አንድነት ፓርቲ – በአምስት የክልል ከተሞች ለሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል

አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአምስት የክልል ከተሞች ለሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊውን የማሳወቅ ተግባር እንደጨረሰ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በመጪዎቹ ቀናት በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በመቀሌ፣ በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ከዋናው የአንድነት ጽ/ቤት እና ከየዞኑ የተውጣጡ ቡድኖችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ ወደ ሚደረግባቸው አካባቢዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ‪#‎milionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬