ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ  ---------------    ዶ/ር ፍሬሕይወት ወልደሃና

– የኩባንያው ንብረት መዘረፉ ይነገራል

የከሰረው የሆላንድ ካር ኩባንያ ባለቤት ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ ከሦስት ዓመት የውጭ አገር ቆይታ በኋላ ባለፈው ሳምንት ወደ አገር ቤት በመመለስ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ ኩባንያቸውን ለመታደግ ያስችላል ብለው ያቀረቡት ዕቅድ ከድርጅቱ ደንበኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ 

ኢንጂነር ታደሰ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ሐሙስ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በሰጡት መግለጫ፣ የከሰረው ኩባንያቸው በሐራጅ ቢሸጥ ማንም ተጠቃሚ እንደማይሆን ገልጸው፣ ይልቁንም ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዕቅድ ይዘው መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢንጂነር ታደሰ ሞጆ በሚገኘው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ የሚገኙትን ያልተገጣጠሙ መኪኖች ገጣጥሞ የቅድሚያ ክፍያ ለከፈሉ ደንበኞች በማስረከብ፣ በቀጣይም ኩባንያው ያለበትን የባንክና የመንግሥት ዕዳ ለመክፈል ማቀዳቸውን አስታውቀዋል፡፡ ዕቅዳቸውን ለመንግሥት አቅርበው ተቀባይነት በማግኘቱ የሕግ ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን፣ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ስድስት ሚሊዮን ብር ይዘው መምጣታቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል፡፡ 

ኢንጂነር ታደሰ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኩባንያው ደንበኞች አካባቢ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት ከኩባንያው መኪና ለመግዛት ቅድሚያ ክፍያ ከፍለው መኪኖቻቸውን ሳይረከቡ የቀሩ ግለሰቦች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ 

የከሰረው የሆላንድ ካር ገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ፍሬሕይወት ወልደሃና ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢንጂነር ታደሰ ከመኪና ገዢዎች ጋር ሳይመክሩ ያቀረቡት ዕቅድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባዮሜዲካል ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ፍሬሕይወት፣ ባለሀብቱ ያቀረቡት ዕቅድ አዲስ አለመሆኑን፣ ለኪሳራ አጣሪ ዳኛና ለገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ቀርቦ ተጨባጭ ማስተማመኛ የሌለው በመሆኑ ውድቅ የተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 

‹‹በዕቅዱ መሠረት ኢንጂነር ታደሰ ስድስት ሚሊዮን ብር ይዤ መጥቻለሁ ነው የሚሉት፡፡ ኩባንያው ያለበት ዕዳ በትክክል መናገር ባይቻልም፣ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ስድስት ሚሊዮንና 80 ሚሊዮን ብር በጣም የተራራቁ ናቸው፤›› ያሉት ዶ/ር ፍሬሕይወት፣ ‹‹ይህንን ዕቅድ መኪና ገዢዎችን (የኩባንያው ደንበኞችን) ሰብስበው ቢያወያዩ መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን ካለው ሁኔታ ግለሰቡ በተጨባጭ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ ደንበኞች የደረሰባቸውን ችግር ለመፍታት ያደረጉት ጥረት የለም፡፡ ከዘመን ባንክ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ ውጪ ከደንበኞች ጋር ያደረጉት ውይይት የለም፤›› ብለዋል፡፡ 

ደንበኞች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ሲከታተሉ ብዙ ውጣ ውረድ እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍሬሕይወት፣ የኩባንያው ባለቤት አገር ጥለው በመኮብለላቸውና ኩባንያው በመዘጋቱ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ሒደት ውስጥ ኪሳራ መታወጁን፣ የኪሳራ አጣሪ ዳኛና ንብረት ጠባቂ መሾሙን አስረድተዋል፡፡ ገንዘባቸውን ከፍለው ንብረታቸውን ያልተረከቡ ግለሰቦች እንደገና ገንዘብ በማዋጣት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ወደመቋጫው ላይ ሲደረስ፣ ባለሀብቱ ከስደት ተመልሰው የሰጡት መግለጫ ውዥንብር እንደፈጠረም አመልክተዋል፡፡ 

‹‹መንግሥት ከለላ አድርጎልኝ መጣሁ ቢሉም በትክክል ግዴታቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸውን የፋይናንስ አቅም ይዘው እንዳልመጡ ድርጅቱ ያለበት ዕዳና ያለው ንብረት በግልጽ ያሳያል፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ መኪኖችን አስረክባለሁ ሲሉ ለዚህ የሰጡት ምንም መተማመኛ የለም፡፡ ከዚህም አልፎ ደንበኞች ለዳኝነት፣ ለጠበቃ፣ ለንብረት ጥበቃና ለመሳሰሉት ተያያዥ ወጪዎች ያወጡትን ተጨማሪ ገንዘብም ሆነ የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ ኢንጂነር ታደሰ የጠቀሱት ምንም ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹የኩባንያው ደንበኞች ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተው የተፈረደላቸው አሉ፡፡ በሒደት ላይ ያሉ አሉ፡፡ ይግባኝ የጠየቁ አሉ፡፡ ተወስኖላቸው የፍርድ አፈጻጸም የሚጠብቁ አሉ፡፡ በተለያየ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ የደንበኞች ፍላጎት ግልጽ ነው፡፡ ገንዘባቸውን ማግኘት ነው፡፡ የተወሰኑት መኪናቸውን ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ አብዛኛው ግን የከፈለውን ገንዘብ ከነኪሳራው ማግኘት ይፈልጋል፤›› ያሉት ዶ/ር ፍሬሕይወት፣ ኢንጂነር ታደሰ ያቀረቡት ዕቅድ በኮሚቴያቸው ተቀባይነት እንዳላገኘ አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ይዘውት የመጡት ሐሳብ ንብረታችንን እንደምናገኝ ማስተማመኛ ስለሌለው አልተቀበልነውም፡፡ በፍርድ ቤት ሒደት እንጨርሳለን፡፡ ዳር የደረሰ ጉዳይ ነው፤›› ብለዋል፡፡ አያይዘውም ኢንጂነር ታደሰ ኮሚቴውን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ደንበኞችን ማነጋገር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ደንበኞች ምን ይላሉ ብለው ማዳመጥ አለባቸው፡፡ አጠቃላይ ስብሰባ ተጠርቶ ከደንበኞች ጋር መወያየት አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡ 

የሆላንድ ካር ንብረት የአገር ሀብት እንደሆነና ንብረት ለመሸጥ ብዙም ፍላጎት እንደሌለ የሚናገሩት ዶ/ር ፍሬሕይወት፣ አዋጭ የሆነና ለሁሉም ወገን የሚጠቅም ዕቅድ ይዞ መቅረብ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 

ከሆላንድ ካር መኪና ገዝተው ያልተረከቡ ሰዎች ከ200 በላይ ናቸው፡፡ ለኩባንያው ብድር የሰጠው ዘመን ባንክ 34 ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋል፡፡ የጉምሩክ ቀረጥና ግብር ዕዳ እንዲሁም የኩባንያ ሠራተኞች የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ኢንጂነር ታደሰ የኩባንያቸው ንብረት 180 ሚሊዮን ብር እንደሚገመትና ኩባንያው ያለበት ዕዳ 63 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የኪሳራ አጣሪ ቡድኑ ይህን አልተቀበለም፡፡ የኪሳራ መርማሪ ዳኛ አቶ አሰፋ ዓሊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተመሰከረለት የዋጋ ገማች የተመነው የሆላንድ ካር ንብረት 83,058,533 ብር ነው፡፡ ኩባንያው ላይ የቀረበው የዕዳ ጥያቄ 160 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ፣ ከዚያ ውስጥ አጣሪ ቡድኑ መርምሮ በመረጃ ያረጋገጠው 74 ሚሊዮን ብር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ አሰፋ ኢንጂነር ታደሰ ያቀረቡትን ዕቅድ በጥብቅ ተቃውመዋል፡፡ ባለሀብቱ በአካል መጥተው እንዳላናገሯቸው አረጋግጠዋል፡፡ በእርግጥ ከአንድ ወር በፊት የአገሪቱ የንግድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የስምምነት ሐሳብ (Composition Proposal) በጠበቆቻቸው አማካይነት ማቅረባቸውን አልሸሸጉም፡፡ 

‹‹የኪሳራ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ፣ ዕዳ ከተጣራ በኋላ ባለቤቱ ድርጅቱን እንደገና ላንቀሳቅሰው እችላለሁ፣ በሐራጅ ቢሸጥ እንጎዳለን፣ ባለቤቶቹ ገንዘብ ጠያቂዎቹ ይጎዳሉ፣ ኩባንያውን አንቀሳቅሼ የእነርሱንም ዕዳ እከፍላለሁ የሚል ዕቅድ አቅርበው ነበር፡፡ ገንዘብ ጠያቂዎች ከተስማሙ (የማይስማሙ ከሆነ እንኳ ፍርድ ቤት ካፀደቀው) መልሰው ሊሠሩ ይችላሉ የሚል የሕግ መብት ስላለ፣ ያንን መብታቸውን ለመጠቀም የስምምነት ሐሳብ ከአንድ ወር በፊት ልከው ነበር፤›› ያሉት አቶ አሰፋ፣ በስምምነት ሐሳቡ ላይ የተጠቀሱ ችግሮችን ነቅሰው አውጥተዋል፡፡ 

‹‹ስድስት ሚሊዮን ብር አገኘሁ ይላል፡፡ ይህ ገንዘብ ያሠራል አያሠራም የሚለውን ለመወሰን አንችልም፣ ሙያችንም አይደለም፡፡ በሕግ የሚጠየቅ ለገንዘብ ጠያቂዎች ዋስትና ተቀማጭ መደረግ አለበት ይላል፡፡ በተጨባጭ ይህን አላደረጉም፡፡ ለማድረግ ስለመቻላቸውና ፈቃደኛ ስለመሆናቸው የገለጹት ነገር የለም፡፡ በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዕቅዱን እንደማንቀበል በጽሑፍ በጠበቆቻቸው በኩል ምላሽ ሰጥተናል፤›› ብለዋል፡፡ 

በፍርድ ሒደት ብዙ ርቀት ሄደው፣ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ንብረት ተቆጥሮ እንዲጠበቅ አድርገው፣ ከብዙ ትግል በኋላ ወደ ጨረታ ሒደት በገቡበት ወቅት ኢንጂነር ታደሰ በድንገት ከተሰወሩበት ብቅ ብለው መንግሥት ከለላ ሰጥቶኝ መጥቻለሁ በማለት የሰጡት መግለጫ፣ ሁሉንም ወገኖች ግራ ያጋባና የጨረታ ሒደቱንም እንዳጨናገፈ አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ 

ገንዘባቸውን ከፍለው መኪናቸውን ሳይረከቡ የቀሩ ግለሰቦች ባዋጡት ሁለት በመቶ ገንዘብ ቢሮ ተከራይተው ባቋቋሙት ተቋም ሥራቸውን እንደሚያካሂዱ የገለጹት አቶ አሰፋ፣ ግለሰቦቹ በፊት የተቀሙት ገንዘብ ሳያንስ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን፣ ይህን ገንዘብ በጥንቃቄ ሥራ ላይ በማዋል ተቋሙ የኩባንያው ደንበኞች ያጡትን ንብረታቸውን ለማስመለስ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡ ዘመን ባንክ አለኝ የሚለውን ገንዘብ ለማስመለስ በመያዣነት የያዘውን የኩባንያውን ንብረት (ፋብሪካ፣ መጋዘንና ሕንፃ) ለመሸጥ ሲነሳ እስከ ሰበር በደረሰ የፍርድ ቤት ክርክር ማስቆማቸውን ገልጸዋል፡፡ ባንኩ አለኝ የሚለውን መብቱን በፍርድ ቤት ያሉ ክርክሮች ሲያልቁ ከተወሰነለት ገንዘቡን እንዲወስድ ተስማምተው ወደ ሥራ መግባታቸውን አስረድተዋል፡፡ የድርጅቱ ሠራተኞችም በፍርድ ቤት አስወስነው የድርጅቱን መኪኖች ለማሸጥ ሲሞክሩ ማሳገዳቸውን ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን 330 ንብረትና ገንዘብ ጠያቂዎች ያሉ መሆናቸውን፣ ከእነዚህ መካከል 242 ያህሉ መኪና ገዢዎች 74 ደግሞ የኩባንያው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የኪሳራ መርማሪውና ንብረት ጠባቂው ከዘመን ባንክ ጋር ተባብሮ የመሥራትን አስፈላጊነት ተረድተው የኩባንያውን ንብረት በጨረታ ለመሸጥ በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያውን አስነግረዋል፡፡ ለማስታወቂያ ብቻ ከ109 ሺሕ ብር በላይ ማውጣታቸውን የሚናገሩት አቶ አሰፋ፣ ስምንት ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ መግዛታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የኩባንያው ንብረቶች በአጠቃላይ በ83,058,533 ብር የመነሻ ዋጋ ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ 

የጨረታ ሰነዱን የገዙት ኩባንያዎች ሞጆ የሚገኘውን የድርጅቱን ፋብሪካና ሌሎች ንብረቶች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡ ጨረታው ሊዘጋ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ኢንጂነር ታደሰ በድንገት የሰጡት መግለጫ ገዢዎችን እንዳራቀ አቶ አሰፋ ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም በጨረታው መዝጊያ ዕለት ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢንጂነር ታደሰ ጠበቃ የኩባንያው ንብረት እንዳይሸጥ የሚከላከል የፍርድ ቤት ማገጃ ለእነ አቶ አሰፋ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የጨረታው ሒደት ተቋርጧል፡፡ 

‹‹በሕግ ተቀባይነት ያለው አሠራር የሚመስለን ዋስትና የመስጠት አቅም ካላቸው፣ ገንዘብ ጠያቂዎችን በኮሚቴያቸው አማካይነት አነጋግረውና ተስማምተው ያንን ስምምነት በፍርድ ቤት አፅድቀው ወደ ሕጋዊ አሠራር መግባት ነው፡፡ አሁን የሰጡት መግለጫ ግራ መጋባት ፈጥሮ ሥራውም ቆሟል፡፡ ይህ የበለጠ ችግር፣ የበለጠ ጥፋት እንዲደርስ ያደርጋል እንጂ ጥቅም ያለው አይመስለኝም፤›› ያሉት አቶ አሰፋ፣ በቀጣይ ምን እንደሚሆን መናገር እንደሚቸግራቸው ተናግረዋል፡፡ 

የኮሚቴው አባላት በሰጡት አስተያየት ዙሪያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ኢንጅነር ታደሰ፣ ያቀረቡት ዕቅድ በመንግሥት ተቀባይነት አግኝቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተደራድረው እንዲሠሩ ተፈቅዶላቸው ወደ አገር ቤት እንደተመለሱ አስታውሰዋል፡፡

‹‹የቀረበው ዕቅድ ዋስትና አይሰጥም ለተባለው ንብረቱ የሚገኘው በእጃቸው ነው፡፡ በእጃቸው ላለ ንብረት እኔ እንዴት ዋስትና ልሰጥ እችላለሁ? እኔኮ መኪኖቹን ስጡኝና ገጣጥሜ ሸጬ ልስጣችሁ አላልኩም፡፡ እኔ ያልኩት የመንግሥትም ተወካዮች ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ እኔ ባመጣሁት ገንዘብ የቴክኒክ ጉዳዮችን ላመቻችና መኪኖቹን ገጣጥመን፣ እሴት ጨምረን ይሸጡና ደንበኞች መኪኖቻቸውን ይረከቡ፡፡ በቀጣይም ሌሎች ባለዕዳዎች ገንዘባቸው ይከፈላቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡

ኢንጅነር ታደሰ በአካል መጥቶ አላናገረንም ለሚለው አቤቱታ በሰጡት ምላሽ፣ ከመጡበት ቀን ጀምሮ የኩባንያው ንብረቶች እንዳይሸጡ ለማሳገድ ሩጫ ላይ ስለነበሩ የሚመለከታቸውን ደንበኞች በጊዜ እጥረት ምክንያት እንዳላወያዩ አምነዋል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ተወካዮች ባሉበት በቅርብ ቀን ከደንበኞች ኮሚቴ፣ ከመርማሪ ዳኛና ከንብረት ጠባቂ ጋር ውይይት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሞጆ ከሚገኘው የሆላንድ ካር መኪና መገጣጠሚያ 610 የመኪና ጎማዎች ከነቸርኬያቸው በቅርቡ መዘረፉን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ፍሬሕይወት እንደማንኛውም ሰው መረጃውን እንደሰሙ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሰፋ በበኩላቸው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለና ለፍርድ ቤት የቀረበ በመሆኑ አስተያየት እንደማይሰጡ ተናግረዋል፡፡ 

ኢንጅነር ታደሰ በበኩላቸው በሁኔታው ማዘናቸውን ለሪፖርተር ገልጸው፣ ‹‹610 የመኪና ጐማ ከነቸርኬው ሲዘረፍ ንብረት ጠባቂዎች የት ናቸው?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ኢንጅነር ታደሰ፣ ‹‹610 ጐማ ለማጓጓዝ በርካታ የጭነት ተሽከርካሪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህ ታቅዶና በቂ ዝግጅት ተደርጐ የተፈጸመ ወንጀል ነው፡፡ ንብረት ጠባቂዎች ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አይደለም፡፡ ንብረቱን ፈርመው የተረከቡ ሰዎች ያስጠይቃቸዋል፡፡ 610 ጐማ ማለት የ110 መኪኖች ጐማዎች ተሰርቀዋል ማለት ነው፡፡ ምን ንብረት እንዳለና ምን ንብረት እንደተሰረቀ አይታወቅም፡፡ የንብረቱ ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አክለውም እርስ በርስ መወነጃጀሉ ቀርቶ በውይይት ችግሮችን ፈቶ ለሁሉም ወገን የሚጠቅም የመፍትሔ ሐሳብ ላይ መድረስ እንደሚበጅ፣ መንግሥትም ያስቀመጠው አቅጣጫ ይህንኑ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

 

ሟች ቀኝ አዝማች ግርማ አበበ

ከንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት እስከ ደርግ ሥርዓት ሶማሊያን አብጠርጥረው በማወቅና ከኢትዮጵያ ወገን የሶማሌ ክልልን በማስተዳደር፣ ብዙ እንደሠሩ የሚነገርላቸው ቀኝ አዝማች ግርማ አበበ በተወለዱ በ86 ዓመታቸው አረፉ፡፡ 

ቀኝ አዝማች ግርማ መንግሥታዊ ኃላፊነት ባለባቸው የሥራ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ከ1943 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ እስከተገለሉበት እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች እየተሾሙ አገልግለዋል፡፡ በ1943 ዓ.ም. የጋራ ሙለታ አውራጃ ዋና ፀሐፊ በመሆን የተመደቡ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜም በአውራጃው ዘመናዊ ትህምርት እንዲስፋፋ ማድረጋቸውን ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው በተፈጸመበት ወቅት የተነበበው የሕይወት ታሪካቸው ይዘክራል፡፡ 

በ1965 ዓ.ም. የኤልከሬ አውራጃ ገዥ፣ በ1966 ዓ.ም. የገናሌ አውረጃ ገዥ፣ በዚያው ዓመት የጅጅጋ አውራጃ ገዥ፣ እንዲሁም በደርግ መንግሥት በ1967 ዓ.ም. የጨርጨር አውራጃ ገዥ በመሆን ያገለገሉት ቀኝ አዝማች ግርማ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ግንኙነት መንግሥታቱን በመምከርና መተግበር አለባቸው ስለሚሏቸው የአስተዳደር ሥርዓቶች ሲናገሩም ይታወቃሉ፡፡ ቀኝ አዝማች ግርማ የሶማሊያን ታሪክ በአራቱም አቅጣጫ አብጠርጥረው ያውቃሉ ከሚባሉ ጥቂት አንጋፋ ሰዎች አንዱ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ 

ከሦስት ዓመት በፊት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ለሶማሌ ላንድ ዕውቅና የመስጠት የህልውና ግዴታ አለባት፤›› በማለት የተናገሩት የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የአልሸባብ ጥቃቶችን ለመመከት ጥሩ አማራጭ አድርገው ከሚያቀርቧቸው የመፍትሔ ሐሳቦች አንዱ የሆነው ለሶማሌ ላንድ እንደ አገር ዕውቅና መስጠትን ሲሆን፣ ምንም እንኳ የሞቃዲሾ ሶማሊያም ኢትዮጵያን በድንበር የሚያዋስን አገር ቢሆንም፣ የሶማሌ ላንድ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ካለው ወዳጅነት፣ ካለው የባህር በርና ሌሎች የኢኮኖሚ ጥቅሞች አኳያ መንግሥት ለሶማሌ ላንድ ዕውቅና መስጠት አለበት ብለው ያምኑ ነበር፡፡ 

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እንግሊዞች የኢትዮጵያን ጦር ለመርዳት መጥተው እንደነበር ለሪፖርተር ሲያስረዱ እንዳስታወሱት፣ በኦጋዴን ማረፊያቸውን አድርገው በቆዩ ጊዜ ሐርጌሳንም ይዘው ስለነበር፣ የኬንያ ሶማሌን ጨምሮ አምስቱን ሶማሌዎች በማዋሀድ አንድ አድርገው ለመግዛት አቅደው ነበር፡፡ ይህም ቢሆን ግን በ1941 ዓ.ም. ኦጋዴንን ለኢትዮጵያ ቢያስረክቡም፣ እንግሊዞች የኦጋዴንን ባላባቶች በመደለል ከኢትዮጵያ እንዲገነጠሉ ለማድረግ ሲሞክሩ እንደነበር ቀኝ አዝማች ግርማ አስታውሰዋል፡፡ 

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከኦጋዴን ባሻገር ደገ ሃቡርንና ጅግጅጋን ከእንግሊዞች እጅ ቢረከብም፣ እግሊዞች ግን ጂቡቲን ጨምሮ የኬንያ ሶማሌን፣ ሶማሌ ላንድን፣ በወቅቱ በጣሊያን እጅ የነበረችውን ሞቃዲሾ ሶማሌን አንድ ላይ አዋህደው የመግዛት ሐሳባቸው አልተገታም ነበር፡፡ እንግሊዞች እንዳሰቡት አምስቱን ሶማሌዎች በማዋሀድ አንዲት የሶማሊያ አገር ለመመሥረት የነበራቸው ዕቅድ በኢትዮጵያ መንግሥት የወቅቱ ፖለቲካ እየጠነከረ መምጣት፣ በኦጋዴን በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት ህልማቸው ሳይሳካ ቀርቷል የሚሉት ቀኝ አዝማች ግርማ፣ እንግሊዞች በእጃቸው ለነበሩት ሶማሌ ላንዶች ነፃነት ለመስጠት መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ ግን የሞቃዲሾ አዲሱ አስተዳደር የአምስቱን ሶማሌዎች ውህደት ዕውን ለማድረግ ሶማሌ ላንድን ወዲያውኑ ወደ ራሳቸው በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያም መምጣት ጀምረው ነበር፡፡ በዚህ አካሄዳቸውም የኢትዮጵያን ሶማሌ ለመገንጠል የመጀመሪያውን ወረራ በ1956 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ እንደፈጸሙ ቀኝ አዝማች ግርማ ለሪፖርተር በሰጡት ቃለ ምልልስ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የሞቃዲሾ ሶማሊያ ከሶማሌ ላንድ መለየት የአምስቱን ሶማሌዎች ውህደትና የታላቋን ሶማሊያ መመሥረት ህልም ቢያከሽፍም፣ ሞቃዲሾ አሁንም ድረስ በሕገ መንግሥቷ ውስጥ ያስቀመጠችው በመሆኑ ይህ አቋም አሁንም ድረስ ለኢትዮጵያና ለሌሎች አገሮች ሥጋት እንደሆነ ቀኝ አዝማች ግርማ ዕምነታቸውን ገልጸው ነበር፡፡ 

‹‹ለጦርነት ስትራቴጂም ሆነ ለፖለቲካ ከሶማሌ ላንድ ጋር መተቃቀፉ ለኢትዮጵያ ትልቅ ጥቅም ይሰጣታል፤›› ያሉት ቀኝ አዝማች ግርማ፣ ለኢትዮጵያ ደኅንነትና ለወሰኗ መከበር ሶማሌ ላንድ ወሳኝ ሚና እንዳላት ገልጸው ነበር፡፡ ለሶማሌ ላንድ ዕውቅና መስጠት አፍሪካውያን ከቅኝ ገዦቻቸው በተረከቡት ወሰን ይፅኑ በሚለው ስምምነት መሠረትም ሶማሌ ላንድ ዕውቅና ማግኘት እንደሚገባት፣ ሞቃዲሾም በዚህ ስምምነት መሠረት ሶማሌ ላንድን ለግዛቷ አካልነት የምትጠይቅበት ምንም ዓይነት የታሪክ አብነት የላትም ብለዋል፡፡ 

ቀኝ አዝማች ግርማ ከወረዳ አስተዳዳሪነት እስከ ምክትል ገዥነት ከዚያም በዋና አገረ ገዥነት በተለያዩ ደረጃዎች የሶማሌ ግዛትንና የሐረር አውራጃዎችን ማስተዳደራቸው ይገራል፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ አራት ጊዜ የተለያየ ሹመት ተሰጥቷቸው አስቸጋሪውን የሶማሌ ክልል፣ ከአጎራባቾቹ ሶማሌ ላንድና ከሞቃዲሾ ሶማሊያ ጋር ተፋጠው እንዳስተዳደሩም የሕወይት ታሪካቸው ይዘክራል፡፡ 

የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት የነበሩት ቀኝ አዝማች ግርማ፣ በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ ሀገር በሐብሮ አውራጃ፣ ገለምሶ ከተማ ተወልደው አድገዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት 60ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸው በትዳር አብረዋቸው ከኖሩት ከወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ሽፈራው ካፈሯቸው ልጆች በተጨማሪ የአሥር ልጆች አያትና የሁለት ልጆች ቅደመ አያት ለመሆን በቅተዋል፡፡ በሚያዝያ ወር ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም ሲለዩ፣ ቀኝ አዝማች ግርማ ከወር በኋላ ተከትለዋቸዋል፡፡

ከመንግሥት አገልግሎት በጡረታ ከተገለሉ በኋላ በ1984 ዓ.ም. የሐረርጌ ተወላጆችና ነዋሪዎች መረዳጃ ማኅበርን በመመሥረትና በምክትል ሰብበሳቢነት በመምራት ተሳትፈዋል፡፡ 

 

 

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሹማምንት ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ

አምስተኛው የኢትዮ አሜሪካ የሁለትዮሽ የመከላከያ ምክር ቤት በአሜሪካ ባደረገው ስብሰባ፣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የደኅንነት ድጋፍና ትብብር መገምገሙ ተሰማ፡፡

ስብሰባው ባለፈው ሳምንት ውስጥ በዋሽንግተን ለሦስት ተከታታይ ቀናት የተካሄዱ መሆኑን ከአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ የኢትዮጵያን ልዑክ የመሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ ናቸው፡፡ በአባልነት ከተሳተፉት መካከል ደግሞ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ ብርጋዴር ጄኔራል ተክለ ብርሃን ወልደ አረጋይና ሌሎች የደኅንነት ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡

የአሜሪካን ልዑክ የወከሉት ደግሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዴቪድ ሮድሪጌዝና በፔንታጎን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሚስ አማንዳ ዶሪ ናቸው፡፡ 

የስብሰባው አጀንዳ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያሉ የፀጥታ ጉዳዮችን መገምገምና የተናጠል መረጃዎችን መለዋወጥ እንደሆነ የኤምባሲው መረጃ ያመለክታል፡፡ በውይይቱ ወቅትም ትኩረት አግኘተው የነበሩት የየመን የደኅንነት ቀውስ፣ የሶማሊያና የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው የመከላከያና የደኅንነት ትብብር ግምገማ እንደተካሄደም ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚሁ ወቅትም የአሜሪካ ጂኦ ስፓሻል የደኅንነት ኤጀንሲና የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ መሠረታዊ መረጃዎችን ለመለዋወጥና ትብብር ለማድረግ ስምምነት ፈርመዋል፡፡

የጅኦ ስፓሻል መረጃዎች ማለት ከአየር ላይ ወይም ከሳተላይት በመሬት ላይ የሚገኙ መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን ነው፡፡ 

ጂኦ ስፓሻል መረጃዎች የማዕድን ሀብቶችን ለማወቅና ለግብርናና ለመሳሰሉት ጥቅም የሚሰጥ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ይህንን እንዲሠራ ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲም የጂኦ ስፓሻል ኢንተለጀንስ ሥራ የማከናወን ኃላፊነት በአዋጅ ተሰጥቶታል፡፡ 

ይህም ማለት ከሳተላይት ወይም ከአየር ላይ በመሬት የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ለደኅንነት ሲባል የመከታተልና የመተንተን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚታየውን የኃላፊነት መጣረስ ለማስተካከልም የማሻሻያ ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

የኮንትራት ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት

በአዲስ አበባ ከተማ በዋና ዋና ጐዳናዎች ላይ ከ132.6 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መንገድ ጠቋሚ ምልክቶችን ለማኖር፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከአንድ አገር በቀል ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡

ከ388 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ አምስት የመንገድ ግንባታዎች ለኮንትራክተሮች ተሰጡ፡፡ዓርብ ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በተደረገው የኮንትራት ስምምነት ላይ እንደተገለጸው፣ በአዲስ አበባ በ52 መንገዶች ላይ የታቀዱትን መንገድ ጠቋሚ ምልክቶች ለመትከል ጨረታውን አሸንፎ ሥራውን የተረከበው፣ ዩኢ ኢንደስትሪያል የተባለው ኩባንያ ነው፡፡ በዚህ ጨረታ ላይ ሦስት ኩባንያዎች ተወዳዳሪ ቢሆኑም፣ ዩኢ ኢንደስትሪያል ያቀረበው ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ አሸናፊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዩኢ ኢንደስትሪያል ጋር ተፎካካሪ በመሆን ቀርበው የነበሩት ጐልድስቶን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ 145.2 ሚሊዮን ብር፣ ሲልክ ትሬዲንግ ኢንተርናሽናል ደግሞ 160.1 ሚሊዮን ብር አቅርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመንገድ ጠቋሚ ምልክቶቹን ለመትከል አሸናፊ የሆነው ኩባንያ ከ700 በላይ የሚሆኑ ምልክቶችን ተክሎ የሚያጠናቅቀው የኮንትራት ውሉ ከተፈረመበት ቀን አንስቶ በ270 ቀናት ውስጥ እንደሆነ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ምልክቶቹ አንፀባራቂ በሆነ አልሙኒየም የሚዘጋጁ ናቸው ተብሏል፡፡ ምልክቶቹ የመንገድ ስያሜዎችን፣ ርዝመትና ሌሎች መረጃዎችን የሚይዙ መሆኑን፣ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ምልክቶች የሚታዩት በቀለበት መንገዱ ላይ ብቻ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ 5.73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸውን አምስት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት ባለሥልጣኑ ከአራት ኮንትራክተሮች ጋር ስምምነት ፈጽሟል፡፡ በጥቅሉ ከ388.3 ሚሊዮን ብር በላይ ከሚወጣባቸው ከአምስቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ እንይ ኮንስትራክሽን የሁለቱን ፕሮጀክቶች ጨረታ አሸንፏል፡፡

እንይ ኮንስትራክሽን ያሸነፈው አንዱ መንገድ ከሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ እስከ ቅድስት ማርያም – ምኒልክ ሆስፒታል – ጃንሜዳ ድረስ የሚዘልቀው 1.7 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ነው፡፡ ይኼንን መንገድ በ74.9 ሚሊዮን ብር እንደሚገነባው ታውቋል፡፡ እንይ ኮንስትራክሽን ከዚህ ፕሮጀክት በተጨማሪ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ግቢ ውስጥ የአስፋልትና የኮብልስቶን መንገድ ለመገንባት የወጣውን ጨረታም አሸንፎ ሁለት የኮንትራት ስምምነቶችን ፈጽሟል፡፡ 

ሁለተኛውን የኢሲኤ ፕሮጀክት ያሸነፈበት ዋጋ 27.7 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ይህ የኢሲኤ የአስፋልትና የኮብልስቶን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግማሽ ኪሎ ሜትር በአስፋልትና በኮብልስቶን ሲሆን፣  የመኪና ማቆሚያና የአስፋልት መንገድ ነው ተብሏል፡፡ የኢሲኤው ሥራ በ35 ቀናት መጠናቀቅ እንዳለበት ተገልጿል፡፡ 

ይህ ፕሮጀክት በፍጥነት ተሠርቶ እንዲያልቅ የተፈለገው ከሐምሌ 3 ቀን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የፋይናንሲንግ ፎር ዴቨሎፕመንት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ከመካሄዱ በፊት ለማድረስ እንደሆነ ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡  

ከአቦ አደባባይ – ብሥራተ ገብርኤል ድረስ ያለውን 1.4 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ለማከናወን ጨረታውን በማሸነፍ ሥራውን የተረከበው አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ነው፡፡ 30 ሜትር ስፋት ያለውን መንገድ ለመገንባት አይኤፍኤች አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 99.4 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ሥራውም በ365 ቀናት ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

የኮንትራት ስምምነቱ እንደሚያመለክተው ከሽሮሜዳ – ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያለውን 2.1 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲገነባ ጨረታውን ያሸነፈው የማነ ግርማይ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ይህንን መንገድ ለመገንባት አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 187.02 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ መንገዱ ጠባብ በመሆኑ አሁን በ20 ሜትር ስፋት በአስፋልት ኮንክሪት ይገነባል፡፡ በስምምነቱ መሠረት መንገዱ 540 ቀናት ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

      

 

በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አረቄ ፋብሪካ ንብረትነቱ የከፍተኞች የኢህአዴግ አመራሮች የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ይህ ፋብሪካ በሃገርና በህዝብ ገንዘብ ተሰርቶ ለባለስልጣኖች ጥቅም ብቻ መዋል የለበትም በማለት ግንቦት 11/2007 ዓ.ም እንዳቃጠሉት የሚስጥሩ አዋቂ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ። ፋብሪካው […]

ምርጫው ሁለት ቀናት ብቻ ቀሩት። በመላ ሀገሪቱ አፈሳው፡ እስሩና እንግልቱ ተባብሶ ቀጥሏል። በአዲስ አበባ ብረት ለበስ ወታደራዊ ካሚዮኖች በብዛት እየታዩ ነው። ከወትሮው የተለየ የሰራዊት ቁጥር በየመንገዱ ላይ እንደሚታይ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በተለይ ወጣቱ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰበት ነው። በአሁኗ ኢትዮጵያ ወጣትነት ወንጀል የሆነ ይመስላል። _በአምቦ 18 ፖሊሶች ታስረዋል። ዶክተር መረራ ጉዲና ሰሞኑን በመንግስቱ ቴሌቪዥን […]

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሚያዚያ 1/2007 ዓ.ም በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የተለጠፈውን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም እያሉ እየቀደዱት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፣ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 በኢህአዴግ የተለጠፈውን የምርጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት እየቀደዱት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በህብረተሰቡ ተግባር የተናደዱት የስርዓቱ ካድሬዎች ምንም አይነት ወንጀል ላልፈፀመ ዜጋ አንተነህ የለጠፍነውን […]

በምርጫ ቦርድ ፖለቲካዊ ውሳኔ የአንድነት ፓርቲን ሰርተፊኬትና ማህተም ያገኙት አቶ ትዕግስቱ አወሉና ተከታዩቻቸው በመካከላቸው በተነሳ ልዩነት ምክንያት በምርጫው በዕጩነት ከቀረቡ ሰዎች መካከል 10ሩ ከምርጫው ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸውን በመጥቀስ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ ቢያስገቡም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ደብዳቤያቸውን እንዲስቡና በምርጫው እንዲሳተፉ እንደተነገራቸው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የመረጃ ምንጭ ተናግሯል ፡፡ እንደ ምንጩ አቶ ትዕግስቱ ሐሰተኛ የስም ዝርዝር በማዘጋጀት […]

ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከኢህአዴግ የም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ ምላሻቸውም በስም ያልጠቀሱዋቸውን ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደምርጫው የገቡት በግማሽ ልብ መሆኑን ፣ የብጥብጥና የሁከት አማራጭ ከተገኘ ያንን ለማካሄድ የሚያስቡ ናቸው ሲሉ ፈርጀዋቸዋል። ” የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ እኛ አሸንፈናል፣ ከተሸነፍን ደግሞ ምርጫው ተጭበርብሮአል፣ ይህንን አውቃችሁ ምላሽ መስጠት አለባችሁ ብለው ሕዝብን […]

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ፣ እና በእነዘላላም ወርቅአፈራሁ የክስ መዝገብ ተከስሰው የሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ባህሩ ታዬ …የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 1፣ 2 እና 3 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ዛሬ በችሎት ጸሀፊ በኩል እንደተሰጣቸው ጠበቃቸው አቶ ተማም አባቡልጉ ገልጸዋል፡፡ ተከሳሾቹ ወደፍርድ ቤት ቢመጡም […]

ሰበር ዜና፡- የቦንጋ ምርጫ በግጭት ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ጊምቦ የምርጫ ክልል በግል ዕጩነት ተመዝግበው የሚወዳደሩት የዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች፣ ደኢሕዴን/ኢሕአዴግን ከወከሉት ዶ/ር መብራቱ ገብረ ማርያም ደጋፊዎች ጋር

በመጋጨታቸው ምክንያት በሥፍራው በመጪው እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ይካሄድ የነበረው ጠቅላላ ምርጫ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጐላ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

‹‹የሁለቱ ዕጩዎች ደጋፊዎች ግጭት በመፍጠራቸው ምክንያት ምርጫውን በሰከነ ሁኔታ ለማካሄድ ይቻል ዘንድ፣ በዚያ ምርጫ ክልል የሚካሄደው ምርጫ ሌላ ጊዜ እንዲከናወን ተላልፏል፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

አቶ ወንድሙ የተቋረጠው ምርጫ መቼ እንደሚካሄድ ግን አልገለጹም፡፡ 

 

ተቃዋሚው አረና ትግራይ “በአባሎቼ ላይ ተፈፅሟል” ባለው ድብደባና ለምርጫ ቅስቀሣ ሥራ በተከራያት መለስተኛ አውቶቡስ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በመላው የትግራይ ክልል የጀመረውን የምረጡኝ ቅስቀሣ ዛሬ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል። ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ የተሽከርካሪዋ የኋላ መስትዋትና መብራት መሰባበሩን በሥፍራው በአካል ተገኝቶ ተመልክቷል። ድብደባ ተፈፀመብን ከሚሉ ሰዎች መካከል ደግሞ ከአፅቢ ከተማ የመጡት አቶ ሄድሮም ኃይለሥላሴ እራሣቸው ላይ በመፈንከታቸው […]

ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ በባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ  በማስፈራራት ጀምሮአል። በምርጫ ቅስቀሳ የፈራው የወያኔ መንግስት ፓርቲዎችን በክርክሩ መርታት ሲሳነው በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አይተናል በክርክሩ የህዝብ አመኔታን ያጣው ገዢው ወያኔ የሚጨብጠው ቢያጣ ንቢቱን ተመስሎ በተሰራ ባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ ላይ ይደነፋ ጀምሮአል ድሮም ኮሮጆ በመስረቅ  ነው 25 ዓመት በሃይል የገዛው ። ገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ […]

‹‹በይልቃል ጌትነት እና በዮናታን ተስፋዬ ላይ መስክር እያሉ ያሰቃዩኛል›› ብርሃኑ ተ/ያሬድ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የፌደራል አቃቤ ህግ በቀን ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የመሰረተው ክስ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ዛሬ ግንቦት 12/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በንባብ ተሰምቷል፡፡ በብርሃኑ ተ/ያሬድ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ ላይ አራት ሰዎች የተካተቱ ሲሆን፣ እነዚህም […]

ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ እንደወጣ ተደርጎ እየተቀሰቀሰ እንደሆን ታወቀ • ‹‹ሰማያዊ በሚያደርገው ቅስቀሳ ስለተደናገጡ ያደረጉት ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ ሰማያዊ ፓርቲ ከ2007 ዓ.ም ምርጫ ራሱን አግልሏል በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የተሳሳተ ቅስቀሳ እየተደረገበት እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ማንነታቸውን ያልታወቁ አካላት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በገዥው ፓርቲ በሚደርስበት ጫና ምክንያት […]

በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቱ በተደራጀ መንገድ መቀጠሉ ተሰማ

በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ የነበረው ጥቃት ጋብ ብሎ የነበረው ቢሆንም፣ በተደራጀ መንገድ እንደገና መጀመሩን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ 

ለበርካታ አፍሪካውያን ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ‘ዜኖፎብያ’ (የዘረኝነት ጥቃት) የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ካወገዘ በኋላ፣ ለተወሰኑ ጊዜያት ተቀዛቅዞ የነበረው ጥቃት እንደገና አገርሽቶ 14 የኢትዮጵያውያን ሱቆች በቀናት ውስጥ እንደተቃጠሉ፣ በደርባንና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በቃጠሎ የሰው ሕይወት ባይጠፋም አንድ ኢትዮጵያዊ አቅሉን ስቶ ሆስፒታል መግባቱን አቶ ኤፍሬም ጠቁመዋል፡፡ 

ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በደርባንና በአካባቢው ወይም ክዋዙሉ ናታል በሚባለው አውራጃ ከጥቂት ቀናት በፊት ለኢትዮጵያውያን የሱቅ ባለቤቶች የማስፈራሪያ ደብዳቤም እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ ለሪፖርተር በኢሜይል የደረሰው ደብዳቤ በአሥር ቀናት ውስጥ እስከ እሑድ ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ፣ ያለበለዚያ ግን ሞት እንደሚጠብቃቸው የሚያትት ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በቅጽል ስማቸው ‹‹የኡምላዚ ነጋዴ ገዳዮች›› ተብለው የሚታወቁት እነዚህ ጥቃት ፈጻሚዎች የሞት ደብዳቤ መሆኑን በመንገር፣ ለኢትዮጵያዊያኑ እንደሰጧቸው አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡

እንደ አቶ ኤፍሬም ማብራሪያ፣ ጥቃቶቹ ድንገት ሳይሆን ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ናቸው፡፡ ‹‹በብዙ ሚዲያዎች ያልተነገረው በመጋቢት ወር አካባቢ የደረሰው የአምስት ኢትዮጵያውያን ተቃጥሎ መሞትም የዚህ ማሳያ ነው፤›› ያሉት አቶ ኤፍሬም፣ የቅርብ ጊዜው ጥቃት በደቡብ አፍሪካ መንግሥትና በዓለም አቀፍ ጫና ለጥቂት ቀናትም ጋብ ብሎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ለዓመታት ለፍተው ያፈሩት ንብረታቸውን ያጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ከተሞች በመሸሽና ከዘመድ ተጠግተው በመኖር ላይ እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡ አንዳንዶች ያላቸውን ንብረት በመያዝ ሱቆቻቸው እንደገና ለመክፈት ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆኑም፣ ብዙዎቹ ሱቆች (ኮንቴይነሮችን) ጨምሮ በደቡብ አፍሪካውያን መወረሳቸውንም ይገልጻሉ፡፡

በቀን ይደረግ የነበረው ተቀይሮ ጥቃት ፈጻሚዎች ሱቆችን በምሽት በእሳት እያቃጠሉ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. የአቶ ኤፍሬምን ጨምሮ አምስት ሱቆች መቃጠላቸውን፣ አቶ ኤፍሬም ግሮሠሪያቸው በመቃጠሉ ምክንያት 400 ሺሕ ብር ያህል እንዳጡ ተናግረዋል፡፡ ዘረፋዎችም እየጨመሩ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንን የሚኖሩበት ቦታ በመሄድ ማስፈራራቱም እንደቀጠለ ይናገራሉ፡፡ በሚያዝያ ወር አካባቢ በነበረው ጥቃት ምክንያት 15 ያህል ሰዎች በቁጥጥር ሥር ቢውሉም፣ በዋስትና መውጣታቸውን አቶ ኤፍሬም ይናገራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያን ለፖሊስ የከሰሱ ሲሆን፣ ጉዳያቸውም እየታየ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ በቅርብ የተቃጠሉ ሱቆች 40 ያህል መሆናቸውን አሁን ደግሞ ከ50 መብለጣቸውን ያስረዳሉ፡፡ በሱቆች መቃጠልና በዘረፋው ምክንያት ከ800 እስከ 1,000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን እንደተጐዱም ያክላሉ፡፡ 

በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 6,000 ያህል ይገመታሉ የሚሉት አቶ ኤፍሬም፣ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ደም መፋሰስ ምክንያት ሊሆን እንደሚችሉም ያስረዳሉ፡፡ ‹‹የነበረው ጥቃት ጋብ ያለ ቢመስልም ተዳፈነ እንጂ አልጠፋም፡፡ አሁንም እሳቱ እንደተቀጣጠለ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለም የኢትዮጵያውያን ደም እንደሚፈስ ምንም ጥርጥር የለውም፤›› ብለዋል፡፡ 

ኢትዮጵያዊያኑ ሥራ መጀመርና ከደቡብ አፍሪካውያን ጋር አብሮ በሰላም መሥራት እንደሚፈልጉ የሚናገሩት አቶ ኤፍሬም፣ ይህ ግን የማይቻል እንደሆነም ግምታቸውን ይናገራሉ፡፡ ቢሆንም ግን ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ ሆኖም ብዙዎች ወደ ሥራ ለመመለስ በመጓጓት ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ንብረቱን የተቀማና የተቃጠለበት ስደተኛ ብዙ ነገር ያጣ ቢሆንም፣ አሁንም ወደ ሱቁ መሄድን መርጧል፤›› በማለት ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዙሉን ንጉሥ ጉድዊል ዝዌልቲንና ቤተሰቦቻቸውን፣ እንዲሁም ሌሎች የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናትን በማናገር ጉዳዩን ለመፍታት እየጣረ ቢሆንም ሁኔታው ግን አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

በሚያዝያው ጥቃት ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 30 ያህል ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ ችሏል፡፡ በአጠቃላይ ከ100 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን የተመዘገቡ ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ ተመላሾች በቅርቡ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ እንደሚሉት፣ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደቡብ በአፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዲፈታ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ አሁን ደረሰ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አቶ ተወልደ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የመመለሱን ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረው ቢሆንም፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ግን ከሞት ጋር መጋፈጥን መምረጣቸው ታውቋል፡፡ መፍትሔው ምን ይሆን? ለሚለው አቶ ኤፍሬም ሲመልሱ፣ ‹‹የደቡብ አፍሪካ መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ጠንካራ ዕርምጃ እንዲወሰድ መደረግ አለበት፤›› ብለዋል፡፡ 

አሁን ደረሰ የተባለውን ጥቃት አስመልክቶ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሙሉጌታ ከልልን በስልክ ለማግኘት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልተቻለም፡፡  

 

 

ዳሸን ባንክ የአዲሱ ፕሬዚዳንት ሹመት እንዲፀድቅለት ጥያቄ አቀረበ

ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ሰይሟል

የዳሸን ባንክ ሥራ አመራር ቦርድ በተሰናባቾቹ የዳሸን ባንክ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ምትክ በተጠባባቂነት የተሰየሙትን አዲስ ተተኪዎች ሹመት እንዲያፀድቅለት፣ ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ ነው፡፡

የዳሸን ባንክ ቦርድ በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን ለቀዋል የተባሉትን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴን ተክተው የባንኩ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ያጫቸው አቶ አስፋው ዓለሙን ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክም ሹመቱን እንዲያፀድቅለት ቦርዱ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ከአቶ ብርሃኑ ቀደም ብሎ የሥራ መልቀቂያ ባስገቡት በቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት በአቶ አበበ ተክሉ ምትክ ደግሞ አቶ ጌትነት ደሴ ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲሠሩ ቦርዱ የሰየማቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ አቶ ጌትነት ይህንን ኃላፊነት እንዲይዙ ከመደረጉ በፊት የባንኩ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

ባንኩ ለሁሉም የባንኩ ከፍተኛ የኃላፊነት መደቦች በተጠባባቂነት የመደባቸው አዲሶቹ ተሿሚዎች በባንኩ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡ አዲሱ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው የባንኩ የኦፕሬሽን ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ በአቶ አስፋው ተይዞ የነበረውን የኦፕሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ ደግሞ አቶ ኃይሉ ቡልቡላ  እንዲይዙት ተደርጓል፡፡ አቶ ኃይሉ ወደዚህ ኃላፊነት እንዲያድጉ እስከተደረበት ጊዜ ድረስ የባንኩ ቄራ ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ነበሩ፡፡ አቶ ብርሃኑ መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ባስገቡት መልቀቂያ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ቢባልም፣ ከኃላፊነት የለቀቁት በግዳጅ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የምክትላቸውም ስንብት በተመሳሳይ የሚታይ ነው እየተባለ ነው፡፡

የዳሸን ባንክ ማኔጅመንት መዋቅር አንድ ፕሬዚዳንትና አራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንደሚኖሩት ያሳያል፡፡ ሆኖም ከአራቱ የምክትል ፕሬዚዳንቶች ቦታዎች የሦስቱ ኃላፊዎች ተሹመውላቸው ሲሠራባቸው ቆይቷል፡፡ አንድ የምክትል ፕሬዚዳንት (ስትራቴጂክ ፕላኒንግ) ቦታ ግን እስካሁን አልተሾመበትም፡፡ ይህ የስትራቴጂክ ፕላኒንግ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ አዲስ በመሆኑ ምደባ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ አስፈላጊነቱ ታምኖ የፀደቀ ስለሆነ አዲሱ የስትራቴጂክ ፕላኒንግ ምክትል ፕሬዚዳንት ይመደባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ዳሸን ባንክ በአገሪቱ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የግል ባንኮች ውስጥ በሀብት ክምችቱ በመጀመርያ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነው፡፡ የአገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት ዓመታዊ ክንዋኔዎች የሚያሳዩ አኅዛዊ መረጃዎችም ከሌሎች የግል ባንኮች ብልጫ ያለው ትርፍ እንደሚያስመዘግብ ያሳያሉ፡፡ የ2007 ዓ.ም. የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸምን የሚያመለክተው የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት የባንኩ ሀብት 24 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይጠቁማል፡፡ ይህም ከሌሎች የግል ባንኮች ብልጫ ያለው ሀብት እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ ከዳሸን ባንክ ቀጥሎ የተቀመጠው አዋሽ ባንክ ሀብቱ 22.4 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ላለፉት አሥር ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛውን ትርፍ እያስመዘገበ የዘለቀው ዳሸን ባንክ የ2007 ዓ.ም. የአሥር ወራት ክንውኑ የሚያሳየው፣ አሁንም ከሌሎች ባንኮች ብልጫ ያለው ትርፍ ማግኘቱን ነው፡፡ 

ባንኩ በአሥር ወራት ከግብር በፊት ያገኘው ጠቅላላ ትርፍ 760 ሚሊዮን ብር መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡ በ2006 ዓ.ም. ባንኩ ከ980 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉ ይታወሳል፡፡ ዳሸን ባንክ ከ720 በላይ ባለአክሲዮኖችን ያሉት ሲሆን፣ እስካለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የተከፈለ ካፒታሉ 1.23 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ይኼም ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ቀጥሎ ሁለተኛው ከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ነው፡፡ የአዋሽ ባንክ የተከፈለ ካፒታል 1.48 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ዳሸን ባንክ ከምሥረታው ጀምሮ የነበሩት አቶ ተከተል ሀብተ ጊዮርጊስ የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ቀጥለውም አቶ ልዑል ሰገድ ተፈሪ የተሾሙ ሲሆን፣ እሳቸውን የተኩት ደግሞ አቶ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ናቸው፡፡ አቶ ብርሃኑ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ሲገለሉ፣ አሁን ለፕሬዚዳንትነት አቶ አስፋው ታጭተዋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ሹመቱን ካፀደቀው አቶ አስፋው አራተኛው የባንኩ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

ከየመን 2,524 ዜጎች መመለሳቸውን መንግሥት አስታወቀ

የመን ውስጥ በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት አደጋ ላይ የወደቁ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል እንደሆኑ በውል ባይታወቅም፣ ከአራት ሺሕ በላይ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው በአስቸኳይ ለመመለስ ሰንዓ በሚገኘው ኤምባሲ መመዝገባቸው ተገለጸ፡፡

ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. የገቡትን ጨምሮ 2,524 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን መንግሥት አስታወቀ፡፡ 

በዕለቱ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ይገባሉ ተብሎ የተጠበቁት የየመን ተመላሾች ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ደከምከም ያሉና ሕፃናት የያዙ ተመላሾች ይበዙ ነበር፡፡

በዕለቱ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 260 መሆኑን፣ ቀደም ሲል የገቡትን ጨምሮ እስካሁን 2,524 ስደተኞች ኢትዮጵያ መግባታቸውን፣ ዶ/ር ቴድሮስ በሥፍራው ለተገኙት ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ 

የየመን መንግሥትን በምትደግፈው ሳዑዲ ዓረቢያና በኢራን በሚደገፉት የሁቲ አማፂያን መካከል በተነሳው የእርስ በርስ ጦርነት በተለይ የውጭ አገር ስደተኞች አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ፍርኃትንና ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር ሪፖርተር ያነጋገራቸው ተመላሾች ተናግረዋል፡፡ ተመላሾቹ እንደሚሉት፣ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎችና በጠረፍ አካባቢዎች የሚገኙ በመሆናቸው ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ 

መንግሥት በቀን ከ200 እስከ 400 ስደተኞች ወደ አገራቸው እየመለሰ መሆኑን፣ እስካሁን የተመዘገቡት ከ4,000 በላይ ዜጎች በሚቀጥሉት አራትና አምስት ቀናት ውስጥ ጠቅልለው ወደ አገራቸው እንደሚገቡ ዶ/ር ቴድሮስ አስረድተዋል፡፡ 

ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ተመላሾች ፊታቸውን ሲያዞሩ ከተመላሾቹ አንዱን ወጣት፣ ‹‹ተቸገራችሁ አይደል? ዘገየንባችሁ? ኤርፖርቱ እኮ ጥቃት ስለደረሰበት የእሱን ዕድሳት እየጠበቅን ነበር፡፡ ነገር ግን አልተሳካም፤›› ሲሉት፣ ወጣቱም መልሶ፣ ‹‹ዶ/ር በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡ በተቻላችሁ መጠን ደርሳችሁልናል፡፡ ረድታችሁናል፤›› በማለት መልሶላቸዋል፡፡ ሌሎችም ተመሳሳይ አስተያየት ነበራቸው፡፡ 

በየመን እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሊቢያ በኢትዮጵያን ላይ የተፈጸመው ዓይነት ጉዳት እንዳለ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እስካሁን ይህ ነው የሚባል ጉዳት የደረሰበት ሰው የለም፡፡ ለደከሙትና ለታመሙት ቅድሚያ ሰጥተን ነው እያመጣን ያለነው፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ከተመላሾች መካከል አንዱ የሆነው ወጣት መኮንን ገበየሁ ሁኔታውን በተመለከተ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ በሶማሊያ በኩል በባህር አድርጎ ነበር ወደ የመን የገባው፡፡ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምብዛም አስቸጋሪ ነገር አልገጠመውም፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ግን፣ ‹‹ወደ አገሬ የምገባበት ቀን ናፍቆኝ ነበር፡፡ በጣም ነው የሚያስፈራው፤›› ብሏል፡፡ መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ኤምባሲ ሄደው መመዝገብ እንዳለባቸው የሰማው መኮንን፣ ተቀጥሮ ይሠራው የነበረውን አስተናጋጅነት ጥሎ መምጣቱን ይናገራል፡፡ እሱ ይኖር የነበረው በዋና ከተማ ሰንዓ ነበር፡፡ በጣም የሚያስጨንቀው በጠረፍ አካባቢዎች ስላሉት ኢትዮጵያውያን መሆኑንም ተናግሯል፡፡ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ሠራተኞች የተደረገለትን ትብብርም አመስግኗል፡፡ 

ፈይሰል አህመድም ከተመላሾች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት በጂቡቲ በኩል ነበር ወደ የመን የተሻገረው፡፡ ያለፈበትን አሰቃቂ ጉዞ ማስታወስ አይፈልግም፡፡ ‹‹ስደት ሲባል አስቸጋሪ ነው፡፡ የእኛ ዓይነቱ ስደት ሕገወጥ ነው፡፡ ሕጋዊ የሚባል ስደት የለም፤›› በማለት በስደት ሆኖ የደረሰበት የከፋ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ቀደም ሲል የመን እንደገባ ገጠር በመሄድ በአንድ እርሻ ውስጥ ተቀጥሮ ያርስ እንደነበር ይናገራል፡፡ ቀጥሎም እርሻውን ትቶ ወደ ከተማ በመግባት ተቀጥሮ የፅዳት ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ ‹‹አሁን በጣም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ መብራት የለም፡፡ ውኃ የለም፡፡ ምግብ የምናበስለው በጋዝ ነበር፡፡ ጋዝ ደግሞ አይገኝም፡፡ ችግር ላይ ወድቀን ነበር፤›› ብሏል፡፡ 

ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ ስደተኞች የከፋ ችግር እንደሚገጥማቸው የገለጸው ፈይሰል፣ በኢትዮጵያዊያን ላይ በተለይ የሚደርስ አደጋ እንዳለ ከሪፖርተር ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡ ፈይሰል፣ ‹‹ሁለቱም ወገኖች አንደኛው የሌላኛው ደጋፊዎች ናችሁ እያሉ ያስፈራሩናል፡፡ ነገር ግን በተለየ ጥቃት አልፈጸሙብንም፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ የከፋ ነው፡፡ እላይህ ላይ ቤት ይፈርሳል፤›› ብሏል፡፡ 

የፈይሰል ሥጋት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን በጠረፍ አካባቢዎች ስለሚሠሩና ጦርነቱም የከፋው እዚያ ስለሆነ ጉዳት እየደረሰባቸው ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡ ‹‹እንዳንድ ጊዜም አልቃይዳ ናችሁ ይሉናል፤›› ብሏል፡፡ ‹‹እባክህን የተቀሩት ኢትዮጵያውያንን እንዳይገድሏቸው መንግሥት እንዲረዳቸው ንገርልን፤›› በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል፡፡ 

በተያያዘ ዜና ከሊቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የማስወጣት ሥራ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን፣ በቅርቡ በሁለቱም አካባቢዎች (በትሪፖሊና በቤንጋዚ) የሚገኙት   100 ስደተኞችን ለማስመለስ መንግሥት በዝግጅት ላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 

አክጉን ግሩፕ የተባለው የቱርክ ኩባንያ በአሥር ቢሊዮን ዶላር በሰንዳፋ አካባቢ ለመገንባት ላቀደው ኢትዮ ተርኪሽ የኢንዱስትሪ ዞን ያስጠናውን የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ፣ የአካባቢና የደን ሚኒስቴር ውድቅ አደረገው፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን የተፅዕኖ ጥናት ውድቅ ማድረጉንም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ በለጠ ታፈረ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ኩባንያው ያቀረበው ጥናት ግልጽነት የጐደለው ነው ብለዋል፡፡ 

አክጉን ግሩፕ ሰንዳፋ አካባቢ ለማስገንባት ከኦሮሚያ ክልል 100 ሔክታር መሬት ተረክቦ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ቢሆንም፣ ግንባታ እንዳይጀምር በመንግሥት ታግዶ ቆይቷል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት የኢንዱስትሪ ዞኑ ይዞታ ከለገዳዲ የውኃ ማጣሪያ ያለው ርቀት አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ ያለው በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ላይ ውኃውን በመበከል ችግር ይፈጥራል የሚል ሥጋት ነው፡፡

ይሁን እንጂ ኩባንያው ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎችን እንደሚያከናውን በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ለሪፖርተር ገልጾ ነበር፡፡ የአክጉን ግሩፕ የቦርድ አባል የሆኑት ሚስተር ዩኑስ አክጉን በወቅቱ የአካባቢ ተፅዕኖ ማስተካከያ ዕቅድ መንደፋቸውን ጠቁመው ነበር፡፡ ይህንንም ለማድረግ የተፅዕኖ መቋቋሚያ የአካባቢና የማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናት እንደሚያካሂዱ ገልጸው ነበር፡፡ 

የአካባቢና የደን ሚኒስትሩ ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት ግን የቀረበው የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መሠረታዊነት ግልጽነት የጐደለው፣ አገሪቱ የምትጠቀምበትን አሠራር ያላሟላና ባለድርሻ አካላትን ያላሳተፈ በመሆኑ ውድቅ ተደርጓል፣ በመሆኑም ኩባንያው እንዲያስተካክል ተነግሮታል ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ እቁባይ አክጉን ግሩፕ ወደ ሐዋሳ ወይም ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ዞን እንዲሸጋገር ሐሳብ ማቅረባቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ኩባንያው ግን በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲሆንለት ጥያቄ እያቀረበ ይገኛል፡፡   

 

ዘ ኢስት አፍሪካን የተሰኘ ድረ ገጽ 50 የሚሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያን ድንበር በማቋረጣቸው ምክንያት፣ የኬንያ የፀጥታ አካላት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ዘገበ፡፡ መንግሥት ግን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ተወልደ ሙሉጌታ ‹‹ብዙም የተጠናከረ መረጃ የለኝም፤›› በማለት ለሪፖርተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በኬንያ ሰሜናዊ ሁር ግዛት የሚገኘውን ኢለሬት ፖሊስ ጣቢያን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የተቆጣጠሩት የሁለቱ አገሮች ድንበር ለማካለል የቅየሳ ሥራ ከተጠናቀቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሆነ፣ የኬንያ ፖሊስን ጠቅሶ ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ክላሺንኮቭ መሣሪያዎችን የታጠቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአሥር ተሽከርካሪዎች ተጭነው የኬንያን ድንበር 16 ኪሎ ሜትሮችን ያህል አቋርጠው በመግባት ገዥ ቦታዎችን በመያዝ፣ የፖሊስ ጣቢያውን የከበቡ መሆናቸውና በአካባቢው ቅኝት ማድረጋቸውን፣ እንዲሁም ፎቶግራፎችን ማንሳታቸውንም እንዲሁ ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

በድረ ገጹ ዘገባ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሥፍራውን እንደሚለቁ ቃል መግባታቸውን ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራዊት ድንበሩን ያቋረጠበትን ምክንያት ያልጠቀሰው ድረ ገጹ፣ የኢትዮጵያ ጦር ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ የኬንያን ድንበር ማቋረጡን አስታውሶ ዘግቧል፡፡

የኬንያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዴቪድ ኦቦነዬ ስለክስተቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ ‹‹ኢትዮጵያና ኬንያ ዘለግ ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸውና ወዳጆች ከመሆናቸው አንፃር ኢትዮጵያውያኑ የከፋ ነገር ያደርሳሉ የሚል እምነት የለኝም፤›› በማለት መግለጻቸውን ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ በማኅበራዊ ድረ ገጾች አስተያየታቸውን ያሰፈሩ ሰዎች፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የኬንያን ድንበር በማለፍ የገባው በመጪው እሑድ የሚካሄደው ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት እንዲካሄድ አስተማማኝ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ በተለይ አልሸባብን የመሳሰሉ ሰርጎ ገቦች የፀጥታ ሥጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የተከናወነ ድርጊት መሆኑንም አክለዋል፡፡ 

 

ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ተርባይን ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

በ350 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ትራንስፎርመር ፋብሪካ አስመርቋል

በግዙፉ መንግሥታዊ የኢንዱስትሪ ተቋም የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሥር የሚገኘው የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ፣ የተርባይን ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ 

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጀመሪያ ላይ ማለትም በ2008 ዓ.ም. የመጀመሪያ ወራት የተርባይንና የጄኔሬተሮች ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ የኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ኢንዱስትሪው ለኃይድሮ ፓወር ማመንጫነት የሚያገለግሉ ተርባይኖችና ጄኔሬተሮች ዲዛይን የማድረግ አቅም መፍጠሩን የገለጹት ሻለቃ አሰፋ፣ በቀጣዩ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን መርሐ ግብር መጀመሪያ ላይ የተፈጠረውን አቅም ወደ ማምረት፣ መትከልና ሥራ ማስጀመር ይቀየራል ብለዋል፡፡ 

ፋብሪካውን ለማቋቋም ምን ያህል ወጪ ያስፈልጋል የሚለውና ሌሎች የአዋጭነት ጥናቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ2002 ዓ.ም. በአሥር ቢሊዮን ብር ካፒታል ሲመሠረት፣ የ200 ሺሕ ብር መንቀሳቀሻ ካፒታል ተፈቅዶለት በኮርፖሬሽኑ ሥር የተደራጀው የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በአሁኑ ወቅት ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንደሚያንቀሳቅስና በሥሩም ሰባት ፋብሪካዎች መቋቋማቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ 

በቅርቡ በ350 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከአዲስ አበባ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ታጠቅ የኢንዱስትሪ ዞን ያስገነባውን የትራንስፎርመር ፋብሪካ ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. አስመርቋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ይህንን ፋብሪካ ከመገንባቱ ቀደም ብሎ የተለያዩ ትራንስፎርመሮችን ምርትና ዕድሳት በማድረግ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያቀርብ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ መጠን ያላቸው ትራንስፎርመሮችን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማቅረቡን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ 

ነገር ግን ቀደም ሲል የሚያመርትበት ወርክሾፕና የአገሪቱ የትራንስፎርመር ፍላጎት መጨመር ራሱን የቻለ ፋብሪካ እንዲያቋቁም አስገድዶታል፡፡ በመሆኑም በቡራዩ ታጠቅ የኢንዱስትሪ መንደር በ28 ሔክታር ላይ ያረፈ ፋብሪካ በቻይናው ፖሊ ግሩፕ አማካሪነት ገንብቶ በይፋ አስመርቋል፡፡ 

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የአገሪቱ የትራንስፎርመር ፍላጎት በዚህ ፋብሪካ እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡ 

‹‹ኢትዮጵያውያን አይችሉትም›› የሚል አስተሳሰብ የነበራቸው ወዳጅ አገሮችን ያሳመኑ ፕሮጀክቶችን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካው በተጨማሪ በ300 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስገነባው የኬብልና ዋየር ማምረቻ፣ የፓወር ፋክተር ኮሬክተርና የኮምፓክት ሰብስቴሽን ማምረቻ፣ በ350 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባ የኢንጂን ማምረቻ ፋብሪካ፣ በ300 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባ የሶላር ፓናል ማምረቻ ፋብሪካ፣ በ200 ሺሕ ብር የተገነባ የሞተርና ጄኔሬተር ፋብሪካ በሥሩ ይገኛሉ፡፡ 

 

የፊታችን እሑድ በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በዘንድሮ የምርጫ ተሳትፎው ላይ በርካታ ችግሮች እየገጠሙት ቢሆንም፣ በምርጫው እስከ መጨረሻው ድረስ ተሳትፎው እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ 

‹‹ለመርሆዋችን ተገዥ በመሆን የምርጫ ተሳትፎአችን እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤›› በሚል ርዕስ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ በምርጫ ተሳትፎው ላይ እየደረሱ ነው ያላቸውን ችግሮች ኢዴፓ ገልጿል፡፡

ፓርቲው ያገኛቸውን ነፃ የአየር ሰዓቶች በመጠቀም አማራጮቹን ለሕዝብ እንዳያደርስ በሚዲያ ተቋማት የደረሰበትን ሳንሱር፣ በየክልሉ በሚወዳደሩ ዕጩዎቹ ላይ የማዋከብ፣ የማስፈራራት፣ ስም የማጥፋትና የመደብደብ ዕርምጃዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው፣ ዕጩዎቹና ደጋፊዎቹ ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸው፣ የፖስተር መቀደድ እንደ ገጠመው፣ ባነሮችን ከቦታቸው ላይ መሰወርና ዕጩዎቹን ከሥራ ማባረር፣ ደመወዝ መከልከል፣ ከአገልግሎት ማግለልና የመሳሰሉት እየደረሱበት ካሉ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡

ኢዴፓ በዚህ መጠኑ ያለፈ ተፅዕኖ ምክንያት በክልል የሚገኙ ጥቂት ዕጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫ እንቅስቃሴ ለማግለል የሚያስገድዳቸው ሁኔታ እንደተፈጠረ በመግለጫው የጠቆመ ቢሆንም፣ የፓርቲው የጥናትና ምርምር ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ግን ችግሩ በድርድር ተፈቶ አሁን ዕጩዎቹ ሥራዎቻቸውን በአግባቡ እያናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ዋሲሁን፣ ‹‹ቁጫና ወላይታ ላይ አባሎቻችን ከሌሎች ፓርቲ አባላት ጋር በመሆን ከምርጫው ራሳቸውን እንደሚያገሉ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ችግሩ በመፈታቱ ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡ የምርጫ ቅስቀሳውንም ሲያከናውኑ ነበር፤›› በማለትም አክለዋል፡፡

‹‹ፓርቲያችን እነዚህ ከመጠን ያለፉ ጫናዎች ቢኖሩም፣ አባሎቻችንና መዋቅሮቻችን ችግሩን ተቋቁመው በምርጫው ውስጥ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እስከ መጨረሻው እንዲዘልቁበት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፤›› በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም በምርጫው ተሳታፊነቱን እንደሚያረጋግጥ ኢዴፓ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በዚህ አገር የምርጫ ሥርዓቱ ጠንካራ መሠረት ላይ ሊቆም የሚችለው በማኩረፍና ራስን ከምርጫ ሒደት በማግለል ሳይሆን፣ በሒደቱ ውስጥ በመቆየት ችግሮችንና ጫናዎችን በመቋቋም፣ በማጋለጥና ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት በማድረግ ነው ብሎ እንደሚያምንም ኢዴፓ አትቷል፡፡

በዘንድሮ ምርጫ ከሚሳተፉ 58 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ኢዴፓ፣ 165 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ 501 ዕጩዎችን ካቀረበው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እና 270 ዕጩዎችን ካስመዘገበው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በመቀጠል፣ በርካታ ዕጩዎችን በማስመዝገብ ሦስተኛ ፓርቲ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡ በቦርዱ መረጃ መሠረት 139 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡   

 

በርካታ የውጭ ኩባንያዎች ከንፋስ ኃይል ለማመንጨት ፍላጎት አሳዩ

በሰኔ 2007 ዓ.ም. መጨረሻ በሚጠናቀቀው የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን፣ ከንፋስ ከሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል 894 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ቢታሰብም፣ ማሳካት የተቻለው 324 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡ 

 

ይህ 324 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሊገኝ የቻለው ከአዳማ አንድ 51 ሜጋ ዋት፣ ከአሸጎዳ 120 ሜጋ ዋትና ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ከተመረቀው አዳማ ሁለት 153 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ድምር ነው፡፡ 

ሌሎች ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ፍጥነት መሄድ ባለመቻላቸው ዕቅዱ ወደሚቀጥለው አምስት ዓመት መሸጋገር ግድ ሆኖበታል፡፡ በዕቅድ ዘመኑ ግንባታቸው ተጀምሮ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቁ የነበሩት አይሻ 300 ሜጋ ዋት፣ መሶቦ-ሐረና 42 ሜጋ ዋት፣ አሰላ 100 ሜጋ ዋትና ደብረ ብርሃን 100 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ 

እነዚህ ፕሮጀክቶች ግን እስካሁን ፋይናንስም ሆነ ኮንትራክተር አላገኙም፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ እነዚህን የንፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማግኘት በርካታ ኩባንያዎች ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡ 

ምንጮች እንደገለጹት የአይሻን ፕሮጀክት የቻይናው ዲዶንግ ፎንግና የጀርመኑ ላፍቶ ኩባንያዎች ለማልማት ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ ከእነዚህ ኩባንያዎች በተጨማሪ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ተሳታፊ እንዲሆን መንግሥት ፍላጎት አሳይቶ በድርድር ሒደት ላይ ይገኛል፡፡ 

አዳማ ሁለትን የገነቡት ኃይድሮ ቻይናና ሲጂሲ ኦቨርሲስ አሰላ ላይ ይገነባል ተብሎ የሚጠበቀውን የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት በአዳማ ሦስት ስም ለመረከብ ድርድር እያካሄዱ ነው፡፡ 

ነገር ግን የአሜሪካው ዲሴንቴ ኩባንያን ጨምሮ የቱርክ፣ የቻይናና የአውሮፓ ኩባንያዎች የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለማግኘት ፍላጎት እያሳዩ በመሆናቸው ውድድሩ መካረሩን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ 

እነዚህ የውጭ ኩባንያዎች ይዘው የመጡት በዓለም አቀፍ ደረጃ የወቅቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከመሆኑም ባሻገር፣ አንድ ተርባይን ያለው የማመንጨት አቅም አሁን ካለው 1.5 ሜጋ ዋት የበለጠ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት በሩን ለድርድር እንዲከፍት እንዳደረገው ታውቋል፡፡ 

ከአዲስ አበባ ከተማ 95 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገነባው አዳማ ሁለት ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በተመረቀበት ወቅት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ እንደተናገሩት፣ የአዳማ ሁለት ፕሮጀክት ሥራ መጀመር በአገሪቱ ከንፋስ ኃይል ይመረት የነበረውን 171 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ወደ 324 ሜጋ ዋት አሸጋግሮታል፡፡ 

‹‹እነዚህ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከውኃ ማመንጫ ጣቢያዎች ጋር የተጣጣመ የኃይል ስብጥር ለመፍጠር ጠቀሜታ አላቸው፤›› ያሉት አቶ ዓለማየሁ፣ ‹‹የዝናብ እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት የንፋስ ኃይል የሚጨምር በመሆኑ፣ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ከመዘርጋት አንፃር ጉልህ ሚና ይጫወታል፤›› በማለትም የፕሮጀክቱን ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ከውኃና ከንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 2,368 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል፡፡ 

ኢትዮጵያ ከውኃ 50 ሺሕ ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ዋት፣ ከእንፋሎት ከአሥር ሺሕ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

በሰኔ 2005 ዓ.ም. ተጀምሮ በግንቦት 2007 ዓ.ም. የተጠናቀቀው አዳማ ሁለት 102 ተርባይኖች አሉት፡፡ አንዱ ተርባይን 1.5 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡ ይህ ፕሮጀክት 345 ሚሊዮን ዶላር ሲወጣበት፣ 85 በመቶ በቻይናው ኤግዚም ባንክ፣ ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

 

አወዛጋቢ በነበረው የባዮ ሴፍቲ ወይም የደኅንነት ሕይወት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የፓርላማው የተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለመጀመርያ ጊዜ ጥልቅ የተባለ ውይይት ካደረገበት በኋላ፣ በረቂቁ ላይ ማሻሻያዎችን በማከል ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ፓርላማው አፀደቀው፡፡

በ2001 ዓ.ም. በጄኔቲክ ምሕንድስና የተለወጠ ህያው ወደ ኢትዮጵያ በሚገባበት ወቅት፣ በኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ደህንነት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያስችል እጅግ ጥብቅ የተባለ የኢትዮጵያ የደኅንነት ሕይወት አዋጅ ፀድቆ ነበር፡፡

የዚህ አዋጅ መፅደቅ በወቅቱ ተከስቶ ለነበረ ድርቅ በጄኔቲክ ምሕንድስና የተለወጠ የስንዴ ዕርዳታ ወደ አገር እንዳይገባ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

ይህ አዋጅ በጄኔቲክ ምሕንድስና የተለወጡ ዘሮች ወይም ህያዋን ለጥቅም እንዳይውሉ ይከልክል እንጂ ለምርምር፣ ለትምህርትና ለሙከራ በዝግ ላብራቶሪ መከናወን የሚቻልበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በዝግ ላብራቶሪ የተፈቀዱ ምርምሮችን ለማድረግ የተቀመጡት መሥፈርቶች አስቸጋሪነትና የአዋጁ ዓላማም ወደ መከልከል ያመዘነ በመሆኑ፣ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ጥቅምት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፓርላማ ቀርቦ ነበር፡፡ 

ረቂቅ አዋጁ የተመራለት የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ከጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ አምስት መድረኮችን በማዘጋጀት ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጐ፣ የውሳኔ ሐሳቡን ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ አንቀጽ ሁለት ንዑስ አንቀጽ 1(5) ላይ የሰፈረውን ድንጋጌ ሙሉ በሙሉ ሰርዞታል፡፡ 

የተሰረዘው አንቀጽ ‹‹የተጤነ ልቀት›› ማለት ከግንዛቤ በመነጨ ስምምነት ልውጥ ህያውን ለንግድ፣ ለምግብ፣ ለዕርዳታ ምግብ፣ አካባቢን ለማፅዳት፣ ለማስተማሪያነት፣ ለምርምር፣ ለመስተዋት ቤት፣ ለውኃ ውስጥ እርባታ፣ ለእንስሳት መኖ፣ ወይም ለሌላ የእንስሳት ግብዓት፣ ለሰው ወይም ለእንስሳት ሕክምና ወይም ለማስወገድ ወደ አካባቢ መልቀቅ እንደሆነ ያስቀምጥ ነበር፡፡ 

ይህ ማሻሻያ ረቂቅ አንቀጽ ላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የአካባቢ ጥበቃ አቀንቃኞች እንዲሰረዝ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ የተለወጠ ህያው ወደ አካባቢ መለቀቁ በኅብረተሰብ ጤና ላይ ጠንቅ እንደሚኖረውና የኢትዮጵያን ብዝኃ ሕይወት ይበርዛል የሚል ነው፡፡

ይህንን ሥጋት ከግምት ውስጥ ያስገባው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አንቀጹን ሙሉ በሙሉ ሰርዞታል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ብሔራዊ የደኅንነት ሕይወት አማካሪ ኮሚቴ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ በሕግ እንዲቋቋምና የኮሚቴው ተግባርም ደኅንነተ ሕይወትን በተመለከተ መንግሥትን ማማከር ነው፡፡ 

ቋሚ ኮሚቴው የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ያቀረቡት ሐሳብን ሙሉ በሙሉ ባይቀበልም፣ የተደረጉት ሁለት ማሻሻያዎችና ብሔራዊ አማካሪ ኮሚቴ በሕግ እንዲቋቋም መደረጉን ሪፖርተር  ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ተቀብለዋል፡፡

ሁለተኛ የተባለው ማሻሻያ ‹‹በግንዛቤ የመነጨ ስምምነት እንዲሰጠው ለሚኒስቴሩ ማመልከቻ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው በላከው አገር ሕግ ዕውቅና ያለው መሆን አለበት፤›› ይላል፡፡ 

በረቂቁ ተቀምጦ የነበረው ግን ‹‹ከግንዛቤ የመነጨ ስምምነት እንዲሰጠው የሚጠይቅ የውጭ ላኪ፣ በላኪው አገር ሕግ ኃላፊነት እንዲወስድ የሚፈቀድለት መሆኑን የሚገልጽ በራሱ በላኪው የተፈረመ ሰነድ ማቅረብ አለበት፤›› የሚል ነው፡፡

የአካባቢ አቀንቃኞቹ ይህ አንቀጽ መሻሻል እንዳለበት፣ ምክንያቱም ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአገራቸው ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚገልጽ ደብዳቤ መጻፋቸው ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው፣ በአገራቸው ሕግ ራሳቸው ዕውቅና ያላቸው መሆን ይገባቸዋል ሲሉ አቤቱታቸውን ሲያሰሙ ነበር፡፡ 

ከግንዛቤ የመነጨ ስምምነት የሚል ስያሜ ያለው ፈቃድ ማግኘት ማለት፣ የተለወጠ ህያውን ወደ አካባቢ የመልቀቅ እንቅስቃሴን ለማካሄድ የሚያስችል ብቻ ነው፡፡ ፓርላማው በቋሚ ኮሚቴው የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ በመቀበል ረቂቁን አፅድቆታል፡፡     

 

በትላንትናው እለት በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተይዞ ወደማዕከላዊ ተወስዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲው አቤል ኤፍሬም ማዕከላዊ በሚገኙ የገዢው ፓርቲ ደህንነቶች ከትላንት ከቀኑ 5 ሠዓት ጀምሮ እስከ እኩለሌሊት በተፈፀመበት ከፍተኛ ድብደባ ኩላሊቱ በመጎዳቱ ዛሬ ጠዋት 11 ሠዓት ላይ ወደምንሊክ ሆስፒታል እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቤል ከመያዙ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች […]

  በኢትዮጵያ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በቀጣይ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ምን ይጠብቃል? በከተማ ያሉ ወጣቶች ድምፃቸውን ሊሰጡት እንደሚችሉ የሚገፀው ፓርቲው የሚያጋጥሙ እንቅፋቶች እንዳሉ ሆነው በከተማ አካባቢ በሚኖረው ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ ሊያገኝ እንደሚችል ፓርቲው ይገልፃል ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርቲው ያለውን አቋም ጨምሮ ትንታኔን ይዞ ቀርቧል ቀሪውን ይመልከቱ Ethiopia’s newest party takes […]

ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ […]

በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡ ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ […]

የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ! እነሆ መልዕክቱን ያንብቡ፤ ሼር በማድረግም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጠይቃችኋል! “ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ) ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን […]

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በሚሊሻዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አዳነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ታዛቢዎቹ ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር አብራችሁ እየሰራችሁ ነው›› እየተባሉ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ በቃሉ ቀሪዎቹን ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር ሲሰሩ አገኘናቸው ብለን እንከሳችኋለን›› እያሉ እያስፈራሯቸው ነው ብለዋል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የምትገናኙበት ነው በሚልም ስልካቸውን […]

    ቢቢሲ ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ የሊቢያ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሜዲትራኒያን ባህር በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ አውሮፓ አዘዋዋሪዎች ከስደተኞች ጋር ታጣቂዎቹን በመቀላቀል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው ታጣቂ ቡድኑ በሰሜን አፍሪካ ጀልባ ባለቤቶች ስራውን እንዲሰሩ በመፍቀድ ከገቢያቸው ደግሞ 50 በመቶ ያህሉን ይቀበላሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ የአይ ኤስ ታጣቂዎች በባህር በሚደረገው ጉዞ ከሌሎቹ ስደተኞች በምን […]

በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ የዞኑ፣ የወረዳውና የየ ምርጫ ክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች […]

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በክልሉ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ሰንካላ ምክንያት የስርዓቱ ካድሬዎች ባሰማሯቸው በሆዳቸው […]

ሃይለማርያም ከስልጣን ሲባረር እ አ አቆጣጠር በ2009 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጥቅምና ምቾት ለመወሰን የወጣው አዋጅ ለሃይማርያም የማያገለግልና ሃይለማርያም የዚህ ተጠቃሚ እንደማይሆን ታውቋል።

ሃይለማርያም ከስልጣን ሲባረር እ አ አቆጣጠር በ2009 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጥቅምና ምቾት ለመወሰን የወጣው አዋጅ ለሃይማርያም የማያገለግልና ሃይለማርያም የዚህ ተጠቃሚ እንደማይሆን ታውቋል።
ቀደም ብሎ ህወሃት ሃይለማርያምን ለማስወገድና የህወሃቱን ቴድሮስ አድሃኖም ጠ/ሚንስቴር አድርጎ ለመሾም መስማማቱን ዘግበን ነበር።

አሁን ደግሞ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሃይለማርያም ስልጣኑን ሲለቅ ከስልጣን ለተገለሉ ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሚደረገው ጥቅምና እንክብካቤ ሊደረግለት እንደማይገባ ህወሃቶች ተስማምተውበታል፡
ለዚህም ያዘጋጁት ምክንያንያት

1ኛ. በProclamation No. 653/2009 አንቀጽ 12. Pension Rights ንኡስ ቁጥር
“1/ Notwithstanding any provision to the contrary under the relevant pension law, if a Senior Government Official who has served for at least one election term:”
አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ቢያንስ የአንድ የምርጫ ዘመን ማገልገል አለበት የሚለውን እንደሚጠቅሱበትና እሱ ደግሞ ይህን ስለማያሟላ ጥቅማ ጥቅሙ አይገባውም። ዳግመኛም እንደማይመረጥ ተወስኗል፤ እንዳውም በምርጫ ጣቢያው በሌላ ተወዳዳሪ እንሚሸነፍ ይጠበቃል፡

2ኛ. ጥቅሙ የሚገባው በረሃ ለታገሉ እንጂ እዚህ ከተማ ተቀምጠው ከድል በሗላ ብቅ ለሚሉ መሆን የለበትም የሚሉ አክራሪ የህወሃት አባላት ለመቶ አለቃ ግርማ የሚደረገው እንክብካቤም ስህተት መሆኑንና እንደሚያንገበግባቸው ተገልጿል፡
ባለራዕዩ መሪ መለስ ዜናዊ በህይወት ኖሮ ያላገኘውን እንክብካቤና ክብር ሃይለማርያም ሊያገኝ አይገባም የሚሉም አሉ፡ ሃይለማርያም ስልጣን ከለቀቀ በሗላ የመለስን ስም የሚያገዝፍ የሃይለማርያምን ደግሞ የሚያቀጭጭ ዶክመንታሪ እንደሚሰራ፡ ዶክመንታሪውም የሃይለማርያም ንግግሮች እየተቀነጨቡ ምን ያህል ብቃት የለለው እንደነበርና እሱን መጀመሪያውኑ ስልጣን ላይ ማስቀመጥ ስህተት እንደነበር የሚዘረዝርና ባንጻሩ መለስ ዜናዊ ካደረጋቸው ንግግሮች ተመርጠው እንደሚካተቱና ምን ያህል ብልህና ባለራዕይ መሪ እንደነበር በንጽጽር እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ሰሞኑን ሃይለማርያም ላይ የተደረገው 15 ሰዓት የፈጀና ከላይ እስከታች እንዲተቹት የተደረገው በህወሃት አቀናባሪነት የዚህ እቅድ አካል እንደሆነ የውስጥ አዋቂ ምንጮት ይገልጻሉ፡ ከግምገማው በሗላ አሁንም ስህተቱን ለመቀበልና ለመማር ዝግጁ አደለም የሚሉት ትችቶች ሳጥኑ ላይ የመጨረሻው ምስማር መሆኑን ያመለክታል።

የሚቀጥለው ሳምንት ምርጫ ነው። ከምርጫው የሚጠበቅ ለዉጥ ባይኖርም መድረክ እና ሰማያዊ( የአንድነት ሰዎች በብዛት በምርጫው እንቅስቃሴ ለማድረግ ስለገቡ) በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ዉስጥም ሆነ ሕዝቡን ለማንቀሳቀስ ጥረት እያደረጉ ነው። በተለይም መድረክ በኦሮሚያና በትግራይ ብዙ ድጋፍ እያገኘ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።

መድረክን እና ሰማያዊ ወክለው ለፓርላማ ከሚወዳደሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል እኝህ አባት ይገኙበታል። በሞያቸው ጠበቃ ናቸው። የመልካም ሴት ባላቤትና የተባረኩ ልጆች አባት ናቸው። ከእኝህ አባት ሴት ልጆች መካከል አንዷ አስተማሪ ሆና ነበር። ከደሞዟ ብዙ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ትረዳና ትደግፍ ነበር። እንደ ዜጋ ሕግ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ጻፈች፣ አስተያየቷን ሰጠች።
እነርሱ መስማትና ማንበብ ከሚፈለጉት ዉጭ እንዲጻፍና እንዲነገር የማይፈልጉት ገዢዎች፣ የአስተሳሰብ ድሆች በመሆናቸው፣ ብእሯን መመከት አልቻሉም። ወደ ጡንቻ ሄዱ። አሰሯት። በዉሸት ክስ ሽብርተኛ ናት ብለው ከሰሷት። ጠበቃ አባቷ ተከራከሩ። ሆኖም ፍርድ ቤቶች የፍትህ አካላት ሳይሆን የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆናቸው፣ ፍትህ ሊገኝ አልቻለም። ይች ወጣት ለአመታት በቃሊቲ ትሰቃያለች። ይች ወጣት ርዮት አለሙ ትባላለች። በዘመናችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬና ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ !!!!

ጠበቃ አባቷ፣ ምን ያህል የሕግ ስርዓት እንደሌለ በመረዳታቸው፣ ፍትህ ከፍርድ ቤት እንደማይገኝ በማወቃቸው ለዚህ ደግሞ በዋናነት ምክንያቱ የተበላሻዉና የበሰበሰው የፖለትካ ስርዓቱ በመሆኑ፣ ይሄንን ስርዓት ለመለወጥ በቀድሞ ወረዳ አራት የመድረክ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።እኝህ አባት ጠበቃ አለሙ ጎቤቦ ይባላሉ።

ትግል የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል። ጠበቃ አለሙ በጥብቅና ሞያቸው ቀጥለው፣ ፍትህ ቢጓደልም “ ምን አገባኝ” ብለው መቀመጥ ይችሉ ነበር። ሆኖም ከራስ አልፎ ለሌላ መቆም ትልቅነት ስለሆነ፣ እኝህን አባትም ትልቅ አባት ስለሆኑ፣ ዝምታን አልመረጡም። ፖለቲካዉን ተቀላቅለው አምባገነንነትን ለመታገል ተነሱ።

የርዮት አለሙን አባት፣ የኛም የነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ አባት የሆኑትን፣ አቶ አለሙን እንምረጥ !!!!! አገዛዙ ከአምስት አመታት በፊት እንዳደረጉት ድምጽ እንዳይሰርቁም፣ ድምጹ እስኪቆጠር ድረስ፣ ሕዝቡ በየምርጫ ጣቢያ ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ራሱ ማስቆጠር አለበት። 3፣ 4 አጋዚ፣ ፌዴራልና ካድሬ ፣ ሺሆችን አስፈራርተው የሕዝብ ድምጽ እንዲሰርቁ ሊፈቅድላቸው አይገባም።

Minilik Salsawi – በየቦታው ትንንሽ ጦርነት የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ የኛ ቅስቀሳ በተሳካ ቁጥር የእነሱ ብስጭት ይግል ነበር፡፡ ካድሬው ለሆዱ፣ መንግስት ለስልጣኑ በሚገባ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይሄ አመላካች ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ካድሬው ሽጉጥ ታጥቆ፣ ጠመንጃ ይዞ እገባለሁ አትገባም የሚል ግብግብ እስከመፈጠር ደርሷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መኪናዎቻችን እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገው ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ሳይቀሩ ተደብድበዋል፡፡ በአባላቶቻችን ላይ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በዘንድሮ ምርጫም ኦሮምያ ላይ እናሸንፋለን ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በኦሮሚያ ብዙ አካባቢዎች ሰፋፊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደናል፡፡ ባኮ፣ አምቦ፣ ጀልዱ፣ ጊንጪ የመሳሰሉት አካባቢዎች እኔ የተገኘሁባቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ በየስብሰባው ከ60ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ ነው ድጋፉን ሲገልፅልን የነበረው፡፡ በተለይ የወጣቱ ድጋፍ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ “ከዚህ በኋላ የፀረ-ዲሞክራሲ አገዛዝ ይብቃን” የሚሉ ህብረ ዝማሬዎችን እያሰማ ነው ህዝቡ በየስብሰባው ላይ ሲታደም የነበረው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲታዩ ቅስቀሳው ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ኦህዴድ፣ በዚህ መልኩ ወጣቱ ለኛ ድጋፍ ይሰጣል ብሎ የገመተ አይመስለንም። አሁን ታዲያ የድንጋጤ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሃረርጌ፣ በባሌ እና በሸዋ አካባቢዎች አባሎቻችንን ማሰር፣ መደብደብና ማዋከብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቅስቀሳ መኪናዎቻችንን መስተዋቶች በድንጋይ የመስበር፣ መኪኖችን በቡና ቤቶች አካባቢ ማሳደር እንዳንችል የማድረግ ሁኔታዎች በስፋት ተስተውለዋል፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆነ አቀባበል ከህዝቡ አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በምርጫው እንወዳደራለን፡፡ በሁሉም ላይ ቦታ ሰፊ አቀባበል ያገኘን ቢሆንም በተለይ ኦሮሚያ ላይ ኢህአዴግ ምርጫውን ካላጭበረበረ በቀር የሚያሸንፍበት መንገድ የለውም፡፡ እኛ ሁለት ነገር ነው የምንጠብቀው፡፡ አንደኛ ኢህአዴግ ካላጭበረበረ በቀር ኦሮሚያ ላይ አያሸንፈንም፣ ሁለተኛ ደግሞ ፖለቲካውን በሚገባ እንዳሸነፍን አሳይተናል፡፡ ሰፊ ድጋፍ እንዳለን አስመስክረናል፡፡ በየትኛውም ሚዛን ከኦህዴድ እንደምንሻል አሳይተናል፡፡ በዚህ ተደናግጠው እኔ በምወዳደርበት አካባቢ ኦህዴዶች ህዝቡን በሬ አርደው ማብላት ሁሉ ጀምረዋል፡፡ የክልሉ ካድሬዎች አሁን አምቦ ከትመዋል፡፡ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡ ኦህዴድና ህዝቡ ከተለያየ ቆይቷል፡፡ ያው በኢህአዴግ ጃንጥላና ጠመንጃ ስር ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ እነሱም እንደማያሸንፉ ያውቃሉ። እኛ በ97 እኮ አሳይተናቸዋል፡፡ በወቅቱ እነ አባዱላን ያሸነፉት እኮ የ6ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ኦህዴድ በኦሮሚያ ሊሸነፍ እንደሚችል በ97 ምርጫ ነው ያረጋገጥነው፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

“መድረክ” አብላጫ ድምፅ ካገኘ ጥምር መንግስት ይመሰርታል:: እኛ በፕሮግራማችን ላይ በግልፅ አስቀምጠናል። በሽግግሩ ጊዜ ጥምር መንግስት ያስፈልጋል ብለናል። ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድና ለመሳሰሉት ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች መልክ ማስያዣ ይሆን ዘንድ የብሄራዊ አንድነት መንግስት ያስፈልጋል፡፡ ከማን ጋር ይመስረት የሚለው በድርድር የሚከናወን ይሆናል፤ ነገር ግን አግላይ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም፡፡አንድ ፓርቲ ሌላውን አግልሎ ኢትዮጵያን መንግስተ ሰማያት ያደርሳል የሚሉ ካሉ ወይ የፖለቲካ ሳይንስ ያልገባቸው ወይም እስከቻልን ድረስ በፈላጭ ቆራጭነት ረግጠን እንግዛ የሚሉ ናቸው፡፡ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ለማምጣት መታለፍ ያለበት አንዱ ሂደት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ማቋቋም ነው። ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በአጭሩ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብበት የምመክረው ምርጫውን እንዳያጭበረብር ነው፤ ውጤቱ የፈለገ ይሁን፡፡ ምርጫን አጭበርብሮ አሸንፌያለሁ የማለት ጊዜ ማብቃቱን ማወቅ አለበት። ያንን ካላደረገ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ለበለጠ ተስፋ መቁረጥ ነው የሚዳርገው፤ ይሄ በተግባር እየታየ ነው። ወጣቱ ከቀይ ባህር እስከ ሜዲትራኒያን ድረስ የባህር ሲሳይ የሚሆነውና በረሃ ውስጥ እንደዚያ የሚታረደው፣ ደቡብ አፍሪካ እንደዚያ የሚቃጠለው በሃገሩ ተስፋ ስላጣ ነው፡፡ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንኳ “የስደት ዘመን ይብቃ” ብሎ ከፖሊስ ጋር እንዴት እንደተጋጨ ተመልክተናል፡፡ አጥፍቶ የመጥፋት ፖለቲካ ይብቃ! የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደጋግመው ያስቡበት። ህዝቡንም ወጣቱንም ተስፋ ማስቆረጥ ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተለይ ወጣቱ በሃገሬ የተሻለ ሥራ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ሊያድርበት ይገባል፡፡ ይሄንን ወጣት ተስፋ ማስቆረጥ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡ – addisadmassnews.com

Image

ከየመን የተመለሱ ስደተኛ ኢትዮጲያውያን ከቦሌ አየር ማረፊያ ተይዘው በመአከላዊ እስር ቤት ታስረዋል በየመን በቀተስተው ግጭት የተነሳ ከየመን ወደ ስአውዲ ሊሻገሩ ሲሞክሩ በስአውዲ ፖሊስ ለቀናት ከታስሩ በህዋላ አምስት የሚሆኑ ኢትዮጲያውያን ከ4 ቀናት በፊት ወደ አዲስ አበባ ቢመለሱም በቦሌ አየረ ማረፊያ በፖሊሶች ተይዘው ወደ መአከላዊ ውስር ቤት መወስዳችውን የBBN ምንጮች አረጋግጠዋል ። እስረኞቹን ቤተስቦች እስረኞቹን ለማግኘት ያደረጉት […]

  የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የነበረው አቶ አለነ ማህፀንቱ በትናንትና ዕለት ያለፍርድ ቤት ማዘዣ በደህንነት ኃይሎች ታፍኖ የተወሰደ ሲሆን፤ በኃይልና በድብደባ የኢሜል አድራሻውንና ፓስዎርድን ከወሰዱ በኋላ ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ አምጥተው እንዲታሰር አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የአንድነት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ በላይ ፍቃዱ እና ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ተክሌ በቀለ በተመሳሳይ ዕለት በደህንነት ኃይሎች ሲዋከቡ የዋሉ ሲሆን ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ […]

የግድብና የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ውል ፈጽሞ እያከናወናቸው ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ለሚመራው የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈለት፡፡ 

ለሥራ አመራር ቦርዱ የማሳሰቢያው ደብዳቤ የተጻፈው የርብ የመገጭና  የጊዳቦ ግድቦች፣ የከሰም መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታና የተንዳሆ የኅብረተሰብና የስኳር ልማትና መጠጥ ውኃ ግንባታን ለማከናወን ውል የገባው የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ፕሮጀክቶቹን በማጓተቱና አፈጻጸሙ ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ነው ለቦርድ ማስጠንቀቂያ የተጻፈው፡፡

በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ተክሌ ሚያዝያ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተጻፈው ደብዳቤ ውኃ ሥራዎች ድርጅት ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በገባው ውል መሠረት በአማራ ክልል የሚገኙትን የርብና የመገጭ ግድቦች ግንባታን፣ በኦሮሚያ ክልል የጊደቦ ግድብ ግንባታን፣ በአፋር ብሔራዊ ክልል የከሰም መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታና የተንዳሆ የኅብረተሰብና የስኳር ልማትና የመጠጥ ውኃ ግንባታ ለማካሄድ ኮንትራት የወሰደ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሊጠናቅቁ አለመቻላቸው ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ ሚኒስቴሩ በተደጋጋሚ የቀረቡለትን የማራዘሚያ ጥያቄዎችም በመቀበል የውል ጊዜን ያራዘመ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ፕሮጀክቶች ወደ ኪሳራ ሊገቡ መገደዳቸውንም ያክላል፡፡

የርብ ግድብ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2007 ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2011 የሚጠናቀቅ ቢሆንም፣ በተያዘው ዓመት እ.ኤ.አ. 2015 አፈጻጸሙ 76.5 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ. ከግንቦት 2011 እስከ ሰኔ 2014 ድረስ እንዲራዘም መደረጉን ለውኃ ሥራዎች ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የተላከው የማሳሰቢያ ደብዳቤ ይገልጻል፡፡ የመገጭ ግድብ ግንባታም እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ መጠናቀቅ ያለበት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 30 ቀን 2016 ነው፡፡ በዚህ ዓመት ያለው የአፈጻጸም መጠን ግን 26.05 በመቶ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የጊዳቦ ግንባታ ግንባታ የተጀመረው ጥር 3 ቀን 2002 ዓ.ም. ሲሆን፣ ይጠናቀቃል የተባለው ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን አራት ጊዜ ውሉ እንዲሻሻል ተደርጎ አሁን ያለበት አፈጻጸም 63.86 ብቻ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በሌሎቹም ፕሮጀክቶች የሚታየው አፈጻጸም ተመሳሳይ መሆኑን የሚያብራራው የሚኒስቴሩ ደብዳቤ፣ ባለድርሻ አካላቱ ማለትም ሚኒስቴሩ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅትና አማካሪው የውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ተመካክረው ቦርዱ እንዲያውቀው ያደረጉ ቢሆንም ሊሻሻል አለመቻሉን ያብራራል፡፡

ሦስቱ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ምክክር ድርጅቱ አጠቃላይ ያለበትን ሁኔታ ቦርዱ እንዲያውቀው ተደርጎ ለማበረታታት መሞከሩን፣ ድርጅቱ ያጋጠመውን የፋይናንስ ችግር በመረዳት ከክፍያ ተመላሽ የሚደረግ 250 ሚሊዮን ብር በብድር መልክ እንዲሰጠው መደረጉን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡

ከመንግሥት ጋርም በመነጋገር ለርብና ለመገጭ ግድቦች ግንባታ ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን፣ እንዲሁም መንግሥት የድርጅቱ ካፒታል እንዲያድግ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተወሰነ ክፍያ መፈጸሙንም ደብዳቤው ያብራራል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተገለጹት ድጋፎች የተደረጉለት ቢሆንም የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ሊሻሻል አለመቻሉንም ጠቁሟል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ከማሳየት ይልቅ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ገልጾ፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ችግሮቹን በመፈተሽ በቀሪው ጊዜ አፈጻጸሙ የሚሻሻልበትን  የበኩሉን ሚና እንዲጫወት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደብዳቤው አሳስቧል፡፡

የሥራ አመራር ቦርዱ ከሚኒስቴሩ በደረሰው ማሳሰቢያ መሠረት ምን እያደረገ እንደሚገኝ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

 

 

አስተዳደሩ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ዋጋ የሚያጠና ልዩ ኮሚቴ ማቋቋሙ ተሰማ

ጭማሪው በካሬ ሜትር ከ27 እስከ 45 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል

‹‹አስተዳደሩ ያደረገው ጭማሪ 15 በመቶ ብቻ ነው›› የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለአሥረኛ ጊዜ ዕጣ ያወጣባቸው 41 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ሰባት ሺሕ ለልማት ተነሽዎች ናቸው)፣ በዋጋቸው ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን ካቢኔው ሊቀበለው ባለመቻሉ፣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዋጋ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡

 

የተወሰኑ የካቢኔ አባላት ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ስብሰባ አድርገው በኮንዶሚኒየሙ ወጪ ላይ መግባባት ባለመደረሱ፣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዋጋ ጥናት እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቀደም ብሎ ተቋቁሞ የነበረው ኮሚቴ ስለ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ያጠናው ጥናት ከመጠን በላይ የተጋነነ በመሆኑ፣ ከሁሉም ዘርፍ የተወጣጣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዋጋው እንደገና መጠናት እንዳለበት ውሳኔ ላይ መደረሱን ምንጮች አስረድተዋል፡፡  አዲስ የተቋቋመው ኮሚቴ የመጀመርያ ስብሰባውን ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ማድረጉንም አክለዋል፡፡

የከተማ አስተዳሩ ለቤቶች ልማት ፕሮግራም ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መበደሩን የሚያስታውሱት ምንጮቹ፣ ለቤቶች ግንባታ የወጣው ወጪና በባንክ ያለው ገንዘብ ሊጣጣም ባለመቻሉ ሁለቱን አጣጥሞ ለመቀጠል በቤቶቹ ላይ ዋጋ መጨመር እንዳለበት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ እምነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የተወሰኑ ሠራተኞች የአሥረኛው ዙር ዕድል ተጋሪ በመሆናቸው፣ ጽሕፈት ቤቱ ሥራውን እንዴት እየሠራና ምን ዓይነት ወጪ ለምንና እንዴት እየወጣ እንደሚገኝ በቅርበት ስለሚያውቁ፣ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን  ያቀረቡ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

በቤቶቹ ላይ መደመር የሌለባቸው የተለያዩ ወጪዎች በብክነት ወይም በሌላ ወጪ መመዝገብ ሲገባቸው በቤቶቹ ላይ በመደመራቸው፣ ለግንባታና ለዲዛይን ወጪ ተገምቶ ሥራውን ለምርምር ብድር የተወሰደ ቢሆንም፣ ከባንክ ጋር የተገባውን ብድር ማፋለሱን ገልጸዋል፡፡ ካቢኔውም በተሠራው የግንባታና የዲዛይን ዋጋ መሠረት ጽሕፈት ቤቱ መሥራት ሲገባው፣ የተጋነነ ዋጋ መቅረቡ ትክክል አለመሆኑን መግለጹን  ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ የጽፈሕት ቤቱም ሠራተኞች ወጪው ለብቻ መያዝ እንዳለበት በመግለጽ የካቢኔውን አቋም እየደገፉ መሆኑም  ተጠቁሟል፡፡ 

የካይዘን ኢንስቲትዩት ባደረገው ጥናት መሠረት በቤቶች ግንባታ ላይ 33 በመቶ ብክነት መኖሩን ለካቢኔው ማሳወቁን የገለጹት ምንጮች፣ ብክነቱን በተለያዩ ነገሮች ማወራረድ ሲቻል በቤቶቹ ዋጋ ላይ መደመር አግባብ አለመሆኑን ካቢኔውም ሆነ የዕጣው ዕድለኞች የሚስማሙበት ሐሳብ መሆኑንም ምንጮች አስረድተዋል፡፡

የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ማንኛውም ዓይነት ክትትልና ጥንቃቄ ቢደረግበት እንኳ እጅግ በጣም አስቸጋሪና ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን፣ የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የከተማ ልማትን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ክርክር ላይ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ቢሮ ኃላፊ በሚያዝያ ወር የመጀመርያ ሳምንት አካባቢ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአሥረኛው ዙር ዕጣ በወጣባቸው ቤቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ እንደሚባለው የተጋነነ ሳይሆን፣ 15 በመቶ ብቻ እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ የነባር 20/80 ባለ አንድ፣ ሁለትና ሦስት መኝታ ቤቶችና እንዲሁም የስቱዲዮ ቤቶችን ለመሸጥ ካስቀመጠው ዋጋ ላይ ከ27 እስከ 45 በመቶ ጭማሪ ማድረጉን የዋጋውን ልዩነት ያሰሉ ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡

የ10/90 ተመዝጋቢዎች ዝቅተኛ ክፍያ በካሬ ሜትር 1,310 ብር የሚከፍሉ መሆኑን በምዝገባ ወቅት የተነገረ ቢሆንም፣ በአሥረኛው ዙር ግን በካሬ ሜትር 1,910 ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡ ልዩነቱ 600 ብር ወይም 45 በመቶ መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ዝቅተኛው የስቱዲዮ ስፋት 29 ካሬ ሜትር ነበር፡፡ 

በተመሳሳይ ሁኔታ ነባር የ20/80 ባለሁለት መኝታ ቤት ተመዝጋቢ በካሬ ሜትር የሚከፍለው 3,452 ብር የነበረ ቢሆንም፣ በአሥረኛው ዙር ዕድለኛ የሆነ ግን በካሬ ሜትር 4,394 ብር ይከፍላል፡፡ ሲመዘገብ ከሚያውቀው ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት 942 ብር ወይም 27 በመቶ መሆኑን ነዋሪዎቹ አሥልተዋል፡፡ ዝቅተኛው ባለሁለት መኝታ ቤት ስፋቱ 65 ካሬ ሜትር ነው፡፡ 

በመሆኑም የዕጣው ባለቤቶች መንግሥት መሬት በነፃ፣ ሁሉንም የግንባታ ግብዓቶች ከአገር ውስጥ ባደረገበት ጊዜ ዋጋው ይኼንን ያህል ሊጋነን እንደማይገባ እየገለጹ ባሉበት ወቅት፣ አስተዳደሩ ዋጋው በልዩ ኮሚቴ እንዲጠና ማድረጉ ተገቢና ዕድለኞቹንም ያሰበ ሊሆን ይችላል በሚል ተስፋ ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ነዋሪዎች የሠሩት ሥሌት ትክክል መሆን አለመሆኑንና አዲስ ስለተቋቋመው ኮሚቴም ማብራሪያ እንዲሰጡ የአስተዳደሩት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችንና የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

 

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የብረት ማዕድን ማውጫና ማቅለጫ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡ ፋብሪካው የሚገነባው በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ ሲሆን፣ የብረት ክምችቱም በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢቅላል አካባቢ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ለዚህ ግዙፍና ለአገሪቱ የመጀመርያ ለሆነው ፋብሪካና የብረት ማዕድን ማውጪያ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ፣ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. የፋብሪካው የመሠረት ድንጋይ በነቀምት ከተማ በተቀመጠበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁሩንዴ እንደተናገሩት፣ የሚገነባው የብረታ ብረት ፋብሪካ በዓመት ከሦስት መቶ ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የተለያዩ ብረቶችን ማምረት ያስችላል፡፡

በቀድሞው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለቤትነት በኢትዮጵያ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ያስችላሉ የተባሉትን የድንጋይ ከሰልና የብረት ማዕድን መገኛ ለማወቅ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ በሚኒስቴሩ በተቋቋመው ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና የቻይና ኩባንያዎች በተሳተፉበት ጥናት፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉአባቦራ ዞን ያዩ አካባቢ ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል መኖሩን፣ በዚሁ ቀጣና ውስጥ ምዕራብ ወለጋ ቢቅላል አካባቢ ደግሞ የብረት ማዕድን ክምችት (አይረን ኦር) ከሌሎች ማዕድናት ጋር መኖሩን አመልክቷል፡፡

በወቅቱ እነዚህን ማዕድናት ማውጣትና ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ለማቋቋም የሚፈለገው ካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ሳይሞከር እንደቀረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ነገር ግን ከመከላከያ ተገንጥሎ በኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለውጥ እንዲያመጣ የተቋቋመው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ በሒደት በሁለቱም ዘርፎች በጥልቀት መግባት ችሏል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት ያዩ አካባቢ የሚገኘውን የድንጋይ ከሰል በማውጣት ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ደግሞ የብረት ማዕድን አውጥቶ የሚያቀልጥበት ፋብሪካ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ግዙፍ ኩባንያ የሆነው ስቲሊ አርኤምአይ  የኦፕሬሽንና የፖሊሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ለማ የፋብሪካውን መገንባት አስመልክተው ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ከውጭ ይገባ የነበረው ቢሌት (ጥቅል ፌሮ ብረት) አገር ውስጥ ማምረት መቻል ትልቅ ትርጉም አለው፡፡

አቶ ተፈራ ጨምረው እንደገለጹት፣ አገር ውስጥ ሲመረት የቆየው ብረት ከወዳደቁ ብረታ ብረት (ስክራፕ) እና ከውጭ በሚገባ ቢሌት ነው፡፡ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወደዚህ ዘርፍ ከገባ ዩክሬን፣ ቻይናና አውስትራሊያ የሚታወቁበት የብረት ምርት በኢትዮጵያ እንዲመረት ያስችላል፡፡

‹‹ይህ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ነው፤›› በማለት አቶ ተፈራ የፕሮጀክቱን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ይኼን አዲስ ፕሮጀክት በሁለተኛው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ያካተተ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

የፕሮጀክቱ ዕውን መሆን ለምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ከመፍጠሩም ባሻገር፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡ 

 

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር በሲሚንቶ ገበያ ውስጥ ችግር ፈጥሯል

የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በገበያ ውስጥ ለተከሰተው የሲሚንቶ እጥረት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ታወቀ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሦስተኛውን መስመር ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ ደርባ ሚድሮክ

ሲሚንቶ ፋብሪካን ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረቱ የማምረት አቅሙን እንዳይጠቀም እንዳደረገበት ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅም ማምረት ባለመቻላቸው፣ የሲሚንቶ አቅርቦት ጫና በዋነኛነት መሰቦና ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ላይ ማረፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከሳምንታት በፊት በዓመት 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማምረት የሚያስችለው መስመር ቁጥር ሦስት መቆጣጠርያ መሣሪያ ተቃጥሎበታል፡፡ ይኼንን መሣሪያ ከውጭ ለማስገባት ልዩ ፈቃድ የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ በአፋጣኝ ማስገባትና ፋብሪካውን ሥራ ማስጀመር አልተቻለም ተብሏል፡፡

የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሦስተኛውን መስመር ከጥቅሙ ውጪ ቢያደርገውም፣ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሙገር የሚፈልገው መሣሪያ አገር ውስጥ የሚገባ በመሆኑ የፋብሪካው ቁጥር ሦስት መስመር ሥራ ይጀምራል፡፡

ደርባ ሚድሮክ ደግሞ የገጠመው ችግር የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ነው፡፡ የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ በመሉ አቅሙ ለማምረት 45 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው እያገኘ ያለው ከስድስት ሜጋ ዋት አይበልጥም ብለዋል፡፡

‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረቱ በሙሉ አቅማችን ሥራ እንዳንሠራ አድርጎናል፤›› በማለት አቶ ኃይሌ የችግሩን ክብደት ይናገራሉ፡፡

የእነዚህ ሁለት ፋብሪካዎች ችግር ውስጥ መግባት የሲሚንቶ ገበያውን ችግር ውስጥ ከቶታል፡፡ በእርግጥ በሥራ ላይ ያሉት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የመሸጫ ዋጋቸው ላይ ጭማሪ ባያደርጉም ነጋዴዎች ግን በመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርገዋል፡፡

መሰቦ ሲሚንቶ ሦስት ዓይነት ሲሚንቶዎች ለገበያ ያቀርባል፡፡ የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋውም በኩንታል 250 ብር፣ 190 ብርና 165 ብር ነው፡፡ ነገር ግን በገበያ ውስጥ የመሰቦ ሲሚንቶ አንድ ኩንታል ከ350 ብር በላይ እየተሸጠ ነው፡፡

በሲሚንቶ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንደሚሉት፣ ማንኛውም ሰው ከፋብሪካው የፈለገውን መጠን ሲሚንቶ መግዛት ይችላል፡፡ በተለይ ደላሎች ክፍያ ተፈጽሞ ሲሚንቶውን ለማግኘት እስከ ሦስት ወራት የሚወስድ በመሆኑ ወረፋቸውን በመሸጥ ብቻ ከአንድ ኩንታል እስከ አንድ መቶ ብር እያተረፉ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ፕሮጀክት ላለውና ንግድ ፈቃድ ላለው ቅድሚያ የሚሰጥ ባለመሆኑ የሲሚንቶ ገበያው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሲሚንቶ ዋጋ በኩንታል ከ350 ብር እስከ 410 ብር ድረስ እየናረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመሰቦ ሲሚንቶ ፕሮሞሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ሐጎስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሙገርና በደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ችግር የገበያው ጫና ወደ መሰቦ ዞሯል፡፡ መሰቦ ይህ ነው የሚባል ችግር የገጠመው ባለመሆኑ ከሰባት ሺሕ እስከ ስምንት ሺሕ ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ በቀን ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት አቅም፣ ካለው ፍላጎት ከአምስት ሚሊዮን ቶን በላይ ትርፍ መሆኑ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ፋብሪካዎቹ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የማምረት አቅማቸውን ሙሉ በመሉ መጠቀም ባለመቻላቸው ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በሲሚንቶ ዘርፍ ያለውን ችግር ለመፍታት ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በዋንኛነት በዘርፉ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግርን ለመፍታት የተመከረ ሲሆን፣ በተለይ የደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካን ችግር ለመፍታት በገፈርሳ ኃይል ማመንጫ የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ በመሆናቸው፣ በአጭር ጊዜ ችግሩ እንደሚፈታ መግባባት ላይ ተደርሷል ሲሉ አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

ከወራት በፊት በአገሪቱ ለተከሰተው የሲሚንቶ ገበያ ችግር የትራንስፖርት እጥረት በምክንያትነት ይቀርብ ነበር፡፡ ይኼም የሆነበት ትራንስፖርት ባለሥልጣን በአገሪቱ የሚገኙ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በጂቡቲ ወደብ የተራገፉ መሠረታዊ ሸቀጦችን እንዲያነሱ በግዳጅ በማሰማራቱ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት ችግሩ የተቃለለ ቢሆንም፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡

 

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚካሄደው አምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለማሸነፍ ተስፋ የሚያደርጉባቸውን አካባቢዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ 

በዚህም መሠረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተለያዩ ሥፍራዎችን ለማሸነፍ ተስፋ እንዳደረጉባቸው የገለጹ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ግን በሁሉም ሥፍራዎች ለማሸነፍ እንደሠራ አስታውቋል፡፡ 

የኢሕአዴግ የሕዝብና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋው፣ ‹‹በሁሉም የምርጫ ክልሎች እናሸንፋለን በሚል ነው እየሠራን ያለነው፡፡ ምርጫ ውድድር ነው፡፡ ውጤቱ የሚታወቀውም በመጨረሻ ሕዝቡ በሚሰጠው ውሳኔ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ሕዝቡ ገና ድምፁን ሳይሰጥ እዚህ አሸንፋለሁ እዚህ ደግሞ እሸነፋለሁ ማለት ትክክል አይደለም በማለት፣ ትንበያ ከምርጫ ሥነ ምግባር መርሆዎች ጋር የሚጣጣም አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 

በዚህ ሐሳብ የሚስማሙት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ፣ ‹‹ጠንካራ ቦታዎች የሚባሉትን የሚወስነው ሕዝቡ ነው፡፡ እዚህ ላይ ነው ብለን ለማለት ያስቸግረናል፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ከክልል ከተሞች ይልቅ በአዲስ አበባ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡ 

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የምርምር ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ ፓርቲያቸው በሦስት የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ 

በዚህም መሠረት የፓርቲው ፕሬዚዳንት የሚወዳደሩበት የዘንዘልማና የጢስ ዓባይ የምርጫ ክልል፣ ደብረ ማርቆስና ወላይታ ፓርቲው ለማሸነፍ ተስፋ የሚያደርግባቸው ሥፍራዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ 

አዲስ አበባ በፓርቲው ከፍተኛ የቅስቀሳ ሥራ የሚሠራበት እንደሆነ የገለጹት አቶ ዋሲሁን ‹‹ነገር ግን በከተማው 11 ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ገዢው ፓርቲ በመኖራቸው ድምፅ የመከፋፈል ዕድሉ ከፍተኛ ነው፤›› በማለት በክልል ከተሞች ያተኮሩበትን ምክንያት አብራርተዋል፡፡ 

አዲስ አበባ ላይ በእርግጠኝነት እንደሚያሸንፉ የገለጹት ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ሲሆኑ፣ በክልልም እንዲሁ ፓርቲው ተስፋ የሚያደርጋቸውን ከተሞች አስታውቀዋል፡፡ 

በዚህም መሠረት ጅማ፣ ኢሉአባቦርና የባሌ አካባቢዎች ከኦሮሚያ፣ ኮንሶና ሆሳዕና ደግሞ ከደቡብ ክልል ለማሸነፍ ተስፋ የሚያደርጉባቸው ናቸው፡፡ ከአማራ ክልል ደግሞ ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴና ወልድያ ፓርቲው ጠንካራ እምነት አግኝቼባቸዋለሁ የሚላቸው ከተሞች ናቸው፡፡ 

‹‹ደቡብ ውስጥ በሁሉም ቦታዎች ለማሸነፍ እየሠራን የነበረ ቢሆንም፣ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማድረግ ባለመቻላችን ዕቅዳችን ሊያንስ ችሏል፤›› በማለት በደቡብ ተስፋ ያደረጉትና አሁን የሚጠብቁት የተለያዩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ 

በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ የደቡብና የትግራይ ክልሎች የማሸነፍ ተስፋ እንዳለባቸው የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችው መቐለ፣ እንዲሁም ከደቡብ ከንባታና ሀድያ አካባቢዎች፣ ጋሞ ጐፋ፣ እንዲሁም ቡርጂ ዞን ውጤት የሚጠብቅባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ 

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ፕሬዚዳንት አቶ ትዕግሥቱ አወሉ በበኩላቸው፣ በተወሰኑ የአዲስ አበባ የምርጫ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ሐዋሳና ዳውሮ፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችና ጅማ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች ተስፋ አለን ብለዋል፡፡

 

ሐና ላላንጐን አስገድዶ በመድፈር ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል የተባሉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠው በልዩነት ነው 

በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. የ16 ዓመት ታዳጊ መሆኗ የተገለጸውን ሐና ላላንጐ፣ በታክሲ አፍነው ወደ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቀራኒዮ አካባቢ በመውሰድ፣ ተፈራርቀው በመድፈር ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል በሚል ክስ

የተመሠረተባቸው አምስት ወጣቶች፣ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ ተባሉ፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔው የተሰጠው በልዩነት ነው፡፡

ተከሳሾቹ ሳምሶን ስለሺ፣ በዛብህ ገብረ ማርያም፣ በቃሉ ገብረ መድኅን፣ ኤፍሬም አየለና ተመስገን ዘገዬ የተባሉ ከ19 እስከ 31 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ሲሆኑ፣ የታክሲ ሾፌርና ረዳት መሆናቸው በክሱ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግ 32(1ሀ) ማለትም በዋና ወንጀል ተካፋይነት፣ የወንጀል ሕግ 539(1ሀ)ን ማለትም ከባድ የሰው ግድያና የወንጀል ሕግ 626 (1)ን፣ ማለትም ዕድሜያቸው 13 በሆነና 18 ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን በሚመለከት የተደነገገውን አዋጅ መተላለፋቸውን ጠቅሶ ክስ መሥርቶ ነበር፡፡ 

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት (የክስ ሒደቱ የተካሄደው በዝግ ችሎት ነው)፣ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ሁሉንም ተከሳሾች በልዩነት ጥፋተኛ ብሎ ለቅጣት፣ አስተያየትና የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የተለዩት ዳኛ ከአንድ እስከ ሦስት ያሉት ተከሳሾች ላይ ከሌሎቹ ዳኞች ጋር ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው ቢሆኑም፣ በአብላጫ የወንጀል ሕግ አንቀጾችን በልዩነት ያስቀመጡት፣ ተከሳሾቹ ማለትም ከአንድ እስከ ሦስት ያሉት ተከሳሾች ላይ የወንጀል ሕግ 539 (1ሀ) [ያገዳደል ሁኔታው ክብደት] እና የወንጀል ሕግ 620(3) [የአስገድዶ መድፈሩ ክብደት] ተገቢ ሆኖ ሳለ፣ በወንጀል ሕግ 620 (2መ) [ጭካኔና ስቃይ መፍጠር] ጥፋተኛ መባል የለባቸውም በሚል ነው፡፡ በአብላጫ ድምፅ በተደራቢነት የተጠቀሰውን የወንጀል ሕግ 620(4)ን [ጠለፋ] የተለዩትም ዳኛ ደግፈው፣ ነገር ግን ይኼ አንቀጽ ወደ ወንጀል ሕግ 585(1) [ከሕግ ውጭ ይዞ መቀመጥ] ስለሚወስድ በእሱ መሠረት ከአንድ እስከ ሦስተኛ ያሉት ተከሳሾች ጥፋተኛ ሊባሉ እንደሚገባ በመግለጽ ተለይተዋል፡፡ 4ኛና 5ኛ ተከሳሾች ግን በዓቃቤ ሕግ ስላልተመሰከረባቸው በነፃ ሊሰናበቱ እንደሚገባ ገልጸው ተለይተዋል፡፡

 

 

የሆላንድ ካር ባለቤት ኩባንያቸውን ለመታደግ ወደ አገር ቤት ተመለሱ

የኩባንያው ንብረት እንዳይሸጥ በድጋሚ ታገደ

በሆላንድ ካር የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያ በተፈጠረ ቀውስ ከሦስት ዓመት በፊት ኪሳራ በማሳወጅ አገር ጥለው የተሰደዱት ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ፣ ኩባንያቸውን ለመታደግ ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ 

ኢንጂነር ታደሰ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ኩባንያውን ለመታደግ የሚያስችል ዕቅድ ነድፈውና ለመንግሥት አቅርበው ተቀባይነት በማግኘታቸው የሕግ ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ከ200 በላይ የሚሆኑ ደንበኞች መኪና ለመግዛት ለሆላንድ ካር ክፍያ ፈጽመው ኩባንያው መኪኖቻቸውን ለማስረከብ ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል፡፡ ለኩባንያው ብድር የሰጠው ዘመን ባንክ በመያዣነት የያዛቸውን የኩባንያውን ንብረቶች ለመሸጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ መኪኖቻቸውን ያልተረከቡት ደንበኞችም በፍርድ ቤት ሲሟገቱ ቆይተዋል፡፡ 

በሆላንድ ካር መክሰር ምክንያት የኩባንያው ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ታደሰ በ2004 ዓ.ም. ወደ ኔዘርላንድ ተሰደዋል፡፡ ኩባንያው በየካቲት 2005 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መክሰሩ በይፋ ታውጇል፡፡ 

አቶ ታደሰ ኩባንያቸው ወደ ኪሳራ ሊገባ የቻለው በመሥሪያ ካፒታል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከሦስት ዓመት በፊት አገሬን ለቅቄ ወጥቼ ነበር፡፡ የወጣሁበት ምክንያት ሆላንድ ካር ውስጥ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ሥራ መሥራት ስላልተቻለ ነው፡፡ ለገጠሙን ችግሮች መፍትሔ ማግኘት ስላልቻልኩኝ ምናልባት ለጊዜው ዞር ማለት ይሻላል በማለት ወጥቼ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ 

ከአገር ከወጡ በኋላ የተቋረጠውን የኩባንያውን ሥራ ለማስቀጠል በተለይ መኪና የገዙ ደንበኞች ንብረታቸውን የሚያገኙበት ዘዴ ከመፈለግ ወደኋላ እንዳላሉ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ፕሮፖዛሎች አስገብቻለሁ፤›› ያሉት ኢንጂነር ታደሰ፣ በመጨረሻ ለመንግሥት ያስገቡት ፕሮፖዛል በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ቀርቦ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና በፍትሕ ሚኒስቴር በተደረገላቸው ድጋፍ የሕግ ከለላ ተሰጥቷቸው አገራቸው ገብተው እንዲሠሩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ 

ሆላንድ ካር የከሰረበት ምክንያት ንብረት በማጣት እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ኢንጂነር ታደሰ አበዳሪያቸውን ዘመን ባንክን ወቅሰዋል፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ ባንኩ የኩባንያውን ንብረቶች የመሸጥ አቋም ነበረው፡፡ ያ ቢሆን የአንድ ቡድን ጥቅም ብቻ ነው የሚጠበቀው፡፡ ባንኩ ንብረቶቹን ሽጦ ገንዘቡን ይወስዳል፡፡ የቀሩት ደንበኞች ምንም የሚያገኙት ነገር አይኖርም፡፡ ከባንኩ ጋር ስንነጋገር የነበረው ወደ ሐራጅ ከተገባ ደንበኞች ስለሚጎዱ ወደዚያ አንግባ ብዬ ብዙ ተከራክሬያለሁ፤›› ብለዋል፡፡ 

ዘመን ባንክ በሠራው የፋይናንስ ዕቅድ ኩባንያውን ለመታደግ በወቅቱ ለሦስት ወራት 17 ሚሊዮን ብር ያስፈልግ እንደነበር ጠቁሞ፣ ከሦስት ወራት በኋላ ያለ ዕዳ መንቀሳቀስ ይችላል የሚል ነበር፡፡ ‹‹ነገር ግን ባንኩ ቶሎ ብሎ ወደ ሐራጅ ማውጣት ስለፈለገ ያንን ለመከላከል የምችለው ኪሳራ በማወጅ ብቻ ነው፡፡ ወደ ኪሳራ በማስገባበት ጊዜ ባንኩ እንደ ሌሎች ደንበኞች ተሰልፎ ይጠብቃል፡፡ እኔ ብቻ ሸጬ ልውሰድ የሚለው አይኖርም፡፡ ይህን ደግመን ደጋግመን ተናግረናል፡፡ እዚያ ውስጥ አንግባ በሚል ተነጋግረናል፡፡ እስከ መጨረሻው ቀን ጠብቄ ወደ ኪሳራ እንዲገባ አድርጌያለሁ፤›› ብለዋል፡፡ 

ሪፖርተር ዘመን ባንክን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ያደረገ ቢሆንም፣ ማኔጅመንቱ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ ‹‹አስተያየት የለንም፤›› ብለዋል አንድ የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊ፡፡ 

ሆላንድ ካር የዘመን ባንክ 34 ሚሊዮን ብር ዕዳ አለበት፡፡ ባንኩ የኩባንያውን ንብረቶች በ83 ሚሊዮን ብር የመነሻ ዋጋ ለጨረታ አቅርቧል፡፡ ሞጆ ከተማ የሚገኘው በ20,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ፣ መጋዘንና የቢሮ ሕንፃ 22.3 ሚሊዮን ብር የተገመተ ሲሆን፣ 236 ያልተገጣጠሙና 70 የተገጣጠሙ መኪኖች 51.7 ሚሊዮን ብር ተተምነዋል፡፡ 

ዘመን ባንክ የጨረታ ማስታወቂያውን ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያስነገረ ሲሆን፣ የጨረታ መዝጊያው ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኢንጂነር ታደሰ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. የኩባንያው ንብረቶች እንዳይሸጡ አግዷል፡፡ እንደ ኢንጂነር ታደሰ ገለጻ ኩባንያው ያለበት የባንክ፣ የደንበኞችና የመንግሥት (ግብር) ዕዳ በአጠቃላይ 63 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ የኩባንያው ጠቅላላ ንብረት ግምት 180 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ኢንጂነር ታደሰ በአውሮፓ ቆይታቸው የገንዘብ ምንጭ ሲያፈላልጉ እንደነበር ገልጸው፣ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በቤልጂየም ከኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ተሾመ ቶጋ ጋር ረዥም ጊዜ ሲወያዩ እንደነበር፣ አምባሳደር ተሾመ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ተናግረዋል፡፡ 

አዲስ የነደፉትን ሆላንድ ካርን ካለበት ችግር አውጥቶ ወደፊት ሊያስኬድ የሚያስችል ያሉትን ዕቅድ፣ ቤልጂየም ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅርበው ኤምባሲው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማቅረቡን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የፍትሕ ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጡበት ተጠይቀው ዕቅዱ ተቀባይነት በማግኘቱ፣ አስፈላጊው የሕግ ከለላ ተደርጎላቸው ወደ አገር ቤት ተመልሰው ችግሮቹን በውይይት እንዲፈቱ እንደተፈቀደላቸው አስረድተዋል፡፡ 

ኢንጂነር ታደሰ ያቀረቡት ዕቅድ በመጀመርያ በፋብሪካ ውስጥ የሚገኙትን መኪኖች ገጣጥሞ ክፍያ ለፈጸሙ ደንበኞች ማቅረብ፣ በመቀጠል የተቀሩትን መኪኖች ገጣጥሞ በመሸጥ ኩባንያው ያለበትን የባንክ ዕዳ መክፈል የሚል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት 150 ያልተገጣጠሙ መኪኖች በፋብሪካው ውስጥ እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ እነዚህን መኪኖች ለመገጣጠም አምስት ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ስድስት ሚሊዮን ብር ከአውሮፓ የገንዘብ ምንጮች ይዘው እንደመጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ሆላንድ ካር ከገባበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት አንድ ዓመት እንደሚፈጅም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ያልተገጣጠመ መኪና ብረት ነው፡፡ አይሸጥም፡፡ ገጣጥመን እሴት ጨምረን ብንሸጠው ሁሉም ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ደንበኞች ንብረታቸውን ያገኛሉ፡፡ ከዚያም ተርፎ ድርጅቱ መቀጠል የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፤›› ብለዋል፡፡ 

ኢንጂነር ታደሰ 115 ደንበኞች ክፍያ ፈጽመው መኪኖቻቸውን አለመረከባቸውን፣ 40 ያህል ደግሞ ቀረጥ ከፍለው መኪኖቹን መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የጀመሩት ጥረት ከሰመረ ወደ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች ለመግባት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

 ከሆላንድ ካር መኪና ከገዙ ግለሰቦች መካከል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ አንዱ ናቸው፡፡ በሆላንድ ካር ቀውስ ከተፈጠረ በኋላ መኪናቸውን የተረከቡ የመጀመርያው ደንበኛ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

‹‹መኪናዬን ከተረከብኩ በኋላ ሌሎች ግለሰቦች መኪናቸውን እንዲያገኙ ጊዜዬንና ገንዘቤን በመሰዋት ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ሆኖም እጃችን አመድ አፋሽ ሆነና ባልሠራነው ኃጢያት ተከሰን ጠበቃ ቀጥረን ተከራክረን ነፃ ወጥተናል፤›› በማለት በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አስታውሰዋል፡፡ ‹‹አሁን ባለሀብቱ ያሉትን ችግሮች ፈትቼ ከባንኩ ጋር ተነጋግሬ ለደንበኞች መኪኖቹን አስረክባለሁ ካሉ በእውነቱ ይህ መልካም ዜና ነው፡፡ የሚደገፍ ተግባር ነው፤›› ብለዋል አቶ ግርማ፡፡ 

 

በምርጫው ሁከት ቢፈጠር እንኳን ከአቅም በላይ እንደማይሆን መንግሥት አስታወቀ

ምርጫውን ተጠቅመው ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን መንግሥት የሚታገስበት ምክንያት እንደሌለና ችግር ከተፈጠረም ከአቅም በላይ ሊሆን እንደማይችል፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ አጠቃላይ የቅድመ ምርጫ ዝግጅት ከጥቃቅን ችግሮች ባሻገር ሰላማዊ እንደነበር ባለፈው ሳምንት ከምሁራንና ከፓርቲዎች ጋር በተደረገ ውይይት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

ቀጣዩ ምዕራፍም ተመሳሳይና ሰፋ ያለ ተሳትፎ የሚደረግበትና ምርጫው በአጠቃላይ እጅግ ሰላማዊ ሆኖ ይጠናቀቃል የሚል እምነት መያዙን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት ሁከትም ሆነ ችግር ለመፍጠር የሚያስችል ምክንያት አለመኖሩን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆኑ ገዥው ፓርቲ በጋራ ባካሄዱት ግምገማ ከሞላ ጎደል ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል፡፡

‹‹ይህ ማለት ግን ምርጫውን ተጠቅመው ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላት አይኖሩም ማለት አይደለም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ይህንን የሚሸከም የሕዝብ ትከሻ የለም፡፡ በመንግሥት በኩልም ለፀጥታ ኃይሎች ሥልጠናና የቁሳቁስ ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ ችግር ከተፈጠረ ከአቅም በላይ ሊሆን እንደማይችል መንግሥት እርግጠኛ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ለፀጥታ ኃይሉ በቅርቡ የተሰጠው ሥልጠናና የአቅም ግንባታ ማዳበሪያ የተከናወነው የተለየ ሥጋት በመኖሩ እንዳልሆነም አስታውቀዋል፡፡ ከምርጫ 97 በኋላ የተደረገ ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ለፀጥታ ኃይሉ መስጠት መደበኛ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ ከቁጥጥር ውጪ የሚወጣ ነገር አይኖርም ብለዋል፡፡ የአቅም ግንባታ ሥራውም ከምርጫ በኋላ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ የነበሩትና በኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይል የመን ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከአዲስ አበባ አዳማ የሚወስደውን የፍጥነት መንገድ ሲጐበኙ የሚያሳይ ፎቶግራፍ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች መታየቱን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ሬድዋን፣ ‹‹ምሥሉን አይቼዋለሁ፡፡ ነገር ግን ዝርዝር መረጃ አልጠየቅኩም፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ ላይ የምሰጠው መረጃ የለም፤›› ብለዋል፡፡