የሕወሓት የበላይነት እስከመቼ ?? … መሸዋወድ እስከየት?

ምንሊክ ሳልሳዊ :- የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 22 ድፍን አመታትን አስቆተረ::

በ22 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሆዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱት የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::

የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::

በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ

አዲስ አበባ የሚገኘው የአንድነት ቢሮ በከፍተኛ ሁኔታ በፖሊስ እና በደህንነት ሃይሎች ተከቧል። የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ነው።

Image

ደሴ በህዝቦቿ አንድነት ደምቃለች ። #Ethiopia #Dessie #UDJ #EPRDF #Demonstration
#MillionsVoicesforlandownership

በደሴው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአስር ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ፍርሃትን ሰብሮ የደሴ ጎዳናዎች ላይ ወጥቷል።
ህዝቡ አሁንም ወደ ሰላማዊ ሰርፉ በመጉረፍ እየተቀላቀለ ነው። መብቱን እና ነጻነትን በማወቅ ጥያቀዎቹን ለማሰማት የአንድነት ፓርቲ ጥሪን ተከትሎ አደባባይ የወጣው ህዝብ በመፈክር እና በዝማሬ ብሶቱን እያሰማ ነው።
“ኢህአዴግ እንዴት ቢንቀን ነው በ30 ብር አበል ነፃነታችንን ለመንጠቅ የሚሞክረው?”
ለሰልፍ ተሳታፊ የቀረበ ጥያቄ
ፖሊስ መንገድ በመዝጋት እየሞከረነው ሆኖም ሰልፈኛው ግን ጥሶ በማለፍ ላይ ነው፡፡
ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራውይህ ቡድን ከሜይ 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካመቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህንአበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግንጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

Image

ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንምአሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውልየለም ብለዋል።በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስበመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱመብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎችእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያንለመረዳት ችለናል።ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውንቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱየገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህንአበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳትፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆችእንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

የመንግስት ባለስልጣናት የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል ሙስና ኮሚሽን አማሯል።

ኢትየጵያ ውስጥ አሁን ያለው የሙስና መጠን ትናንትና ከነበረው እጥፍና ከእጥፍ በላይ አሻቅቧል፡፡ አሁን አገሪቷ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ወደላይ እንዲያሻቅብ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱም የሙስና ጣርያ መንካት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አሳሳቢ መሆኑን መግለጽ ቀርቶ የእገሌን አገር ደረጃ አያክልም የሚለውን አባባል የኢትዮጵያ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡በአሁኑ ወቅት ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቷል፡፡ ባለጉዳይም ጉቦ ካልሰጠ ጉዳዩን እንደማያስጨርስ፤ ጉዳይ ፈጻሚም ገንዘብ ካላገኘ ጉዳይን ማስጨረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በገሃድ በሚታይበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በጉምሩክ፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሆስፒታሎች፣ በኢሚግሬሽን፣ ወዘተ ጉዳይን ለማስጨረስ ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡

ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡ ጉቦ የማይቀበል የማይረባና የማይጠቅም ተብሎ የሚሰየምበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን እያንዳንዱ ሰው በሚገባ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህ በመሰለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም ሲባል ምን ማለት ነው? መረጃው የተገኘውስ ከየት ነው? ከተበዳይ ወይስ ከበዳይ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢዎች አነስተኛም ይሁኑ ትላልቅ የፕሮጀክት ጨረታዎች ያለኮሚሽን ክፍያ የተፈጸሙ ናቸው የሚል ጥናት ፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ምንልክሳልሳዊበአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግዢዎችና ጨረታዎች ሕጋዊነትን ለማስያዝ ብቻ የሚካሄዱ ካልሆነ በስተቀር፣ አስቀድሞ ከታቀደውና ከታለመው ሰው ወይም ድርጅት ውጭ ማንም እንዲገባ በማይፈቀድበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የዋህ ሰው ሳይቀር በሚገባ የሚረዳበት ደረጃ ላይ እኮ ነን ያለነው፡፡ ግዢዎች ሲፈጸሙ ወይም ጨረታ በሚወጣበት ጊዜ የሚደረገውን ለአብነት እንይ፡፡

እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡

የጨረታ ዶክመንት ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ሰው ከሳምንታት ወይም ወራት በፊት አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱ (ቴክኒካል ስፔስፊኬሽኑ) በአጫራቹ ድርጅት አማካይነት በተመረጡና በታመኑ ሰዎች እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ ይህ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ግዥ በሚፈጽሙ ተቋማት ውስጥ በግልጽ እንደሚደረግ ግልጽ ነው፡፡ ፀሐይ የሞቀውም ነው፡፡ ለጨረታ ወይም ለግዥው የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ለጨረታ የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ አስቀድሞ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከተሰጠ በኋላ፣ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖረው ተፈላጊው ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዲያቀርብ ተደርጎ ተመራጭ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ምንልክሳልሳዊበአንዳንድ ግዥዎች አሸናፊ እንዲሆን የሚፈለግ የተጫራች ድርጅት ስፔስፊኬሽን እንዳለ የጨረታ ዶክመንት ሆኖ እንደሚቀርብ በግልጽ በሚታወቅበት ደረጃ ላይ ነን፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ያሉ ግዥዎችና ጨረታዎች ከፍተኛ ሙስና እየተፈጸመባቸው የሚካሄዱ መሆኑ ቢታይም፣ ሕጋዊነትን ተከትለው እንደተፈጸሙ ስለሚቀመጡ (በወረቀት፣ በአካሄድና በአሠራር) እጅግ የረቀቁና ሥር እየሰደዱ የመጡ ሙስናዎችን ለማየት ግን አዳጋች አይደለም፡፡ ምንልክሳልሳዊአንድ ድርጅት ከሁለት በላይ የተለያዩ ስም የያዙ የድርጅት ስሞችን ይዞ በመቅረብ አንዱ አሸናፊ ሌሎች አጃቢዎች ሁነው እንደሚቀርቡ በግልጽ ይታወቃል፡፡ የጨረታ ጊዜዎችን እጅግ በማሳጠር አሸናፊ እንዲሆን ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ግን አስቀድሞ መረጃውን በመንገርና ተዘጋጅቶ እንዲቆይ በሚደረግ፣ የሌሎች ተጫራቾችን ጊዜ በማሳጠርና የዝግጅት ጊዜ እንዲያጡ በማድረግ የሚፈጸሙ ግዥዎችና ጨረታዎች ናቸው እየተካሄዱ ያሉት፡፡ምንልክሳልሳዊ

አንዳንድ ቦታ ጨረታ በሚዘጋጅበት ወይም በሚካሄድበት ጊዜ ተጫራቾቹ በአጫራቹ ድርጅት ግለሰቦች ስም የሚጠሩበት አጋጣሚ እንዳለም በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡ ማን አሸነፈ ሲባል የአጫራቹ ግለሰብ ስም እየተጠራ እገሌ አሸነፈ ተብሎ በሚነገርበት ደረጃ ላይ እንዳለን ለማንም ባልተሰወረበት ሁኔታ ላይ ነን፡፡ እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጨረታ በኋላ አሸናፊው ድርጅት በፕሮጀክቶች ክትትልና በዕቃ ርክክብ ከሚፈለገው ደረጃና ብቃት በታች አፈጻጸም ያሳያል፡፡ ከሚፈለገው ዕቃ ውጭ አቅርቦቶች ሲካሄዱ ዝም እየተባለ የሚፈጸሙ የፕሮጀክቶች ግዥዎች ከበስተጀርባቸው ትልቅ ሙስና እንደሚካሄድባቸው ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ምንልክሳልሳዊ

ለዚህ ትልቅ ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ በመንገድ ግንባታ፣ በትላልቅ ግድቦች ግንባታ፣ በውኃ ሥራዎች፣ በቴሌኮም ፕሮጀክቶች፣ በቤቶች ግንባታና ማጠናቀቂያ ላይ ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ በእጅጉ ይታወቃል፡፡ እንደ ምሳሌ ለማቅረብ ከኤርፖርት እስከ መስቀል አደባባይ እየተሠራ ያለው መንገድ ቀደም ብሎ ለሌላ ድርጅት ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኋላ ግን ተቀይሮ ለሲአርቢሲ ተሰጥቷል፡፡ የመጀመርያው ተጫራችና አሸናፊ ድርጅት አቅም ሲመዘን እንኳን በዚህ ትልቅና አስቸጋሪ መንገድ እንዲሳተፍ በገጠር መንገድም ለማሳተፍ የሚያስችል ብቃት እንደሌለው ግልጽ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ድርጅት አሸናፊ እንዲሆን ተመርጦ የነበረው አላስፈላጊ ግንኙነት በመመሥረቱ ነበር፡፡ የዚህ ዓይነት መሰል ገጠመኞች ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ባንኮች ብድርና የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት በግልጽ ኮሚሽን በሚቀበሉበት አገር ላይ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ አይደለም እንዴት ይባላል?

የፀረ ሙስና ኮሚሽን አንዳንድ ሰዎች አሳሳቢ የሚባል የሙስና መረጃ ሲያገኙ፣ በተለይ ከሀብታም ነጋዴዎች ጋር የሚያያዝ ከሆነ ቀድመው ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ከሚጥሩ ይልቅ ለግልግል በሚሯሯጡበት አገር ላይ እያለን፣ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ነው እንዴት ይባላል? በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሮች ድረስ በሀብታም ተፅዕኖ ሥር በወደቁበት፣ ጉቦ በመቀበል የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡበት፣ ሀቅን በገንዘብ በሚለውጡበት፣ በጠራራ ፀሐይ ብሉ ሌብልና ቪኤስኦፒ በካርቶን በሚጫንበት፣ የሰው ሕይወት በገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት፣ ዓይን ያወጡ ሙሰኞች በሰፊው ሕዝብ ፊት ደረታቸውን ነፍተው ጉራቸውን በሚነፉበትና ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ወቅት መሆናችን እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም እንዴት ይባላል?

ትናንትና ለሀቅ፣ ለዲሞክራሲና ለአገራቸው ብልጽግና ሲሉ የወጣትነት ዕድሜያቸውን በረሃ የወጡ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ቀብረው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ጀግኖች በሙስና ተነክረው ሀብታም ሥር በተንበረከኩበት ወቅት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ቅጥረኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሠራርና መመርያዎችን ጥሰው በኔትወርክ በተሳሰሩበት ወቅት፣ እርስ በራሳቸው እሳትና ጭድ ሁነው በማይተማመኑበት ወቅት፣ ለሕዝብ ህልውና ዋስትና በታጣበት ወቅት፣ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሳስብ አይገባም ተብሎ እንዴት ይነገራል?

ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ፣ ከአሳሳቢነቱ በላይም ጊዜ የማይሰጠውና ወረርሽኝ በሆነበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይም ሙሰኞች የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ወሬዎች በሚናፈሱበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንዱ ቅንጣት ጥፋት የሌለው ይመስል ከራባቱን አስሮ ‹‹ሙስናን እንዋጋ›› የሚለው ከበስተጀርባው ትልቅ ጥፋት ተሸክሞ ነው፡፡

እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ምንልክሳልሳዊ

Image

ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል:

(አዲስ አድማስ መጋቢት 20 2006 ዓ.ም)

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኗን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በዚህም መሠረት ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ አሠራሮችን ለማረምና ለማስተካከል ጥረት እያደረገች ቢኾንም ባለሥልጣናቱ ከማን ጋር መሥራት እንዳለባቸው በትክክል አለመለየታቸውንና ግንኙነቱም ሙሰኞችን በአይዟችኹ ባይነት የሚያበረታታ እንደኾነ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡

ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን በዚህ መልኩ ለባለሥልጣናቱ ለማቅረብ ያስገደዳቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎቹ፣ ‹‹ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ ያነሣሣል፤ በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ባሉት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁበት መግለጫቸው ነው፡፡

የመንግሥት የተለመደ እገዛ እንዳላቸው በአጽንዖት የጠቀሱት አስተዳዳሪዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፣ መንግሥት በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ገለልተኛ ኦዲተር መድቦ በማኅበሩ ላይ የሀብትና ንብረት ቁጥጥር የማካሔድ ድጋፉ እንዳይለያቸው ያስተላለፉት ጥሪ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና የቀረበ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ መንገድ ማከናወን በሚገባት ተግባር ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የሚጋብዝና ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥ እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ ከተገኙት የመንግሥት ሓላፊዎች ጋራ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንደተካሔደ በተገለጸው የኹለትዮሽ ውይይት፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በመቃወም ሰበብ የወጣው የአስተዳዳሪዎቹ መግለጫ ዋነኛ ዓላማ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ወስና የምታካሒደውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ሒደት መጋፋት ነው ተብሏል፡፡ መላውን የሀገረ ስብከቱን አድባራት አገልጋዮች ለመወከል የማይበቁ ጥቂት ግለሰቦችን በመያዝ ይደረጋል የተባለው ይኸው እንቅስቃሴም ‹‹የት እንደሚያደርስ እናየዋለን›› የሚሉ ንግግሮች ጭምር ከሊቃነ ጳጳሳቱ የተሰሙበት እንደነበር ምንጮቹ አስታውቀዋል፤ ጉዳዩም በመጪው ግንቦት በሚካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓቢይ መነጋገርያ መኾኑ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡

ከሀገረ ስብከቱ አድባራት የተውጣጡ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎች ያደረጉት ስብሰባ፣ አስተባባሪዎቹ ከፓትርያርኩ ተሰጥቶናል ከሚሉት ፈቃድ በቀር በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዘንድ በይፋ የታወቀና የተፈቀደ እንዳልነበረ ምንጮቹ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንን በሁከትና ሽብር ለሚከሱ በቂ ሕጋዊነትና ውክልና የላቸውም ለተባሉ አካላት ፓትርያርኩ የሰጡትን የስብሰባ ፈቃድ፣ በቅርቡ ማኀበሩ አገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ እንዳያካሒድ ከተጣለበት እገዳ ጋር ያነፃፀሩ ታዛቢዎች፣ ሁኔታው የፓትርያርኩን ርምጃዎች መርሕ አልባነት የሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር መተዳደርያ ደንብ ያለውና ግልጽ ተልእኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር፣ህልውናና አገልግሎት በግልጽ አስተዳደራዊ ጫና ውስጥ መግባቱን እንደሚያመለክት ታዛቢዎቹ ያምናሉ፡፡

ከመዋቅር፣ ከሀብትና ንብረት ቁጥጥር ጋራ በተያያዘ በማኅበሩ ላይ የሚቀርቡት ውንጀላዎች፣ በፀረ አክራሪነት ስም የሚናፈስበትን ፕሮፓጋንዳ በማጠናከር ፖሊቲካዊ ርምጃ እንዲወሰድበት ፍላጎት ያላቸውን አካላት ምኞት በጉልሕ እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡ ማኅበሩ ሃይማኖቱን የሚጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያኑን የሚከባከብና ሀገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ያለውን ዓላማ የሚረዱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናንና የመንግሥት አካላትም የተቃዋሚዎቹን አቋምና መግለጫ በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ትውፊት ውጭ ነው በተባለ የሌላ እምነት አስተምህሮ የተነሳ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መካከልና በደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተገለጸ ነው፡፡

ከኮሌጁ ውጭ ከሚገኙና በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋር የዓላማና የጥቅም ግንኙነት መሥርተዋል በተባሉ ጥቂት ደቀ መዛሙርት አማካይነት በኮሌጁ ውስጥ ከመንጸባረቅ አልፎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው የተባለው ይኸው አስተምህሮ፣ አስተዳደራዊ መፍትሔ እንዲበጅለት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት ጥር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ለኮሌጁ አስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ እስከ አሁን ምላሽ አለማግኘቱ ውጥረቱን የበለጠ እንዳባባሰው ለአዲስ አድማስ የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡

የአስተምህሮው ውዝግብ አፋጣኝ መፍትሔ አለማግኘቱ ከደቀ መዛሙርቱ አልፎ የምክር ቤት አባላትን ለሁለት እንደከፈለ ተገልጧል፡፡ ኮሌጁንና ደቀ መዛሙርቱን በቅንነትና በትጋት ለማገልገል በደቀ መዛሙርቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠውና ከፍተኛ ሓላፊነት የተጣለበት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት፣ ‹‹ከልማቱ ጥፋቱ አመዝኗል›› ያሉት ጸሐፊውና አንድ የአመራር አባሉም ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡

‹‹ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ትውፊት ውጭ የኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲዘራ ድምፀ ተዓቅቦ ከማድረግ ባሻገር ችግር አለባቸው ከሚባሉት ደቀ መዛሙርት ጎን ተሰልፈው ኮሌጁንም ኾነ ሓላፊነት የሰጠንን ደቀ መዝሙር በቅንነት እንዳናገለግል የአንዳንድ መማክርት አባላት ተግባር አውኮናል›› ያሉት ሁለቱ አባላት፤ በዚህ ሳምንት ለኮሌጁ ዋና ዲን ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ የችግሩ ተባባሪ በመኾኑ ከሓላፊነቱ ታግዶ ጉዳዩ እንዲጣራና እምነታቸውና ሥነ ምግባራቸው በተመሰከረላቸው ደቀ መዛሙርት እንዲተካ ጠይቀዋል፡፡

‹‹የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ፣ በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት የሚያራምዱ›› ያሏቸውን ወገኖች አጥብቀው እንደሚቃወሙ የገለጹ የደቀ መዛሙርት ተወካዮች በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ለመጠበቅና ለማስፋፋት የቆመ በመኾኑ አስተዳደሩ፣ በቃል፣ በድምፅና በጽሑፍ የሚቀርቡለትን ማስረጃዎች መርምሮ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡

የአሜሪካን ባለስልጣናት ኢህአዴግን በተመለከተ የሚጠቀሙት ቃልና የድምጻቸው ቃና ተቀይሯል::

ጎልጉል ፦ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።

ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

አቶ መለስ በጓዶቻቸው ቋንቋ “ተሰው” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ተቸግሮ ነበር። ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ፖሊስና ዋንኛ የአገሪቱን ተቋማት ጠቅልሎ የያዘው ህወሃት በቀጥታ አሜሪካ ባደረገችው ጫና ሳይወድ በግዱ አቶ ሃይለማርያምን በጠ/ሚኒስትርነት ለመሰየም ተገደደ። የስልጣን ክፍተቱን በተመለከተ አቻ ድርጅቶችና ህወሃት ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበር “ምደባ” በሚል ኢትዮጵያ በደቦ የሚመሯት አራት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሰየሙላት።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት እንዳሉት አሜሪካ ስጋት የገባት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር። መለስ እንዳለፉ ልዩ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሁኔታውን በመገምገም ስራ የጀመረችው አሜሪካ አሁን አሁን በህወሃት ስትራቴጂ የተሰራው ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ዋንኛ የችግር ምንጭ ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየመከሩበትና የመፍትሔ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው።

“We cannot afford to lose Ethiopia” አሜሪካ ኢትዮጵያን ልታጣት አይገባም በማለት ለጎልጉል የዋሽንግቶን ዘጋቢ የተናገሩት የዲፕሎማት ምንጭ “የአሜሪካን ባለስልጣናት ኢህአዴግን በተመለከተ የሚጠቀሙት ቃልና የድምጻቸው ቃና ተቀይሯል” ሲሉ የጉዳዩን ክብደት አመላክተዋል።

በዋሽንግቶን የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ኢህአዴግን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል። አዲስ አበባም ተወካይ በመላክ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በግል እየተነጋገሩ ነው። በያዝነው ሳምንትም ለተመሳሳይ ስራ አዲስ አበባ የተጓዙ አሉ። እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ የህወሃት ሰዎች ውስጣዊ ችግር እንዳለ አይቀበሉም። በግል ያነጋገሯቸው የሌሎች ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ግን ኢህአዴግ ውስጡ አለመረጋጋትና ስጋት የተሞላው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ አንድ ችግር ቢፈጠር ለማረጋጋት አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ ህዝቡ በተለይ በህወሃቶች ላይ የሚያሳየው ጥላቻ እየተካረረ መምጣቱ፣ በአገሪቱ የሚፈጸመው ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት፣ አፈናውና ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ ተግባራት ተዳምረው ህዝቡን ክፉኛ ማስቀየሙ ያልታሰበ ችግር ሊቀሰቅስ እንደሚችል አሜሪካ መገንዘቧን ያወሱት ዲፕሎማት፣ “ህወሀቶች የቀጠናው የሰላም ምንጮች ስለመሆናቸው ለራሳቸው ምስክርነት ለመስጠት ቢሞክሩም በተግባር የሚታየው ግልባጩ ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ላይ የተተከለው የጎሳ አገዛዝ እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ዲፕሎማት “በጎሳ አስተሳሰብ የተዋቀረው ኢህአዴግ ችግሩ ከገነፈለ ሊቆጣጠረው የሚችል ባለስልጣንና መሪ የለውም። አስተዳዳራዊ ማዕከላዊነት አይታይበትም። በግል የሚወስን ባለስልጣንና ርምጃ የሚወስድ አካል የለውም” ሲሉ የስጋቱን ግዝፈት ያሳያሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ችግሩ ቢከሰት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰቡ አዳጋች እንደማይሆን ይጠቁማሉ። አያይዘውም “አሜሪካ ቸል ብላ ስትመለከተው የነበረውን ጉዳይ አጽንኦት ብትሰጠው አይገርምም” ብለዋል። አሜሪካ ይህንን የምታደርገው ለራሷ ስትል እንደሆነ ያልሸሸጉት ዲፕሎማት አንድ ጥያቄም ጠይቀዋል። “እናንተስ ለራሳችሁ ስትሉ ምን እየሰራችሁ ነው?” ከረጅም ፈገግታ ጋር።

አልቃይዳን ከምንጩ ማድረቅ በሚለው የመለስ ስትራቴጂ ለኢህአዴግ ግብር ስታስገባ የነበረችው አሜሪካ ግብሯን ስትገብር የኖረችው በፔንታጎን ወታደራዊ ውሳኔ መሰረት ነበር። ኢህአዴግም ግብሩ እንዳይቆምበት በአዲስ አበባ ታክሲ ላይና ህዝብ በሚያዘወትርባቸው ቦታዎች ፈንጂ በማፈንዳት ሲጫወተው የነበረውን ድራማ ዊኪሊክስ (ሹልክ ዓምድ) አምባሳደር ያማማቶን ጠቅሶ ማጋለጡ አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ይመስላል ኢህአዴግ የቀድሞውን ጨዋታ የመጫወት እድሉ እንዳከተመ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ባደባባይ የመለስን ስብዕና በመዝለፍ ባልተለመደ መልኩ ተናግረው ነበር።

ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ዲፕሎማት “እናንተስ” በሚል ለሰነዘሩት ጥያቄ ማብራሪያ ተጠይቀው “እኔ ኢትዮጵያዊ ብሆን አገሬን አስቀድማለሁ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። አሜሪካ አማራጭ ማጣቷንም እንደ አንድ ችግር አንስተዋል።

በዲፕሎማቱ አስተያየት ላይ ገለልተኛ ወገኖችን አነጋግረናል። ያሰባሰባንቸው አስተያየቶች “አሜሪካ እዚህ ደረጃ ከደረሰች፣ ኢህአዴግም በዚህ ደረጃ ከተመደበ ተቃዋሚዎች የግል ጉዳያቸውንና ፕሮግራማቸውን ለህዝብ ውሳኔ በመተው ለመጪው ትውልድና ለአገር ሲሉ ከመቧደን በሽታ ሊፈወሱ ይገባል” የሚል ይገኝበታል።

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀናጅቶ መበተን፣ ተደራጅቶ መፍረክረክ፣ ተደላድለው መስለል በተለያዩ ወቅቶች ህዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገዋል። የሚፎካከሩትን ፓርቲ ትተው እርስ በርሳቸው ለተራ ጉዳይ ሲሻኮቱ ዓመታት አሳልፈዋል። በዚህም የተነሳ “አማራጭ የለም” በሚል ኢህአዴግን ማንገስ ግድ እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎች “የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህንን አስተሳሰብ ሰብረው አገር መምራት እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ ህብረት መፍጠር ይገባቸዋል። ይህም ካልሆነ የርስ በርስ ውዝግባቸውን ማቆምና የራሳቸውን የቤት ስራ መስራት ላይ ማተኮር ግዳጃቸው ይሆናል” ብለዋል።

ምሁራን ከተደበቁበት ሊወጡ እንደሚገቡም ያሳሰቡ አሉ። አገር የመምራት፣ በህዝብ የመታመን፣ የህዝብን ይሁንታ ማግኘት እንችላለን የሚሉ ከፊት ለፊት፣ አሁን ከፊት ያለውን ችግር በመጥረግ የወደፊቷን ኢትዮጵያ በመገንባትና መጪውን ትውልድ በማዳኑ ስራ አጋዥ ሃይል ለመሆን መወሰን እንደሚገባቸው በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል። ከሁሉም በላይ ግን “አሁን ካለው ህዝብን ካገለለ ዘመናዊ የመሳፍንት ስርዓት ኢትዮጵያንና ህዝቧን ማሻገር የሚችል ሞገሰ ሙሉ፣ ቅን፣ ከጥላቻ የጸዳ፣ ከሥልጣን ይልቅ የወደፊቷን ኢትዮጵያ አሻግሮ መመልከት የሚችል መሪ ወደ ፊት ወጥቶ በግልጽ ለህዝብ የሚተዋወቅበትን መንገድ የማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ድረገጾች፣ ሬዲዮኖች አገር ወዳድ የመገናኛ አውታሮች አጀንዳ አድርገው ሊወያዩበት ይገባል” የሚለው አስተያየት ሚዛኑን የደፋ ሆኗል።

“…የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም::” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ምላሹን አልቀበልም በማለቱም በፖስታ ቤት ተልኮለታል ህገ መንግስቱ እውቅና የቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ሳይሸራረፍ መተግበሩን እንዲከታተል በአዋጅ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ዓ.ም መነሻውን ፓርቲው ከሚገኝበት ቀበና በማድረግ በአራት ኪሎ አደባባይ በመዞር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በአዋጅ የተሰጠውን ጊዜ ገደብ አሳልፎ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ኦፊሰሩ በደብዳቤያቸው ‹‹በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና ፣የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡››ብሏል፡፡ የአገሪቱ ፓርላማ ‹‹ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ባወጣው አዋጅ ‹‹የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ግዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም››(አዋጅ ቁጥር 3/1983 )በማለት ያወጀውን በአዋጁ ስር የተቋቋመው ጽ/ቤት በማን አለብኝነት በመሻር የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም ብሏል፡፡

አንድነት አዋጁን የጣሰውን ደብዳቤ እንደማይቀበል በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ በመጻፍ በአካል ቢሯቸው በመገኘት ለመስጠት ቢሞክርም በአስገራሚ ሁኔታ ኦፊሰሩ ደብዳቤውን አልቀበልም ብለዋል፡፡
የኦፊሰሩ ድርጊት ህገ ወጥ መሆኑን የተገነዘበው ፓርቲያችን ደብዳቤውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትቶ ከመውጣቱም በላይ በሪኮማንዴ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡ ኦፊሰሩ እየሰሩ የሚገኙት ነገር ህገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘቡም ለፌደራል ፖሊስ፣ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በግልባጭ ደብዳቤው እንዲደርሳቸው መደረጉን የአንድነት የአዲስ አበባ ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው ተናግረዋል፡፡ በህገ ወጥ ደብዳቤ የሚሰረዝ ሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ባለመኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ እንደሚደረግ አቶ ነብዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ Finotenetsanet
Image

Image

ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ዘረኝነት ባታራምዱ የተሻለ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ / ሕወሓት/ ነው፡፤ ዋናው ትግላችንም ሕወሓትን ማስወገድ ነው። እናንተ የትግራይ ህዝብ ላይ አተኩራችሁ አቃቂር ስታወጡ ሕወሓት እናንተን እንደማስረጃ እየተቀሰ በትግራይ ውስጥ ጥላቻን እየዘራ ነው። ስለዚህ ዘር እየጠሩ ዘመቻ አያዛልቅም ለህዝቦች አንድነት እና ፍቅር ተባብረን ብንነሳ መልካም ነው።

በቅኝ አገዛዝ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በአምባገነን ስር አት ውስጥም ባንዳዎች ይፈለፈላሉ ። ይህ የታወቀ ነገር ንው። ውዴታዊ ባንዳነት እንዳለ ሁሉ ግዴታዊ ባንዳነት ከዛ መላመድም እንዳለ ታሪክ ስናገላብጥ አንብበናል። ቢሆንም መልካም የህዝቦችን ታሪክ እየያዝን ለክፉው ታሪክ መቃብር እየማስን እየቀበርን በትግል ወደፊት በመገስገስ በኢትዮጵያ ላይ የተጫነውን የሕወሓት አምባገነናዊ ጁንታ መንግለን መጣል አለብን ።

እደግመዋለሁ !!! ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ድርጅት ይወልዳል ያድጋል ይሞታል፣ህዝብ ግን ለዘላልም ይኖራል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!!ምንሊክ ሳልሳዊ

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው።
ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው። ጎልጉል

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።

ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።

የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡

ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል። ጎልጉል

የበደለ፣ የአገር ሀብት ያባከነ፣ ሕገ የረገጠ ግለሰብ ማጥፋቱ እየታወቀ ይቀጣል ወይስ አይቀጣም ለሚለው ጥያቄ ወሳኙ ማስረጃ መሆኑ እየቀረ ነው፡፡ የፖለቲካ ገጠመኝ ሆኗል፡፡ ይታሰራል የተባለው ሊሾም፣ ተጠያቂ ይሆናል የተባለው ጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡

መልካም አስተዳደር በሕግና በመርህ ደረጃ መከበር አለበት ተብሎ የታወጀ፣ የተነገረ፣ የተለፈፈለት ነው፡፡ በተግባር ደግሞ አቤት ብዬ ሰሚ አገኛለሁ፣ ቅሬታ አቅርቤ ይፈታልኛል የሚል ዜጋ የለም!!!! በዚህ ዙሪያም ጉቦና ጥቅማ ጥቅም የበላይነት እየያዙ ነው፡፡ የአቅም ማነስ ችግር ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች የችግር መፍቻ መድረኮች መሆናቸው ቀርቶ መደበቂያ እየሆኑ ነው፡፡ ‹‹በስብሰባና በሥልጠና ምክንያት ኃላፊ የለም›› የሚል ማስታወቂያ መለጠፍ ነው የቀረው፡፡ ኃላፊ ቢሮው ገብቶ አቤቱታ አንብቦ ችግር መፍታት መርህና ግዴታው መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡

የሕግ የበላይነት እንዲኖር፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የፕሬስ ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ሕገ መንግሥትና ሕጎች አሉን ????????? ከድህነት የሚያላቅቅ፣ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር የሚያሸጋግር፣ የቤት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የትራንስፖርት፣ ወዘተ ችግሮችን የሚፈታ ዕቅድም አለን ???????????

እነዚህ አሉ ማለት ግን ዲሞክራሲ ተረጋገጠ፣ ልማት እውን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመርህ ደረጃ ተግባር ላይ ካዋልናቸው ይጠቅማሉ፡፡ ካላከበርናቸው፣ ከረገጥናቸውና ከጣልናቸው ደግሞ ገጠመኝ ይሆናሉ፡፡ ፍትሕ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ምንሊክሳልሳዊ የፍትሕ መጓደል በሚያሳስብ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በፍትሕ አካላት ውስጥ በአቅምና በአመለካከት ድክመት አለ፡፡ የሥነ ምግባር ጉድለት በትልቁ እየታየ ነው፡፡ በጠበቆች፣ በዳኞችና በዓቃቢያነ ሕግ በኩል አሳሳቢ የሥነ ምግባርና የአቅም ችግር እየተስተዋለ ነው፡፡

በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት መጠናከር እያሳዩ ከመጓዝ ይልቅ እየተልፈሰፈሱና እየተንገዳገዱ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ፍትሕ ማግኘት መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ ጉቦ የአንቀጾች ሁሉ የበላይ አንቀጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ሰላማችን፣ ሉዓላዊነታችን፣ አንድነታችንና ህልውናችን በመርህ ደረጃ ዋስትና ያላቸው መሆናቸው ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ ሆነዋል፡፡ የአገር እና የህዝብ ህልውና ገጠመኝ በመሆኑ ወያነ ደግሞ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በጋራ የዛፍ ላይ እንቅልፉን የሚለጥጠውን ወያነን በማውረድ ህዝባዊ የበላይነትን መቀናጀት የዜግነት ግደታችንን መወጣት አለብን::ምንሊክሳልሳዊ

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!!
ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው::እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው የሚላተሙ የጆተኒ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በላም አለኝ ተስፋ ህዝባችንን አረንቋ ውስጥ እየጨመሩት ነው::

ለጋች አገራት የሚያወጧቸው ሃሰተኛ ጸረ አፍሪካ ሪፖርቶች በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ተገን አድርጎ የተመቻቸው የብሄራዊ ጥቅማቸው ፎርሙላ ስኬት የአምባገነኖችን እድሜ በማስረዘም ህዝብ እንዲጭበረበር የህዝብ ጥያቄዎች እንዲደናቀፉ ለገዢዎቻችን የልብ ልብ ሰቷቸዋል:: ለብሄራዊ ጥቅም አስጊ ይሆናሉ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን እስከማጨማደድ እየዘለቀ በኢጅ አዙህ ህዝባዊ ጥያቄዎች እንዲታፈኑ እየተደረገ አምባገነናዊ አገዛዝን አፍልተውብናል እንሱ ለጋሽ አገራት::

መሰረታዊ ፍላጎቶች እና የአገልግሎት ፍጆታችን በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበት አገር መንግስት ፕሮጀክት ለመጨረስ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ በሚልበት አገር ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የለኝም በሚልበት እና የመንግስት ካዝና ባዶ ሆኖ በዕቃ ግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ከቱጃሮች መንግስት በሚበደርባት አገር ጥቂት ፖለቲካው የወለዳቸው ሃብታሞች እጅግ ብዙ የኢኮኖሚ ድቀት ያፈራቸው ደሃዎች በፈሉበት አገር ምን አይነት የኢኮኖሚ እድገት እንደተመዘገበ አነጋጋሪ ነው:; እስከመቼ የአምባገነኖችን ደጋፊዎች ዉሸት ተሸክመን እንዘልቃለን::

መብራት ውሃ ስልክ ሀገሪቷ ተሰርቶ እና ተበድራ ሳይሆን በተፈጥሮ የታደለችው ጸጋዋ እንደሆነም ያለን ሃብት ይመሰክራል ህዝቡ ያለውን ቴክኖሎጂ ከተፈጥሮ ሃብቱ ጋር አደባልቆ እንዳይጠቀም እኛ እናውቅላቹዋለን የሚሉ የወያኔ አውሬዎች ቀፍድደው ይዘውታል::
በቀላል ሊፈታ የሚችል ችግርን በፖለቲካዋ ሳንካ መተብተብ ምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ህዝቡ አስፈላጊውን የአገልግሎቶች አቅርቦት እንዲያገኝ መደረግ አለበት ብለን ካሁን በፊት ብንጮህም ከቀድሞ በባሰ መልኩ ብሶበት ይገኛል::

በአለማችን በረሃ በተባሉት አገሮች የውሃ አቅርቦት በሰፊው ለህዝባቸው እየሰጡ ሲሆን የተጣሩ ውሃዎች ሳይቀር በርካሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው::በኢትዮጵያችን ግን በተፈጥሮ የታደልነውን ውሃ በፖለቲካ ሹማምንት ልፍስፍስነት ልንጠቀምበት አልቻልንም ትልልቅ እና ገባር እንዲሁም ትንንሽ ወንዞች እና የተፈጥሮ ውሃ ምንጮች በሞሉባት ሃገራችን ህዝብ ውሃ ተጠማሁ ሲል መመልከት አስደንጋጭ ነው::ሃገሪቱ በውሃ ችግር ተውጣልች::የውሃ እጥረት ኖሮን ሳይሆን በአግባቡ አለመጠቀም እና ችግሩን የመፍታት ባህል ስላሌለን ነው::ለጎረቤት አገሮች ውሃ እንሰጣለን እየተባለ ባለበት የፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ እኛ በጥማት ማለቃችን አሳፋሪ ነው::

ወድ መብራት ስንመጣ ደሞ መንግስት ያለ እንኳን ተደርጎ ማሰብ ይከብዳል:: የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መብራት ጠፍቶ ሲመጣ መብራት መጣ ብሎ መጮህ ነው ተብሎ በሰው ሃገር ጋዜጦች እስኪቀለድብን ድረስ ወያኔ በህዝብ ጭንቅላት ጢባጢቦ እየተጫወተች ነው::ይህ እንደገጠመኝ እና እድል የሚታየው የመብራት እቃቃ ጨዋታ በአግባቡ መፍታት እየተቻለ ችግሩንም ማድረቅ እየተቻለ ለምን መዘናጋት እንደሚፈጠር ማስረዳት የሚችል ባለስልጣን አልተገኘም::በኤሌክትሪክ መጥፋትና ሥርዓት አልበኝነት ምክንያት በርካታ ኢንዱስትሪዎች ሥራቸውን እያቆሙ ናቸው፡፡ በርካታ ማሽኖች ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ናቸው፡፡ በመኖሪያ ቤቶች ቴሌቪዥኖች፣ ፍሪጆችና ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እየፈነዱና እየተቃጠሉ ነው፡፡ በመብራት መጥፋት ምክንያትም የየዕለቱ ኑሮ ይዘቱም ገጽታውም እየተበላሸ ነው፡፡ ከመኖሪያ ቤቶች አልፎ ካፌዎችም በመብራት መጥፋት ምክንያት ‹‹ተረኛ መድኃኒት ቤት›› እየመሰሉ ነው፡፡ ሻይ ታዞ ‹‹ይቅርታ መብራት የለም›› የሚል መልስ መስማት የተለመደ እየሆነ ነው፡፡ እውነት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ፣ ለኢንዱስትሪዎቿም ሆነ ለሁሉም ዓይነት እንቅስቃሴዎቿ የሚሆን በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል የላትም? አይኖራትም? አላትም ይኖራታልም፡፡ በቂ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች የንፋስ የኃይል ማመንጫዎች የፀሐይ የኃይል ማመንጫ አቅም የጂኦ ተርማል የኃይል ማመንጫ አቅምም አለ፡፡ እንኳን ለራስዋ ለሌሎች አገሮችም የሚሆን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ዕምቅ ሀብት አላት፡፡ ኦኖም ግን በአግባቡ የሚያዳርስ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተቷት ህዝቧ አስፈላጊውን የአገልግሎት መብቶች እና አቅርቦቶች ሊያገኝ አልቻለም::በሃይል ግንባታ ሰበብ በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ወደ ስልክ እና ኢንተርኔት ኔትወርክ ስንመጣ በጸሎች የሚገኝ ያውም ተለቅሶ መፍትሄም የጠፋለት ጉዳይ ከሆነ ቆይቷል:: በአለማችን በስፋት ይህን የኔትዎርክ ችግር ተቀርፎ ባለበት ሰአት የወያኔ ባለስልጣናት ግን በአደናባሪዎቻቸው በኩል በፋይበር ቅንጠሳ እና በህንጻ መብዛት ቢያሳስቡም ከነሱ ቀድሞ ንቃተ ህሊናው ያደገውን ህዝብ ግን ሊሸውዱት አልቻሉም:: ያው እንደለመዱት በጠበንጃ እና ሽብር በመንዛት ዝም አሰኝተውታል:: የወያኔ መንግስት የህዝብን የአገልግሎት አቅርቦት ጥያቄዎች መፍታት እየቻለ እንዳይፈቱ በማድረግ በሚፈጸም አሻጥር እራሱ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሊገነዘበው አልደፈረም:: የመልካም አስተዳደር ብልሃት የሞላበት አመራር ህግ አክባሪ እና አስከባሪ ባለስልጣንትን ለማግኘት ሁላችንም በትግሉ ላይ እንረባረብ።ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል።

“ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
goolgule.com/

ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

Image

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም›› /አቶ ስብሓት ነጋ/
(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

አክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

* * *

ሐራዊ ማስታወሻ፡-

*አቶ ስብሓት ወጣቱ ሲሉ የጠሯቸው የስብሰባው ተሳታፊ ከከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ከሚገኘው ሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴን ነው፡፡ እኒህ ስመ መነኮስ እንደ በጋሻው ደሳለኝ ላሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን ዐውደ ምሕረት በመፍቀድና ምእመኑን ሰላም በመንሳት በወረዳው የማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ያደረጉ፣ ከትምህርቱም ከግብረ ገቡም የሌሉበት ግለሰብ ናቸው፡፡

መንግሥት አካሂደዋለኹ በሚለው የፀረ አክራሪነት ትግል አጋር መስለው የተጠጉ ግለሰቦች [የደብር አስተዳዳሪ ለማሾም 60,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 60 ጎራሽ የተባሉትንና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነሥተው ወደ መ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ሓላፊነት የተዛወሩትን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢን ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያን ይጨምራል] ያላቸውን አግባብነትና የሚሰጡትን መረጃ ትክክለኛነት (ቅንነት) ማጤን ይገባዋል፡፡

አቶ ስብሓት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያራምዱትና በልዩ ልዩ ዘገባዎች ሲገለጽ የቆየው አቋማቸው በተለይ ከ፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ በሚገባ ይታወቃል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም?›› ማለታቸው በአባባል ደረጃ ተገቢ ቢኾንም እርሳቸው የጠቀሱትን ሕገ መንግሥታዊ መብት ለማስከበር ቢያንስ በግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም በመጠኑ የሞከሩ ብፁዓን አባቶች ምን እንደደረሰባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሊቃነ ጳጳሳቱን ልናመሰግናቸው ፈልገን ወይም አቶ ስብሓት እንዳሉት ‹‹በሩን ከፍቶ ያንቀላፋ የለም›› ለማለት አይደለም፡፡ በሌላ መድረክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኹኔታው ምሬታቸውን በገለጹበት ወቅት ‹‹ብትሰየፉስ!›› ያሏቸው የመከራቸው ፍጻሜ ገና መኾኑን ስለሚያሳይ፡፡

አቶ ስብሓት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱና በቀድሞው ፓትርያርክ መካከል የተደረገው የውስጥ ትግል በተጧጧፈበት ወራትና ከዚያም ወዲህ በእጅጉ ይጠሏቸው ነበር የሚባሉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው ለማስወገድ ማኅበሩ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ካገኘበት የአገልግሎት ዓላማና ስልት ውጭ ሚና ለመስጠትና መሣርያ ለማድረግ የገፋፉበት ኹኔታ በማኅበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደነበር ይነገራል፡፡

ግፊታቸው በወቅቱ በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች መካከል ልዩነት ፈጥሮ እንደነበር የሚገለጽ ቢኾንም ተቀባይነት ያገኘ ግን አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የቤተ ክህነት ዕዳ ነው›› በማለት ‹‹የተቃዋሚ ፖሊቲካ መድረክነት›› እንደሚታይበት ወዘተ ባለፈው ዓመት የፍትሕ ጋዜጣ ጽሑፋቸው የሰነዘሩበት ሒስም የዚያ ማወራረጃ እንደኾነ ይታሰባል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ዓላማና ከሚፈለግበት አገልግሎት አኳያ በድክመት የሚተችበትና ገና ብዙ እንደሚቀረው የብዙዎች እምነት ቢኾንም በሰሞኑ ስብሰባ አቶ ስብሓት ወጣቱ ባሏቸው አባ ዮናስ ጥቆማ በኩል አልፈውና የአባ ዮናስን ንግግር አጉነው ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰጡት አስተያየት ወይ አቅጣጫ መነሻው ጥላቻ የወለደውና ቅንነት የጎደለው መረጃ እንደኾነ የመረጃው ጠቋሚ ሰው ስለ ማኅበሩ ባላቸው አቋምና በወረዳቸው ከማኅበሩ አባላት ጋራ ባላቸው ግንኙነት መረዳት አያዳግትም፡፡

መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

አባ ዮናስ ከእውነት የራቀ ጥቆማቸውን፣ አቶ ስብሓትም በዚሁ ላይ የተመሠረተ አስተያየታቸውን/አቅጣጫቸውን በሰጡበት መድረክ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ናትናአል ፣ አቡነ ኄኖክ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስ በአጸፋ የመናገርና ምላሽ የመስጠት ዕድል ተነፍገዋል፡፡ ይኸው የስብሰባው አካሄድ ከአዳራሹ ውጭ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ አጠያይቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ቤተ ክርስቲያን ከአክራሪነት አንጻር የተገለጸችበትንና ማኅበሩን አስመልክቶ የተሰነዘሩ ሐሳቦችን መንበረ ፓትርያርኩ በቀላሉ እንደማይመለከተውና በጥብቅ እንደሚነጋገርበት ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚኒስቴሩ ሓላፊዎች እንዳሳሰቧቸውም ተገልጧል፡፡

Hara tewahdo

Image

ታላቁን ገመና የደበቀው የ“የንጉሡ ገመና”
የመጽሐፉ ርዕስ – የንጉሡ ገመና
የገጽ ብዛት – የ172
የታተመበት ዘመን – 2006 ዓ.ም
የሽፋን ዋጋ – ብር 49.75
አሳታሚ – ግርማ ለማ
የመጽሐፉ ይዘት ከታሪክ ዘውግ የሚመደብ ሆኖ አሳታሚው ሁለት ምንጮችን ተጠቅመው ነው ያሳተሙት፤ እነሱም ለ14 ዓመታት በንጉሥ አሽከርነት ያገለገሉት የአቶ ሥዩም ጣሰው መንዜው የግል ማስታወሻና የልዩ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ቀይ ሽብርን አስመልክቶ ያሳተመው “ደም ያዘለ ዶሴ” የተሰኙ መፃሕፍት ናቸው፡፡
በተለይ አቶ ሥዩም ከልጅነታቸው ጀምረው በቤተመንግሥት ያደጉና ለድፍን 14 ዓመታት በንጉሡ አሽከርነትና አልባሽነት ያገለገሉ በመሆናቸው የንጉሠ ነገሥቱን ጓዳ ጐድጓዳ፤ የአሽከሮችን፣ የደንገጡሮችንና የወቅቱን ባለሥልጣናት ጠቅላላ ሁኔታ የማየት ብቻ ሳይሆን የማወቅ ዕድሉ ስለነበራቸው ማስታወሻቸው ተአማኒነት ይኖረዋል። አቶ ሥዩም ንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣናቸውን ተቀምተው መጀመሪያ በቤተመንግሥታቸው ቀጥሎም በ4ኛ ክፍለ ጦር እስረኛ እስከሆኑበት ድረስ ንጉሡን በታማኝነት አገልግለዋል፤ በደርግ ዘመን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኖረው ኢህአዴግ ሲገባ በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ከጠባቂዎች አምልጠው ራሳቸውን ማጥፋታቸው ይነገራል፡፡ ወደ መጽሐፉ እንመለስ፡፡
አሳታሚው ግርማ ለማ፤ በምስጋና ገጹ ላይ የጽሑፉን ዋና ቅጅ (ኦሪጅናል) የሰጠው “በያን ናስር” የተባለ ሰው መሆኑን ጠቅሷል፤ ግን በያን የሥዩምን ጽሑፍ እንዴት እንዳገኘው ወይም የሥዩም ወኪል ይሁን፤ የገለጠልን ነገር የለም፤ የተገኘበት መንገድ ቢጠቀስ በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሥዩም የሞተው በድንገት ነው፤ የተያዘውም ሳያስበው ቤቱ በታጣቂዎች ተከቦ ነው፡፡ ስለዚህ ሃሳባችንን ወደአልተፈለገ ጥርጣሬ እንዳያመራን ግርማ ረቂቁን እንዴት እንዳገኘው ቢገልጥልን መልካም ነበር፡፡ የተጻፈልን ታሪክ ነዋ! ታሪክ ያለአስተማማኝ ማስረጃ ሊታሰብም ሊጻፍም እጅግ ይከብዳል፡፡
መጽሐፉ የምስጋናና የመግቢያ ገጾችን ሳይጨምር፣ በዘጠኝ ምዕራፎች የተዋቀረ ነው፡፡ ስምንቱ ከስዩም ጣሰው ማስታወሻ የተወሰዱ ሲሆን ዘጠነኛው ምዕራፍ “ደም ያዘለ ዶሴ” ከተባለው መጽሐፍ የተገለበጠ ነው፡፡
የመጽሐፉ ጠንካራ ጐኖች
መጽሐፉ በንጉሡ ጓዳና ቢሮ ውስጥ ስለነበረው እውነት የገለጠልን በመሆኑ፣ የንጉሠ ነገሥቱን አጠቃላይ ሰብዕና ለሚያጠና ሰው ትልቅ የታሪክ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ንጉሡ በካህናትና ባለሥልጣናት ዘንድ ተፈርተው ይከበሩ ስለነበር፣ ድምሩ ህዝብም አባቱን እየተወ “ኃይለሥላሴ ይሙት” በማለት በስማቸው ይምልና ይገዘት ነበር፡፡ ግን እንደ ሥዩም ጣሰው ጓዳቸውን ገብቶ የማየት ዕድል ቢገጥመው ኖሮ ምን ያህል ሲታለል እንደኖረ ይገባውና ከልቡ ይቆጭ ነበር ያሰኛል፡፡ ለማንኛውም የመጽሐፉን ጠንካራ ጐኖች በአምስት ከፍያቸዋለሁ፡፡
ገመና አንድ
ንጉሡ ተደባዳቢ ነበሩ
ንጉሡ አሽከሮቻቸውን ይደበድቡ ነበር፤ “…የፀጉር ቅባት ፓንተን ሳቀርብላቸው ቀና አሉ፤ አዩኝ፡፡ አሰቡ አሰቡና ‘ማታ ማነው ፍራፍሬውን የደገሰው’ ብለው ጠየቁኝ፡፡ እኔም ራሴ መሆኔን ነገርኋቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ብድግ አሉና ተያያዙኝ፡፡ እስከሚደክማቸው ድረስ ደበደቡኝና ቁጭ ብለው ፀጉራቸውን አበጠሩ፡፡ ክራባታቸውን አሰሩና ተነሱ። ልብሳቸውን ለብሰው ሲጨርሱ ጠሩኝ፡፡ እኔም አቀርቅሬ ተጠጋሁ፡፡ አስጐነበሱና እስከሚበቃቸው ወገሩኝና እየተሳደቡ ወደ ቁርሳቸው ሄዱ” (ገፅ 11-12)
ይህን አይነት እርግጫና ጥፊ ለሥዩም አዲስ አልነበረም፤ በየጊዜው ይገረፋል፤ የስድብ ውርጅብኝ ይዘንብበታል፡፡ ሁለት ቀን ብቻ ከተገረፈ በኋላ ብር እንዲሰጠው አድርገዋል፤ ይህ አንድም ምሥጢራቸው እንዳይወጣ ማባባያ ነው፡፡ አለዚያም ካሣ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሆኖም የሥዩም (አሽከርና የታሪኩ ፀሐፊ መሆኑን አንዘንጋ) ትልቁ ፈተና ከንጉሡ ዱላ ይልቅ የሴት አሽከሮች በእሱ ላይ ማደምና ከባለሥልጣናት ጥርስ ውስጥ ማስገባት ነበር ትልቁ ፈተና የሆነው። ለዚያ ሁሉ እርግጫ፣ ጥፊና ዱላ ሰበቡ ንጉሡ የገረዶችንና የአሽከሮችን ወሬ ስለሚሰሙ ነው፡፡ (ገፅ 14)
ንጉሡ ወሬ ይወዳሉ፤ የሆነ ያልሆነን ሁሉ የሚቀላምድላቸውን ሰው ያስጠሩትና ምንም ሳያጣሩ የተወራበትን ሰው ራሳቸው ይገርፋሉ፤ ካስፈለገም ግዞት ይልካሉ፡፡ (ገፅ 21 እና 24)
ገመና ሁለት
ንጉሡ ሴሰኛ ነበሩ
ንጉሡ ሴት በጣም አብዝተው ይወዱ ነበር፤ በዚህ የተነሳ ከጽዳት ሠራተኞች፤ ከአበሻ ወጥ ቤቶች፣ ከእንጀራ ጋጋሪዎች፣ ከቅንጬ ቤቶች፣ ከሴተኛ አዳሪዎች፣ ከሆስተስና ከባለ ትዳር ሴቶች ጋር ይቀብጡ ነበር፡፡ “ሴቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የሚገቡት ቀን ከምሳ መልስ እረፍት በሚያደርጉበት ጊዜ ከ8-10፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ጃንሆይ ገብተው ከተኙ በኋላ ትንሽ ቆይተው ደወል ይደውላሉ፡፡ በዚያ ጊዜ በዚህ ነገር የተለየ ባለሟል የሆኑ አሽከሮች በተራቸው ይገቡና “ዕገሊትን ጥራ” ሲባል ይጠራል፡፡ ምን አልባት እርሱ ከተጠራችው ሴት ጋር ሽርክና ከሌለው ወይም ከምትወስደው ገንዘብ በብዛት ካላካፈለችው “እርሷ አሁን የለችም” በማለት የርሱ ሽርክ በየጊዜው ብዙ ገንዘብ የምትሰጠውን ሴት “ዕገሊት አለች፤ እርሷ ከሥራዋ ላይ አትጠፋም” በማለት ይቀላምድና ይጠራል፡፡ ሲገቡና ሲወጡ የተለየ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ሴቶቹ በሚያሳዩት መለዋወጥ የተቀረው ሰው እዚያ ቦታ እንደደረሰች ይገባዋል” (ገፅ 51)
“ቢሮ የሚደረገው ደሞ ሌላ ነው፤ ቢሮ በሚሠሩበት ጊዜ ረፈድ ሲልና አንዳንድ ባለሥልጣኖችን ካነጋገሩ በኋላ ገለል ብለው ቢሮ አጠገብ ካለው መኝታ ቤት ጐራ ይላሉ፡፡ ከዚያም በዚያ አካባቢ ከሚሠሩት ሴቶች ውስጥ የፈለጓትን አስጠርተው ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ ወደ ቢሮአቸው ይገባሉ፡፡ …ሆስቴሶችንና ሌሎችን ደግሞ እምድር ቤት ካለው ቢሮ ነው የሚያገኙአቸው” (ገፅ 51)
ይህ ሁሉ ሲሆን እንደየሴቶቹ የንቃት መጠን ዛቅ ያለ ገንዘብ ይከፈላቸዋል፤ ከሥራ ቤት፣ እንጀራ ቤትና ወጥ ቤት ለሚመጡት ሴቶች የሚከፈላቸው አነስተኛ ገንዘብ ሲሆን ለጽዳት ሠራተኞችና ለሌሎች ሴቶች ግን ከ70-80 ሺህ ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ ሴቶቹ ደግሞ ወደ ንጉሡ ላቀረባቸው ሰው (ደላላው) ከ5-10 ሺህ ብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ ነበረባቸው። በዚህ የተነሳ ከንጉሡ ጋር የተገናኙ ሴቶች ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቆንጆ ቪላና ዘመናዊ መኪና ይገዙ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እንዲያውም ፖለቲካዊ ሥልጣኑን ተቆጣጥረው የፈለጉትን ያስሾሙ ያስሸልሙ፤ የጠሉትን ደግሞ ያሰቃዩት ነበር (ገፅ 51)
አንዳንድ የንጉሡ ውሽሞች በጣም ቀበጦች ስለነበሩ በመንግሥት ወጭ፣ አስተርጓሚ ጭምር ተመድቦላቸው ለሽርሽር ፈረንጅ አገር ይሄዱ ነበር። በጣም የሚያሳዝነው ግን ንጉሡ የባለቤታቸውን የዕቴጌ መነን አስፋውን ጌጣጌጥ ሳይቀር ለውሽሞቻቸው መስጠታቸው ነው፡፡ ለአንዳንድ ውሽሞቻቸውም ቋሚ ደሞዝ ተቆርጦላቸው የቤተ መንግሥት አሽከሮች በየወሩ እቤታቸው ድረስ እየሄዱ ይከፍሉ ነበር፡፡ (ገፅ 56)
ይህ ድርጊት ያንገበገበው ሥዩም “ኢትዮጵያ በተለይ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ስትገዛ የኖረችው በንጉሠ ነገሥቱ ሳይሆን በእልፍኝ አስከልካዮች፣ በጥቂት የእልፍኝ አሽከሮችና በገረዶች ነበር፡፡ …ቤተመንግሥቱ ቤተመንግሥት መሆኑ ቀርቶ ፍጹም የሰይጣን ቤት ሆኖ ነበረ” ሲል ትዝብቱን አስፍሯል። (ገፅ 20)
ገመና ሶስት
ንጉሡ አይጾሙም ነበር
ንጉሡ አክሱም ጽዮንንና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን ስለአሠሩ ካህናት ያወድሷቸዋል፤ ይሰግዱላቸዋል፡፡ “አቤቱ ፍርድን ለንጉሣችን ስጠው” እያሉም ዘወትር ይፀልያሉ፤ እንደ ጻድቃንና ሰማዕታት በመቁጠርም መልክአ ኃይለሥላሴ ደርሰውላቸው ነበር፡፡ ሆኖም ንጉሡ የክርስቲያንን ህግና ሥርዓት በመጣስ፣ አርብና ረቡዕን እንዲሁም ሌሎች አጽዋማትን አይጾሙም ነበር፡፡ (ገጽ 25 እና 34)
ገመና አራት
ንጉሡ ጠንካራ ሰራተኞችንና ታማኞችን አይወዱም ነበር
“ግርማዊነታቸው የሚወዱት ሰው ፈጣን፣ አጭበርባሪ፣ አሳባቂ፣ በዕውቀት ያልበሰለ፣ እርሳቸውን አምታቶ የሚያታልላቸውን ሰው በጣም ይወዱታል፡፡ የጥቅም ተካፋዮቻቸው በሙሉ በዕውቀት ያልበሰሉ፣ የሰውን መብት በፍጹም ያልተረዱ፣ ሰውን ሸጠው ለመክበር ብቻ ጽኑዕ ዓላማ ያላቸው፣ ለኔ እንጂ ለኛ የሚል መንፈስ ፈጽሞ የሌላቸው ጨካኞች፣ ሰው በችግር ሲሰቃይ ሲያዩ ከማዘን ይልቅ መደሰትን የሚመርጡ ከንቱዎች ናቸው፡፡
“ግርማዊነታቸው አጥብቀው የሚጠሉት ሰው እውነትን በጣም አድርጐ የሚወድ፣ ዘወትር የሚከራከራቸው፣ በእውነት ፍጹም በሆነ መንገድ የሚወዳቸው፣ ሲዋሹ የሚያስተባብላቸው፣ የሚታሙበትን ነገር እንዲተው የሚነግራቸው፣ የማይንቀዠቀዥ፣ አዋቂ ሰው በፍጹም አይወዱም” (ገፅ 31) ይለናል፤ ሥዩም በ14 ዓመት የአሽከርነት ዘመኑ የታዘበውን ሲያካፍለን፡፡
ገመና አምስት
ንጉሡ ስስታም ነበሩ
ንጉሠ ነገሥቱ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገርና እጅግ ብዙ ህዝብ የመግዛታቸውን ያህል ስስታቸውም ያን ያህል አሳፋሪ እንደነበር በመጽሐፉ ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል፡፡ በልጅነት ዘመናችን የምናውቃቸው ንጉሥ፤ በየቦታው ሲዘዋወሩ ብር እንደጥሬ እየበተኑ የሚሄዱ መሆናቸውን ነበር፡፡
ሥዩም የሚያውቀውን እውነት ሲነግረን ግን ስስታቸው በጣም የወረደና ለማመን የሚያስቸግር ሆኖ እናገኘዋለን “…በተለይ ከኬኩ ትንሽ በቄንጠኛ አኳኋን ቆርሰው ከበሉ በኋላ በምልክት አድርገው በጥንቃቄ እንዲቀመጥ ይናገራሉ፡፡ በማግስቱ ሲመጣ ትንሽ ለውጥ ከታየበት “ማነው የተጫወተበት” በማለት ማሰቃየት ነው፡፡ አንድ ኬክ ከሶስት እስከ አምስት ቀን ድረስ እየተመላለሰ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ ሐሙስ ቀን ተጀምሮ እንደሆነና ቅዳሜ ደብረዘይት ቢሄዱ አብሮ ይሄዳል፤ ማሩንም በጣም አድርገው ይቆጣጠራሉ፡፡ ከማስቀመጫው ብልቃጥ ውስጥ ትንሽ ጐድሎ ያገኙት እንደሆነ “እንደፈለጋችሁ ትጫወቱበታላችሁ” ብለው መለብለብ ነው” (ገፅ 33) ሲል ያየውን ትዝብት ያካፍለናል፡፡
ከዚህ ሌላ መኝታ ቤታቸው በስጦታ ዕቃዎች፣ በቸኮላት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ስለሚሞላ ዕቃ ቤት ይመስል ነበር፤ እንዲያውም አትክልትና ፍራፍሬው፤ እንዲሁም ቸኮላትና ኬኩ እየተበላሸ የመኝታ ቤታቸውን ሽታ ያበላሸው ነበር፡፡ (47፣ 116፣ 117)
ከመጽሐፉ ውስጥ በጣም የገረመኝ ቢኖር (ገፅ 149) ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ለንጉሡ ልክ “ልዩ ካቢኔ” ይባል እንደነበረው የስለላ ተቋም፣ በየቀኑ ለንጉሡ ደብዳቤ ይልኩ የነበሩ መሆናቸው ነው፤ ለመሆኑ ቀኛዝማች ተሥፋን ከንጉሡ ጋር ያውም በየቀኑ የሚያገናኛቸው ምን ብርቱ ምሥጢር ነበር ይሆን እንድል አድርጐኛል፡፡
የመጽሐፉ ድክመት
መጽሐፉ ከላይ በመጠኑም ቢሆን የነካካኋቸውን ጉዳዮች የዓይን ዕማኙን ሥዩም ጣሰውን ዋቢ አድርጐ የመቅረቡን ያህል ሌላ ድክመት እንዳለበትም መዘንጋት አያሻም፡፡
አሳታሚው በመግቢያው ላይ “አሽከር ሥዩም (አፈሩን ገለባ ያድርግለትና) በሰነዱ ውስጥ ጽሑፉን ለንባብ ሳያበቃው እንዳይሞት አምላኩን የተማጸነበት ፀሎት አለ” ብሎናል፡፡ ግን ይህንን ከሰነዱ ውስጥ አናገኘውም፡፡ ይህ የሚያሳየን የሥዩም ሰነድ የተነካካ ወይም የተቆራረጠ ፍሬ ነገር አለው ማለት ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ አንድ አካል ሲቆረጥ ሌላውን ምሉዕ እንደማያደርገው ሁሉ የሥዩም ጽሑፍም የቋንቋ አርትኦት ብቻ ተደርጐለት መታተም ነበረበት፡፡
ሌላው ከወሲብ፣ ከንዋይና ከሃይማኖታዊ ገመናቸው ይልቅ የንጉሱ ፖለቲካዊ ገመና ቢታከል ኖሮ ጽሑፉን ተወዳጅ ያደርገው ነበር፤ ሰዎችን በምሥጢር መግደልና ማስገደል፣ በፍርድ አካባቢ የነበረው ሸር ሁሉ ሊገለጽ በተገባ ነበር፡፡ ይህን አይነቱን ታላቅ ገመና ሥዩም ሳይነካካው አልቀረም፤ ግን በመጽሐፉ ላይ አናገኘውም፡፡ ይህ ደግሞ ታላቁንና ለ44 ዓመታት የኖሩበትን ገመና ምስጢር አድርጐብናል፡፡ ከገጽ 141 ጀምሮ እስከ ገጽ 172 ያለውና “ደም ያዘለ ዶሴ” ከሚለው መጽሐፍ እንዳለ ተገልብጦ የቀረበልንም የመጽሐፉ ትልቅ ድክመት ነው፡፡ እንደ ትርፍ አንጀት የተለጠፈውን 32 ገጽ ከዋናው መጽሐፍ “ደም ያዘለ ዶሴ” ላይ አንብበነዋል፤ እዚህ ላይ መደረቱ ለምን አስፈለገ?
addis admass newspaper

Image

በአሜሪካ፣ በፈረንሳይና ቤልጂየም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ነበራቸው
የ25 ሚሊዮን ዶላር ባለፀጋ ነበሩ – ወደ ቢሊዬነርነት ተጠግተዋል
ቤተ-መፅሃፋቸው ራሳቸው ባሰባሰቡት 10ሺ መፃህፍት የተሞላ ነበር

በሳምንቱ ማጠናቀቂያ ግድም “ጮማ” የሆነ መረጃ እጄ ገባ፡፡ አንድ ወዳጅ ነው መረጃውን ከባህር ማዶ በኢሜይል ያሻገረልን፡፡ The New York Times የዛሬ 105 ዓመት፣ አፄ ምኒልክ ሲሞቱ ነው ዘገባውን ያወጣው – ኖቨምበር 7 ቀን 1909 ዓ.ም፡፡ “ንጉስ ምኒልክ እዚህ ኢንቨስትመንት አላቸው” በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍ፤ከአቢሲኒያ የተመለሰውን የቤልጂየም አሳሽ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ ቃለመጠይቅ በማድረግ የተጠናቀረ እንደሆነ ኒውዮርክ ታይምስ ይገልፃል፡፡ የሚታወቁትን ታሪኮች እየዘለልኩ “ጮማ ጮማ” የሆኑትን መረጃዎች ነው የማቀብላችሁ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ከመዘጋቱ በፊት በዚህ በአዲሱ የአፄ ምኒልክ ታሪክ ላይ ትንሽ ጥናትና ምርምር ቢያካሂድ ትክክለኛው ታሪክ (ያልተጭበረበረው ማለቴ ነው!) ለትውልድ ይሸጋገራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “የለም! የአፄ ምኒልክን ጉዳይ አጥንቼ ፋይሉን ዘግቻለሁ” የሚል ከሆነም እንዳሻው፡፡ የኒውዮርክ ታይምስ መረጃ ግን የሚያወላዳ ዓይነት አደለም፡፡ ለመሆኑ እኚህ የጥቁር ህዝብ ኩራት፣የአድዋ ጀግና—–አዳዲስ ገድሎች ምን ይሆኑ? (የተጭበረበርነው ታሪክ ማለት ነው!)
ባሮን ዲ ጃርልስበርግ ለጋዜጣው እንደተናገረው፤ ምኒልክ ከሌሎች የአህጉሪቱ ነገስታት ጨርሶ የተለዩ መሪ ነበሩ፡፡ በዲፕሎማትነት፣ በኢንቨስተርነት (ፋይናንሰር)፣ በተዋጊነት የሚስተካከላቸው አልነበረም፡፡ በተዋጊነትና በዲፕሎማትነት ያላቸውን ብቃትና ዋጋ ያስመሰከሩት ጣልያን በአቢሲኒያዎች ድል በተነሳች ወቅት ነበር ይላል – ጃርልስበርግ። በመጨረሻዎቹ የንግስና ዘመናቸው ግን ምኒልክ ይበልጥ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው እንደታወቁ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
የንግስና ዘውድ ከመድፋታቸው ቀደም ብሎ በወጣትነት ዘመናቸው የኢንቨስትመንት ዝንባሌ እንደነበራቸው የሚያስታውሰው ዘገባው፤በዚያ እድሜያቸው በፈረንሳይና ቤልጂየም የማዕድን ማምረቻዎች ውስጥ ቀላል የማይባል መዋዕለ ንዋይ አፍስሰው ነበር ይለናል፡፡ ከንግስናቸው በኋላ ግን አገር በማስተዳደር ሥራ በመወጠራቸው ከኢንቨስትመንቱ ተስተጓጉለው እንደነበር የኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
“ዛሬ የአቢሲኒያው ገዢ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማስፋፋት በአሜሪካ የባቡር ሃዲድ ሥራ ላይ ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻ አላቸው” ሲል አሳሹ የንጉሱን ወቅታዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ገልጿል፡፡
አፄ ምኒልክ በአሜሪካ እንዲሁም በፈረንሳይና ቤልጂየም ያላቸው አክስዮንና ኢንቨስትመንት ሲደማመር ከ25 ሚሊዮን ዶላር የማያንስ የግል ሃብት እንደነበራቸው ይገመታል ብሏል- አሳሹን ጠቅሶ የዘገበው ጋዜጣው፡፡
“እኚህን ጥቁር የአቢሲኒያ ገዢ በተመለከተ በእጅጉ የሚያስደንቀው ጉዳይ ሁለ-ገብነታቸው ነው” ሲል የሚያደንቀው የቤልጂየሙ አሳሽ፤ንጉሱ የተዋጣላቸው ቋንቋ አዋቂ ነበሩ ይላል – ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ጣልያንኛ አቀላጥፈው ይናገሩ እንደነበር በመጥቀስ፡፡ ሁለመናቸውን ለአገራዊ ጉዳዮች ለመስጠት ቢገደዱም አዲስ የወጡ የአውሮፓ የስነጽሑፍ ስራዎችን ለመቃኘት ግን ጊዜ አያጡም የሚለው ጃርልስበርግ፤ ብዙ ጊዜ አዲስ የአውሮፓ ደራሲ ስም ሲጠቀስ እምብዛም አይደናገራቸውም ነበር ብሏል፡፡
እሳቸውን ከሁሉም በላይ የሚያኮራቸው ራሳቸው ባሰባሰቧቸው 10ሺ መፃሕፍት የተደራጀው ቤተመፅሃፋቸው ሲሆን መፃህፍትን በተመለከተ ዋነኛ ትኩረታቸው በአፍሪካና በእስያ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ላይ የሚያጠነጥኑ ሥራዎች ነበሩ ይላል – ለኒውዮርክ ታይምስ ምስክርነቱን የሰጠው ባሮን ዲ ጃርልስበርግ፡፡ ለካስ ምኒልክ ወደው አይደለም– ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሥልጣኔ፣ ዘመናዊ አስተዳደር ወዘተ—-ሲሉ የኖሩት፡፡ (የንጉሱን ታሪክ ተጭበርብረናል!?)

addis admass amharic newspaper

ምንሊክ ሳልሳዊ:- ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ ባለስልጣኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ያልታሰበና ያልተጠበቀ ግጭትና ችግር በአገራችን ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለ ነው::ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት ተብላ ትጠቀሳለች እንጂ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጣሉ፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጋጩ፣ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ተባሉ፣ ወዘተ የሚል አንሰማም ነበር፡፡

አሁን በዘመን ወያኔ በመስጊድም በቤተክርስቲያንም አካባቢ ይህን እየሰማን ነው፡፡ የህዝብን አንድነት ለመናድ የሚፈልገው ገዢው ኢህኣዴግ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት እና መተራመስን ለመፍጠር ፕሮፓጋንዳውን በስፋት እየነዛ ይገኛል::በምእራብ ኢትዮጵያ ያልተሳካውን በምስራቅ ኢትዮጵያ ለመድገም አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል::ይህ መንግስታዊ ሽብር አደጋ አለው::ድሮ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ለማስታረቅ ሩጫ ነበር፡፡ አሁን ለማባባስ የሚሯሯጥ ወያኔያዊ ኃይል እንዳለም በግልጽ እየታየ ነው፡፡ መፍትሔ ከማስገኘት ይልቅ የበለጠ ብጥብጥ እንዲከሰት የመንግስታዊ አካላት ስውር እጆች ግፊት እየበዛ ነው፡፡

የኑሮ ውድነት በህዝቡ ላይ ተደራርቦ ከጭነት ልክ በላይ እየሆነ ነው፡፡ ብር እየመነመነችና እየከሳች በመሞት በየቀኑ የቀብሯ ጥሩንባ እንደተነፋ ነው፡፡ የሃገራሽን ገንዝብ ብር በራሷ ግሽበቱ ተሽኖባት አትክልትና ፍራፍሬን ፣ ስንዴና ጤፍን፣ ትራንስፖርትና ልብስን፣ የላስኪት ቤትን እና የቤት ኪራይን፣ የተማሪውን ደብተርና ስክሪፕቶን መጋፈጥ ተስኗታል፡፡ የኑሮ ውድነት የሚያስከትለው የወንጀል ድርጊት አለ፡፡ ኑሮ ውድነቱ ወንጀልን ወልዷል::ሴቶች እህቶቻችን እድሜ እና የስራ ሁኔታ ሳይለይ ስጋቸው በመሸጥ ስራ ላይ ሲሰማሪ ከተማሪ እስከ ባለትዳር ከሕጻናት እስከ አዛውንት የሚያቀርቡ የወሲብ ደላሎች በሃገሪቱ ከትመዋል::ይህም ዋነኛ አደጋ ነው::

ለፖለቲካው እና ለስልጣኑ አትኩሮት የሚሰጠው ኢህኣዴግ ተቋማትን በሚገባ አለመገንባቱና ሥርዓቱን በሁሉም ዘርፍና መስክ አለመሞከሩን ብዙ ቀዳዳዎችን እንዲፈጠሩ ከማድረጉም በላይ፣ ለችግርና ለአደጋ የሚዳርግ ሁኔታ መኖሩ በገሃድ እየተስተዋለ ነው፡፡ የሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት በስራ ላይ ሊውል ነው ከሚለው ዘገባ ጀምሮ እስከ ማዕድን በመገኘቱ ሀብት ተፈጠረ ብለን በሰማን ማግስት ፖታሽና ወርቅ ፍለጋው ዩራኒየም ፍተሻው ተቋረጠ:ነዳጅ የሚፈልግ ኩባንያ ሥራ እንዲያቆም ተደረገ መባሉን ስንሰማ ያሳስበናል፡፡ ሃገሪቱ ወደ አደጋ ውስጥ ሰተት ብላ መግባቷን እና እንደማትወጣውም ይጠቁመናል::

ወያኔ በፖለቲካ ታማኝነት ያደራጃቸው እውቀት እና ልምድ የሌላቸው በሙስና እና በዝምድና የተሳሰሩ አትኮሮታቸው በሰው አገር ንብረት እና ገንዘብ ማከማቸት በሆኑ ባለስልታናት የተዋቀሩ መሥርያ ቤቶች ሲልፈሰፍሱና ውሳኔ መስጠት ሲያቅታቸው ማየቱም ወዴት እየሄድን ነው የሚያሰኝ ሆኗል፡፡ ይህም ከባድ እና እስካሁን ሊፈታ ያልቻለ አደጋ ነው::

በዳያስፖራው ያለው ዘረኝነት፣ ጐሰኝነት፣ መከፋፈል፣ መራራቅ፣ ሃይማኖትን መጠቀሚያ ማድረግ፣ ከጠላት ጋር ወግኖ መሟገት፣ አገርንና የአገርን ክብር አሳልፎ መስጠትና ፖለቲካን ቢዝነስ በማድረግ ለአትራፊነት መወራጨት፣ አስፈሪ የሆነ አቋምና እንቅስቃሴ ማድረግ አሳሳቢ ነው፡፡ይህም እንዲፈጠር ከባድ ሚና የሚጫወተው ከሃገር ቤት የሚራመደው አሳዛኝ የፖለቲካ ፖሊሲ ሲሆን እንዲሁም ወያኔ እያሰለጠነ የሚያሰማራቸው የበግ ለምድ የለበሱ ቀበሮዎች የሚረጩት መርዝ ነው ይህም ሌላኛው በሃገር ላይ የተደቀና አደጋ ነው::

አንድነታችንን የሚፈታተኑ የጠባብ ጐሰኝነትና አካባቢያዊ ስሜት የተላበሱ አስተሳሰቦች እዚህም እዚያም ሲሰሙና በቦታው መሟሟቂያ ሲሆኑ ማስተዋልም የተለመደ ሆኗል፡፡ የረዥም ዘመናት አንድነት ያለውን በፍር የተሞላውን በማህበርዊ እሴቱ እና ጉዞው አለም ያደነቀውን ኢትዮጵያዊነት የሚሸረሽሩ መንግስታዊ የማፊያ እጆች ሕዝብን በማፈናቀል እና ጎሰኝነትን እና ስልጣንን የማስረዘሚያ ስልት በማድረግ ከህዝብ አናት ላይ የሚሸኑ ትናንሽ የመንደር መንግስታት እንዲፈጠሩ በማድረግ የአብሮነት ፍቅርን እና አንድነትን በማደፍረስ በስፋት እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ እያየነው ያለነውን ከባድ አደጋ በሃገሪቱ ላይ እንዲሰራፋ አድርጓል::

እደግመዋለሁ::ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ እና ባለስልታኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ሃገራችን እና ህዝቧ ሊወጡበት የማይችሉት ከባድ አደጋ ከፊታችን መደቀኑን ልብ ብለን በአንድነት እና በጋራ ከላይ የተቀመጡትን አደገኛ ሽብሮች የፈጠረውን በስልታን ላይ ያለውን መንግስት በአንድነት በመታገል ወደ ከርሰ መቃብሩ ከተን ዳግም እንዳያንሰራራ ማድረግ የኢያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታ ነው::

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በአገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም መብቶች ያለምንም ገደብ የሚከበሩበትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ላለፉት ዓመታት በርካታ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል፡፡ ዜጎች የመደራጀትና ሀሳባቸውን የመግለጽ ህገ-መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ጧት ማታ በመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች ቢለፈፍም፤ ሁሉም ነገር የይምሰልና የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ ነው፡፡

ከሕግ በላይ የሆነ አገዛዝ ባለበት አገር በየስፍራውና በየክልሉ የሚገኙ ካድሬዎችና የስርዓቱ ባለሟሎች እራሳቸውን ከህግ በላይ አድርገው ቢቆጥሩ የሚገርም አይደለም፡፡ በዚሁም ምክንያት በገዢው ፓርቲ ተቋማት፣ ኃላፊዎችና ባለስልጣናት የሚፈፀመው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ድርጊቶች እጅግ እየከፋ መጥቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በፓርቲያችን በአንድነት የተሰጣቸውን የተለያዩ ተልዕኮዎችን ለለማስፈፀም ወደ ደቡብ ክልል በተንቀሳቀሱት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ም/ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ላይ እና ከ32 በሚበልጡ የወላይታ ዞን አመራሮች ላይ መጋቢት 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም መንግስታዊ ውንብድና ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በወላይታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ላሊሼ ኦሌ የሚመሩና የደህንነት ሰዎችን ጨምሮ ከ8-1ዐ የሚሆኑ መንግስታዊ ወሮበሎች የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አባላት የተሰበሰቡበትን ግቢ በሀይል ሰብረው በመግባት የፓርቲ ሰነዶችን፣ ሁለት ሳምሰንግ ጋላክሲ ስልኮችን ጨምር በድምሩ ከ2ዐ የሚበልጡ የሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ሄደዋል፡፡

ወሮበሎቹ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም አመራሮቻችንን ወደ ፖሊስ ጣቢያ አስገድደው ወስደዋል፡፡ ከፓርቲያችን አመራሮቻችን የተነጠቁ ስልኮች በዞኑ ፖሊስ አዛዥ ቢሮ ውስጥ ፈሳሽ ውስጥ በመጨመር ከጥቅም ውጭ በማድረግ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮችና የዞኑን ም/ቤት አመራሮች ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው አድርገዋል፡፡ አመራሮቹን አፀያፊ በሆነ ማጎሪያ ውስጥ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡30 አስረው ማደሪያ ሊያገኙ በማይችሉበት ሰዓት ለቀዋዋቸዋል፡፡ ይህ አይነቱ ከመንግስታዊ አካል የማይጠበቅ ውንብድና በሚሊዮኖች ድምጽ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ወቅት ሐምሌ 5 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በዚሁ ዞን ተፈፅሞ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የጠራነውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለማደናቀፍ ታርጋ የሌላቸውን ሞተር ሳይክሎች በመጠቀም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ አባላትን በመደብደብና በመዝረፍ እንዲሁም የተከራየነውን አዳራሽ ጥበቃዎች ዘግተው እንዲሄዱ ከመደረጉም ባሻገር ከግለሰብ የተከራየነውን ሞንታርቮ ዘርፈው እስከ ዛሬም አልመለሱም፡፡

ምንም እንኳ የአንድነት ከፍተኛ አመራርና አባላት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን በሚካሄደው ትግል ውስጥ መንገላታት፣ መደብደብ፣ መታሰርና ሞትም ካለ አይናቸውን ሳይጨፍኑ አፍጠው ለመቀበል ዝግጁ ቢሆኑም ይህን አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ የማንመለከተውና አስፈላጊውን ነገሮች አጣርተን ተገቢውን ፖለቲካዊና ሕጋዊ እርምጃ የምንወስድበት ጉዳይ መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡

ሕገ መንግሥቱ ላይ የሠፈረውን የመደራጀት መብትና እና በተሻሻለው በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ‹2› የፖለቲካ ፓርቲዎች የዕለት ከዕለት ተግባሮችን ስር ፤ የሕዝቡን ፖለቲካዊ ግንዛቤ ማዳበር፣ የፓርቲውን ዓላማ ለሕዝቡ ማስረጽ፤ ዜጎች በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መቀስቀስ፣ በሕዝቡና በመንግሥት ተቋማት መካከል ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረግ የሚሉ ግልጽ ድንጋጌዎች ሰፍረዋል፡፡ በአንፃሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዛ አባሎቻቸው ጋር በማንኛውም ጊዜ መሰብሰብ እንደሚችሉ እየታወቀ በመንግስትና በገዢው ፓርቲ የሚፈፀሙ ሕገ ወጥ ተግባሮች በየእለቱ ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ሕግ ማክበርም ማስከበርም ያልቻለው ኢህአዴግ ሠላማዊ ትግሉን የሚደፈጥጡ ድርጊቶች ፈፃሚና አስፈፃሚ ካድሬዎች እና ሕገ አስከባሪ የተባለው የወላይታ ዞን ፖሊስ አዛዥ አይነት ግለሰቦችን በማበረታታት ሕጋዊና ሠላማዊ ትግሉን ወደ ጠርዝ እየገፋ ይገኛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮችና ለወላይታ ዞን የወረዳ አመራሮችና አባላት ያለንን ክብር እየገለፅን፣ በወላይታ ሶዶ በአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና የፓርቲያችን የዞኑ ምክር ቤት አባላት ላይ የተፈፀመው መንግስታዊ ውንብድና ስርአቱ የወረደበትን የዝቅጠት ደረጃ አመላካች እንደሆነ ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

ድል የሕዝብ ነው!
መጋቢት 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ

መጭው ምርጫ ያሰጋው ወያኔ ሕዝቡን ለማደናበር እና ለማጭበርበር ሊረዳኝ ይችላል ያለውን አዲስ የልማታዊ ዲሞክራሲ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን የባለራእዩ የሚሉት የመለስ ዜናዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በዝግታ ለማስቀረት እና ሕዝቡ አኩርፎበታል ያለውን የማንፌስቶ ሰነድ ለማዘጋጀት በአቶ በረከት የሚመራው ቡድን ስራውን መጀመሩ ታውቋል::

ተቃዋሚዎች ከፍተኛውን ድምጽ አግኝተው ከጨዋታ ውጪ ያደርጉኛል የሚል ስጋት ያደረበት ወያኔ በ1997 የተከሰተው አይነት ሽንፈት እንዳይደርስበት ከሰነዱ ዝግጅት ጎን ለጎን ስብሰባዎችን በማካሄድ ተቃዋሚዎች ከምርጫ የሚወጡበትን እና ምርጫውን የሚያጭበረብርበትን አዲስ ስልት እየነደፈ መሆኑንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል::የህዝቡ ብሶት እንደበረታ ያወቀው ሕወሃት መራሹ መንግስት በጭንቀት እና በምእራባውያን ጫና ተወጥሮ እንደሚገኝ ይታወቃል::

የመለስ ዜናዊ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በሃገሪቱ የአገልግሎት አቅርቦት ማጣትን:ሙስናን :ድህነትን:የዜጎች ስደትን :ስራ አጥነትን የኑሮ ውድነትን ወዘት ከማስፋፋቱም በተጨማሪ ምንም አይነት ውጠት እንዳልታየበት እና እስካሁን የተተገበረው የተጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ ምንም የፈየደው ነገር እንዳሌለ ኢሕኣዴግ በራሱ ድርጅታዊ ጉባዬ እና ስብሰባዎች መናገር ከጀመረ ሰነባብቷል::ምንሊክ ሳልሳዊ

ዛሬ መጋቢት 14 ቀን ነው፡፡ የኢህአፓው መሪ ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ከደርግ ዋና ጽ/ቤት ለተላኩ ወታደሮች እጄን አልሰጥም ብሎ ከኪዳኔ በየነ ህንጻ (በድሮው አጠራር ፊሊፕስ ህንጻ) ላይ ራሱን ወርውሮ ህይወቱን ያጠፋው ልክ በዛሬዋ እለት በ1969 ዓ.ል. ነው፡፡ ኢህአፓዎች ተስፋዬ ደበሳይ ራሱን ያጠፋበትን ያንቺን ቅጽበት የቆራጥነትና የጽናት ተምሳሌት አድርገው ይዘክሯታል፡፡

Image

በእርግጥም ተስፋዬ ደበሳይ ቆራጥ ነበር፡፡ ላመነበት ዓላማ ሺዎችን አንቀሳቅሷል፡፡ ለጠላቶቹ ሳይንበረከክ ህይወቱን ሰውቷል፡፡ በርሱ ሞት ያዘኑት ኢህአፓዎች “ተስፋዬን ከምናጣ ሌሎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶቻችን በሙሉ ቢጠፉ ይሻለን ነበር” በማለት መሪር ሐዘናቸውን አሰምተዋል፡፡ የደርግ መንግሥት እርሱ በሞተበት ዕለት ባወጣው መግለጫ አንድ ክፍለ ጦር ሰራዊት የተደመሰሰ ያህል ነበር የፎከረው፡፡
ተስፋዬ ደበሳይ ማን ነው? በኢህአፓ ውስጥ የነበረው ሚና ምን ይመስል ነበር?… ህይወቱ የተፈጸመው እንዴት ነው? እስቲ በጥቂቱ እንየው፡፡
*****
ኢሮብ በትግራይ ክፍለ ሀገር፣ [deleted] አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ወረዳ ናት (በአሁኑ የአስተዳደር አወቃቀር በትግራይ ክልል፣ ምስራቃዊ ዞን ውስጥ ነው የምትገኘው)፡፡ በዚህች ወረዳ ከትግርኛ ተናጋሪው ብሄረ-ትግራይ በተጨማሪ ኢሮብ የሚባለው አነስተኛ ብሄረሰብ ይኖራል፡፡ ይህ ህዝብ በውስጡ ሶስት ዐይነት ማህበረሰቦች አሉት፡፡ አንደኛው ደመክኒቶ ይባላል፡፡ የዚህ ማህበረሰብ አባላት የካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ማህበረሰብ “ሀሳበላ” የሚባል ሲሆን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ይበዙበታል፡፡ ሶስተኛው ማህበረሰብ “ዳልገዳ” ይባላል፡፡ እነዚህኛዎቹ ደግሞ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ማህበረሰቦች የሚናገሩት ቋንቋ በኤርትራ ምድር ከሚነገረው የሳሆ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም ኢሮብ እና ሳሆ በኢኮኖሚ ስምሪታቸው ይለያያሉ፡፡ የሳሆ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አርብቶ አደር ነው፡፡ ኢሮቦች ግን በእርሻ ስራና በአነስተኛ ዕደ-ጥበባት ነው የሚተዳደሩት፡፡ የኢሮብ ወረዳ ተራራና ሸንተረር ይበዛዋል፡፡ በአካባቢው ካሉት ተራሮች መካከል “አሲምባ” እና “አይጋ” ትልልቆቹ ናቸው፡፡

በዚህች የኢሮብ ወረዳ ውስጥ አሊቴና የምትባል አነስተኛ መንደር አለች፡፡ ይህች መንደር የአጋሜ አውራጃ ርዕሰ ከተማ ከሆነችው አዲግራት 35 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች፡፡ የመንደሪቷ ነዋሪዎች በአብዛኛው ካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ተሰፋዬ ደበሳይ በዚያች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው በ1933 የተወለደው፡፡ ወላጅ አባቱ አቶ ደበሳይ ካህሳይ ይባላሉ፡፡ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ምህረታ ዓዶ-ዑማር ነበሩ፡፡ ተስፋዬ የቤተሰቡ የበኩር እና ብቸኛ ወንድ ልጅ ነው፡፡ ከርሱ በኋላ የተወለዱት ስድስት ልጆች በሙሉ ሴቶች ናቸው (ለዚህ ጽሑፍ የመረጃ ምንጭ ከሆነው የመጋቢት ወር/2005 የኢህአፓ ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው ከስድስት እህቶቹ መካከል አምስቱ በህይወት ይገኛሉ፤ ወላጅ አባቱም በህይወት አሉ)፡፡

አሊቴና በዚያ ዘመን ትምህርት ቤት አልነበራትም፡፡ ስለዚህ ህጻኑ ተስፋዬ የትምህርት ጉጉት ቢኖረውም እድሜው አስር ዓመት እስኪሆነው ድረስ ትምህርት ቤት ለመግባት አልታደለም፡፡ በ1943 ግን አዲግራት ከሚኖሩት አክስቱ ዘንድ ሄደና ትምህርት ቤት እንዲያስገቡት ለመናቸው፡፡ አክስቱም በከተማዋ ከሚገኝ ታዋቂ የካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት አስገቡት፡፡ ተስፋዬም እስከ ስምንተኛ ክፍል በዚሁ ት/ቤት ከተማረ በኋላ ዘጠኛ ክፍልን መቀሌ በሚገኘው አጼ ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀቀ፡፡ ይሁንና በወቅቱ የትምህርት ወጪውን በራሱ ሸፍኖ መማር እንደማይችል በመረዳቱ ፊት ወደ ነበረበት የካቶሊክ ት/ቤት ተመለሰ፡፡ እዚያም እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማረ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ጣሊያን ሀገር ተላከ፡፡ በሀገረ ኢጣሊያ ሮም ከተማ ካለው Urbaniana University በፍልስፍና ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪውን ተቀበለ፡፡

ተስፋዬ በስራው ዓለም ሲሰማራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራበት መስሪያ ቤት የማስታወቂያና መርሐ ብሄር ሚኒስቴር ነበር፡፡ በዚህ መስሪያ ቤት የምርምር ክፍል ሃላፊ ሆኖ እየሰራ በማታው ክፍል የአባዲና ፖሊስ ኮሌጅ አስተማሪ ለመሆን በቅቷል፡፡ በ1964 ለተጨማሪ ስልጠና ወደ አውሮጳ (ስዊዘርላንድ) ተልኳል፡፡ በዚያ እያለም በመቀጣጠል ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ልቡን ስለወሰደው ትምህርቱን ትቶ ሙሉ በሙሉ ወደዚያው ገብቷል፡፡

ታዲያ እርሱ ወደ ስዊዘርላንድ በሄደበት ወቅት በአውሮጳው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር እና በአሜሪካው የተማሪዎች ማህበር መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ይካሄድ ነበር፡፡ ሁለቱ ማህበሮች የተወዛገቡት የድርጅት ምስረታና አደረጃጀት፣ የኤርትራ ጥያቄ፣ የብሄረሰቦች መብት፣ የትጥቅ ትግል አስፈላጊነት በመሳሰሉ አርዕስተ ነገሮች ዙሪያ ነበር፡፡ በጊዜው የድርጅት አስኳል ለመመስረት ጥረት ያደርግ የነበረው የአልጄሪያው የስደተኛ ተማሪዎች ቡድን ከአሜሪካው ማህበር ጋር ተቀራራቢ አቋም አሳየ፡፡ የአውሮጳው ማህበር መሪዎች በሀገር ቤት ከነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ጋር አንድ ዓይነት አቋም ላይ ደረሱ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይ ግን የአውሮጳው ማህበር መሪዎችን ውሳኔ በመቃወም ከአልጄሪያው ቡድን ጋር ወገነ፡፡ በዚህም መሰረት የአልጄሪያው ቡድን፣ የአሜሪካው ቡድንና አውሮጳ የነበሩት ጥቂት ተማሪዎች በድርጅት ምስረታ ሂደት ላይ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱ ለወራት ሲብላላ ከቆየ በኋላ በዓለም ዙሪያ ተበታትነው የነበሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ተማሪዎችንም ማካለል ጀመረ፡፡ በስተመጨረሻም በሚያዚያ ወር 1964 “የኢትዮጵያ ህዝቦች አርነት ድርጅት” (ኢህአድ) ተወለደ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይም ለድርጅቱ አመራር ከተመረጡ ሰባት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ሆነ፡፡
*****
ኢህአድ የተወለደው በውጪ ሀገር ነው፡፡ ከ1964-1966 በነበሩት ዓመታት ዋነኛ ስራው ድርጅቱን ማስተዋወቅና አባላትን ማሰባሰብ ነበር፡፡ ከፍልስጥኤም ነጻ አውጪ ድርጅትና ከኤርትራ ግንባሮች የተሰጠውን ድጋፍ በመጠቀም የትጥቅ ትግል የመጀመር እንቅስቃሴ ሲያደርግም ቆይቷል፡፡ የድርጅቱ ቀዳሚ ዓላማ ከገጠር በሚጀመር የትጥቅ ትግል በረጅም ጊዜ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ነበር፡፡ የኢህአድ መሪዎችም ድርጅቱ ቀዳሚ ሰራዊቱን ሊያሰማራበት ወዳሰበው የአሲምባ ተራራ በመሄድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር እንዲሰጡ ለማድረግ ታስቧል፡፡ ይሁንና በ1966 የፈነዳው የኢትዮጵያ አብዮት የትግሉን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀየረው፡፡ የአሮጌው ስርዓት መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ ሁሉም በየፊናው አወቀ፡፡ “በርሱ ቦታ ተተክቶ ሀገሪቱን የሚመራው ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ ግን አነጋጋሪ ሆነ፡፡ በዚህም በተራማጅ አብዮተኞች መካከል ከፍተኛ ውይይት ተቀሰቀሰ፡፡ በመደምደሚያውም የፓርቲ ቅርጽ የነበራቸው ቡድኖች በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ቢያደርጉ ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሚሆን ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በመሆኑም በውጪ ሀገር የነበረው የኢህአድ አመራር ወደ ሀገሪቷ ለመግባት ወሰነ፡፡

ከኢህአድ ከፍተኛ መሪዎች መካከል በቅድሚያ ወደ አዲስ አበባ የገባው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነው፡፡ ጊዜውም ሰኔ 1966 ነበር፡፡ በወቅቱ የወታደሮች ቡድን የሆነው ደርግ ተመስርቶ የአጼውን መንግሥት ለመጣል እያኮበኮበ ነበር፡፡ በሀምሌ ወር አጋማሽ ላይ ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ በመሻር ልጅ ሚካኤል እምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ መረጣቸው፡፡ ልጅ ሚካኤልም ካቢኔአቸውን ሲያቋቁሙ በስዊዘርላንድ የሚያውቁትን ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን የመሬት ይዞታ ሚኒስትር እንዲሆን ጠየቁት፡፡ እርሱ ግን ከውጪ የመጣው ለዚያ አልነበረምና አንዳች ምክንያት ፈጥሮ አሉታዊ መልስ ሰጣቸው፡፡ በምትኩ በመስሪያ ቤቱ በኤክስፐርትነት ቢቀጠር ለመስራት ፈቃደኛ እንደሆነ ገለጸላቸው፡፡ በዚህም መሰረት ከነሐሴ 1966 ጀምሮ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ሆነ፡፡

ተስፋዬ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ድርጅቱን በማስፋፋትና አባላትን በማደራጀት ስራ ላይ ነበር የተጠመደው፡፡ የድርጅቱ ልሳን የሆነችውን “ዲሞክራሲያ” ጋዜጣ ከሚያወጡ አርታኢያን መካከልም አንዱ ነበር፡፡ በድርጅቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሆኖ የተመረጠው ብርሃነ መስቀል ረዳ ከሰራዊቱ ጋር ስለነበር በርሱ ቦታ በጊዜያዊነት አመራር የሚሰጠውም ተስፋዬ ደበሳይ ነበር፡፡ በወቅቱ በድርጅቱ አመራር ላይ ከነበሩትም መካከል በዕድሜም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚበልጠው እርሱ ነበር፡፡

ተስፋዬ እስከ ታህሳስ 1967 በአዲስ አበባ ከተማ ከቆየ በኋላ ከመሬት ይዞታ ጋር ለተያያዘ የመስክ ስራ ወደ ትግራይ ተጓዘ፡፡ እግረ መንገዱንም አሲምባ የሚገኘውን የድርጅቱን ጀማሪ ሰራዊት ለመጎብኘት ወደዚያው ጎራ አለ፡፡ በጊዜው የነበረውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለሰራዊቱ ካብራራ በኋላ ግን ያልተጠበቀ ችግር ተከሰተ፡፡ ስምንት ያህል የሰራዊቱ አባላት ከጀማሪ ሰራዊቱ በመነጠል ለደርግ እጃቸውን ሰጡ (እጃቸውን የሰጡት ሰዎች ተስፋዬ መኮንን፣ ኃይለ እየሱስ ወልደ ሰንበት፣ አበበ በየነ፣ ዘከሪያ መሐመድ፣ አያሌው ከበደ፣ ጋሻው መንግሥቱ፣ ሀይሌ ወልደ ጊዮርጊስና ዳዊት አሰፋ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች በ1968 መጀመሪያ ላይ “ማሌሪድ”፣ ማለትም “የማርክሲስት ሌኒኒስት ሪቮሉሽናሪ ድርጅት”ን መስርተዋል)፡፡ ታዲያ የነዚህ ሰዎች ከኢህአፓ አፈንግጦ መውጣት የዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን ማንነት አጋለጠው፡፡ በመሆኑም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህቡዕ ለመግባት ተገደደ፡፡
*****
ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ህቡዕ ከገባ በኋላ የሙሉ ጊዜ አብዮታዊ ሆኗል፡፡ ኢህአድን በሙሉ አቅሙ አገልግሏል፡፡ በነሃሴ ወር 1967 ድርጅቱ ስሙን ቀይሮ “ኢህአፓ” (የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ) የተሰኘውን ዝነኛ መጠሪያውን የያዘበትን ጉባኤ በዋናነት ያዘጋጀውም እርሱ ነው፡፡ የድርጅቱ የፍልስፍና ሊቅ (ideologue) ሆኖ የሚያገለግለውም እርሱ ነበር፡፡ በኢህአፓ መስራች ጉባኤ “ዋና ጸሐፊ” የሚባል የስልጣን ተዋረድ ሲሻር በቀዳሚነት የማዕከላዊ ኮሚቴ ጸሐፊ ሆኖ ማገልገል የጀመረው እርሱ ነበር (ይህ የጸሐፊነት ቦታ በየጊዜው ይለዋወጥ ነበር፤ ጸሐፊው የሚመረጠውም በፓርቲው ጉባኤ ሳይሆን በፖሊት ቢሮው ነው)፡፡

እስከ 1968 አጋማሽ ድረስ በነበረው ጊዜ የኢህአፓ አመራሮች ማንነት በግልጽ አይታወቅም፡፡ በዚያን ጊዜ ህቡዕ ለመግባት የተገደዱት ብርሃነ መስቀል ረዳ እና ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ ናቸው፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የፓርቲው ስራ የሚከወነው በተስፋዬ ነበር (ብርሃነ መስቀል ለፖሊት ቢሮው ስላልተመረጠ ከፍተኛ ሃላፊነት አልተሰጠውም፤ በተጨማሪም ከሌሎች መሪዎች ጋር መነታረክ ጀምሮ ነበር) ፡፡

የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ከተመሰረተ በኋላ ግን አመራሩን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ በጽ/ቤቱ የተመረጡት ከፍተኛ ካድሬዎች የኢህአፓ መሪዎችን ስለሚያውቋቸው ለደርግ አሳልፈው ይሰጡአቸዋል የሚል ስጋት ሰፈነ፡፡ በመሆኑም በ1968 መጨረሻ ገደማ ሁሉም መሪዎች ህቡዕ ለመግባት ተገደዱ፡፡ ታዲያ የኢህአፓ የትግል ስትራቴጂም መለወጥ የጀመረው ከዚህ ወቅት ጀምሮ ነው፡፡ ከ1968 ክረምት ወራት በፊት በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ብቻ ያደርግ የነበረው ኢህአፓ የደርግ ፋሺስትነትን ለመከላከል በሚል የከተማ ትጥቅ ትግል የጀመረው ያኔ ነው፡፡

አንዳንድ ወገኖች የትጥቅ ትግሉ በዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ግፊት የመጣ ነው ይላሉ፡፡ ከሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም ጀምሮ መገደል ያለባቸውን ከፍተኛ የደርግና የመኢሶን ባለስልጣናት ዝርዝር እያዘጋጀ የሞት ፍርድ ያስወስን የነበረው ተስፋዬ ደበሳይ ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡ ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ የተስፋዬን ትግሬነት በመጥቀስ ብቻ ሻዕቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሽብር ለመቀስቀስ የመደበው የጥፋት ወኪል ነው የሚል መረጃ የሚያስነብቡ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ ሆኗል (ለነገሩ ተስፋዬ የኢሮብ ተወላጅ ነው እንጂ ትግሬ አልነበረም)፡፡ ይሁንና እንዲህ ዓይነቱን የተናጥል ክስ በተስፋዬ ላይ የሚያጠናክር ማስረጃ የለም፡፡ ኢህአፓ የከተማ ትጥቅ ትግል እንዲጀምር የወሰኑት ብዙሃኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ናቸው እንጂ ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ አልነበረም፤ ውሳኔውን የተቃወሙት ጌታቸው ማሩ እና ብርሃነ መስቀል ረዳ ብቻ ነበሩ (በጊዜው የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የነበሩት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ፣ ዮሐንስ ብርሃኔ፣ ዮሴፍ አዳነ፣ ክፍሉ ታደሰ፣ ክፍሉ ተፈራ፣ ዘርዑ ክህሸን፣ ኢያሱ አለማየሁ፣ ሳሙኤል አለማየሁ፣ አበራ ዋቅጅራ፣ ፍቅሬ ዘርጋው፣ ጸጋዬ ገብረመድህን፣ ብርሃነ መስቀል ረዳ፣ ጌታቸው ማሩ እና ጸሎተ ህዝቅያስ ነበሩ)፡፡

*****
መስከረም 13 ቀን 1969፡፡ በዚህች ዕለት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ለመግደል ያልተሳካ ሙከራ ተደረገ፡፡ በዚህም የተነሳ ኮሎኔሉ ኢህአፓን ለማጥፋት ቆርጠው ተነሱ፡፡ በስውር የሚያካሄዱትን ርሸና ይፋ ማውጣት ጀመሩ፡፡ በታህሳስ ወር የኮሎኔሉን እርምጃ የሚቃወሙ መኮንኖች በደርግ ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ አካሄዱ፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላ (ጥር 25/1969) ኮሎኔል መንግስቱ ማንም ባላሰበው መንገድ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት “ለምሳሌ ያሰቡንን ቁርስ አደረግናቸው” በማለት አወጁ፡፡ “አብዮቱ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል” ተባለ፡፡ “ቀይ ሽብር” በይፋ ታወጀ፡፡ “ነጻ እርምጃ” ተፈቀደ፡፡

በወቅቱ የኢህአፓው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ አዲስ አበባ ውስጥ እንደነበረ ደርጎች ያውቁ ነበር፡፡ ነገር ግን አድራሻውን በትክክል ማወቅ አልቻሉም፡፡ ኢህአፓም ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ እየተባባሰ በመሄድ ላይ የነበረውን የደርግ እርምጃ ለመቀልበስ እንደማይችል አውቆታል፡፡ ይሁንና የከተማውን የትጥቅ አመጽ አላቋረጠም፡፡ ደግሞም ዋና መሪውን ከደርግ አፍንጫ ስር አውጥቶ ከደህና ቦታ ለማድረስ አልሞከረም፡፡

ታዲያ ኢህአፓዎች መሪአቸው ከከተማው ወጥቶ ለደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ቢደበቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ በተለይ በመጋቢት ወር አጋማሽ (1969) ከሚካሄደው የቤት ለቤት አሰሳ ነፍሱን እንዲታደግ ይመኙ ነበር፡፡ ይሁንና መሪው ከከተማው ለመውጣት ምንም ዓይነት ፍላጎት አልነበረውም፡፡ “በዚህ ክፉ ቀን ተከታዮቼን ጥዬ ከከተማ አልሰደድም” በማለት ቆርጧል፡፡ አሰሳው ከመጀመሩ አስቀድሞ በነበሩት ቀናት ራሱ ሸኝ ሆኖ በልዩ ልዩ እርከን ላይ ያሉ ኢህአፓዎችን ከከተማው ወደ ገጠር ይሸኝ ነበር፡፡ ለምሳሌ የቤት ለቤት አሰሳው ከሚካሄድበት ዕለት በፊት በነበሩት ቀናት (ከመጋቢት 10-13 ባሉት ቀናት) ተስፋዬ ደበሳይ በርካታ የኢህአፓ አባላትን ከከተማ እያስወጣ ወደ ገጠር መሸኘቱ ተመዝግቧል፡፡ በነዚያ ቀናት በርካቶች ወደ አሲምባና ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ሄደዋል፡፡ እርሱ ግን እዚያው ሆኖ አሰሳው የሚያመጣውን ውጤት ለማየት ይጠባበቅ ነበር፡፡
*****
ዕለቱ መጋቢት አስራ 15/1969 ነው፡፡ ደርግ የቤት ለቤት አሰሳውን እያካሄደ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤት እየተከፈተ ይፈተሻል፡፡ “አናርኪስት” ተብሎ የተጠረጠረ ሰው እየተያዘ ወደ ማዕከላዊ ምርመራና የቀበሌ እስር ቤቶች ይጋዛል፡፡ ከእስራቱ ለማምለጥ የሞከረ ያለ ምንም ጥያቄ ይገደላል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ያረፈበት የበሪሁን ማሪዬ ቤትም እንደሚፈተሽ መረጃው ለኢህአፓ አሀዶች ደርሷል፡፡ በመሆኑም የተስፋዬን ህይወት ለመታደግ ቀኑን በመንግሥት ቢሮ ውስጥ ተደብቆ ማሳለፍ አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል (በወቅቱ ቢሮዎች አይፈተሹም ነበር)፡፡ በዚህ መሰረት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይና በሪሁን ማሪዬ አምባሳደር ቴአትር አካባቢ ባለው ኪዳኔ በየነ ህንጻ ውስጥ በሚገኘው የበሪሁን ሚስት ቢሮ ለመደበቅ ወሰኑ፡፡ በበሪሁን ማሪዬ ሾፌርነትም ከመርካቶ አካባቢ ወደ አምባሳደር ቴአትር እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ ተክለ ሀይማኖት አካባቢ ሲደርሱ ግን ተስፋዬን በሚያውቅ ሰው እይታ ውስጥ ገቡ፡፡ ያ ሰው ወዲያኑ ለደርግ ጸጥታ ሀይሎች በመደወል የተስፋዬን መገኘት አበሰራቸው፡፡ ለራሱ ደግሞ በቀስታ (እነርሱ ሳያዩት) ከኋላ እየነዳ ተከተላቸው፡፡ ደርጎች ለወራት ሲፈልጉት የነበረው አውራ ጠላታቸው ዱካ መገኘቱን ሲሰሙ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ተባለው ስፍራ አሳሽ ጦር ላኩ፡፡

ተስፋዬ ደበሳይና በሪሁን ማሪዬ ወደ ኪዳኔ በየነ ህንጻ ገቡ፡፡ ሆኖም ህንጻው እንደጠበቁት ነጻ ሆኖ ስላላገኙት ወደ መጡበት ለመመለስ ወሰኑ፡፡ ፈጠን ባለ እርምጃ ከህንጻው መውጫ በር ላይ ሲደርሱ ግን ለነርሱ የተላከው አሳሽ ጦር ህንጻውን ከቦ አገኙት፡፡ በዚህን ጊዜም ወደ ህንጻው ለመመለስ ሩጫ ጀመሩ፡፡ ሆኖም በቅርብ ርቀት ላይ የነበሩት አሳሾች ተኮሱባቸው፡፡ በሪሁን ማሪዬ ወዲያውኑ ተገደለ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይ ደግሞ ግንባሩ ላይ ቆሰለ፡፡ እርሱ ግን አልቆመም፡፡ የህንጻውን ፎቆች በትጋት ወጣ፡፡ ከስድስተኛው ፎቅ ላይ ሲደርስ አንድ ክፍት ቢሮ አየ፡፡ ከቢሮው በመግባት በመስኮቱ በኩል ወደ ውጪ ተወረወረ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም መሬት ላይ ተፈጠፈጠ፡፡ የኢህአፓው መሪ እንዲህ ባለ አሳዛኝ ትራጄዲ ከምድር ላይ ተሰናበተ፡፡
*****
ስለዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ በኢህአፓ ወገን በይፋ የተጻፈው ታሪክ ይህ ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አንዳንድ ጸሐፊዎች አሟሟቱን በሚመለከት አወዛጋቢ ታሪኮችን ማስነበብ ጀምረዋል፡፡ ውዝግቡ ለጊዜው አይጠቅመንም፡፡ የታሪክ ጸሐፊዎች ሐቁን እስከሚያወጡት ድረስ አወዛጋቢውን ታሪክ ብንዘለው ይሻላል፡፡ በጣም የምንስማማበት ጉዳይ ቢኖር ሀይሌ ፊዳ የመኢሶን ግርማ እና ኩራት እንደነበረው ሁሉ ተስፋዬ ደበሳይም የኢህአፓ አውራ የነበረ መሆኑን ነው፡፡ መኢሶንን ያለ ሀይሌ ፊዳ፣ ኢህአፓንም ያለ ተስፋዬ ደበሳይ ማሰብ አይቻልም፡፡ ሁለቱም የአንድ ትውልድ ፈርጦች ነበሩ፡፡ ሁለቱም በተሳሳተ ስሌት እርስ በርስ ተዋጉ፡፡ ሁለቱም በጨካኙ ስርዓት ተበሉ፡፡

የዶ/ር ተስፋዬ ታሪክን የማሳርገው በሚከተለው ታዋቂ የኢህአፓ መዝሙር ነው፡፡
“ቢወቀጥ አጥንቴ ቢንቆረቆር ደሜ
ለአዲስ ሥርዓት ልምላሜ
ፍጹም ነው እምነቴ
ትግሉ ነው ሕይወቴ”
*****
አፈንዲ ሙተቂ
መጋቢት 14/2006

(የትረካ ምንጮች)
1. ባቢሌ ቶላ፣ የትውልድ እልቂት፣ 1985፣ አዲስ አበባ
2. ክፍሉ ታደሰ፣ “ያ ትውልድ” ቅጽ 1፣ 1987፣ አዲስ አበባ
3. ክፍሉ ታደሰ፣ “ያ ትውልድ” ቅጽ 2፣ 1990፣ አዲስ አበባ
4. የያ ትውልድ ተቋም፣ “ዝክረ ተስፋዬ ደበሳይ”፣ መጋቢት 2005፣ ከኢንተርኔት የተገኘ
5. ገነት አየለ አንበሴ፣ የሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ትዝታዎች፣ 1994፣ አዲስ አበባ
(አፈንዲ ሙተቂ)
The writer, Afendi Muteki, is a researcher of the Ethnography and History of the peoples of East Ethiopia. He is an author of “Harar Gey”, an Ethnography book about the historical city of Harar. You can read some of his articles on his blog and his facebook page.

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ዛሬ በጽ/ቤቱ መግለጫ ሰጠ ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!

ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!

Image
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡

ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
Image
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የውህደት ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሰሞን ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ነው፡፡ የዚሁ አካል የሆነ እንቅስቃሴ በመኢአድና አንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባላት በእጅጉ እያሳዘነ ነው፡፡
Image
በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀውን ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በሰጠነው የደብዳቤ መልስ ላይ እንደገለጽነው በአንድነት ፓርቲ እይታ አመራሩ የፊት ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብሰባ ሠፊ የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡
በዚሁም መሠረት፡-
የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈፅማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መሠረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር፣ የፊርማው ስነ ሥርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር፡፡
በከፍተኛ አመራሮችና በሁለቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ መሠረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንቶች ተስማምተው፣ የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈራርመን፤ ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል የዕውቅና ሠነድ አግኝተን የመጨረሻ የስነ-ስርዓቱን መርሃ-ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት በኩል በቁጥር መ/ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በእለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንዳማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ከደብዳቤው እንደተረዳነው መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ የሚቀለብስ፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተስማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግባቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ በማንሳትና በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል፡፡ ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ ምክንያቱ የመኢአድ ፕሬዚንት ሲሆኑ ይህን ሁኔታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎች፣ በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሁለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለሕዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ ኃላፊነቱን የሚወስዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይም ፕሬዝደቱ መሆናቸውን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓርቲያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም

ፀረ ሰላም ሃይሎች
የፀረ ዲሞክራሲ ሃይሎች
የፀረ ልማት ሃይሎች
ኣሸባሪዎች
ነውጠኞች
ነጭ ለባሾች
የደርግ ርዝራዦች
ያለፉት ስርዓት ቅሪቶች
የኣፄው ስርዓት ናፋቂዎች
ኣደገኛ ቦዘኔዎች
ኪራይ ሰብሳቢዎች
የግል ጥቅም ኣሳዳጆች
ጥገኞች
ትምክህተኞች
ነፍጠኞች
የስልጣን ጥመኞች
ተስፈኞች
ጠባቦች
እንክርዳዶች/ጉርዶች
መሃል ሰፋሪዎች
ኣድሃሪያን
የቀለም ኣብዮተኞች
የሻዕቢያ ቅጥረኞች/ ጋሻጃግሬዎች
ኣክራሪ ቡድኖች
የሰለፊ/ወሀቢ እምነት ኣራማጆች
ፅንፈኞች
ቆ… ሻሻ (እደግመዋለሁ ቆ… ሻሻ!)
የበከተ/የገማ/የበሰበሰ ኣስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች
ዝቃጮች
ሁከተኞች
ፀብ ኣጫሪዎች
ተቸካዮች
ተንበርካኪዎች
ጥራዝ ነጠቆች
ስግብግብ ነጋዴዎች
ተለጣፊዎች/ተነጣፊዎች
የኢንተርሃምዌ ኣራማጆች
ሗላቀር ኣስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሃይሎች
ህገ መንግስቱን በጉልበት ለመናድ የሚዶልቱ ሃይሎች
ኣንዳንድ ኣርቆ ማሰብ የተሳናቸው ዜጎች (ዘገምተኞች )




(ደከመኝ በነጠብጣብ ልለፈው )
*****

የቀረ የለም። ምሁር ነሽ፡ ፖለቲካ ኣያገባኝም የምትይ መሃል ሰፋሪ ነሽ፤ የእምነት ሰው ነሽ፡ ነጋዴ ነሽ፡ ምንድነሽ ሁልሽም ቅጥያ ኣለሽ!

የልማት ሰራዊቱ ከሁሉም ጋር ስለማይስማማ (ከራሱም ጭምር) ለሁሉም ቅጥያ ኣዘጋጅቷል፤ ባንዳች የስድብ ምትሃታዊ ሃይል ነው ስርዓቱ የቆመው ማለት ሳይሻል ኣይቀርም።

Image
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::

ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል::

የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ

በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል::

የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም::ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

ከ50 በላይ የሚሆኑ የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት መታሰራቸው ተጠቆመ::
ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት እያቀረበ ባለው የማንነትና የራስ አስተዳዳርነት ጥያቄ ምክንያት፣ ከ50 በላይ የሚሆኑ አባላትና አመራሮቹ መታሰራቸውን የቅማንት ብሔረሰብ አመራር ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ‹‹ቅማንት የሚባል ሕዝብ የለም ያለ አካል ባይኖርም የራስ አስተዳደር ግን ሊፈቀድ አይችልም›› በሚል የክልሉ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጎንደር ከተማ እስከ 300 ሺሕ የሚደርሱ ተወላጆች በተገኙበት ሰላማዊ ሠልፍ https://www.facebook.com/photo.php?fbid … =3&theater ማድረጉን ተከትሎ፣ በተለይ በአመራር ኮሚቴው ላይ ጫናና ወከባ ሲደርስበት መቆየቱን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት በተቀናጀ መንገድ በአባላቱና በአመራሩ ላይ በአድማ በታኝና ፖሊስ ሠራዊት በታገዘ ኃይል አማካይነት፣ ከየካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በድምሩ 50 አመራርና አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በመተማ ወረዳ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገው በሰላም ካጠናቀቁ በኋላም የታሰሩ አባላት እንዳሉም አክሏል፡፡

የክልሉ መንግሥት በምን ምክንያት እንዳሰራቸው ግልጽ ባያደርግም፣ የታሰሩ አባላቱ በቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዳይጠየቁ፣ ከጎንደር በ80 እና 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ዳባትና ደባርቅ ወረዳዎች ተወስደው መታተሰራቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የቅማንት ብሔረሰብ ተወካይ ኮሚቴ በአባላቱና አመራሩ ላይ የአማራ ክልል መንግት ፈጽሞብኛል ስለሚለው እስራትና መንገላታት ማብራሪያ እንዲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መምርያ ሲጠየቅ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮማንደር ሰኢድ መሐመድ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምርያን ለማብራሪያ ጠቁመዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምርያ ፖሊስ ባልደረባ የሆኑትና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ፖሊስ፣ ‹‹እኛ ቅማንት የሚባል ብሔረሰብ አናውቅም፤ የምናውቃቸው አማራ መሆናቸውን ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ በበኩላቸው የሰሜን ጎደር ዞን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወደ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ቢጠቁሙም፣ የቢሮም ሆነ የግል ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው የኮማንደሩን ምላሽ ማካተት አልተቻለም፡፡ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ምንጭ ረፖርተር ጋዘጣ

Image

የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል። እነተክሉ ሃዋዝ በዚህ ወንጀለኛ ከተገደሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ያክላሉ።

በ1983ዓ.ም ሕወሐት/ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ምክትል የነበረው ብስራት አማረ ከቤተ መንግስት የጃንሆይ የነበረ ከፍተኛ ወርቅ በመዝረፍ መውሰዱን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚህ የዘረፋ ወንጀል ሆለታ እስር ቤት እንዲገባ መደረጉን ያመለክታሉ። በነስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲፈታ ተደርጐ ወደ አሜሪካ የተሸኘው ብስራት አሜሪካ ሲጓዝ የዘረፈውን ወርቅ ይዞ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች በግርምት ይገልፃሉ። ብስራት አማረ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ቅርስ የሆኑትንና የዘረፋቸውን ወርቆች መሸጡንና አንዲት ሴት ለማሻሻጥ የተቀበለችውን 1ኪሎ ወርቅ ከወሰደች በኋላ እንደካደችው ማወቅ ተችሎዋል። ብስራት አማረ ስለዚሁ ጉዳይ ተበሳጭቶ የነገራቸው ምንጮች ማረጋገጫ ይሰጣሉ።

የብስራት ታናሽ ወንድም የሆነውና በደህንነት ቢሮ ይሰራ የነበረው ታጋይ ጠስሚ (ጠስሚ -ትርጉሙ ቅቤ ማለት ነው) ከስራው በመልቀቅ የአስመጪና ላኪነት ትልቅ ቢዝነስ መክፈቱን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ ድርጅቱ የተከፈተው ብስራት አሜሪካ ከገባ በኋላ በላከለት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል። (ስለዚሁ ጉዳይ በ1995 ዓ.ም በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ መደረጉና የብስራት ወንድም ቅቤ ኢትኦጵ ቢሮ ድረስ በመምጣት የጋዜጣውን አዘጋጅ በድንጋጤ ተውጦ “የራሴን ቢዝነስ ተቋም ነው፤ እነማን መረጃ እንደሚሰጧችሁ አውቃለሁ። እባካችሁ የእኔንም፣ የወንድሜንም ስም አታንሱ?” በማለት ተማጽኖ አቅርቦ ነበር።)

ብስራት አማረ ከሽማግሌው ስብሃት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ መቆየቱን ያወሱት ምንጮቹ፣ ወንጀለኛውና ዘራፊው መቀሌ ሄዶ አስገደ ገ/ስላሴን እንደከሰሰ አስታውቀዋል። የደርግ ወንጀለኞች ከአሜሪካ በገዢው ፓርቲ እየተወሰዱ ነገር ግን የኢ.ህ.አ.ፓ አባላትንና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ የፈጀና የአገር ቅርስ የዘረፈ ወንጀለኛ ጠያቂ ማጣቱ አስገራሚ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ጠያቂ አካል ካለ በወንጀለኛው ብስራት አማረ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ መሆናቸውን አክለዋል። ይህን ምስክርነትና ማረጋገጫ ሊሰጡ የሚችሉና በአሜሪካ የሚኖሩ ሶስት የቀድሞ የሕወሐት ሹሞች እንዳሉና የብስራትን ወንጀል ጠንቅቀው የሚያውቁ መኖራቸውን አያይዘው ጠቁመዋል።
===ከኢየሩሳሌም አርአያ ከኢየሩሳሌም አርአያ ከኢየሩሳሌም አርአያ ===

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

Image

መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

ከነዚህም እጎአ በ2009 ዓም የወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህግ አንዱ ነው ። ህጉ ከባድ ተፅዕኖ ማሳደሩና መዘዞቹም በውይይቱ መነሳታቸውን ሆድንፌልድ ገልፀዋል ። « በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ለሚታገሉ ድርጅቶች በሚለገሰው ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ እርዳታ ላይ በተጣሉትን ገደቦች ላይ ተነጋገግረናል በዚህ ህግ ምክንያት በኢትዮጵያ ዓለም ኦቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አይሰሩም ። በርካታ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ማካሄድ አቁመዋል ወይንም ከነጭራሹ ተዘግተዋል »

መድረኩ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ ያደርጋል የተባለው ጫና ነበር ።

«ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተገቢው የህግ ሂደት ውጭ እንዲሁም በልዩ ደንቦች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉትን ገደቦችም በውይይቱ ተነስተዋል ። በተለይ ስብሰባው በኢትዮጵያ 12 ጋዜጠኞች በቨረ ሽብሩ ህግ ምክንያት መከሰሰሳቸውኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የጋዜጠኝነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ የመታሰራቸውም ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ተነጋግሯል ።

ሆድንፌልድ እንደሚሉት በውይይቱ በኢትዮጵያ የነጻ ሚዲያ መገደብም ተነስቷል ። በጎርጎሮሳውያኑ 2012 5 ጋዜጦች መዘጋታቸው በአሁኑ ሰዓትም ኢንተርኔ ት ከሚጠበቀው በላይ ቅድመ ምርመራ ይካሄድበታል ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንንና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱ ድረገፆች በኢትዮጵያ እንዳይሰሙና እንዳይታዩ በመንግሥት ይታገዳሉ ሲሉ ተወያዮቹ መገለፃቸውን ተናግረዋል ሆድንፌልድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንያሽሽልም ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ።

« የ2009 ዓም የበጎ አድራጎት ና የሲቪክ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል ሁለተኛ የፀረ ሽብር ህግ በደል መፈፀሚያና ጋዜጠኖችን ማፈኛ እንዳይሆን እንዲሰረዝ በፀረ ሽብሩ ሕግ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ እንዲሁም ተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ በፊት የመሰብሰብ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል ።»

ዶቼቬለ ስለ ውይይቱ ና ስለተሰጡት አስተያየቶች የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሆኖም በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የሰብዓዊ መብት ተመራማሪው አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ያኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችለመድረኩ የሰጡትን አስተያየት አጋርተውናል ።

http://www.dw.de/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1% … a-17495793

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

የግለሰብ ነጻነት ታፍኖ የጎሣ ነጻነት መታወጁ ፋይዳ እንዳላመጣ ታየ፤ የግለሰብን ነጻነት ለመደፍጠጥ ሲባል የጎሣዎች ነጻነትም አብሮ ተደፍጥጦ ነበር፤ ይህንን አስቀድሞ ለማየት ለምን ሳይቻል ቀረ? የሚል ጠያቂ ከመጣ መልሱ ቀላል ነው፤ በሚልዮኖች ብር እየወጣ መንገድ ሲሠራና አስፋልት ሲለብስ ቆይቶ ከጥቂት ወራት በኋላ የባቡር ሀዲድ ለመዘርጋት ተብሎ የተሠራውን አስፋልት የለበሰ መንገድ ማፍረስ እንዳስፈለገ አይተናል፤ የባቡሩ ጉዳይ ለምን አስቀድሞ አልታየም? የጎሣን ነጻነት ለማጉላት ሲባል የግለሰብን ነጻነት መደፍጠጡ ዞሮ ዞሮ የጎሣውንም ነጻነት አንደሚደፈጥጠው ያልታየበት የተለየ ምክንያት የለውም፤ አሰቀድሞ አለማየት የባሕርይ ነው፤ በተጠቀሱት ምሳሌዎች ሁለቱም ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ልዩነቱ የአንዱ ዋጋ የሚከፈለው በፖሊቲካ ኪሳራ ሲሆን፣ ሌላው የሚከፈለው በኢኮኖሚ (በሀብት) ኪሳራ ነው፤ ሆኖም የፖሊቲካውም ሆነ የሀብቱ ኪሳራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙሉ ያለምንም የጎሣ ልዩነት ሲጫንበትና ችጋር ሲያንዣብበት በሥልጣኑ ወንበር ላይና በዙሪያው የሚንሳፈፉት ፈጣሪዎቹ ናቸውና የችግሩ ሸክም ሲያልፍም አይነካቸው! እንኳን ለፖሊቲካና ለሀብት ኪሳራ ለሕይወት ኪሳራም ቢሆን የማይጠየቅ መሆኑን በምክር ቤት በሚባለው ውስጥ በድፍረት የተነገረበት አገዛዝ ነው።

የትግራይ ሕዝብ የአገዛዙ ጉልበትና የጥቅም ተካፋይ ነው እየተባለ እስቲያምመው ድረስ በሐሜት ተለበለበ፤ የሚናገርለት ቡድንና የሚናገርበት መድረክ ሳያገኝ ሃያ ሁለት ዓመታት ያህል ኢትዮጵያዊ ትእግስቱን አሳየ፤ ዛሬ አረና የሚባለው የትግራይ የፖሊቲካ ቡድን ወያኔ ለብቻው በትግራይ ሲቆጣጠረው የቆየውን የፖሊቲካ መድረክ ለመጋራት ፊት ለፊት በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል እየተጋፈጠው ነው፤ ይህ አዲስ ሁኔታ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ የፈጠረውንና ሊፈጥር የሚችለውን የፖሊቲካ እንቅስቃሴ እንኳን ሌሎች በሩቅ የሚከታተሉ ወያኔዎችም ገና አልገባቸውም፤ በፖሊቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው አገዛዙ ችግርን አስቀድሞ የማየት ብቃት እንዳላሳየ ከላይ በተጠቀሱት ምሳሌዎች አረጋግጠናል፤ ስለዚህም አገዛዙ በትግራይ የገጠመውን ሰላማዊ ፉክክር ለመቋቋም አዲስ ዘዴ አላገኘም፤ እስካሁን በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደተደረገው ሁሉ በትግራይም ተቀናቃኞቹን በእስርና በዱላ ለማገድ እየሞከረ ነው፤ ሌላ ዘዴ ገና አላገኘም፤ የሚፈልግም አይመስልም፤ በዱላ መጠቀም ሲለመድ አንጎል ይደነድናል፤ ወገንን ጠላት ያደርጋል፤ ወገን ጠላት ከሆነ ማን ወዳጅ ሊሆን ነው? ትልቁ አደጋ ይህ ነው።

መሠረታዊ ችግርም አለበት፤ በእውነተኛ የጎሣ ፖሊቲካ ውስጥ የማይታዩ ነገሮች እየተከሰቱ ነው፤ በአንድ ጎሣ ውስጥ ከባድ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት፣ የሥልጣን ክፍፍልም ሆነ የሀብት ልዩነት ጎልቶ ሲወጣ የጎሣው ሥርዓት መክሸፉንና መምከኑን ያመለክታል፤ መስታወት ሆኖ የመሠልጠንና የመለወጥ ልዩነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው፤ መሠልጠን የማይለውጣቸውን ሰዎች መማር ይለውጣቸዋል፤ ከማትጊያ ጋር በሚሰጥ የቡድን መመሪያ የሚሠሩትን ሰዎች በግል ማንበብና ማሰብ ይለውጣቸዋል፤ ይህንን የማይቀርና ሊታገድ የማይችል የለውጥ አቅጣጫ ማየት የማይችሉ ለዛሬ እንጂ ለነገ የሚኖሩ አይደሉም፤ በትግራይ በመታየት ላይ ያለው የነጻ ሰዎችን፣ የነጻ ግለሰቦችን አስተሳሰብ የሚገልጽ አንቅስቃሴ ለትግራይ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፤ የመንጋ አስተሳሰብን ለመረዳት ፌስቡክን ማጥናት ነው፤ የወያኔ የካድሬ ሠራዊት በሻገተው አስተሳሰቡ (መለስ ዜናዊ በጸያፍ ቃላት ገልጾታል፤) እያየው በዚያው በለመደውና ባስለመዱት የዱላና የጉልበት ዘዴ ሊያመክነው እየጣረ ነው፤ ወጣቶቹ ግን እየተደረገ ያለውን በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከተጫነባቸው የተስፋ ክምር ጋር እያስተያዩ ማን እንደጠገበና ማን እንደተራበ ያያሉ፤ ያመዛዝናሉ፤ አቅዋማቸውንም ያስተካክላሉ፤ የትግራይ ወጣቶች የፖሊቲካ ንቃትና ነጻ አስተሳሰብ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ የወያኔ ካድሬዎች አስበው ሊደርሱበት አይችሉም፤ የተለመደው አስቀድሞ አለማየት አወዳደቅን የሚጎዳ፣ የሚያስከፋና የሚያሳፍር ያደርገዋል!

የጭቆና ሠራዊት እንዲሆን የሚሠለጥነው የካድሬ ሠራዊት ጸረ-ማሰብ ነው፤ አስቦ ሳይሆን ለትእዛዝና ለሆዱ የሚገዛ ነው፤ ከላይ እስከታች በአንድ አስተሳሰብ ብቻ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የአገር ጉዳዮችን ለሕዝባዊ ሙግት አይከፍትም፤ ስለዚህም ሀሳቡ አይናፈስም፤ ስለዚህም አስተሳሰቡ የጊዜ መጫወቻ ይሆናል፤ ይሻግታል፤ ጸረ-ማሰብ ሆኖ ከመሻገት መዳን አይቻልም፤ መለስ ዜናዊ ይህንን በደንብ ያውቅ ነበር! ዛሬ እነኮኸንና እነሺን (ኮኸን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ውስጥ የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ የነበረ ሲሆን ሺን ደግሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ነበር፤) በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የሚናገሩት በኤርትራና በሶማልያ ላይ የተነደፈው መመሪያ አልሠራምና እንደገና መፈተሽ አለበት እያሉ ነው፤ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት የማንን መሠረታዊ ጥቅም ለማራመድ ነው? በጊዜው ጥያቄውን ለመመርመርና በትክክል ለመመለስ ካልተቻለ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ሲለዋወጥ የኢትዮጵያ አገዛዝ ይጨማደድና ብዙ ባዶ ቀፎዎችን ይዞ ይቀራል።

“ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ማለት ይሄ ነው፡፡
ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ::

ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ …” ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ “አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም” የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡ በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡

አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ “ጌታ ተሰቅሏል”፡፡ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና ሰው ግንኙነት የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የወገናዊና ኢወገናዊ፣ የፍትሐዊና ኢፍትሐዊ፣ ወይስ ቡድናዊና ኢቡድናዊ? ምን ይመስላል፡፡ የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡

አንዱ ለአመራሩ ሚሥጥር ቅርብ በመሆኑ አስቀድሞ ኢንፎርሜሽን ያገኛል፡፡ ቤቱን ከውርስ ያድናል፡፡ ሌላው ለኢንፎርሜሽኑ እሩቅ ነውና ላዩ ላይ ይታወጅበታል፡፡ ለብዙሃኑ ጥቅም ሲባል ጥቂቶቹ ቢጎዱም ምንም አይደለም የሚለውም አስተሳሰብ መመርመር ይኖርበታል፡፡ የአብዮቱ ጦስ ይሁን የካፒታሊዝም ጦስ ባልለየበት አገር አዋጆችና መመሪያዎች ሲከለሱ ማየት ቢያንስ ያስገርማል፡፡ አቀንቃኙ Protagonist እና ተቃራኙ antagonist በቀላሉ አይለዩም፡፡ ከሥልጣን ይባረራሉ፡፡ ተባራሪዎቹ ያወጡት ህግና መመሪያ ምን እንደሚሆን ዕጣ-ፈንታው አይታወቅም፡፡ ከሁሉም ይሰውረን! ህዝብ ብቻ ግራ እንደተጋባ ይቀጥላል፡፡ “ሰው ይጫኑብህ ግንድ? ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል፣ ሰው ከተጫነኝ ማን ያነሳልኛል፤ አለ” የሚባለው ግራ-ገብ ዘመንን የሚያመላክተን ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን! ከሚጫነን ይገላግለን፡፡ ከወዶ-ገባነት ይቅር ይበለን!!#MinilikSalsawi

አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ በማድረጉ ነው። ይሄንን ለማስቆም ሕዝቡን ማስተባበርና ማደራጀት ቀዳሚና ብቸኛ አማራጭ ነው።

አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶ አሉ። ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ የአንድነት ፓርቲ ነው። የአንድነት ፓርቲ «የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ» እና «የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት» በሚል ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ይህ እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።

በቅርቡ በባህር ዳር አስደናቂ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል። በቦታዉ የተገኙ ወገኖች ድምጻቸውን ያሰሙት አንድን ፓርቲ ብለው አልነበረም። ኢትዮጵያን ብለው ነዉ እንጂ። የባህር ዳሩ ሰልፉ ያማከለው በአንድ ድርጅት ዙሪያ አልነበረም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ዙሪያ እንጂ። ይህ በባህር ዳር የተደረገውን አይነት የነጻነት እንቅስቃሴ በተጧጧፈ መልኩ በመላው አገሪቷ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።

በአገሪቷ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 መሰረት፣ የዜጎች የመሰባሰብ ፣ በሰላም ትእይንተ ሕዝብ የማድረግ ሙሉ መብት የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም ይህ የሚሊዮኖች ለነጻነት ንቅናቄ ሰላማዊና የአገሪቷ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የሚደረግ በማንም ዜጋ ወይንም ቡድን ላይ ያላነጣጠረ፣ የተወሰኑትን ጠቅሞ ሌላዉን የሚጎዳ ያልሆነ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በመደብ፣ በጾታ ልዩነት ሳያደርግ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ለፍትህና ለነጻነት ለማሰባሰብና ለማንቀሳቀስ ታሰቦ የታቀደ እንቅስቃሴ ነው።

በዳያስፖራ ያለው ማህበረሰብም የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል እንደመሆኑ፣ የድርሻዉን መወጣት ይጠበቅበታል። በመሆኑም ይሄን የሚሊዮኖች ድምጽ ወይንም በባህር ዳር የተደረገዉን አይነት እንቅስቃሴ በሌሎች ከተሞች እንዲደረግ ለመርዳትና ለማጠናከር፣ የዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ይህ ግብረ ኃይል በዳያስፖራ ባሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት አነሳሽነትና በዉጭ ካሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት በተጨማሪ፣ ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግልን በሚደገፉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት ፣ ፓልቶክ ክፍሎችና ግለሰቦች ተባባሪነት፣ «እኛም የሚሊዮኖች አንዱ አካል ነን» እያሉ ቀናና የሚያኮራ ኢትዮጵያዊ ምላሽ እየሰጡ ያሉና ለመስጠትም የተዘጋጁ፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ለነጻነትና ለፍትህ ለማሰባሰብ የተዋቀረ ነው።

የሚሊየነሞች ንቅናቄ አዲስ አበባ እና ድረደዋ አስተዳደሮችን ጨምሮ፣ በኦሮሚያ የአዳማ፣ የላፍቶና የነቀምቴ ከተሞችን፣ በደቡብ ክልል፣ የአዋሳ፣ የጂንካና የቁጫ ወረዳዎችን፣ በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማን፣ በአማራዉ ክልል ደሴ፣ የወልዲያ፣ ደብረ ታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ እና በምእራብ አርማጭሆ የአብርሃ ጅራ ከተማን ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳን ከተማ፣ በጋምቤላ ክልል የ ጋምቤላ ከተማ የሚያዳርስ ይሆናል።

የሚሊየምን እንቅስቃሴን በተመለከተ በየጊዜዉ ወቅታዊ መግለጫ የምንሰጥ መሆናችንን እየገለጽን። በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እንደከዚህ በፊቱም ታላቅ ድጋፉን እንዲያበረክት በአክብሮት እንጠይቃለን። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ አገር ናት። ለአገራችን መነሳታችን ሊያስከፋ የሚችለው፣ ወይንም ዝምታን ተስፋ ቆርጠን መቀመጣችን ሊያስደስት የሚችለው አምባገነኖችን ብቻ ነው። በሕዝባችን ላይ ግፍ የሚፈጽሙ አይደሰቱ። እንነሳ። የድርሻችንን እንወጣ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይላ ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ በሚከተሉት አድራሹ ሊያገኙን ይችላሉ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

[email protected]
404- 518-7858

“ዳውድ ኢብሳ ሲሞት ጥሩኝ” በሚል ርዕስ በለጠፍኩት አነስተኛ ሐተታ ላይ ሁለት ዓይነት ተቃውሞዎች ቀርበውብኛል፡፡ አንደኛው “ኦነግ በአማራው ላይ የሰራውን ሴራ እና ሸፍጥ እያወቅክ ጥብቅና ቆመህለታል” የሚለው ሲሆን ሁለተኛው “የኦፒዲኦን ድርጅታዊ ህልውና አንኳሰስክ፤ አቶ አለማየሁንም ረገጥክ” የሚል ነው፡፡ ስለ ኦፒዲኦ የጻፍኩት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የድርጅቱ አባላት እራሳቸው በየአጋጣሚው የሚናገሩትን ነው በፌስቡክ የደገምኩት፡፡ በተለይ ደግሞ አባላቱ ከስራቸው ሲባረሩ፣ ወይ ደግሞ ከድርጅቱ ከድተው ወደ ውጪ ሀገር ሲኮበልሉ “ኦፒዲኦ የኦሮሞን ህዝብ ለማጭበርበር ሆን ተብሎ የተፈጠረ ድርጅት ነው” የሚል ጩኸት በማሰማት ነው የሚታወቁት፡፡ እነ ዮናታን ዲቢሳ፣ ዱባለ ጃሌ፣ ኢብራሂም መልካ ሲያደርጉት የነበረው ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የነርሱን ፈለግ በመከተል አይደለም እንዲያ ብዬ የጻፍኩት፡፡ ከነርሱ በፊትም እንደዚያ ስል ነበር፡፡
——
ኦነግን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየሁበት ግንቦት 1983 ጀምሮ የድርጅቱን የፖለቲካ መስመር ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ግን ድርጅቱ በሚያራምደው ርዕዮተ ዓለምና በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመርኩ፡፡ በዋነኛነትም “የመገንጠል ፖለቲካው የኦሮሞን ጥያቄ የትም አያደርሰውም” የሚል ሀሳብ አነሳሁ፡፡ እንዲሁም የሚከተላቸው ስትራቴጂዎቹ ፍጹም ሊዋጡልኝ አልቻሉም፡፡ በዚህም ከኦሮሞ ወንድሞቼ ጋር ብዙ ጊዜ እነታረክ ነበር፡፡ በተለይም በዚያ ጊዜ ኦነግን መተቸት Taboo ተደርጎ ይቆጠር ስለነበር ከቅርብ ጓደኞቼ ጭምር እስከመጣላት ደርሰናል፡፡ እናም ከ1990 ጀምሮ የድርጅቱ ተቃራኒ እንጂ ደጋፊ አይደለሁም፡፡

እንዲህ በመሆኑ ግን ድርጅቱን በሐሰት መክሰስ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ድርጅቱን በሰራው ጥፋት ብወቅሰው ማለፊያ ነው፡፡ ባልሰራው ወንጀል መክሰስ ግን ለማንም የሚበጅ አይሆንም፡፡ እንደምሳሌም ኦነግ የሚከሰስባቸውን ጭፍጨፋዎች እንመልከት፡፡ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ አሰቦት ገዳም ወዘተ…

እነዚህ ጭፍጨፋዎች መከሰታቸው ሁላችንንም ያሳዝነናል፡፡ አንድ ቀን እውነቱን ፈልፍለን የማውጣት ግዴታም ተጥሎብናል፡፡፡ ነገር ግን በርካታ ሰዎች በሁሉም ጭፍጨፋዎች ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርጉ በጣም እገረማለሁ፡፡ በተለይም ዛሬ በህትመት ላይ የሌሉ ሁለት የግል ጋዜጦች ይህንን ፕሮፓጋንዳ እየደጋገሙ ሲያስተጋቡት ሳይ “ስለ የትኛው ሀገር ነው የሚያወሩት” እያልኩ እደነቅባቸው ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ጋዜጦቹ የመረጃ እጥረት የነበራቸው መሆኑን በማወቄ ብቻ አይደለም፤ የጂኦግራፊ እውቀትም ያጠራቸው ስለሚመስለኝም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ “አረካ”ን እንውሰድ፡፡ ይህቺ ከተማ የት ነው ያለችው? ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ?

ይገርማል! አረካ ማለት በደቡብ ክልል በወላይታ አውራጃ ከሶዶ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኦነግ እዚያ ድረስ ሄዶ ሀገር አላስተዳደረም፡፡ “አረካ የኦሮሚያ ግዛት ናት” ብሎ የሚያውቅም አይመስለኝም፡፡ እናም ጂኦግራፊን በትክክል የሚያውቅ ጋዜጠኛ የአረካውን ግጭትና ጭፍጨፋ ለኦነግ አይሰጥም ነበር፡፡ በተጨማሪም የአረካው ግጭት የደረሰው ኦነግ የሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣና በእጁ የነበሩት መሬቶች በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ከወደቁ በኋላ ነው፡፡

የአረካው ግጭት በሽግግሩ ዘመን ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት የውይይት አጀንዳ ሆኖ እንደቀረበ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ ያለቁት የ31 ሰዎች ግድያ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ መንግሥቱ በይፋ አምኗል፡፡ ዳሩ ግን ለግድያው የተሰጠው ምክንያት በጣም አነጋጋሪ ነበር፡፡ መንግሥት ያቀረበው ምክንያት “ሰልፈኞቹ የተገደሉት ቦንብ በመወርወራቸው ሳቢያ የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው” የሚል ነው፡፡ ይሁንና ይህንን ምክንያት ብዙዎች አልተቀበሉትም፡፡ ብዙዎች እንደተጠራጠሩት እስከ ዛሬ ድረስ ቆይቷል፡፡ በነገራችን ላይ በአረካ የሞቱት የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች ነበሩ፡፡ እነዚያ ወታደሮች “የጡረታ መብታችን ይከበርልን” በማለት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት፡፡
——–
በሚያዚያ ወር 1984 በወተር ከተማ በተካሄደ ጭፍጨፋ የሞቱትም በተመሳሳይ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተገደሉ የሽግግር መንግሥቱ በወቅቱ አምኗል፡፡ ይሁን እንጂ በወተር የተገደሉት 230 ሰዎች በሙሉ ኦሮሞዎች እንጂ አማራዎች አልነበሩም፡፡ እነዚያ ሰዎች የተገደሉት ኢህአዴግ ከከተማቸው ወጥቶ ኦነግ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ በመጠየቃቸው ነው (ወተር ለአንድ ዓመት ያህል በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፤ ኦነግ ከከተማዋ ሲወጣ ኢህአዴግ ገብቶባታል፤ ነዋሪዎቹ “እንደ ቀድሞው ጊዜያችን ኦነግ ወደ ከተማዋ ይመለስ” በማለታቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት)፡፡ ጋዜጦቹ ግን “ኦነግ አማራዎችን ጨፈጨፈ” እያሉ ነበር የሚዘግቡት፡፡
——-
በ1984 (ወሩን አላስታውሰውም) በአሰቦት ገዳም በተካሄደ ግድያ ሰባት መነኮሳት ሞተዋል፡፡ ይህንን ግድያ የፈጸሙትም በወቅቱ የአሰቦት ከተማን ለትንሽ ጊዜ ተቆጣጥሮ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት እስላማዊ ግንባር (IFLO) ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ ግድያው ስር ሳይሰድ በአፋጣኝ ያስቆሙት ደግሞ ኢህአዴግና ኦነግ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች አንድ ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በወሰኑት ውሳኔ መሰረት IFLO ከከተማው ተባርሮ አካባቢው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡
——
በአርባ ጉጉ የተፈጸመው እልቂት በሁለት ተጎራባች መንደሮች መካከል በተካሄደ ግጭት ነበር የተለኮሰው፡፡ እያደር ግን መርቲ ጀጁ እና አሰኮ የሚባሉ የአርባ ጉጉ ወረዳዎችን አዳርሷል፡፡ በግጭቱ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች በእኩል ደረጃ ተጎድተዋል፡፡

በአርባ ጉጉ ግጭት የራሳቸውን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የፈለጉ ወገኖች እጃቸውን አስገብተውበታል ይባላል፡፡ በመሆኑም በውጤቱ ከሁሉም ግጭቶች የከፋ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ግጭት ከሁለቱም ወገን እስከ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች መሞታቸው ይነገራል፡፡ ከመቶ ሺህ ያላነሰ ሰው ወደ ሀረርጌና ሸዋ ክፍለ ሀገሮች ተፈናቅሏል፡፡ ሆኖም ኦነግ በዚህ ግጭት ውስጥ እጁን ማስገባቱን የሚያረጋግጥ ፍንጭ እስከ አሁን ድረስ የለም፡፡ ኦነግ በወቅቱ በአርባ ጉጉ አውራጃ ምንም ይዞታ አልነበረውም፡፡ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትም ቢሆን በግጭቱ የከሰሰው ኦህዴድን (OPDO) እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡ በተለይም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የምዕራብ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ የነበረው ኮሎኔል ዲማ ጉርሜሳ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ስሙ በሰፊው ይነሳ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዚያን ጊዜ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሐሰን ዓሊ ከእፎይታ መጽሔት ጋር (ግንቦት 1985) ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “አቶ ዲማ ጉርሜሳ ንጹሕ ነው” በማለት ከመከላከላቸውም በላይ ለግጭቱ ዋነኛ ተጠያቂ ያደረጉት መአሕድን እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡

የግል ጋዜጦች ግን ነገሩን አራግበው በኦነግ ላይ አላከኩት፡፡ ነገሩን ሳያውቁት ቀርተው የተደረገ አይመስለኝም፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች -ተከፍሎአቸው እንዲህ እንደሚያደርጉ በደንብ እናውቃለን፡፡
——–
የበደኖ ጭፍጨፋ! አዎን! ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ትራጄዲ ይህኛው ነው፡፡ በርግጥም እልቂቱ በተፈጸመበት ወቅት በደኖ በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡ የሞቱት ሀምሳ ያህል ሰዎች ለምን እንደተገደሉ ባይታወቅም አድራጎቱ በኦነግ ወታደሮች እንደተፈጸመ ድርጅቱ ራሱ አምኗል፡፡ ኦነግ በወቅቱ በወታደሮቹና በአዛዦቹ ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ቢልም የተወሰደውን እርምጃ ምንነት አልገለጸም፡፡ በነገራችን ላይ በዚህኛውም እልቂት ከሞቱት መካከል ግማሽ ያህሉ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
—–
ከላይ በዝርዝር እንዳስረዳሁት የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጄዲዎች መካከል አብዛኛዎቹ በኦነግ የተፈጸሙ አልነበሩም፡፡ ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ድርጊት በበደኖ የተፈጸመው ነው፡፡ የእውነት ቀን ሲመጣ ያንን ፋይል ማውጣታችንም አይቀሬ ነው፡፡ ይሁንና በኦነግ ያልተፈጸመውን ከርሱ ጋር አያይዞ መጻፍ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡ እንዲያውም የያኔዎቹ የግል ጋዜጦች የሚያራግቡት ወሬ በተወሰነ መልኩ የኦነግ ጨካኝነትን ከመግለጽ ይልቅ “ኦሮሞ ጨካኝ ነው” የሚል እድምታ ለመፍጠር የታለመ ነበር የሚመስለው፡፡

እርግጥ የኦነግ ወታደሮች በብዙ አጋጣሚዎች ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል፡፡ እርሱን አንክድም፡፡ የነርሱ ገፈት ቀማሽ ሆኖ የዘለቀው ግን በአብዛኛው ኦሮሞው ነው እንጂ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ አልነበረም፡፡ በተለይ አንዳንዶቹ የኦነግ ወታደሮች “ጎበና፤ ቢተምቱ.፤ ወዘተ..” ለሚሏቸው ግለሰቦች ምህረት አልነበራቸውም፡፡ እንዲሁም ተጻራሪ ድርጅት ሊያቋቁሙ ነው በሚል ፍርሃት አባላቶቻቸውን ጭምር እስከ መግደል ይደርሱ ነበር (የኦነግ የሀረር ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን አቶ አራርሶ ወዳይን እና በመቻራ ከተማ የተገደለውን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ካሊድ ሃጂ ኑራን መጥቀሱ ይበቃል)፡፡ ሆኖም ጋዜጦቻችን ድርጅቱ የፈጸመውን ማውራት ይተውና ድርጅቱ ያልፈጸመውን ወንጀል ይነግሩን ነበር! ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው፡፡

ለማጠቃለል ያህል እኔ ለኦነግ አልተከላከልኩለትም፡፡ አንዳች ጥብቅና አልቆምኩለትም፡፡ የጻፍኩት የማውቀውን ሐቅና የማምንበትን አቋሜን ነው፡፡ ይሁንና ይህ አባባሌ ኦነግን ከመፍራት እንዳይወሰድብኝ አደራ እላለሁ! አስፈላጊ ከሆነ በኦነግም የተፈጸሙ ስህተቶችና ጥፋቶችን አንድ በአንድ መዘርዘር እችላለሁ፡፡

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!!

[ውንብድና ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ]

ሁዳ የሚባል እስር ቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው እስረኞች ይማቅቃሉ – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በዓለም ዉድድር አለ። ዉድድሩ በህዝቦች መካከል ነው። ህዝቦች ዉድድሩን ለማሸነፍ አብሮነትን ይፈልጋሉ። በአብሮነት የራሳቸው ደህንነትና ጥቅም ማስከበር ይሻሉ። ደህንነታቸውንና ጥቅማቸው ለማስከበር ሀገር ይመሰርታሉ። ሀገር መስርተው በመንግስት ይወከላሉ። የመንግስት ተግባር ታድያ የህዝቡን ጥቅምና ደህንነት መጠበቅ ነው። በዚሁ መሰረት መንግስት የህዝቦች ተወካይ ጠበቃ መሆን ይጠበቅበታል።

የህዝቦች ወኪል (ጠበቃ) ለመሆን መንግስት በተለያዩ ሀገሮች ኤምባሲ ይከፍታል። የኤምባሲው ሰራተኞች የሚወክሉትን ህዝብ ጥቅምና ደህንነት ይጠብቃሉ፣ ያስጠብቃሉ። ለዚሁ ተግባራቸው ሲባል ህዝብ ደሞዛቸውን ይከፍላቸዋል። ደሞዛቸው የሚከፈላቸው ከመንግስት ካዝና ነው። የመንግስት ገንዘብ የሚሰበሰበው ከህዝብ ነው፤ በግብር መልክ።

ካርቱም የሚገኙ ጓደኞቼ እንደላኩልኝ ከሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲ (በካርቱም) ሰራተኞች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሰማርተው ኢትዮጵያውያንን አደጋ ዉስጥ እየጣሉ ይገኛሉ። የሰዎች ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ሰዎችን አደጋ ዉስጥ ማስገባት ምን ይሉታል? የመንግስት አካላት ወንጀልን ከመከላከል ይልቅ ቁማርተኞች ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?!
የኢትዮጵያ መንግስትም (መንግስት ልበለው) ከህዝብ ኪስ የሚከፈሉ የኤምባሲ ሰራተኞች አሉት። በተለያዩ ሀገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በህዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ የሚከፍላቸውን ህዝብ የሚበድሉ መሆናቸው እናውቃለን። ዛሬ ትኩረቴ የሳበ ግን በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ሱዳን ዉስጥ የሚቸገሩ ዜጎቻችንን ደህንነት ከመከታተል ይልቅ ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን እስርቤት ይከታሉ። እስካሁን ድረስ በሱዳን ብዙ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ጠያቂ በወህኒቤቶች እየማቀቁ ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሱዳን ሀገር የሚደርስባቸው ችግር፣ እስር፣ እንግልት እያወቁ በሰዎች ንግድ መሰማራታቸው ይገርማል። የኤምባሲው ሰራተኞች በሀገራቸው ሰዎች ንግድ ነው የተሰማሩ።

በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንደሌላቸው (መንግስት አልባ እንደሆኑ) ነው የሚቆጠረው። “ሑዳ” በሚባል ወህኒቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እነዚህ እስረኞች ያለ ምንም የፍርድቤት ዉሳኔ የተያዙና ከ8-12 ዓመት በወህኒቤቱ የቆዩ ናቸው። ተሰቅለው የተገደሉም መዓት ናቸው። በሱዳን የኢትዮጵያውያን ህይወት ርካሽ ነው። መስከረም አያሌው የተባለችም በሰባት ሱዳናውያን መደፈሯ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን መንግስት አልባ (stateless) ሁነው ሲሰቃዩ የኤምባሲው ሰራተኞች ግን ሰዎች እየገዙና እየሸጡ (በሰዎች ንግድ ተሰማርተው) ገንዘብ ይሰበስባሉ። ዘመናዊ መንግስታዊ የንግድ ባርያ መሆኑ ነው።

ኢትዮጵያውያን ክብራችንን የምናስመልስበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። አቶ መሐመድ ቱፋና አቶ በላቸው ግን ተግባራቹሁ ሁሉ እየተከታተልነው እንገኛለን።

ታላላቅ ግድቦችን በመሥራት ላይ የሚገኙ ታዳጊ አገራት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረገው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው ዘገባ መሠረት አገራቱ ለከፍተኛ ዕዳ እና ከዚያ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ችግሮች የሚጋለጡ መሆናቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ “ለሕዝባችሁ የምታስቡ ከሆነ ገንዘቡን ለሌላ ተግባር አውሉት” በማለት ምክርም ሰጥቶዋል፡፡

እኤአ ከ1934ዓም ጀምሮ በ65 አገራት የተገነቡ 245 ግድቦችን በማካተት የተደረገው በዓይነቱ ለየት ያለው አጠቃላይ ጥናት በቅርቡ እየተገነቡ ያሉትን ታላቅ ግድቦችንም ያካተተ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ካለው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጀምሮ እስከ ብራዚሉ የአማዞን ቤሎ ሞንቴ የግድብ ፕሮጀክቶችን የሚገነቡት ታዳሽ ኃይልን አጠቃቀም ለማጎልበት እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለመጨመር በሚል እንደሆነ የጠቀሰው ጥናታዊ ዘገባ ግንባታው በርካታዎችን ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ የሚያደርግና ለብዝሃ ህይወት አደጋ እንዲጋለጡ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

እንደነዚህ ዓይነቱን የግድብ ሥራ የሚቃወሙ ቡድኖች እንደሚሉት የታላላቅ ግድቦች የኮንስትራክሽን ወጪ ሲጀመር ከታሰበው በጀት በአማካይ ከ90 በመቶ በላይ ተጨማሪ ወጪ የሚያስከትል እንዲሁም ከአስር ግድቦች ስምንቱ ከተወሰነላቸው የመጠናቀቂያ ጊዜ እንደሚያልፉ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑን በኢትዮጵያና በብራዚል የሚገነቡት ግድቦች የፓኪስታንንና የምያንማርን (በርማ) ጨምሮ “ከፍተኛ ወጪ እንዲሁም ከመመጠናቀቂያ ጊዜያቸው በማለፍ የአገራቱን የኢኮኖሚ ገጽታ ችግር ውስጥ” እንደሚከቱ ዘገባው ያስረዳል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት ምሁራን እንደሚሉት ግድብ መሥራት አስፈላጊና እነርሱም በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃዋሚ አለመሆናቸውን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ያለው ታዳጊ አገራቱ ካላቸው የኢኮኖሚ ሁኔታ አኳያ በእንደዚህ ዓይነት የታላላቅ ግድብ ሥራ ላይ መጠመዳቸው ወደፊት ግድቦቹ በሥራ ላይ ሲውሉ ከሚጠይቁት ከፍተኛ ወጪና አገራቱ ግድቦቹን ለማንቀሳቀስ ከሚጠፈለግባቸው ከፍተኛ የፋይናንስ ጥያቄና ብቃት ማነስ አኳያ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመዘርዘር አስረድተዋል፡፡ “በመሆኑም” ይላሉ ከምሁራኖቹ አንዱ “በመሆኑም ይህንን ሁሉ ሁኔታ አንድ ላይ ስንወስደው ግድቦቹን መገንባት ስሜት የሚሰጥ አይደለም፡፡”

እንዲህ ያለው መረጃና ማስጠንቀቂያ ይፋ ቢሆንም የግድቦቹን መሠራት የሚደግፉ ወገኖች ቀድሞ የተሠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ አድርገን ነው የምንገነባው በማለት ለሚቀርበው ማስረጃ መከላከያ ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም የኦክስፎር ዩኒቨርሲቲ ዘገባ የበርካታ ዓመታት መረጃ በመውሰድ ያወጣው ዘገባ ላይ እንዳመለከተው የግድቦቹን ሥራ ለማጠናቀቅ፣ ከተሰሩም በኋላ ለጥገናና ግድቦቹ በሥራ ላይ እንዲቆዩ ለማካሄድ የሚወጣው ወጪ ባለፉት በርካታ ዓመታት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዳልመጣ ያስረዳል፡፡ በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሌላው ምሁር ሲናገሩ “እነዚህ ኢኮኖሚያችን እያደገ ነው የሚሉ አገራት በእርግጥ ለዜጎቻቸው ዋስትና ግድ የሚላቸው ከሆነ ገንዘባቸውን ከታላላቅ ግድብ ሥራ ይልቅ በሌላ (ሰብዓዊ) ተግባር ላይ ቢያውሉት ይሻላል” ብለዋል፡፡

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የኦሞ ወንዝን ተከትሎ በሚገነባው ግድብ ላይ ስለተፈናቀሉት ዜጎች በቅርቡ ባወጣው በሳተላይት ፎቶ በተደገፈ ማስረጃ መሠረት በኢትዮጵያና በኬኒያ የኦሞን ወንዝ ተከትለው የሚኖሩ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በግድቡ ሥራ ምክንያት የመኖር ኅልውናቸው ያከተመ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡ ሰሞኑን የኢህአዴግ ባለሥልጣናት (ከግብርና ሚ/ር) በኢህአዴግ ፓርላማ ሲጠየቁ በሰጡት ቃል አንዳችም የተፈናቀለ ሰው የለም በማለት የመለሱ ሲሆን በተደጋጋሚ ማስረጃ ተደግፎ የሚወጣውን መረጃ አጣጥለውታል፡፡
Image
(ፎቶ: AP)

goolgul

የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በዶ/ር ደብረጺሆን ፍቃድ ካልሆነ ምንም አይነት ውሳኔ መስጠት አይችሉም::

የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና ባለስልጣኖቻቸው በሙስና እና በዘረፋ ላይ ተሰማርተዋል::
የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ማኮላሸት ለአለቃ ጸጋዬ በርሄ ተሰቷቸዋል::
የጦር ሰራዊቱን በተጠንቀቅ የሚከታተሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ተደራጅተው በየእዙ ተበትነዋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ በመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት መኮንኖች ስር የሰደደው የሙስና እና የዘረፋ አድራጎት በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥም ከሹሙ ከአቶ ጌታቸው እና ከባለስልጣኖቻቸው ጀምሮ እስከ ገራፊዎች ድረስ መንሰራፋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ የደህንነት ባለስልጣኖቹ የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት በከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ ባማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ከዚህ ቀደም በሙስና የተከሰሱ የስርኣቱ ባለስልጣናትን ተገን በማደርግ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::ምንሊክ ሳልሳዊ

ኢትዮጵያውያን በሕወሓቱ የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ምንጮሹ አክለው ገልጸዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕወሓትን ሳይጨምር ብኣዴን ኦሕዴድ ደኢሕዴግ እና አጋል የክልል ጎሳ ፓርቲዎች ከአቶ ደብረጺሆን በሚወርድ ትእዛዝ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ በፍቃዳቸው መፈጸም እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል:: በቅርቡ የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ሞት ተከትሎ አፈጻጸሙ በዶ/ር ደብረጺሆን መልካም ፍቃድ እንደሆነ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተባለው የኦሕዴድ ሙክታር ከድር አቶ አለማየሁ ደክመው እያየ እና እያወቀ ሆስፒታል እንዲሄዱ አስቸኳይ ትብብር እንዲደረግ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ስትጠይቀው ለዶ/ር ደብረጺሆን ነግረሽ አስፈቅጂ በማለት ሕወሓት በኦሕዴድ አናት ላይ ምን ያህል እየሸና እንዳለ እንዲሁም በሞራላቸው አመራሮቹ እንዳይራመዱ እያደረገ እንዳለ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው:: ማንኛውም የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅት በድርጅቱ ሊቀመንበር ወይንም ምክትል አማካኝነት በቅድሚያ ለዶ/ር ደብረጺሆን ሪፖርት ማድረግ እና ሁኔታው ታይቶ ፈቃድ እና ውሳነ ካልተሰጠው በስተቀር መፈጸም እንደማይችል ትእዛ መተላለፉ ሲታወቅ በአዲስ አበባ እና በክልል ያለው የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ በአለቃ ጸጋይ በርኸ ስር ክትትል እየተደረገ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑ ሲታውቅ የጦር ሰራዊቱን በተመለከት በተዋረድ የሚያስተዳድሩ የወታደራዊ ደህንነት የሕወሓት መኮንኖች ተደራጅተው በየእዙ መመደባቸው ታውቋል:: ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

Image
ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በተዘጋጁ ሁለት ፅሁፎች፣ የድህረ መለስን ኢህአዴግ የኃይል አሰላለፍ ለማመልከት መሞከሬ የሚታወስ ቢሆንም፤ ዛሬም ያልተጠበቁ ክስተቶችን ማስተዋላችን አልቀረም፡፡ በርግጥ «አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ ፪» በሚል ርዕስ ቀርቦ በነበረው ተጠየቅ ከሞላ ጎደል ሀገሪቷን እንደንጉስ ሚካኤል ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯት ህወሓት እና ብአዴን መሆናቸው የተጠቀሰበት አውድ ብዙም አልተቀየረም፡፡ ይሁንና በኦህዴድ እና ደኢህዴን ውስጥ እየታየ ያለው የእርስ በእርስ መተጋገል መደምደሚያ ምናልባት ወቅታዊውን መልከአ ኢህአዴግ ሊለውጠው የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ እገምታለሁ፤ ማን ያውቃል? …እነዚህን ኩነቶች ታሳቢ አድርገን የገዢው ፓርቲ አክራሞትን በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደመመልከቱ እንለፍ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ «ብላቴኖች»
ክልሉን የሚያስተዳድረው የደኢህዴን የአመራር አባላት በስርዓቱ ልሂቃን የፖለቲካ ግምገማ ገና «ብላቴና» ተደርገው የሚወሰዱበት የትምክህት ዘመን አላከተመም፡፡ በርግጥ ድርጅቱ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ላይ የተሳተፈ ባለመሆኑ፣ ዛሬም ፖለቲካን (ሀገር ማስተዳደርን) በበረሃው ትግል ተፈትኖ ከማለፍ ጋር ከሚያጋምዱት የግንባሩ ጉምቱ መሪዎች ዘንድ፣ ይህን መሰል ማጣጣያ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለደኢህዴን ደካማነት በምክንያትነት የሚነሳው ጉዳይ ከአወቃቀሩ ጋር የሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በክልሉ የሚገኙ 56 የተለያዩ ዘውጎችን ማቀፉ ለመከፋፈል አደጋ በቀላሉ የሚጋለጥበትን ዕድል የማስፋቱ እውነታ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ከክልሉ ነዋሪዎች በቁጥር የሚልቁት የወላይታና የሲዳማ ተወላጆች፣ በደኢህዴን ውስጥ ያላቸው ተሰሚነት (ተፅዕኖ) የገዘፈ መሆኑን ለመረዳት፣ ሕገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርነትም ሆነ የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ከሁለቱ ብሔሮች በቀር፣ ለሌሎቹ የሰማይ ያህል የራቀ ያደረገውን «ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት» መጥቀሱ በቂ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ የያዘውን መንግስታዊ ስልጣን የሚመጥን ተሰሚነት ለማግኘት ድርጅታዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ያተኮሩ የሚመስሉ ክስተቶችን ሲከውን ታዘብናል፡፡ ኩነቱን በስነ-አመክንዮ ለማጠናከር ጥቂት ማሳያዎችን ላቅርብ፡- በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ፣ በደኢህዴን ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ተገዳዳሪዎቹን ከኃላፊነታቸው ከማንሳትም አልፎ፣ ደጋፊዎቹ (ታማኞቹ) እንደሆኑ የሚነገርላቸውን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀምጧል የሚያስብለው፣ ከወራት በፊት በፓርቲውም ሆነ በደቡብ ክልል ከእርሱም የበለጠ ተሰሚነት የነበረውን ሽፈራው ሽጉጤን አንስቶ፤ ትጉህ አገልጋዩ እንደሆነ የሚነገርለትን ደሴ ዳልጌን ተክቶታል፤ በቅርቡ ደግሞ ሌላኛው ‹የደኢህዴን ቁልፍ ሰው› የሚባለው የፖለቲካ (የድርጅት) ጉዳይ ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አለማየሁ አሰፋን ያለአንዳች ኮሽታ «በትምህርት ስም» ከቦታው አንስቶታል (ይህ ጉዳይ እስከአሁን ድረስ መንግስታዊው ሚዲያ የዜና ሽፋን አላገኘም)፡፡ በግልባጩ ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩ፣ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉ ጓዶቹን በፌደራል መንግስቱ ወሳኝ የስልጣን እርከኖች ላይ አስቀምጧል፡፡ ለማሳያ ያህልም አሰፋ አብዩ /ሀድያ/፣ ወርቅነህ ገበየውን ተክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ ደበበ አበራ /ከፋ/፣ የኢህአዴግ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ውዱ ሀቶ /ሸካ/፣ የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር፤ አማኒኤል አብርሃም /ወላይታ/፣ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ፤ ሰለሞን ተስፋዬ /ጉራጌ/፣ በተመሳሳይ ማዕረግ የፕሬስ አማካሪ፤ ካይዛ ኬ (ጂንካ) በገቢዎች ባለስልጣን የገብረሀዋድን ቦታ ተክቶ የገባ እና የፌደራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊ ተደርጋ የተሾመችውን የወላይታዋ ተወላጅን መጥቀስ ይቻላል (ከደኢህዴን የሥራ-አስፈፃሚ አባላት መካከል የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን እና መከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳም የሲዳማ ተወላጅ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል) ይህንን ጉዳይ እንዲህ በብሔር ደረጃ ቁልቁል አውርደን እንድንመለከተው የሚያስገድደን ስርዓቱ ከሚያራምደው የፖለቲካ ፍልስፍና እና በክልሉ እየተነሱ ካሉ የማንነት ጥያቄዎች ጋር የመቆራኘቱ አንድምታ ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች ራሳቸውን ችለው
በክልል ደረጃ ለመዋቀር ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው አያሌ መስዋዕትነትን መክፈላቸው ይታወሳል (በኢህአዴጋዊ የክልል አሰያየም ቀመር ሕገ-መንግስታዊ ድጋፍ ያላቸው መሆኑ ሳይዘነጋ)፡፡ ይሁንና ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝ የክልሉ አስተዳደር መቀመጫ የሆነችውን አዋሳን ከመውሰዳቸውም በላይ፣ ሊያስከትል የሚችለው አለመረጋጋት ሲታከልበት፣ ህዳጣን ልሂቃኑን የኢኮኖሚ ጥቅመኝነት ያሳጣቸዋል፡፡ ይህ ስጋትም በደኢህዴን ውስጥ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ካሉ የአመራር አባላት ድርጅታዊ ድጋፍ ለማግኘት ብርቱ ትግል ከሚያደርገው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በወሳኝ ሰዓት፣ መሀል መንገድ ላይ ቢያስተቃቅፋቸው የማይታመን አይሆንም፡፡

የእነዚህ አዳዲስ ኩነቶች (ሹም ሽሮች) መግፍኤ፣ በሁለት የቢሆን ሃሳቦች ተነጣጥለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ኃይለማሪያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመቱን ተከትሎ ‹በዚህ ላይ ፈርም›፣ ‹ይህንን ተናገር›፣ ‹እንዲህ አይነት አስተያየት ስጥ!!› ወዘተ የሚሉ ከጀርባ ሆነው የሚሾፍሩት የአለቆቹ ቀጭን ትዕዛዛትን የሚገዳደርበት ፖለቲካዊ ጉልበት ለማሰባሰብ እና በቁርጥራጭ ጨርቅ በተጣጣፈው እናት ድርጅቱ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ስልታዊ በሆነ መልኩ አስወግዶ ቅቡልነቱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ጀምሯል የሚል ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላኛው ደግሞ ከኢትዮጵያውያንም አልፎ በውጪ ዜጎች ሳይቀር ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻንጉሊት ነው› የሚለውን እምነት ለማስቀየር በህወሓትና ብአዴን እየተደረገ ያለ ፖለቲካዊ ጨዋታ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው፡፡
ኦህዴድ
ባለፉት የህወሓትም ሆነ የአቶ መለስ ዜናዊ የበላይነት በገነኑባቸው ዘመናት፣ ኦህዴድ ምንም እንኳን ስርዓቱን ካነበሩ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ባይካድም፣ በስጋት መታየቱ የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ እንዲያውም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ራሱ «ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው» ማለቱ አይዘነጋም፡፡ ከሶስት ያላነሱ የስራ አስፈጻሚ አባላቱ፣ ድርጅቱን ከድተው ኦነግን መቀላቀላቸውም የውንጀላው ማሳያ ተደርጎ እስከመወሰድ ደርሶ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም ኦህዴድን የተረጋጋ አመራር እንዳይኖረው ከማደናቀፉም ባሻገር፣ በተቀነባበረ ማኪያቬሊያዊ ሴራ እርስ በርስ በማይተማመኑና በተከፋፈሉ ሰዎች ስር እንዲቆይ አስገድዶታል፡፡ ግና፣ ኩነቱን ምፀት የሚያደርገው ህወሓት በረሃ እያለ ያሳትመው በነበረው ልሳኑ «የኦሮሞ ጥያቄና የኢትዮጵያ አብዮት» በሚል ርዕስ ባሰራጨው ፅሁፍ ኢህአፓን «የኦሮሞ ሕዝብ በነፍጠኛው ላይ የነበረውን ተገቢ ጥላቻ በማራገብ ፋንታ ለማብረድ በተጨባጭ ተንቀሳቅሷል» («የትግል ጥሪ» 3ኛ ዓመት ቁጥር 10፣ 1979 ዓ.ም) ሲል ይከስሰው እንደነበረ ማስተዋላችን ነው፡፡
በአናቱም አቶ መለስ እስከ ህልፈቱ ድረስ በኦህዴድ ደስተኛ እንዳልነበረ ይነገራል፡፡ ይህ ግን ‹የኦሮሞን ሕዝብ በአግባቡ አላገለገለም› ከሚል ቁርቆራ የተነሳ አይደለም፤ እንዲህ አይነቱ ስሜት ሌላውን ክልል ቀርቶ ትግራይንም የሚመለከት ቢሆን አሳስቦት አያውቅምና፡፡ የእርሱ ቅሬታ ‹ህዝቡን አሳምነውም ሆነ ጠርንፈው ከድርጅቱ ጎን አላሰለፉትም›፣ ‹ሁላችንንም በሚያሳጣ መልኩ ዘረፋ ውስጥ ገብተዋል›፣ ‹ዲሲፕሊን የላቸውም…› የሚሉና ሌሎች መሰል መነሾዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ የድርጅቱ «እንዝህላልነት» ደግሞ የህዝቡ ልብ ይበልጥ ኦነግን እንዲናፍቅ ማስገደዱን መለስ ዜናዊ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የክልሉን ባለስልጣናት ሁሉ ወደ ጎን ብሎ እታች ድረስ በመውረድ የወረዳ አመራሮችን ቀጥታ ያለ ሥልጣን ተዋረድ በስልክ እስከማናገር የተገደደባቸው ቀናት የበዙት፡፡ በርግጥ በድርጅቱ ስብሰባዎች ላይ መተላለፍ ያለባቸውን ውሳኔዎች በፅሁፍ መስጠት እና ለአመራርነት የሚመረጡ ሰዎችን መመደብ ድረስ ባሉ ጉዳዮች ጣልቃ የመግባቱ ነገር ማንም አሌ የማይለው በግልፅ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ከምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት አባዱላ ገመዳ ዕድሜውን ሙሉ ሲፈራ የኖረው መለስ ዜናዊን ብቻ ነበር፤ መለስ ደግሞ ይህችን ምድር ለመጨረሻ ጊዜ ከተሰናበታት አንስቶ የተቆጠሩት በርካታ ወራት ፍርሃቱን ጥሎ ነፃነቱን እንዲጎናፀፍ ለመርዳት ያስችሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም በዚህ መልኩ ተፈጥሮ ያመቻቸለትን ታሪካዊ አጋጣሚ ተጠቅሞ ይደቆስ የነበረውን ኦህዴድ ከወደቀበት ለማንሳት ሙከራዎችን እያደረገ ይመስለኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኦህዴድ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አንዳንድ አጀንዳዎችና አቋሞችን የአባዱላ ግፊት እንዳለባቸው ስናስተውል፣ «ጄነራሉ» ወሳኝ ሰው ለመሆን እያደረገ ያለው የጥንጣን ጉዞ ምን ያህል እየሰመረለት እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ይህንን መከራከሪያ ከለጠጥነው ደግሞ፣ ከህወሓት/ብአዴን ጋር ትከሻ መገፋፋት ጀምሯል ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ ይህም ባይሆን እንኳ ከኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ ተሰሚነት እንዳለው ለመናገር የሚያስደፍሩ ማስረገጫዎች አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀን የከዳ ዕለት በተናጠል በኃላፊነት ሊያስጠይቁት የሚችሉ ጉዳዮችን ሳይቀር፣ በያዘው ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን ከመወሰን ይልቅ በቡድን እንዲያልቅ ሲስማማ፤ በግልባጩ አፈ-ጉባኤው ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ውስጥ ተነስተው ለአቶ መለስ ይቀርቡ የነበሩ ጉዳዮችን ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ሲቋጫቸው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡ ኦህዴድንም በሚመለከት ‹በድርጅታዊ መደጋገፍ› ስም ማንም ጣልቃ መግባት እንደማይችል በይፋ እስከ መናገር መድረሱን ምንጮች ጠቅሰውልኛል፡፡ በቀጣይ አመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶም እየተደረገ ባለው ዝግጅት በሃሳብ አመንጭነት እየተሳተፈ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ለምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተወከሉ እና ምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች /ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በተገኙበት/ «የአውራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያት» በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረቡ አስረጅ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ ስርዓቱ በምርጫ ስም የሚፈፅመውን ደባ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው፣ ሁለቱ የቦርዱ ኃላፊዎች የዚህ አይነቱ ውይይት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነው)፡፡ እንዲሁም ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በአዳማ ለክልል አፈ-ጉባኤዎች ሰፊ ትንተና ሰጥቷል፡፡
የአባዱላ ገመዳንና የበረከት ስምኦንን መገፋፋት በጨረፍታም ቢሆን ሊያሳይ የሚችለው ሌላኛው ሁነት ደግሞ ወ/ሮ አና ጎሜዝን አስመልክቶ ሊነሳ የሚችለው ነው፡፡ በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፉ «የቅኝ-ገዥነት መንፈስ ያልለቀቃት» ብሎ የገለፃትን አና ጎሜዝ (የመለስ በስድብ የተሞላ የኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ መጣጥፍ ሳይዘነጋ)፣ ከሁለት ወራት በፊት አዲስ አበባ

በመጣችበት ወቅት አባዱላ በጓዳዊ ስሜት እንዳስተናገዳት ራሷ ከመመስከሯም በዘለለ፣ እነርሱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣቸው «እየተመካከርን ነው» የሚል የወዳጅነት መንፈስ የረበበበት የፎቶ ዘገባ ማቅረባቸውን እናስታውሳለን፡፡ ይህች ተራ የምትመስል ሁነት ለበረከት የምታስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ‹እናንተ እንደሰይጣን የረገማችሁትን ሁሉ እየተከተልን አንረግምም» የምትል እኩዮች ነን አይነት ትከሻ መጋፋት ትመስለኛለች፡፡
በአናቱም አባዱላ አብዛኛው የኦህዴድ አመራርን በዙሪያው ማሰባሰብ ስለመቻሉ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም በአደባባይ እስከመዘላለፍ የተደራረሱትን አቶ ሙክታር ከድርንም ከጎኑ ማሰለፍ ችሏል፡፡ በአንድ ወቅት የግል ጠባቂው የነበረውና አሁን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አብይ አህመድ በእንዲህ አይነቱ ጊዜ ውለታ ለመመለስ የሚያደርገው ተጋድሎ የማይናቅ ጠቀሜታ አስገኝቶለታል፡፡ የሰሞኑ ሹም ሽርም የራሱ የሆነ አንድምታ አለው፡፡ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማዕከላዊ ኮሚቴ ድምጽ ከስልጣኑ የተሻረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አለማየሁ አቱምሳ (እርሱን ማንሳት የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው ብቻ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በርግጥ ሰውየው አሁን አልፏልና በባህላዊ ልማዳችን መሰረት ነፍስ ይማር ብለን እናልፋለን) በ2002ቱ ምርጫ ማግስት አቶ መለስ ከካድሬዎቹ ይሁንታ ውጪ አባዱላን ለመተካት ያመጣው እንደነበር ይታወሳል፡፡ (በነገራችን ላይ በወራት እድሜ ውስጥ በመለስ የተሾሙ የክልል ፕሬዚዳንቶች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ከሽፈራው ሽጉጤ እና አያሌው ጎበዜ ቀጥሎ አለማየሁ አቱምሳ ሶስተኛው ሰው መሆኑ ነው) የድርጅቱ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሆነው የተመረጡት ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞም የአባዱላን የበላይነት ለመቀበል ግለ- ሂሳቸውን ውጠዋል፡፡ ይህም ሆኖ የክልሉ አስተዳዳሪ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ ገና መልስ አላገኘም፡፡ ምናልባት (ከስራ አስፈፃሚዎችም መካከል መምረጥ እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ) በሌሎች አካባቢዎች እንደታየው ከድርጅቱ ሊቀ-መናብርት (ሙክታርና አስቴር) አንዳቸውን መሾም ቢፈልጉ እንኳ ዕውን የሚሆንበት ዕድል የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት አባል አይደሉምና፡፡ በእኔ ግምት እስከሚቀጥለው የምርጫ ዘመን ድረስ ቦታው አዲስ ሰው ሳይሰየምበት በምክትል ፕሬዚዳንቱ አብዱል አዚዝ ስር እንዳለ የሚቆይ ይመስለኛል፡፡
ከምርጫው በኋላስ? ….አፈ-ጉባኤው በኦህዴድ ውስጥ ለማስፈን እየሞከረ ካለው «አምልኮ አባዱላ» ተነስተን «ተገፈተርኩበት!» የሚለውን ያደረ ቁጭቱን ስንደምርበት ወንበሩን ራሱ ይይዘው ይሆናል ከሚል ጠርዝ ያደርሰናል፤ አሊያም ከሽርኮቹ ሙክታር ከድር እና ወርቅነህ ገበየው አንዳቸውን አሾሞበት በጨፌ ኦሮሚያም የሚካኤል ስሁልን መንፈስ ማንበሩ አይቀርም ብሎ ቅድመ ግምት ማስቀመጥ ይቻላል (ይህ መላምት የህወሓት-ብአዴን ጥንካሬ በዚሁ ከቀጠለ እና የእነርሱ ፍላጎት ደግሞ የተለየ ከሆነ ከህልም ሊዘል አለመቻሉን በማመን ላይ የተመሰረተ ነው)
ኦህዴድን ካነሳን የሌንጮ ለታን ኦዴግን መፃኢ እድልም መመልከት ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ወስኖ ጨርሷልና፤ ሂደቱንም ለማመቻቸት ከግንባሩ መሪዎች አቦ ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ሌንጮ ባቲ፣ ዶ/ር ዲማ ነጎዎ፣ ዶ/ር ታደሰ ኤባ እና ዶ/ር በየነ አሰቦ ጋር ከስምምነት ለመድረስ፣ ኢህአዴግ በውጪ ሀገር ከሚገኙት የጄኔራል ታደሰ ብሩ ልጆች በተጨማሪ፣ ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፓስተር ዳንኤል፣ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ በቀለ ነዲ (የአዋሽ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ)፣ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን የመሳሰሉ አደራዳሪዎችን ማሳተፉ ይነገራል፡፡
ይህም ሆኖ ድርድሩ በስኬት ተቋጭቶ ኦዴግ ሀገር ቤት መግባት ቢችል እንኳ፣ ኦህዴዶች ‹አያሰጋንም› የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ፡፡ ግና፣ ያለፉት ሁለት አስርታት ዘግናኝ ክስተቶች አሻራ ዛሬም በረዣዥሞቹ የባሌ ተራሮች በጉልህ ተቸክችኮ የመታየቱ እውነታ፣ በስርዓቱ ላኮረፈው የኦሮሚያ ህዝብ፣ ኦዴግን አማራጭ የሚያደርግበት «አኪር» ሸሽጎ ይዞ እንደሆነ ማን ያውቃል? ይህ እንግዲህ እነ ሌንጮ «ካዳሚ» ለመሆን አይመጡም በሚል ስሌት ከተቃኘ ነው፡፡ ይሁንና ከድርድሩ ጀርባ ያለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት
ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ውስብስብ የሚያደርጉ ክስተቶችን ግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይኸውም በአፈ-ጉባኤ አባዱላ ፊት አውራሪነት ስር ለመጠናከር እየሞከረ ያለው ኦህዴድ፣ ከሰዎቹ ሀገር ቤት መግባት ምን ያተርፋል? ምንስ ያጣል? ከሚለው ጋር ይያያዛል፡፡
መቼም የኦዴግን መምጣት፣ ኦቦ ሌንጮ «እንጮቴ» (ተወዳጅ ባሕላዊ ምግብ ነው) በአይኑ ላይ እየተመላለሰ እንደሆነ ከሰነዘረው ቀልድም ሆነ «ከሌሎች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዘመናዊ ፌደራሊዝምን እመሰርታለሁ» ብሎ በደምሳሳው ከገለፀው ዓላማው ጋር አያይዞ ማለፍ አይቻልም፡፡ አሊያም ያኔ እርሱ ሸገርን ተሰናብቶ ሲወጣ ገና ያልፀደቀውን አንቀፅ 39ን «አስፈፅማለሁ» በሚል ቀቢፀ-ተስፋ ተገፍቶ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ በግልባጩ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ‹የኦዴግ መሪዎች በኦነግ ዘመን ለእስር የዳረጓቸውን በሺ የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ተወላጆችን ለማስፈታት ሲሉ፣ በታማኝ ተቃዋሚነት ለመታገል ወስነው ነው የሚመጡት› የሚለውን መከራከሪያቸውን ለመቀበል የሚቸግረው ደግሞ፣ እስረኞቹን መፍታት ለሃያ አመታት ያህል በክልሉ ላይ ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የሚታወቀውን ኦህዴድን ሊያሳጣ የመቻሉ ነገር ነው፡፡ ያም ተባለ ያ፣ «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲል ጠቢቡ

ሰለሞን ሁሉም ቋጠሮ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል፡፡ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው በኦህዴድ ውስጥ አባዱላ ገመዳ ወሳኝ እየሆነ የመምጣቱ እውነታ ብቻ ነው፡፡
ህወሓት-ብአዴን
በዋናነት ሀገሪቷን እንደሚያሽከረክሯት የሚነገርላቸው ህወሓት እና ብአዴን፣ በመጪዎቹ ጊዜያት ‹ኢህአዴግ ለዳግም ክፍፍል ሊዳረግ ይችላል› በሚል ፍርሃት ድርና ማግ ሆነው እየሰሩ ስለመሆኑ እየሰማን ነው፡፡ በርግጥ ‹መለስ ህወሓትን አዳክሞ ነው ያለፈው› የሚል የትግርኛ ተናጋሪዎች ድምፅ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል (በነገራችን ላይ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የህወሓትን የምስረታ በዓል የካቲት 11ን በብሔራዊ ደረጃ ማክበር መቅረቱን በይፋ ከማወጃቸውም በላይ፣ መለስ ራሱ ለመጨረሻ ጊዜ በመቀሌው የሰማዕታት አዳራሽ የተገኘው 35ኛው ዓመት በተከበረበት ወቅት ነበር፡፡ ይሁንና ከህልፈቱ በኋላ ድርጅቱ የደረሰበትን ድክመት ለመሸፋፈን በደመቀ መልኩ እያከበረው ይገኛል፤ ለዚህም ይመስለኛል በአምናውም ሆነ በዘንድሮው በዓል ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መቀሌ የሞቀ ተገኝቶ ንግግር ከማድረግም አልፎ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ጋር በትግሉ ዘመን በተቀነቀኑ ዜማዎች ሲደንስ በቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተን ሦስተኛው ሚሊንየም ገባ እንዴ? ብለን ግራ የተጋባነው፡፡ አልበሽርስ አንድ ቻርተር አውሮፕላን ለክልሉ በስጦታ ያበረከተው ዕውን በዓሉን አስመልክቶ ነው? ወይስ በምትኩ የተሰጠው ነገር ኖሮ? መቼም የህወሓት የምስረታ በዓል እንዲህ ሊያስፈነጥዘው እይችልም)
‹ህወሓት ተዳክሟል› የሚለውን ቅሬታ የሚያሰሙ የቅርብ ሰዎች፣ ድርጅቱ አቅምና ልምድ በሌላቸው መሪዎች ስር ማደሩን ይጠቅሳሉ፡፡ ተስፋ የጣሉበት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ቢሆን ከአምባገነንነቱም በላይ ሀሳቡን አፍታቶ የማስረዳት ችሎታው ደካማ መሆን መፍትሄውን አርቆ ሰቅሎታል፡፡ እንደ ድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አገላለፅ የ«ጠንካራ ተተኪ» አልቦነትን ለመረዳት፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኃላፊነቱ በተነሳው አቶ ዘርዓይ አስገዶም ቦታ ላይ የዋልታ ስራ አስኪያጅ መመደቡ እና ራሱ ዘርዓይም በጓሮ በር የብሮድካስት ባለስልጣን ሆኖ መሾሙን (አዲስ ፊት አለመታየቱን) መመልከቱ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘው አርከበ እቁባይም ለአመራርነት ለቀረበለት ጥያቄ እያንገራገረ እንደሆነ ተሰምቷል፤ አቦይ ስብሃት ነጋም ኢ-መደበኛ በሆነ የጠረጴዛ ወግ ህወሓት «በግብር በላ» መሪዎች እጅ መውደቁን በቁጭት መናገራቸው ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና በዚህ ቀውጢ ወቅት ሁለት ተቋማት ድርጅቱን ለጊዜውም ቢሆን ፖለቲካዊ ጉልበቱን እንዳይነጠቅ ታድገውታል፡፡ ደህንነቱ እና ሰራዊቱ፡፡
የሆነው ሆኖ ህወሓት ዛሬም ከብአዴን ጋር በማበር (በአባይ ፀሐዬ እና በበረከት ስምኦን የፊት መሪነት) የፖለቲካው አሽከርካሪነቱን እንዳስከበረ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች የስርዓቱን ርዕዮተ-ዓለምንም (በተለይም አብዮታዊ ዲሞክራሲን) ከሌሎች ጓዶቻቸው በበለጠ ማብራራት እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ በጅጅጋ ከተማ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተከበረበት ወቅትም ሆነ ከሳምንታት በፊት በመቀሌ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ አባይ ፀሐዬ የርዕዮተ-አለሙ «ተንታኝ» ሆኖ የቀረበው ከዚህ አኳያ ነበር፡፡ በአናቱም አባይ እና በረከትን ጨምሮ ከኦህዴድ ኩማ ደመቅሳ፤ ከደኢህዴን ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡ በዋናነት ለኢህአዴግ የስልጣኑ መሰረት (ከታጠቀው ኃይል እና ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬው በተጨማሪ) ‹በልማታዊ መንግስት፣ በጥርነፋ፣ ሳር-ቅጠሉን በማደራጀት፣ የብሔር ጉዳይን በማጎን እና መሰል ጭብጦችን በማስጮኽ የሚያምታታበት ርዕዮተ-ዓለሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የእነ በረከት የተሰሚነት ምስጢርም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በርግጥም የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. የተሰበሰበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከልን ለማቋቋም የሚያስችል ደንብ ማፅደቁን እና የአራቱም ድርጅት የአ&#4632

የፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ

የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
ፓትርያርኩ ጽኑ አቋም ስለሌላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
ፓትርያርኩ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸውብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል

Image

የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ። ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ።
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኩኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፤ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናንም የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው አጀንዳነት አስይዘው ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦች ሕጎች፣ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው ተደርጎ የሚሻሻልበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
አቡነ ማትያስ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ ‹‹በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት›› የሚመዘን፣ ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚህ መግለጫቸው ላይ በመወያየት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት፣ ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ መተርጎም በሚያስችል ኹኔታ በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያም ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ፣ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ የብዙኃን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረበላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልፀዋል።
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የሚናገሩት አንድ አገልጋይ፤ የፓትርያርኩ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ እንዳነሣሣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፤ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት ይጋራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታም ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም ብለዋል፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ከሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙና ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱን አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት፣የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቀፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን “እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስትያን በአባትነት ለመምራት ተግዳሮቱ የበዛ ቢሆንም ወደ ዕድገትና ሥልጣኔ የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

Image

(አፈንዲ ሙተቂ)
———-
ኤርትራን በኢትኖግራፊ መነጽር በዳሰስኩበት የክፍል አንድ ጽሑፌ ላይ የተሰነዘሩ አንዳንድ አስተያየቶች የኤርትራን ችግር ከመሰረቱ እንዳስሰው አነሳስተውኛል፡፡ በተለይም ብዙዎች የሚሳሳቱባቸውን ነጥቦች ማብራራት ተገቢ ሆኖ ታይቶኛል፡፡ ስለዚህ በራሴ ጥናት በደረስኩበት መደምደሚያ መሰረት የግል እምነቴን የሚያንጸባርቀውን ይህንን መጣጥፍ አሰናድቻለሁ፡፡

====የኤርትራ ጥያቄ አነሳስ===

አንዳንዶች “የኤርትራ ጥያቄ በኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች የተፈጠረ የስነ-ልቦና መቃወስ ነው” የሚል እይታ አላቸው፡፡ ይሁንና ይህ አነጋገር ከመሰረታዊ የታሪክ ሐቅ ጋር ይጋጫል፡፡ የኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች ኤርትራን ለ60 ዓመታት ይዘዋታል፡፡ ይሁን እንጂ ህዝቡን የተለየ ስነ-ልቦና ያለው ህዝብ አድርገው ለመቅረጽ ብዙም አልሞከሩም፡፡ በሌላው የአፍሪቃ ሀገር እንደሚታየው ኤርትራዊያን ከጥንታዊ ማንነታቸው ብዙም አልተለወጡም፡፡ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን በሚገባ አስጠብቀዋል፡፡ ለምሳሌ በኢጣሊያዊት ኤርትራ ጣሊያንኛ መናገር የሚችለው ህዝብ ከመቶ አስር እጅ ብቻ ነበር፡፡

የኤርትራ ጥያቄ መንቀልቀል የጀመረው በእንግሊዞች አስተዳደር ዘመን ነው፡፡ በዚያ ዘመን ፓርቲ፣ የሙያ ማህበራት፤ ነጻ ፕሬስ፣ ወዘተ በተግባር ላይ በመዋላቸው ህዝቡ በግዛቲቱ የወደፊት እጣ ላይ እንዲነጋገር መንገድ ከፍተዋል፡፡ ይህ ውይይት ተጧጡፎ ሁለት ተጻራራ ጎሳዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፤- የአንድነትና የነጻነት ጎራ፡፡ ታዲያ የአንድነት ጎራው ዛሬ እንደሚባለው መላውን የኤርትራ ህዝብ የሚወክል አልነበረም፡፡ የነጻነት ደጋፊም ዛሬ እንደሚባለው በጣም አናሳ አይደለም፡፡ ከተባበሩት መንግሥታትና ከልዩ ልዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት 40% የሚሆነው የራቢጣ ኢስላሚያ ፓርቲ ደጋፊ እና 6 % የሚሆነው የሊበራል ፕሮግሬሲቭ ፓርቲ (የወልደአብ ወልደማሪያም ፓርቲ) ደጋፊ “ነጻነት”ን ይፈልጉ ነበር፡፡ የአንድነት ደጋፊዎች (የሀገር ፍቅር ማህበር አባላትና ሌሎቹም) ብዙሃን የነበሩ መሆናቸው ትክክል ቢሆንም ከኤርትራ ህዝብ 48 % የሚሆነውን ብቻ ነበር የሚወክሉት፡፡ የተቀረው አነስተኛ ቡድን ፕሮኢታሊያ (የጣሊያንን ሞግዚትነት የሚፈልግ ፓርቲ) ደጋፊዎች ነበሩ (እነዚህኛዎቹ ከኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች የተወለዱ ክልሶቸ ነበሩ)፡፡

የኤርትራን ጥያቄ ከዐረቦች ተንኮልም ከእስልምና ተስፋፊነት ጋር ማያያዝም አግባብ አይደለም፡፡ ጥያቄው በኤርትራ ምድር ነው የተነሳው እንጂ በዐረቦች ዘንድ አይደለም፡፡ ዐረቦች ከጥንት ጀምሮ ሁለታችንንም “ሐበሻ” ነው የሚሉን፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ኤርትራን ለመያዝ የዘመተችው ግብጽ ፍላጎቷ ሁሉንም የሰሜን ምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት ጠቅላላ በመያዝ የአባይን ምንጭና የቀይ ባህር ንግድን መቆጣጠር እንጂ ኤርትራን ለብቻ ገንጥላ የተለየ ቀጣና ማድረግ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነበር ግማሽ ጦሯን ይዛ ከዘይላ እስከ ሀረር ድረስ የተዘረጋ ግዛት የመሰረተችው፡፡ በኤርትራ በኩል ግን ከምጽዋ በስተቀር ሊሳካላት አልቻለም፡፡ በራስ አሉላ የሚመራው ጦር ድባቅ እየመታት መልሶአታል፡፡ በታጁራና ጅቡቲ በኩል የመጣውን ጦሯን (በኮሎኔል ሙዚንገር የሚመራውን) ደግሞ የአፋር ጀግኖች ደምስሰውታል፡፡

በእንግሊዞቹ ዘመን የነጻነቱን ጥያቄ በስፋት ይደግፉ የነበሩት ሙስሊሞች እንደነበሩ መካድ አይቻልም፡፡ ሙስሊሞቹ ይህንን ሃሳብ ሲያቀነቅኑ የነበሩት በዘመኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ይታይ ከነበረው ተጨባጭ እውነታ በመነሳት እንጂ “ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ስለሚጠሉት አይደለም፡፡ የኤርትራዊያኑ ሙስሊሞች ስጋት “በኃይለ ሥላሤዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተቀላቀልን በሀይማኖታችን ምክንያት ከፍተኛ ጭቆና ይፈጸምብናል፤ ስለዚህ ኤርትራ ነጻ ሀገር ብትሆን ነው መብታችን የሚከበረው” የሚል ነው፡፡ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት የሙስሊሞቹን ስጋት ለመቅረፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ቢወስድ ኖሮ የኤርትራ ጥያቄ ባልተከሰተ ነበር፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለቱ ጎራዎች ተቀራራቢ ሚዛን ነው የነበራቸው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንድትተሳሰር ያደረገበት አንዱ ምክንያትም የሁለቱ ጎራ ደጋፊዎች የተቀራረበ የሀይል ሚዛን (46ለ48) ያላቸው መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ በሌላ በኩል በእንግሊዞች አስተዳደር የመጨረሻ ዓመታት በሁለቱ ጎራዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሽኩቻና መጠፋፋት ይካሄድ ስለነበር የተባበሩት መንግሥታት የትኛውንም ጎራ ደግፎ ጥያቄውን ቢፈታው የከረረ የርስ በርስ ጦርነት ይከሰታል የሚል ፍርሃት አድሮበት ነበር፡፡ በመሆኑም “ኤርትራ በፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ጋር ብትዋሃድ በሁለቱም ጎራ መካከል ፍጅት እንዳይቀሰቀስ ለማገዝ ይችላል” የሚል እምነት ነበረው፡፡

=====የፌደሬሽኑ ፎርሙላ====

ይህኛውም ብዙ ሰዎች የሚሳሳቱበት ነጥብ ነው፡፡ የኃይለ ሥላሤ መንግሥትም ሆኑ የደርግ መንግሥት ደጋፊዎች ለኤርትራ የተፈቀደው ፌዴሬሽን ምን ዓይነት እንደሆነ ግንዛቤው ያላቸው አይመስለኝም፡፡ “ፌዴሬሽኑ መነካት አልነበረበትም” የሚል ሐሳብ ሲሰነዘር ለተቃውሞ የሚነሱትም በዚሁ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ በሌላ በኩል የነጻነት ጎራ ደጋፊዎች በተባበሩት መንግሥታት የተፈቀደውን የፌዴሬሽኑን ፎርሙላ ከከፍተኛ ቅሬታ ጋር የተቀበሉት መሆናቸውም ይረሳል፡፡

ለኤርትራ የተፈቀደው ፌዴሬሽን ዛሬ ላይ ተሁኖ ሲታይ እጅግ በጣም “ሊበራል” የሚባል ነበር፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶችም በዚያ ሞዴል ቢቀረጹ ኖሮ ዛሬ የሚታየው ምስቅልቅል ሁኔታ ተለውጦ ሀገራችን ሌላ መልክ በያዘች ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነጻ ያልወጡት ሶማሊላንድና ጅቡቲም የኛ አካላት ሊሆኑ ይችሉ ነበር ለማለትም ያስደፍራል፡፡ ነገር ግን ንጉሡና ባለሟሎቻቸው በግዴለሽነት ሰረዙት፡፡
——
ኤርትራ በወቅቱ ከኢትዮጵያ ጋር የተዋሃደችበት ፌዴሬሽን በትክክለኛው አገላለጽ ሲታይ “ሙሉ ራስ ገዝ አስተዳደር” የሚባል ነው፡፡ ኤርትራ የራሷ ፓርላማ፣ ህግ አስፈጻሚና ህግ ተርጓሚ አካላት አሏት፡፡ መንግሥቱን የሚመራው “ዋና ስራ አስፈጻሚ” (Chief Executive officer) በፈረቃ ከክርስቲያን ደገኞቹና ከሙስሊም ቆለኞቹ እንዲመረጥ ተወስኗል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው ክርስቲያን ከሆነ የፓርላማው ፕሬዚዳንት ከሙስሊም ቆለኞች ነው፡፡ ስራ አስፈጻሚው ከቆለኞቹ ሲመረጥ ደግሞ የፓርላማው ፕሬዚዳንት ከደገኞች ይሆናል፡፡

የኤርትራው ራስ ገዝ አስተዳደር ከውጭ ጉዳዮች፣ ከገንዘብ ነክ ጉዳዮች፣ ከንግድና ከመገናኛ በስተቀር በሁሉም ነገሮች ላይ መወሰን ይችላል፡፡ እነዚህ አራት ዘርፎች የሚመሩት የፌዴራሉ መንግሥት ሆኖ በሚሰራው የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ነው፡፡ የምጽዋና የአሰብ ወደቦችም በፌዴራሉ መንግሥት ስር ነበር የሚተዳደሩት፡፡
—-
ታዲያ ይህ ፌዴሬሽን ምን በደለ?. ምን አጠፋ?… ይህንን ፌዴሬሽን ለማፍረስ መቸኮል አግባብ ነው?…. ዛሬ እኮ ለኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ያልተማከለ አስተዳደር ያስፈልጋታል ነው እያልን ያለነው፡፡ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ግን በማን አለብኝነት አጠፋውና ረዥሙን ጦርነት ቀሰቀሰ፡፡ የሀገራችንም ታሪክ ሌላ መልክ ያዘ፡፡

===ፌዴሬሽኑ እንዴት ፈረሰ?====

ሌላው በብዙ ሰዎች የሚሰነዘረው አባባል “ፌዴሬሽኑ የፈረሰው በአንድነት ኃይሎች ሙሉ ፈቃደኝነትና ግፊት ነው” ይላሉ፡፡ ይህኛውም አባባል ምንም ማስረጃ የለውም፡፡ እንዲያውም በፌዴሬሽኑ ዘመን የፌዴሬሽኑ አስተዳዳሪዎች ይከተሉት ከነበረው አድሎአዊነት የተነሳ ከአንድነት ጎራ ደጋፊዎች መካከል እጅግ የሚበዙት የፌደሬሽኑ ተቃዋሚ በመሆን የነጻነቱን ጎራ ተቀላቅለዋል፡፡ በተጨማሪም የቢትወደድ አስፋሓ መንግሥት በኤርትራ ሰራተኞችና የሙያ ማህበራት ላይ በሚያካሄዳቸው የእመቃ ተግባራት ብዙዎችን አስቀይሟል፡፡ ስለዚህ የአንድነት ሀይሎች ጉልበት ኖሯቸው በመንግሥቱ ላይ ግፊት የሚፈጥሩበት ሁኔታ በጭራሽ አልነበረም፡፡ አብዛኛው የኤርትራ ህዝብ “አደይ ኤሪትሪያ”ን መዘመር የጀመረው በነዚያ አመታት ነው፡፡

ፈዴሬሽኑን በግልጽ ያፈረሱት የቢትወደድ አስፋሓ ደጋፊችና ጄኔራል አቢይ አበበን የመሳሰሉ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ሹማምንት ናቸው፡፡ ቢትወደድ አስፋሓ ከመጀመሪያኑ በኤርትራ የተሾሙት ለዚሁ ነበር፡፡ እኝህ ሰው በኤርትራ ተወለዱ እንጂ አልኖሩባትም፡፡ ዕድሜአቸውን ያሳለፉት እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በትርጉም ስራ ላይ ነበር፡፡ በጣሊያን ወረራ ዘመን በአዲስ አበባ ሀገረ ገዥነት ተሹመው በአዲስ አበባ ገነተ-ልዑል ቤተ መንግሥት የሚቀመጡት የዱክ ኦፍ አኦስታ እና የጄኔራል ናዚ አስተርጓሚ ነበሩ፡፡ በኋላም በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለጣሊያን መንግሥት በአስተዳዳሪነት ተሹመው ለሰጡት አገልግሎት ቤኒቶ ሙሶሎኒ ፊት ቀርበው የፈረሰኛ ኒሻን ተሸልመዋል (አምባሳደር ዘውዴ ረታ፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ ገጽ 461-462 ተመልከቱ)፡፡

ቢትወደድ አስፋሓ ለሶስት ዓመታት በኤርትራ ፌዴሬሽን የንጉሠ ነገሥቱ ምክትል እንደራሴ ነበሩ፡፡ በዚያ ዘመን በደጃች ተድላ ባይሩ የሚመራው የኤርትራ አስተዳደር በሁለት እግሩ ቆሞ እንዳይሰራ በማድረግ ተግባር ላይ ነው የተጠመዱት፡፡ በዚህ ረገድ ከዋናው እንደራሴ ራስ አንዳርጋቸው መሳይ (ሁለተኛው የልዕልት ተናኘወርቅ ባለቤት) ጋርም ዘወትር ይወዛገቡ ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር አጼ ኃይለ ሥላሤ አማቻቸው በቢትወደድ አስፋሓ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ በስራ ከመበለጥ የመጣ የዝቅተኝነት ስሜት (inferiority complex) አድርገው መቁጠራቸው ነው፡፡

ቢትወደድ አስፋሓ ከ1955 ጀምሮ ፌደሬሽኑ እስከፈረሰበት ድረስ (1962) ቺፍ ኤክስኩቲቭ ኦፊሰር ወይንም የራስ ገዙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ በሉ፡፡ የኤርትራን ዋና አስፈጻሚ የሚመርጠው የኤርትራ ፓርላማ ነው፡፡ ተመራጩ የፓርላማው አባል መሆን አለበት፡፡ ይሁንና የአጼ ኃይለ ሥላሤ “የኤርትራ ስራ አስፈጻሚ የግዴታ የፓርላማው አባል መሆን የለበትም” በሚል የጉልበተኝነት ስሜት ቢትወደድ አስፋሓ ለፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚነት እንዲመረጡ አድርገዋል፡፡

ቢትወደድ አስፋሓ የኤርትራ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሲሾሙ መጀመሪያ ያደረጉት ነገር ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ህጋዊ ሽፋን ለማሰጠት የኤርትራ ፓርላማ የኃይለ ሥላሤ መንግሥት እንደሚፈልገው አድርጎ ማዋቀር ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በተባበሩት መንግሥታት ታዛቢነት የሚካሄደውን የምርጫ ዘይቤ ለወጥ በማድረግ አሁን በአፍሪካ የሚካሄደውን የምርጫ ቲያትር አመጡ፡፡ ለምሳሌ ከምዕራብ ቆላ በሚመረጡ ሙስሊሞች ወንበሮች ላይ ለርሳቸው ታማኝ የሆኑትን የደጋ ሙስሊሞችን አስመርጠዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ነበር ፌዴሬሽኑን የማፈራረሱ ስራ የተጀመረው፡፡ ፓርቲዎች ታገዱ፡፡ ነጻ ፕሬስም ታገደ፡፡ የሰራተኛ ማህበራትም ታገዱ፡፡ “ዐረብኛ የባዕድ ቋንቋ ነው” በሚል ከህገ-መንግሥቱ ተፍቆ ወጣ፡፡ ከዚያም የኤርትራ ባንዲራ እንዳይውለበለብ ተደረገ፡፡ በማስከተልም ትግርኛ ከስራ ቋንቋነት ተሰረዘ፡፡ በምትኩ አማርኛ የስራ ቋንቋ ሆነ፡፡ “ዋና ስራ አስፈጻሚ” የሚለው የፌዴሬሽኑ ገዥ መጠሪያም “ዋና አስተዳዳሪ” በሚል ተተካ፡፡ ፡ በመጨረሻ ላይ “የኤርትራ ፓርላማ ወስኗል” በሚል ፌዴሬሽኑ ፈረሰ፡፡

ፌዴሬሽኑ እንዲህ እየተገዘገዘ ነበር ቀስበቀስ የፈረሰው፡፡ የፈዴሬሽኑ አፍራሾችም ድሮ ለአንድነት የታገሉ የአንድነት ሀይሎች ሳይሆኑ ቢትወደድ አስፋሓ በሚፈልጉት መንገድ የተመረጡ አድር ባዮች ነበሩ፡፡

ይህንን የቢትወደድ አስፋሓን ታሪክና የማምታት ዘዴ ብዙዎች ጽፈውታል፡፡ በአማርኛ ታሪኩን በሰፊው የጻፉት ግን አምባሳደር ዘውዴ ረታ ናቸው፡፡ አምባሳደር ዘውዴ መጽሐፉን ሲጽፉ ቢትወደድ አስፋሓን የአንድነትና የነፃነት ጠበቃ በማድረግ ነው የሚያንቆለጳጵሱት፡፡ ቢትወደድ አስፋሓ የወሰዱትን እርምጃ አንድ በአንድ እየተረኩልን እንኳ ህገ-ወጥነታቸውን ያደንቁላቸዋል፡፡ ታዲያ በጣም የሚያሳዝነው ነገር በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ለማስመለስ ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግልና ፌዴሬሽኑ እንዳይፈርስ ያደረጉት ጥረት ሰፋ ብሎ የቀረበ መሆኑ ነው፡፡ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ለአጼ ኃይለ ሥላሤ “በህግ ፈርመን የተቀበልነውን አደራ ማክበር አለብን” የሚል ተደጋጋሚ ምክር ቢሰጧቸውም ንጉሡ በጭራሽ ሊሰሟቸው አልፈቀዱም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት ሀገር የመሆናቸው እርሾ ተጠነሰሰ፡፡

===የኤርትራ ነጻነት ትግል እና የኤርትራዊነት ስነ-ልቦና===

የኤርትራ ነጻነት ትግል የተለኮሰው ፌዴሬሽኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ታዛቢዎች በወጣለት ህገ-መንግሥት መሰረት ስራዎቹን በአግባቡ ማከናወን ስላቃተው ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በ1950ዎቹ አጋማሽ አብዛኛው ህዝብ ከአንድነት አቀንቃኝነት ወጥቶ ወደ ነጻነት ፈላጊው ጎራ መቀላቀል ጀምሯል፡፡ ትግሉን በተደራጀ መንገድ የመጠንሰሱን ሃሳብ የወጠነው ግን ሰባት ሰዎች የመሰረቱት “ማህበር ሸውአተ” የሚባለው እድር መሳይ ማህበር ነው፡፡ ይህ ማህበር ከጥቂት ጊዜ በኋላ “ምንቕስቓስ ሓርነት ኤርትራ” (“ሐረካት ታሕሪረል ኤሪትሪያ”/Eritrean Liberation Movement) የሚባል ድርጅት ወለደ (ድርጅቱ በታሪክ ምዕራፎች “ሐረካ” እየተባለ ነው የሚጠራው)፡፡

“ሐረካ” ወደ ትግሉ የገባው ፌዴሬሽኑ ከመፍረሱ ከሶስት ዓመታት አስቀድሞ ነው፡፡ የትግሉ ዋነኛ ዓላማም “የኤርትራ ፌዴሬሽን በህገ-መንግሥቱ መሰረት ስራውን እንዲያከናውን መጠየቅ” ነበር፡፡ ይሁንና አብዛኛው ኤርትራዊ ኤሊት ለአስር ዓመታት ባየው የፌዴሬሽኑ አሰራር ተስፋ የቆረጠ በመሆኑ “የፌዴሬሽን አሰራርን በጭራሽ አንቀበልም” ባይ ሆነ፡፡ በተለይም የቀድሞ የኤርትራ ፓርላማ አባላት በዚህ ላይ ግትር አቋም ያዙ፡፡ በመሆኑም ከነጻነት በመለስ ሌላ አማራጭ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆነው “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” ወይንም “ጀብሃት ታሕሪረል ኤሪቲሪያ” (ጀብሃ) እ.ኤ.አ መስከረም ወር 1961 በካይሮ ከተማ ብዙ ህዝብ በተሰበሰበት ተመሰረተ፡፡ ጀብሃ ትግሉን ለሃያ ዓመታት ከቀጠለበት በኋላ በውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ተዳክሞ ሲወድቅ ከርሱ የተገነጠለው “ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ” ወይንም “ጀብሃት አሽ-ሻዕቢያ ሊ-ተሕሪረል ኤሪቲሪያ” (ሻዕቢያ) እርሱን ተክቶ መዋጋቱን ተያያዘው፡፡ በ1983 (1991) ኤርትራ ነጻ ሀገር ሆነች ፡፡ የኤርትራ የነጻነት ትግል የተጓዘበት መንገድ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ “የቅኝ ገዥዎች ተንኮል”፣ “የዐረቦች ሸር” ወዘተ.. የሚሉ ሰበቦችን መደርደር ራስን መደለል ነው፡፡

ኤርትራዊነት “የቅኝ ተገዥነት ስሜት የፈጠረው የተቃወሰ ስነ-ልቦና ነው” የሚለውም ክስ ከዚሁ ጋር ነው የሚታየው፡፡ ኤርትራዊያንን እስከምናውቃቸው ድረስ ለፈረንጅ ገዥ ያላቸው ስሜት ከኛ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ለዚህም ነበር በ1929-1933 የኢጣሊያ ወረራ ዘመን በርካታ የኤርትራ ጀግኖች ድንበር አቋርጠው ከኢትዮጵያ አርበኞች ጋር የተቀላቀሉት፡፡ የኢትዮጵያ ባንዲራ በኢጣሊያ ወታደሮች መረገጡ አንገብግቦት የጠላቶቹን አንገት በሰይፍ የቀላው ጀግናው ዘርዓይ ደረስ ከተወለደበት ኤርትራ ውጪ የተቀረውን የኢትዮጵያ ክልል ለአንድም ቀን ረግጦ አያውቅም፡፡ ጀግኖቹ አብረሃ ደቦችና ሞገስ አስገዶምም በቅኝ ገዥዋ ኮሎኒያል ኤሪትሪያ ነበር የተወለዱት፡፡ የህዝቡ ስነ-ልቦና በቅዥ ተገዥነት ስሜት የተቃወሰ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ የበረከቱ ጀግኖች በሀገሩ ላይ ባልበቀሉ ነበር፡፡
——
ለኤርትራ ጥያቄ መፈጠር እርሾ የሆነው የቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳይሆን የኛ መንግሥታት ሲያካሄዱት የነበረው ኢ-ፍትሐዊነትና ብሄራዊ ጭቆና ነበር፡፡ ያለፉት መንግሥታት ቤታችንን በማስተካከል ለሁላችንም እንዲመች ቢያደርጉት ኖሮ ጥያቄው ባልተፈጠረ ነበር፡፡ ለዚህ ፋና ወጊ የነበረውን የልጅ እያሱ ፖሊሲ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ይልቅ ከኤርትራዊያን ጋር የማንግባባው “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥ ነበረች” በሚለው አገላለጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቀርቶ ረጅም ሀገር አቋርጠው ምጽዋን ለአራት መቶ ዓመታት የያዙት ኦቶማን ቱርኮች እንኳ ቅኝ ገዥ ተብለው አልተጠሩም፡፡ መንግሥታቶቻችን የኤርትራን ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ለመስማት ባይፈለጉትም አውሮጳዊያን እንዳደረጉት አዲስ ሀገር በወረራ አልያዙም፡፡ መሬቱ ከጣሊያኖች መምጣት በፊት በራስ አሉላ ስር “መረብ ምላሽ” ተብሎ ይተዳደር ነበር፡፡ በጥንቱ ታሪክ ውስጥ ደግሞ ኤርትራ “ባህረ ነጋሽ” የሚል ስያሜ የነበራት ዋነኛዋ የኢትዮጵያ አስኳል እንደነበረች ነው የምናውቀው፡፡ የጥንቱ “አቢሲኒያ” (ሐበሻ) የሚለው አጠራር መጀመሪያ የተፈጠረው በኤርትራና በትግራይ ውስጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን በግንቦት ወር 1983 የለንደን ኮንፈረንስ ሲካሄድ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ማለታችሁ ትልቁ ስህተታችሁ ነው፤ ኢትዮጵያዊያን እኛ እንጂ ሌሎች አይደሉም ብትሉ ኖሮ ትንሽ እውነት ይኖርበት ነበር” ያሉትን መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ የፕሮፌሰር መስፍን አገላለጽ ለዘመናችን ሰው ባይስማማም የታሪክ ሐቅ አለበት፡፡

====የመንግሥታቱ የቅራኔ አፈታት እንከኖች====

የኤርትራን ጥያቄ ያወሳሰበው አንዱ ምክንያት መንግሥታቱ ቅራኔዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አለመከጀላቸው ነው፡፡ ሁሉም ሀገረ ገዥ እና አስተዳዳሪ ጦርኝነትን እንጂ ተስፈኝነትን ሲዘምር አልታየም፡፡ እስቲ ነገሮችን በምሳሌ ላስረዳ፡፡

ጀብሃ በአንድ ጊዜ ብዙ ተከታዮችን ለማፍራት የቻለው ራስ አስራተ ካሣ በሚያካሄዱት የጭካኔ ዘመቻ የኤርትራ ቆላ ህዝብ በብዛት ወደ ግንባሩ በመጉረፉ ነው፡፡ ራስ አስራተ ከሚወስዱት እርምጃ ሳይታረሙ ተከታታይ ዘመቻዎችን ሲያካሄዱ ደግም ህዝቡ በብዛት ወደ ሱዳን ተሰደደ፡፡ የተቀረው ጀብሃን ተቀላቀለ፡፡ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርስ “ሬድ ቲርስ” በተሰኘው መጽሓፋቸው ራስ አስራተ ያዘመቱት ጦር በወሰደው እርምጃ በአንድ ጀንበር ብቻ ከአምስት ሺሕ የማያንስ ህዝብ ማለቁን ያስረዳሉ፡፡

የደርግ መንግሥት ሲመጣም ችግሩ ተባባሰ እንጂ አልተቃለለም፡፡ በተለይም ሻዕቢያ ተከታታይ ድል በሚቀዳጅባቸው የመጨረሻዎቹ ዓመታት ሺዎች በታንክና በመድፍ አልቀዋል፡፡ ለምሳሌም በዓለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ የመነጋገሪያ አጀንዳ ለመሆን የበቃውንና በ1980 በቀይ ባህር ዳርቻ ባለችው የሸዒብ ከተማ ህዝብ ላይ የደረሰውን ፍጅት መጥቀስ ይቻላል፡፡

እነዚህ መንግሥታት የኤርትራን ችግር በሰላም ለመፍታት የወሰዷቸው እርምጃዎች ኢሚንት ናቸው፡፡ ራስ አስራተና የአሜሪካ ሚሊታሪ አዛዦች በአጼ ኃይለ ሥላሤ ጠያቂነት የተቋቋመውን የሰላም ኮሚቴ በመጥለፍ ጀብሃና ሻዕቢያ እንዲጨራረሱ ለማድረግ ሞከሩ፡፡ የደርግ መንግሥት ደግሞ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የክፍለ ሀገሩን ችግር በሰላም ለመፍታት ያግዛሉ በማለት ተስፋ ያሳደረባቸውን ጄኔራል አማን አንዶምን አስገደለ፡፡ እንዲህ ማድረጋቸው ሳያንስ በጄኔራል አማን ላይ ተከታታይ የቅጥፈት ወሬ ማስወራት! ያሳዝናል፡፡

ደርጎች እስከዛሬ ድረስ “ጀኔራል አማን የተገደሉት ወንበዴዎቹ ኤርትራን እንዲገነጥሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸው ስለተደረሰበት በዚህ አኩርፈው ቤታቸው ውስጥ ስለመሸጉ ነው” ይላሉ፡፡ በደርግ ወገን ሆነው የጻፈ የትኛውም ሰው ይህችን ቃል ይደጋግማል፡፡ ይሁንና ለህሊናቸው ታማኝ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም “በጄኔራል አማን ላይ የተደረገው ቅጥፈት እጅግ በጣማ ያሳዝናል፤ ጄኔራል አማን ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንዳትገነጠል ተገቢውን ጥረት ያደረጉ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው” በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል (የክህደት ቁልቁለት የተሰኘውን መጽሐፍ አንብቡ)፡፡ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎም በሰጡት የምስክርነት ቃል ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

የደርግ መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎች የኤርትራ ጥያቄ እጅግ በጣም የተወሳሰበ እንዲሆን ነው ያደረጉት፡፡ ደርግ በመውደቂያው ሰሞን ከሻዕቢያ ጋር ንግግር ለማድረግ መሞከሩ ሚዛን የሚደፋ ዜና ለመሆን ያልቻለው ወርቃማው እድል ካመለጠ በኋላ የተመዘዘ ካርድ ስለሆነ ነው፡፡

ከደርግ ቀጥሎ የመጣው ህወሐት ለኤርትራ ጥያቄ እውቅና መስጠቱ የሚያስወድሰው ነው፡፡ ነገር ግን ከኤርትራዊው አጋር ድርጅቱ (ሻዕቢያ) ጋር ወደፊት አብሮ መኖር ስለሚቻልበት ሁኔታ በመነጋገር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያሰፋበትን ሁኔታ መቀየስ ሲገባው “የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚል ግትር አቋም የሚያራምድ ሆኖ ተገኘና ህዝቡን አስቀየመ፡፡ በተጨማሪም የኤርትራ ሪፈረንደም በተካሄደበት ወቅት ውሳኔውን የሚያጸድቅበት “ማንዴት” ከህዝብ ያልተሰጠው የሽግግር ጊዜ መንግሥት ይዞ ውሳኔውን በማጽደቁ የህዝቡን ልብ ሰበረው፡፡ ለዚህችው ብቻ ሲታገል የኖረ አስመሰለበት፡፡
——–
ከላይ እንደለገጽኩት የኤርትራ ጥያቄ አግባብነት የነበረው ጥያቄ ነው፡፡ መንግሥታቱ ግን በተገቢው መንገድ አላስተናገዱትም፡፡ ኃይለ ሥላሤና ደርግ በጀብደኝነት ጥያቄውን ረገጡት፡፡ ይህኛው መንግሥት ደግሞ ከህዝብ ስል&

By Addis Admass Newspaper , Written by Administrator

Image

ኪሳራው በጊዜ ሲሰላ፣ የአገሪቱን የስልጣኔ ጭላንጭል ያዳፈነ፣ የ30 ዓመት የኋሊት ጉዞ ነው።
30 ዓመት ቀላል አይደለም፤ እነ ደቡብ ኮሪያ ከድህነት ወደ ብልፅግና የተሸጋገሩበት ጊዜ ነው።
“የአብዮተኛው ትውልድ”ን ኪሳራዎችን ለመደበቅ ተብሎ ብዙ ታሪክ ተድበስብሷል
ትምህርት የተስፋፋው፣ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ያደገው ከአብዮቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ?
የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የመንገድና የአየር ትራንስፖርት በፍጥነት የተሻሻለውስ መቼ ነው?
በእህል ምርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በኤክስፖርት መስኮች የብልፅግና ምልክት የታየውና የጠፋውስ?
የሙያ ፍቅር ያበበው፤ ስነፅሁፍ፣ ትያትርና ሙዚቃ ያደገው፤ ስፖርት የተሻሻለው መቼ ይሆን?

በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የመጡ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት ያካሄዱት ዊሊያም ሻክ፤ በአገሪቱ እያቆጠቆጠ ከመጣው የትምህርትና የስልጣኔ ጅምር ጋር መልካም የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ እንደነበር ይገልፃሉ። አንደኛ፤ የዘመኑ ወጣቶች እንደ ጥንቱ የመንግስት ስልጣንንና ተቀጣሪነትን አልያም የሃይማኖት መሪነትንና ሰባኪነትን የሚመኙ አይደሉም። ሁለተኛ፤ “ይሄኛው ሙያና ይሄኛው የሕይወት ዘይቤ፣ ለአማራ፣ ለኦሮሞ ወይም ለሶማሌ ተወላጅ ነው። ያኛው ሙያና ያኛው የኑሮ ዘይቤ ደግሞ ለትግራይ፣ ለወላይታ ወይም ለጉራጌ ተወላጅ ነው” የሚሉ የዘልማድ አዝማሚያዎችን አይቀበሉም። የ1950ዎቹ ወጣቶች የሙያና የግል ሕይወታቸውን በራሳቸው መንገድ መምራት እንደሚችሉ የሚያምኑ ሆነዋል።
ተማሪዎቹ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ቢሆኑም፤ የሙያ ምርጫቸው ይመሳሰላል። ከመንግስት ስልጣንና ተቀጣሪነት ወይም ከሃይማኖት ሰባኪነት ይልቅ፤ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጡት ለምህንድስና ወይም ለህክምና ሙያ፣ ለሜካኒክነት ወይም ለአስተማሪነት ሙያ እንደሆነ ጥናቱ ገልጿል። በአጭሩ፤ በያኔው የስልጣኔ ጭላንጭል፤ ለእውቀትና ለሳይንስ፤ ለሙያዊና ለምርታማ ስራ ክብር የሚሰጥ ትውልድ እየተፈጠረ ነበር። በአገሪቱ እየታየ የነበረውንም የትምህርትና የኢኮኖሚ ብሩህ አቅጣጫ ያመላክታል። Occupational Prestige, Status, and Social Change in Modern Ethiopia: William A. ShackSource: Africa: Journal of the International African Institute, Vol. 46, No. 2 (1976), pp. 166-181
በ1950ዎቹ ዓ.ም ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ከእንቅልፏ እየነቃች እንደነበረ የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎችንም መጥቀስ ይቻላል። የሃዲስ አለማየሁና የፀጋዬ ገብረመድህን ድርሰቶች፣ የነጥላሁን ገሠሠና የነምኒልክ ወስናቸው የሙዚቃ ስራዎች፣ ዛሬ ከአርባ እና ሃምሳ አመታት በኋላም፣ ወደር አልተገኘላቸውም። በእግር ኳስ እና በሩጫ ስፖርቶችም እንዲሁ።
በመንግስት አስተዳደር በኩልም፤ ትልቅ “የስልጣኔ አብዮት” የተካሄደው፣ ከ1960ዎቹ “አብዮተኛ ትውልድ” በፊት ነው። ለሺ አመታት በሃይማኖታዊ ሰነዶች (በክብረ ነገስትንና በፍትሃ ነገስት) ላይ ተመስርቶ የቆየውን የአገሪቱ ሥርዓትና ሕግ፣ ከኋላቀርነት ለማላቀቅና የስልጣኔ እድል ለመፍጠር ያስችላሉ የተባሉ የሕገመንግስት እና የምርጫ ህጎች ከ1923 እስከ 1948 ዓ.ም ፀድቀዋል። የተለያዩ የፍትሐ ብሄርና የወንጀል ሕጎች ከ1935 እስከ 1960ዎቹ መግቢያ ድረስ ታውጀዋል። የወንጀልና የፍትሐ ብሄር ህጎቹ እስከ ዛሬ ድረስ ይሰራሉ – (በ2000 ዓ.ም የተወሰነ ማሻሻያ ቢታከልባቸውም)።
ነገር ግን ሕጎችን በማወጅ ብቻ ሳይሆን፤ በግል አርአያነትና ጥረትም አገሬውን ወደ ስልጣኔ ለማራመድ ሙከራዎች ተደርገዋል። “በለውጥ ላይ የምትገኝ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በ1948 ዓ.ም ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሞን ሜሲን፤ በ1925 ገደማ ዓ.ም የንጉሡ ሴት ልጅ መሞቷን ጠቅሰው፤ ለሟቿ ልዕልት የተዝካር ድግስ እንደማይዘጋጅ በአዋጅ መነገሩን ይገልፃሉ። ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ያለ አቅማቸው በሚደግሱት ተዝካር ኑሯቸው መናጋቱ ብቻ አይደለም ችግሩ። የየአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት በየፊናቸው ተዝካር ሲደግሱ፤ የአካባቢው ነዋሪና ገበሬ፤ ወደደም ጠላም፤ እህል፣ ከብት እና ገንዘብ እንዲያዋጣ ይገደዳል። ገበሬዎችን ከዚህ ልማዳዊ ሸክም ለመገላገል ነበር የንጉሡ ሙከራ – ይላሉ ፀሐፊው።
ይህም ብቻ አይደለም። የድሮ ለቅሶ እንደዛሬ አይደለም። በእርግጥ ዛሬም ቢሆን፤ የአገራችን ለቅሶ ለታይታ የሚቀርብ ቅጥ ያጣ ልማድ ነው። ግን የድሮው ይብሳል። ሰው ሲሞት፣ ልብስ መቅደድና ፀጉር መንጨት፤ ፊት መቧጨርና ደረት መደለቅ፤ መሬት ላይ መንከባለልና አፈር መልበስ የተለመደ ነበር። ነውጠኛ ለቅሶ ይሉሃል ይሄ ነው። ይህን ለማስቀረት ንጉሡ እንደጣሩ የሚገልፁት ሲሞን ሜሲን፤ ነጠላ አዘቅዝቆ መልበስ የተጀመረው ያኔ ነው ይላሉ። Changing Ethiopia፡ Simon D. MessingSource: Middle East Journal, Vol. 9, No. 4 (Autumn, 1955), pp. 413-432።
እንዲህ በየመስኩ የስልጣኔ ጭላንጭሎች ብቅ ብቅ ቢሉም፤ የ1960ዎቹ ተማሪዎችና ወጣት ምሁራን፤ በንጉሡ ደስተኛ አልነበሩም። እንዲያውም፤ ንጉሡን እንደ ዋነኛ ጠላት ፈርጀዋቸዋል። “ንጉሡ አገሪቱን በኋላቀርነት አስረው ይዘዋል። ህዝቡን ከትምህርት አራርቀውታል፤ በተለይ ሴቶች በመሃይምነት ጨለማ ተውጠዋል (ድርብ ጭቆና እንዲሉ)። ህዝቡ ከመሰረተ ልማትና ከኢኮኖሚ እድገት፣ ከኤሌክትሪክና ከስልክ፣ ከመንገድና ከትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዳይተዋወቅ፤ የእርሻና የኢንዱስትሪ እድገት እንዳያይ ያደረጉት ንጉሡ ናቸው” የሚሉ ውግዘቶች፤ በያኔዎቹ “የአብዮታዊ ትውልድ” አባላት እንደተጀመሩ እስከዛሬ ዘልቀዋል።
እውነታው ግን፤ ሙሉ ለሙሉ የዚህ ተቃራኒ ነው። በእርግጥ፤ የንጉሡን ዘመን በብዙ ምክንያቶች መተቸት ይቻላል። “የአገሪቱ የስልጣኔ ጅምር ተንቀራፈፈ፤ መፍጠን ነበረበት” ብሎ መተቸት ስህተት አይሆንም። በአብዮቱ የመጣው ለውጥ ግን፤ ጭራሽ የስልጣኔ ጅምርን አዳፍኖ የሚደመስስ ሆነ። ከንጉሡ ድክመት ይልቅ “የአብዮታዊው ትውልድ” ጥፋት በብዙ እጥፍ ይልቃል። “የአብዮታዊው ትውልድ” በርካታ አባላት ታዲያ፣ ይህ ታሪካዊ ውድቀታቸውና ኪሳራቸው በግልፅ እንዲታወቅ አይፈልጉም። ለዚህም ነው፤ እንደያኔው አሁንም ጨምር፤ የንጉሡን አስተዳደር ከማውገዝና ከማጥላላት ያልቦዘኑት። ነገር ግን እውነታውን ለዘላለም መሸፈን አይችሉም። የንጉሡንና የአብዮቱን ዘመናት፤ የዛሬውንም ጭምር ለመመዘንና ለማነፃፀር የምንችልባቸው መረጃዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ ጥቂቶቹን ብቻ እንመልከት።

ትምህርት ከጀማሪ እስከ ዩኒቨርስቲ
በ1938 ዓ.ም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር፣ 35ሺ እንደነበር የሚገልፁት ዶ/ር ተከስተ ነጋሽ፣ ከአስር አመት በኋላ 95ሺ እንደደረሰ ይገልፃሉ – ዘጠኛ ሺ ገደማ የአንደኛ ደረጃ፣ አራት ሺ ገደማ የሁለተኛ ደረጃ፣ አራት መቶ ገደማ የከፍተኛ ትምህረት ተማሪዎች። በ1955 ዓ.ም፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አስር ሺ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ 305 ሺ መድረሱን ዶ/ር ተከስተ ጠቅሰዋል – በወቅቱ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እንደነበሩ በማስታወስ Education in Ethiopia Nordiska Afrikainstitutet, Uppsala። እንደገና ከአስር አመት በኋላ በአብዮቱ ዋዜማ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር 1.04 ሚሊዮን ደርሷል – በሃያ አመታት ውስጥ ከአስር እጥፍ በላይ በማደግ።
በደርግ ዘመን፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት የተመዘገበው የተማሪዎች ቁጥር ወደ 2.9 ሚሊዮን ገደማ ነው – በሶስት እጥፍ አድጓል ማለት ነው። በኢህአዴግ 20 አመታት ውስጥስ? የተማሪዎቹ ቁጥር ወደ 15 ሚሊዮን ገደማ ሆኗል። በደርግ ዘመን ከነበረው ቁጥር ጋር ሲነፃፀር በአምስት እጥፍ ይበልጣል።
በንጉሡ ዘመን በሃያ አመታት ውስጥ ከሃያ እጥፍ በላይ የጨመረው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር በ1966 ዓ.ም 190ሺ ገደማ እንደደረሰ የሚገልፀው የአለም ባንክ መረጃ፣ በደርግ ዘመን ወደ 900ሺ እንደተጠጋ ይገልፃል። የደርግ ዘመን የተመዘገበው የአራት እጥፍ እድገት ከንጉሡ ዘመን ያነሰ ነው። በኢህአዴግ ጊዜም እንዲሁ። ኢህአዴግ ደግሞ በሃያ አመታት ውስጥ ወደ አምስት እጥፍ ገደማ በማሳደግ 4.5 ሚሊዮን አድርሶታል።
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቁጥር፣ በንጉሡ ዘመን በሃያ አመታት ውስጥ፣ ከአራት መቶ ገደማ ወደ 6500 አካባቢ ጨምሯል – በአስራ አምስት እጥፍ። በደርግ ዘመን ወደ ሶስት እጥፍ ገደማ አድጎ 18ሺ የደረሰ ሲሆን፣ በኢህአዴግ የሃያ አመታት ጊዜ፣ እንደ ንጉሡ ዘመን ከአስራ አምስት እጥፍ በማደግ ከ350ሺ በላይ ሆኗል።

ትምህርት በወንዶችና በሴቶች
የአብዮተኞቹ አንዱ መፈክር፣ የፆታ እኩልነት የሚል አልነበር? እስቲ የሴት ተማሪዎችን ድርሻ እንመልከት። አብዮተኞቹ የንጉሡን ዘመን ሲያወግዙ ስትሰሙ፤ በአብዮቱ ዋዜማ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ የሴቶች ድርሻ ከዜሮ በታች የነበረ ነው የሚመስላችሁ። ነገር ግን፣ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በ66 ዓ.ም. ከአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች መካከል 32 በመቶ ያህሉ ሴቶች ነበሩ። በደርግ ዘመን የሴቶች ድርሻ ወደ 40 በመቶ ገደማ ደረሰ፣ በኢህአዴግ ደግሞ ወደ 47 በመቶ።
በከፍተኛ ትምህርት፣ እዚህ ግባ የማይባል ድርሻ የነበራቸው ሴቶች፣ በ1952 ዓ.ም ወደ 3 በመቶ ድርሻ ካገኙ በኋላ፣ በሶስት እጥፍ አድጎ በአብዮቱ ዋዜማ ወደ አስር በመቶ ገደማ ድርሻ ለመያዝ የበቁ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን የሴቶች ድርሻ ወደ 18 በመቶ አድጓል። በኢህአዴግ ዘመን ደግሞ፣ ወደ 30 በመቶ ገደማ ደርሷል።
በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ፈጣን እድገት የተመዘገበው መቼ እንደነበር፤ ይሄው መረጃው ራሱ ይናገራል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ላይም አብዮተኞቹ ለውጥ አላመጡም። በንጉሡ ዘመን፣ በመጨረሻዎቹ ሃያ አመታት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ከሰላሳ እጥፍ በላይ ስለጨመረ፣ የተማሪዎቹ ቁጥር በአብዮቱ ዋዜማ 8700 ገደማ ደርሶ ነበር። በደርግ ዘመን የታየው እድገት ኢምንት ነው። የተማሪዎች ቁጥር ከአስር ሺ ብዙም ፈቀቅ አላለም። በመጀመሪያዎቹ የኢህአዴግ አስር አመታትም እንዲሁ፣ የእድገት ፍንጭ አልታየም። ከዚያ በኋላ ነው በፍጥነት ማደግ የጀመረው። በኢህአዴግ ሃያኛ አመት ላይ፣ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ቁጥር፣ ከሰላሳ እጥፍ በላይ በማደግ ከ350ሺ በላይ ሆኗል።

የ“መሰረተ ልማት” አቅርቦት
በ1947 ዓ.ም፣ በአገሪቱ የነበረው አመታዊ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት፣ 33 ጊጋዋትሃወር እንደነበር የውሃ ሚኒስቴር ባለሙያ መረጃ ያሳያል። በአማካይ ለአንድ ሰው 1600 ዋትአወር… በጣም ትንሽ ነው። ለአንድ ቤተሰብ በቀን ለ25 ደቂቃ አንድ አምፖል ብቻ ያበራ ነበር እንደማለት ነው። እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ ሃያ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግን፣ አቅርቦቱ በ18 እጥፍ ጨምሯል። 18 እጥፍ? ፈጣን እድገት ነው።
የአለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በአብዮቱ ዋዜማ አመታዊው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት 590 ጊጋዋትአወር ደርሶ ነበር። ግን በእነዚሁ አመታት ውስጥ የሕዝብ ቁጥርም ስለጨመረ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል የማግኘት እድል በ18 እጥፍ ሳይሆን በ11 እጥፍ ነው የጨመረው። ይሄም ቀላል አይደለም። በቤተሰብ በየቀኑ 5 ሰዓት ያህል አምፖል እንደማብራት ቁጠሩት። ይሄ በንጉሡ ዘመን ነው።
በደርግ ዘመንስ? በ17 የደርግ አመታት ውስጥ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት 1210 ጊጋዋትአወር ነው የደረሰው። በንጉሡ ዘመን ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በአንድ እጥፍ ብቻ ነው የጨመረው። ግን ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል የማግኘት እድላቸው ብዙም አልጨመረም። ለምን ቢባል፣ የሕዝብ ቁጥርም ጨምሯላ። እናም፣ በቤተሰብ ሲሰላ፣ በየቀኑ 6 ሰዓት ለማይሞላ ጊዜ አንድ አምፖል የማብራት ያህል ነው። በአጭሩ፣ በደርግ ዘመን ኤሌክትሪክ የመጠቀም እድል የተሻሻለው፣ ከሰባት በመቶ ባነሰ መጠን ነው።
በኢህአዴግ ዘመንስ? ከ1983 ዓ.ም እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሃያ አመታት እድገት እንመልከት። የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦቱ በምን ያህል ጨመረ? አሁንም የአለም ባንክ መረጃን ነው የምጠቅሰው። በጊጋዋትአወር፣ 1210 የነበረው ወደ 5000 ገደማ ጨምሯል። በአራት እጥፍ ገደማ ማለት ነው። ነገር ግን፣ በንጉሡ ዘመን እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ በነበሩ ሃያ ዓመታት፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከ18 እጥፍ በላይ ማደጉን መዘንጋት የለብንም። በደርግ ዘመን ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ግን፣ በኢህአዴግ ዘመን የታየው እድገት በእጅጉ የተሻለ ነው። ሰዎች በኤሌክትሪክ የመጠቀም እድላቸውስ ምን ያህል ተሻሻለ? በኢህአዴግ ሃያ አመታት ውስጥ፣ ከአንድ እጥፍ በላይ ተሻሽሏል። በቤተሰብ ሲሰላ፣ በየቀኑ ወደ 15 ሰዓታት ያህል አንድ አምፖል ለማብራት የሚችል የኤሌክትሪክ ሃይል ተገኝቷል እንደማለት ነው።
እንግዲህ አስቡት። በ1947 ዓ.ም አንድ የኢትዮጵያ ቤተሰብ በአማካይ በየቀኑ ለ25 ደቂቃ ብቻ አንዲት አምፑል ማብራት ይችል ነበር። በ1966 ዓ.ም፣ በየቀኑ ለ5 ሰዓታት ያህል ማብራት ቻለ። በ1983 ዓ.ም ወደ 6 ሰዓት ያህል ፎቀቅ አለ። በ2003 ዓ.ም፣ ወደ 15 ሰዓት ገደማ አደገ። የትኛው ዘመን እድገት ይሻላል?
እንደ ኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ሁሉ፤ የመንገድ ግንባታ፣ የአውሮፕላን ትራንስፖርትና የስልክ መስመር አገልግሎትም እንዲሁ፤ ከአብዮቱ ዘመናት ይልቅ በንጉሡ ጊዜ የተሻለ እድገት ተመዝግቧል። ለምሳሌ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ፤ ከ1950 ዓ.ም እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ወደ ስድስት እጥፍ ገደማ በመስፋፋት፣ 45ሺ ገደማ የስልክ መስመሮች አገልግሎት ላይ ውለዋል።
በደርግ ዘመንስ? በሁለት እጥፍ ገደማ ነው ያደገው – ወደ 135ሺ ገደማ የስልክ መስመሮች። እንደ ንጉሡ ዘመን ከስድስት እጥፍ በላይ እድገት የታየው በኢህአዴግ ዘመን ነው። የስልክ መስመሮች ቁጥር በሃያ አመታት ውስጥ 900ሺ ደርሰዋል።
ይህም ብቻ አይደለም። እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ፣ የኤክስፖርት ገበያ አራት እጥፍ ገደማ አድጓል – ከ70 ሚሊዮን ዶላር ወደ 270 ሚሊዮን ዶላር። በደርግ ዘመን፣ በእነዚያ ሁሉ አመታት፣ የኤክስፖርት ገበያ በአንድ እጥፍ እንኳ ማደግ አልቻለም። ከ470 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ አላለፈም። በኢህአዴግ ዘመንም በመጀመሪያዎቹ አስር አመታት፣ ከኤስፖርት ገበያ የተገኘው ገቢ እዚያው ገደማ ተገድቦ ቆይቷል። ከዚያ በኋላ ነው ከቀድሞው የተሻለ ፈጣን እድገት መታየት የጀመረው። በጥቅሉ፣ በሃያ የኢህአዴግ አመታት ውስጥ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ የኤክስፖርት ገቢ፣ ከአራት እጥፍ በላይ በማደግ፣ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል – በንጉሡ ዘመን ከተመዘገበው እድገት ጋር ተቀራራቢ ነው።

የእህል ምርትና እጦት
የእህል ምርትን ደግሞ እንመልከት። ከአብዮቱ በፊት በነበሩ 20 ዓመታት፣ ለአንድ ሰው በአማካይ በየአመቱ 175 ኪሎ ገደማ እህል ይመረት ነበር። በአብዮቱ ዘመናት በደርግ ጊዜስ? ለአንድ ሰው በአማካይ 135 ኪሎ ገደማ እህል ነው በየዓመቱ ሲመረት የነበረው። በሌላ አነጋገር፤ የሕዝብ ብዛትን ከግምት አስገብተን ስናሰላው የእህል ምርት፣ በንጉሡ ዘመን የ30 በመቶ ብልጫ ነበረው።
በኢህአዴግ ዘመንስ? በመጀመሪያዎቹ የኢህአዴግ አስር አመታት፣ የአገሪቱ የእህል ምርት፣ ከደርግ ዘመንም የባሰ ነበር – በየአመቱ በአማካይ ለአንድ ሰው 125 ኪሎ እህል ነበር የሚመረተው። ቀጥለው ባሉት አስር አመታትስ? ምርቱ በአማካይ ወደ 165 ኪሎ ግራም ገደማ ደርሷል። በእርግጥ ያለፉትን ስምንት አመታት ብቻ ካየን፣ የአገሪቱ የእህል ምርት እየተሻሻለ፣ በአማካይ 175 ኪሎ ገደማ እንደደረሰ እናያለን። በአጠቃላይ ሲታይ፤ ከአብዮቱ ዋዜማ ጀምሮ ወደ ታች ሲያሽቆለቁል የነበረው አብዮታዊ የውድቀት ጉዞ ቀስ በቀስ የተገታው፤ የሶሻሊዝም አብዮት ከተገታ በኋላ ነው። ቀስ በቀስም እያገገመ፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በንጉሱ ዘመን ወደ ነበረበት ደረጃ ለማደግ ችሏል። በሌላ አነጋገር፤ ኢትዮጵና ኢትዮጵያዊያን በአብዮቱ ሳቢያ ለድህነትና ለረሃብ ከመዳረጋቸው በተጨማሪ፤ ለ30 አመታት ያህል የኋሊት ተጉዘዋል። አዲሳድማስ ጋዘጣ ነጻ አስተያየት

ብሄር ብሄረሰብ፤ የዘር ፓለቲካ… ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)

እውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥfa
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።
ተስፋ ገብረሥላሴ
ፊደል የቆጠርሁት በአገራችን የህትመት ፋናወጊ (እና አርበኛ) የሆኑት ተስፋ ገብረሥላሴ ያሳትሟት በነበረው የባለ ፲ ሣንቲም ፊደል ነበር። ከፊደሏ ሽፋን ላይ ታዲያ ‘ተስፋገብረሥላሴ ዘብሄረ ቡልጋ’ ይላል። መጠየቅ እወድ ነበርና መርጌታን ‘የንታ ብሄረ ቡልጋ ምን ማለት ነው?’ ብየ ጠየኳቸው። የንታም ልጄ ብሄር ማለት በግእዝ አገር ማለት ነው። ቡልጋ ደሞ ሽዋ ክፍላገር ውስጥ የሚገኝ አውራጃ ነው። የተስፋ ገብረሥላሴ አገር እዚያ ነው፤ አሉኝ።
ከዚያ አስኮላ ትምርት ገብቸ ፬ኛ ክፍል ህብረተሰብ መጽሀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ‘ብሄረሰቦችን’ የሚያሳይ ስዕል ተደርድሮ አየሁ። በተለይ ሲዳማን የዎከሉት ቆንጃጅት ሙገጫ ሲዎግጡ የሚያሳየው ስእል አይረሳኝም። ይሁን እንጅ ብሄረሰብ የሚለው ቃል አልገባኝም ነበርና አስተማሪየን ጠየኳት። እሷ ግን ጎሳ፣ ነገድ ቅብጥርሴ ብላ የባሰ ግራ አጋባችኝ። ደግነቱ ማታ ማታ የንታ ዘንድ ወንጌል እማር ነበርና ወንበር ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብዬ ሄጄ የንታን ‘ብሄረሰብ ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየኳችው። የንታም ብሄር ማለት አገር ነው፣ ሰብ ደሞ ሰው ማለት ነው። እንግዲህ ብሄረሰብ ያው የሰው አገር መሆኑ ነዋ አሉኝ። የበለጠ ግራ ተጋባሁ። ህብረተሰብ መጽሀፌ ውስጥ ያዬሁት የሚያማምሩ ቆንጃጅትን ምስል እንጅ ወንዝ ወይ ጋራና ሸንተረር አልነበረማ።Ethiopia and Eritrea map
ሁሉ ሆነና ደርግም በኢሕአዴግ ተተካ። አሁን ግራ ያጋባኝ የነበረው ‘ብሄረሰብ’ የሚለው ቃል ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ተብሎ ተራብቶ መጣ። የግዕዙን ቀጥተኛ ትርጉም ካየን እንግዲህ አገራት፣ የሰው አገራትና ህዝቦች እያልን መሆኑ ነው። ይሁንና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ተብለው ይጠሩ የነበሩት የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች አሁን ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ሆነው የተባዙት አንዳንዶቹ ብሄረሰቦች ወደ ብሄርነት ሌሎቹ ደግሞ ወደ ህዝብነት ተለውጠው ይሁን በሌላ ምክንያት በውል አይታዎቅም። በአንጻሩ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚል ቃል አይገኝም። ፖለቲከኞችም ‘የኢትዮጵያ ህዝቦች’ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ አትሰሙም። ይህ አጋጣሚ የሚመስለው ካለ እሱ የዋህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት (ልክ በኢህአዴግ የመጀመሪያዎቹ ሰባት የስልጣን አመታት ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ዘፈን እንደማዳመጥ ያለ) በትምክህተኝነት ሊያስከስስ የሚችል የፖለቲካ ፋውል መሆኑን እያንዳንዱ ካድሬ ስለሚረዳ ነው።
የኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ስልጣኑም ሆነ ምድሩ አንዲሁም በላዩና በውስጡ ያለው ሀብት ሁሉ ‘የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የጋራ ሀብት ነው ይላል። ይህ ደግሞ ከሌሎች ኣገሮች ሕገ፡መንግስታት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል (ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚለው ሀረግ እንደ ዋሊያ ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚታወቀው)። ይህ ይገርመኝ ነበርና ከአስር ኣመታት በፊት ከህገ፡መንግስት ጋር በተገናኘ የመመረቂያ ጽሁፍ ሳዘጋጅ ለመሆኑ አነዚህ የኣገሪቱን የፖለቲካ ስልጣንና ሀብት ኣንድም ሳያስቀሩ ጠቅልለው የያዙ ፍጡራን በትክክል አነማን ናቸው? ኣንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩት በምን ነው? በአገሪቱ ውስጥስ ስንት ብሄሮች፣ ስንት ብሄረሰቦችና ስንት ህዝቦች አሉ? ለምሳሌ የቀበሌ መታወቂያ ስትወስድ ብሄርህን ተጠይቀህ ጉራጌ ብለህ ከሞላህ በኋላ ማታ በኢቲቪ የጉራጌ ብሄረሰብ ስላስመዘገበው ልማት ትሰማለህ። ታዲያ ብሄርና ብሄረሰብ አንድም ሁለትም ናቸው? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዠ መልስ ፍለጋ ሰነዶች ማገላበጥ ነበረብኝ። የህገ፡መንግስቱን ረቂቅ (ፕሪፓራቶሪ ዎርክስ) ሳይቀር አገላብጨ የሚረባ ነገር ላገኝ አልቻልሁም። ሕገ፡መንግስቱን በማርቀቅ የጎላ ድርሻ ነበራቸው የሚባሉትን ሰዎችም ጠይቄ ያገኘሁት ውጤት ኣልነበረም። በጣም ተገረምሁ። በአገራችን ላይ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሁሉን ሀብትና ስልጣን ‘የተቆጣጠሩት’ ግኡዛን ማንነት እንዴት አይታዎቅም? ይህ እኮ እጅግ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።
በተለይ ህዝቦች የሚለው ቃል ግራ አጋቢ ነው። በአለም ላይ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም እንድ አይነት ማንነት ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚኖሩባቸው አገራት ከአምስት አይበልጡም፤ ይህም ቢሆን በጣም የሚያከራክር ነው። ይሁን እንጅ የብራዚል ህዝቦች ወይንም የኬንያ ህዝቦች ቢባል እንግዳ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ህዝብ በትርጉሙ ያልተወሰነ ቁጥርና ማንነት ያላቸው ሰዎችን ያካተተ የጥቅል (የወል) ስም ስለሆነ ነው። ለዚህም ነው የአለም ህዝብ ቁጥር እንጅ የአለም ህዝቦች ቁጥር የማንለው። በርግጥ ፈረንጆቹም ከቅኝ በፊት ይኖሩ የነበሩ ቀደምት ጎሳዎችን (ትራይብስ) ለማመልከት ኢንዲጅነስ ህዝቦች ወይም አማዞን ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ይላሉ። ይህ ግን ቀደምት ጎሳዎችን (ነገዶችን)የሚተካ ተለዋጭ ቃል እንጂ ተደራቢ ስያሜ አይደለም። ስለሆነም ቀደምት ጎሳዎችና ኢንዲጅነስ ህዝቦች አይሉም። እንዲያውም ኢንዲጅነስ ህዝቦች የየአገራቸው (ሰፊ)ህዝብ አካል ናቸው። ለምሳሌ የካናዳ ህዝብ በአገሩ የሚኖሩ ኢንዲጅነስ ህዝቦችን ያጠቃልላል። በዚህ አግባብ ከመደበኛ ሰዋሰው ርባታ ተቃራኒ ቢመስልም በአንድ አገር ውስጥ ህዝብ የሚለው ቃል ህዝቦች ከሚለው ቃል ይሰፋል ማለት ነው። ከላይ በጠቀሁት ምሳሌ የካናዳ ህዝብ ካናዳዊያንን በሙሉ ሲያመለክት የካናዳ ኢንዲጅነስ ህዝቦች ግን የካናዳ ህዝብ አካል የሆኑ (ከአጠቃላዩ ህዝብ ፭ ፕርሰንት እንኳን የማይሞሉ) ግን ደግሞ የየራሳቸው የተለየ ማንነት ያላቸውን ነገዶችን ብቻ የሚያመለክት ነው። በሁሉም አገሮች የሚኖሩ የተለያዬ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ሁሉ በአንድ ላይ የዚያ አገር ህዝብ ተብለው ነው የሚታዎቁት።
ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ሁለት አደናጋሪ ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ህዝቦች የሚለው ቃል አግባብ በሌላው አለም እንደሚታወቀው ሁሉ ቀደምት ነዋሪወችን (ኢንዲጅነስ ትራይብስ) ለማመልከት ነው እንዳይባል ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ያልሆነው ማን እንደሆነና ማን ከማን እንደሚቀድም አይታወቅም። እንዲያውም ሁሉም ‘ብሄር ብሄረሰቦች’ ቀደምት ነዋሪወች ናቸው ማለት ይቻላል። ቢያንስ ይህ ላለመሆኑ ተቃራኒ ማስርጃ የለም (እንዲያውም እኮ እንደ ሳይንሱ ከሆነ የአለም ህዝብ ሁሉ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው)። ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አንዳንዶች እንደሚሉት አናሳ ቁጥርና አገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማመልከት ነው እንዳንል እነሱው መልሰው ታዳጊ ብሄረሰቦች (አንዳንዴ አናሳ ብሄረሰቦች) ሲሏቸው እንሰማለን። ያ ከሆነ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦች በሚለው አገላለጽ ብንስማማ እንኳን ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አላስፈላጊ ድግግሞሽ ከመሆንና ከማደናገር ኣልፎ የሚጨምረው ነገር የለም ማለት ነው። ሁለተኛውና በጣም የሚገርመው በአለም ላይ ባልተለመደ ሁኔታ በአገሪቱ የሚኖሩት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በአንድላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይሆኑም። ይህ የሆነው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሕገ፡ መንግስታዊ ቃልኪዳን ገብተናል ያሉት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የሚጋሩት ማንነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ይሁን በሌላ ምክንያት አይታወቅም። ለነገሩ የአንድ አገር ህዝብ አካል ለመሆን የዚያ አገር ዜጋ ከመሆን ሌላ ምን የተለየ የጋራ ማንነት ያስፈልጋል?
ግድየለም፤ ያ ሁሉ ፖለቲካ ነው ብለን እንለፈው። እኛስ ቢሆን ቃላትን (አንደኣብዛኛዉ ነገራችን) እንደልባችን የምንጠቀመው ለምን ይሆን? ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፈለች፣ የዘር ፖለቲካ ያጠፋናል፣ የጦር ሰራዊቱ ከኣንድ ዘር በወጡ አዛዦች ቁጥጥር ስር ነው፣ አቶ እከሌ በተቋሙ ውስጥ የነገሰውን ዘረኝነት በመቃዎም ስልጣናቸውን ለቀቁ፣ ወዘተ…በየቀኑ የምንሰማው ሮሮ ነው። ለመሆኑ ዘር ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ዘር አለ? ለምሳሌ አማራ አንድ ዘር ትግሬ ደግሞ ሌላ ዘር ናቸው? ከሆነስ ከየት ነው የመጡት? እንደሚታወቀው ያን ያህል ሩቅ ከማይባል ጊዜ በፊት ግእዝ እንጂ ትግርኛም አማርኛም ኣልነበሩም። ታዲያ ያኔ ትግሬ ነበር? ኣማራስ? ሌላው ቀርቶ ሴሜቲክ፣ ኩሽቲክ የሚባለውስ ምናልባት ቋንቋን ከመግለጽ (ይህም አከራካሪ ይመስለኛል) የዘለለ ያለው አንድምታ ምንድን ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ችሎታየም አላማየም አይደለም፤ ነገር ግን በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመስሉኛል። እንዲያውም ስለማንነታችን ሳይንሳዊ ብንሆን ብዙ ችግራችን የሚቃለል ይመስለኛል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ እንጅ እናንተ ቦታ የላችሁም፤ መሬቱ በሙሉ የእነሱ በመሆኑ እናንተ የመሬት ባለቤት መሆን አትችሉም ሲለን ቢያንስ እነዚያ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በትክክል እነማን እንደሆኑ እንዲነግረን እንጠይቃለን። በአንጻሩ ደግሞ እኛ የዘር ፖለቲካ ወዘተ…ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ መረዳትና ማስረዳት ያለብን ይመስለኛል።
[email protected]
በዚሁ ላብቃ።
ሰላም

ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።
ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም::
ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በጸረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ ከነበሩ አባቶቻቸዉና አያቶቻቸዉ የተወረሰ ፋሽስት ጣሊያን ለደረሰባት ሽንፈት በዘርና በሃይማኖት ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ተክላብን የሄደቺው ተንኮል አካል ነው ::
የዚህ የጥፋት አጀንዳ አስፈጻሚ የሆነው ወያኔ የጀመረውን አገር የማፍረስና ህዝብ የመከፋፈል አጀንዳ ለማሳካት በየክልሉ የተኮለኮሉ ምስሌኔዎች እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብና ክልል ላይ እየፈጸሙት ያለው በደልና ሰቆቃ አዲስ ምዕራፍ በያዘበት በአሁኑ ወቅት እራሳቸዏን ለባርነት አዋርደው ህዝባቸውን በማዋረድ ላይ የሚገኙት የብአዴኑ አለምነህ መኮንንን የመሳሰሉ ሆድ አደሮች ውርደት በቃን ዘረኝነት በቃን ብለው በተነሱ ዜጎች ላይ እየወሰዱ ያለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሆኖአል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ሞክራሲ ንቅናቄ ከሰሞኑ በደረሰው መረጃ ወያኔ ከአማራው ቀምቶ በትግራይ ክልል ባስገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ንጽሃን ዜጎች ለምን በወያኔ የግፍ አገዛዝ ትማረራላችሁ እየተባሉ በወያኔ ታማኝ ሚሊሻዎች
እስር እንግልትና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አረጋግጦአል:: በዚህ በአዲስ መልክ በተጀመረዉ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ መሳሪያ ያነገቡ የህወሃት ሚሊሻዎች ከክልላቸዉ ዉጭ ወደ ተለያዩ የአማራ ከተማዎችና ወረዳዎች ሰርገዉ እየገቡ የእነሱን ቋንቋ የማይናገረዉን ሁሉ የግንቦት 7 ተላላኪዎች ናችሁ በሚል እያሰሩ በመደብደብ ላይ ናቸዉ።
ይህ በመሆኑ ዛሬ አትዮጵያን ከሱዳንና ትግራይን ከጎንደር ጋር በሚያዋስኑ የአማራ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ገበሬዎች እጃቸዉ እርፍ ከሚጨብጥበት ግዜ በወያኔ ሰንሰለት የሚታሽበት ግዜ ይበልጣል፤ የመንግስት ሰራተኛዉና የከተማ ነዋሪዉም ቢሆን አብዛኛዉን ግዜ የሚያጠፋዉ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ግምገማ በመቀመጥ ሲሆን ተማሪዉና ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ “መጡ አልመጡም” እያለ ሌሊቱን የሚያሳልፈዉ በየጫካዉ እየተሸሸገ ነዉ።
የዚህ አይነት አስከፊ ግፍና መከራ በአፋር ፡ በጋምቤላ በኦጋዴንና በኦሮሚያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ሲፈጸም ቆይቶአል:: ? ወያኔ እራሱ አርቅቆ ባጸደቀውና በሐምሌ ወር 1987 ዓም በስራ ላይ የዋለዉ የወያኔ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ በዘጠኝ የፌዴራል ክልሎች መከፈሏንና እያንዳንዱ ክልል እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መብቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ህገ መንግስት መሠረት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ቋንቋ፤ የአስተዳደር ማዕከልና እንዲሁም የክልሉን ሠላምና ጸጥታ የሚያስከብር የፖሊስ ኃይል ይኖረዋል ይላል። ታድያ ለምንድነዉ እያንዳንዱ ክልል የራሱ ፖሊስ ኃይል አያለዉ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ የህወሃት ታማኝ ሚሊሻዎች አማራ ክልል ዉስጥ እየገቡ አማራዉን የሚያሰቃዩት?
መልሱ ቀላል ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝባዊ አምቢተኝነቱ እያየለ በመጣና የነጻነት ኃይሎች ጡንቻ በፈረጠመ ቁጥር ወያኔ አንገቷ ላይ ቀጭል እንደታሰረባት በቅሎ ይደነብራል። የደነበረ ደግሞ መራገጡ አይቀርምና መሳሪያ ያነገቡ ኃይሎችን እንቅስቃሴ እገታለሁ በሚል ከንቱ ጥረት ደንባራዉ ወያኔ የፈሪ በትሩን በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች፤ ወጣቶችና ሠራተኞች ላይ ማሳረፍ ጀምሯል።
ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የኮነነዉና የህዝብና የአገር ጠላት አድርጎ የሳለዉ ድርጅት የለም፤ የወያኔ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንን የአገዛዙን አቋም በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰምተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ማን ለመብቱና ለነጻነቱ እንደቆመና ማን መብቱና ነጻነቱ ላይ እንደቆመበት ለይቶ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ። ስለዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔዎች አላፊዉንና አግዳሚዉን “ግንቦት ሰባት” ነህ እያሉ ከሚያሰቃዩ፤ ህዝብንና ግንቦት ሰባትን ያስተሳሰረዉ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ነዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ቢመልሱ ለእነሱም፤ ለእኛም ለአገርም ይበጃል የሚል የጸና እምነት አለዉ። ወያኔ በኢህአዴግ ስም ያሰጠጋቸዉን ምሰለኔዎች ጨምሮ ከራሱ ዉጭ ሌላ ማንንም አያምንም፤ ስለዚህም ነዉ የአገሪቱን የመከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያደረገዉ። ዛሬ በግልጽ እንደምንመለከተዉ ወያኔ በጉልበት ለያዘዉ ስልጣን ያሰገኛል ብሎ በሚጠረጥረዉ ቦታ ሁሉ የራሱን ልዩ ሚሊሺያ እየለላከ የኢትዮጵያን ህዝብ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አየሄደ እያጠቃ ነዉ። ግንቦት ሰባት ወያኔና የፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐቱ የቆሙት በፍጹም ማንሰራራት የማይችሉበትት የመጨረሻ መቀበሪያ ጉድጓዳቸዉ ጫፍ ላይ ነዉ የሚል ጽኑ እምነት አለዉ። ሆኖም ጉድጓድ ጫፍ ላይ የቆመ ጠላት በራሱ ተወርዉሮ ጉድጓዱ ዉስጥ አይገባምና ይህንን የተዳከመ ጠላት እተፈራገጠ ጉዳት ከማብዛቱ በፊት ለመደምሰስ ክንዳችንን አጠናክረን በህብረት እንደ አንድ ሰዉ እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

እየደጋገምን የምናጠፋው ጥፋት እኛን ራሳችንን ይዞ እንዳይጠፋ መጠንቀቅ ያባት ነው!

ያለ ለውጥ፣ ያለ ዋስትና መራመድ አይቻልም፡፡
በማንኛውም ረገድ ራስን መቻል እንደሚኖርብን ልብ እንበል፡፡ በምግብ ራሳችንን ችለን ረሀብተኛ ዲሞክራሲ ይዘን እንጓዝ ብንል የማያዋጣንን ያህል፤ በባዶ ሆድም ዲሞክራሲን አንግቦ መጓዝ ወንዝ አያሻግረንም፡፡ ጥቂት የናጠጡ ሀብታሞችና አያሌ የኔ-ብጤዎች ያሏት ሀገርም ሆነ ሰላሟን አጥታ ብዙ ሀብታሞችን ያፈራች ሀገር እንድትኖረን አይደለም ደፋ-ቀና የምንለው፡፡

እንደጥንቱ መፈክር “ጉዟችን ረጅም ትግላችን መራራ” ነው ማለትም አያዛልቀንም፡፡ ሁሌም ረጅም፣ ሁሌም መራራ መሆን የለበትምና! ያለ ለውጥ፣ ያለ ዋስትና መራመድ አይቻልም፡፡ የለውጥ አንቀሳቃሹ በአብዛኛው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ በዕውቀት የተገነባ፣ ለውጥ የገባው፣ ዛሬ ላይ የተደረሰው ብዙ ለውጥና መስዋዕትነት ታይቶ መሆኑን የተረዳ ወጣት እንጂ “ፋስት” በሚል ታርጋ የታሸገ የቢዝነስ ተሯሯጭ ለብ-ለብ ትውልድ ብቻ እንዳይሆን አገርና ነገር የገባው ወጣት መገንባት ያስፈልጋል፡፡ባለራዕይ-ለማኝ ዐባይ ሲገደብ የምሰጥህ ሁለት ብር አበድረኝ ይላል::

ያልፈጠርነውን፣ ያላስተማርነውን፣ በአግባቡ ያላነፅነውን ልጅ የሌለ ቅፅል ሰጥተን ብናሞካሸው ረብነት የለውም፡፡ በአናቱ ቅቤ ጣል ያለበት ሹሮ ዓይነት ካፒታሊዝም ኑሮአችን ቅቤ በቅቤ ነው እንደማያሰኝ ሁሉ፤ በእንዲህ ያለ ሥርዓት ውስጥ የሚያድግም ልጅ በአርቲፊሻል የተኳኳለ ከመሆን በቀር ኦርጅናሌ እንደማይሆን እናስተውል፡፡

ከመጠላለፍ ይሰውረን፡፡አደቡን ይስጠን፡፡ በተጠራጠርነው ሁሉ ፍርድ ከመስጠት ያድነን፡፡ እየደጋገምን የምናጠፋው ጥፋት እኛን ራሳችንን ይዞ እንዳይጠፋ መጠንቀቅ ያባት ነው! የምንገባው ቃል መፈፀሙን የሚያረጋግጥልን አንድም ታሪካችን፣ ሁለትም ለራስ መታመናችን ነው! በተግባር የምንሠራው በቃል የምናወራውን ካልመሰለ ዕቅዳችን፣ ስትራቴጂያችን ሁሉ፤ ውሃ የበላው ቤት እንደሚሆን አንርሳ! በታሪክ ያየነው ስህተት እንዳይደገም መጣጣር አዲስ ታሪክ መሥራት ነው!

የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤

አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤

ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ ዓላማዎችና ዘዴዎች ላይ መከራከርና ሀሳብን ማጥራት አስፈላጊ ነው፤ በሰላማዊ ትግል ተግባር አለ ቢባልም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ ወይም የተቃውሞ አቅዋሞችን ከማሳየት አያልፍም፤ አገዛዞች ጃዝ! ብለው ውሻና ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ሲለቁ የጉልበት ጥርስና ዱላ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያርፋል፤ ጉዳት ይደርሳል፤ ሰላም ይቃወሳል፤ በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል ቂም ይጀመራል።

ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤ ‹የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ።

አራት፣ ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት!

በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም።

አምስት፣ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፤የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፤ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፤ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው።

የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡ በሰውነት ደረጃ ሕዝቡ መብቶቹን ሁሉ እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣

በዜግነት ደረጃ ሕዝቡ ለሥልጣን የሚያበቃውን የዜግነትና የፖሊቲካ መብቶች እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣ ሕዝቡ የሰውነትና የዜግነት መብቶቹን ተገንዝቦ በአገዛዝ ስር አልተዳደርም የማለት መንፈሳዊ እምቢተኛነት እንዲያድርበት ማድረግ፣ በግልጽ ጭቆናን የሚጠላና ለመብቶቹና ለነጻነቱ በቆራጥነት የሚቆም ሕዝብ እንዲፈጠር ማበረታታት፣ መብቶቹንና የሥልጣን ባለቤትነቱን የተረዳና ከጭቆና ጋር የተጣላ ሕዝብ በፖሊቲካ መስመር ቡድኖችን እየፈጠረ እንዲደራጅ ማድረግ፣ ያወቀና የነቃ፣ በፖሊቲካ መስመር የተደራጀና ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና የሚጠላ ሕዝብ ለማንም ጉልበተኛ የማይንበረከክ ሕዝባዊ ኃይል እንዲሆን መጣር፣

የትጥቅ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ በሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አውርዶ ወንበሩን ለራሱ ለመውሰድ ነው፤ ይህንን ሲያደርግ ሕዝቡን ወደጎን ትቶ ወይም ዘልሎ ነው፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በጠመንጃ ሥልጣን የሚይዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥልጣኑን ለሕዝብ እናስረክባለን፤ ትክክለኛ ምርጫ እናካሂዳለን በማለት ሕዝቡን በተስፋና በጠመንጃ ይዞ ነው፤ ነገር ግን ሥልጣንን ሕዝብ ለፈቀደው አስረክበው ከቤተ መንግሥት ሲወጡ አናይም፤ ሲሸሹ ወይም ሬሳቸው ሲወጣ እንጂ።

ብዙውን ጊዜ የማይታሰብ ወይም ብዙዎች የሚዘነጉት የሁለቱ ትግሎች የገንዘብ ወጪ በጣም ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ነው፤ ሰላማዊ ትግል በሕይወትም፣ በንብረትም፣ በመሣሪያም በዝግጅትም የሚያስከፍለው ዋጋ ከትጥቅ ትግል ጋር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ ነው።

ስለዚህም በሁለቱ በተለያዩ ስልቶች አራማጆች መሀከል የሚደረግ ክርክር ምን ዓይነት ነው? የሰላማዊው የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ የትጥቅ ትግል የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የወያኔ አገዛዝ ነው፤ በሌላ አነጋገር በሰላማዊ ትግል ሕዝቡ በሰላማዊ ትግል ትንሽም ቢሆን የነጻነትን አድማስ ለማስፋት እንዲችል ድፍረትን በማስተማር በኩል የማይናቅ አስተዋጽኦ ቢያደርግም አገዛዙን የመነቅነቅ ኃይል ገና አላዳበረም፤ አንድም ውጤት አላሳየም፤ የትጥቅ ትግሉ ከፉከራና ከሽለላ እስካሁንም አልወጣም፤ የሰላማዊ ትግል ዓላማ ሕዝቡ መብቶቹን እንዲያውቅ ለማንቃትና ለመብቶቹ እንዲታገል የሚያስችለውን ብቃት ለማስጨበጥ ነው፤ ስለዚህም ዘዴው በሕዝቡ ላይ ነው፤ የትጥቅ ትግሉ ዘዴ አገዛዙን በጉልበት ገልብጦ በዚያው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ ሌላ አገዛዝ ለመመሥረት ነው።

በኢትዮጵያ ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ሁሉ የቆሙበትንና የቆሙለትን ዓላማና ዘዴ በግልጽ ተገንዝበው ካልተሰለፉ በተንፈራጠጠ አስተሳሰብ የተባበረ ተግባር ሊገኝ አይችልም።

EMF

Image

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ወላይታ ሶዶ 18 ሰዎች ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨለማ ቤት ታስረዋል::
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!” የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ማስፈራሪያ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች

ምንሊክ ሳልሳዊ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ሃይለማርያም ደሳለኝ ምንጭ ናት በምትባለው በወላይታ ሶዶ ከከፍተኛ ደረጃ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች አጋለጡ::ነዋሪዎቹ እንዳሉት ካለምንም ምክንያት የሚያፍኑ የሚያስሩ የሚገርፉ እና ከፍትህ እና ፍርድ ቤት በላይ የሆኑ ትናንሽ ቡድናዊ መንግስታት እና እንዳሻቸው በህዝቡ ላይ የሚፈነጩ ካድሬዎች የወላይታን ህዝብ በስቃይ እና በሰቆቃ ውስጥ እያኖሩት መሆኑን ነዋሪዎቹ አማረው ተናግረዋል::

ባለፈው ሳምንታት ውስጥ እንኳን ከተያዙት የወላይታ ነዋሪዎች መካከል አቶ አየለ ሃሚሶ የሚባል የከተማውን የፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት እና ዳኛ ደብድባችኋል ተብለው ካለምንም ማስረጃ 18 ሰዎች ተይዘው ላለፉት አስረ አምስት ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በጨለማ ቤት ታስረው ይገኛሉ::እነዚህ እስረኞች የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሌሊሼ ኦላ እና ግብረበሮቹ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን እንዲሁም ደብዳቢዎቹን ጭናችሁ አድርስቹሃል የተባሉ የባጃጅ ሹፌሮች በቁጥጥር ስር ውለው እየተገረፉ መሆኑን በስቃይ ላይ ያሉት እስረኞች ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በሽብርተኛነት እና ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዛቹሃል በማለት እንግልት እና መንግስታዊ ሽብር በከተማው የፖሊስ አዛዥ እና ግብረአበሮቻቸው የተፈጸመባቸው ሲሆን በሻንጣዎቻቸው ላይ ፍተሻ አድርገው ምንም የጦር መሳሪያ እንዳላገኙ እና “ወላይታ ለመግባት ምንም አይነት ፈቃድ ከማንም አንጠብቅም ምክንያቱም አገራችን ነው” በማለት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ቢመልሱም “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ
አድርሰውባቸዋል::

ዛሬ የካቲት 26 2006 “አሁን መሄድ ትችላላችሁ” ብለው ከአዲስ አበባ የሄዱትን ሶስቱን የሰማዊ ፓረቲ አመራሮች 1ኛ/ አቶ ጌታነህ ባልቻ 2ኛ/ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 3ኛ/ አቶ ይሁን አለሙ ሲለቁዋቸው ከሀዲያ ጀምረው የሰሯቸውን ስራዎች የያዙበትን ሰነዶች፤ቃለ ጉባኤዎች እና ሁለቱን የወላይታ ተወካዮችን /አስተባባሪዎችን/ እስካሁን ያለቀቋቸው ሲሆን ስለ ንበረታችሁ የምናውቀው ነገር የለም በማለታቸው ንብረቶቻቸውን ሳይረከቡ ወደ አርባምንጭ መንቀሳቀሳቸው ታውቋል::

የታሰሩት የሰማያዊ ፓረቲ የወላይታ አስተባሪዎች ባይፈቱም፤ የተወሰዱባቸው ንብረቶች ባይመለሱላቸወም ሰራው መቀጠል ሰላለበት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ አርባ-ምንጭ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ነገ የአርባ ምንጭ ሰራቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ወላይታ ሶዶ ከትማ ተመልሰው የታሰሩትን የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎችን ለማስፈታት ትግሉ የሚቀጥል ሲሆን ንበረታቸውንም የማስመለሰ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ትላንትና የካቲት 25 2006 በሶዶ ከትማ ላይ ያደረጉዋቸው ሰበሰባዎች https://www.facebook.com/blueparty.ethi … =notify_me ይህንን ይመሰል ነበር፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

እስከዛሬ ብዙ ቀልዶችን ሰምቻለው አንደዚህ ግን ያዝናናኝ ቀልድ የለም አንድ የቀድሞ የግብጽ ጀነራል ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የማታቆም ከሆነ እናፈነዳቸዋለን አሉ ለአንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ እንድታቆም ሶስት አማራጮች አሉ ብለዋል።

የቀድሞው የግብጽ ጀነራል በቀዳሚነት ያስቀመጡት አማራጭ በኢትዮጵያ ፣በሱዳን እና በግብጽ 20 ሚልዮን የሚደርስ የሙዝ እና የዛፍ ችግኝ በመትከል እና የዝናብ ሁኔታው እንዲስተካከል በማድረግ እና አማራጭ በመስጠት ኢትዮጵያ ግድቡን የምታቆምበትን መንገድ ማመቻቸት ነው ብለዋል።

ሁለተኛው አማራጭ የቀድሞ የግብጽ ንጉስ ሱልጣን አብዱል ሃሚድ የኢትዮጵያን አንድ ሶስተኛ መሬት ያስተዳድር ስለነበር ይህን መሬት አንዲሰጠን መጠየቅ ነው ያሉት የቀድሞ ጀነራል የዩጋንዳ አንድ ሶስተኛ መሬትም የግብጽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንንም ለማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደተዘጋጁ ነው የሚናገሩት። ሁለቱ አማራጮች የማይሰሩ ከሆነ ግን « በመሬታችን መሞት የለበንም መሞት ካለብንም ግድባቸው ስር ነው መሞት ያለብን ስለዚህ እዛው ሄደን ልንፈነዳቸው ይገባል በመሆኑም ኢትዮጵያ ከሶስቱ አማራጮች አንዱን መምረጥ አለባት» ብለዋል።
እንኳንስ ለሙቅ ለገንፎም አልደነግጥ አለ የሃገሬ ሰው!! አፈነዳለሁ በሎ ፈነድቶ የአሞራ እራት መሆን እንዳለ አያውቁም እንዴ ጀነራል? ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀነራል ሶስቱም የኛ ምርጫ አይደሉም የኛምርጫ ወንዛችንን መገደብ ነው…እኔ የሚገርመኝ ኧረ ግብፅ በጣም አበዛችው
አንድ ሰሞን ክቡር ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር ” ለሚያስፈራራክ ሰው መፍትሄው አለመፍራት ነው ” ሳስበው ሳስበው ይህ ሰው ጅል እንጂ ጄነራል አይደለም!! ቂቂቂ ቂቂቂ ደስ የሚለው ነገር ጅነራሉም ሆኑ አንዋር ሳዳት አንድ አይነት እምነት አላቸው እዚያው ሄደን እንሙት !! እኛ መግደል መገዳደል ሰልችቶናል ሁላችንም በህይወት እንኑር ነው አቋማችን እግድህ የኛ መሬት ለባዐዳን መቀበርያ ይመች ይመስል የአሁኑ ትውልድም እንደ ድርቡሽ እዚያው እንሙት ቢያንስ እንደ ጣልያኖቹ የገዳዮችና የሟቾች ሃውልት በኢትዮጵያ ምድር ይኑረን አጥንታችን በኢትዮጵያ መሬት ካልተቀበረ የሞትን አይመስለንም ካሉ ባንወደውም ባንፈልገውም ሙትን ለመቅበር ከሟቹ ይልቅ ጉልበትና አቅም ይጠይቃልና ለዚያው መዘጋጀት ነው አንድም ሞት የናፈቃቸው ግብጻውያንን እዚየው ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሞታቸው እንድከናወን መጸለይ ነው ካልሆን ግን ምን ይደረግ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር ? ይስሙኝ እማ ጀኔራል በአባይ የመጣ እንኳን የኢትዮዻያ ወጣት እማማ አያቴ ትዘምታለች.ቂቂቂ እንዳዉም አረፈዳችሁ ቂቂቂቂቂቂ ቂቂቂ
ጀነራል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ”ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ትንቢተ ኢሳይያስ 19;1-10 ላይ
ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
2፤ ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።
3፤ የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።
4፤ ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
5፤ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።
6፤ ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።
7፤ በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።
8፤ ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።
9፤ የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ።
10፤ ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች።

ይስሙኝ እማ ጀኔራል በነገራችን ላይ ይኼን ግድብ ማፈንዳት አይደለም መገላመጥ በነፍስ ያወራርዳል፡፡ግድቡ የኢህአዴግ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ኢጣሊያንን ያየ በእሳት አይጫወትም” አለች እማማ አያቴ . ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ አይ አቅምን አለማወቅ ያሳዝናል የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫ መታጠቅ እንዲህ የሚያስፈነጭ መስሏቸው ከሆነ ከጣሊያን ይማሩ፡፡ጦርነት ሚጠይቀው ወኔና አላማ ነው ፡፡እንኳን ለግድባችን ….ይሞታል፡፡ታሪክ ጠይቁ የማን ልጆች እንደሆንን የሚኒልክ እና የቴድሮሥ አንፈራም ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው ግድቡ ስር ለመሞት መጀመሪያ መድረስ ይጠይቃል፤ ማፈንዳቱ ሳይሻላችሁ አይቀርም? ግን ልታፈነዱ ስትመጡ ልትፈነዱ አንደምችሉ አስባችሁ ግቡ! አገሪቱ ኢትዮጵያ, ህዝቡ ደግሞ የአድዋ ባለ ታሪክ ጀግና አንደሆነ ለአፍታም አንዳትዘነጉ! ቀልደኞች ቂቂቂ!! ጋሸ ጀነራሉ ወግ ከወግነቱ አልፎ አያውቅም ሞያ በልብ ነው ካወራህ ይበቃህል ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ለጠላት የተንበረከኩበት ዘመን የለም የታሪክ አሻራውን ማየት ከፈለክ ሜዳውም ፈረሱም ይህው። ጋሸ ጀነራሉ እንደዚህ አይነት ቀልድ ግብፅም ጀመረች እኛ ማን እንደሆን አታቅም እንዴ? ካላወቀች ጣሊያንን ትጠይቅ! ጀግኖቹ ኢትዮዽያኖችነን!!! ከእሳት እንዴት ችላ ትጠጋለች!! እኛ እኮ ለሚጠሉን እሳት ነን ለሚወዱን ደግሞ ዉሀ ነን.. እ!

ስሙኝማ በነገራችን ላይ አረብ ሲባል የሻገተና የአስተሳሰብ ደኃ ነው፡፡ እንደልማዳችሁ እናፈነዳለን ብልችሁ ስትነሱ እራሳችሁ ላይ አፈንድታችሁ ታልቃላችሁ፡፡ አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል፤ እንኳንስ የኃይል እጥረት እያለብን ይቅርና ቢተረፈረፈንም ግድቡ አይቆምም ፡፡ ደግሞ እንዳይገርማችሁ ፤ ይህ ከአራቱ ግዶቦች የመጀመሪያው ነው 3ቱ በቅርብ ጊዜ በቅደም ተከተል ግንባታ ይጀመራል፡፡ ስለሆነም ውኃችን ነዳጃችን ነው ፡፡ ነዳጂ በነፃ አለ እንዴ??? በነገራችን ላይ ጀኔራል ሙዝ እና ችግኙም አሪፍ ሀሳብ ነው። ከግድቡ በኃላ ወደዛም እንዘምታለን ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀኔራል ይልቁንም ለብዙ ሺህ አመታት ያለከልካይ የአባይን ውሃ ተጠቅመዋል ስለዚህ ለኢትዮጵያ በርካታ በሊዮን ዶላር ሊከፍሉ ይገባቸዋል!!!!
አሁን ነው መበቀል አረብን እስካሁን በትንሽ ሳንቲም የአበሻን ጉልበት የበዘበዙበት ሳያሳቸው በዚም መጡ ይሄ ግድብ ክብራችንን ከፍ የሚደርግልን ነው በዛውም ልክ ግድቡ ላይ ጥቃት ደርሶ ማለባበስ በቁም እንደመሞት ነው ለአገራችን ክብር መንግስት ራሱን ሊዘጋጅበት እና በማንኛውም እንቅስቃሴ አፀፋዊ መልስ ሊሰጥ ይገባል የስካሁኑ ውርደት በአረቦች ይብቃ ካለበለዚያ ሀገርንም በማስደፈር እስካሁን ከነበሩት መንግስት ቀዳሚው የትውልድ ተወቃሽ መሆኑ ማይቀር ነው እናም መንግስት በሁሉም ነገር አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ይገባል፡

ስሙኝማ ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው፡፡ ግብፆች ከድርድር ውጪ የጦርነት አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የተያያዙት ተራ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው፡፡ ያው ማስፈራራት ነው፡፡ ቢሆንም በደካማ ጎናችን አይጠቀሙም ማለት አይታሰብም፡፡ የግብፅ ግብረሰናይ ድርጅቶችም ሆኑ ማናቸውም የግብፅ መሰረት ያላቸው የኢንቨስትመን ስራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገ ሊጎዱን ይችላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሊሰራ የሚችል ወታደራዊም ሲቪል ደህንነት ተቋም ሊመሰረት ይገባል፡፡ መስራት ከባድ ነው፡፡ ማፍረስ ቀላል ነው፡፡ የቁማር ጨዋታው ውጤት ግልጽ ስላይደለ መዘጋጀቱ አይከፋም፡፡ በድንበር አካባቢ ያለንን የፀጥታ አጠባበቅ ማጥበቅም ግድ ይለናል፡፡
ግድቡ ተዓምር ባያመጣልን እንኳ ግብፅ ለዘመናት ያፈራረሰችንን ማካካሻ ስለሚሆን ለእኔ ልዩ ትርጉም አለው፡፡ ለብዙ ላልተገለፁ ነገሮችም መሰረት ይሆናል፡፡ አይደለም 6ሺ 200 ሜጋ ዋትም ካመነጨ በድል አድራጊነት እንዳጠናቀቅን እቆጥራለሁ፡፡የግብፅን የውስጥ መተራመስ ፈጣሪ ለኛ ብሎ ያደረገው እንደሆነስ ማን ያውቃል! ባይሆን ኖሮ የሚተኙልን አይመስለኝም፡፡ በዚህ ምስቅልቅል ጊዜ ይህን ያህል ከተንፈራገጡ ደህና ቢሆኑ ውጤቱን ገምቱ…መንግስትም ለማናቻውም ማስፈራራት ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ግድ ነው፡፡
ይስሙኝ እማ ጀኔራል በትምቢቱ ኢሳያስ መዝ67:31 ኢትዮጵያ ላይ ጦርን እንዳታነሱ ትደቃላችሁ ብሏል።በደንብ ይወቁን ይምጡ ሙዝ እንዳሉ የርሳስ ሙዝ በልተው ይሄዳሉ።
ቂቂቂ ቂቂቂ
ህዝብ ሆይ ስማ እንደወርቅ የነጠረ እንደ ብር የነጣ ሀበሻዊ ማንነትህ በሙዝ ተቀይራል እና መሳሪያም ያለህ መሳሪያ ጀገሪያም ያለህ ጀገሪያ አንካሴም ያለህ አንካሴ እነኚህ የሌላችሁ ወኔአችሁን ይዛችሁ ወደ አባይ ውጡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ሀበሻ ቢኖር እንጣላለን ማርያምን!!!!!!!
አሁንስ ትግስቴ እያለቀ ነዉ ያአባቴን ak-47 መሳሪያ ይዤ ልሸልል ነዉ ያበጠ ይፈንዳ ምነዉ ሸዋ
አረ ጎራው አረ ጎራው ንቡ ወለደና ቀፎውን ጨነቀው፣
ማር ብቻ መስሎታል መርዙን አላወቀው፣
የማን ዘር ነኝና ከማስ ተወልጄ
ሚኒልክ ያወረሰኝ ዛሬም አለ በጀ።
ዘራፍ ዘራፍ የማንን ሀገር ማን ይነካታል፣
ካለ ሀበሻ ያስከብራታል።
የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ፣
የአውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ።
ዘራፍ ዘራፍ!!! ዘራፍ!!! ዘራፈ!!
የምኒሊክ ልጅ ነኝ የበላይ የዛ ሳተና
ለጣልያንም ያልተኛ ቆራጡ ጀግና እኔነኝ ያለ ይሞክረኛ !!! ዘራፍ ዘራፍ!!!ተተተተተተተተተ ”ኢትዮጵያ ታበፅእ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር
እንግዲ እነሱ በሚፈልጉት አማራጭ መሄድ ይችላሉ መብታቸው ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ያለን አንድ እና አንድ ነው ያለን ያም የኃያላን ኃያል የነገስታት ንጉስ በረዶ የሚያዘንብ ፈርኦንን ከነሰራዊቱ በባህር የጣለ ድንቅ መካር እና ኃያል አምላክ ነው እሱም እጃችንን ዘርግተን ለምነን ከኛ ጋር ነው ስለዚህ ቀድመን አሸንፈናቸዋል
እኛስ እንሙት ችግር ብርቃችን አይደለምና መጪው ትውልድ ግን እኛ ያየነዉን ችግር እኛ ያለፍንበትን የድህነት ህይወት መቅመስ የለበትም ብሔር ሀይማኖት ሳይለየን ሁላችንም በአንድነት ለመጪው ትውልዳችን መስዋት ከፍለን ማለፍ አለብን ስም አይሞትም ታሪክም አይሞትም::እነሱ ያውሩ እኛ እንሰራለን ©2014 ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከ Love on The way

ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች 750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡

በብኣዴን ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል።
ሕወሓት በአማራው ክልል አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ ሊደርግ ነው።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፤ የብኣዴን ካድሬዎች ድርጅታቸውን እና አመራራቸው ላይ የሚታየውን ጉዳይ በተመለከተ የፖለቲካ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ተከትሎ ከሕወሓት አሽከር ከሆኑት ጋር በስብሰባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስብሰባው እንደተበተነ ታውቋል:: በሕወሓት እና በብኣዴን መካከል ልዩነቶች የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ተከስተው አሁንም በስፋት ቀጥለው ይገኛሉ::የተለያዩ ነባር የብኣዴን ካድረዎችን በሰብብ አስባብ የሚያንጠባጥበው ሕወሓት አሁንም አሽከሮቹን አሰማርቶ በድርጅታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲደረግ እና የሕወሓት ደባልነትና ፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያበቃ የጠየቁትን ወደ ገደል ለመግፋት አየተሯሯጠ ነው::

ባለፉት ሳምንታት በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ የተጠሩ ስብሰባዎች በሕወሓት አሽከሮች እና በለውጥ ጠያቂዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ስብሰባው ሲበተን …ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው ስብሰባ በከፊል ካድሬዎቹ ስላልመጡ ለሚመጣው ሳምንት የተላለፈ መሆኑን ታውቋል::በሕወሓት አሽከሮች እና በብኣዴን ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል::

አዲስ በወጣው እቅድ መሰረት በአማራው ክልል በድጋሚ አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ እንደሚደርግ እና በዚህ መካከል አስቸጋሪ እና አድመኞች የጸረ ሰላም እና የጸረ ሕዝብ ሃይሎችን የመደምሰስ እንዲሁም በአዲሱ የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አስፈላጊው ጥቅማጥቅሞችን ለአዳዲስ አባላት መስጠት የሚል ይገኝበታል::ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱ ችግር በፓርቲው ላይ የሚፈጥሩ ካድሬዎችን በማስወገድ በአዳዲስ ለመተካት ታቅዷል::

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግለ ለማጎልበትና የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ ለመገምገምና ለማጠናከር እነዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ የመስክ ጉብኝት እንዲያደርጉ በሶስት ቡድን የተከፈለ ልኡካን በሃገሪቱ ማሰማራቱ ይታወቃል:: እነዚህ የልኡካን ቡድን አባላት የመስክ ጉበኝት በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ በተግባራዊ ስራ ላይ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት በሚከተለው የመስክ ጉብኝት ምደባ መሰረት በሃገሪት የተለያዩ መስመሮች የተጓዙ የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ አመራሮች …
ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሸዋ ሮቢት ጨምሮ በደሴ መስመር ላይ ያሉ የሰሜን ሸዋ የፓርቲው የዞን/የቀጠና አመራሮችን በማወያየት ጉዞውን ወደ ወልዲያ እና ደሴ ያቀና ሲሆን ……

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ የያዘ የጉዞ መስመር 2 ልዑክ ቡድን የካቲት 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከምስራቅ ጎጃም የዞን አስተባባሪዎች ጋር በደብር ማርቆስ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን 18 (አስራ ስምንት) ወረዳዎች የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ በ10 (አስሩ) ወረዳዎች ማለትም፡-
1ኛ. አነደድ 2ኛ. ደ/ማርቆስ ከተማ ወረዳ 3ኛ. ጎዛአምን 4ኛ. ማቻከል 5ኛ. ደብረ ኤሊያስ 6ኛ.ባሶ ሊበን
7ኛ. እናርጅ እናውጋ 8ኛ. ጎንቻ ሲሶእነሴ 9ኛ. እነብሴ ሳርምድርጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር/መርጦ ለማርያም 10ኛ. ሁለት እጁ እነሴ
ከላይ በተገለፁት ወረዳዎች የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ተዘርግቶ ስራዎች እየተሩ ሲሆን ወደቦታው ያቀናው የልዑክ ቡድን እነዚህን ወረዳዎች ከሚያስተባብረው የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በቀጣይ ቀናት በባህር ዳር፣ ወረታ (ደቡብ ጐንደር) እና ጐንደር በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ኢትዮጵያ ልዕካን ቡድን የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የያዘው የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶዶ ላይ ካለው መዋቅር ጋር አሰፈለጊውን ስብሰባና ግምገማ ካካሄዱ ቦሀላ ወደ ቀጣይ ከተማ ወደሆነችው አርባ ምንጭ ጉዞ ሲጀምሩ በሰዶ ፖሊሶች ተይዘው በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ ይገኛሉ::

ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ እና ምግብ እንዳይትገባላቸው የተደረጉት የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶስት አባላት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች የሆኑ ያልተማሩ ካድረዎች በበላይ ትእዛዝ በሚል ህገመንግስቱን በረገጠ መልኩ ሰላማዊ ትግልን መርጦ በመንግስት ተመዝግቦ በሚገኝ ፓርቲ እና አመራሮች ላይ የእስር እርምጃ መውሰዳቸው የዲሞክራሲ እሾዎች ማበባቸውን ያመለክታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ

“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ…አንባገነናዉያን ጋር እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ!

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 24/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ገደብየለሽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማመላከት ያደረጋቸዉን ጥናቶች ዋቢ በማድረግ በየካቲት 20/2006 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።መሰረቱን አርሊንግተን ቨርጂኒያ ያደረገዉ ፖለቲኮ የሚባለዉ ጋዜጣ/መጽሔት የኦባማ አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስትን ከመሰሉ ለነጻነት ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ያለዉ ምጸታዊ የዲፕሎማሲ ቁርኝትንም ይተቻል።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የዩናይትድ እስቴትስ መንግስታት ዜጎቻቸዉን ከሚጨቁኑ አገራት ጋር ግንኙነት ለመመስረት እምብዛም እንደማይጥሩ ፖለቲኮ እየገለጸ፤ለሚዛናዊነቱ ተስፋ የተጣለበት የኦባማ ካቢኔ ከሌሎቹ የዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዝዳንቶች በባሰ መልኩ ለዜጎቻቸዉ ደህነነት ምቹ ካልሆኑ 25 አገራት ጋር ግንኙነት አለዉ ሲል የኦባማን የብሐራዊ ደህነነትና ጥበቃ አማካሪ የሆኑትን ሱዛን ራይስ ንግግርን በዋቢነት ያቀርባል። ራይስ “ግልፅ እንሁን አንዳንዴ እኛ አጥብቀን የምንይዛቸዉን ዉድ የሆኑ መብቶችን ከማያከብሩ መንግስታት ጋር የስራ ግንኙነት አለን” በማለት በባለፈዉ የነሐሴ ወር መናገራቸዉን ፖለቲኮ ይገልጻል።

ፖለቲኮ ለነጻነት የማይመቹ ብሎ ከጠራቸዉ 25 አገራት ዉስጥ ኢትዮጵያን በቁጥር 11 ላይ ያስቀመጠ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ይመሯታል የምትባለዋ ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጓን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣መንግስትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አካላትን ለማሰር እንደ ማህተም ትጠቀምበታለች ሲል ተጠያቂ ያደርጋል።ፖለቲኮ አክሎም የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በ1999 ሶማሊያን በመዉረር እራሱን ለዩናይትድ እስቴትስ ግልጋሎት ማቅረቡንያስረዳል። ይህንንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በአሜሪካ የሰለጠኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከብሔር ብሔረሰቦች የተነሱ አማጺያንን ለማስቆም የጦርነት ወንጀል መፈጸማቸዉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ክስ ቢቀርብበትም ዋሽንግተን አዲስ አበባን በዲፕሎማሲ “እቅፍ-እቅፍቅፍ” እያደረገች መቀጠሏን ገልጿል።

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ይጥሳሉ ከሚባሉት ጭቋኝ አገራት ጎራ ብትመደብም ፤እንደ አዉሮፒኣይኑ ቀመር በ2008 ብቻ ከዩናይትድ እስቴትስ 969 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ ተቀብላለች!

በኢትዮጵያ ዉስጥ ቀጣይ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ግድያ፣እስር፣የሐይማኖትነጻነትን መነፈግ፣የፕሬስ ነጻነት መመንመን፣የመማርና ማስተማር ሒደት ነጻነት በመንግስት መዳፍ ዉስጥ መግባት፣የመደራጀት-የመሰባሰብ-ሐሳብን በነጻ የመግለጽ ሁለንተናዊ መብት፣ የፍርድ ቤት አሰራር መበላሽትና በስልጣን መባለግን በመተንተን የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየካቲት 20/2006 አመታዊ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። የኦባማ አስተዳደር አካል የሆነዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳቃቂ የሆነ የመብት ረገጣ ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖሩን እያወጀ የኦባማዉ ቤተ-መንግስት ኢትዮጵያን ከመሰሉ በአንባገነናዉያን ከሚመሩ አገራት ጋር “መለስ-ቀለስ” ማለቱ እያስተቸዉ ነው። የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን የሚመሩት ጃን ኬሪ አገራቸዉ ከስህተት የጠራች አለመሆኗን ያስረዳሉ።

“ዛሬ ስለ ሌሎች አገራት ያለዉ ሪፖርት ይፋ ለማድረግ ብንመጣም፤ እዚሁ አገራችን ላይ እራሳችንን በከፍተኛ መልኩ ተጠያቂ እናደርጋለን! እንከን የለሽ አለመሆናችንን እናዉቃለን” ጃን ኬሪ።

ጃን ኬሪ መስሪያቤታቸዉ ይፋ ያደረገዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ዋሽንግተን ዲሲ ባሉ የመስሪያ ቤቱ አባላት ጥናት ብቻ የተዘጋጀ ሳይሆን በእያንዱ አገራት ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ሲያስረዱ “በመላዉ አለም ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በጥናት እንደዚሁም እነዚህን ጽሁፎችን በመጻፍ አክቲቪስቶችን በመቅረብ መንግስታትን በማናገር የኤንጂኦና የሚዲያ ሪፖርቶችን በመተንተን አያሌ ሰአታትን አባክነዋል”ሲሉም ገልጸዋል።

ኬሪ ለነጻነትና ለመብት በሚደረግ ጥረት ዉስጥ ግለሰባዊ ሚና የጎላ መሆኑን መሆኑንም ይገልፃሉ።ከተለያዩ አገራት የለዉጥ ተምሳሊት የሚሏቸዉን ግለሰቦችን ስም በማንሳት የኢትዮጲያዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሚናን አድንቀዋል “እስክንድር ነጋ ሐሳብን በነጻ ስለመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚጽፍ ነው” ብለዋል።

በሚያዚያ 4/2004 የፔን አሜሪካን ሽልማትን ያገኘዉ እስክንድር ነጋ አለም አቀፋዊ ትኩረትን ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት በሽብር ፈጠራ ወንጅሎት ከመስከረም 3/2003 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል።

የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነጻነትን ከሚነጥቁ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ነጻነትን ከተነፈጉ ብዙሗን አጋር በመሆን አብሮ እንደሚቆም ኬሪ ቃላቸዉን እያደሱ ይናገራሉ “ዛሬ ቃላችንን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን! ክብርን ከሚነፍጉ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ክብርን ከሚሹ ብዙሗን ጋር አብረን ለመቆም ዝግጁ መሆናችንንም ለመግለጽ እንወዳለን!”በማለት ቢያስረዱም መንግስታቸዉ ከጨቋኝ አንባገነናዊያን ጋር በሚያደርገዉ ዲፕሎማሲያዊ ቅርርብ ተጠያቂ እየሆነ ነው።

በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ብዙ ቃልኪዳን የገቡት በራክ ኦባማ ቃሊኪዳናቸዉ አለተፈጸመም። በተመሳሳይ መልኩ ያሁኑ የዉጭ ጉዳይ መስራያ ቤት ሐላፊ ጃን ኬሪም ሆኑ የቀድሞዋ ሒላሪ ክሊንተን ከአንባገነናዊያን ጋር ያለዉን ግንኙነት ሲያደረጁ እንጂ ሲያመነምኑ አልተስተዋለም በማለት በርካታ ምሁራን፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ተንታኞች ወቀሳ ያቀርቡባቸዋል።

በጥር 12/2001 ቃለመሃላ የፈጸሙት ፕሬዝዳንት ኦባማ ሰላምና ክብርን ለሚሹ የአለማችን ዜጎች የርሳቸዉ መመረጥ ብስራት እንደሆነ አመላክተዉ ነበር። ከትላላቅ የአለማችን መዲናዎች ጀምሮ ወላጅ አባታቸዉ እስከመጡበት የኬኒያ መንደር የተስፋ ቃል ነበራቸዉ! እንዲም በማለት ስሜትን በሚነካ መልኩ ተናግረዉ ነበር…

“ከትላልቆቹ መዲናዎች እስከ አባቴ የተወለደባት መንደር ዛሬ ለሚመለከቱን ህዝቦችና መንግስታት፤ አሁን አሜሪካ የእያንዳንዱ አገር የእያንዳንዱ ግለሰብ ወዳጅ ናት! ሰላምና ክብርን ለሚፈልጉ ሴቶችና ህጻናት ዳግም ለመምራት ዝግጁ ነን” ፕሬዝዳንት በራክ ኦባማ።
ኦባማ ምንጫቸዉ ለሆነችዋ አፍሪካ ፕሬዝዳንታዊ ሐይላቸዉን በመጠቅም ያበረከቱት አስተዋፅኦ አናሳ ነዉ።ፕሬዝዳንቱ ቃለመሃላቸዉን ሲፈጽሙ ስልጣንን በማጭበርበር-በሙስናና የሐሳብ ልዩነትን በማፈን በሚቆናጠጡ አንባገነናዉያን ላይ ጣታቸዉን ቢቀስሩም ከነዚህ ምቹ ያልሆኑ አሳፍሪ መንግስታት ጋር እርሳቸዉም ይሁን ካቢኔአቸዉ ዲፕሎማሲያዊ ገደብን አለማበጀቱ አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።

በአሜሪካዋ መዲና በዋሽንግተን ዲሲ ጥር 12/ 2001 ቀዝቃዉ አየር በጭብጨባ እየሞቀ ብዙዎች እያለቀሱ ኦባማ ለአንባገነናዊያን መልእክት አስተላልፈዋል…

“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ…አንባገነናዉያን ጋር
እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ።

ብዙ የተገቡ ቃልኪዳስኖች ተግባራዊ ሳይሆኑ በየካቲት 20/2006 ከዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአመቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲታወጅ “ከነጻነት ፈላጊዎች ጋር እንቆማለን!” የሚል ቃልኪዳን ተገብቷል።የዩናይትድ እስቴትስ መንግስት ባወጣዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት “ጨቋኝ-አፋኝ-አሳሪ-ገዳይ-ኢዲሞክራሲያዊ” መሆኑን ይፋ አድርጓል። ፖለቲኮ ጋዜጣ/መጽሔት ይህ ሪፖርት በወጣበት ማግስት የኦባማ አስተዳደር ኢትዮጵያን ከመሰሉ ለዜጎቻቸዉ ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ይወዳጃል ሲል ይተቻል።

የዲሞክራሲ ተምሳሊት ነን የሚሉ የምእራቡ አገራት ለአንባገነናዊያን ዲፖሎማሲያዊ ከለላ መስጠታቸው የጥቅም ትስስር ወይስ ምጸታዊ የሆነ የዲፕሎማሲ ጨወታ? የሚለዉ ጥያቄ ቢነሳም …ትችቱእንደቀጠለ ነዉ።

ሳዲቅ አህመድ

የደሴ ሕዝብ ከመለስ ፋውንዴሽን ጋር በተያያዘ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈለግበታል::

ምንሊክ ሳልሳዊ :- ከደሴ የሚደርሱኝ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሕወሓት አዛዥነት በብኣዴን ሰብሳቢነት የመለስ ዜናዊን አመራር አካዳሚ ሕንጻን ለመገንባት የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝቡ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠበቅበት እና ለግንባታው የግዴታ አስታውጾ እንዲያደርግ እያስገደዱት መሆኑን እና ሕዝቡም ከኑሮ ውድነት ጎን ለጎን ከአፉ ላይ ሊጎርሰውን ያዘጋጀውን በጉልበተኞች እየተነጠቀ መሆኑን በማማረር አቤቱታውን ማሰማቱን የደሴ የለውጥ ሃዋርያ ወጣቶች አንድነት ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው መረጃ ገልጽዋል::

መረጃዎቹ እንደጠቆሙት የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክፍለከተሞች ባሉ የወያኔ ካቢኔዎች ሲሆን እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በግል እንዲሰበስብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ለሰበሰበ ሽልማት ስለሚሰጠው የሚል ቅል ስለተገባላቸው የስልታን እና የደሞዝ እድገት ለማግኘት እና ታማኝነታቸውን ለማረጋገጥ በሽፍን ድጋፍ ሕዝቡን በግዳጅ እና በማስፈራራት በዛቻ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያደረጉት ሲሆን ይህንን በተመለከተ ሕዝቡ በቤቱ አሊያም በስብሰባ ካልተገኘ በቅጣት ሁሉ መልክ ተጨማሪ እንዲከፍል ይደረጋል የሉት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ሕዝቡ በሚሄድበት መስሪያቤት አሊያም ስብሰባ ቀደም ብሎ የከፈለ ሰው ደረሰኙን ካልያዘ ጉዳዩን ለማስፈጸም በድጋሚ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን እረስቸዋለሁ ሄጄ ላምጣ የሚል ነገር ተቀባይነት የለውም::

እንዲሁም በደሴ የብኣዴን ጽ/ቤት ሃላፊነት ተጨማሪ ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል በግዳጅ ገንዘብ እየተሰበሰበ ሲሆን የጽ/ቤቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታዊ ይርጋ (የቀድሞ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ) ከዚህ ቀደም በሙስና ታስረው የነበሩ እና ከህግ ውጪ ለፖለቲካው አስፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው በትእዛዝ ከተፈቱ በኋላ ሲቭል ሰርቭስ ኮሌጅ ተልከው ሰልጥነው በደሴ የብኣዲን ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው ከተመደቡ ጀምሮ በግዳጅ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖረውን በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ እያስገደዱ የመንግስት ሰራተኛውን ከደሞዙ ላይ 30% እንዲቆረጥ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም በየቤቱ የብኣዴን ካድሬዎች እየዞሩ ከቀበሌ ሰዎች ጋር በመሆን ሕዝቡ 100 ብር እንዲከፍል በበደል ላይ በደል እየፈጸሙበት ይገኛል:: እንዲሁም ባለሃብቱን እያስገደዱት ያሌለን ገንዘብ እንዲተፋ ወጥረው ይዘውታል ሲሉ ለምንሊክ ሳልሳዊ መረጃውን ልከዋል::
=================ምንሊክ ሳልሳዊ====================
በሌላ ዜና በደዜ ከተማ ዙሪያ ጨለማን ተገን አድርገው የሰዎች ግድያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች ከበፊቱ በበለጠ በመበርከቱ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ አራት ሰአት በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የሰአት እላፊ ገደብ መጣሉን የከተማው ነዋሪዎች ለምንሊክ ሳልሳዊ በስልክ ገልጸውለታል::

ባለፉት ሁለት ቀናት በመላው አገሪቱ የተካሄዱትን ፍተሻዎች በተመሳሰለ መልኩ የሞባይል ቤቶች እና የኢንተርኔት ካፌዎችን እንዲሁም የመረጣቸውን ብሎም የጠረጠራቸውን ግለሰቦች በድንገት ፍተሻ በማካሄድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞባይሎች ላፕቶፖች ዲስክቶፖች ኮምፒተሮች እና የሚሞሪ ካርዶች ሰብስቦ የወሰደው የደሴ ፖሊስ ሰአት እላፊውን ጥሶ የተገኘ ነዋሪ በጸጥታ ሃይሎች ለሚወሰድበት ማንኛውም እርምጃ መንግስት ተጠያቂ እንደማይሆን ገልጿል::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ የደሴ ከተማ በፌዴራል ፖሊስ ወታደራዊ ልምምድ ተወጥራ እንደምታመሽ ታውቋል:; ቁጥራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊሶች ከምሽቱ 3 30 ጀምሮ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ በዋናው የከተማዋ መንገዶች በመጠቀም ላይ ሲሆኑ በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ነግረውታል::ይህንን እያደረጉ ያሉት የከተማውን ነዋሪ ለማስፈራራት እና ለማሸበር እየጣሩ እና በሃርቡ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የፌዴራል ፖሊሶች ለሊቱን በወታደራዊ ልምምድቸው ጊዜ ስለሚጮሁ ህዝቡን ከስራ ቤቱ ገብቶ እንዳያርፍ እንቅልፍ እየነሱት ሲሆን ምን ያክል መንግስት ጭንቀት ላይ እንዳለ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩት ነዋሪዎች ገልጸዋል::መረጃውን ላቀበላችሁኝ የደሴ ወጣቶች አመሰግናለሁ ምንሊክ ሳልሳዊ::

Image

ውህደት ለምን ይኮነናል? በዳንኤል ተፈራ
#Ethiopia #UDJ #AEUP #Blueparty #EPRDF #Ginbot7

ሰሞኑን በውህደት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቷል፡፡ እየተለፋበት ባለው የውህደት እንቅስቃሴ ላይ ዘመቻ የከፈቱ ኃይሎችን በሦስት ከፍሎ ማየት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

1ኛ. ኢህአዴግ ሲሆን ተቃዋሚዎችን በተበታተነ ሁኔታ በመግጠም አሸናፊ ሆኖ መውጣት ይቻላል ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ ወደ ኮሮጆ ግልበጣ ከሚሄድ ይልቅ ተቃዋሚዎችን ከፋፍሎ ወይም ተሰባስበው አንድ ትልቅ የፖለቲካ ሃይል እንዳይፈጥሩ በማድረግ ለማሸነፍ መሞከር የመጀመሪያ ምርጫው ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ ውህደቶች እንዳይሳኩ ትግል ማድረጉን ይቀጥላል፡፡ በአጠቃላይ ዉህደት ለዚህ ስርዓት አይመቸውም፡፡

2ኛ. በሁለተኛነት ብቻችንን የኢትዮጵያን ፖለቲካ መሸከም እንችላለን የሚሉ ወገኖች እንዲሁ የውህደት እንቅስቃሴው ላይ ቀስት ለመስበቅ የተጣደፉ ይመስለኛል፡፡ ባለብዙ መልኩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን ለእንደዚህ አይነት ሀሳብ የሚመች አይደለም፡፡ ፖለቲካችን ወደድንም ጠላንም አታካችም ቢሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን ማቀራረብ የሚፈልግ፣ በውይይት መለዘብ የሚገባውና በብሄርና ህብረብሄር ጫፎች የተወጠረ ነው፡፡ ስለዚህ በሀገር ጉዳይ ላይ መወያየትና ውህደት መፍጠር ተገቢ ነው፡፡ አንድን ‹‹ግሩፕ›› ብቻ እወክላለሁ የሚል የፖለቲካ ሃይል ውህደትን በመኮነን፣ ያውም ውህደት ያስፈልጋል የሚሉ የፖለቲካ ሃይሎችን ሀሳብ ሳያከብርና በጣም ተራ የሆነ ምክንያት እየሰጠ ውህደቱ እንዳይሳካ ይታገላል፡፡ ቢያንስ ብቻየን የኢትዮጵያን ፖለቲካ እሸከማለሁ ማለት መብት እንደሆነ ሁሉ ውህደት ያስፈልጋል ማለትም መብት እንደሆነ የሚያምን አይመስለኝም፡፡ እናም ወንጋራ ሀሳብ የሚያቀርቡ አንዳንድ ግለሰቦች ቆም ብለው ቢያስቡ መልካም ይመስለኛል፡፡

3ኛ. በሦስተኛነት ውህደትን የሚኮንኑት በቅንነት የተቃውሞ ጎራው በመዋሃድ ትልቅ ሃይል መሆን ይገባዋል ብለው ሲወተውቱ የነበሩትና እስካሁን በውህደት ትልቅ ሃይል አለመፈጠሩ የሚያስቆጫቸው አንዳንድ ግለሰቦች ናቸው፡፡ ግን ደግሞ ፖለቲካ ያው ፖለቲካ ነውና እንደ ቅን ሰዎች ሃሳብ ነገሮች ላይሄዱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በሆደ ሰፊነት ውህደቶች እንዲሳኩ መጣር የእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ሁሉ ውትወታና ስራ መሆን አለበት፡፡ በመጨረሻ ግን እኔ በግሌ እንደማምነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ የተወሰኑ ግለሰቦች ሊሸከሙት እንደማይችሉ ነው፡፡ ምናልባት ወደፊት ግን ይቻል ይሆናል፡፡ የግለሰቦች መብት የሚረጋገጥበት ስርዓት ከተዘረጋ በኋላ ማለት ነው፡፡ ጎበዝ አሁን እየተደረገ ያለው ትግል ግን ስርዓት የመፍጠር ነውና ሃሳብን እያቻቻሉ መዋሃድ ተገቢና ወቅታዊ ነው፡፡

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።

በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣ እንደገና መልሰን የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን። እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው።

የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን። በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው። ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው። “ኢትዮጵያዊያን በህግ ፊት እኩል ናቸው” ይላል። ከሁሉ በላይ ደግሞ የ1995ቱን ስናይ “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው” ብሎ እጅግ ኣጠንክሮ ለዜጎች መብት መቆሙን ይደነግጋል። በውነቱ ይህ ኣንቀጽ ብቻውን ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዋስትና ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ተግባራዊው እውነት ደግሞ ለብቻው በተቃራኒው ተንሰራፍቶ ይታያል። ይህ ለምን ሆነ? እንዴት እንዲህ ሊሖን ይችላል? ብለን ነው መጠየቅ ያለብን። እንዲህ ስንጠይቅ የችግሩ ዋና ጉዳይም የስርዓት እጦት ሳይሆን ሌላ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። በርግጥ ለወደፊቱዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ስርዓት ማምጣት ያስፈልጋል። በተለይም ብዙህነቱዋን ተንከባክቦ የሚይዝ ማህበራዊ የፖለቲካ ስርዓት ያሻናል። ያ ማለት ግን ከችግራችን እንድንወጣ ብቻውን ዋስትና ነው ማለት ኣይደለም። የቱንም ያህል ጥሩ ስርዓት ዘርግተን ከችግራችን ሳንወጣ ልንቆይ እንችላለን። ርግጥ ነው የማንነት ፖለቲካ ማህበራዊ ቀውስን ያመጣ ችግሮች የበለጠ እንዲነዱ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ መንግስት ውድቀት በሁዋላ ከዚህ የፖለቲካ መዋቅር መውጣታችን ለመፍትሄ ትልቅ በር ኣለው። ይሁን እንጂ ኣሁንም ቢሆን የቱንም ያህል ቆንጆ ስርዓት እናምጣ ኢትዮጵያን ከመከራና ከርሃብ የሚያወጣት እሱ ብቻውን ኣይደለም። ታዲያ ምንድነው? የሚል ጥያቄ መምጣት ኣለበት። ኣዎ፣ ዋናው የሃገራችን ችግር ያለው የፖለቲከኖች ስብእና ተክለሰውነት ወይም ፐርሰናሊቲ ጋር የተገናኘ ነው።

ሃገራችን ከችግር እንድትወጣ ከተፈለገ የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። የችግሮቻችን ቁንጮም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እጦት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስንል ኣንድ ፓርቲ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የፍርድ ቤቱን ልጓም ለቀን መልሶ ከበላንም ይብላን፣ በራሳችን ላይ ይፍረድብን፣ ብሎ በራስ ላይ የመወሰን ኣቋም ነው። ወታደሩን ኣገርህን ጠብቅ የፓርቲ ጠባቂ ኣይደለህም ኣንተ ኣገር ጠባቂ ነህ ለማለት የፖለቲካ ሰዎችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ፖሊሱን፣ ባንኩን፣ ሚዲያውን ሁሉ ልጓሙን ለቆ በሙያህ ኣገልግል ብሎ መወሰን ሲቻል ነው ከገባንበት ኣረንቋ የምንወጣው። የናፈቀንን ዴሞክራሲ በህይወት የምናየው። ጥያቄው ይህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዴት ሊመጣ ይችላል ነው። የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ከራስ ጥቅምና ዝና በላይ የህብረተሰብን ዝናና ጥቅም በተጠሙ ሰዎች ሊነቃነቅ ይችላል። ኣንድ ቁርጠኛ መሪ ኣገር ሊለውጥ ይችላል። በታሪክ የታዩ ኣንዳንድ ቁርጠኛ መሪዎች በየሃገሩ ተነስተው ጥሩ መሰረት እየጣሉ ኣልፈዋል። በሃገራችንም የተጠማነው ይህንን ነው።

በኣሁኑ ጊዜ ተቃዋሚው ክፍል መንግስትን ኣጥብቆ ማውገዙ ትክክል ነው። የህዝቡም ልብ ነጸብራቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መንግስት በማንኛውም መንገድ ሲወድቅ ስልጣን ይዞ ጥሩ ስርዓት መዘርጋቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ቁርጠኝነት (political commitment) ያላቸውን ሰዎች ይዘዋል ወይ? ብለን እንድናስብ ያደርገናል። በዚህ ረገድ ተቃዋሚው ጥቃቅን በሆኑ ፖሊሲዎች ከመከፋፈል ይልቅ ወደ ጋራ እያመሩ ከሁሉ በላይ የፖለቲከኞችን ስብእና የመገንባቱ ላይ ማተኮር ለነገይቱ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። ይህን ስብእና ወይም ተክለሰውነት የመገንባት ስራ ፓርቲዎችን ቢዚ የሚያደርግ ወቅታዊ ስራ መሆን ኣለበት። ኢትዮጵያ በኣሁኑ ደረጃዋ ጥቃቅን ፖሊሲዎችን በማነጻጸር የምታማርጥበት ጊዜ ላይ ኣይደለችም። መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ያጣች በመሆኑዋ የስካንዲኒቪያው ኣይነት ዴሞክራሲ ይሻልሻል የኣሜሪካው ኣይነት? ማለቱ ያልበላትን የማከክ ያህል ነው። ሁሉቱም ሆኖላትስ ነው?
ዋናው በኣሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጉዳይ ፓርቲዎች እኔ እሻላለሁ ለማለት ዋናው መመዘኛቸው የተሰባሰቡት በተለይም ኣመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች የፖለቲካ ቁጠኝነት ኣላቸው ወይ? ቁርጠኝነት በሞላቸው ሰዎች ቁጥር የትኛው ፓርቲ ያይላል? የሚል ልብ ያለው ድጋፍ ነው በተግባር የሚታየው ወይም መታየት ያለብት።

በቲየሪ ደረጃ በኣሁኑዋ ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ ኣይገባም። ይሁን እንጂ በተግባር ይገባል። ይገባል ብቻም ሳይሆን ፍርድ ቤት የፖለቲካ መሳሪያ ነው። ኣሁን እዚህ ጋር የጎዳን የስርዓቱ ወይም የኣሰራሩ ጉዳይ ሳይሆን መከራ ውስጥ የከተተን ጉዳይ የግለሰቦች ስብእና ጉዳይ ሆኖ ነው የምናየው። ለምን እነዚህ ግለሰቦች ስርዓቱን ይጥሳሉ፣ ህጉ ለምን ኣቅም ያጣል? ካልን የፖለቲከኞቹ ላእላይ ስብስብ በተለያየ የግል ጥቅማጥቅም የተተበተበ በመሆኑ ነው። ድህነታችንም ኣንዱ ኣስተዋጾ ያደረገ ይመስላል። የተሻለ ስራ ለማግኝነት፣ ከድህነት ለመላቀቅ፣ ፖለቲካን መሳሪያ ማድረጉ የተለመደ መሆኑና ወደዚያ ጠጋ ያሉ ሃላፊዎች በዚህ ሞቲቭ የተሞሉ ስለበዙበት ስርዓቱ በቁሙ እንዲሞት ኣድርጎታል።

ባለፈው ጊዜ ኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋታል የሚል ኣንድ ኣርቲክል ጽፌ ነበር። በርግጥም በኣሁኑ የነጻነት ትግል ኣሰላለፍ በኩል ጎድሎ የታየው ይሄ ነውና ይህንን ማቋቋም ተገቢ ነው። ይህ ኮሚሽን ፓርቲዎችን እያበራታታ ይህን ተፈላጊ ስብእና በመገንባቱ ረገድ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ፣ የመፍትሄ ኣሳቦችን በማጠናቀር ረገድ፣ ለኣዲሲቱዋ ኢትዮጵያ የሚሆነውን ኣዲስ ሰውነት በመጠቆሙ ረገድ ከባድ ሚና ሊጫወት ይችላል። ከዚያ በተረፈ ደግሞ እኛ ተራ ዜጎች መሪዎቻችንን የማጎልበትና ወደ ህብረት የመግፋት እንዲሁም ስብእናቸውን የመገንባት ሃላፊነት ኣለብን።

የብዙ ኣፍሪካ ሃገሮች ችግር ይሄ ይመስለኛል። ታግለን በብዙ መስዋእትነት ኣንድ ኣምባገነን ከጣልን በኋላ መልሰን በሌላ ኣምባ ገነን እንተካለን። ሌላው ኣለም እየተሻሻለ ሲሄድ ይሄኛው ክፍለ ኣለም ወደ ኋላ የቀረበት ትልቁ ምክንያት የነጻነት ታጋዮች ራሳቸው በሚገባ ለኣመራር የሚበቃ ስብእና ሳያዳብሩ ወደ ስልጣን ስለሚመጡ ነው።ደቡብ ሱዳን ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ለብዙ ኣመታት የነጻነት ትግል ታግለው፣ ብዙ ደም በመፍሰሱ ዓለም ሁሉ እነዚህ ሰዎች ቢገነጠሉ ይሻላል ብሎ ፈርዶላቸው ተገነጠሉ። የዳርፉሩን እልቂት የማያውቅ፣ ያልሰማ ያለም ክፍል የለም። ያ ሁሉ ሆኖ ኣዲስ ኣገር ከመሰረቱ በኋላ ገና ኣንድ ጊዜ እንኳን ምርጫ ሳያካሂዱ፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይመሰርቱ፣ ከሁለት ዓመት ያልዘለለ እድሜ ያላትን ኣገር በጎሳ ከፋፍለው ማመስ ጀመሩ።

ያለ መታደል ሆኖብን በኣንዳንድ ኣፍሪካ ሃገራት የሚነሱ መሪዎች ስልጣን ላይ ከመጡ በሁዋላ ሁለት ነገር በጣም ይወዳሉ። ኣንደኛው ዝና ሲሆን ሁለተኛው ገንዘብ ነው። ሁለቱም እጆቻቸው ይዘዋል። ባንዱ ስልጣን በሌላው ገንዘብ። ዝናውን ወደው ገንዘቡን ችላ የሚሉ ቢሆኑ ትንሽ ይሻል ነበር። ነገር ግን ሁለቱንም በሃይል ስለሚወዱና ለዚህ የተሰጠ ስብእናቸው በውስጣቸው ስላልሞተ ክብ በሆነ ችግር ውስጥ እንድንወድቅ ኣድርጎናል።ኢትዮጵያዊያን በዚህ ላይ ልንነቃ ይገባናል። በተለይ የፖለቲካ ሰው መሆን የፈለጉ ወገኖቻችን፣ መሪ መሆን የሚሹ ወገኖቻችን በየጊዜው የባህርይ ለውጥ እያሳዩ በኣመለካከትና በሃላፊነት ስሜት እያደጉልን እንዲሄዱ እንሻለን። ከፍ ሲል እንዳልኩት እኛ ተራ ዜጎች ከውጭ ሆነን መፍረድ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻችንን መንከባከብና ፍቅርን ክብርን ማሳየት ለፖለቲካ ቁርጠኝነታቸው ሃይል ይሰጣል።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

[email protected]
ገለታው ዘለቀ