የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከሀገር እንዳይወጡ በቅርስ ጥበቃ ረገድ መስሪያ ቤታቸዉ ከሌሎች ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለዶቼ ቬለ ገለጹ።