ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጋቸው ተጠቅሷል

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዘካርያስ አሰፋና የኢንስቲትዩቱ የፋሲሊቲና ሰርቪስ አስተዳደር ኃላፊና የጨረታ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጉይቴ ወልደ ማርያም፣ ሳሊም መሐመድ ባሙኒፍ

ከሚባል አጠቃላይ አስመጪ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር ሙስና ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ 

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዘካርያስ ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም፣ ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ የአዳራሽ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ፑልፒት/አንትሮንስና መድረክ ከእነአክሰሰሪዎቹ ግዢ ሲፈጸም፣ የፌዴራል የግዥ አፈጻጸም መመርያን በመተላለፍ 3,590,179 ብር ክፍያ አላግባብ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡ ግዢው የተፈጸመው ከ1998 ዓ.ም. እስከ 2002 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የተለያዩ ጊዜያት መሆኑንም ክሱ ይጠቁማል፡፡ 

ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለመግዛት በተለያዩ ጊዜያት የወጡትን ጨረታዎች ማሸነፉ የተጠቆመው ሳሊም መሐመድ ባሙኒፍ አጠቃላይ አስመጪ ቢሆንም፣ ሐምሌ 1 ቀን 1997 ዓ.ም. የወጣውን የፌዴራል መንግሥት የግዥ አፈጻጸም መመርያ ቁጥር 28ን የጣሰ መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ መመርያው እንደሚያብራራው በማንኛውም ሁኔታ ጨረታውን ላሸነፈ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋው 30 በመቶ በላይ ቅድሚያ ክፍያ አይፈጸምም፡፡ ነገር ግን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ለአሸናፊው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ከጠቅላላ ዋጋው 60 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ በቅድመ ክፍያ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ 

የግዥ መመርያ ቁጥር 28 አንቀጽ 2 እንደሚያስረዳው፣ ቅድመ ክፍያ የሚፈጸመው አሸናፊው ድርጅት በቅድሚያ ክፍያ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ ብቻ መሆኑን ቢደነግግም፣ ዋና ዳይሬክተሩ ግን ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ያለምንም ዋስትናና ከመመርያ ውጪ 60 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ያለዋስትና እንዲከፈል መፍቀዳቸውን፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

በሌላ በኩል የመንግሥት የግዥ ሥርዓትን ለመወሰንና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲውን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 430/1997 አንቀጽ 43 እና የግዥ መመርያ ቁጥር 28 አንቀጽ 11.14 ላይ የተደነገገውን፣ ተከሳሾቹ መተላለፋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ድንጋጌዎቹ እንደሚያስረዱት፣ የጨረታው አሸናፊ ቢያንስ የውሉን ዋጋ አሥር በመቶ ለውል ማስከበሪያነት ለመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ማስያዝ እንዳለበት ቢገልጽም፣ ድንጋጌውን በመተው ግዴታዎቹ በውሉ እንዳይካተቱ ማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ አሸናፊው ድርጅትም በድንጋጌው መሠረት ገቢ ማድረግ ያለበትን ገንዘብ እንዳላስያዘ ክሱ አክሏል፡፡ 

የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን በውሉ መሠረት ገቢ ማድረግ ሲገባው ሳያደርግ ቢቀር፣ በግዥ መመርያው መሠረት ዕቃውን ካላቀረበበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ዜሮ ነጥብ አንድ በመቶ በጠቅላላ ሒሳቡ (በተከፈለው መጠን) ተባዝቶ ቅጣት እንደሚከፍል መደንገጉን ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ ይህንን ባለመፈጸማቸው መንግሥት 1,058,953.4 ብር በድምሩ ማጣቱን ጠቁሟል፡፡ 

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስና አቶ ተስፋዬ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ ጠቅላላ አስመጪው አቶ ሳሊም መሐመድ (በሌሉበት) በልዩ ወንጀል ተካፋይነት የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

አቶ ሳሊም በሌሉበት የተከሰሱ ሲሆን፣ አቶ ዘካርያስ የተጠቀሰባቸው የሕግ አንቀጽ ዋስትና እንደሚከለክል ተነግሯቸው ክሳቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ታዟል፡፡ አቶ ተስፋዬ የተከሰሱበት የወንጀል ሕግ ዋስትና እንደማይከለክል ተገልጾ በ7000 ብር ዋስትና ውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የአቶ ሳሊምን መቅረብ ለመጠባበቅ ለሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ 

 

ውኃ እስኪሞላ የሚጠበቀው ግልገል ጊቤ ሦስት በአምስት ተርባይኖች ሊጀምር ነው

የግልገል ጊቤ ሦስት ኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ግንባታው ከ92 ከመቶ በላይ ተጠናቆ ግድቡ ውኃ ማጠራቀም እንደጀመረ ተገልጾ፣ በክረምቱ ወራት ጥሩ ዝናብ ማግኘት ከቻለ በአምስት ተርባይኖች ኃይል ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑ ተነገረ፡፡ 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንዳስታወቁት፣ የፕሮጀክቱ ግንባታ በአብዛኛው ተጠናቋል፡፡ ከ1,870 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው ጊቤ ሦስት፣ በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላው የማመንጨት አቅሙ ግማሽ ያህሉን ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

በጠቅላላው አሥር ተርባይኖች ያሉትና በአንዱ ብቻ 187 ሜዋ ጋት ኃይል የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት፣ ቁመቱ 276 ሜትር የሚረዝም ግድብ አለው፡፡ ምንም እንኳ የዚህ ግድብ ቁመት ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ ባይጠናቀቅም፣ ውኃ የመያዝ አቅም ላይ በመድረሱ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ግድቡ ውኃ እንዲያጠራቅም መዘጋቱን ኢንጂነር አዜብ አስታውቀዋል፡፡ 

ግልገል ጊቤ ሦስት ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በመንግሥት ከተገነቡ አራት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በርዝማኔው ከአፍሪካ ትልቁ ሲሆን፣ 11.8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው፡፡ ከቻይና መንግሥት ከተገኘ 470 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጨምሮ በጠቅላላ ወጪው 1.47 ቢሊዮን ዶላር እንደወጣበት የሚነገርለት ጊቤ ሦስት፣ አካባቢያዊ ተፅዕኖው ሰፊ ነው ተብሎ በርካታ ተቃውሞዎች ሲነሱበት መቆየቱ አይዘነጋም፡፡  

 

 

 

የምስክሮች ቃል እንዳይዘገብ ፍርድ ቤት ከለከለ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት)፣ የአረናና ሰማያዊ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ከሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰማት ጀመረ፡፡

ክሱን የመሠረተው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን አቅርቦ ከማሰማቱ በፊት፣ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀጽ 32 መሠረት ምስክርነቱ በዝግ እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹‹በምስክሮቼ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል›› የሚል ነበር፡፡ 

ተከሳሾቹ ግን የተጠቀሰባቸው ሕግ እስከ ሞት ድረስ ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑን በመጠቆምና ምስክርነቱን ሕዝብ መስማት እንዳለበት በመግለጽ፣ ምስክርነቱ በግልጽ ችሎት እንዲታይ ፍርድ ቤቱን በመጠየቅ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ተቃውመዋል፡፡ 

ሁሉንም እስረኞች በመወከል ለፍርድ ቤቱ ያመለከቱት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌው ሲሆኑ፣ ያሉት ማረሚያ ቤት ውስጥ መሆኑንና የምስክሮቹ ዝርዝር ሊደርሳቸው የሚገባ ቢሆንም መከልከላቸውን አስረድተዋል፡፡ 

በመሆኑም በምስክሮቹ ላይ ማንም ዛቻና ማስፈራሪያ ሊያደርስ የሚችልበት መንገድ እንደሌለ ጠቁመው፣ የዓቃቤ ሕግ ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግላቸው አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ምስክርነቱን በዝግ ችሎት የሚያየው ከሆነ፣ ሁሉም ተከሳሾች የግፍ ፍርደኛ ሆነው ወደ እስር ቤት እንደሚመለሱና በቀጣይም ምንም ዓይነት ክርክር እንደማያደርጉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር በማዳመጥ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ፣ ምስክርነቱ በግልጽ ችሎት እንዲታይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ነገር ግን የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የሚናገሩትንም ሆነ ስማቸውን ጠቅሰው የኅትመትም ሆነ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን መዘገብ እንደማይችሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ 

በዕለቱ በአሥረኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ተፈሪ ላይ አንድ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ተሰምተዋል፡፡ 

ተከሳሾቹ አቶ ዘለዓለም ወርቅአገኘሁ ጋሻው፣ የአንድነት አመራር የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ እንዲሁም አቶ ዮናታን ወልዴ፣ አቶ አብርሃም ሰለሞን፣ አቶ ሰለሞን ግርማ፣ አቶ ባህሩ ደጉና አቶ ተስፋዬ ተፈሪ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሪል ስቴትና ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ለማስተላለፍ ልዩ ጨረታ አወጣ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ይህ ልዩ ጨረታ፣ ስምንት ቦታዎችን ብቻ የያዘ ቢሆንም ቦታዎቹ ሰፋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ 

ስድስቱ ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት፣ ሁለቱ ቦታዎች ደግሞ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውሉ ናቸው፡፡ ቦታዎቹ በአራት ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አራት ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት ቀርበዋል፡፡ ዝቅተኛው የቦታ ስፋት 14,089 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 55,386 ካሬ ሜትር ነው፡፡ የቦታዎቹ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 191 ብር ሆኖ 60 ዓመት የሊዝ ዘመን ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን፣ 23,913 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ የሪል ስቴት ቦታና 8,998 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ ቀርቧል፡፡ የእነዚህ ቦታዎች የመነሻ ዋጋም በካሬ ሜትር 191 ብር ነው፡፡ 

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማም አንድ ቦታ ለሪል ስቴት ልማት ቀርቧል፡፡ የቦታው ስፋት 57,752 ካሬ ሜትር መነሻ ዋጋው በካሬ ሜትር 299 ብር ነው፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውል 6,014 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ 

ጨረታው እስከ ሐምሌ 23 ቀን ድረስ ይፋ ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ይከፈታል ተብሏል፡፡ 

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ፣ መሬት በዋነኛነት ለአልሚዎች የሚቀርበው በጨረታ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀላል ፕሮጀክቶች 14 ጊዜ ጨረታ አውጥቷል፡፡ ለሆቴል፣ ለሪል ስቴት፣ ለትምህርትና ለጤና ተቋማት ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ያቀረበው በሁለት ጨረታዎች ብቻ ነው፡፡ 

የመጀመርያው ጨረታ ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ወጥቶ ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. መከፈቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጨረታም የወጡት ቦታዎች ሰፋፊ ቢሆኑም ቁጥራቸው አሥር ብቻ ነበር፡፡ 

ባለሙያዎች አስተዳደሩ የመሬት ዋጋ ንረትን ለማርገብ በርካታ ቦታዎችን ለጨረታ ማቅረብ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡ 

 

የቻይና ሪል ስቴት ኩባንያ በአራት ቢሊዮን ብር ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ሊገነባ ነው

ከፀሐይ ሪል ስቴት ቀጥሎ ሁለተኛው የቻይና ኩባንያ በአራት ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ አኖረ፡፡

ሲኖ ማርክ የተባለው ይህ የቻይና ኩባንያ አገር በቀል ኩባንያ ከሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ ጋር ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት የፈጸመው፣ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት ነው፡፡ 

ግንባታው የሚካሄደው ሳባ ኢንጂነሪንግ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በገዛው አዲስ ብሎክ ሼር ኩባንያ ይዞታ በሆነው፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ 60 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ነው፡፡ 

የሳባ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሳምሶን በኩረ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዚህ ሥፍራ ላይ ከፍታቸው 20 ፎቅ የሆኑ 21 ሕንፃዎች ይገነባሉ፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት ግንባታ አራት ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ በኢንቨስትመንቱ ላይ ሁለቱም ኩባንያዎች እኩል ድርሻ እንደሚኖራቸው ኢንጂነር ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ 

ሕንፃዎቹ በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፉ ሲሆን፣ በተቀረው ቦታ ላይ የተለያዩ የስፖርት ማዕከላት፣ የገበያ ማዕከላት፣ የሕፃናት መጫወቻዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች ይካተታሉ፡፡

ይህ ግንባታ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚጠናቀቅ መሆኑን፣ ሽያጩም ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚካሄድ ኢንጂነር ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ 

የሕንፃዎቹን ግንባታ ለማስጀመር ባለፈው እሑድ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት የሲኖ ማርክ ኩባንያ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ያን ሲን ሊ እንደተናገሩት፣ የሕንፃዎቹ ግንባታ በፈረንሳይ የሕንፃ አሠራር ዘይቤ ይከናወናል፡፡ 

የቻይና ኩባንያዎችን ጨምሮ የህንድ፣ የቱርክና የአውሮፓ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ከተማ በሪል ስቴት ልማት ለመሳተፍ ፍላጎት ከማሳየት አልፈው ፕሮፖዛል በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ 

ነገር ግን መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በራሳቸው መንገድ፣ በሪል ስቴት ልማት እንዲሳተፉ ለማድረግ የጀመረውን የፖሊሲ ጥናት ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ ይገኛል፡፡ 

የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ሲጂሲ ኦቨርሲስ መንግሥት ለውጭ ኩባንያዎች መሬት ስለመስጠትም ሆነ ስለመከልከል አቅጣጫ ከመያዙ በፊት፣ በየካ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ አካባቢ ባገኘው መሬት የሪል ስቴት ልማት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

ሲጂሲ ኦቨርሲስ ከሌላ የቻይና ኩባንያ ጋር በመሆን ያቋቋመው ፀሐይ ሪል ስቴት በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በ2.5 ቢሊዮን ብር በጀት፣ ከፍታቸው 12 ፎቅ የሆኑ የመኖሪያ ሕንፃዎችን እየነባ ይገኛል፡፡ 

አዲሱ የቻይና ኩባንያ ሲኖ ማርክ ከሳባ ኢንጂነሪንግ ጋር ግንባታ የሚያካሂድበት መሬት ባለቤት አዲስ ብሎክ ሼር ኩባንያ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን የሚያመርት ሲሆን፣ ሳባ ኢንጂነሪንግ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ገዝቶታል፡፡ 

ሳባ ኢንጂነሪንግ ከኢትዮጵያ ባሻገር በሩዋንዳ፣ በኡጋንዳ፣ በታንዛኒያ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በመክፈት በውኃ ሥራዎችና በተለያዩ የግንባታና የማማከር ሥራዎች የተሰማራ አገር በቀል ኩባንያ ነው፡፡ ሲኖ ማርክ ደግሞ ከአሥር ዓመታት በላይ በሪል ስቴት ልማት ውስጥ እንደቆየ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ 

 

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በድጋሚ በተደረገበት ኦዲት ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡንና የደኅንነት ደረጃውን አስጠብቆ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ጠንካራ ከሚባሉት አምስቱ አንዱ ተቋም መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

አምስት አባላት ያሉት የዓለም የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ለአሥር ቀናት ባካሄዱት የኦዲት ምርመራ፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና የሚቆጣጠራቸውን ኢትዮጵያ የአየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የበረራ ደኅንነትን ለማስጠበቅ የተሠሩትን ሥራዎችና የተወሰዱ ቁጥጥሮችን በመመርመር ኦዲት አካሂደዋል፡፡

 በዚህም መሠረት ባለሥልጣኑ በአጠቃላይ ውጤት 68.68 በመቶ በማግኘቱ ከዓለም አማካይ ውጤት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን፣ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው አስታውቀዋል፡፡ በዓለም የአቪዬሽን ድርጅት የዓለም አማካይ ውጤት ተብሎ የተቀመጠው 60 በመቶ ነው፡፡ 

ሲቪል ኢቪዬሽን ባለሥልጣን ከተፈተሸባቸው ስምንት ዋና ዋና የኦዲት ይዘቶች ውስጥ በተለይ በአምስቱና ባለሥልጣኑ በራሱ በሚተገብራቸው መስኮች 78 በመቶ በማምጣት ትልቅ ውጤት ማስዝገቡን አስታውቀው፣ ባለሥልጣኑ በሚቆጣጠራቸው ሦስቱ ተቋማት የተገኘው ውጤት 51 በመቶ በመሆኑ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ሊባል እንደሚችል ይፋ አድርገዋል፡፡ ምንም እንኳ በአጠቃላይ ውጤቱ በዓለም ከተቀመጠው አማካይ ውጤት ከፍ ያለ ቢሆንም፣ በሦስቱ ተቋማት የተመዘገበውን ዝቅተኛ አንፃራዊ ውጤት ለማሻሻል ሥራዎች እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ 

ከዘጠኝ ዓመት በፊት ኦዲት ተደርጎ ያስዘመገበው ውጤት 66 በመቶ ነበር ያሉት ኮሎኔል ወሰንየለህ፣ በአሁኑ መጠነ ሰፊና አጠቃላይ ኦዲት ተፈትሾ ያስመዘገው ውጤት፣ ሲቪል አቪዬሽን የመቆጣጠር ብቃቱና ጥንካሬው የታየበት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየትኛውም መዳረሻ የመብረርና የተጓዦችን ደኅንነት የማስጠበቅ ብቃት እንዳለው የተረጋገጠበት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኦዲት ሪፖርቱ መሠረት ምንም ዓይነት መሠረታዊ የደኅንነት ክፍተቶች አለመኖራቸውንም አስታውቀዋል፡፡ 

ከዚህ ባሻገር የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በአሜሪካው የአቪዬሽን አስተዳደር ኦዲት ተደርጎ በዘርፉ ደረጃ አንድ የተባለውን ደኅንነት ደረጃ በማስጠበቅ፣ በአሜሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ያለምንም የደኅንነት ክፍተቶች በረራዎችን ማካሄድ እንደሚችል አረጋግጦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡  

 

 

 

ሚካኤል ዲኖ ይባላል። የአዲስ አበባ ልጅ ነው። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ጋዜጦች እና የሬድዬ ፕሮግራሞች ፅሁፎችን በማቅረብ የጋዜጠኝነት ሙያን እንደተቀላቀለ መረጃዎች ያሳያሉ። በ2002ዓ.ም በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በምትዘጋጀው ፍትሕ ጋዜጣ ላይ በሪፓርተርነት እና በዓምደኝነት እየሰራ፣ ጋዜጣዋ የተደበቀውን የመለስ ዜናዊ ሞት በማተሟ …

ጋዜጠኛ ሚካኤል ዲኖ የሚያስተዳድራቸው ደካማ እናቱንና ተሰናብቶ፣ የሚወዳትን አገሩን ጥሎ ተሰደደ Read more »

(ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ) – ገዥው ፓርቲ የ2007 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫን የመንግስትን መዋቅርና ኃብት ያለገደብ በመጠቀም የዜጎችን በነፃነት የመምረጥ መብት በመዋቅር በማፈን አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት እጅግ በርካታ ህገ ወጥ ተግባራት ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓይነቱ የለየለት የውንብድና ስራ ተቃውሞ ያላቸው ዜጎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚያባብስ ሊቢያ ውስጥ በስደት ላይ በሚገኙ በኢትዮጵያውያን ላይ […]

ኢሳት ዜና ) ባለፈዉ ሃሙስ ሌሊት፥ አርብ ንጋት ላይ የቴፒ ወህኒ ቤትን ሰብረው ፖሊሶችን ገድለው እስረኛ ያስለቀቁት ታጣቂዎች የፍትህና የነጻነት ጥያቄ አንግበው መነሳታቸውን የእንቅስቃሴው መሪ ካለበት ለኢሳት በሰጠዉ ቃለምልልስ ገልጸ። ጥቃቱት ተከትሎ በእነሱ ወገን ሁለት ሰዎች መገደላቸዉን ያመነ ሲሆን፥ አንደኛው የንቅናቄው መስራች፥ ሌላኛዉ ሟች ቡድኑን በቅርቡ የተቀላቀለ መሆኑን አመልክቷል። ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገው የእንቅስቃሴው መሪ፥ ከዚህ […]

በሊቢያ የተሰውትን ኢትዮጵያውያን ሰማእታትን ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ባደረግነው ክትትል ወያኔ London, UK ያደረገውን ድራማ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ሊደገም እየተዘጋጀ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ህዝቡን ለማምታታት ሁለት ነገሮች ተከስተዋል። አንደኛው መምህር ዘበነ በሚያስተዳድረው የደብረ ገነት መድኃኒዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጅቶ …

በሙታን ስም ድራማ በዋሽንግተን ዲሲ Read more »

በሽብርተኝነት ተከሰው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች መሰማት ተጀመረ፡፡ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተካተቱት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን የሰው ማስረጃዎች ምስክርነት ዛሬ ሰኔ 01/07 ዓ.ም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ማሰማት ጀምሯል፡፡ ምስክሮች መሰማት ከመጀመራቸው […]

‹‹ከ500 በላይ ሰራተኞች ከወርልድ ቪዥን ሊለቁ ይችላሉ፡፡እስካሁን 170ሰራተኞች መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡››ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ሰራተኛ። መንግስት ባወጣው አስገዳጅ ህግ ምክንያት ከ500በላይ ሰራተኞቹን ሊያጣ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት 170ሰራተኞች መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው፡፡በ2012(2004) ዓም በወጣው የማሃበራዊ ዋስትና አዋጅ መሰረት የጡረታ ፈንድ ተቋቁሞ ሁሉም ሰራተኛ ማሃበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ሲደረግ የዕርዳታ ድርጅቶች ደግሞ ከፕሮቪደንት ፈንድ እና ከጡረታ እንዲመርጡ መደረጉ ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረታ […]

የጎንደር ህዝብ ድምፃችን ተሰርቃል በሚል ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ተነገረ የአየር ንብረት ለውጥ አፍሪካን እየጠቀመ ነው የሚል አንድ አወዛጋቢ የጥናት ውጤት ይፋ ሆነ የወያኔ  መከላከያ ሠራዊት እየፈረሰ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ነው፡፡  የተዳከመውን የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለማጠናከር ሲባል  የተባረሩት አመራሮች እንዲመለሱ መስማማታቸውን ተገለፀ፣ POSTED BY ASEGED TAMENEFiled under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Addis Ababa University, Africa, […]

በሁለት የዓባይ ተፋሰስ ገባር ወንዞች ላይ 2026 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

መንግሥት ለዓባይ ተፋሰስ ገባር በሆኑ ሁለት ወንዞች ላይ በድምሩ 2,026 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ 

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ግንቦት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የበጀት ዓመቱ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በሚቀጥለው ዓመት ሊተገበሩ የታቀዱትን የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርገዋል፡፡ 

የሚኒስትሩ ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተጠኑ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል በታምስ ወንዝ ላይ በጋምቤላ ክልል ውስጥ የሚገነባው 1,700 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በዳቡስ ወንዝ ላይ የሚገነባውና 326 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የዳቡስ አንድ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት መሆኑን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ የሁለቱም የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ዝርዝር ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑንና የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ዝርዝር ጥናት 81 በመቶ መከናወኑን፣ የዳቡስ አንድ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ደግሞ 71 በመቶ መከናወኑን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ መኩሪያ ለማ፣ የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሸካ ተራራ አናት የሚመነጨውና በጋምቤላ አድርጐ የባሮ ወንዝን፣ በመቀጠልም ከነጭ ዓባይ ተፋሰስ ጋር የሚቀላቀለው የታምስ ወንዝ ላይ የሚገነባው ነው፡፡ የታምስ ወንዝ ባሮ ወንዝን ከመቀላቀሉ በፊት በጋምቤላ ክልል ኃይል አመንጭቶ እንዲያልፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ 

ይህንንም እውን ለማድረግ በኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ዲዛይን ድርጅትና በአንድ የጣሊያን ኩባንያ ዝርዝር ጥናቱ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ ምን ያህል ይሆናል የሚለው ዝርዝር ጥናቱ ሲጠናቀቅ እንደሚታወቅ አስረድተዋል፡፡ ከታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት የማመንጨት አቅም በመጠኑ ብልጫ ያለውና በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክት ግንባታው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው 1,870 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጀመር፣ የተያዘለት በጀት 1.8 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ አምስት ዓመታትን ያሳለፈ ቢሆንም፣ የታምስ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ ማነፃፀሪያ ተደርጎ ይገመታል፡፡

የዳቡስ ኃይድሮ ፓወር ማመንጫ ፕሮጀክት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በወለጋ በኩል ከኦሮሚያ በሚያዋስን አካባቢ በሚፈሰው የዳቡስ ወንዝ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ ይህ ወንዝ የጥቁር ዓባይ ገባር ሲሆን፣ ዓባይን ከመቀላቀሉ በፊት ቤንሻንጉልን ከወለጋ በሚያዋስነው አካባቢ 326 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ታቅዶ፣ የፕሮጀክቱ ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑን አቶ መኩሪያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ይህ ፕሮጀክት በመንግሥት ቅድሚያ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን፣ በመጀመሪያ ጥናቱ 628 ሚሊዮን ዶላር በጀት ያስፈልገዋል ተብሎ እንደተገመተ፣ ነገር ግን ትክክለኛ ወጪው የተጀመረው ዝርዝር ጥናት ሲጠናቀቅ የሚታወቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

መንግሥት ዘንድሮ በሚጠናቀቀው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ከአምስት ዓመት በፊት በአገሪቱ የነበረውን አጠቃላይ 2,000 ሜጋ ዋት የኃይል አቅርቦት ወደ 10,000 ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የዕቅድ ዘመኑ ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ዕድሜ እየቀረው በተግባር ማቅረብ የቻለው ተጨማሪ ኃይል 310 ሜጋ ዋት መሆኑን፣ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ለፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ይሁን እንጂ በዕቅድ ዘመኑ ይጠናቀቃሉ ተብለው የተገመቱት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አማካይ አፈጻጸማቸው ከ60 በመቶ በላይ በመሆኑ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ወደ አገሪቱ የኃይል ማስተላለፊያ ቋት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

በተለይ 1,870 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትና 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ገናሌ ሦስት ፕሮጀክት በግንቦት ወር ውስጥ የነበራቸው አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈጻጸም 90.27 በመቶ እና 73.82 በመቶ በመሆኑ፣ በ2008 ዓ.ም. 2,521 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደ ሥርጭት ሥርዓት ውስጥ እንደሚገባ ይገመታል፡፡

ከቀሪዎቹ መካከል የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 6,000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም፣ ከቆሻሻና ከጂኦ ተርማል ኃይል ለማመንጨት ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ደረጃ በመነሳት፣ እስከ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ማገባደጃና እስከ 2009 ዓ.ም. እንደ ቅደም ተከተላቸው እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡ 

 

ከጁባ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ 20 ሚሊዮን ብር የመዘበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ከሁለት ዓመት በላይ ካስቆጠሩት፣ የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር የተያያዙ ሌሎች አምስት የንግድ ተቋማት ላይ ክስ ለመመሥረት በምርመራ ላይ መሆኑን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና በምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ገብረጊዮርጊስ እንዲሁም በሌሎች የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና በንግድ ሥራ በተሰማሩ የግል ተቋማት ባለሀብቶች ከግብርና ከታክስ ጋር በተገናኘ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. እንደነበር ይታወሳል፡፡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ረጅም የምርመራ ጊዜ ቢወስድም ክስ ከተመሠረተባቸውና ክርክር ከተጀመረ ከዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን በማየት ላይ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ምስክርን በመስማት ላይ ይገኛል፡፡

የእነ አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና ባለሀብቶች የክስ ሒደት ከላይ በተገለጸው ደረጃ ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት፣ የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ የወንጀል ምርመራ ጋር የተያያዙ ናቸው ያላቸው አምስት ድርጅቶች በመንግሥት ላይ የ361.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት እንዳደረሱ በማረጋገጥ፣ በተጨማሪ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ለምክር ቤቱ አሳውቋል፡፡ 

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌማን ባለፈው ሐሙስ ለፓርላማው ባቀረቡት ሪፖርት፣ ‹‹በቀድሞ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣናት፣ አንዳንድ የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና ከፍተኛ ነጋዴዎች ላይ ተጀምሮ ከነበረው ምርመራ ጋር በተያያዘ የአገር ውስጥ ግብርና የጉምሩክ ቀረጥ ባለመክፈል በተጠረጠሩ አምስት የግል ኩባንያዎች ላይ የኢንስፔክሽን ኦዲት በማስደረግ በተገኘው ማጣራት፣ 361.6 ሚሊዮን ብር የመንግሥት ታክስ አለመከፈሉ በመረጋገጡ ምርመራው እየተከናወነ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ባቀረቡት ሪፖርት የተጠረጠሩትን ድርጅቶች ማንነት አልገለጹም፡፡ የድርጅቶቹን ማንነት ለማጣራት ሪፖርተር ያደረገው ሙከራም አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታና በሌሎች ባለሀብቶች ላይ ክስ በመሠረተበት ወቅት፣ ምርመራ የተደረገባቸውና ክስ ያልተመሠረተባቸው 15 የግል ኩባንያዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡

እነዚህም ኒያላ ሞተርስ፣ ፔትራም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሞኤንኮ፣ ጌትአስ ትሬዲንግ፣ አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሜቴክ፣ አይካ አዲስ ትሬዲንግ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ሆላንድ ካርስ፣ ቶታል ኢትዮጵያ፣ ሚድሮክ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ድሬ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ፣ ኢትዮ ሌዘር፣ ኢትዮ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽኑ በሌሎች በጠረጠራቸው የሙስና ወንጀሎች ላይም ምርመራ እያደረገ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ 

ቦሌ ክፍለ ከተማ በሐሰተኛ ማስረጃ መሬት እንዲያገኙ ተደርጓል በሚል በቀረበ ጥቆማ፣ 89 የመሬት ጉዳዮች ላይ ምርመራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች ለሚከናወኑ ግንባታዎች የሚውሉ ጠጠር፣ ፕሪካስትና ብሎኬት ግዥ ጋር በተያያዘ አምስት ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ በተጠረጠሩ ሠራተኞችና አቅራቢዎች ላይ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን የኮሚሽኑ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን (ጁባ) ቅርንጫፍ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመመሳጠር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅም በማዋላቸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ 

  

 

 

በፕሮቪደንት ፈንድ የታቀፉ የግል ድርጅት ሠራተኞችን በመንግሥት በሚተዳደረው የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲዘዋወሩ የሚያስገድድ ማሻሻያ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ፣ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ዘንድ ተቃውሞ ቀሰቀሰ፡፡

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ 7/5/2003 በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም. ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ በፊት፣ የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፋን ያላቸው የግል ድርጅት ሠራተኞች በነበራቸው የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነት ለመቀጠል እንዲወስኑ፣ ወይም በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ስለሚሸፈኑበት ሁኔታ ሊስማሙ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡

በዚህ የተነሳም በአገሪቱ የሚገኙ በርካታ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በተሰጣቸው አማራጭ ላይ ውይይት በማድረግ በፕሮቪደንት ፈንድ መታቀፍን መምረጣቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከአራት ዓመት በኋላ ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ማሻሻያ አዋጅ የቀድሞውን አማራጭ በማስቀረት፣ ሁሉም የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በጡረታ ዕቅድ እንዲሸፈኑ ማሻሻያ አቅርቧል፡፡

ማሻሻያው በዚህ ላይ ብቻ ሳይሆን የግል ኩባንያ ባለቤቶች በግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ዐቅድ ሥር እንዲታቀፉ፣ እንዲሁም ከአሥር ዓመት በታች ያገለገሉ የግል ድርጅት ሠራተኞች በሚለቁበት ወቅት ቀደም ሲል ይፈቀድ የነበረውን ክፍያ ያስቀራል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ የግል ባንክ ኃላፊ፣ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ በሚፈቅደው መሠረት፣ በሁሉም ቅርንጫፎች የሚገኙ ሠራተኞች በፕሮቪደንት ፈንድ እንዲታቀፉ በፍላጎታቸው መምረጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለፓርላማ በመቅረቡ ግን ከሠራተኞች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑንና ውሳኔ ለመወሰን መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡

ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ በፕሮቪደንት ፈንድ ወይም ቀድሞ በነበራቸው ጡረታ ለመቀጠል ተስማምተው ሲቆጥቡ የነበሩ ሠራተኞች፣ የፕሮቪደንት ፈንድ ወደ ግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ እንደሚዘዋወር በረቂቅ አዋጁ የተካተተ በመሆኑ ቢፀድቅ የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትል እንደሆነ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

አንድ ስማቸውንም ሆነ የሚሠሩበትን መሥሪያ ቤት መጥቀስ ያልፈለጉ ሥራ አስኪያጅ ‹‹እንዴት በሕግ የተሰጠን መብት ተጠቅመው ፕሮቪደንት ፈንድን የመረጡ ሠራተኞችን ገንዘብ ለመውሰድ መንግሥት ሕግ ያወጣል?›› ሲሉ ድርጊቱን ተችተውታል፡፡ 

በማከልም ጉዳዩ የሠራተኞችን መብት መደፍጠጥ እንደሆነና መንግሥት ማድረግ የነበረበት ለፕሮቪደንት ፈንድ የማኅበራዊ ዋስትና የሕግ ከለላ በመስጠት፣ በቀጣሪዎች እንዳይመዘበር መቆጣጠር ነበረበት በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግልግልና ዳኝነት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ወልደ ገብርኤል፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የግል አስተያየታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮሐንስ አስተያየታቸውን መስጠት የጀመሩት፣ የግል ጡረታ ቦርድ ውስጥ የግል ባለሀብቶች እንዲወከሉ በሕጉ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰው፣ በዚህ ቦርድ ውስጥ የግሉ ዘርፍን በመወከል የተቀመጠ ሰው በዚህ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ በስምምነት ፈርሞ ከሆነ፣ የግሉን ዘርፍ የሚወክል ግለሰብ ነው ብለው እንደማያምኑ በመግለጽ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ተወካዮች የግሉን ዘርፍ የሚወክሉ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ምክንያቱም የግሉ ዘርፍ የመንግሥት ተጧሪ የመሆን ፍላጐት አለው ብዬ አላምንም፤›› ብለዋል፡፡ 

በ2003 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባው የግል ድርጅቶች ጡረታ አዋጅ ቀደም ሲል በፕሮቪደንት ፈንድ ወይም በጡረታ ዐቅድ ተሸፍነው የነበሩ ሠራተኞች፣ ከፕሮቪደንት ፈንድና ከጡረታ ዐቅድ እንዲመርጡ በተሰጣቸው ዕድል ነፃ ውይይት አድርገው ፕሮቪደንት ፈንድን ይጠቅመናል ብለው መወሰናቸውን አቶ ዮሐንስ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ውሳኔ እንዳልወሰኑ አድርጐ በመውሰድ እንደገና ወደኋላ ሄዶ ሠራተኛው የወሰነውን ውሳኔ መሻር የሕግ መርሆዎችን የሚጥስ ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹በንጉሡ ጊዜ ፀረ አብዮት ወንጀል ፈጽመሃል፤›› ተብለው በደርግ ጊዜ ሰዎች እንደሚከሰሱ ገልጸው፣ ይህንንም ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ሥርዓት ጋር አነፃፅረውታል፡፡ ሌላው አቶ ዮሐንስ  ያነሱት በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የግል ኩባንያ ባለሀብቶች በጡረታ ዐቅድ እንዲታቀፉ ማሻሻያ ማቅረቡ ትክክለኛነት ላይ ነው፡፡

የኩባንያ ባለቤቶች ወይም ባለሀብቶች በርካታ የማኅበራዊ ዋስትና አማራጮች እንዳሏቸው፣ ከእነዚህም መካከል የጡረታ ኢንሹራንስ ሊገዙ እንደሚችሉና ሌሎች የመሳሰሉትን ማድረግ እንደሚችሉ እየታወቀ፣ መንግሥት የራሱ ተጧሪ ሊያደርጋቸው መፈለጉ አስገራሚ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የግል ድርጅት ማለት በኢትዮጵያውያን ብቻ የተያዘ አለመሆኑንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ያቋቋማቸው ኩባንያዎችም እንዳሉ የሚገልጹት የሕግ ባለሙያው፣ እነዚህ የውጭ ዜጎች በአገራችው የተሻለ የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋን የሚያገኙ ሆነው ሳለ መንግሥት እነዚህንም ተጧሪ ለማድረግ ማሰቡ አስደናቂ ነው ብለዋል፡፡

መንግሥት ይህንን ማሻሻያ እያደረገ የሚገኘው ካለው ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎት አንፃር እንደሆነ እንደሚገምቱ የሚገልጹት ባለሙያው፣ ‹‹መንግሥት ያልተረዳው ከመንግሥት የተሻለ አገር የሚያለማው የግል ባለሀብቱ መሆኑን ነው፤›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ይህ ረቂቅ ማሻሻያ ሙሉ አይደለም ብለው የሚከራከሩበት ሌላው ነጥብ የጡረታ ሽፋን ያላቸው የቤተሰብ መሪዎች፣ ‹‹የተሽከርካሪ አደጋ ሊሆን ይችላል ወይም በፍትሕ እጦት በሚደርስ የሕግ ተጠያቂነት ለእስር በሚዳረጉበት ወቅት፣ የእሱን ወይም የእሷን እጅ ጠበቀው የሚኖሩ ቤተሰቦቹን የማይሸፍን ጎደሎ ነው፤›› ብለውታል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅና ሞሪታንያ የመሳሰሉ አገሮች በተገለጸው ዓይነት ችግር ለሚፈጠር የቤተሰብ ቀውስ ‹‹የቤተሰብ አበል›› የሚል ዋስትና እንዳላቸው፣ ይህ ማሻሻያ የሚፀድቅ ከሆነ ይህንን ነጥብ ሕግ አውጪው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ፓርላማው ባለፈው ሐሙስ በአዋጁ ላይ አጭር ውይይት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዋናነትና፣ በተደራቢነት ደግሞ ለሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቶታል፡፡

 

የሸራተን አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሸራተን አዲስን ከ16 ዓመታት በላይ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የቆዩት፣ የዴንማርክና የፈረንሣይ ጥምር ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው ሚስተር ዢያን ቪ. ማኒጐፍ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ከሸራተን አዲስ ማኔጅመንት የወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ ሚስተር ማኒጐፍ ላለፉት ወራት በከባድ ሕመም ሲሰቃዩ ከርመው በቅርቡ በሕክምና እየተረዱ ባሉበት አሜሪካ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ 

ከ20 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደኖሩና ላለፉት 16 ዓመታት ሸራተን አዲስን ሲመሩ የነበሩት ሚስተር ማኒጐፍ፣ የአርመን ዝርያ እንዳላቸውም ተጠቁሟል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሆቴሉን እየመሩ በቆዩባቸው ጊዜያት፣ በተለይ ከሆቴሉ ሠራተኞች ጋር ባለመስማማታቸውና ከሠራተኞቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲደርስባቸው መቆየቱም ይታወሳል፡፡ አንድ የውጭ ዜጋ በአገሪቱ ዜጐች ላይ በደል መፈጸም እንደሌለበትና ካለመኖሪያ ፈቃድ ለረጅም ጊዜ መኖር እንደሌለበት በመጠቆም፣ ሠራተኞቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ደብዳቤ ማቅረባቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በርካቶችም ከሥራ መሰናበታቸው አይዘነጋም፡፡ 

ስለሚስተር ማኒጐፍ ሕልፈት የሸራተን አዲስ ማኔጅመንት ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጠው ሪፖርተር ጥረት ቢያደርግም፣ ‹‹ፋክስ እናደርግላችኋለን›› ከማለት ባለፈ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ 

ሚስተር ማኒጐፍ ልጅም ሆነ ትዳር እንደሌላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

 

መርካቶ ሸራ ተራ በደረሰ እሳት ቃጠሎ ንብረት ወደመ

ሰባት ሰዎች በጭስ ታፍነው ጉዳት ደርሶባቸዋል

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሸራ ተራ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ፣ ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወደመ፡፡ 

አደጋውን ለመቆጣጠር በአካባቢው ያለው የፕላስቲክ ጫማ፣ ዘይት፣ ሳሙና፣ ብርድ ልብስና ለመቀጣጠል አደገኛ የሆኑ ዕቃዎች ክምችት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ አካባቢው በጭስ በመታፈኑ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ወደ ውስጥ ደፍረው ለመግባት እንዳዳገታቸውና ለረዥም ሰዓታት እሳቱን መቆጣጠር ሳይቻል መቆየቱንም አክለዋል፡፡ 

የእሳት ቃጠሎው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ መጀመሩን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ነጋዴዎች በመተባበር ከየጊቢው ውኃ በመቀባበልና በየጣራው ላይ ወጥተው ውኃ በመርጨት የተቻላቸውን ካደረጉ በኋላ፣ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እንደደረሱላቸውም ተናግረዋል፡፡ 

የእሳቱ መነሻ በውል ባይታወቅም ከመሀል አካባቢ እንደተነሳና ቤቶቹም እርስ በርስ የተያያዙ በመሆናቸው፣ ለመኪና መግቢያ አስቸጋሪ እንደነበር የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን ሠራተኞች ገልጸዋል፡፡ እሳቱ እየጨመረ በመሄዱ ከሰባቱም ክፍለ ከተማ የእሳት መከላከያ ማሽነሪዎች ቢመጡም፣ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት አለመጥፋቱም ታውቋል፡፡ አራት የውኃ ቦቴዎች ውኃ በማቅረብ ሲተባበሩ እንደነበር፣ አንድ የኤርፖርቶች የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪ ተጨምሮ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡ የተዳፈነ እሳት፣ የፕላስቲክ ዕቃዎችና ጨርቃ ጨርቆች ለማጥፋት ሲያስቸግሩ ተስተውሏል፡፡ ሠራተኞቹ እሳቱን እያጠፉ ባለበት ጊዜ ከሥር ከሥር የሱቆቹ ባለቤቶችም ከተቃጠለው ዕቃ ክምር የተለያዩ ዕቃዎችን ለማውጣት ሲረባረቡ ታይተዋል፡፡

አብዛኞቹ በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች ዕቃቸውን በማውጣትና እሳቱ ያልደረሰበት ቦታ በመከመር የማዳን ሥራ ሲሠሩ ተስተውለዋል፡፡ ነጋዴዎቹ አይሱዙ በመከራየት ዕቃቸውን በመጫን ወደተለያዩ ቦታዎች ሲወስዱና ቤታቸውም የተቃጠለባቸው ነዋሪዎች እያለቀሱ በከፍተኛ ሐዘን ሲዋከቡ ታይተዋል፡፡ ንብረታቸውንም አድነው በየቦታው የከመሩት ነጋዴዎች ሲመሽባቸው በላስቲክ እየሸፈኑ ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዋል፡፡ 

በወቅቱ ከአሥር በላይ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች በማሰማራት ከ150,000 ሊትር በላይ ውኃ፣ 300 ሊትር ፎም እንደተጠቀሙ የገለጹት አቶ ሰለሞን መኰንን፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ናቸው፡፡ እንደሳቸው ገለጻ፣ የእሳት አደጋው ተነስቷል ተብሎ የተደወለው ከቀኑ 8፡57 ሰዓት ላይ ነው፡፡ ከተደወለላቸው በኋላ ግን፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀድሞ በመድረስ ዕርዳታ እንደጀመረ፣ ሌሎቹም ስድስቱ ክፍላተ ከተሞች በየተራ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ እሳቱ አስቸጋሪ ቢሆንም ከአራት ሰዓት በኋላ ለመቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡ እስከ ዓርብ ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት ድረስ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ማወቅ አልተቻለም ነበር፡፡ 

 

አብረዋቸው የተከሰሱ የድርጅት ባለቤት በዋስ ተለቀቁ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምርያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በፈቃዱ አሰፋ፣ ተጠርጥረው ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በነፃ ተሰናበቱ፡፡

አብረዋቸው ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኤቢ ፕላስት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ጌታቸው በየነ፣ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ወደ ማታለል ወንጀል ተቀይሮ የ200 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ሁለቱም ተጠርጣሪዎች ተመሳጥረው በሕገወጥ መንገድ የ3,211,411 ብር የግዥ ውል እንዲፈረም በማድረግ በመንግሥትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን በመጥቀስ፣ የሙስና ወንጀል ክስ መስከረም 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም. ነው፡፡

አስተዳደሩ ለሚያስገነባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግብዓት የሚሆን የሳኒተሪ ዕቃ እንዲገዛ የወጣውን የጨረታ የግዥ አፈጻጸም መመርያን ባልተከተለ መንገድ፣ ከደረጃ በታች የሆነ የሳኒተሪ ዕቃ እንዲገዛ መደረጉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ሁለተኛ  ተከሳሽ ጨረታውን አሸንፈው ያቀረቡት ምርት ደግሞ ዩፒቪሲ መሆኑ ሲገባው ዩፒቪሲ የሚል ማኅተም የተለጠፈበት የፒፒሲ ምርት መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡ ይኼም የሆነው ምክትል ሥራ አስኪያጁና ነጋዴው ተመሳጥረው መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ፣ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ የ3.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት እንደደረሰም አስረድቷል፡፡ ሁለተኛው ተከሳሽም በተደጋጋሚ በጨረታ እንዲሳተፉና አሸናፊ እንዲሆኑ አቶ በፍቃዱ እንደረዷቸው  ክሱ ይገልጻል፡፡ 

አቶ አብርሃም ጌታቸው የተባሉት የፒቪሲ ፕላስት ድርጅት ባለቤት የሌሎችን ሰዎች አለማወቅ ተጠቅመው በፒፒሲ ምርት ላይ ዩፒቪሲ የሚል ማኅተም በማስቀመጥና በማታለል፣ በመንግሥት ላይ የ78,147,296 ብር ጉዳት ማድረሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

አቶ በፈቃዱ ሌላው የተከሰሱበት ወንጀል በጽሕፈት ቤቱ የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ ተገቢ ምክንያት ሳይኖራቸው፣ የ8551 ብር ባለ24 ካራት ስምንት ግራም ብራስሌት ወርቅ ቶፕና ሰላም ኮንስትራክሽን ከተባሉ ተቋራጮች መቀበላቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰዎች ምስክሮች፣ የሰነድ ማስረጃዎችና የኤግዚቢት ማስረጃዎች በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረቡት ክሶች ስለመፈጸማቸው አስረድተዋል? ወይስ አላስረዱም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ መመርመሩን በውሳኔው ገልጿል፡፡

አቶ በፍቃዱ ሁለተኛው ተከሳሽ ጨረታ እያሸነፉ የሚያቀርቧቸው የሳኒተሪ ምሮቶች ከስፔስፊኬሸን በታች ስለመሆናቸው ጥቆማ ሲደርሳቸው፣ ሁለተኛው ተከሳሽ (ኤቢ ፕላስት) እንዳይሳተፍ የማድረግና ጨረታውንም የመሰረዝ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል? የሚለውን ከፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የአደረጃጀትና የሥራ መዘርዝር መመርያ ላይ መመልከቱን እንዲሁም ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር መመሳጠራቸው በዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች መረጋገጥ አለመረጋገጡንም ጭብጥ ይዞ መመርመሩን ዘርዝሯል፡፡

አቶ በፈቃዱ ኤቢ ፕላስት የተባለው ድርጅት የሚያቀርበው የሳኒተሪ ዕቃ ከጥራት በታች መሆኑ ጥቆማ ሲደርሳቸው፣ ወደሚመለከተው የሥራ ክፍል መምራታቸውንና በኢትዮጵያ ምዘናና ተስማሚነት ተቋም ተልኮ እንዲመረመር መደረጉን ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ አስረጂነት የጠራቸው የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መመስከራቸውን ገልጿል፡፡ ከጥራት በታች መቅረቡ ተረጋግጦ ጨረታው መሰረዙን ማስረዳታቸውንም አክሏል፡፡ ቅሬታ ቀርቧል ተብሎ ሳይጣራ ጨረታ  መሰረዝ እንደማይችልና ወደሚመለከተው ክፍል ተልኮ ማጣራት መደረጉን፣ ከምስክሩ መረዳት መቻሉን ፍርድ ቤቱ በስፋት ተንትኗል፡፡ አቶ በፍቃዱ ለሚመለከተው ክፍል መርተውና ለዋና ሥራ አስኪያጁ የክፍሉን ውሳኔ አቅርበው ጨረታውን ያሰረዙ በመሆኑ፣ በቀረበው ክስ የአቶ በፈቃዱ ኃላፊነት ነው ተብሎ በማስረጃነት የቀረበው እሳቸውን የማይመለከትና እሳቸውም ቢሆኑ ኃላፊነታቸውን የተወጡ መሆኑን ከማስረዳት ባለፈ፣ የሚያስጠይቃቸው ሆኖ አለመገኘቱን በውሳኔው ጠቅሷል፡፡

ጥራትን የመቆጣጠር ሥልጣን በጽሕፈት ቤቱ አደረጃጀት መሠረት የአቶ በፍቃዱ ሳይሆን የሌላ ኃላፊ መሆኑን፣ የተለያዩ ጽሕፈት ቤቱ ያወጣቸው መመርያዎች እንደሚያረጋግጡ ፍርድ ቤቱ በዝርዝር ገልጿል፡፡ ቀርበው በመሰከሩት ሰዎችም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች በአቶ በፈቃዱ ላይ ስላላስረዱባቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ/141 መሠረት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤቱ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አቶ አብርሃም ጌታቸው የኤቢ ፕላስት ድርጅት ባለቤትም የተጠረጠሩበት ወንጀል ሙስና ሳይሆን ወደ ማታለል ወንጀል ተቀይሮላቸው በ200 ሺሕ ብር ዋስ ሆነው እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ በፍቃዱ ላይ የቀረበው ስምንት ግራም  ብራስሌት ወርቅን በሚመለከት ምስክሮች ካለመሰማታቸውም በተጨማሪ፣ ወርቁ የተገዛው በስማቸውና በአግባቡ መሆኑን ጠቅሶ በእሱም በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ በፍቃዱ ከእስር እንዲፈቱና ብራስሌት ወርቃቸው ከኮሚሽኑ ኤግዚቢት ክፍል እንዲመለስላቸው አዟል፡፡ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ለሐምሌ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

 

የአገሪቱ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከአቅም በታች እያመረቱ ነው

ዳንጎቴ የገነባውን ግዙፍ ሲሚንቶ ፋብሪካ በእጥፍ እንደሚያሳድግ አስታወቀ

በአገሪቱ ሲሚንቶ በማምረት የተሰማሩ 17 ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ሳቢያ፣ ከአቅማቸው ከግማሽ በታች እያመረቱ ነው፡፡ ሰሞኑን ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው ዳንጎቴን ጨምሮ ዋና ዋና የአገሪቱ ፋብሪካዎች በአሁኑ ወቅት ማምረት የቻሉት በዓመት 5.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብቻ ነው፡፡ 

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ ይመረታል ተብሎ የታቀደው የሲሚንቶ መጠን ከ17 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነበር፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎቹ ያመርታሉ የተባለው መጠን 11.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሆን፣ ፋብሪካዎቹ ማምረት የቻሉት ግን 5.47 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሲሚንቶ ወደ ሶማሊያ፣ ጂቡቲና ደቡብ ሱዳን እየተላከ እንደሆነ አቶ አህመድ አስረድተዋል፡፡

እነዚህን ፋብሪካዎች ይቀላቀላል ተብሎ የሚጠበቀው ዳንጎቴ፣ በዓመት 2.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተውን ፋብሪካ ሥራ ያስጀመረው ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ነው፡፡ በማግሥቱም የናይጄሪና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ፋብሪካውን አስመርቋል፡፡ ከአዲስ አበባ 85 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ሙገር ከተማ አዳዓ በርጋ ወረዳ ውስጥ በ134 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈው ግዙፍ ፋብሪካ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት መሆኑን ናይጄሪያዊው ቢሊየነር የዳንጎቴ ግሩፕ ሊቀመንበርና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ አስታውቀዋል፡፡ 

አሊኮ ዳንጎቴ አዲሱ ፋብሪካ ገና ሥራ ከመጀመሩ የእሱን ተመሳሳይ ፋብሪካ በተመሳሳይ ወጪ ለመገንባት መነሳታቸውንና የፋብሪካው ግንባታም በዚህ ዓመት ውስጥ እንደሚጀመር፣ ፋብሪካውን ለመመረቅ ለተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ለሌሎች ባለሥልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በበኩላቸው፣ አሊኮ ዳንጎቴ ተጨማሪ ማስፋፊያ ለማካሄድ መወሰናቸው እንዳስደሰታቸውና በግላቸውም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን ክትትል እንደሚያደርጉለት ለዳንጎቴ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡ 

መቶ በመቶ ከራሳቸውና ከአገራቸው በተገኘ ገንዘብ ፋይናንስ ተደርጓል የተባለለት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት መጀመር፣ በአገሪቱ በወቅቱ የተከሰተውን የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከ400 ብር በላይ በኩንታል እየተሸጠ የሚገኘው ሲሚንቶ ከጥቂት ወራት በፊት በ230 ብር በችርቻሮ ገበያው ውስጥ ሲሸጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ አንዱን ኩንታል በፋብሪካ ዋጋ በ207 ብር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል፡፡ በአገሪቱ ካሉት 17 ፋብሪካዎች በተጨማሪ 18ኛው ሆኖ የተመዘገበው ዳንጎቴ፣ 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት የሚያስችለው መሠረተ ልማት ተዘርግቶለታል፡፡ 

በአንፃሩ ሌሎች ትልልቅ ፋብሪካዎች በኃይል አቅርቦት እጦት ሳቢያ ከአቅማቸው በታች ለማምረት መገደዳቸው ይታወቃል፡፡ በሰኔ ወር በከፊል ማምረት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ የሚጠበቀው የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ችግር እንደሚያቃልል ተስፋ ተደርጓል፡፡ 

ዳንጎቴ ግሩፕ ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ዕውን ያደረገው ፋብሪካ በምሥራቅ አፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ ቢነገርለትም፣ በናይጄሪያ ያሉት ሦስት ፋሪካዎች በዓመት ከ20 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ሲሚንቶ ያመርታሉ፡፡ 

በሌላ በኩል በናይጄሪያው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ የሚመራው ዳንጎቴ ግሩፕ፣ በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ የፖታሽ ማዕድን ምርት ላይ ለመሠማራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ መስጠቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ በምሥራቅ አፍሪካ ግዙፍ የተባለውን ፋብሪካ ሥራ ኢትዮጵያ ውስጥ አስጀምሯል፡፡ 

የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ኩባንያው ፈቃድ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቆ ነበር፡፡ ሚኒስቴሩ ኩባንያው ያቀረበውን የፖታሽ ማዕድን የማምረት ፈቃድ ሲያጠና ቆይቶ እምነት የሚጣልበት ሆኖ በማግኘቱ፣ ያቀረበውን የፈቃድ ጥያቄ መቀበሉን አቶ ቶሎሳ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ሦስት የውጭ ኩባንያዎች በፖታሽን ማዕድን ምርት ላይ በማሰማራት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ለመሥራት ቆርጠው የመጡ መሆናቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ፈቃድ መስጠት አቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ዳንጎቴ ፈቃድ መስጠት ከቆመ በኋላ ፈቃድ የተሰጠው ኩባንያ ሆኗል፡፡ 

‹‹ደብዳቤ አስገብተው ነበር፡፡ የዳንጎቴ ኩባንያ ባለቤት አገራችንን አምኗል፡፡ ይህን ሁሉ ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ሲያደርግ የሚሠራ ሰው መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ስለዚህም ፈቃድ ልንሰጠው ወስነናል፡፡ ቦታውን ለይቶ እንዲያቀርብ እየጠበቅነው ነው፡፡ ልክ እንደ ሲሚንቶው በፖታሽም እንደሚሠራ ይጠበቃል፤›› በማለት አቶ ቶሎሳ ለዳንጎቴ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ በፖታሽ ማዕድን ላይ ለመሰማራት እየተንቀሳቀሱ ካሉት ሦስት የውጭ ኩባንያዎች በተጨማሪ ዳንጎቴ አራተኛው እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ 

ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ አፋር ክልል በዳሎል አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ ክምችት እንዳለው የሚታወቀውን የፖታሽ ማዕድን፣ በናይጄሪያ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓት ሊያውለው ይፈልጋል፡፡ ከዳንጎቴ በተጨማሪ የካናዳው አላና ፖታሽ የምርት ፈቃድ ማግኘቱን አቶ ቶሎሳ አስታውሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የምርት ፈቃድ ያገኘው አላና ፖታሽ፣  የመሠረተ ልማትና የማምረቻ ፋብሪካ የመትከል ሥራ ማከናወን እንደሚጠቅበት፣ ሚኒስቴሩም ኩባንያው ይህንን ሥራ በወቅቱ ያከናውናል ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡ 

የኖርዌይ ያራ ኢንተርናሽናል እህት ኩባንያው በሆነው ያራ ዳሎል ቢቪ አማካይነት ባቀረበው ጥናት መሠረት የምርት ፈቃድ ሊሰጠው መሆኑን፣ የፋይናንስ ችግር ስለሌለበትም በፍጥነት ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥም የመሠረተ ልማት ሥራዎችን አጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ይታሰባል፡፡ ሦስተኛው የእንግሊዝ ኩባንያ የሆነው ሰርከም ሚነራልስ የሚባለው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የአዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተነግሮለታል፡፡ በስምንት ወራት ጊዜ ውስጥ የምርት ፈቃድ ለማግኘት ወደ ሚኒስቴሩ እንደሚመጣ አቶ ቶሎሳ ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ ቁንጮ ከበርቴ የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ በአንዳንዶች ዘንድ ‹‹ከብክለትና ከብድር የፀዳ›› እየተባለ ከተነገረለት የሲሚንቶ ፋብሪካቸው በተጨማሪ፣ በጥጥና በሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ዳንጎቴ ጥናት ላይ በመሆኑ ያቀረበው የፈቃድ ጥያቄ የለም፡፡

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ ከዓለም ሀብታሞች ተርታ ያሰለፋቸው የ20 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ የግል ሀብት ያላቸው ባለፀጋ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥም 16 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በ16 አፍሪካ አገሮች ውስጥ ያንሰራፏቸውን የንግድና የኢንቨስትመንት መስኮች እንደሚያስፋፉ፣ አዳዲሶችንም እንደሚገነቡ ይፋ አድርገዋል፡፡ በቀን 650 ሺሕ በርሜል ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለውን ማጣሪያ ጨምሮ፣ ሦስት ሚሊዮን ቶን ዩሪያና አሞኒያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ዕውን ለማድረግ እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ 

እ.ኤ.አ. በ1996 ወደ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፊታቸውን በማዞር በአፍሪካ ግዙፍ ግዛት የፈጠሩት አሊኮ ዳንጎቴ፣ በ20 ዓመታቸው ከአያታቸው በተበደሩት 500 ሺሕ ኒያራ (የናይጄሪያ መገበያያ ገንዘብ) በሲሚንቶ ንግድ ሥራ እጃቸውን አፍታትዋል፡፡ በሁለት ዓመት የሚከፍሉትን ገንዘብ በሦስት ወራት ውስጥ ለአያታቸው በመመለስ ስኬታማ የንግድ ጉዞ የጀመሩት ዳንጎቴ፣ ፎርብስ መጽሔት በሚያወጣው የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛው በመሆን እየመሩ ይገኛሉ፡፡ 

 

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ የቀጣዩን ዓመት 223.4 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ፣ ምክር ቤቱ አፅድቆ ለፓርላማ ላከው፡፡ 

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በ2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት 223 ቢሊዮን 397 ሚሊዮን 819 ሺሕ 216 ብር እንዲሆን ወስኗል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ከፍተኛ በጀት ተቀብሎ ካፀደቀ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡ 

ይህ በጀት በ2007 ዓ.ም. ከተያዘው 178.6 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር በ44.8 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡ ነገር ግን ለደመወዝ ጭማሪ በዓመቱ መጀመሪያ በተያዘው በጀት ላይ ስምንት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የበጀት ሥሌት ቀርቦ በመፅደቁ፣ የ2007 ዓ.ም. በጀት በአጠቃላይ 186.6 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

ለ2008 ዓ.ም. ከተያዘው በጀት ትልቁ ለፕሮጀክቶች የተመደበው ነው፡፡ ከአጠቃላይ በጀቱ 37.4 በመቶ ለካፒታል ፕሮጀክቶች፣ 34.7 በመቶ የሚሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው ቀመር ላይ ተመሥርቶ ለክልሎች የሚከፋፈል ነው፡፡ የበጀቱ 22.6 በመቶ ለመደበኛ ወጪዎች ይውላል፡፡ 5.4 በመቶ ደግሞ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ይውላል ተብሏል፡፡

ለክልሎች ከሚከፋፈለው በጀት የአዲስ አበባ አስተዳደር በቀጥታ ተቋዳሽ ባይሆንም፣ በተለይ ለግዙፍ ፕሮጀክቶች በፌዴራል መንግሥት አማካይነት ያገኛል ተብሏል፡፡ 

በተለይ በመጠጥ ውኃ፣ በቀላል ባቡር ትራንስፖርትና በተወሰነ ደረጃ ለቤቶች ልማት በጀት እንደሚመደብለት ታውቋል፡፡ 

ይህ በጀት ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቀው በተለይ ከአገር ውስጥ የገቢ ምንጮች፣ ከዕርዳታና ከብድር ነው፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚያቀርበው በጀት እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሚጀመርበት 2008 ዓ.ም. የቀረበውም በጀት በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህንን በጀት በማስፈጸም በኩል ዘንድሮ በተካሄደው ምርጫ መንግሥት መመሥረቱን ያረጋገጠው ኢሕአዴግ የሚያዋቅረው አዲስ ካቢኔ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ 

 

የቀድሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት ቅጣት ተቀንሶላቸው ከእስር ተፈቱ

ጥፋተኛ የተባሉበት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል

ሥልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተከሰው ሰባት ዓመታት ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ ከሦስት ዓመታት የእስር ቆይታ በኋላ ቅጣቱ ተቀንሶላቸው ግንቦት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር ተለቀቁ፡፡

አቶ ያረጋል በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ከፌዴራል መንግሥት በተሰጠ የበጀት ድጎማ ከክልሉ በጀት የግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ፣ የጣና በለስ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና የአሶሳ የቴክኒክና የሙያ ማሠልጠኛ ተቋማትን  ለማስገንባት በክልሉ የወጣውን የግዥ መመርያ ቁጥር 1/1992 አንቀጽ 9.1 እና 2 ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ግዥ እንዲፈጸም፣ የሦስቱ ፕሮጀክቶች ጨረታ ያላግባብ እንዲሰጥ አድርገዋል በሚል ግብረ አበሮቻቸው ከተባሉ ጋር መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡

የሥር ፍርድ ቤት የቀረቡለትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ እንዲከላከሉ ካደረገ በኋላ፣ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ በማለት ቅጣቱን ወስኖባቸው ነበር፡፡

አቶ ያረጋል በሕዝብና በመንግሥት ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረሳቸው የሰባት ዓመታት ጽኑ እስራትና የ20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሲጣልባቸው፣ የሥር ፍርድ ቤት ፍርድን በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን አቤቱታ ተመልክቶ፣ ‹‹የሥር ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ እንዳላገኘው ጠቁሞ ‹‹አያስቀርብም›› ብሎ መዝገቡን ዘግቶት ነበር፡፡ የሥር ፍርድ ቤቶች የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል በማለት ለሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

ለሰበር ችሎቱ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳስረዱት በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ የተደረገው ተገቢ ማስረጃ በዓቃቤ ሕግ በኩል ስላልቀረበ ነው፡፡ ከወንጀል ተጠያቂነት መርህ መንፈስና ይዘት ውጪ ነው ብለዋል፡፡ የመከላከያ ማስረጃቸው ይዘት ውድቅ የተደረገውም ያላግባብ እንደሆነ፣ የእስራት ቅጣቱም በወቅቱ ያለውን የቅጣት መመርያ መሠረት ያላደረገ መሆኑን፣ እሳቸው ያቀረቧቸው የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች የታለፉት ያላግባብ መሆኑን ዘርዝረው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻርላቸው ወይም እንዲስተካከልላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

አቶ ያረጋል የተከሰሱት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) (ለ) በዋና ወንጀል አድራጊነት በአንቀጽ 33 በወንጀል ድርጊቱ በዋናነት በመሳተፍና በአንቀጽ 407 (1) (ሀ) (ለ)፣ (2) እና (3) ሥልጣንን አለግባብ መጠቀም ወንጀሎች ነበር፡፡ ወንጀሉን ክደው በመከራከራቸው ከሳሽ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹንና የሰነድ ማስረጃዎቹን አቅርቦ ወንጀሉን መፈጸማቸውን ማረጋገጡን የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ተረጋግጧል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱም የክርክር ሒደቱንና ውሳኔውን አልተቃወመውም፡፡ የመመርመርም ሥልጣን እንደሌለውም አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣቶችን የሚወስነው የወንጀል አድራጊውን የሕይወት ታሪክ፣ ወንጀል ለመፈጸም ያነሳሱትን ምክንያቶችንና የሐሳቡን ዓላማ፣ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃውን፣ የወንጀሉን ከባድነትና የአፈጻጸሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የወንጀል ሕጉንና የቅጣት መመርያውን ያገናዘበ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ መገንዘቡን የገለጸው ሰበር ችሎቱ፣ መነሻ ቅጣቱ ከተወሰነ በኋላ መጠኑ መሰላት ያለበት ሕጉ ስለቅጣት አወሳሰን የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወጣው የቅጣት አወሳሰን መመርያም እንደሚያሳይ ጠቁሟል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በአቶ ያረጋል ላይ የቅጣት ማክበጃ አለማቅረቡን የሥር ፍርድ ቤት ማረገገጡን ሰበር ችሎቱ ገልጾ፣ ቅጣቱን በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ማስላቱ ግን የሕግ ስህተት መሆኑን አስረድቷል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ቅጣቱን ሲወስን የቅጣት ውሳኔ የሚመጣው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑንና የጥፋተኝነት ውሳኔ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ቆይቶ ሊወሰን የሚችል በመሆኑ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት ጊዜ በሥራ ላይ ያለው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ አግባብ አለመሆኑን ሰበር ችሎቱ በፍርዱ ተችቷል፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 (1) እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ስምምነት አንቀጽ 14 (2) (ሐ)፣ በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 7 (1) (መ) መሠረት አንድ ተከሳሽ የተፋጠነ ውሳኔ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች፣ የሥር ፍርድ ቤት በውሳኔው አለማገናዘቡን በመጥቀስ ሰበር ችሎቱ ተችቷል፡፡

አቶ ያረጋል ክስ የተመሠረተባቸው ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም. መሆኑን የጠቆመው ሰበር ችሎቱ፣ ክሱ በቀረበበት ወቅት የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመርያ ቁጥር 1/2002 መሆኑን ገልጿል፡፡ ይኼ መመርያ በቁጥር 2/2006 መሻሻሉንም እክሏል፡፡ መመርያው ቁጥር 1/2002 የቅጣት ማቅለያ በሚያስቀንሰው እርከን ላይ የእርከን ቅጣት መጠኑን መሠረት አድርጎ ቅጣትን የሚቀንስ ሲሆን፣ የተሻሻለው መመርያ ቁጥር 2/2006 ግን የማቅለያ ምክንያቶች በሚያስቀንሱት የእርከን መጠን ላይ ያደረገው ልዩነት አለመኖሩን ሰበር ችሎቱ በፍርዱ አስቀምጧል፡፡ በቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ምላሽ የእርከን አቀናነስ ላይ መመርያ ቁጥር 1/2002 ከመመርያ ቁጥር 2/2006 የተሻሻለና አቶ ያረጋልን የሚጠቅም መሆኑንም ሰበር ችሎቱ አስረድቷል፡፡ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ ስድስትና ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 22 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር የተሻለው መመርያ ተፈፃሚነት አንዲኖረው እንደሚገባ በሰበር ችሎቱ የተለያዩ መዝገቦች የሕግ ትርጉም እንደተሰጠበት አስታውሶ፣ ለአቶ ያረጋል አይሸሹም የቅጣት አወሳሰን መመርያ 1/2002 የተሻለ ሆኖ በማግኘቱ የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሕግ ስህተት ፈጽሞ እንዳገኘው አስታውቋል፡፡

ሌላው የፍርድ ቤት ለአቶ ያረጋል ከያዘላቸው ሦስት የቅጣት ማቅለያዎች በተጨማሪ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ለረዥም ጊዜ ሕዝብንና መንግሥትን ማገልገላቸው የራሱ የሆነ ዋጋ ያለው አገልግሎት እንጂ በደፈናው ‹‹የኃላፊነት ግዴታ ነው›› ተብሎ በሥር ፍርድ ቤት የሚታለፍ አለመሆኑን ሰበር ችሎቱ ገልጿል፡፡ አቶ ያረጋል በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የመሪነት የሚናቸውን የተወጡ በመሆናቸው በወቅቱ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንትና ከአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም የበላይ ጠባቂ ሽልማት የተቀበሉና ሌሎች ልማቶችን በአመርቂ ሁኔታ የፈጸሙ መሆናቸው፣ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ሊያዝላቸው እንደሚገባ ሰበር ችሎቱ ገልጿል፡፡ በድምሩ አራት የቅጣት ማቅለያ ሲያዝላቸው በመመርያ ቁጥር 1/2002 አንቀጽ 16(17) ድንጋጌ መሠት እያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ሦስት እርከን የሚያስቀንስላቸው በመሆኑ፣ አቶ ያረጋል በ12 የቅጣት ማቅለያ የሥር ፍርድ ቤት ለቅጣት ከያዘው እርከን 27 ወደ እርከን 15 ወርዶ ቅጣቱ የሦስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሆን ፍርድ ሰጥቷል፡፡ የገንዘብ መቀመጫውን እንደማይነካም አክሏል፡፡ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች መሻራቸውንም አስታውቋል፡፡

 

በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ በለቡ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ የተገነባው የግል የቆርኪ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ ማምረት መጀመሩ ተገለጸ፡፡ 

ጵንኤል ኢንዱስትሪ በተባለ ኩባንያ የተገነባው ፋብሪካ፣ አሁን ባለው የማምረት አቅም አንድ ቢሊዮን ቆርኪዎችን በዓመት እንደሚያመርት፣ በቅርቡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም አቅሙ 1.8 ቢሊዮን እንደሚደርስ ታውቋል፡፡ 

የኩባንያው ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ብርቱካን በቀለ፣ ፋብሪካውን ገንብቶ ለመጨረስ ሁለት ዓመት እንደወሰደና 40 በመቶ የሚሆነው የግንባታ ወጪ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በተገኘ ብድር መሸፈኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የለቡ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ፋብሪካው 2,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መገንባቱን ዋና ሥራ አስኪያጇ አስረድተዋል፡፡ ፋብሪካው ዓለም አቀፍ ጥራቱን እንዲያሟላ ተደርጎ የተገነባ መሆኑንና የእጅ ንክኪ ሳይኖረው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ቆርኪዎችን እንደሚያመርትም ወ/ሪት ብርቱካን አስታውቀዋል፡፡

ፋብሪካው ምንም ዓይነት ብክነት እንዳይኖረው ተደርጎ መገንባቱን፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የምርት ሥራ እንዳይስተጓጎል የራሱ ጄኔሬተር ተተክሎለታል ብለዋል፡፡ 

ፋብሪካው በዋናነት ለአገር ውስጥ የቢራ፣ የለስላሳና የኮስሞቲክስ ውጤቶችን ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ምርቱን እንደሚያቀርብ፣ ከአጠቃላይ ምርቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ወደ ጂቡቲና ፑንትላንድ የመላክ ዕቅድ እንዳላቸው ወ/ሪት ብርቱካን ገልጸዋል፡፡ 

ፋብሪካው ለ63 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን፣ በቅርቡም መጠነ ሰፊ የማስፋፋት ሥራ እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡ ጵንኤል ኢንዱስትሪ በ2006 ዓ.ም. በ120,000 ብር የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ በአገሪቱ ሥራ ፈጣሪ ከሆኑ ሴቶች አንዷ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ወ/ሪት ብርቱካን፣ አልሙኒየምን ከመሳሰሉ ምርቶች የሚሠሩ የሕንፃ በርና መስኮቶች፣ መሰል ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ አምስት የቆርኪ ፋብሪካዎች ሲኖሩ፣ አጠቃላይ የማምረት አቅማቸው የምርቱን ፍላጎት ባለሟሟላቱ ዋና ዋና የመጠጥ አምራቾች ከውጭ አገር በብዛት ቆርኪ ለማስገባት መገደዳቸው ይነገራል፡፡ 

 

86 ኤርትራውያን ስደተኞች በአይሲስ ታጣቂዎች ተጠልፈው ከትሪፖሊ ውጭ መወሰዳቸው ተሰማ። እስካሁን ግን አይሲስ ሀላፊነት መውሰዱን አልገለፀም። አንድ በእንጊሊዝ የሚታተም ጋዜጣ እንደጠቀሰው በምህራብ ሊቢያ ነው 86 ኤርትራውያን በISIS የተጠለፉት Militants from Islamic State of Iraq and the Levant (Isil) are believed to have kidnapped 86 Eritrean refugees from a smugglers’ caravan in westernLibya. The militants struck […]

በትናንቱ የቪኦኤ ዘገባ ላይ አቃቤ ሕግ ቅሬታ አቀረበ ጦማሪ አቤል ዋበላ ችሎት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ ‹‹ሥነ-ሥርዓት ያዝ!›› ዳኞች ‹‹እናንተ ራሳችሁ ሥነ-ሥርዓት ያዙ! ይህ ችሎት ነው፡፡ ግልጽ ነው›› አቤል ዋበላ ‹‹ውሳኔው ለሁሉም ከሆነ፣ ለአቃቤ ህጉም ሆነ ለአለቃው ጠ/ሚኒስቴርም መሆን አለበት፡፡›› ‹‹ጓደኛዬ (አቤል) የሚቀጣ ከሆነ ውሳኔው እኔም ላይ ይታዘዝ›› ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ትናንት ምሽት ከ3፡00 ሰዓት […]

የተሟላ ማስረጃ ሳይኖር በወጪ የተመዘገበ 368 ያልተወራረደ ሒሳብ መገኘቱን፣ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ገቢ መኖሩንና ሌሎችንም ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ዋና ኦዲተር በ2006 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት በጀት ተጠቃሚ የሆኑ 135 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲትን ያልተከተሉ 78 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕጉ መሠረት ያላወራረዱት ሁለት […]

አሸባሪነት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ ያልቻለው ሕዝቡ በሙሉ ሰላይ በመሆኑን ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ ከአገር ተሰድደው የሚውጡት አብዛኛዎቹ ገጠሬ ወጣቶች እንደሆኑና ሟቹ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዳሴ አባት በጣም እንደሚናፍቋቸው ተናገሩ፡፡ ቀድሞ በቃል አቀባይነት ሲሰሩ የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኬኒያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ስታንዳርድ ዲጂታል ከተባለ የኬኒያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ድርጅታቸውን በመወከል  […]

[ Read In PDF ] የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ …

የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ – በአበራ ለማ Read more »

መቶ ከመቶ ደፈንኩ ያለን ‹‹ሰነፉ››ተማሪ ኢህአዴግ በቀጣይ በሚያደርገው የግምባሩ ጠቅላላ ጉባኤ በኃይለማርያም ደሳለኝ ወንበር ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ወርሃ መስከረም የሚሰየመው ‹‹የኢህአዴግ መንግስታዊ ጉባኤም››(ፓርላማ ለማለት ቢቸግረኝ ያወጣሁለት ስያሜ ነው) የሚቀርብለትን እንደወረደ ያጸድቃል፡፡ ይህንን የሚጠብቁ ፌስ ቡከሮች በበኩላቸው የራሳቸውን ጥንቆላ እያስነበቡን ነው፡፡ማንም ይምጣ ያው ነው ያሉ ወገኖችም ቢሆኑ ቢያንስ በወንበሩ ላይ የሚቀመጠው ግለሰብ ‹‹ጉልቻው››በመሆኑ መቀያየሩ […]

ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት የተባለው በአለም ላይ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እሰራለሁ የሚል ተቋም የ 102 የአለም ሀገራትን የፍትህና ህግ ስርአት ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ከ 100 ሺህ የማያንሱ ህዝቦችን መጠይቅ በማድረግ ጭምር የተጠናቀረው ይህ የተቋሙ ሪፖርት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ … የፍትህና ህግ የበላይነት ጉዳይ ብዙ ጊዜ የህግ ሰዎች ስራ ብቻ ተደርጎ […]

በአሜሪካን ሀገር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች ይኖራሉ! እነዚህ ስደተኞች ከጥቃቅን ስራዎች አንስቶ እስከ_ታላላቅ ካምፓኒዎች በወዛቸው ያገኙዋትን ዶላር አጠራቅመው… አንድ ቀን ሀገሬ እገባለው ከሚል ተስፋ ጋር ሕይወትን ይገፋሉ! ህልሙ የሞላለት ጥቂቱ ጠቅልሎ ሲመጣ አብዛኛው ግን በዥዋዥዌው የአሜሪካ ህይወት ባለበት ሰምጦ ይቀራል! ስደት የእድሜ ወፍጮ ነው! በአምስት አመት ውስጥ ሀገሬን አያታለው ያለ ዲያስፖራ ሳይታሰብ ስምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች […]

ለ17 ዓመታት ያህል ፊፋን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ስዊዘርላንዳዊው ሴፕ ብላተር አሁን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታውቀዋል። በሳቸውና በተቀሩት ጓደኞቻቸው ላይ አሜሪካ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ከቀናት በፊት ምርመራ መጀመሯን ተከትሎ ፊፋ እየታመሰ ነው። ደቡብ አፍሪካም የዓለም ዋንጫን በሃገሯ ለማካሄድ ለፊፋ 10ሚሊዮን ዶላር ጉቦ መስጠቷን አምናለች። አሜሪካ የወንጀል ምርመራ መክፈቷን ተከትሎ የፊፋ ዋና መስሪያቤት የሚገኝበት ስዊዘርላንድ ወንጀል መርማሪዎችም በተናጥል […]

የጀርመን ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት አምስተኛውን ዙር የፌዴራልና የክልል ምርጫ በተመለከተ ከሶስት ጋዜጠኞች ውይይት አድርጎ ነበር። የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ሂሩት መለሰ፡- ከየማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ)፣ ከ.ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል) እና ከገበያው ንጉሴ(የጀርመን ሬድዮ የብራስልስ ዘጋቢ) ጋር፤ ስለቅድመ ምርጫውና ድምፅ የተሰጠበት ሂደትና ውጤቱ እንዲሁም የወደፊት ዕጣፈንታና የውጭ ኃይሎች ሚና አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ከተነሱት መህል፡- 1/የማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ):- *የተቃዋሚ ተወካዮች እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል። ውጤቱ ለጥርጣሬ ክፍት ያደርጓል። *አባሎቻቸውን ገለልተኛ ታዛቢ ሆነው የቀረቡት የአገርውስጥ ማህበራት የፓለቲካ ድጋፍ እንዲሰጡ የተደራጁ እንጂ ገለልተኛ አይደሉም። *የውጭ ኃይሎች ላይ መንጠልጠል ጥገኛ አስተሳሰብ ነው። የጉዳዩ ዋና ባለቤት ህዝብ ነው። ህዝቡ ድምፄን ተሰርቋል ብሎ ካመነ እስከመቼ(ለምን) ቁጭ ብሎ ያያል? *ተቃዋሚዎች በራሳቸው ለማሸነፍ አልገቡም። ተበታትነውና ዓቅመቢስ ሆነው ነበር የቀረቡት። አንድም ተቃዋሚ በተወዳደረባቸው ቦታዎች በሙሉ ቢያሸንፍ መንግስት ለመመስረት የሚችል አልነበረም። * በእኛ ዓይነት ብዝኃ-ህብረሰብ ውስጥ በዚህ ደረጃ ማሸነፍ አይቻልም። አንድም ድርጅት እንዲህ ዓይነት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር አይቻለውም። ውጤቱ ለኢህአዴግ አስደንጋጭ እንጂ መልካም ነገር አይደለም።ድርጅቱ ያየዘው አቋም መፈተሽ አለበት። *ተቃዋሚዎችን በማድቀቅ ሳይሆን ሜዳውን ክፍት አድርጎ በተሻለ አስተሳሰብ ለመብለጥ መስራት አለበት። *ነገሩ ሂዶ ሂዶ ወዴት እንደሚያደርሰን አይታወቅም። —– 2/ ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል)፡- *ማን አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነበር። *የሸንጎ ምርጫ ከኳስ ጨዋታ ጋር እኩል ነው። ገለልተኛ ዳኛና ሜዳ በሌለበት አይደረግም። *ተቃዋማ ፓርቲዎች ምንም ተስፋ አልነበራቸውም። *ዕርዳታ ሰጪ […]

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፋይናንስ ሕጋዊነትን ያልተከተሉ ቢሊዮን ብሮች መኖራቸውን ይፋ አደረገ

እየተገነቡ ያሉ የባቡር ፕሮጀክቶች ችግሮችን ጠቆመ

-የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግለት ፓርላማውን በአፅንኦት ጠየቀ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የፋይናንስ ሕጋዊነትን ያልተከተሉ ቢሊዮን ብሮችን ለፓርላማው ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ይፋ አደረገ፡፡

የተሟላ ማስረጃ ሳይኖር በወጪ የተመዘገበ 368 ያልተወራረደ ሒሳብ መገኘቱን፣ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ገቢ መኖሩንና ሌሎችንም ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡

ዋና ኦዲተር በ2006 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት በጀት ተጠቃሚ የሆኑ 135 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲትን ያልተከተሉ 78 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕጉ መሠረት ያላወራረዱት ሁለት ቢሊዮን ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር መኖሩን ጠቁሟል፡፡ በዚህ ያልተወራረደ ሒሳብ ተጠያቂ ከሆኑት መሥሪያ ቤቶች መካከል የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 666.4 ሚሊዮን ብር፣ የትምህርት ሚኒስቴር 433.4 ሚሊዮን ብር፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር 144.2 ሚሊዮን ብር ሕጉን ባልተከተለ መልኩ ወጪ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡ 

ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች በወጣው ሕግና ደንብ መሠረት የመንግሥት ገቢ በወቅቱና በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንና በሌሎች 12 ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶች ላይ በድምሩ አንድ ቢሊዮን ብር ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ገቢ መኖሩንም ዋና ኦዲተር ይፋ አድርጓል፡፡

በወጪ ለተመዘገቡ ሒሳቦች የተሟላ መረጃ መኖሩን ለማረጋገጥ ባደረገው ኦዲት በ29 መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ፣ 368 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቦ መገኘቱን ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ገልጸዋል፡፡ 

ተሟልተው ካልቀረቡ ማስረጃዎች መካከልም ከዕቃ አቅራቢው የተሰጠ ማስረጃ ሳይቀርብ፣ ላቀረበው የክፍያ ጥያቄ ብቻ በወጪነት የተያዘ፣ ተራና አግባብነት የሌላቸው ደረሰኞች ማለትም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሌላቸው ደረሰኞችንና የመሳሰሉትን ሕጋዊ ያልሆኑ ማስረጃዎች በመያዝ የተከፈሉ ወጪዎች እንደሚካተቱም ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ (በ2006) መሥሪያ ቤቶች የፈጸሙት ክፍያ ትክክለኛነትን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በ19 መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ ምክንያቶች የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ 473.469 ሚሊዮን ብር መኖሩን የዋና ኦዲተሩ ሪፖርት ያሳያል፡፡ ከእነዚህም መሥሪያ ቤቶች መካከል ትልቁን ድርሻ ማለትም የ273.845 ሚሊዮን ብር ትክክለኛነቱ ያልተረጋገጠ ወጪ የተመዘገበበት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ነው፡፡

ይህ መሥሪያ ቤት ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ግዥዎችን በተመለከተ ኦዲት ያለማስደረግ ሥልጣን ከዓመት በፊት በአዋጅ የተሰጠው ሲሆን፣ የዋና ኦዲተር የኦዲት ግኝትም ይህንን መብቱን ያልጣሰ እንዲያውም ራሱ መሥሪያ ቤቱ ኦዲት መደረግ ይችላል ብሎ ያቀረበው ሰነድ ላይ የተደረገ ኦዲት ውጤት መሆኑን ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል፡፡ 

የዕቃ አገልግሎትና ግዥ በመንግሥት ደንብና መመርያ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በ63 መሥሪያ ቤቶች ሕግን ያልተከተለ የ957.5 ሚሊዮን ብር ግዥ መፈጸሙን ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡ 

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በአሁኑ ወቅት 98 በመቶ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት የማድረግ አቅም ቢፈጥርም፣ ከዚህ ቀደም በኦዲት ያገኛቸው ችግሮች ዛሬም አለመፈታታቸው አሳሳቢ እንደሆነ አቶ ገመቹ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

‹‹በተለይ ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ ተሰብሳቢ ሒሳቦች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ ግንባታዎችና ግዥዎች በልዩ ሁኔታ ሊታዩ የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸውን ማስገንዘብ እወዳለሁ፤›› ሲሉ ዋና ኦዲተሩ አሳስበዋል፡፡

የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከፋይናንስ ሕጋዊነት በተጨማሪ የክዋኔ ኦዲት ማለትም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ አፈጻጸምን ከተሰጣቸው ኃላፊነትና ከአገሪቱ ሕጐች ጋር ያለውን መጣጣም በመገምገም ሪፖርት ያደርጋል፡፡ በዚህም መሠረት በ2006 ዓ.ም. የክዋኔ ኦዲት ከተከናወነባቸው መሥሪያ ቤቶች መካከል የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የመሠረተ ልማት ግንባታ አፈጻጸም ይገኝበታል፡፡

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መመርያ መሠረት መጀመርያ የፕሮጀክት ምርመራ እንደሚደረግ፣ ፕሮፋይል በተዘጋጀላቸው ፕሮጀክት ሐሳቦች ላይ ዝርዝር ጥናት ከመደረጉ አስቀድሞ የፕሮጀክት ረቂቅ ሰነድ ይዘጋጅና ቅድሚያ የሚሰጣቸው የፕሮጀክት ሐሳቦች ወደ ዝግጅት ሒደት እንዲገቡ ይደረጋል ቢልም፣ በኮርፖሬሽኑ እየተተገበሩ ያሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በ1999 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስቴር መሪነት አጥኚ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ አማራጭ የየብስ ትራንስፖርትን አስመልክቶ ያደረገው ጥናት እንጂ፣ እያንዳንዱን ፕሮጀክት አስመልክቶ የተጠና የፕሮጀክት ጥናት ሰነድ አለመኖሩን ዋና ኦዲተሩ ይፋ አድርገዋል፡፡ 

የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶች ክትትል፣ ቁጥጥርና ድኅረ ትግበራው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፕሮጀክት አዘገጃጀት ማኑዋል መሠረት ሊካሄድ የሚገባው ቢሆንም፣ በዚያ መልኩ እየተካሄደ አለመሆኑን የዋና ኦዲተሩ ሪፖርት ያስረዳል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ የሚያገለግል በኮንትራት ውሉ ውስጥ የተጠቀሱ ለግንባታ ሥራ፣ ለቁጥጥርና ክትትል አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችና ማኑዋሎች ለምሳሌ የጥራት ማረጋገጫ ማኑዋል የመሳሰሉትን ኦዲቱ እስከተከናወነበት ጊዜ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ማቅረብ ባለመቻሉ፣ የፕሮጀክት ውሉ በሚለው የጥራት መሥፈርት መሠረት ፕሮጀክቱ እየተከናወነ መሆኑን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በፕሮጀክቶች የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ውስጥ የሚጠቀሱ ምክረ ሐሳቦች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባ ቢሆንም፣ ኮርፖሬሽኑ በሚዘረጋው የአዲስ አበባ ሚኤሶ መስመር ይህ እየሆነ አለመሆኑን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

ለአብነትም የባቡር መስመሩ በሚያልፍበት በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በርካታ የቱሪስት መተላለፊያ መንገዶችን ሳያስፈቅዱ መዘጋት፣ ያለፈቃድ መንገዶችን በፓርኩ ውስጥ እየቀደዱ ማውጣት፣ በፕሮጀክቶቹ የሚሠሩ የውጭ አገር ባለሙያዎች የዱር እንስሳትን ያለ ፈቃድ እያደኑ ለምግብነት የሚጠቀሙ መሆኑን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በሚኤሶ-ደወሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ ያለውን የእሳተ ገሞራ መከሰት ሁኔታ ሊገመግም የሚችል ጥናት እንዲደረግ ኮንትራቱን የወሰደው ድርጅት ቢጠይቅም፣ በአካባቢው የላይኛው የመሬት ክፍል ላይ የመሬት መሰንጠቆች እየታዩ እሳተ ገሞራ የመከሰቱን ሁኔታ ሳያጠኑ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዲደረግ መፍቀዱ ተገቢ አለመሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ 

የባቡር ፕሮጀክቶች ሲተገበሩ ከኮንትራት ውሉ ውጪ ለሚጨመሩና ለሚቀነሱ ጉዳዮች ኮርፖሬሽኑ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅርቦ እንዲፈቀድ ማድረግ ሲገባው፣ ኮርፖሬሽኑ ግን የሰበታ ሚኤሶ ፕሮጀክት ከ1.639 ቢሊዮን ዶላር ወደ 1.841 ቢሊዮን ዶላር የኮንትራት ዋጋው ከፍ ሲል ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ ያልተፈቀደ መሆኑን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዳቢሶ የሪፖርታቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቀረቡት የኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ፓርላማው መንግሥትን በማሳመን እንዲተባበር ነው፡፡

በፓርላማውና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በተደረጉ ጥረቶች ከሐምሌ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የመሥሪያ ቤቱ የደመወዝ ስኬል ከምርጫ ቦርድ እኩል እንዲሆን ቢወሰንም፣ በተመሳሳይ ጊዜ በተደረገው አጠቃላይ የሲቪል ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት እንዳይካተት በመደረጉ የተፈቀደው የደመወዝ ማስተካከያ የነበረውን ሠራተኛ የማረጋጋት ፋይዳ ሳያስገኝ መቅረቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የተነሳ ከ60 በላይ የመሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሒሳብ ባለሙያዎች በአብዛኛው ቁልፍ ቦታ ላይ ይገኙ የነበሩ መሥሪያ ቤቱን ለቀው መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

በመሆኑም ጥራት ያለውና በርካታ መሥሪያ ቤቶችን የሚሸፍን የኦዲት ሥራ እንዲሠራ የሚፈለግ ከሆነ፣ መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርበታል ያሉት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ፣ ‹‹ፓርላማው በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ›› በይፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ ባለሙያ ኦዲት የሚደረገው ሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ሆኖ ሳለ ለዋና ኦዲተር የደመወዝ ጭማሪ የሚያደርገው ሥራ አስፈጻሚው መሆን እንደሌለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም ነፃነቱን ጠብቆ ሥራውን እንዲሠራ ጭማሪው ውሳኔ ማግኘት ያለበት በፓርላማው መሆን እንዳለበት ተከራክረዋል፡፡

ዋና ኦዲተሩ ላቀረቡት ፓርላማው ጣልቃ እንዲገባ የሚል ጥሪ ወዲያውኑ ምላሽ የሰጡት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ፣ በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ላይ እንደሆኑና በቅርቡ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡  

 

 

የሰማያዊ ፓርቲ አባል ጽኑ እስራት ተፈረደበት

ሰባት አባላቱ ተከላከሉ ተባሉ

አይኤስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አረመኔያዊ ግድያ ለማውገዝ፣ መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠርቶ በነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል›› ከተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ

አባላት መካከል ናትናኤል ያለምዘውድ የተባለው አባል፣ በሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈረደበት፡፡

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የቀረበለትን የወንጀል ክስ ሲሰማ የከረመው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ መናገሻ ወንጀል ችሎት በፍርዱ እንዳብራራው፤ ፍርደኛው ናትናኤል ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አብዮት አደባባይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል፡፡ ‹‹ወያኔ አረደን፣ ኢቲቪ ሌባ›› የሚል መፈክር በማሰማት፣ ከግብረ አበሮቹ ጋር መረበሹንም አመልክቷል፡፡ በፌዴራል ፖሊሶች ላይ ድንጋይ መወርወሩም ተመልክቷል፡፡ የሰዎችና በዕለቱ በሞባይል የተቀረፀ የቪዲዮ ማስረጃ ቀርቧል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን ካሰማ በኋላ ናትናኤል ተከላከል ቢባልም መከላከያ ምስክር እንደሌለው በመግለጹ፣ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እንዳለው በፍርዱ ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ወገኖች የቅጣት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቆ፣ ዓቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ 

ተከሳሽ ናትናኤል በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ብጥብጥ የፈጠረውን ቡድን መምራቱን፣ በሠልፉ ላይ የተገኙት ብዛት ያላቸው ስለነበሩ ብጥብጡ በፖሊስ ኃይል ባይበተን ኖሮ፣ ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችል እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ብጥብጡ ጠቅላላ ምርጫው ሊደረግ በነበረበት ዋዜማ የተደረገ ስለነበር ብጥብጡ አገር አቀፍ ሊሆን ይችል እንደነበር በመግለጽ፣ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወስንለት ዓቃቤ ሕግ የክስ ማክበጃ ሐሳቡን ማቅረቡን ፍርዱ ያስረዳል፡፡

ፍርደኛው ናትናኤል ግን ‹‹ትምህርቴን አቋርጫለሁ፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት እንድጀምር ይፈቀድልኝ፤›› ከማለት ባለፈ ያቀረበው የቅጣት ማቅለያ እንደሌለ ፍርድ ቤቱ ፍርዱን ሲያነብ ተሰምቷል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ ላይ እንደገለጸው፣ ፍርደኛው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 490 (3) ማለትም፣ ስብሰባን ወይም ጉባዔን የማወክ ጥፋት የተፈጸመው በቡድን ወይም የጦር መሣሪያ በመያዝ ከሆነ፣ ከሰባት ዓመታት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ የሚደነግገውን መተላለፉን ጠቁሟል፡፡ ፍርደኛው መንግሥት በሊቢያ ኢትዮጵያውያን የተፈጸመባቸውን አሰቃቂ ግድያ በተመለከተ ሕዝቡ ሐዘኑን እንዲገልጽና ተቃውሞውን እንዲያሰማ በጠራው ሠልፍ ላይ ድርጊቱን በመፈጸሙ፣ ብጥብጡ የተፈጠረው አገራዊ ምርጫ በሚደረግበት ዋዜማ ከመሆኑ አንፃር ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ቀላል ሊሆን እንደማይችል የሚያመለክት መሆኑን ጠቁሞ፣ የወንጀሉን ደረጃ ከባድ ብሎታል፡፡ 

ዓቃቤ ሕግ ፍርደኛው ከግብረ አበሮቹ ጋር በሚል ለማክበጃ የተጠቀመበትን ሐሳብ የወንጀሉ ማቋቋሚያ መሆኑን በመጠቆም፣ ማክበጃውን ውድቅ አድርጐበታል፡፡ ፍርደኛው የወንጀል ሪከርድ የሌለበት በመሆኑ አንድ ቅጣት ተቀንሶለት በሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ሰጥቷል፡፡ 

ማትያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና መሳይ የሚባል አንድ ወጣት በተመሳሳይ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ዓቃቤ ሕግ ሁለት የሰው ምስክሮች ካሰማባቸው በኋላ፣ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ የፈለጉት እርስ በርሳቸው ለመመሰካከር የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ምስክር መሆን እንደማይችሉ በመግለጽ ሌላ መከላከያ ካላቸው እንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡   

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ማስተዋል ፍቃዱና ቤተልሔም አካለ ወርቅ በቀረበባቸው ተመሳሳይ፣ ‹‹ሰላማዊ ሠልፍን ማወክና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል›› የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በመከላከያ ምስክርነት ለማሰማት ለሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥረዋል፡፡

 

 

ግድያውን ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ እጁን ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ዲስትሪክት የማይፀብሪ ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ፣ ስድስት የባንኩ ሠራተኞች ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተገደሉ፡፡

ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተለመደ ሥራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ፣ በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተደብድበው የሞቱት የቅርንጫፉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ ገብሩ፣ የባንኩ ኮንትሮለር አቶ አትንኩት ደምሴና የደንበኞች አገልግሎት ኦፊሰሮች የነበሩት ወ/ሮ ለምለም ግደይና አቶ አስማማው ገብረ ማርያም መሆናቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ንጉሤ ግርማና አቶ ጌትነት ባዩ የተባሉ በኮሜርሻል ኖሚኒስ አማካይነት የተቀጠሩ የባንኩ ሠራተኞችም መገደላቸውን አቶ ኤፍሬም አክለዋል፡፡

የባንኩ ሠራተኞችን በመግደል የተጠረጠረው የጥበቃ ሠራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ፣ ግድያውን ሊፈጽም የቻለበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ የሥራ አፈጻጸሙን በሚመለከት ምክር፣ ተግሳጽና ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው ከደቂቃዎች በኋላ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥበቃና የፅዳት ሠራተኞችን የመቅጠርና የመቆጣጠር ሥራን ለኮሜርሻል ኖሚኒስ መስጠቱን የጠቆሙት አቶ ኤፍሬም፣ የባንኩን ሠራተኞች በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብም የተቀጠረው ከዚያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተጠርጣሪው በሥራው ላይ ተገቢ ያልሆነ ባህሪያትን በማሳየቱ በባንኩ ኃላፊዎች ቢመከርም ሊስተካከል ባለመቻሉ፣ የቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጁ መቐለ ለሚገኘው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ የጥበቃ ሠራተኛውን በሌላ እንዲተካላቸው ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ 

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊዎች በሠራተኞቻቸው ላይ ቅሬታ ሲደርሳቸው በቦታው በመገኘትና ሠራተኞቹንና የተቋሙን ኃላፊዎች በማነጋገር፣ ሠራተኛው ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሥራውን እንዲቀጥል ወይም እንዲባረር እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ተጠርጣሪውም በዕለቱ ተመክሮ፣ ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በዕለቱ ተረኛ ስለነበር መሣሪያውን ይዞ ወደ ሥራው መሰማራቱን ተናግረዋል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ሁለት የፍተሻ ሠራተኞችን አቁስሎ ሌሎቹን መግደሉን አስረድተዋል፡፡ 

የተገደሉት የባንኩ ሠራተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ያስታወቁት አቶ ኤፍሬም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ወልዳይ ገብሩ ቤተሰቦቻቸው በሚኖሩበት በዓደዋ ልዩ ስሙ ወርኢ ዳጋብር ቀብራቸው እንደተፈጸመም አክለዋል፡፡ ኮንትሮለሩ አቶ አትንኩት ደምሴ በትውልድ ሥፍራቸው ባህር ዳር የቀብራቸው ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ ወ/ሮ ለምለም ግደይና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሁለቱ ሠራተኞች አቶ ንጉሤና አቶ ጌትነት፣ በዚያው በማይፀብሪ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ አቶ አስማማው ከማይፀብሪ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲማ በሚባለው አካባቢ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ባንኩ በሠራተኞቹ ላይ በደረሰው ያልታሰበና ድንገተኛ አደጋ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ሠራተኞቹ መገደላቸው ከተሰማበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ቀብራቸው እስከተፈጸመበት ዕለት ድረስ፣ የመቀሌ ዲስትሪክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሻግሬ አስመላሽ በሥፍራው ተገኝተው ያደረጉት አስተዋጽኦም ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የንግድ ባንክ ጠቅላላ የጥበቃዎች ሥራ አስኪያጅም እዚያው ሆነው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አስታውቀዋል፡፡  

 

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት፣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በየጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

መኢአድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ምርጫውን አስመልክቶ በፕሬዚዳንቱ አቶ አበባው መሐሪና በሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሲሰጥ፣ በምርጫው ወቅት ገጠመኝ ያላቸውን ችግሮችና ጫናዎች ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

‹‹ባለፉት አራት ምርጫዎች በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ አስቀምጦ ሙሉ በሙሉ ተሻሽሎ ይካሄዳል የሚል ዕምነት ቢኖረንም፣ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ አምባገነንነት በቀየረው ገዥ ፓርቲ አፈና፣ ወከባ፣ እስራትና ግድያ የተነሳ ምርጫው ሳይሳካ ቀርቷል፤›› በማለት መኢአድ አስታውቋል፡፡

መኢአድ በምርጫው ዕለትና ከዚያ ቀደም ብሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ደረሰብኝ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተቀር ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎችን ጨምሮ አባላቱ መታሰራቸውንና ታዛቢዎቹ ከምርጫ ጣቢያ መባረራቸውን ገልጿል፡፡ 

‹‹ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና፣ ሰላማዊ እንደሆነ ይገለጽ እንጂ በተግባር የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ሰው እየደበደቡ፣ እያሰሩ፣ እያንገላቱ፣ ከመኖሪያ እያፈናቀሉና የግድ ንብን ምረጡ ብለው ለማስፈራራታቸው ተጨባጭ መረጃ ባለበት ሁኔታ እንዴት ብሎ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ እንደተካሄደ የሚያውቀው አፋኙ ሥርዓት ብቻ ነው፤›› በማለት መኢአድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ 

በምርጫው ምክንያት የታሰሩ የፓርቲ አባላትና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ ‹‹ምርጫው ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ የሲቪክ ማኅበራት ባልተገኙበት ኢሕአዴግ ባደራጃቸው የሲቪክ ማኅበራትና አባብሎ ወደ ታዛቢነት ያሰማራቸው የምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት የተካሄደ በመሆኑ፣ ይህንን የፖለቲካ ድራማ የተከናወነበት ምርጫ የማንቀበለው መሆኑን እናስታውቃለን፤›› በማለት መኢአድ መግለጫውን አጠቃሏል፡፡

የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው ሲገልጹም፣ ‹‹ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መክረን ዘክረን ወደፊት የምናሳውቀው ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ 

በተመሳሳይም በዋና ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የዘንድሮው ምርጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መካሄዱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የተለያዩ ክስተቶች በማንሳት አስረድቷል፡፡ በፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮና በሌሎች ኃላፊዎች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ለምርጫ ቦርድ ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች ቁጥራቸው ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ተቀንሶ ፓርቲው በተወሰኑለት ዕጩዎች ብቻ እንዲወዳደር መደረጉ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡

እንዲሁም በአማራ፣ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዕጩ ምዝገባ ወቅት፣ በቅስቀሳና በምርጫው ዕለት አጋጠሙኝ ያሏቸውን ችግሮች በባለ 6 ገጽ መግለጫው አስታውቋል፡፡ አብዛኛዎቹ ችግሮችም ከዕጩዎች አለመመዝገብ፣ ከአባላት መዋከብና መታሰር እንዲሁም የታዛቢዎች በሥፍራው ተገኝተው መታዘብ ከመከልከላቸው ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡

‹‹ጠጣር ግድፈቶች በተንፀባረቁበትና በተስተዋሉበት ሁኔታ የሕግ የበላይነት ተሟልቷል ተብሎ ከነጉድፉ መቀበል የፖለቲካ ቃር የሚያስይዝ ከመሆኑም በላይ፣ ከቀደምቶቹ ምርጫዎች 2002 እና 2005 (ማሟያና አካባቢያዊ) ባልተለየ መልኩ በአንድ ቅርጫት የተቀመጠ የቅድመ ምርጫ ሒደትና ውጤት በመሆኑ ፓርቲው አልተቀበለውም፤›› በማለት አስታውቋል፡፡ 

ቀጣይ አቅጣጫቸውን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸውም ጥያቄ፣ ‹‹በትግል ደክመን ሳይሆን በመንግሥት ጫና ምክንያት መፈናፈን ባለመቻላችን ምንም እንኳን ዛሬ በዝረራ ብንወጣም፤ ዝረራው ግን ለነገው ቁጭት ጭሮብናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ 

ፓርቲው ለወደፊቱ ሁለት አቅጣጫዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ አንደኛው ብሔራዊ መግባባትን ማስገኘት የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት የሚሉ ናቸው፡፡

 

 

 

በቅርቡ ተጨማሪ የግንባታ ጊዜ የተሰጠው ሚድሮክ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለዓመታት አጥሮ ባስቀመጣቸው 13 ቦታዎች ከመስከረም 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግንባታ ለማካሄድ 18 ቢሊዮን ብር መመደቡ ታወቀ፡፡

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እነዚህን ቦታዎች በሕጉ መሠረት መንጠቅ ቢኖርበትም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጉዳዩ  ጣልቃ በመግባት በልዩ ሁኔታ ተጨማሪ የግንባታ ጊዜ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህ መሠረት የግንባታ ጊዜ የተጨመረለት ሚድሮክ በቦታዎቹ ላይ ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የሚድሮክ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ የ13 ቦታዎች ግንባታ በመስከረም 2008 ዓ.ም. እንዲጀመር፣ ለሚድሮክ ኮንስትራክሽን መመርያ መስጠታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በ13ቱም ቦታዎች ላይ የሚሠሩት ሕንፃዎች ዲዛይንን ናሽናል ኮንሰልት ኩባንያ ከጣሊያንና ከስፔን ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሠራ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረበ መሆኑ ታውቋል፡፡

የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በመስከረም ወር ለማስጀመር ሙሉ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ሚድሮክ ለዓመታት አጥሮ የያዛቸው ቦታዎች ካዛንቺስ፣ ሜክሲኮ፣ ሳር ቤት፣ ፒያሳና ጉርድ ሾላን ጨምሮ በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ቦታዎች ቀደም ሲል የተሰጣቸው የግንባታ ጊዜ በማለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲነጠቁ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ አስተዳደሩ እነዚህን የሚድሮክ 13 ቦታዎች ጨምሮ ታጥረው የተቀመጡ 109 ቦታዎች ላይ ስለሚወስደው ዕርምጃ ጥናት ማስጠናቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ በሚድሮክ የተያዙትን ቦታዎች በተመለከተ መውሰድ ያለበትን ዕርምጃ እንዲያጠና ልዩ የባለሙያዎች ኮሚቴ አዋቅሮ አስጠንቷል፡፡

ኮሚቴው ባጠናው ጥናት ሚድሮክ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ መሠረት ያወጣ ቢሆንም፣ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ምንም ዓይነት ግንባታ አለማካሄዱን በመግለጽ ቦታዎቹ  ለሌሎች አልሚዎች እንዲሰጡ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

በዚህ መሠረት በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ አጠገብ የሚገኘውን ቦታ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ደግሞ ጉርድ ሾላ በሻሌ ሆቴል አካባቢ የሚገኘውን ቦታ ካርታ አምክኗል፡፡ 

ነገር ግን ሼክ አል አሙዲ በቦታዎቹ ላይ ግንባታ ያልተካሄደው በሚድሮክ ብቻ ሳይሆን በከተማ አስተዳደሩ ጥፋት ጭምር ነው በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ የሚያካሂዷቸው ግንባታዎች ግዙፍና ውብ በመሆናቸው ለከተማው ከፍተኛ ጠቀሜታ ስለሚኖራቸው የግንባታ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከመከረ በኋላ የሼክ አል አሙዲ አላሙዲ ጥያቄ በልዩ ሁኔታ እንዲስተናገድ ወስኗል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ በሰጠው መመርያ መሠረት ሚድሮክ የውል ማሻሻያ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

 

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ2008 በጀት ዓመት ለማከናወን ላቀዳቸው የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከ35 ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጥያቄ አቀረበ፡፡

ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለ2008 ዓ.ም. የተጠየቀው በጀት ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡ በ2007 በጀት ዓመት ተፈቅዶለት የነበረው በጀት 30 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ 

የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለ2008 ዓ.ም. ከተጠየቀው በጀት ውስጥ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በኢትዮጵያ መንግሥት ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ ወደ 11 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በጀት ግን በውጭ የፋይናንስ ተቋማት የሚሸፈን ይሆናል ተብሎ የተቀመረ እንደሆነ አቶ ሳምሶን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለዘርፉ የሚመድበው በጀት ማደግ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች የበለጠ እንዲሳተፉ ይረዳል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በመንግሥት ከፍተኛ በጀት ከሚበጀትላቸው ተቋማት መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ተጨማሪ በጀት በማስፈቀድም የሚታወቅ ነው፡፡

በየዓመቱ የሚፈቀድለት በጀት እየጨመረ የመጣው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ለ2008 በጀት ዓመት እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሳምሶን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ2007 በጀት ዓመት በአሥር ወራት ውስጥ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለኮንትራክተሮች አስተላልፏል፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ከ25.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1,529.4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ናቸው፡፡ በ2008 በጀት ዓመትም ከ25 ያላነሱ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ያስጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

 

ምርጫው ከምንጊዜውም የተሻለ ቢሆንም የሕግ ጥሰቶች እንደነበሩበት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ቢጠናቀቅምና በአንድ ምርጫ ጣቢያ 1,000 ሰዎች ብቻ መመረጥ ቢኖርባቸውም፣ ሕጉ ከሚያዘው በተቃራኒ በአንዳንድ ጣቢያዎች ከ1,000 በላይ ድምፅ ሰጪዎች

መመዝገባቸውና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካይ  ታዛቢዎች መጓደል፣ ከታዩ ችግሮች መካከል እንደሚጠቀሱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዘንድሮው ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ሁሉ የተሻለና ሰላማዊ እንደነበር ገልጾ፣ ከሁለት ሺሕ ጣቢያዎች በላይ ባደረገው ክትትል የተወሰኑ ስህተቶችን ማስተዋሉን ገልጿል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በሰጡት የቅድመ ሪፖርት መግለጫ፣ ኮሚሽኑ ከ45,000 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች በ2,000 ያህሉ 200 ሠራተኞችን አሰማርቶ የምርጫውን ሒደት መገምገሙን ገልጸዋል፡፡ 

ኮሚሽነሩ በተለያዩ ጣቢያዎች በሕጉ መሠረት በአንድ ጣቢያ ከ1,000 ያልበለጡ ተመዝጋቢዎች ድምፅ መስጠት ሲገባቸው፣ ከዚያ በላይ ድምፅ የተሰጠባቸው አካባቢዎችን መታዘቡን በመግለጽ ለወደፊቱ መስተካከል እንደሚገባው በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የወከሉ ታዛቢዎች መጓደል በኮሚሽኑ ሠራተኞች ከተስተዋሉ እንከኖች እንደሚካተት ጠቁመዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባን በሚመለከት በምርጫ ሕጉ መሠረት በቂ ጊዜ ተሰጥቶት መከናወኑን፣ በአንዳንድ ፓርቲዎች ከሒደቱ ጋር ተያይዞ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ቦርዱ ያደረገውን ጥረት በቅድመ ምርጫ ወቅት በበጐ ከታዩ ጥረቶች እንደሚካተት ኮሚሽኑ አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በዘንድሮው ምርጫ የሴቶች ተመራጭነት ተሳትፎ በገዢው ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ባለፈው ምርጫ ከነበረበት 28 በመቶ ወደ 37 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉ፣ ለዚህም ደግሞ ቦርዱ በገንዘብና በተለያዩ ድጋፎች ማበረታቻ መስጠቱንም በኮሚሽኑ ከተገለጹ በጎ ጎኖች ውስጥ ተካቷል፡፡

እንዲሁም ለፓርቲዎቹ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲረዳ የአየር ጊዜና የኅትመት ሚዲያ ድልድል መደረጉ ለምርጫው መልካም አስተዋጽኦ ማድረጉን አምባሳደር ጥሩነህ አስረድተዋል፡፡ በአንፃሩ አንዳንድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸው የአየር ጊዜና የጋዜጣ ዓምዶችን በአግባቡ መጠቀም ያለመቻላቸው በቅድመ ምርጫ ወቅት ከታዩ ችግሮች ውስጥ እንደሚካተቱ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

በምርጫው ዕለትም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት የምርጫ አስፈጻሚዎች ድምፅ የሚሰጠቱንም ሆኑ ሌሎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነቶች መወጣታቸውንና በአግባቡ ማጠናቃቃቸውን የኮሚሽኑ ቅድመ ሪፖርት ገልጿል፡፡ በተመሳሳይም በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጠረውን የምርጫ ወረቀት እጥረትም በኮሚሽኑ ሪፖርት ተካቷል፡፡

በምርጫ ወቅት ለመራጩ ሕዝብ ስለአመራረጥ ግንዛቤ መስጠቱን ያወሱት ኮሚሽነሩ፣ አልፎ አልፎ ድምፅ አልባ የምርጫ ወረቀቶች እንደነበሩም ገልጸዋል፡፡

በድኅረ ምርጫ ወቅት በሁለት ምርጫ ጣቢያዎች የኮሚሽኑ የክትትል ሥራን ባለመረዳት ባለሙያዎች የድምፅ ቆጠራውን መከታተል ባይችሉም፣ በሌሎች ኮሚሽኑ በመረጣቸው ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራውን በሚገባ ለመታዘብ ችሏል ሲሉ አምባሳደር ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

የድኅረ ምርጫ ሒደቱን አሁንም ቢሆን በኮሚሽኑ ክትትል እያደረገበት መሆኑን፣ እስካሁን ያለው ሒደትም ከምንጊዜው በበለጠ ሰላማዊ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ማስተዋላቸውን አመልክተዋል፡፡

ነገር ግን በመላው አገሪቱ ከነበሩ ጣቢያዎች አምስት በመቶውን ብቻ ተከታትሎ ምርጫው ፍትሐዊና ነፃ ነው ብሎ መደምደም ተዓማኒነቱን ሊያመለክት ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄም ለኮሚሽነሩ ቀርቦ ነበር፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ፣ ‹‹በስታትስቲክስ የአሠራር ሕግ መሠረት አምስት በመቶ የሚሆን ናሙና በመውሰድ አጠቃላይ ድምዳሜ መድረስ ስለሚቻል፣ ባሰማራናቸው 200 ሠራተኞች 2,000 በሚሆኑ ጣቢያዎች ክትትል በማድረጋችን አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ ውጤት ላይ መደምደም ያስችላል፤›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ኮሚሽኑ የምርጫውን አጠቃላይ ሪፖርት በሰኔ ወር መጨረሻ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

 

ጦማሪ አቤል ዋበላ የእስራት ቅጣት ተፈረደበት

ፍርድ ቤት በመድፈር ወንጀል ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ የተባለውና በሽብር ወንጀል ተከሰው በክርክር ሒደት ላይ ከሚገኙት ጦማሪያን መካከል አንዱ የሆነው ጦማሪ አቤል ዋበላ፣ በአራት ወራት እስራት እንዲቀጣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ተሰጠ፡፡ 

ተከሳሹ በሌሎች ቀጠሮዎች መልካም ፀባይ እንደነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ጠቁሞ፣ የአራት ወራት እስራቱን በሁለት ዓመታት ገድቦለታል፡፡

ጦማሪ አቤል ጥፋተኛ የተባለው ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ አዲስ ሲዲ ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርብ፣ የቀረበው ሲዲ ‹‹የሚመለከተው ሶሊያና ሽመልስን ብቻ ነው? ወይስ እኛንም ያካትታል?›› የሚል ጥያቄ  ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ እንዳይናገር ሲከለክለው በመናገሩና ፍርድ ቤቱን ‹‹ራሳችሁ ሥነ ሥርዓት›› በማለት  ኃይለ ቃል ተናግሯል ተብሎ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

 

 

ዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር […]

በመጀመርያው ምስል ላይ የሚታየው ሰው ብሩስ ጄነር ይባላል, በፈረንጆቹ 1976 በክረምት ኦሎምፒክ ለአሜሪካ በዴካትሎን ስፖርት የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘ ስፖርተኛ ነው :: በሁለተኛም ምስል ላይም ሙሉ ልብስ ለብሶ የሚታየው ይኸው ብሩስ ጄነር ሸምገል ብሎ ነው , ከኦሎምፒክ ስፖርቱ በሁውላ , በቀጣይ ህይወቱ የመኪና እሽቅድድም ስፖርት ላይም ተሳትፎ ነበረው , እውቅናውን ተጠቅሞም የተለያዩ የቴቬ ሾዎች ይሰራል .. […]

የህዝብ ጠላት የሆነው ህወሓት ከህዝብ አብራክ የተከፈለውን መከላከያ ሠራዊት በፀረ-ህዝብነት ሙሉ ለሙሉ የማሰለፉ ዓላማው ሲከሽፍ በዓይኖቹ በብረቱ በመመልከት ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰሞኑን በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በመኮብለል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡ ህዝብን ለማጥፋት የቆመውን ህወሓትን ከድተው ለህዝብ ከቆመው አርበኞች ግንቦትት 7 ጎን ከተሰለፉት ከእነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የአግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አባላት […]

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ። በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት ለፊት ይገናኛሉ። የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት […]

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ጠርቶት ከነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ የተካተቱት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ማስተዋል ፍቃዱ እና ቤተልሄም አካለወርቅ በአቃቤ ህግ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍን በማወክና ሁከትና ብጥብጥ […]

አወ – የተግባር እርምጃ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ስለሆነ እኔ በበኩሌ ትግሌን በተግባር ጀምሬአለሁ፡፡ ከታች ለዘረዘርኳቸው እርምጃዎች እናንተም ጨምሩበትና ወደ ተግባር እንግባ!!! «ጠብታ ውሃ ነው ደንጋይ የሚበሳ፣ እንጩህ ዝም ብለን – ሕዝብ እስከሚነቃ፣ አገር እስኪነሳ፡፡» – ሜሮን ጌትነት እውነት ነው ሜሮን – እንጩህ !!! ዝምታው ይሰበር!!! ህወሃት በሰላም፣ በምርጫ ስልጣኑን ይለቃል ማለት ሰማይ ይታረሳል ብሎ ማሰብ […]

የወያኔ ባለስልጣኖች ብዙ ሰዓት የፈጀ የውስጥ ስብሰባ ማድረጋቸው እና በስብሰባው ሀይለኛ የሆነ የእርስ በእርስ የቃላት ሽኩቻ ማድረጋቸውንና የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን ማን ይያዘው በሚለው ጉዳይ በመካከላቸው አለመግባባት መፈጠሩ የደረሰን ዜና ያስረዳል:: በደረሰን ዜና መሰረት በስብሰባው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ላይ ከባለስልጣናቱ ከኢህአዲግ የተለያዩ ወቀሳ እና ትችት የደረሰባቸው ሲሆን በደረሰን ዜና መሰረት ጠቅላይ ሚኒስር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ […]

ምንጮቻችን እንደገለጹልን ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙዎቹን የትግራይ ተወላጆችን 1 ለ 5 በሚል አደራጅቷል:: ይህም በአሻንጉሊቶቹ የተከበበት ኢህአዲግ ካለው መሰል አደረጃጀት ጎን ለጎን ነው:: እነኝሁ 1 ለ 5 የተደራጁት የወያኔ አባላትም ወደዱም ጠሉም ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ለሚመደብላቸው ሰው ስለሚኖሩበት፣ ስለሚሰሩበት በአጠቃላይ ስላዩት፣ ስለሰሙት፣ ስለሰለሉት ዘገባ (ሪፖርት) ያደርጋሉ:: ባለፈው እሁድ ከተካሄደውና ወያኔ እራሱ ተወዳዳሪ፣ እራሱ […]