የወያኔ ልሂቆች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ፤….ጦርነቶች የሚዋሹት ውሸት ሲመረመር

መጀመርያ በዚህ የዓመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (‘ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)
ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል። በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን መጀመርያ በዚህ የአመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬውየታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (‘ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)
ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል። በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን ብለው አጥቂዎቻቸውን ወይንም መሰሎቻቸውን ያታልላሉ። እንሰሳዎቹ በማታለል ዘዴ የሚኖሩበት ምክንያት የተለያዩ ምክንያቶች አሉዋቸው። ለምግብ፤ ወይንም እራሳቸው ከጥቃት ለመከላከል ሊሆን ይችላል።ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እራሳቸውን እና ሌሎችን ሆን ብለው ለማታተለል/ለመዋሸት “የተሰሩ ፍጡሮች” ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያነበብኳቸው አንዳንድ የስነ ልቦና መጻሕፍቶች ይገልጻሉ።
የተለያየ ውሸት የተለያ ምክንያት ቢኖሮውም፡ ዋሾች አድማጭ ፈላጊዎች ናቸው። አታላዮች/ዋሾዎች እንደ እንደተሰጥዎአቸው የማጭበርበር፤ የመዋሸት ወይንም ማራኪ የንግግር ችሎታቸው ይለያያሉ። የተከታዮቻቸው ብዛትም አንደሚጠቀሙበት የማጭበርበር ስልት ይለያያል። ተራ ዋሾዎች ካደጉበት የውሸት ባሕሪ በመነሳት ሕዝብን የመምራት ፍላጎት እያዳበሩ በሄዱ ቁጥር፤ በመንግሥት፤ በፖለቲካ፤ በሃይማኖት ግብተው መሪነቱን ከያዙ፤ አደገኛ የውሸት ባሕሪያቸው በመጠቀም ሕዝቡን በውሸት ጐዳና በመምራት፤ “ዋሾ ማሕበረሰብን” ይገነባሉ።
እራሱን ያታለለ ማሕበረሰብ “የሕሊና ጎዶሎ/ሃንዲካፕ” ነው። ሌላ ቀርቶ በየጽሑፎቻችን ላይ የሚታዩ ግድፈቶች/ የቃላት ስህተቶች ልብ ሳንላቸው አልፈን ከታተሙ በሗላ ነው ስህተቶቹ ግልጽ ሆነው የሚታዩን። የዋህ ሕሊናም በአታላዮች አስተሳሰብ ሲጠለፍ እራሱን መፈተሽ ስለሚያቅተው፤ ከመሪዎቹ የሚነገሩት ሁሉ እውነት ስለሚመስለው፤ እሱም በውሸቱ ዘመቻ እየተካፈለ በሄደ ቁጥር እየዋሸ እንደሆነ አይታወቀውም። በመጠጥ ከሰከረ ይልቅ፤በውሸት የሰከረ ማህበረሰብ አስቸጋሪ ስለሚሆን (ዲናያል/ክሕደት) እውነታውን ለማስጨበጥ ጊዜ ስለሚፈጅ፤ የእውነት አስተማሪዎች ከዚህ ማሕበረሰብ ጋር ከፍተኛ ግብግብ ይገጥማቸዋል።
ይህ አሳዛኝ ባሕሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በባሰ ደረጃ በወያኔዎች ዘመን ተከስቷል። የ ‘ወያኔ ትግሬ’ የውሸት ባሕሪ በታሪካችን፤በባሕላችን፤ በአርበኞቻችን እና በሉዓላዊነታችን ክብር ላይ ጥቃት አድርሷል። ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነው።
ለዚህ ጹሑፍ መነሻ የሆነኝ፤ ሶሞኑን ‘ትግራይ ኦን ላይን’ በተባለው “ፍሎሪዳ” መሰረቱ ያደረገ የወያኔዎች ድረገጽ “Woyane Tigray: 39 Years and Still Standing” በሚል ያስነበበውን መነሻ በማድረግ ነው። (ጸሐፊው ሞቡቱ ሴሰ ሴኰም ሆነ ጋዳፊ ከወያኔ ዕድሜ በላይ እንደገዙ አላወቀም።
“እንደ ጋዳፊ
መለስን በጥፊ ፤
ሳንፈልጋቸው
ሃያ አመታቸው!”
ተብሎ የተጨፈረለትን የወያኔ ስርዓት አልሰማም መሰለኝ።) ርዕሱን በዚሁ ልምልስ እና ጸሓፊው በበላይ ዘለቀ እና በአሉላ መካካል ያለው ልዩነት ያነጻጸረበትን የውሸት ክስ እንመለከት።ከብርሃነ ካሕሳይ በሚል የተጠቀሰው ርዕሰ የጻፈው ጸሐፊ የዓይጋ ድረገጽ አዘጋጅ ወይንም የትግራይ ኦንላይን አባል አዘጋጅ እንደሆነ ይገመታል።ቢሆንም ባይሆንም ቁም ነገሩን ብቻ እንመልከት።
“…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa. Unfortunately, the courageous Belay Zeleke was subsequently hanged by Emperor Hailesellaise upon his return from Bath, England, where he had resided after fleeing the country, leaving the people at the mercy of the Italian occupiers.” http://www.tigraionline.com/articles/wo … years.html (By Berhane Kahsay
Tigrai Onlne – February 09, 2014)
ይህ ውሸት ተደጋግሞ በወያኔ ትግሬ መሪዎች እና ተኮልኳሊዎቻቸው ተነግሯል። ባለፈው ወር የዶጋሊ በዓል ማክበር ሲገባ፤ ወያኔዎች ሳያከብሩት በዝምታ አልፈውታል። በዚህ የተነሳ ወዳጄ አቶ ብርሃኑ ሰፋ ያለ ቅሬታው ኢ ኢ ዲ ኤን በተባለ ማሕበራዊ መድረክ ለተቃዋሚውም ሆነ ለወያኔዎች ለምን አንዳልተከበረ ቅሬታው ገልጿል። ቅጁም ለእኔ አስተላልፎልኛል። ድሮ ደርግ ምፅዋ ላይ /ዶጋሊ ላይ ስለ አሉላ ያዘጋጀው የሲምፖዚየም ንግግር በመጽሐፍ ተጠርዞ አንዳነብበው ልኮልኝ አንብቤ አንድ ነገር አንዳዘጋጅ ተማጽኖኝ ነበር። ንባቡ ገና ሳልጀምር ወያኔዎች ከላይ የተመለከተው ሚዛን ያልጠበቀ የክስ እሮሮ በራሳቸው ከማድረግ ይልቅ በሌለው ላይ ክስ ሲያወርዱ አንብቤ ነው ይህ ድንገተኛ መልስ ለመጻፍ የተነሳሳሁ።
ወየኔዎች የውሸት ክስ፤ስም ማጥፋት፤ ክሕደት የድርጅታቸው ባሕርያዊ ቋሚ መለያቸው ነው። በጣም በርከት ያሉ መጽሐፍቶች የአጼ ዮሐንስም ሆነ የራስ አሉላ ታርክ እና ሞገስ ‘አማራ ታሪክ ጸሐፊዎች”’ ብለው ወያኔዎች በሚጠሯቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ጻሀፊዎች የጻፏቸው እያንኳሰሱ፤ ዛሬ ወያኔዎች ከ22 አመት ንግሥና በሗላ ገንዘቡ፤ሕትመቱ፤ሳነሱሩ፤ውሸቱ ፤ብዕሩ፤መዛግብቱ፤ዩኒቨርሲቲው እና ምርምር ተቋማቱ በእጃቸው ቁጥጥ ባለበት ዘመን ምንም ሳይጽፉ በሃያ ሁለት አመት ውስጥ ስለ ዮሐንስ አንድ መጽሐፍ (በትዕቢት የተቆለለ ፤በውሸት የተበረዘ) የገብረኪዳን መጽሐፍ ብቻ ነው። ወደ ሃውልት ስንገባም፤ ወየኔዎች በአገሪቱ ስም ከውጭ አገር ዕዳ እየተበደሩ ወደ ኪሳቸው ከማግበስበስ እና ልጆቻቸው ወደ ውጭ አገር እየላኩ ከማስተማር እና እራሳቸውም በውድ ገንዘብ እየገዙ ዲግሪ ከማግኘት በስተቀር ለንጉሡም ሆነ ለራስ አሉላ ሃውልት ማሰራት ሲችሉ ወይንም ሕዝቡን አሰባስበው (እርዳታ እንኳ ካስፈለገ) ከማስሰራት ይልቅ እስካሁን ደቂቃ ድረስ ምንም የሰሩላቸው ሃውልት ወይንም መታሰቢያ የለም።
ስለ አሉላ ተሰራ የተባለው ሃውልት “የተቀመጡበት ፈረስ የአህያ ምስል በመያዙ፤ሕዝቡ ተቃውሞውን በማሰማት ሌላ የፈረስ ምስል የያዘ ሃውልት እስኪሰራ ድረስ በአቡጀዲ ሸፍነውት አንደነበረ ይታወቃል።
አንዳንዶቹ የሚሉት ያህያ ምስል አንዲቀመጡ የተደረገው ሆን ተብሎ በሻዕብያ አፍቃሬ ኤርትራዊያን ወያኔዎች ሴራ ምክክር እንዲቀረጽ አንደተደረገ በሃሜታ መልክ ይሰማል።
በሃያ ሁለት አመት ለአጼ ዮሐንሰም ሆነ ለአሉላ ይህ ነው የሚባል አጥጋቢ መታሰቢያ አንዳልሰሩላቸው የምከራከረው በመረጃ ነው። አማራ አንዲህ አደረገ ፤ያለፉት ጸሐፊዎች የንጉሳችን ታሪክ አልጻፉም፤ ሃውልት አልተሰራላቸውም… እያሉ በውሸት እስካሁን ድረስ የወያኔ ትግሬዎች የትግራይን ሕዝብ ሲያታልሉ 22 አመት አልፏቸው ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንስ የሰሩት አንደም መታሰቢያ አይገኝም። ይልቁንስ ወያኔዎች “ለአሉላ ወይንም ለዮሐንስ” ሃውልት ነፍገው ኤርትራ ምድር ድረስ ሄዶ፤ ምፅዋ እና ሳሕል የኢትዮጵያን ሰራዊት የወጋ በክሕደቱ ዘመን ከጠላት (ሻዕቢያ) ጋር ተሰልፎ የወጋን የራሳቸው ታጋይ ለሆነው “ሓየሎም አርአያ “ (ሐዱሽ አርአያ) ሽሬ አውራጃ ውስጥ ሃውልት አቁመውለታል። ታዲያ
“…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa.”
በማለት የወያኔ ቱልቱላዎች በታሪክ ጻሀፊዎች እና ባለፉት ገዢዎች ላይ የትግሬ እና የአማራ አርበኞችን እያነጻጸሩ የሚከስሱት ዘረኛ ክስ ከመክሰስ በፊት ሁሉም ነገር በእጃቸው ባለበት ሃያ ሁለት አመት እራሳቸው ያልሰሩትን ሌሎች አንዲሰሩላቸው መጠበቅ እና መክስስ አስገራሚ ክሰ ነው?
ለመታሰቢያ የቆሙ ከጣሊያን ወራሪዎች ጋር ተዋግተው በክብር የተሰውት የነ ደጃዝማች አፈወርቅ ፤የነ አቡነ ጴጥሮስ ፤የነ አሉላ፤ የእነ ምኒሊክ ወዘተ መታሰቢያ ሃውልቶች እያፈራረሰ እና እንዲፈርስ ዘመቻ እያካሄደ ያለው የሃያ ሁለት አመት አሳፋሪ ታሪክ የታቀፈው ማን ሆኖ እና ነው ማቆሚያ የሌለው ሃያ ሁለት አመት “የሕፃናት ልቅሶ እና ክስ” እየተለቀሰ ሌላውን ወገን ተወቃሽ የሚሆነው? ወያኔዎች ትንሽ የአደብ ሓፈረት የሚባል የሕሊና ገዢ እንዴት አንደተለያቸው ይገርመኛል? በሃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንሰ ጀብዱ አንዳንጽፍ ተከለከልን ካላችሁ፤ ውጭ አገር ሲኖሩ የነበሩ በርካታ የትግሬ ምሁራን የማን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ኖሮው ነው (ከዘውዴ ገ/ስላሴ በቀር) አማራው እንዲጽፍላቸው የጠበቁት እና ተከሳሽ የሚያደርጉት? ያስ ተከድኖ ይብሰል፡ – ሃውልት አልቆመላቸውም፤ ታሪካቸው አልተጻፈም .. ወዘተ… የምትሉት አሰልቺ ልቅሶ ‘ሃያ ሁለት አመት’ ሙሉ ከማልቀስ እና ከመክሰስ ያለፈ ስራ ምን ሰራችሁ? እስኪ ንገሩን? ምን ሃውልት ሰራችሁ? የሐለፎም ሓውልት? የወያኔ ተጋዮች ሃውልት? ለነሱ ከማቆም ይልቅ ለክሳችሁ መነሻ የሆነው የወላጆቻችን ጀግንነት እና ንግሥና አማራዎች ነጠቁን ብላችሁ በረሃ ለመሄድ ከገፋፋችሁ ምክንያት አንዱ ከሆነ የአሉላም ሆነ የዮሃንስ ሃውልት ቅድሚያ ለምን አልሰጣችሁትም? የአሉላ እና የዮሐንስ ገድል ይበልጣል ወይስ አሉላ እና ዮሐንስ ያስከበሩትን ድምበር እና ባሕር ያስደፈሩ እና የዘጉ የወያኔ ታጋዮች ገድል? የአሉላም ሆነ የዮሐንስ ገድል የቀበረ እና በባንዳ ተልዕኮ የተሳተፉትን የጎሳ ታጋዮች ገድል ጎልቶ በበላይነት አንዲታይ እያደረገ ያለው ማን ነው? ኢትዮጵያዊያኖቹ ዮሐንስ እና አሉላ መታሰቢያ ሳይቆምላቸው፤ ለጎሳ ታጋዮች ለምን ቅድሚያ ተሰጣቸው?
የወያኔ ውሸት ታሪክን የመበረዝ እና የማጣመም ባሕሪ በምን ዓይነት የአጻጻፍ ዘዴ ቢጻፍ የውሸታቸው ክምር አንዴት መግለጥ እንደሚቻል ሳስበው ይጨንቀኛል። በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ፤ዓድዋ፤ባድመ፤ዓድዋ… የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬዎች የመከላከል ታሪክ እና ጀግንነት ብቻ ነው እያሉ ያለ ምንም ሐፍረት ወይንም ዩልኝታ የሚገልጹት ባሕሪያቸው ሳስበው ለሕሊና ይከብዳል። የዚህ ውሸት ማቆሚያው መቸ እና የት ይሆን?
የዶጋሊ፤የሳሐቲ፤ወዘተ …. ወዘተ… ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተቀላቀሉበት አንዳንዱም በመሪነት የመሩዋቸው ታላላቅ ውግያዎች ውጤት እንጂ የትግሬዎች ብቻ አይደለም። ድሉ እና ሱታፌው የትግሬዎች አንጂ የተቀሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሱታፉ አልነበረም፡ የሚሉት ተዳጋገሚ ውሸታቸው በመጽሐፍም በንግግራቸውም በየስብሰባውም እስኪሰለቸን ድረስ ደጋግመውታል። ሃቁ ግን እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን በተጠቀሱት ጦርነቶች የተሳተፉት ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የተሳተፉበት ውጊያ እና ድል ነበር። መረጃውም ቆየት ብየ አቀርባለሁ። ይህ መረጃ ላንዴ እና ለመጨረሻ ውሸታቸውን የሚያቆም በመሆኑ መረጃውን እንድትጠቀሙበት በጥንቃቄ አስቀምጡት።
መረጃውን ከመጥቀሴ በፊት ማለት የምፈልገው ነገር፤ መረጃው ካነበቡት በሗላ አንዳንድ ወያኔዎች፤ “ምንም እንኳ ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰራዊቶች በዶጋሊ፤ በጉራዕ…ወዘተ ይኑሩ እንጂ አብዛኛው ተዋጊ የትግሬ ሰራዊት ስለነበር፤ ድሉ የትግሬ ሰራዊት ነው፡ የሚሉ የወያኔ ጐሰኞች ሊኖሩ ይችላሉ።ለነዚህ የምሰጠው መልስ “ዓድዋ ላይ የተሳተፈው ተዋጊ ሠራዊት፤ አብዛኛው ትግሬዎች ሳይሆኑ የሸዋ የንጉሥ ምኒሊክ ሠራዊቶች ናቸው። ሌላ ቀርቶ የወያኔ ወዳጅ የሆነው አይሁዳዊው ‘ኤሪክ ሓጋይ’ “አሉላ” በተባለው መጽሐፉም የትግሬ ሰራዊት እጅግ ጥቂት ስለነበረ አሉላ የሰራው የውግያ አስተዋጽኦ ጎልቶ የሚታይ አልነበረም። ኢሚንት ነው። በማለት መስክሯል። በዚህ ክርክር ከገባን “ከራስ መንገሻ (አሉላ) ሸራዊቶች” ይልቅ ከሌሎች ኢትዮጵያ መንደሮች የመጣ በተለይም ከሸዋ በብዛት የተሳተፈ ሠራዊት ስለነበር፤ የዓድዋ ድል ‘የሸዋ ሠራት ድል’ መሆን አለበት ሊባል ነው ማለት ነው?” ዋናው የውሸት ቀፎ የሆነው የ ‘ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ’ ድርጅት፤ በድርጅቱ ሁለተኛ ጉባኤ (1975) ያጸደቀው ውሳኔ አንዲህ ይላል “በአገራችን የሰሜን ጦርነቶች በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ… የተካሄዱ ጦረነቶችና ድሎች የኤርትራ ሕዝቦች እና የትግራይ ሕዝቦች ድል ነው”። ሲል በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በእነ አምደጽዮን (ከሸዋ እየገሰገሱ) እና በመሳሰሉት የድሮ ነገሥታት ከሩቅ ያገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወደ “ሓማሴን ምድር ወይንም ወደ ባሕረ ምድር” (ኤርትራ) በመሄድ ከቱርኮች እና ከመሳሰሉ ወራሪዎች ተዋግተው ጠላት ድል የመቱትን ሁሉ በመደበቅ፤በአካባቢው የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬ ጀግኖች ውጤት እያሉ ሚዛን ያጣ ትምክሕት በማሰራጨት አዲሱን የትግራይ ትውልድም ያንን ውሸት እየተቀበለ በዛው ትምክሕት እየተወጠረ መራመድ ጀምሯል።
አሁን ወደ መረጃዬ ልሂድ።
«—-ዘመናዊ የካራቢነር ጠመንጃና መድፍ የጨበጠው የግብፅ ጦር ወደትግራይ አምርቶ የመረብን ወንዝ ተሻገረ።በኅዳር 7 ቀን 1875 ከዚህ ወንዝ አጠገብ ጉንደት ከተባለች ሥፍራ ላይ በንጉሠነገሥት ዮሐንስ 4ኛ የተመራ የኢትዮጵያ ሠራዊት መንገድ ዘጋበት።ንጉሡ ሠራዊቱን በሁለት ከፍሎ ፤ አንዱን ክፍል ራሱ፤ ሁለተኛውን ክፍል በዚያን ጊዜ የተመሰከረለት ጀግና የነበረው ራስ አሉላ እንዲመራው አደረገ። ሁለቱም የኢትዮጵያ ክፍለ ጦር ከተለያየ አቅጣጫ ደወ ግብፁ ምሽግ ተንቀሳቀሱ። የጉንደት ጦርነት ሙሉ ቀን ፈጀ። ከምሽቱ ላይ ድሉ ለኢትዮጵያውያን ማድላቱ እየለየ መጣ። አብዛኛቹ በጀግንነት የተዋጉ ግብፃውያን ከትግሉ አውድማ ላይ የወደቁ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ አራኪል ቤይ እና ሻምበል አረንድሩፕ ያገኛሉ። ከፊሉ ተማረከ፣ አምልጦ ምፅዋ ሊገባ የቻለው በጣም ጥቂት ነው።
« ከዚህ ውድቀትም በኋላ ከዲቭ እስማኤል በኢትዮጵያ ላይ ቀጣዩን ዘመቻ ለመክፈት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ። ለቀጣዩ ጦርነት ካሁኑ የበለጠና የተሻለ ትጥቅ ያለው ሠራዊት ለማዝመት ወሰነ። ላሁኑ ዘመቻ 20,000 ወታደር አዘጋጅቶ በእጁ የሚገኘውን የተሻለ መሣሪያ ሁሉ አስታጠቀው። እስማኤል ለአዲሱ ዘመቻ በጀርመን አገር በወታደራዊ ሥልጠና የተመረቀውን መኮንን ሙላይ ሐሰን ፓሻን አዛዥ አድርጎ ሾመው። ከሱም ጋር ሌሎች የግብፅ የጦር መሪዎች አብረውት የዘመቱ ሲሆን፣ ከነዚህም አንዱ ዝነኛው ራቲብ ፓሻ ነበር።
በታኅሣሥ ወር 1875 የከዲቩ ጦር ምፅዋ ላይ አርፎ በዝግታ ወደ ማህል ኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ጀመረ። በየካቲት 1876 ከመረብ ወንዝ ተጠጋ።
« ለዚህ የግብፅ ወረራ ምላሽ ዮሐንስ 4ኛ በሞሐመዳውያን ላይ “የመስቀል ዘመቻ“ አዋጅ አስነገረ። ንጉሡ ከጎጃምና ከሸዋ የማጠናከሪያ ኃይል እንዲመጣ አድርጎ ፣ጠቅላላው የሠራዊቱ ቁጥር 60,000 ደርሶ ነበር። ሁለቱ ሠራዊቶች በመጋቢት ወር 1876 ጉራዕ ላይ ተጋጠሙ። ግብፆች ምሽጋቸውን ዙሪያውን በጉድብ ሰንሰለት ስላጠሩት የኢትዮጵያውያኑን ጥቃት ለመከላከል አመችቷቸው ነበር። ከግጥሚያው መጀመሪያ ላይ ስለቀናው ተደፋፍሮ ሙላይ ሐሰን በልምድ የበሰለውና ሽማግሌው ወታደር ራቲቭ ፓሻ ተው እያለው ጠላቱን በግላጭ ገጥሞ እደመስሳለሁ ብሎ ከምሽጉ ወጣ። ይህ ውሳኔ ለግብፆች መጥፊያቸው ሆነ። የኢትዮጵያ ወታደር በቁጥሩ ከወራሪው ጦር እጅግ ከፍ ያለ ነበርና የውጊያውን ሰልፍ ጥሶ እየተወረወረ ከጠላቱ ምሽግ ውስጥ ገባ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጊያው ወደ መተላለቅ ተለውጦ የግብፅ ጦር በድንጋጤ ተውጦ ፈረጠጠ። ሙላይ ሐሰን ፓሻ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዞ ከንጉሡ ፊት ቀረበ። ንጉሡም ድል የሆነበትን ቀን እንዳይረሳው ሲል ከክንዱ ላይ ሁለት መስቀል እንዲተኮስበት አደረገ። በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም ውል ከተደረገ በኋላ ከዲቭ እስማኤል ፣ ሙላይ ሐሰን ፓሻና ሌሎችም በጉራይ ጦርነት ላይ ከሱ ጋር የተማረኩትን ከፍተኛ መኮንኖች ማስለቀቂያ ከፍሎ አስፈታቸው።»(ገጽ 289 እስከ 299፣“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003)
ስለሆነም በጉራዕ፤በጉንደት፤በስዋኪን፤በዶጋሊ፤በዓድዋ፤በማይጨው፤መመሳሰሉት ጦርነቶች እና በቅርቡም የትግሬው ወያኔ እና የኤርትራው ሻዕቢያ በጫሩት 70,000 የሚገመት ተጠያቂ የሌለው ሕይወት የበላ የጥላቻ ጦርነት ከሁሉም ወይንም ከከፊል የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖር ሕዝብ የተካፈለበት ጦርነት ነበር። ወያኔዎች በሁለተኛ ጉባኤያቸው የኛ የትግሬዎች ገድል ብቻ ነው ብለው ያሉት በውሸት የተመሰረተ “የትግራይ ጦር ብቻ” የተሳተፈበት ጀግንነት ያሉትን ውሸትም ሆነ፤ የወያኔ ታሪክ ጸሐፊዎች ነን የሚሉን ትምክሕተኞቹ የትግሬ ብሔረተኞች በመጽሐፍቶቻቸው የሚዋሹት እና የሚመኩባቸው የተጠቀሱት የትግሬ ጦር ውሎ ጀብዱ ሁሉ የትግሬ ብቻ ሳይሆን ጦሩ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው አገር ይኖሩ የነበሩ ዜጎች በጦርነቱ ተካፋይ እንደነበሩ ከላይ ለመከራከሪያ ያቀረብኩት የመረጃ ሰነድ ማለትም “የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003 ያስረዳል።
የትግሬዎች እና የተጠቀሱት የአካባቢ ተሳታፊዎች የቁጥር ልዩነት ይችላል ወይ? አዎ ምናልባት ሊኖረው ይችላል። ያም በእርግጠኝነት ይህ ነው ማለት ባይቻልም ካራት ወይንም ከሦሰት ክ/ሃገራት የተውጣጡ ተዋጊዎች በቁጥር አነስተኛ ማሕበረሰብ ከነበረው ከትግራይ ጦር ሲነጻጻር ሊበዛ ወይንም እኩል ሊሆንም ይችልም ይሆናል። የጉራዕ/ጉንደት ጦርነት ግን ከጎጃምና ከሸዋ በብዛት የዘመተ መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ጎንደርና ወሎ ያልተጠቀሱበት ምክንያት ሁለቱም በንጉሡ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር የነበሩ በመሆኑ ተሳትፎአቸው ግልጽ ስለሆነ ነው።
አሁን መረጃው ሰጥቻለሁ። የወያኔ ትግሬ ጸሐፍት ጉረኞች በየመጽሕፍቶቻችሁ እና በየቃለ መጠይቃችሁ የምትነዙት አጉል ጉራ እና ታሪክ አደፍራሽነታችሁ ረገብ አንድትሉ በግራ ቀኝ የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች አንብቡ። ለዚህም ነበር አፄ ዮሐንስ ‘የትግሬ ልጅ ሆይ” ሳይሆን ሲሉ የነበሩት ለጦርነት ሲዘጋጁ “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ” ነበር እያሉ መላውን ግዛታቸው ያለው ሕዝብ ለጦርነት ጥሪ ሲያደርጉ የነበሩት። ለዚህም ነበር “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።“(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ) ሲሉ የነበሩት።
ወያኔዎች የትግራይ ወያኔ ብሄረተኞች ከንጉሥ ዮሐንስ “የኢትዮጵያዊነት” ትርጉም ምን ማለት አንደሆነ ሊማሩት አልፈቀዱም። አለማፈራቸው ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለው “ማንነት” ትግራዋይነት አንጂ “ኢትዮጵያ” የሚባል ማንነት የለንም መላት ጀምረዋል። ንጉሥ ዮሐንስ እያሉን ያሉት ግን “ኢትዮጵያ ማንነትህ ናት” -ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።” ሲሉ በወርቃማው ‘ኢትጵያዊ ማነንት’ ትርጉማቸው ተርጉመውልን ቢሄዱም “የወያኔ ባንዳዎች” ወደ ቁልቁል ወደ መንደራቸው በመሸማቀቅ “ትግራዋይነት” አንጂ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንንት የለም፤ በማለት ወደ “ትግሬነት” ወደ “ኤርትራዊነት” ማንነት ወደ እሚሉት ደደቢታዊ እና ናቕፋዊ የግንጠላ አዝማሚያ እና መንደርተኛነትን አጥብቀው ማማንዠክ ይዘዋል።
የትግራይ ኦን ላይን ውሸታሞች በአማራ ሕብረተሰብ እና አርበኞች ላይ ያላቸው የጥላቻ መንፈስ ከኤርትራዊያኖቹ የባሰ ጥልቅ እንደሆነ ልብ ያለው በበሰለ ሕሊና የተከታተላቸው ታዛቢ የሚመሰክረው ቢሆንም ዛሬም ከሃያ ሁለት አመት በሓላም ጥላቸው እና ትንኰሳው ስላልበረደላቸው፤ በትግሬው አሉላ እና በአማራው በላይ ዘለቀ (አማራ እና ትግሬ የሚለው በሽታቸው ሲያወዳድሩ) መካከል ልዩነት ፈጥረው “አማራዎች” የአሉላን ክብር እንድያንስ አድርገዋል፡ እያሉ የአማራ ጸሐፊዎችን የሚከስሱት ውሸት እራሳቸው በራስ አሉላ ላይ እያደረጉት ያሉት ደባ እንዳይጋለጥ የሚያደርጉት ተንኰል ነው። የሚከተለውን ጉድ አንብቡ፤
“Tigrai Rep. officially disowns the indomitable lion of Dogali, Ras Alula” በሚል ርዕስ ወንድማችን ጌታሁን በቀለ የዘገበውን እንመልከት።
The Horn Times Newsletter, Dec 2, 2012
By Getahune Bekele
“ The great Abyssinian chief Ras Alula is at present a person of much interest to the Italians, and the Reforma is publishing a sketch of his life, in the course of which it is stated













