ፍራንክፈርት፣ ሳዋ ፣ሳሃራ ፣ ሜዲትራንያን፣ ላምባዱሳ በልጅግ ዓሊ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
‹‹ሀገሬ ናይጄሪያ ኢትዮጵያን ለማሸነፍ ምትችልበት ብቸኛው መንገድ አንድም ጸሎት አሊያም ዕድል ነው፡፡›› የቀድሞው ዝነኛውና ኮከብ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ካኑ ለአንድ ታዋቂ የስፖርት ድረ ገጽ በሰጠው አስተያየት ነበር እንዲህ ያለው፡፡ በጨዋታው ላይ የሆነው ሁሉ እንዳለ ሆኖ በእውነትም ካኑ እንደገመተው የናይጄሪያዎቹ ፈጣን ንስሮች ‹‹በጸሎትም ወይም በዕድል›› ሊባል በሚችል ሁኔታ የኢትዮጵያ አቻዎቻቸውን 2-1 በማሸነፍ ለ2014 የብራዚሉ […]
ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-eA ይጫኑ!
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family
Ethiopia, Corruption Charges
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ህግ አንድ ግለሰብ ከመንግስት በማስፈቀድ አንድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲይዝ ቢፈቀደልትም ፣ በተግባር ግን አብዛኛው ህዝብ በመሳሪያ አሰሳ ስም የግል መሳሪያውን መቀማቱን በተለያዩ የመገናኛ ብሀን ሲዘገብ ቆይቷል። በ1997 ምርጫ ወቅት የአንድ ብሄር አባላት በገዢው ፓርቲ ህወሀት ራስን የመጠበቂያ መሳሪያ እንዲታደላቸው መደረጉ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል። የፌደራል አቃቢ ህግ …
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 13ኛውን የአርብቶ አደሮች ቀን ለማክበር ደቡብ ኦሞ ዞንን ለማክበር በተገኙበት ወቅት ለእርሳቸው ክብር መገለጫ እንዲሆን እስከ 20 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የሚነገርለት ስታዲያም በጅንካ ከተማ ተስርቶላቸው ነበር። ይሁን እንጅ ስታዲየሙ ሶስተኛ አመቱን ሳይደፍን ለሁለተኛ ጊዜ ፈርሷል። በመጀመሪያ ከክቡር ትሪቡኑ በስተቀኝ በኩል ያለው ክፍል ፈርሶ ጥገና …
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኩባንያው ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎችን ታክስ ሳይከፍል በቴሌ ስም ሲያስገባ በመገኘቱ ንብረቱ እንዲወረስ እንደሚደረግ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ቴሌ ለኩባንያው እቃዎችን እንዲያስገባ ፈቃድ አለመስጠቱን በመግለጹ ችግሩ ይፋ መውጣቱን ጋዜጣው ዘግቧል። ሁዋዌ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በአይነት ከ235 በላይ እቃዎችን አስገብቷል፤ ይኸው ኩባንያ ከሶስት ወር በፊት የማስፋፋት ስራ ለመስራት በሚል …
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ። ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣ የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች […]
የቅሪተ አፅም እድሜ መለክያዉ እንዴት ነዉ፤ ረጅም እድሜ እንዳለዉ የሚነገረዉ ቅሪተ አፅምስ መገኛ ቦታዉ እንዴት ይታወቃል? ከመቶ ሽ በላይ እድሜ ያላቸዉን ቅሪተ አፅሞች እድሜ መለክያ ዘዴ እጅግ ቀላሉ ነዉ ያሉን ዶክተር ብርሃኔ አስፋዉ ሉሲ «ድንቅነሽ» ስትገኝ ከነበሩ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
10 ያህል የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይበልጥ ተባብረው በጋራ ለመታገል ያስችላቸው ዘንድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸውን ኣስታወቁ።
የዩናይትድ ሴቴትስ የአፍሪቃ እዝ አፍሪኮም ዋና አዛዥ ዴቪድ ሮድሪገዝ እና በአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሊንዳ ግሪንፊልድ አሜሪካ ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት
«የጀርመንና ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉባኤ » የተሰኘ ውይይት እዚህ ጀርመን ኮሎኝ ከተማ ውስጥ ባሳለፍነው ሣምንት ተሰናድቶ ነበር። በውይይቱ የኢትዮጵያ እና የጀርመን መንግሥት ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ ባለሀብቶች እና እንግዶች ተሳትፈዋል።
ታዋቂዋ የበርማ የዴሞክራሲ ታጋይና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንግ ሳን ሱቺ ሽትራስቡርግ በሚገኘዉ የአዉሮጳ ፓርላማ በመገኘት ትናንት የሰብዓዊ መብት የሳካሮቭ ሽልማት ተቀብለዋል።
News, Ask the Doctor, Agriculture and Business
ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-ej ይጫኑ!
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ የሀይማኖቱ አስተማሪ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱትን ነጥቦች ዘርዝሮ አቀረበ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀይማኖት አባቶች በድፍረት መናገራቸው ከምን የመጣ ይመስለውታል ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ ምናልባትም ለውጡ ከፓትርያርኩ ጋር የተያያዘ ሳይሆን …
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር የህወሀት ተጋይ የነበሩትና በአሁኑ ጊዜ በገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙት ታዋቂው ታጋይ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፣ ልጆቻቸው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። የማነ የተባለው ልጃቸው፣ በእስር ቤት ላይ በደረሰበት ግፍ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ሆኗል። አህፎም ደግሞ ከስራ ገበታው ላይ ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ፣ …
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታን በተመለከተ በተለይም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን የኦጋዴን ህዝብ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ያሳየውን ዶክመንትሪ ፊልም የተመለከቱ የስዊዲን የህግ ጠበቃና የአለም አቀፍ የህግ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሪስት ስቴላ ያርዴት የመንግስት ባለስልጣናትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንደተዘጋጁ በማስታወቃቸው እሳቸውንና ሌሎችን እንግዶች በመጋበዝ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 …
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት ግድም ሆላንድ የታወቀ የባሕር ኃይል ሆኖ ከደቡብ አፍሪካ እስከደቡብ አሜሪካ፣ የኔዘርላንድ የቆዳ ስፋት 41 526 ኪ.ሜ. ካሬ ወይም የትግራይ ግማሽ ነው፤ የሕዝቡም ቁጥር አሥራ ስድስት ሚልዮን ተኩል አይሞላም። የትግራይን ግማሽ በሚሆን መሬት ላይ የትግራይን ሦስት እጥፍ ግድም የሚያህሉ ሰዎች ይኖሩበታል።
ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡ ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ […]
በሙሥና የተጠረጠሩ ክሥ ተመሠረተባቸው
የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ዕውቅ ነጋዴዎች ላይ ትናንት ክሥ መሥርቷል።
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አምስተኛ የወንጀል ችሎት ትናንትና ዛሬ በዋለው ችሎት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የነበሩት የአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፣ እንዲሁም አንዳንድ ከፍተኛ ነጋዴዎች በሃገሪቱ ላይ በመቶዎች ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት በማድረስ ተከስሰዋል።
የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሦስት የተለያዩ መዝገቦች፤ ባጠቃላይ በአርባ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ከመቶ በላይ ክሦችን መመሥረቱ ታውቋል።
ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና …
የኢትዮጵያ መንግስት ቢያንስ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስራ ፈላጊዎችን ወደ ሳውዲ አረቢያ እንዳይገቡ ማገዱን ኣስታወቀ።
በዚሁ መሰረት 40 ሺሽ ያህል ቀደም ሲል የተፈቀዱ ቢዛዎችም ተሰርዘዋል።
የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር የጀርመን የአፍጋኒስታን ኩንዱዝ ተልዕኮ ማብቃቱን ባለፈው ቅዳሜ አስታውቋል። የጀርመን ጦር ኩንዱዝን ሙሉ ለሙሉ ለቆ መውጣት የአካባቢውን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለጦሩ የተለያየ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አፍጋናውያንን አስግቷል ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለአሥር ቀናት በመላ ሀገሪቱ እና ከሀገር ዉጪ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ተወካዮች በተገኙበት የሀገረ ስብከቱን ጳጳሳት ጠርታ በውስጧ ስላሉ ችግሮች አወያይታለች።
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የካንሰር ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልጻል። ድርጅቱ አያይዞም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2020ዓ,ም 65 በመቶ የሚሆኑ የካንሰር ታማሚ በአዳጊና በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገራት እንደሚገኝ ከወዲሁ ጠቁሟል።
የኢትዮ ምሕዳር ዋና አዘጋጆች እና ጋዜጠኛ ሚልዮን ደግነው እና ጌታቸው ወርቁ ክስ ተመሥርቶባቸው ሀዋሳ በሚገኘው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በጀርመን ባለፈው መስከረም ወር በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የብዙኃኑን ድምፅ ያገኙት የክርስትያን ዴሞክራቶች እና የክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ጋ በቅርቡ የጥምር መንግሥት ያቋቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
33 ፓርቲዎች እየተባሉ የሚጠሩት በ15/02/ 05 የአዳማ ፔቲሽን ተብሎ የሚጠራውን የፈረሙ ናቸው፡፡ የጋራ ስምምነት ሰነድ የፈረሙት 24 ፓርቲዎች ሲሆኑ ጥቅምት 10 ቀን በዋለው ስብሰባቸው ወደ ቅንጅት አድገዋል፡፡ እሁድ በተደረገው ስብሰባቸው የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመመስረቻ ፅሁፍና መለስተኛ የድርጊት ፕሮግራም በመፈረም “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ/ ትብብር/ በሚል ተሰይመዋል፡፡ በዚህ ውስጥ የተካተቱት 10 ፓርቲዎች ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ያልተካተቱበት ምክንያት ተብራርቷል፡፡ […]
ኢዮብ ይስኃቅ
ከዕለታት አንድ ቀን ባልተለመደ ድፍረት የሙስና ኮሚሽን ሰይፉን ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ አሳረፈ። እንደመድኃኒት ብልቃጥ እዚህም እዚያም ተወሽቆ የነበረ ብርና ንብረት እያስቆጠረ ወንጀለኞቹን ዋስ እየከለከለ ወደ ወህኒ ወረወረ። ሚኒስትሮች ከቦታቸው ተፈናቀሉ፤ የሙስና እናት የሚለውን ሜዳሊያ ያጠለቀችው ወ/ሮ አዜብ ከኤፈርት ተባረረች። ያዲሳባ ከንቲባነትም ሱሚ ነው ተባለች። ከሁለት ብቻ ሳይሆን ከብዙ ያጣች ሆነች። ህዝቡ እልል ለማለት ቢፈልግም ወያኔን ስላላመነ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ያዘ።
ፖሊስ ምርመራውን አልያዝኩትም የማውቀው ነገር የለም ብሏል:: ባለፈው ኦክቶበር 13 2013 በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ከመደረጉ ቀደም ብሎ በቦሌ ኡዋንዳ አከባቢ የደረሰው ፍንዳታ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሸበር በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል:: …
ባለፈው ሳምንት በቦሌ የተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑ ተረጋገጠ Read more »
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን …![]()
DW Amharic – Oct. 21, 2013
Aired on Oct. 21, 2013
Temsegen Melaku Comedy Collection
ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-ea ይጫኑ!
የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ
የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ
የአየር ንብረት እየተለወጠ የመሆኑ ነገር እውነት መሆኑንና ለውጡ ለሚያስከትለው አደጋም የአፍሪካ መጋለጥ ምን ያህል የሰፋ እንደሆነ ለአህጉሪቱ ተጠራጣሪዎች ማስረዳትና እነርሱን ማሳመን የመጀመሪያው ተግባር መሆን እንደሚገባው ተገለፀ፡፡
አፍሪካ የልማት ጎዳናዋን ከበለፀጉ ሃገሮች መቅዳት አለባት የሚባለውም ስህተት ነው ሲሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከፈተው “የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ” ሦስተኛው ጉባዔ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡
ዋና ፀሐፊው የአፍሪካን የዛሬ የአየር ንብረት ለውጥ ይዞታ አውሮፓን ከስድስት መቶ ዓመታት በፊት አጋጠሟት ከነበረውና ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ከፈጀው አጥፊ ወርርሽኝ ጋር …
Climate Change and Development in Africa Conference
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት በም/ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚመራው የልኡካን ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን የግንባሩ ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ9 የክልል መሪዎችንና ባለሀብቶችን አስከትለው በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ ቀብሪደሀር አየር ማረፊያ ባረፉበት ወቅት ነው። ባለስልጣኖቹ ጉበኝት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ …
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፦አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ቢሆንም፤ መሬቱ ግን ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ቦታዎቹ በብዛትና በስፋት የሰፈሩት ገበሬዎቹች አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ …
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ራሱ የ 40 በ 60 መኖሪያ ቤት ሠርቶ ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ አምነው ከ81 ሺህ ሰዎች በላይ ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በሁዋላ፤ ሀሳቡን በመቀየር ከፋዮቹ በማህበር ተደራጅተው ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መወሰኑ ተመዝጋቢዎችን አሳዝኗል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ በአሁኑ ጊዜ መቶ በመቶ የከፈሉ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው …
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል። የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ …
‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ የአንድነት ምልክት የኾነች ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሉዓላዊት ናት፡፡ ትላንት የነበረችው ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖት ዛሬም አትለወጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ በመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷ ሕዝቡን አንድ አድርጋ ትቀጥላለች፡፡›› ‹‹ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ በካህናትና ምእመናን ላይ ሁሉ ሥልጣኑ ይሠራል፡፡ ውሳኔው ይግባኝ የለውም፡፡›› ‹‹የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለእምነታችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ዋስትና የሚሰጥ …![]()
News, Sports, African Topics and Health
የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፣ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ አ የእግር ኳስ ግጥሚያ በዛሬው የስፖርት ጥንቅራችን ሰፋ ያለ ቦታ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን በተመለከተ ከአድማጮች የደረሱን አስተያየቶችን አካተናል። የአትሌቲክስ ውድድር ውጤትም የዝግጅቱ አካል ነው።
ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሚዋጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በእስረኞች ላይ ይፈጸማሉ ባላቸው ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ሪፓርት ይፋ ኣድርገዋል።