በአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀውና በሰላማዊ ትግል ላይ ሰፊ ምርምር ባደረጉት በአቶ ግርማ ሞገስ በሰላማዊ ትግል ላይ እየተሰጠ ያለው ሳምንታዊ ስልጠና ቀጥሏል፡፡ በስልጠናው በሰላማዊ እና ትጥቅ ትግሎች መካከል ንጽጽራዊ ትንተና የተሰጠ ሲሆን ትንተናው በስድስት ክፍሎች የተከፋፈለ ነበር፡፡ የሰላማዊ ትግል እና የትጥቅ ትግል ልዩነቶች በመንግስት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች (የስልጣን ምንጮች) ጥያቄ ዙሪያ፣ መንግስት በማስወገድ ጥያቄ […]

የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብርካው አስተዳደር ላይ ያለቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ መልስ እንደሚሠጣቸው ቃል ገብቶ እንደነበር ታውቋል፡፡ ነገር ግን በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በለቱ የወጣው […]

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ – ከአዲስ አባባ

እነሆ ይቺ  ሀገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤ ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተማሪዎች  የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲው ትክክለኛነቱን አረጋግጦዋል፡፡ የተማሪዎች አመጽ የተነሳው መንግስት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብ እና የአምልኮ  ስርዓት ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ነው።  ” ተማሪዎች  እምነታችሁ ተው ፣ ማተባችሁን በጥሱ” ተብለናል ይላሉ። በ2004 እና በ2005 ዓም ተማሪዎች ህጉን እንዲተገብሩ  ሙከራ ቢደረግም  ተማሪዎች ለመቀበል ፈቃደኛ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ  በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በበሽታው እስካሁን ከ4 በላይ ሰዎች ሞተዋል። 3 ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ተኝተዋል። በአዲስ አበባ የማጅራት ገትር በሽታ ክትባት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል። የማጅራት ገትር ሕመም በተዋህሲን አማካይነት ተከስቶ የአንጎልን ህብለሰረሰር በተለይ ከራስ ቅል በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ሕመም ነው፡፡ በባክቴሪያ አማካይነት የሚከሰተው ማጅራት ገትር በሽታ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም መጨረሻ በይፋ የተመሠረተው የመለስ ፋውንዴሽን ዓላማውን ለማሳካት ከሕዝብ ገንዘብ በመዋጮ መልክ ለማሰባሰብ እያደረገ ያለው ጥረት የታሰበውን ያህል ውጤት እያስገኘ አለመሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ በመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 781/2005 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተመሰረተው ይህው ፋውንዴሽን ቤተመጻህፍትና ሙዚየም ለማቋቋም በማሰብ ሕዝቡ ገንዘብ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል በሚል በ210 ሚሊዮን ዩሮ ወይም በ5 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገነባው የአሸጎዳ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 120 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት፣ በአዳማ ከተገነባው ከሁለት እጥፍ በላይ የሚበልጥ ነው። ከ90 በመቶ በላይ በፈረንሳይ መንግስት የተሸፈነው ፐሮጀክት ሙስና እንደተፈጸመበት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ …

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።

የኢትዮጲያ የንፋስ ማመንጫ አቅምን ወደ ስምንት ከመቶ ከፍ ያደርጋል የተባለውና 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪል ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተመረቀ።

በርካታ ንፁሐን የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ አዳዲስ የጭካኔ ርምጃዎቹ ዜጎችን ፍርሃትና ስጋት ላይ ጥሏል። የናይጀሪያ መንግስት ጦር አሸባሪዉን ቡድን ቦኮ ሃራምን በተጠናከረ ኃይል እንዳያንሰራራ አድርጎ ለመምታት አልሟል። ምንም እንኳን በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ለዚህ ተግባር ቢሰማሩም ቡድኑ አሁንም በጥቃቱ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነዉ።

ከ 3 ሳምንት በፊት ከሊቢያ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በመጠጋት ላይ ከነበሩ 500 ያህል ኤርትራውያን ከሚያመዝኑባቸው ስደተኞች የ364 ቱ ህይወት ያለፈበት አደጋ በሜዴትራንያን ባህር ላይ እስከ ዛሬ ከደረሱት የሞት አደጋዎች እጅግ የከፋው ነው ።

በሞዛምቢክ እአአ ከ1976 እስከ 1992 ዓም በገዢው ፓርቲ ፣ ፍሬሊሞ እና በተቀናቃኙ ሬናሞ መካከል የተከሄደው የርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ከ21 ዓመት በኋላ በቀድሞዎቹ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ውጥረቱ እንደገና እየተካረረ መጥቶዋል።

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል  የመስከረም ወር ደሞዛቸው ያለፈቃዳቸው ተቀንሶ ከተሰጣቸው በሁዋላ የጀመሩት ተቃውሞ እየተስፋፋ መሆኑን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። የጨንጫ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች መምህራን የተቆረጠው ደሞዛችን ካልተመለሰ ስራ አንሰራም በሚል አድማ ከመቱ በሁዋላ፣ በዛሬው እለት ደግሞ በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ በአማራ ክልል ላኩማ ወረዳ ሁለት የሚሊሽያ ሀላፊዎችንና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪን በቁጥጥር ስራ ማድረጉን ገለፀ፡፡ ንቅናቄው ሰሞኑን 22 የፖለቲካ አመራሮች በላኩማ ወረዳ በሚገኘው በሰላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መልቀቁን ገልጾ ሶስቱን አመራሮች ግን አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ …

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር 2005 አካባቢ ተከስቶ የነበረው ማጅራት ገትር ወረርሽኝ እንደገና በአዲስ መልክ በመቀስቀሱ የክልሉ ጤና ቢሮ ሕዝቡን የመከተብ ስራ ላይ መጠመዱ ተሰማ፡፡ ክትባቱ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ ሲሆን ክትባቱን መውሰድ ያለባቸው ደግሞ ዕድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ ነዋሪዎች ብቻ መሆናቸው ለምን የሚል …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ ተካሂዶ በነበረ ግጭት ለሞቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በነብስ ወከፍ 90 ሺህ ብር እንዲከፈል ተወሰነ፡፡ ለሞቱ ሲቪል ሰዎች የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም መቅረቱን ግን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ሚሊሺያዎች እና ነዋሪዎች ከመከላከያ አባላት ጋር ባደረጉት ግጭት ስምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞተው ሰባት መቁሰላቸውን መዘገባችን …

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የውሃ ሽፋን 94 በመቶ ደርሶአል ቢባልም በአሁኑ ወቅት መሃል አዲስአበባን ጨምሮ አብዛኛው አዳዲስ የማስፋፊያ አካባቢዎች በቂ የውሃ ሽፋን የማያገኙት ከ40 በመቶ አይበልጡም። የአዲስአበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን እንደሚናገረው የከተማዋ የውሃ ሽፋን እያደገ ቢመጣም ውሃን በቁጠባ የመጠቀም ልምድ ባለመዳበሩ እስከ40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ብክነት በከተማዋ ውስጥ …

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ኮርያዊ በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡ ስማቸው ይፋ ያልሆነው ዲፕሎማት የሚወክሉትን ሀገር ትተው ከአንድ ወር በፊት የደቡብ ኮርያን መንግስት አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲ በኩል ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተለያዩ የሁለቱ ኮርያዎች መገናኛ ብዙሀን በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡ ዲፕሎማቱ ወደ ደቡብ ኮርያ ኢምባሲ በመግባት ጉዞአቸውን እንዲያመቻችላቸው ጠይቀው ከአዲስ …

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባሌ ዞን በጎባ ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ አዲስ ከተማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ኤም ኦ ሲ ሚሺኒሪ ኦፍ ቻርቲ የተባለው ድርጅት በ1984 ሲቋቋም ዋና አላማው በዞኑ እና በአካባቢው የሚኖሩ እና እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ የአካል ጉዳት ያለባቸው ማለትም፤ መስማት እና ማየት የማይቸሉ፤ መራመድ የማይችሉ፤የአዕምሮ ዘገምተኞች፤እንዲሁም በዕድሜ …

ኢትዮጵያ ውስጥ አጋጣሚዎች ካልፈቀዱ በስተቀር ከቤተሰብ ተለይቶ መኖር ብዙም አልተለመደም። ከነዚህ ከአጋጣሚዎች አንዱ ወጣቶች ለዮንቨርስቲ ትምህርት ወደ ሌላ ከተማ ተመድበው ሲሄዱ ነው።

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አበበ አካሉ ትናንት 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡ ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አመታዊ ስብሰባውን እያከናወነ በሚገኝበት ሰዓት በተለያዩ አነጋጋሪ ክስተቶች መታጀቡን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፌደራል መንግስት ጉዳዩች ሚኒስትር ተወካዩች በተገኙበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጳጳሳት በተገኙበት በተካሄደ ውይይት ጳጳሳቱ የመንግስት ተወካዩች ላቀረቡት ሐሳብ ያላቸውን ልዩነት በመግለጽ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን እንዲሰበስብና ለህገ መንግስቱ ተገዢ እንዲሆን […]

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Journalist Dawit Kebede(ቪዲዮ አለው)

“እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 25, 2013)፦ በሀገር ቤት ይታተም የነበረው “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ እና የድረ ገጹ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመት በሰሜን አሜሪካ የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚበር ገለጸ። በጉዳዩ ላይ ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ጋር በቪዲዮ ቃለምልልስ አድረጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በአጀንዳነት ተይዟል፤ ዐሥር አህጉረ ስብከት ተለይተዋል፡፡ በተጭበረበረ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃና የዶክትሬት መመረቂያ ጥናትን አስመስሎ መቅዳት/plagiarism/ ክሥና ወቀሳ እየቀረበባቸው የሚገኙት፣ ሓላፊነትን በተገቢው ኹኔታ ባለመወጣትና በትጋት ባለመሥራት የተገመገሙት ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ፣ በከባድ እምነት ማጉደል በተቀሰቀሰባቸው የካህናትና ምእመናን ተቃውሞ ከቅ/ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪነት የሚነሡት አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንንና የመሰሏቸው ቆሞሳት ከታሳቢ ዕጩዎች መካከል …

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣  በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው …

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሀንና ሰላምን ለ20 አመታት የመሩት የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉወርቅ ገብረህይወት  ጡረታ ወጥተው በእርሳቸው ምትክ የህወሀት አባሉ አቶ ተካ አባዲ ዛሬ ስራስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል። የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ ሆነው የቆዩት አቶ ተካ፣ ከሰራተኛው ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ በመግባትና በአስተዳደራቸው ብልሹነት ይታወቃሉ። ዛሬ ከሰአት ሹመቱ ይፋ ሲሆን የብርሀንና …

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኘው ትልቁ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት ቤት በመንግስት ትእዛዝ እንዲታሸግ ተደርጓል፡፡ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከ600 በላይ ተማሪዎች የእስልምና ሀይማኖት አስተምሮዎችን ይማሩበት ነበር። መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማትን እያሸገ ነው። መንግስት  ድርጅቶቹ የአክራሪነት መፈልፈያ ሆኗል በማለት ይከራከራል። የመንግስትን እርምጃ የሚቃወሙ ሙስሊሞች በበኩላቸው …

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤይሩት ኢትዮጵያዊቷ በመኪና አደጋ  ደርሶባት አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ባለመቻሏ ህይወቷ አለፈ። ኢትዮጵያዊቷ አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ያልቻለችው- ቆንስላ ጽፈት ቤቱ ሀላፊነት አልወስድም በማለቱ እንደሆነ ተዘግቧል። በዚህም ሳቢያ መዳን ስትችል የነበረችው ወጣት  ህክምና ባለማግኘቷ ለህልፍት መብቃቷ፤ ዜናውን በማህበራዊ መገናኛዎች የተከታተሉትን ሁሉ አሳዝኗል። የቆንጽላ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች፤  ለግድብና ለተለያዩ ነገሮች እያሉ …

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሌ በራያ ቆቦ ወረዳ ከ40 በላይ መንገደኞች ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ በመገልበጡ ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶችም ቆስለዋል። መኪናው ከጭንቱ ልክ በላይ ሰዎችን ጭኖ መጓዙ ታውቋል። በኢትዮጵያ የመኪና አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨ መ ረ መሄዱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል።

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያው ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ሙታሬ በምትባለውና ከሞዛምቢክ ጋር ድንበርተኛ በሆነችው ከተማ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ በፖሊስ እንደተያዙ ማክሰኞ ማምሻውን ተዘግቧል፡፡ ተጠርጣሪ ስደተኞቹ በግምት ከ20 እስከ 30 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚምባቡዌ በሕገወጥ መተላለፊያ በኩል መግባታቸውን ያስታወቁት፣ በዚምባቡዌ ቤት ብሪጅ ዲስትሪክት የፖሊስ …

ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል ​​
ኢትዮጵያ ሌላ ባለአራት ቢሊየን ዶላር የኃይል ማመንጫ ሥራ ልትጀምር ነው
የኢትዮጵያ ጂዖ-ተርማል ኢነርጂ መገኛ የስምጥ ሸለቆ ክልል ​​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል ከሚባል ኩባንያ ጋር የኩርቤቲን የከርሰ-ምድር እንፋሎት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለማከናወን ውል ተፈራርሟል፡፡

ፕሮጀክቱ አራት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም ወደ ሰማንያ ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተገልጿል፡፡

ጂዖ-ተርማል ኢነርጂ ​​
ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍ የውጭ ቀጥታ መዋዕለ ነዋይ እና የግል የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭ ኩባንያ መሆኑ ነው፡፡

ይህንንና ሌሎችም በተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት ላይ የተቀናበሩ ዘገባዎችን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ህልም አላቸው፤ ቀሪዎቹ በቅዠት የተሞሉ ናቸው።

በቅርቡ የአፍሪካ መሪዎች ቢያንስ በአፍሪካ ህብረት ስልጣን ያላቸውና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች ስለህግ ልዕልና፣ ስለዘር ማደን (ማሳደድ) የማያቋርጡ አስደንጋጭ የቅዠት ሪፖርቶች በገፍ እያቀረቡ ነው። ቅዠታቸውም የፍትህ ጎራዴ ስያሳድዳቸው በላብ ተጠምቀው ከእንቅልፍ ይነቃሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ዴሞክራሲ አለ’ ለማለት ያስቸግራል – ክቡር ገና
የፓርላማ አባላት ከተመረጡበት አካባቢና ሕዝብ ፍላጎት ይልቅ የፓርቲያቸውን ያስቀድማሉ ሲሉ አቶ ክቡር ገና አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ዴሞክራሲ አለ’ ለማለት ያስቸግራል” ብለዋል የኢኒሽየቲቭ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና፡፡

“አብዛኛው ተቃዋሚ ኃይልም ከመንግሥት የተሻለ መሆኑን አላሣየም ወይም እስከአሁን በግልፅ አልወጣም” ብለዋል አቶ ክቡር አክለው፡፡

አቶ ክቡር ስለአዲሱ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት በአንድ መፅሔት ላይ ያሠፈሩትን ፅሁፍ መነሻ አድርጎ እስክንድር ፍሬው አነጋግሯቸዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡