ፖለቲካዊ ሥልጣንን በመጠቀም ያላግባብ ዜጋን መጉዳት በራሱ ፖለቲካዊ ሙስና ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ:-ሕንፃ- መኪና -ቪላ -ኢሮ -ብርና ዶላር -ጠበንጃ እና ቦምብ- እየተቆጠረ ሙስና እንደሚወራልን ሁሉ … የሃገሪቷን ዜጎች የጎዳ ;ሕግን እና ህገመንግስትን ያጣመመ; የራሱ መንግስት ያለውን;የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና የግል ቂምበቀሉን ተገን አድርጎ የተንቀሳቀሰ ; መብት ጥሰት የፈጸመውን ;የዜጎችን መብት ያፈነውን ;ህገወጥ ተግባር በዜጎች ላይ የፈጸመውን ;ከህገወጦች ጋር የተባበረን ተቆጥሮ ;በፖለቲካ ሙሰኝነት መች ነው ለፍርድ የሚቀርበው??
በሃገሪቱ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ በሕወሓት መሪነት እየተፈጸመ ያለው ደባ እጅግ በረቀቀ መንገድ ከመስፋፋቱም በላይ በሙስና ስም የሚጠመዱ ሰዎች በውስጥ የፖለቲካ ቁርሾ ላይ የተለየ ሃሳብ ያነገቡ እና ስውር እጆች የሚያጠምዷቸውን እንደሆነ እያየን ነው ይህ ራሱን ችሎ በገዢው ፓርቲ ውስጥ የሚካሄድ የውስጥ ሽኩቻን የታከከ ፖለቲካዊ ሙስና ነው::
በየድርጅቶች ውስጥ የተለየ ሃሳብ እና የትችት ሙድ ያላቸውን ሰዎች ወይንም ከነማን በነማን እየጦዙ ነው የቡድን ስሪት ተለጣፊ አመራሮችን ለማፈን ሃያልነትን መጠቀም የፖለቲካ ሙስና ነው::እስከዛሬ እርምጃ ተወሰደባቸው የተባሉ ሰዎች ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ ችግር እንዳለ መረጃዎች ሲጠቁሙ በግል ቂም በቀለም የታሰሩ ሰዎች አላግባብ እየተንገላቱ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዥነት የእስር ቤት ውስጥ ያለውን ሁኔታ ተቃዋሚን እንዲሰልሉ የተያዙ አስመሳይ የሙስና እስረኞች እንዳሉ የታወቀ ጉዳይ መሆኑ በራሱ የፖለቲካ ሙስና ነው::
በጠበንጃ ሃይል የያዙትን ስልጣን ተጠቅመው በምርጫ በህዝብ ተመርጠናል የሚሉ አካላት ህዝባዊ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ አነስተኛ እና ጥቃቅን ሆድ አደር ካድሬዎችን በማሟሟቅ ላወጡት እና ላጸደቁት ህጋቸ ተገዢ ከመሆን ይልቅ እንደፈለጉ እና እንዳሻቸው ራሳቸውን ከአገሪቱ መናብርታት እኩል በማሰለፍ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ተገን አድርገው እና ተጠቅመው የሚፈልጉትን እየጠቀሙ የማይፈልጉትን እያጠቁ ይገኛሉ::ፖለቲካዊ ሥልጣንን በመጠቀም ያላግባብ ዜጋን መጉዳት በራሱ ፖለቲካዊ ሙስና ነው፡፡
የግል ቂም በቀል የፖለቲካ አመለካከት እና ተመሳሳይ ጉዳዮችን በማጣቀስ ልዩነት ጠላትነት የሚመስላቸው ያልበሰሉ የስርኣቱ ካድሬዎች የግል ጸበኞቻቸውን የፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን ለፖለቲካ የንግድ ድርጅቶቻቸው አስጊ የሆኑትን ጠንካራ ነጋዴዎች በሙስና አልተሳሰር ያሉ ኢንቨስተሮችን የፖለቲካ ባላንጣ ቤተሰቦችን እንደ ጠላት በማየት መሬት እንዳያገኙ መከልከል፣ ፈቃድ መሰረዝ እና አለመስጠት ፣ የያዙትን መንጠቅ፣ የባንክ አካውንታቸውን ማገድ እና ብድር እንዳያገኙ ማከላከል ፣ የብቃት ማረጋገጫ እንዳትሰጧቸው፣ የሥራ ፈቃዳቸው እንዳይታደስ፣ ወዘተ እየተባለ መጉዳት፣ ማንከራተትና ሕገወጥ ተግባር በመፈጸም ስልጣንን ያለአግባብ የሚጠቀሙ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች የሚፈጸሙት የፖለቲካ ሙስና በአገሪቱ አግጥጦ እየታየ ነው፡፡
ራሳቸው ያወጡትን እና አፈጻጸሙ እና አተረጓጎሙን እንኩዋን በተግባር ያልተረዱትን ሕግ በመጣስ ባለስልጣናት የግል እና የወል ጠላቶቻቸውን ድርጅቶቻቸውን ማሳሸግ ማጉላላት ማዘረፍ ማስደብደብ ባልሆነ ወንጀል መክሰስ፣ ፋይል ማስከፈትና ማስፈረድ በተግባር ይታያል፡፡ ጎን ለጎን ዘመድ እና ወዳጅ ለሆነና ከራስ ፍላጎት ጋር የሚስማማ ሥራ ላለው ደግሞ ሕግ ቢጣስም እንዳይጠየቅ፣ እንዳይያዝ፣ እንዳይከሰስ፣ ከተከሰሰም ፋይሉ እንዲዘጋና ክሱ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነም ሳይያዝ ወደ ውጭ አገር እንዲሸሽ በማድረግ ከኢኮኖሚ ሙስና ይልቅ ከፖለቲካ ሥልጣን አጠቃቀም አንፃር ሲታይ ግን ሥልጣንን መከታ በማድረግ የሚፈጸም አደገኛ የፖለቲካ ሙሰኛ ነው፡፡ ሕንፃ- መኪና -ቪላ -ኢሮ -ብርና ዶላር -ጠበንጃ እና ቦምብ- እየተቆጠረ ሙስና እንደሚወራልን ሁሉ … የሃገሪቷን ዜጎች የጎዳ ;ሕግን እና ህገመንግስትን ያጣመመ; የራሱ መንግስት ያለውን;የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና የግል ቂምበቀሉን ተገን አድርጎ የተንቀሳቀሰ ; መብት ጥሰት የፈጸመውን ;የዜጎችን መብት ያፈነውን ;ህገወጥ ተግባር በዜጎች ላይ የፈጸመውን ;ከህገወጦች ጋር የተባበረን ተቆጥሮ ;በፖለቲካ ሙሰኝነት መች ነው ለፍርድ የሚቀርበው??