ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች
ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያታገዱ:
የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል:: ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል:: ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: […]
ምክር እስከመቃብር (ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)
ክፍል ሁለት (በእውቀቱ ሥዩም) እንደምነሽ ሸገር የከሰመው ወንዝሽ የከሰመው ወዝሽ የሚታየው ነጥፎ እንደምነው ጣፎ እንዴት ነው ቀበና እስቲ ድንጋይ ላጥምድ መረብ ልጣልና፡፡ በነገራችን ላይ በኣዲስ ኣበባ የሚገኙ ካፌዎችና ምግብ ቤቶች“ ኒውዮርክ”“ ዴምቨር” “ወዘተረፈ ተብለው የሚጠሩትን ያክል ባውሮፓና በኣሜሪካ ያሉ ሬስቶራንቶች ደግሞ ”ዱከም“ ፤ ኣራትኪሎ ፤ ፒያሳ በሚል ተሰይመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ምንድር ነው ፡፡ ኣዲስ ኣበባ […]
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው
• ‹‹ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሰሙ የተክለሀይማኖት መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እርምጃውን በመቃወም ለድብዛ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠታቸው ተገልጾአል፡፡
የሁለቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጋር በመሆን ከተማው አደባባይ ላይ በመውጣት ‹‹አህአዴግ አይገዛንም፣ ኢህአዴግ ሌባ፣…›› የመሳሰሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ተከትሎም ፖሊስ ተማሪዎቹን እያፈሰ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጥያቄ የሚጠይቁና ፖሊስ ተቃውሞውን አደራጅተዋል ብሎ የሚጠረጥራቸውን ተማሪዎች እየፈለገ እያሰረ መሆኑን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ17ቱም ወረዳዎች የሚገኙ ተማሪዎች ስልጠናውን ካልወሰዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልጠናውን መቃወማቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ
ኢድሪስ ገላውዴዎስ- አንጋፋው “ጀብሃ”
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
“ሻዕቢያ” የሚለው ስም ሲነሳ የዑስማን ሳልህ ሳቤ ስምም አብሮ ይነሳል፡፡ በእርግጥም “ሻዕቢያ” የሚለውን ስያሜ በስራ ላይ ከማዋል ጀምሮ ድርጅቱን በሁለት እግሩ እንዲቆም ያደረገው ሳልህ ሳቤ በመሆኑ እርሱን እንደ ሻዕቢያ መስራች መመልከቱ አግባብ ነው፡፡ የ“ጀብሃ” ስም ሲጠቀስ ደግሞ ብዙዎች የሚያስታውሱት ሓሚድ ኢድሪስ አዋቴን ነው፡፡ ሆኖም ስህተት ነው፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ በታሪክ የሚታወሰው ጀብሃ የትጥቅ ትግል በጀመረበት ጊዜ የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ “ጀብሃት ታሕሪረል ኤርትሪያ” (በአጭሩ “ጀብሃ”) ወይንም በትግርኛ ስሙ “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) የሚባለው የኤርትራ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅት የተመሰረተው ግን ሃሚድ አዋቴ ትግሉን በባርካ በረሃ ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት አስቀድሞ ነው፡፡ የድርጅቱ መስራቾች በአብዛኛው በካይሮ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ የቀድሞው የኤርትራ ፓርላማ አባላት የሆኑ ጥቂት ሰዎችና ነጋዴዎችም ተቀላቅለቸዋል፡፡ ከመስራቾቹ መካከል ሙሐመድ ሳሊህ ሁመድ፣ ሙሐመድ አደም ኢድሪስ፤ ሰዒድ ሁሴን፣ ጣሓ ሙሐመድ ኑር፣ ወዘተ…ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህን ሰዎች አሰባስቦ የድርጅቱን መሰረት በመጣል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ሰው ኢድሪስ ገላውዴዎስ ይባላል፡፡
ኢድሪስ ዑሥማን ገላውዴዎስ በ1934 በከረን ከተማ አቅራቢያ በነበረችው “በይት ጀክ” በተባለች አነስተኛ ከተማ ነው የተወለደው፡፡ ኢድሪስ የቤኒአምር (ትግረ) ብሄረሰብ ነው፡፡ አባቱ ሀብታም ነጋዴ የነበሩ ከመሆኑም በላይ በተጨማሪም በምዕራባዊው ኤርትራ ሰፊ እርሻ ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ኢድሪስ መደበኛ ትምህርቱን የጀመረው በ1942 የአባቱ እርሻ በሚገኝባትና በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ላይ ባለችው የአሊጊደር ከተማ ነው፡፡ በ1947 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ከሰላ (ሱዳን) ተላከ፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎውንም የጀመረው በከሰላ ከተማ በነበረበት ወቅት ነው፡፡
እንደሚታወቀው በዚያ ዘመን ኤርትራ በእንግሊዞች አስተዳደር ስር ነበረች፡፡ በዘመኑ ኤርትራ ነጻ መውጣት አለባት የሚሉና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ትቀላቀል የሚሉ ሁለት ጎራዎች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያውን ጎራ የሚያንቀሳቅሰው “ራቢጣ አል-ኢስላሚያ” የሚባል ፓርቲ ሲሆን ሁለተኛውን ጎራ የሚመራው ደግሞ “ማሕበር ሀገር ፍቕሪ” የሚባለው ቡድን ነው፡፡ የኢድሪስ አባት የራቢጣ አባል የነበሩ እንደመሆናቸው “ኤርትራ ነጻ ትሁን” በማለት ከሼኽ ሱልጣን ኢብራሂም ጋር ብዙ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኢድሪስም በአባቱ ላይ ባየው የትግል መንፈስ በጣም ተማረከ፡፡ መሆኑም “የራቢጣ” የወጣቶች ክንፍ አባል ሆነ፡፡
ኢድሪስ በ1951 ትምህርቱን በከፍተኛ በማዕረግ በማጠናቀቁ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የስኮላርሺፕ እድል አገኘ፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብቶም የህግ ትምህርት ማጥናት ጀመረ፡፡ ከዓመት በኋላም የኤርትራ ተማሪዎች ማህበር ሲመሰረት የማህበሩ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ፡፡ ኢድሪስ በዚህ ማህበር ኤርትራዊያ ስደተኞችን ለማሰባሰብ በሰፊው ተጠቅሞበታል፡፡
ኢድሪስና ጓዶቹ በስደት ላይ ሆነው የሀገር ቤቱን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉት ነበር፡፡ በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ለኤርትራ የሰጠው የፌዴሬሽን መብት እየተሸረሸረ ነው በማለት ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ በ1957 የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ ታገደ፡፡ ከዓመት በኋላም ትግርኛና ዐረብኛ የስራ ቋንቋ መሆናቸው አብቅቶ በአማርኛ ሲተኩ ደግሞ “ሐረካ” (Eritrean Liberation Movement) የተባለው ድርጅት በሚስጢር ተመሰረተ፡፡ ”
የሐረካ ዓላማ ፌዴሬሽኑ በተቀመጠለት ደንብ መሰረት እንዲሰራ መጠየቅና ለዚህም እስከ መጨረሻው መታገል ነበረ፡፡ በተጨማሪም የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ አልወሰደም፡፡ ይህ ድርጅት በካይሮ የነበሩትን ተማሪዎች በአባልነት ለማሳተፍ ሲሞክር ግን ተቃውሞ ገጠመው፡፡ እነ ኢድሪስ ገላውዴዎስ የሐረካ ዓላማና የትግል ስልት አዋጪ መስሎ ስላልታያቸው ድርጅቱን እንደ ከንቱ ማህበር ነበር ያዩት፡፡
በ1960 ነው፡፡ ኤርትራዊያን በፌዴሬሽኑ አሰራር ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ በርካቶቹም በአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት የተሾሙት ቢትወደድ አስፋሓ ወልደሚካኤል ለባርነት ሊዳርገን ነው እያሉ መነጋገር ጀምረዋል፡፡ ከዓመት በፊት የኤርትራ ሰራተኞችና ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሳቢያ በሀገር ቤት ተቃውሞ ማድረጉም ብዙ እንደማያራምድ አምነዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች የመንግሥትና የፓርላማ ስልጣናቸውን በመተው ወደ ውጪ መሰደድ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ስደተኞች ካይሮ ከሚገኙት ተማሪዎች ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ ስለ ድርጅት ምሥረታ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱም ፍሬያማ ሆኖ በመውጣቱ በጁላይ ወር 1960 ከነጻነት በስተቀር የፌዴሬሽንን ፎርሙላ የማይቀበል አዲስ ድርጅት ተመሰረተ፡፡ ይህም ድርጅት “ጀብሃት ታሕሪረል ኤሪቲሪያ” ወይንም “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) ተብሎ ተሰየመ፡፡
“ጀብሃ” ሲመሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆኖ የተመረጠው የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበረው ኢድሪስ ሙሐመድ አደም ነው፡፡ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ነው፡፡ የድርጅቱ ላዕላይ ምክር ቤት (Supreme Council) አባላት ኢድሪስ ሙሐመድ አደም፤ ኢድሪስ ገላውዴዎስ፣ ሙሐመድ ሳሊሕ አሕመድ፣ ዑሥማን ኢድሪስ ኪያር፣ ሙሐመድ ሰዒድ ኪያር፣ ሲሆኑ ከአንድ ዓመት በኋላም ዑሥማን ሳልህ ሳቤ ተቀላቅሎአቸዋል፡፡
“ጀብሃ” ከተቋቋመ በኋላ በምዕራብ ኤርትራ በረሃ በተበታተነ ሁኔታ ከሚታገሉት እነ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴን መከሳሰሉ ፋኖዎች ጋር ተገናኘ፡፡ ለአዋቴም የግንባሩን ወታደራዊ ክፍል እንዲመሩ ውክልና ሰጣቸው፡፡ በመስከረም 1/1961 በሃሚድ አዋቴ አዝማችነት በጀብሃ ስም የትጥቅ ትግሉ ተጀመረ፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ ከአንድ ዓመት በኋላ ሲገደሉ ደግሞ የወታደራዊውን ክንፍ የመምራቱ ስልጣን ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ተሰጠ፡፡ በዚህም የኢድሪስ ገላውዴዎስ መቀመጫ ከካይሮ ከተማ ወደ ሱዳኗ ከሰላ ከተማ ተቀየረ፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከሰላ ከደረሰ በኋላ በሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን እያሰባሰበ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ ለድርጅቱ ድጋፍ ለማግኘት ወደ ልዩ ልዩ ሀገራት ተጉዟል፡፡ በዚህም ውጤት አግኝቶበታል፡፡ ለምሳሌ በ1967 ወደ ቻይና ተጉዞ እነ ማኦ ዜዱንግን በማሳመን ለጀብሃ የመሳሪያና የስልጠና ድጋፍ አስገኝቷል (በዚያን ጊዜ ወደ ቻይና ሄደው ስልጠና ካገኙት መካከል አንዱ የአሁኑ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው)፡፡ ወደ ኩባ በመሄድም የጀብሃ ተዋጊዎች የፓራ-ኮማንዶ ስልጠና እና የመሳሪያ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ከሶሪያና ከኢራቅም ብዙ እርዳታ አስገኝቷል፡፡ የእስያ-አፍሪቃ የወዳጅነት ኮንፈረንስ በተካሄደበት ጊዜም ድርጅቱን በመወከል ተሳትፏል፡፡
ከዚህ ቀደም በጻፍኳቸው ጽሑፎች እንደገለጽኩት “ጀብሃ” የሚባለው ድርጅት በኤርትራዊያን ክርስቲያኖች ላይ ውገና ያካሄድ ነበር፡፡ የዚህም መነሻ “ለኃይለ ሥላሤ መንግሥት አሳልፈው የሸጡን ክርስቲያኖቹ ናቸው” የሚለው የተሳሳተ ፍረጃው ነው፡፡ እርግጥ የኃይለ ሥላሤ መንግሥት ኤርትራዊያን ሙስሊሞች ወደ ስልጣነ-መንግሥቱ እንዳይቀርቡ አድርጓል፡፡ በመንግሥት ስልጣንም ሆነ በፓርላማው ውስጥ የተሰገሰጉት በአብዛኛው ደገኛ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ይሁንና የእነዚህ ጥቂት ሰዎች ምግባር ሁሉንም የኤርትራ ህዝበ ክርስቲያን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ጀብሃ ኤርትራዊያን ክርስቲያኖችን በጥርጣሬ ማየቱና በድርጅቱ ውስጥ የነበሩትንም እያሳደደ መምታቱ ትክክል አልነበረም፡፡ ድርጅቱንም ለውድቀት ያበቃውም ይህ የውገና አቋሙ ነው፡፡
ይህ ወገንተኛ አቋም የሁሉም የጀብሃ አባላት አቋም አልነበረም፡፡ በመሆኑም በ1969 በወታደራዊ ግንባር የተሰለፉት አባላት ፓርቲው ራሱን እንዲፈትሽና እንዲያሻሽል የሚቀሰቅሰውን የአዶብሃ ኮንፈረንስ ጠሩ፡፡ በኮንፈረንሱ ማጠቃለያም ድርጅቱ ራሱን እስካላሻሻለ ድረስ ካይሮ የሚገኘው ላዕላይ ምክር ቤት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የካይሮው ምክር ቤት ኮንፈረንሱን በህገ-ወጥነት ፈረጀው፡፡ ሆኖም በከሰላ የሚገኘው ኢድሪስ ገላውዴዎስ የተነሱትን ጥያቄዎች እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከአመራሩ ጋር ተጋጨ፡፡ በድርጅቱ ውስጥ የነበረውንም ከፍተኛ ስልጣን አጣ፡፡ ይሁንና የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበርነቱን አልተወውም፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ የጀብሃን ወታደራዊ ክንፍ በሚመራበት ወቅት ነበር በዑሥማን ሳልህ ሳቤ እና በኢሳያስ አፍወርቂ የሚመሩት ቡድኖች ከድርጅቱ ተንገጥለው የወጡት፡፡ የጀብሃ አመራር እነዚህን ቡድኖች በወታደራዊ ጥቃት የማጥፋት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ግን ውሳኔው ኤርትራዊያንን የበለጠ ይከፋፍላል በማለት ተቃወመው፡፡ ወታደራዊ ዘመቻዎችንም እንደማያስፈጽም ለድርጅቱ መሪዎች ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የድርጅቱ መሪዎች ኢድሪስን ከወታደራዊ መሪነቱ አስነሱትና በውጪ ጉዳይ ላይ ሾሙት፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ድርጅቱን በውጪ ጉዳይ ሃላፊነት በሚመራበት ወቅት ድርጅቱ በጣም እየተዳከመ ነበር፡፡ ቢሆንም ኢድሪስ በውጪው ዓለም የድርጅቱን ስም የሚያስጠሩ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ1978 ታላቋ ሶቭየት ህብረት ጀብሃ ከደርግ መንግሥት ጋር እንዲወያይ በፈጠረችው መድረክ ላይ ድርጅቱን ወክሎ ተገኝቷል፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ጀብሃ ፍርስርሱ ወጣ፡፡ በኤርትራ ምድር የቀረው ትርፍራፊ ጦሩ በሻዕቢያ ተደመሰሰ፡፡ ድርጅቱም በስም ያለ በተግባር ግን የሌለ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህንን የተመለከተው ኢድሪስ ገላውዴዎስ በድርጅቱ መሪዎች ላይ ከፍተኛ ሂስ ጽፎ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ ሁሉንም ኤርትራዊያን በእኩል ሁኔታ አለማየቱና ዲሞክራሲያዊ አሰራር የሌለው መሆኑ ለሞት እንዳበቃው አሰመረበት፡፡ በመሆኑም ከጀብሃ አመራር ራሱን አገለለ፡፡
በ1991 ሻዕቢያ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር ኢድሪስ ገላውዴዎስ ለአዲሱ መንግሥት እውቅና እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ እነ ኢሳያስ አፈወርቂም ወደ ሀገር መጥቶ በስራ እንዲረዳቸው ጥሪ አቀረቡለት፡፡ ኢድሪስም ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ሀገር ውስጥ ገባ፡፡ ከ1991-1993 በነበሩት ዓመታትም ከዶ/ር በረከት ሃብተ ሥላሴ ጋር የሪፈረንደም ኮሚሽን ሃላፊ ሆኖ ሰራ፡፡ በተከታዮቹ ዓመታት ደግሞ የህገ-መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል ሆኖ በመስራት ላይ እያለ እ.ኤ.አ በ1998 አረፈ፡፡ የቀብር ስርዓቱም በብሄራዊ ደረጃ ተፈጸመለት፡፡
የጀብሃ አባላት ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ሁለት ዓይነት እይታዎች ነው ያላቸው፡፡ ኢድሪስ ድርጅቱን ለመመስረትና የወታደራዊ ክንፉን መሰረት ለመጣል ያደረገውን አስተዋጽኦ በበጎ ዐይኑ ይመለከቱታል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን አድርባይ ሆኖ ድርጅቱን ከድቷል በማለት ይኮንኑታል፡፡ የሻዕቢያ አባላትና ደጋፊዎች ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስን በበረሃ ውስጥ የተገኘ ተክል አድርገው ነው የሚያዩት፡፡ “ጀብሃ ከውጥኑ ጀምሮ በርሱ ቢመራ ኖሮ ኤርትራዊያን እርስ በራሳቸው አይጋደሉም ነበር” በማለትም ያምናሉ፡፡ ሐቁ የትኛው እንደሆነ ታሪክ ነው የሚፈርደው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስ ማለት ከላይ የተገለጸው ሰው ነው፡፡
—–
ምንጮች
ኢሀአደግ መጪውን ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አመራሮቹን እያሰለጠነ ነው።
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህደግ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የአስልጣኞች ስልጠና ለከፍተኛ አመራሮቹ እየሰጠ ነው።
24 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ሲያቀኑ ባህር ላይ ሰጠሙ
ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን አገር ውስጥ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ ሞቻ በሚባለው የወደብ ከተማ አቅራቢያ ሲደርሱ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ 24ቱም አትዮጵያውያን አልቀዋል። የሁሉም አስከሬን መገኙቱን ባለስልጣኑ ሲናገሩ፣ የተረፉ ካሉም በማፈላለግ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ወር ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ማለቃቸው ሲታወስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባህር ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር …
የደብረማርቆስ የመሰናዶ ተማሪዎች የመንግስትን ፖሊሲ ተቃወሙ
ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪዎች ኢህአዴግን እንዲመርጡ በሚል በግዳጅ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ተማሪዎች ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሰጥተዋል ። ኢህአዴግ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን የመሰሉ ሰዎችን አሸባሪዎች ማለቱ ትክክል አለመሆኑን የሚገልጹት ተማሪዎች፣ ኢህአዴግን የሚበልጡት በመሉ አሸባሪ እያለ እንደሚፈርጃቸው ተናግረዋል ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚኖርበት ቤት 400 ሺ ብር እንደሚከፈልበት የተናገሩት ተማሪዎች፣ …
በአዳማ በሚካሄደው ስብሰባ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሳይቀሩ ሞባይል ስልክ ይዘው እንዳይገቡ ተከለከሉ
ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከመላው አገሪቱ ለተውጣጡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መጪውን ምርጫ በተመለከተ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን፣ ከስልጠናው በፊት ማንኛውም ባለስልጣን ስልክ ይዞ መግባት እንደማይችል ጥብቅ የሆነ መልእክት በመተላለፉ፣ ሁሉም ባለስልጣናት ስልካቸውን መኪናቸው ውስጥ እየተዉ ወይም ለሹፌሮቻቸው እየሰጡ መግባታቸው ታውቋል። ወደ ስብሰባው የሚገባ ሰው ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መያዙንና አለመያዙን ለማረጋገጥ …
እነ አቶ አንጋው ተገኝ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጥቅምት ወር በጎንደር፣ በትግራይና በጎጃም አካባቢዎች የተያዙ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ፍድር ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የሰማያዊ፣ የአንድነትና የመኢአድ ፓርቲዎች የዞን አመራሮች ታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ፣ አመራሮቹ ለ3ኛ ጊዜ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ “ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ …
የኦሮምያ ክልል የአድማ ብተና ዋና አዛዥ እስከ ጠባቂዎቻቸው አረፉ
ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በተለይም በአምቦ፣ በአለማያና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ለተፈጸሙ ግድያዎችና በሌሎች አካባቢዎች ለደረሱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑት ኮማንደር ፣ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓም ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና ተገልብጦ ከ3 ጠባቂዎቻቸው ጋር በሂርናና አሰበ ተፈሪ መካከል በሚገኝ አንድ ገደላማ ቦታ ላይ ገብተው ህይወታቸው ወዲያውኑ አልፎአል። ኮማንደሩ የተሳፈሩበት …
ኢሀአደግ መጪውን ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አመራሮቹን እያሰጠ ነው።
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሀደግ በመጪው ግንቦት ውር የሚካሄደውን ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የአስልጣኞች ስልጠና ለከፍተኛ አመራሮቹ እየሰጠ ነው።
በጋራ ህዝቡን የምናታግልበትን መንገድ እንድንፈጥር ጥሪዬን አቀርባለሁ – (የሰማያዊ አመራር ኢያስፔድ ተስፋዬ)
(አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚና የወጣቶች ክፍል ሃላፊ ናቸው። በቅርቡም ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት/ባንክ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ተባረዋል። በነገረ ኢትዮጵያ ብዙ ጊዜ ጽሁፎችን የሚያቀርቡ ወጣት ፖለቲካኛ ናቸው። በጋራ ህዝቡን ማታገል እንደሚገባ በመገልጽ በተለትም ለሰማያዊና ለአንድነት ፓርቲ ጥሩ ያቀረቡበት ጽሁፍን ያንብቡ) ለውጡ ይመጣል! ጥያቄው ግን ተዘጋጅተናል ወይ? ————————————————- ስለ 1966ቱ ለውጥ ብዙ ተብሏል፡፡ በለውጡ ወቅት […]
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ዲሴምበር 30, 2014
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የአንድነት፣ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ: – በሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ ዘጋቢ
የአንድነት፣ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ! ለጥር 19/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው! በሽብር ክስ ተጠርጥረው የመኢአድ፣ የሰማያዊና የአንድነት አመራሮች በዛሬው እለት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን የአንድነት ፓርቲ ጠበቃ አቶ ገበየሁ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም በነበረው ሰነድ፣ አሻራ እና ቃላቸውን ወስደዋል እንዲሁም አስረላጊ ምርመራም አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ምንም ምርመራ ያደረጉት ነገር ስላልተገኘ ደምበኞቼን የዋስትና መብታቸው […]
የቦኮ ሐራም ጥቃት በምዕራብ አፍሪቃ
አንዳድ አጥኚዎች እንደሚሉት አራቱ መንግሥታት በጋራ ከመቆም ይልቅ አንዱ ሌላዉን ለማጥቃት አሸባሪዉን ቡድን እንደመሳሪያ እየተጠቀሙበት ነዉ
ጤናና ተፈጥሮ በ2014
አምና ሊባል አንድ ቀን የቀረዉ ጎርጎሪዮሳዊዉ 2014ዓ,ም በጤናዉ ረገድ ዓለም ያደናገጡ በሽታዎች የተከሰቱበት ነበር። በዚህ ዓመት ከታዩት በሽታዎች ሳርስ፣ ማርቡርግ እና የወፍ ጉንፋን በየተቀሰቀሱበት አካባቢ ሲወሰኑ፤ ኤቦላ ግን መነሻዉ ምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ቢሆንም የተሐዋሲዉ ስርጭት በርካታ ቦታዎችን ነካክቷል።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በሳዑዲ አረቢያ
አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ አዲስ ሕግ አርቅቋል።
በልዩ ቅናሽ የመጻሕፍት ሽያጭ ወር
‹‹ከአንድ ሊቅ በሚጠበቅ መልኩ በተጠያቂነት ደረጃ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት መላ ዘመናቸውን አሳልፈዋል›› – የሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዜና ሕይወት እና ዕረፍት
ከትምህርት ቤትና ከመጻሕፍት ያገኙት ዕውቀት አራት ዓይና ያደረጋቸው ሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በተጠያቂነት ደረጃ የሚገኙና አገልግሎታቸውም ሙሉ ነበር፡- ቀዳሽና መዘምር፤ ጋዜጠኛና ሰባኬ ወንጌል፤ ጸሐፊና ተርጓሚ፤ አስተዳዳሪና መምህር፤ የአውራጃ አብያተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፤ ኤርትራን ጨምሮ የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስምንት መምሪያዎች ምክትልና ዋና ሓላፊ፡፡ ሊቁ በሓላፊነት በተመደቡባቸው ቦታዎች …![]()
ለውጡ ይመጣል! ጥያቄው ግን ተዘጋጅተናል ወይ? ነው፡፡ Eyasped Tesfaye
ለውጡ ይመጣል! ጥያቄው ግን ተዘጋጅተናል ወይ? ነው፡፡
————————————————-
ስለ 1966ቱ ለውጥ ብዙ ተብሏል፡፡ በለውጡ ወቅት የነበሩትን ሰዎችም ሆነ ሌሎቹን የሚያስማማ አንድ ነገር ቢኖር የለውጡ ግብታዊነት እና ለውጡን ሊሸከም የሚችል ድርጅት በወቅቱ አለመኖሩ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን ለውጡ ገና ነው ብለን ብንዘናጋ እንደ ኃይሌ ፊዳ ልንሳሳት የምችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ይመስሉኛል (ሀይሌ ፊዳ ከብርሀነ መስቀል ጋር ባደረጉት ውይይት ለውጡ ገና ነው ብዙ አመታትንም ይፈልጋል ብሎ ነበረ)፡፡ ከዚያ ይልቅ ለውጡን ለመቀበል በሚያስችል ተክለ ሰውነት ላይ ለመገኘት ምን እናድርግ የሚለው ላይ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡
ብዙዎች በመኢሶን እና በኢህአፓ መካከል የነበረው ልዩነት ያለፈውን ትውልድ ዋጋ እንዳስከፈለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንዳንዶች የሁለቱ ልዩነት የእናቸንፋለን እና የእናሸንፋለን የቃላት ጨዋታ ነበረ ሲሉ በሚያነሱት ሀሳብ ባልስማማም (ልዩነታቸው መሰረታዊ ነበር ብዬ ስለማምን) የሁለቱ ልዩነት ግን ትውልዱን ዋጋ ማስከፈሉን የማይቀበል ማንም ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡
ስለሁለቱ ልዩነት ሲነሳ ቢያንስ በሁለት ወቅቶች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
የመጀመሪያው ከለውጡ በፊት የነበረው እና ከለውጡም በኋላ እስከተወሰነ ድረስ አብሮ የዘለቀው የሁለቱ ፓርቲዎች የመደጋገፍ ጊዜ ነው፡፡ በአልጀርስ የነበረው የኢህአድ/ኢህአፓ መስራች ቡድን ከሀይሌ ፊዳው የመኢሶን መስራች ቡድን ጋር በአንዳንድ ነጥቦች ሳይስማሙ ቢለያዩም ልዩነታቸው ሰፊ የሚባል አልነበረም፡፡ ለዚህም ማሳያው የኢህአፓ ልሳን የነበረችው የዴሞክራሲያ የመጀመሪያ ዕትሞች እና የመኢሶን ልሳን የነበረችው የሰፊው ህዝብ ድምፅ ጋዜጣ የመጀመሪያ ዕትሞች በይዘት መመሳሰል እና በሀሳብ መደጋገፍ ነው፡፡ ይህ ሂደት እነ ሀይሌ ፊዳ ከውጪ ወደ ሀገር ቤት እስኪገቡ ድረስ የቀጠለ እንደነበርም ታሪክ መዝግቦ ያስቀመጠው ሀቅ ነው፡፡
ሁለተኛው ወቅት ደግሞ ለውጡ ከመጣ በኋላና እነ ሀይሌ ፊዳ ሀገር ቤት ከገቡ በኋላ ያለው እና በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት መሰረታዊ እየሆነ የሄደበት እና በጣም የተለጠጠበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በመኢሶን እና በኢህአፓ አመራሮች መካከል ግንኑነት ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም (ለአብነትም ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ከዶ/ር ሀይሌ ፊዳ ጋር፤ ነገደ ጎበዜ ከአለማየሁ ሀይሌ(ደርግ ውስጥ ሰርጎ የገባ የኢህአፓ ሰው ነው ይባል ነበር) ጋር ተገናኝተው አውርተዋል) ከረፈደ በኋላ የተደረገ ውይይት በመሆኑ ያመጣው ለውጥ አልነበረም፡፡
በእኔ እይታ ለሁለቱ ድርጅቶች አለመስማማት አቢዩ ምክንያት ከለውጡ በኋላ ኢህአፓ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት (ማስ ቤዝ) ማግኘቱ በመኢሶን በኩል ለደርግ ሂሳዊ ድጋፍ እየሰጡ መቀጠል ይሻላል ወደሚለው ሀሳብ እንዲሄዱ የገፋቸው ይመስለኛል፡፡ ከመነሻው የነበራቸውን አነስተኛ ልዩነት አጥብበው በጋራ ቢሄዱ ኖሮ አንዳቸው ተለይቶ ህዝባዊ መሰረት የሚገነባበት እና ሌላኛቸው ህዝባዊ መሰረት ለመያዝ ከወታደሩ ጋር የሚሰለፍበት ሁናቴ አይኖርም ነበር፡፡
ለማንኛውም ይህን ያነሳሁት በታሪኩ ላይ ለመነታረክ ሳይሆን ዛሬም ከታሪክ ሳንማር ያለፈውን ስሀተት እንዳንደግም ካለኝ ፍርሀት ነው፡፡
ዛሬ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ እና አንድነት በጋራ ሆነው ለሚመጣው ለውጥ ራሳቸውን ካላዘጋጁ በስተቀር ከለውጡ በኋላ ልዩነታቸውን አጥብበው ለውጡ ተፈጥሯዊ ይዘቱን ጠብቆ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ለማስቀጠል ይችላሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ልዩነታቸውን አሁን ላይ ማጥበብ እና በጋራ መቆም ካልቻሉ ከለውጡ በኋላ እንደ ጠላት የሚተያዩበትም እድል እጅግ በጣም የሰፋ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በተለይም ደግሞ ለውጡን ተከትሎ ከሁለት አንዳቸው ከፍ ያለ መስዋዕትነት የከፈሉ እንደሆነ፡፡
የተቃዋሚዎች በአንድ መቆም ለለውጡ ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለውጡን ለማምጣትም የተሻለው እና አጭሩ መንገድ ነውና የየፓርቲዎቹ አመራሮች(በተለይም የሰማያዊ እና የአንድነት) ዛሬ ነገ ሳይሉ ቁጭ ብለው በመነጋገር ወደ አንድ የሚመጡበትን እና በጋራ ህዝቡን የሚያታግሉበትን መንገድ እንዲፈጥሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ፡፡
በደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ መረር ያለ ተቃውሞ ተነስተዋል:: በጎጃም የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ
በደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ መረር ያለ ተቃውሞ ተነስተዋል::
በጎጃም የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል፡፡ በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርገዋል እየጠደረጉ ሲሆን ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል፡፡
ተማሪዎቹ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ ከሆነ ለተቃዋሚዎችም ይፈቀድ፣ ለምን ለግጭት የሚጋብዙ ቅስቀሳ ትቀሰቅሳላችሁ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ምሁራንንም ጭምር ለስደት የዳረገ ነው፣ ከቻይና እና ከኮሪያ የሚያስተሳስረን የታሪክም ሆነ የባህል መሰረት የለንም፣ ኢህአዴግ 23 አመት ያልተገበረውን ዴሞክራሲ ሊያስተምረን አይችልም›› የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት ተቃውሞዎች እየተነሱ ሲሆን በተለይም ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ ላይ ተማሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግ ሌላ፣ ኢህአዴግ ሌባ›› የሚል ጩኸት በማሰማታቸው ሲሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ 20፣ 20 ሆነው በየክፍሉ እንዲሰለጥኑ ተደርገዋል፡፡ በተለይ በደብረማርቆስ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹ የካድሬ ስልጠና አንሰለጥንም በማለት መረር ያለ ተቃውሞ እያሰሙ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የትልቁ ዋርካ ትልቁ ቅርንጫፍ
አለቃ ገብረሃና ማን ናቸው?
ሰለዋት ከልዩ ልዩ አካባቢዎች
የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ
በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክንበመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡
የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል፡፡
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል፡፡
በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣ ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል፡፡
ተጠያቂነትም በተመለከተ ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራም ለሚያስከትለው ማንኛውም የወንጀል ድርጊት ወይም የፍትሐብሄር ጉዳት የፕሮግራሙ ሃላፊና የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪው በአንድነት ተጠያቂ ይሆናሉ ይላል፡፡
በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል መረጃ መረብ አማካይነት የቀረበ ፕሮግራምን ቁጥጥርን በተመለከተ ከህብረተሰቡ በቅሬታ መልክ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመመርመር፣ተቆጣጣሪ የመመደብ ስልጣን ወደፊት ለሚቋቋመው ባለስልጣን መ/ቤት ሃላፊነቱን ይሰጣል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የቴሌቪዥንን ከአናሎግ ወደዲጂታል ሽግግርን ለማቀላጠፍና የግል ቴሌቪዥን ለመፍቀድ ይረዳል ተብሎአል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢትዮጵያ የሚዲያ ባለስልጣን የሚባል መ/ቤት ይቋቋማል፡፡
የብሮድካስት አግልግሎት የሚመራበትን ሥርዓት ለመደንገግ ከ15 ዓመታት በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 178/1991 የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ፈቃድ ለግል ባለሃብቶች የፈቀደ ቢሆንም ይህ ተግባራዊ ሳይሆን አዋጁ በቁጥር 533/1999 የተሻሻለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተሸሻለውም አዋጅ ቢሆን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያ የተፈቀደ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ኢትዮጵያ ለዚህ ደረጃ ገና አልበቃችም በማለት አዋጁ እንዳይፈጸም እስካሁን ድረስ መከልከሉ የሚታወቅ ነው፡፡
በኮምቦልቻ የገዢውን ፓርቲ ካድሬዎች በጥያቄ ያፋጣጡ ተማሪዎች ህዝብ ልታሳምጹ ነው የሚል ማስጠንቀቂያዎች ደረሳቸው
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሮብ ጀምሮ ለ3 ቀናት በተካሄደው የመሰናዶና የመምህራን የፖለቲካ ስልጠና ላይ የገዚውን ፓርቲ ካድሬዎች በጥያቄ ከማፋጠጥ ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው ዘረኝነት፣ የፍትህ እጦትና ሙስና ላይ አስተያየቶችን የሰጡ ተማሪዎች ከስብሰባው መጠናቀቅ በሁዋላ ተማሪውንና ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት አስባችሁዋል በሚል ማስጠንቀቂያና ባስፈራሪያ እንደደረሳቸው ዘጋቢያችን ገልጻለች። ለተማሪዎች በሚሊኒየም ትምህርት ቤት በፕላዝማ የተደገፈ …
ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል። አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ …
የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ
ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክንበመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት …
History | ያልሰመረው የቤልጅየም ኢትዮጲያን የመግዛት ውጥን
(ወልደብርሃን ስሁል) የዛሬ መቶ ሰባ ዓመት አካባቢ አንዲት “ሚጢጢየ” አውሮፓዊት ሃገር ማንም ሳይቀድማት ኢትዮጵያን በጉልበት ይዛ ቅኝ ለመግዛት “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብላ” ቆርጣ ተሰናዳች። በቆዳ ስፋቷ አንድ ትልቅ ወረዳ እምታክል ናት። አፍሪካ ውስጥ ግን የራሷን መቶ እጥፍ የሚያክል ግዛት መቆጣጠር እሚያስችል አቅምና እብሪት ነበራት። ህልሟን ለማሳካት ፕሮጀክት ቀርፃ feasibility study አካሄደች። እቅዷና ጥናቷ ያነጣጠረውም በዘመነመሳፍንቷ ኢትዮጵያ ላይ ነበር። የቀይ ባህር አካባቢ ደከም ባለ አውሮፓዊ ሃይል እንዲያዝ ትሻ የነበረችው ታላቋ ብሪታንያም ይሁንታ ሰጠቻት፤ በወርራ ቅኝ ልትገዛን ቆርጣ ለተነሳችው ቤልጅየም! ቤልጅየም ለኢትዮጵያ ያሰበችው ፕሮጄክት ብሎንዲል ከሚባል እብሪተኛ ሰው የጀብድ ልክፍት ጋር የተቆራኘ ነበር። ግብፅ በወርኔር ሙዚንጀር፤ ጣልያን በፔትሮ አንቶኖሊ ምን እንዳደረጉን ጠንቅቀን እናውቃለን። ከነሱ በፊት ቀድሞ ስለተሰናዳልን የብሎንዲል Humanitarian Mission ግን ብዙ አናውቅም። ነገሩ ያስገርማል እንጂ አያስቅም። “ገድለ‐ብሎንዲል” በጥቂቱ እንዲህ ነበር፦ የቤልጂግ መንግስት መጀመርያ በ1841 ከፍተኛ በጀት መድቦ ብዛት ያላቸው የስለላ ወኪሎቹን ወደ ግብጽ አሰማራ። ወኪሎቹም “ለሳይንሳዊ ጥናት እና ለሰብአዊ ተልእኮ” በሚሉ ሽፋኖች ካይሮ ላይ ከትመው ስለ ኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩ። ማንኛውንም ዓይነት መረጃ በዝርዝር እየቀራረሙ ከሚያቀርቡት ሪፖርት የቤልጂየም ንጉስ ቀዳማዊ ሊዮፖልድ “በውስጧ ሁከት የነገሰባት ኢትዮጵያን” በቀላሉ መውረርና መቆጣጠር እንደሚችል አመነ። ለወረራም ቋመጠናም የሰላዮቹ አስተባባሪ በአካል ወደ ኢትዮጵያ ሂዶ “ሰብዓዊ ተልእኮ” የሚል ስም ያለው ጉብኝት እንዲያካሂድ አዘዘው። ዋናው ተልእኮው ግን ለወረራ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር እና ባስቸኳይ እሚተገበር የድርጊት መርሃ ግብር እንዲያዘጋጅ ነበር። […]
የካስትሮ ወንድሞች፣ የአፍሪካ ወንድሞች እና ወንድም ኦባማ፣
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ኩባ በመጨረሻ ከቀዝቃዛው ጦርነት በአሸናፊነት ወጣችን? እ.ኤ.አ ጃኗሪ 1959 ፕሬዚዳንት ፉልገንሲዮ ባቲስታንን ከስልጣን ካባረሩ በኋላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ካስትሮ እንዲህ ብለው ነበር፣ “አምባገነን አይደለሁም፣ ወደፊትም እሆናለሁ ብዬ አላስብም፡፡ በጠብመንጃ ኃይል ስልጣንን አልይዝም”፡፡ በዚያ መግለጫ …
የትናንትናውን የቢሮ ማስተዋወቅ ቅስቀሳ ተከትሎ የኮምቦልቻ አንድነት የድርጅት ጉዳዮች ሀላፊ በደህንነትና ጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ተይዘው ተጠየቁ፡፡
ትናንት በ19/04/07 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ የኮምቦልቻ ጽ/ቤት መከፈቱን ተከትሎ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት የአንድነት አመራሮች መካከል አቶ ተማም መሀመድ በከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ተጠርተው ተጠይቀዋል፡፡ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎቹ ‹‹እናንተ ያለጊዜው የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጋችሁ ነው፤ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር እያሰባችሁ ነው፤ሳታሳውቁ ነው የምትሰሩት›› የሚሉ ጥያቄዎች ያቀረቡባቸው ሲሆን፤ አቶ ተማም እኛ ቢሯችንን ስንከፍት ተገቢውን የማሳወቂያ ደብዳቤ ለሚመለከታቸው […]
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ዲሴምበር 29, 2014
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
ሮማ፤ ከሰጠመችዉ መርከብ ነፍስ የማዳኑ ተግባር መጠናቀቁ
አድርያቲክ ዉቅያኖስ ዉስጥ መስጠም ከጀመረችዉ መርከብ ተሳፋሪዎችን የማዳኑ ተግባር መጠናቀቁን የጣሊያን መንግሥት አስታወቀ።
የዓለም አበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች 2014
«ዓለም ከሁለተኛዉ ያዓለም ጦርነት ወዲሕ የዘንድሮን ያክል ሕዝብ ተሰዶ፤ተፈናቅሎባት አያዉቅም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለበርካታ ሕዝብ አስቸኳይ እርዳታ እንዲያቀርብ የዘንድሮን ያክል ተጠይቆ አያዉቅም።»
የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉዝግብና ማስተባበያዉ
የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) ከአፋር መስተዳድር ገዢ ፓርቲ ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)ጋር ያካሄደዉ ዉህደት ህገ ወጥ ነዉ በሚል በዶቼ ቬለ የተላለፈዉ ቃለ መጠይቅ ከሃቅ የራቀ ነዉ ሲል አስተባበለ።
ሶማልያና አሸባብ የዉስጥ ሽኩቻ
የሶማልያ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ የመረጃ ኃላፊ እንደሆኑ የተነገረላቸዉ ግለሰብ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በሶማልያ ለሚገኝ የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልና ለሶማልያ መንግሥት ጦር እጃቸዉን ከሰጡ በኋላ ግለሰቡ ከዓመት በፊት ቡድኑን ጥለዉ መዉጣታቸዉን አሸባብ ዛሬ አስታወቀ።
ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያ ታገዱ:: የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል::ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል::

ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: ነዋሪነት በጀርመን የሆነው እና ለአርበኞች ግንባር ትግል ታላቅ አስታውጾ እንዳበረከተ የሚነገርለት አቶ ካሳዬ መርሻ በግንባሩ አባላት አስፈላጊዉን ወጪ ተሸፍኖለት ለጉዞ ሲንደረደር በሻእቢያ መከልከሉ በውጪ የሚኖሩ የግንባሩ አባላትን ያሳሰበ ቢሆንም ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::
በዚህ ምክንያት በውጪ የሚኖሩ የአርበኞች ግንባር አባላት እና ደጋፊዎች የተወከለው አቶ ካሳዬ እንዳይመጣ በሻእቢያ መከልከሉን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በደብዳቤ መላካቸው ሲታወቅ በአስመራ የሚገኙ የግንባሩ አመራሮች ሁኔታውን እንዲፈቱ በደብዳቤያቸው ያሳውቁት አባላቱ በአግባቡ የተወከለው ሰው በውህደቱ ጉባዬ ላይ እንዲገኝ ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል::የወከሉት ሰው በመከልከሉ በውህደቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬም አስምረውበታል::በቂ ሃይል እና ተንካራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት አርበኞች ግንባት አባላቱ በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ ተግተው እንደሚሰሩ እና ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል::
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት በሃገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃገራዊ አቋም እንዳይኖራቸው ሕወሓት/ኢሕ አዴግ በሰርጎ ገብነት እየገባ እንደሚያፋልሳቸው ሁሉ በውጪ የሚኖሩ ድርጅቶችንም እንዲሁ ሻእቢያ በውስጥ ጉዳያቸው እየገባ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንዲሽከረከሩ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል::
ከጀርመን የተወከሉት አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ እንዳይገቡ ካልተፈለገበት አንዱ ምክንያት ከዚህ ቀደም በግንባሩ ላይ በሻእቢያ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን የግንባሩ አባላት እና ታጋዮች ይህንን በደንብ ስለሚያውቁ በውህደቱ ላይ እንዲገኝላቸው ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ሻእቢያ ግን አንድ ጊዜ ጥርስ ስለነከሰበት እንዳይመጣበት ከልክሏል::እንዲሁም በውጪ የሚኖሩ አባላት ውህደቱ ላይ ችግር ካለ እንዲወገድ ወደፊትም ችግሮች እንዳይፈጠሩ አመራሩን ለማስተካከል እና አማራጮችን መጠቀም በሚል ስልት አቶ ካሳዬ የራሱን የፖለቲካ ልምድ ተጠቅሞ ሊያስተካክል ይችላል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች እንዲስተካከሉ በፊትለፊት ይናገራል የሚሉ ፍራቻዎች በሻእቢያ ስላሉ የተወከሉት አባል ወደ አስመራ እንዳይገቡ ከልክለዋል::
አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ ሁለት ጊዜ ካሁን ቀደም ሂዶ ካለምንም ፍርሃት ለሻእቢያ ግንባሩን በተመለከተ ያለውን ችግር እና ወደፊት መሆን የለበትን ጉዳይ ካለፍርሃት አፍረጥርጦ ስለተናገረ እንዲሁም አቶ ካሳዬ የአርማጮ ተወላጅ በመሆኑ በአከባቢው ያለውን እና በግንባሩ ታጋዮች ዙሪያ ያለውን ጉዳይ አንስቶ ካለፍርሃት ለሻእቢያ መናገሩ ለአሁኑ መከልከል ምክንያት ቢሆንም ጉዳዩን ለመፍታት አስመራ እና አውሮፓ ያሉ የግንባሩ አመራሮች እየጥሩ መሆኑን ምንጮች ከአስመራ ተናግረዋል:
******************************************************************************
የወያኔ አየር ሃይል ባልደረቦች ይዘውት የገቡትን ሄሊኮፕተር ተከትሎ አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ የአዲስ አመትን ጋዜጣዊ መግለጫ አስታከው ይናገራሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ ሲሆን የወያኔ ቃል አቀባዮች ሌመንግስት ታማኝ ለሆነ ጋዜጣ ሄሪኮፕተሩ ለማስመለስ ጥረት አለመደረጉን መግለጻቸው ቢታወቅም የሕወሓት ጦር ጄኔራሎች ግን ካልተመለሰ ምሳችንን አስመራ እንበላለን ሲሉ መደንፋታቸው የወያኔ ባለስልጣናቱን አለመናበብ አመልክቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔ በውጪ ከሚኖሩ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመደራደር ማንዣበቡን ፍንጮች ጠቁመዋል:: ወያኔ በስልጣን የመቆየት እድሉ እንደተመናመነ በማወቁ ድርድር የማድረግ ፍላጎት ማሳየቱ እና በታሪክ ልንከስም ነው ያሉት ባለስልጣንን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገዢው ፓርቲ የገባበትን አጣብቂኝ ሊወጣው ባለመቻሉ ውንደለመደው በማዘናጋት ጊዜ መግዣ መፈለጉን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በወህኒ ቤት ዘረፋ እንደተካሄደባቸው አስታወቁ
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በወህኒ ቤት ዘረፋ እንደተካሄደባቸው አስታወቁ ‹‹በደምበኞቼ ላይ ዘረፋ ተፈፅሟል›› ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ‹‹በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ›› አቶ ሀብታሙ አያሌው ‹ከፍተኛ በደል ተፈፅሞብኛል›› አቶ ዳንኤል ሺበሺ በእነ ዘላለም ወርቅነህ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አራት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ በወህኒ ቤት ውስጥ በመንግስት የደህንነት አባላት ዘረፋ እንደተካሄደባቸው ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡ በሽብርተኝነት ተወንጅለው ክስ የተመሰረተባቸው […]
የባህርዳሩ የጥር 3 ህዝባዊ ሰልፍ ዝግጅት ቀጥሏል!!
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጥር 3 በባህርዳር ለሚያደርገው ህዝባዊ ሰልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚያከናውኑ ከፍተኛ የፓርቲው ልዑካን ወደ ስፍራው አምርቷል፤ ቀደም ሲል የሰሜን ቀጠና ሀላፊ አቶ አእምሮ አወቀ የሄዱ ሲሆን አሁን ደግሞ አቶ አስራት ጣሴና አቶ ብሩ በርመጅ ወደ ስፍራው አቅንተዋል። የከተማው አስተዳደር ሰልፉን ላለመፍቀድ አሁንም እያንገላገረ ቢሆንም፤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የሰልፉን ቦታና ጊዜ አንድነት […]


