዝብቷን አካፍላን ነበር:: ከነዚህ የርስ በርስ ፍረጃዎች ውስጥ የሚከተሉት በስፋትየምናስተውላቸው ናቸው:-
 . ኢቲቪ ወይም ኢሳት
 . ኢህአዴግ ወይም ተቃዋሚ
. አይጋፎረም ወይም ኢትዮጲያን ሪቪው
. አዲስዘመን ወይም ፍትህ
. ኢትዮጲያወይም ሞት ወይም ገንጣይ ተገንጣይ
. እምየሚኒሊክ ወይም አፄ ዮሃንስ
. ኢትዮጲያፈርስት ወይም ኦሮሞ ፈርስት
. ልማትወይም ሰብአዊ መብት
. ንኡስከበርቴ ወይም ደሃ
. ኪራይሰብሳቢ ወይም ልማታዊ
. ሰለፊስትወይም አህባሽ
. የውጪሲኖዶስ ወይም የሃገር ውስጥ ሲኖዶስ
. የምርጫትግል ወይም የትጥቅ ትግል
. ጠባብወይም አገር ወዳድ
. ባንዳወይም ጀግና
. የባንዳልጅ ወይም የጀግና ልጅ
. X ወይምY እያለ ይቀጥላል::
ይህን የፍረጃ ብዛት እና አይነት ለግዜው በዚህ እናብቃው:: የፅሁፌ መነሻ ርዕሥ በርካታ ሃሳቦችን ማስነሳት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራንበተመለከተ የተለያዩሃሳቦችን ማንሳትና ማወያየት እንደሚችል ግልፅ ነው:: አነሰም በዛም እነዚህን ሃሳቦች እያነሱ መወያየትም ሆነ መተራረም ስለ ድክመታችን አውቀን የማስተካከያ እርምጃ እንድንወስድ ይረዳናል:: ድክመቱን በገደምዳሜ እያየንየምናልፈው ከሆነግን ለሃገራችንም ሆነ ለህዝባችን ፋይዳ አናመጣም:: መፅሃፉ እንዳለውም አስቀድሞ በአይናችን ያለውን ምሰሶ ማውጣት ስንችል ነው የጓደኛችንን ጉድፍ ማየት የምንችለው:: ነገርግን የኛ ዳያስፖራ እሱ ያለው እንጂ ሌላው የሚለው ትክክል አይደለም ብሎ የማሰብ አዝማሚያ ያሳያል:: እናም ምናልባት የኔ ሃሳቦች ከተወደደው ዳያስፖራሃሳብ ጋር ካልተስማሙ የማይስማሙበትን ሁኔታ ለመስማት ዝግጁ መሆኔን አስቀድሜ ልግለፅ:: የባህርያችንን ጥልቀት ለማሳየትም ይመስላልኢትዮጵያየገባ አንድ ፀሃፊ በማግስቱ ስለ ኢትዮጵያውያን ከአንድ በላይ መፅሃፍ ሊፅፍ ይችላል:: በሁለተኛው ቀን ምናልባት ከተሳካለት ለጋዜጣየሚሆን መጣጥፍ ሊፅፍ ይችላል:: ሳምንት ሲቆይ ግን ሰው ስለ ኢትዮጵያውያን አንድአረፍተ ነገር እንኳ መፃፍ አይችልምአለየሚባለው:: ለማንኛውም ለዛሬ የሚከተሉትንእዛም እዛም የረገጡሃሳቦችንላንሳ:: ነገር ግን የማነሳቸው ሃሳቦች ከጥቂት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችጋር ግንኙነት የሌላቸው እና እንደማይመለከታቸውም ባውቅም ብዙሃኑን ይወክል ዘንድ እነዚያን ጥቂቶችም የፅሁፌ አካል አድርጌያቸዋለሁ:: ለዚህአስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ::

1)  የእርስ በእርስ ፍረጃ መፍትሄ ይሆነናል?
ፍረጃ በማንኛውም ልኬትቢለካ ወደምንፈልገው የልማት ግብ ሊያደርሰን አይችልም:: ክፍፍሎችንና ፍረጃዎችንእየተከተልን ስንጨቃጨቅእና ስንፈራረጅ ዓለም ጥሎን መሄዱ አይቀርም::  የፍረጃችንን ጥልቀትየሚያሳይ አንድ ትዝብት ላንሳ:: አንዱ የውጭ ሃገር ዜጋ ስለኛ ክፍፍል እና ፍረጃ ከሃበሻ ጋር ሲወያይእናንተኢትዮጵያውያን በእስካሁኑሂደት በብሄር፤ በጎሳ፤ በቋንቋ፤ በሀይማኖት እናበመሳሰሉት ተከፋፍላችኋል:: አሁን የቀራችሁ ነገር ቢኖር በስማችሁ ፊደል ቅደም ተከተል መከፋፈል ነው፡፡አለየሚባል መራራ የቀልድ እውነታ አለ:: በብዛት እንደምንታዘበውም አብዛኛውስለወቅታዊው ፖለቲካየሚያወራልን ኢትዮጵያዊሁሉ አንድነትን ወይም ህብረትን የሚሰብክልን የራሱብሄር ከፍታ ቦታ ላይ ሊሆን እንደሚችል ካሰበ ብቻ ነው:: የርሱን ብሔር የተመለከተ ሌላ ታሪክ ወይም ድርጊት ከተነገረ ከርሱ በላይ የዘር ፖለቲካን አራማጅ የለም:: ፍረጃውም በአይነት በአይነት ተደርድሮ ይቀርባል:: ይህንን አይነት አካሄድን የሚያሳየን ደግሞ በተለያዩ ግዜያት ጣል በሚደረጉ አመለካከቶች ስር የሚሰጡ አስተያየቶችን መመልከትስንችል ነው:: እንደዚህ አይነት አመለካከትና አካሄድምናልባት የምንፈራውን ከማፋጠን ያለፈ ፋይዳ የለውም:: ስለ አንድነት ሲሰብክ የነበረ ኦሮሞ ስለ ኦሮሞ እርሱ የማያምንበት ተፅፎሲያነብ ለዛ ፅሁፍ መልስ ወይም ማስተካከያ እና መከራከሪያ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ የፀሃፊውን ዘር እያነሱ ጥንብ እርኩሱን በማውጣት ፍረጃ የሚያወጣለት ከሆነምኑን ስለ አንድነት ሰበከው? ስለዘር ፓለቲካ ጎጂነት አሳምሮ አቀነባብሮ የሚሰብከንሰው ስለትግሬ መጥፎነት በማውራት እና በመፈረጅ ካጠናቀቀው የቱላይ ነው አንድነትን የሚያሳየው? አንድነት ሃይል ነው እያለ የሚያስተምር ሰውስለ አማራ ጨቋኝነት እያነሳ እና አማራውን እየፈረጀ ሌላው ብሄር አማራን እንዲጠላ ከሰበከ የቱ ላይ ነው አንድነቱ ያለው? አንድ ነን እያለ ትግሬን አትመኑ ካለን፣ አንድ ነን እያለ አማራ በድሎናል በማለት ያለፈ ታሪክ ካወራ፣ አንድ ነን እያለ ኦሮሞ የመጣው ከዚያ ነው ካለ የቱ ጋር አንድነቱ ያለው? የሚወራው አንድነትስ የማን ነው? አንድነቱ ከግለሰቦች ካልጀመረ እንዴትስ አንድነት ይሆናል? ይህን ትዝብት ለግዜው እዚህ ልግታዉና ወደ ቀጣይ ሃሳብ ላምራ::
2)  ምን ያህል ዳያስፖራዎች ናቸው ሃገራቸውን የሚወዱት?
የግሌ መልስምናልባት20% የሚሆኑት ይወዱ ይሆናልባይነኝ:: ሃገርን የመውደድ ልኬቱ በኔና በነሱ ሊለያይ ይችላል:: ለኔ ሃገርን መውደድ ማለት የግል ፍላጎትን እና ምቾትን ለሃገር አሳልፎ መስጠት ነው:: ሃገርን መውደድ ማለት እራስን አሳልፎ እስከመስጠት ማለት ነው:: ሃገርን መውደድ ማለት መከራን እና ችግርን መሸሽ አይደለም:: አንድ ሰው ፖለቲከኛ ሲሆን ለግል ጥቅሙ ሳይሆን ለህዝብና ለሃገር ሊሰራ ቆርጦ ተነሳ ማለት ነው:: ሆኖም ግን አንድ ችግር ሲያጋጥመው የሚኮበልልከሆነ ቀድሞውኑ የተነሳው ለራሱ ግላዊ ጥቅም እንጂ ለሃገርና ለህዝብ አልነበረም ማለት ነው:: ከዚህ የፖለቲከኞች ቁማር ጋር በተያያዘ የበርካቶችን ታሪክ ማንሳት ይቻላል:: ነገር ግን ከዚህ በፊትም ብዙ ስለተባለ ልለፈው:: በኔ አመለካከት ፖለቲከኛ ለያዘው አላማ ሞትን የሚጋፈጥ እንጂ የሚሞዳሞድ ወይምወደ ባእድ ሃገር የሚፈረጥጥ አይደለም::
ሌላው በዚህ ርዕስ ስር የማነሳው ሃሳብ ሰልፍን ይመለከታል:: በተለያዩሃገሮች ላይ ሃበሾች ሰልፍ ሲወጡ ይታያሉ:: ለምንድን ነው ሰልፍ የሚወጡት? ሀገራቸውን ስለሚወዱወይስ በሌላ ምክንያት? ከላይ እንዳልኩት 80%ምክንያታቸው ሌላነው:: ሃገሩንና ህዝቡን የሚወድ ሰው በሩቁ ሆኖሊመታችሁነው ተጠንቀቁ” “ሊገላችሁ ነው ሽሹወይምገደላቸው ገረፋቸውእያሉ በባዶ ሜዳ መፈክር ማሰማት አይደለም:: ሃገሩን የሚወድ ሞትንም ቢሆን ተጋፍጦ ለሃገሩ ለውጥ ያመጣል እንጅ በተንደላቀቀ ኑሮ ላይ ሆኖ እንዲህ እኔ እንደምጽፈው መፈክር እያዘጋጁ መሰለፍ አይደለም:: ከተሰላፊዎቹ መካከልበርካታ የሃገሪቱ አንጡራ ሃብት ፈሶባቸው በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ ነገር ግን ብር Read more ›

የደብሩ ምእመናን በፍ/ቤቱ ውሳኔ ግራ ተጋብተዋል ዋና ጸሐፊው ከሥራቸው ታግደዋል፤ በምትካቸው ሌላ እንዲመደብ ተጠይቋል በሰነድ ማጭበርበር እና ሰነድ ማሸሽ በተፈጸመ ከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በኀምሳ ሺሕ ብር ዋስትና መለቀቃቸው ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የደብሩ ዋና …

(ተመስገን ደሳለኝ)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለትንተና አዳጋች መሆኑን የሚናገሩ ምሁራን መከራከሪያቸው ፖለቲከኞቹ ከርዕዮተ-ዓለም ይልቅ ‹‹ሴራ››ን ማስቀደማቸውን በመጥቀስ ነው። በርግጥም አብዛኛው የፓርቲዎቹ የአመራር አባላት ከክህሎት እና ርዕዮተ-ዓለም መራቀቅ ይልቅ በዘልማዱ ፖሊቲካ የተካኑ ናቸው፡፡ በተለይም የ1966ቱ ‹‹አብዮት›› ያሰረፀው የ‹‹ፓርቲ ፖለቲካ›› የተደራ ‹‹ሴራ›› ምን ያህል ኩነትንም ታሪክንም መቀየር እንደሚችል አሳይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …