ዓለም አቀፍ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድርና ዕርዳታ እንዲያቆሙ ግብፅ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን መንግሥት መረጃ እንዳለው አስታወቀ፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው የሦስትዮሽ ድርድር ሦስተኛ ስብሰባ በቅርቡ ያለውጤት ከተበተነ በኋላ፣ በግብፅ በኩል አፍራሽ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓርብ ረፋድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና፣ በግብፅ በኩል የቀረበውና በኢትዮጵያና በሱዳን ውድቅ የሆነው ሐሳብ፣ እስካሁን ግድቡን አስመልክቶ የተጀመሩ ውይይቶችን ወደኋላ የሚመልስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ባለሙያዎች ያሉበትና ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የኤክስፐርቶች ፓነል ለአንድ ዓመት በግድቡ ዙሪያ ጥናት አካሂዶ ባወጡት ሪፖርት፣ ከተወሰኑ ቴክኒካዊ ማስተካከያዎች ውጪ ግድቡ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የፓነሉ ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሦስቱ አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች ያሉበት ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን፣ ግብፆች አዲስ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የኮሚቴውን ሥራ በበላይነት እንዲከታተል የሚል ሐሳብ ነው ያቀረቡት፡፡

እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ፓነል መቋቋም ላይ ሳይሆን፣ ሚናውን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ ልዩነት የተነሳ ያለውጤት ስብሰባው ከተበተነ በኋላ፣ ግብፆች በሚዲያዎቻቸው ‹‹ኢትዮጵያ ለመተባበር እምቢተኛ ሆነች›› እያሉ እያቀረቡ መሆኑንና ከዓለም ባንክ፣ ከአይኤምኤፍና በሌሎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በምንም ምክንያት ኢትዮጵያ በገንዘብ እንዳትደገፍ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን መንግሥት መረጃ እንደደረሰው አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ይቋረጣል የሚል እምነት ያላቸው ግብፃውያን፣ የገንዘብ ተቋማቱ ኢትዮጵያ የዚህን ግድብ ግንባታ ካላቆመች በማንኛውም መንገድ የሚያደርጉትን ዕርዳታ እንዲያቆሙ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ ግብፃውያን ከዚህ አፍራሽ ድርጊታቸው ተቆጥበው በኤክስፐርቶች ፓነል ሪፖርት መሠረት መተባበራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ ከተለመደው አፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማስታወቅ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሑመራና በመተማ አካባቢ ኢትዮጵያ ለሱዳን መሬት ስለመስጠቷ እየተነገረ ስላለው ጉዳይ መንግሥት አስተባብሏል፡፡ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሱዳን በግድቡ ላይ ባሳየችው አዎንታዊ አቋም ምክንያት፣ ሲያወዛግብ የቆየውን ሰፊ የድንበር መሬት መስጠቷ የተዘገበ ቢሆንም፣ አምባሳደር ዲና ግን፣ ‹‹እንኳን መሬት ሊሰጥ ይቅርና በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ውይይትም አልተቋጨም፤ እስካሁንም ስምምነት ላይ የተደረሰ ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡

ላለፉት አሥር ዓመታት ድንበሩን በተመለከተ ሲሠራ የቆየው የጋራ ኮሚሽን፣ በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር እንዲካለልና የግጭት መንስዔ የሆነውን ጉዳይ ለመፍታት እየሞከረ መሆኑን፣ በቅርቡ ‹‹ለሱዳን መሬት ተሰጠ›› ተብሎ የተነገረው ግን መሠረት የሌለው ወሬ መሆኑን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡

በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡

በአደባባይ የሚጽፉ ሰዎች ሁለት ነገሮችን ለይተው መገንዘብና ለሌሎችም ሲየያስተላልፉ ለይተው ማስተላለፍ አለባቸው፤ አንዱ የሆነና የተረጋገጠ ሁነት ነው፤ይህንን ሳይበርዙና ሳይከልሱ እንዳለና እንደተገኘ ማስተላለፍ ግዴታ ነው፤ ሁለተኛው የራስ አስተያየት ነው፤ የጠራውንና የነጣውን አውነት ከጎደፈ የግል አስተያየት ጋር አጋብቶ ማቅረብ ወይ አለማወቅ ነው፤ አውቀው ከሆነም ለማታለል ከመሞከር የሚቆጠር ነው፤ በአለንበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የምናየው ፊደሎቹን ማወቅ እንደሙሉ እውቀት ይቆጠራል፤ ወይም በሌላ አነጋገር ፊደልን ማወቅ የመጻፍ ችሎታን ይሆናል፤ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፤ ፊደሎችን ማወቅ ትልቅና መሠረታዊ የእውቀት ጎዳና ላይ መግባት ነው፤ ጎዳናው ግን በጣም ረጅም ነው፤ በእውቀት ጎዳና ላይ መግባት የእውቀት ባለቤት ከመሆን ጋር እንዳይደባለቅ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአገራችን ፊደልን ማወቅ ሌላም አደጋ አለው፤ ፊደልን ማወቅ ከሥልጣን ጋር ሲጋባ የሚያስከትለውን ውድቀት ከአንዴም ሁለቴ አይተናል፤ እያየንም ነው፤ ስለዚህም ፊደል ኃላፊነትን ያመጣል፤ አለዚያ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ያየነው ውድቀት እየተከበረ ይቀጥላል፡፡

መጻፍ እንደመናገር ሊቆጠር ይቻላል፤ሆኖም በመጻፍና በመናገር መሀከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ በንግግር ላይ ከሰዎች በሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ እንዲህ ማለቴ ነው ብሎ የተናገሩትን እዚያው ለማረምና ለማስተካከል ይቻላል፤ በተጻፈ ነገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ወዲያው የመታረም ዕድል የለም፤ ስለዚህም ለመጻፍ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው ፊደልና ሥልጣን ሲጋቡ ሰንደቅ ዓላማው ጨርቅ ነው ከማለትም ሊያልፍ ይችላል፤ ለምሳሌ የደርግን የትርፍ ቤቶች አዋጅ ብንመለከተው ‹‹ትርፍ ቤት›› ሲል ትርፍን እንተወውና ‹‹ቤት›› ለሚለው ትክክለኛ ትርጉም አልሰጠም፤ ስለዚህም በጭራሮ የተያያዘ ምንም ‹‹ቤት›› የሚያሰኘው (መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ … የሌለው) በሃምሳ ሳንቲም የሚከራይ ነገር ‹‹ቤት›› ተብሎ በሺህ ብር ከሚከራይ ቤት ጋር ተወረሰ! ያፈረ የለም እንጂ አሳፋሪ ነው!

እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከየት የሚመጣ ነው? አንድ አጠቃላይ የአስተሳሰብ ችግር አለ፤ ለየት ያለውን ከጅምላው፣ ግዙፉን ከረቂቁ፣ አንዱን ከብዙው ያለጥንቃቄ ማደባለቅ በአማርኛ በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ የአስተሳሰብ ችግር ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (አበሻና ሆድ የሚለው ጽሑፍ ባሕር ተሻግሮ የአበሻን ነገር-ዓለም ትቶ የተጠበሰ ውሻ (ሆት ዶግ) የሚበላውንም አስቀየመውና ሌሎች ስለአበሻ የጻፍኋቸውን ተውኩት እንጂ አበሻና መናገር የሚለው በተለይ ለባሕር ማዶው ዘሎ-ጥልቅ ተስማሚው ነበር፤) በማናቸውም ነገር ላይ ለመቀባጠር በጣም ኃይለኛ ምኞት አለው፤ አንዱ ያስተሳሰብ ችግር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሳያስቡና ሳይጨነቁ አፍ እንዳመጣ ከመናገር ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፤ አሁን ደግሞ የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤ የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤ ለውጡ የተጣራ ባይሆንም ሃያ ዓመታት መፍጀቱ የወያኔን የመማር ፍጥነት የሚያመለክት ነው፤ የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል፤ ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ ምን እንደሚባል እንጃ! ከቀኝ ወደግራ የዞረ? ወይስ ከግራ ወደቀኝ? ወይስ … ቀኝ ፖሊቲካ ባዶ ከረጢት ይዞ ይቀራል።

በተደጋጋሚ እንዳየሁት ለግለሰብ መብቶች የቆመ ቀኝ-ዘመም፣ ለቡድን መብቶች የቆመ ግራ-ዘመም የሚባል ይመስላል ይህ ስሕተት ነው።

ቀደም ሲል የታወቀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እኔን ቀኝ-ዘመም እያለ ጽፎ ሳይ ይህ ሰው በአውነት አንድ መዝገበ ቃላት ማየት አቅቶት ነው? ወይስ እኔን በተለየ ዓይን ለማየት ከመፈለግ የተነሣ ነው? ወይስ የሲአይኤውን መልክተኛ ፖል ሄንዜን ሰምቶ ነው? የሱ ጎሣ አባል መሆንንና አለመሆንን እኔ የምመርጠውና የምወስነው አይደለም፤ ታምራት በኢትዮጵያዊነት ወይም በዜግነት ዓይን ሊመለከተኝ አለመቻሉም የእኔ ጥፋት አይደለም፤ ሁሉም ቢቀር በሰውነት ደረጃ ሊያየኝ ይችል ነበር፤ ይህንንም አልቻለም፤ እንግዲህ ወይ እኔ ሰው አልሆንኩለትም፤ ወይ እሱ ወደሰውነት ደረጃ አልደረሰም፤ በታምራት ነገራ ቀኝ-ግራ መጋባት እንደኔው ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረው ክፍሉ ሁሴን ወደጥናት ተመልሶ የታምራትን ስሕተት አረጋገጠ፤ እኔም እንዲሁ አደረግሁና የታምራት ነገራን ግራ መጋባት አረጋገጥሁ፤ ታምራት ነገራ የጎሣ ቀኝ ገብቶት ግራ ፖሊቲካ ቀኝ ሆኖበታል! ቀኝ-ግራ ፖሊቲካ በጎሣ አባልነት የሚገኝ ወይም የሚታጣ ይመስለዋል፤ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ ቆሞ መከራከር ለታምራት እንግዳ ነገር ይመስለኛል፤ ገና እሱ ሳይወለድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለምን የኢትዮጵያ ራድዮ በኦሮምኛ አይናገርም? በማለት ጌታቸው ኃይሌ ጋር ሆነን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰዎችን ሞግተን ነበር፤ ይህ ለታምራት የቀኝ ፖሊቲካ ነው፤ የሱ ጎሣ-ዘመም ፖሊቲካ ግራ መሆኑ ነው! ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።

አሁን ደግሞ ሰሎሞን አብርሃም ይህንኑ የታምራት ነገራን ስሕተት ለመድገም የዳዳው ስለመሰለኝ በዝምታ ለማለፍ አልፈለግሁም፤ ሰሎሞን (liberalism) የሚለውን የአንግሊዝኛ ቃል በባሕርዩ የሌለበትን ትርጉም ሊሰጠው ይዳዳዋል፤ ሰሎሞን አብርሃም ሊጽፍበት የተነሣው ጉዳይ በእኔ ግምት በጣም ወቅታዊና አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የግል ስሜትን ከሁነት ጋር፣ ያልተጣራ የተውሶ ሀሳብን (‹‹ፊዩዳሊዝም፣ ሊበራሊዝም››…) ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አስተሳሰቡን ያጎደፈው ይመስለኛል፤ ያነሣው ጉዳይ በተለይም እንደሱ ላለ ፖሊቲከኛ ከስሜተኛነትና ከወገንተኛነት የጸዳ ቢያደርገው (‹‹ወግ አጥባቂ፣ቀኝ አክራሪ›› ..)፣ወይም ደግሞ ያልተጣራ (‹‹የሊበራል ዴሞክራሲን ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ይመስላሉ፤›› እያለ በጎን ከሚጎሽም የጸዳውን እውነት ፊት ለፊት እያቀረበ ድካማቸውን ቢተነትን የሚጠቅም ይሆን ነበር።

ግራና ቀኝ ፖሊቲካ የሚባለውን ከጎሣ ፖሊቲካ ጋር ለማገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች ወጣቶችን ወደአስከፊ ስሕተት እንዳይመሩ መጠንቀቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ የጎሣ ሥርዓትን የሚቃወሙትን ወገኖች በሌላ መንገድ ለመቋቋም ቢሞክሩ የተሻለ ነው፤ በጎሣ ክፍፍል ማመን ሌላው ቀርቶ በሰውነት ደረጃ ለመሰለፍም ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የጎሣ ፖሊቲካን ከግራ ፖሊቲካ ማዛመዱ እሳትና ውሀ ነው።

የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባፈለግ፣ ቁሸት ሕኖይቶ) ህዝብ የከፈተው ዓመፅ ዛሬ (ዓርብ 09/05/06 ዓም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ (12:10) ላይ ቆሟል። ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል። የፀጥታ ሃይሎች ግን ከአከባቢው አልራቁም።
አስተዳዳሪዎች ህዝቡን በፌደራል ፖሊስ አስከብበው ሲያስፈራሩት የዋሉ ሲሆን የህዝቡን ጥያቄ (ካሳ የመክፈሉ ጉዳይ) ለመመለስ ተስማምተዋል። ስለዚህ ህዝቡ በጠየቀው መሰረት መንግስት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል። የታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች ግን አይፈቱም። ህዝቡ “የታሰሩትን ይፈቱልን” ብሎ ሲጠይቅ “እርምጃ እንወስድባችኋለን፣ ማንም መጥቶ አያድናችሁም” የሚል ማስፈራርያ ደርሷቸዋል። ስለዚህ መንግስት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩትን ዜጎች ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለም።
የመንግስት አካላት ህዝቡን ካሳ ለመክፈል ሲስማሙ የህዝቡን ጥያቄ ትክክለኛነት ተቀብለውና አምነው እንደሆነ አቅርበዋል። ጥያቄው ያነሱት ዜጎች ከእስር ለመፍታት ግን ፍቃደኛ አይደሉም። በትግራይ ዜጎች መብታቸው ሲጠይቁ ለእስር ይዳረጋሉ። የአፅቢ ወንበርታ ጠያቂዎች ምሳሌ ናቸው። ታሳሪዎች የዛሬን ጨምሮ ስምንት ናቸው።
ጥያቄ የጠየቀ ዜጋ ለምን ይታሰራል? ጥያቄ የመጠየቅ መብት የለውም? መንግስት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ለምን ወደ ሃይል እርምጃ ይሄዳል? አምባገነኖች በራስ የመተማመን ባህሪ ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።
አብርሃ ደስታ

የወያኔን የሚዲያ አፈና ማመከን የጊዜው አጣዳፊ ተግባር ነው::

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝባችን ስለራሱና ሰለአገሩ ምንም አይነት መረጃ ከአማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች እንዳያገኝ ያሉትን ዕድሎች በሙሉ ድርግም አድርጎ ዘግቶ ኖሮአል።

የወያኔ መሪዎችና ተሿሚዎች በየግላቸው ምንም ቁብ በማይሰጡትና ተቃዋሚዎች እንዲያከብሩት ነጋ ጠባ በሚወተውቱት የአገሪቱ ህገመንግሥት አንቀጽ 29 ዕውቅና ካገኙ የዜግች መብቶች አንዱ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ሆኖ ሳለ እየተካሄደ ያለውን የሥልጣን ብልግናና አገሪቱን እያራቆተ ያለውን ዘረፋ በመተቸታቸው ብቻ በአንድ ወቅት እንደ አሸን ፈልተው የነበሩ የነጻ ጋዜጣ አዘጋጆችና አሳታሚዎች በሽብርተኝነት ተወንጅለው ከፊሉ ከአገር እንዲሸሽ ሌላው አፉን ዘግቶ እንዲቀመጥ አለያም የፈጠራ ክስ እየተመሰረተባቸው እስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል። አሁንም በመደረግ ላይ ናቸው። በወያኔ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት አፈና የአሜሪካና የጀርመን መንግሥታት በየግላቸው የሚያስተዳድሩዋቸው የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮኖች እንኳ ከጥቃቱ ማምለጥ ስላልቻሉ እነሆ እስከዛሬ ያልተቋረጠ የማጥላላት ዘመቻ ይካሄድባቸዋል።

ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ከቻሉና ከየትኛውም መዲያ መረጃ የማግኘት መብታቸው ከተረጋገጠ ሥልጣን ላይ ውሎ እንደማያድር ጠንቅቆ የተረዳው የወያኔ አገዛዝ በዚህ የሚዲያ አፈና ተግባሩ በመቀጠል ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮን እንዲሁም ህዝብ አልፎ አልፎ ሃሳቡን ለመግለጽ በሚገለገልባቸው ጥቂት የአገር ውስጥ ህትመቶች ላይ የተለመደውን የጥቃት ጅራፉን ለማሳረፍ ታጥቆ ተነስቶአል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በመረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤቱ ተዘጋጅቶ የህወሃት ቀድሞ ታጋዳላዮች በሚቆጣጠሩትና እንደግል ንብረታቸው በሚፈነጩባቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የተሰራጨው ዘገባ እንደሚያመለክተው ከአሁን ቦኋላ ማንኛዉም የመንግስት ባለስልጣን፤ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምንም አይነት ቃለመጠይቅ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአል። ማስጠንቀቂያውን ተላልፎ በተገኘ ማንም ሰው ወይም ድርጅት ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትበትም ዛቻና ማስፈራሪያ በተለመደው የቃላት ጋጋታ ተገልጾአል።

ይህ ከሰሞኑ የወያኔ ብሄራዊ መረጃ ደህንነትና ኮሚኒኬሽን መስሪያቤት ያወጣዉ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች የሚናገሩትን ፤ የሚጽፉትን፤ የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ብቻ ሳይሆን የሚያስቡትንና ሊደግፉት ወይም ሊቃወሙት ይችላል ተብሎ የሚጠረጠረውን ሁሉ አስቀድሞ ለመቆጣጠር ፍላጎቱ ያለው መሆኑን ነው።

ከሰሞኑ መግለጫ የተለየ ነገር ቢኖር ህዝባችንን በፍርሃት አንገት ለማስደፋት ሲባል የወያኔ ፓርላማ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ንቅናቄያችንን ግንቦት 7ንና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንን በአንድነት የመፈረጅ ስልት ይፋ መደረግ መቻሉ ብቻ ነው።

የወያኔን ቁንጮዎች ጨምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይገነዘበዋል ብለን እንደምናምነው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት የተቋቋመው የአገራቸው ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ቅን ዜጎች ባዋጡት የገንዘብ መዋጮና በሚሰጡት ያልተቋረጠ የእውቀትና የፋይናንስ ድጋፍ ነው። ተቋሙ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 22 አመታት በወያኔ የሚዲያ ሞኖፖሊ ተይዞ የኖረውን የአገራችንን አየር ክልል ሰንጥቆ በመግባት ህዝባችን ስለ አገሩና ስለራሱ ጉዳይ በቂ መረጃ እንዲያገኝ በመጣር ላይ ያለ ብቸኛ መገናኛ ብዙሃን ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኝ ነው።

ሃቁ ይሄ ሆኖ ሳለ ለምንድነዉ ታዲያ ላለፉት ሁለት አመታት ስብሀት ነጋን ጨምሮ የተለያዩ የገዢዉ ፓርቲ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ሳይቀሩ በተደጋጋሚ ቀርበዉ በስነ ስርኣት የተስተናገዱበትን ይህንን ሚዲያ የወያኔ ፓርላማ ቀደም ሲል በአሸባሪነት ከፈረጀው ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ጋር መወንጀሉ ለምን ይሆን ? መልሱ ቀላል ነው። ከአገዛዙ ያልወገኑ ማናቸውም ሚዲያዎች እንደሚያደርጉት ኢሳት ስርጭቱን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነጋ ጠባ በኢትዮጵያ ቴለቪዥንና ሬዲዮ የሚደሰኮረው ልማትና ዕድገት ተጠቃሚው ሥልጣንን የሙጥኝ ያሉ የቀድሞ ታጋዳላዮችና የቅርብ ዘመዶቻቸው እንጂ ህብረተሰቡ አለመሆኑን በግልጽ ከማጋለጥ ባለመቆጠቡ ጥርስ ውስጥ ገብቶአል። ከዚህም በተጨማር ለምዕራባዊያን ፍጆታና ድጋፍ ማግኛ በየአምስት አመቱ የሚደረገው የምርጫ ተውኔት ወቅት ስለተቃረበ ተቃዋሚዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው በዚህ ሚዲያ ያብጠለጥሉኛል፤ የስልጣን ብልግናውንና የሙስናውን ጉዳይ ይዘከዝኩታል የሚል ፍርሃትና ስጋትም አለው። በእርግጥ ዝክዘካው በይስሙላ ምርጫው ላይ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እኛ የጉዳዩ ባለቤቶች ቀርተን ምዕራባዊያን ለጋሾችም አያጡትም። ሆኖም ግን ወያኔ ፈርቶአል ተረብሾአል። ስለዚህም ኢሳትና አሁን በአክራሪ ድርጅቶች ልሳንነት የተፈረጁት የአገር ውስጥ ህትመቶች ከምርጫው በፊት መጥፋት ይኖርባቸዋል። ያ ካልሆነ በመላው አገሪቱ የሰፈነው የሥልጣን ብልግናና የሃብት ዘረፋ የፈጠረው የኑሮ ውድነት ያስመረራቸው ሚሊዮኖች የመጪውን ምርጫ ውጤት አስታከው ሆ ብለው አደባባይ ሊወጡና የአገዛዙን የሥልጣን እድሜ ለማሳጠር ተቃዋሚዎች ለሚያካሄዱት ትግል መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተፈርቶአል። ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከብዙ የወያኔ ጥቃትና አፈና ተርፈው አገር ውስጥ በመታተም ላይ በሚገኙ 8 መጽሄቶች እና ለኢትዮጵያዊያን ብቸኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ ላይ የተጀመረውን አዲሱን ዘመቻ በቸልታ አይመለከተውም።

መረጃ ሃይል ነውና አገራችን ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ሥር እየሰደደ የመጣው ድህነት እንዲቀረፍና ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የሚሻ ዜጋ ሁሉ ወያኔ በሚዲያ ላይ የጀመረውን ጥቃት ለማስቆም ከጎናችን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል።

ወያኔ በመረጃና ደህንነት መሥሪያቤቱ አማካይነት ያስተላለፈው የሰሞኑ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ በተለይም በሰላማዊና ህጋዊ ትግል ወያኔን መቀየር ይቻላል በማለት አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች መተንፈሻ ለማሳጣት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ህዝባችን እንዲረዳና በህዝባዊ እምቢተኝነት ሴራውን ለማክሸፍ መነሳት ጊዜው ግድ የሚል የወቅቱ አንገብጋቢ የትግል ጥሪ መሆኑን ግንቦት 7 የፍትህና የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያስገነዝባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ::

ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል።

ጥር 8፣ 2006 ዓም በሁሉም የአማራ ክልል ወረዳዎች በተደረገው የብአዴን ስብሰባ ላይ ወጣቶች መረጃ በማስተላለፍ እና ለአሸባሪዎች መሳሪያ የሚሆኑ ሰዎችን በመመልመል ላይ በመሆናቸው የግንኙነት ሰንሰለቱን ለመበጠስ አባላቱና አመራሩ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው ተገልጾላቸዋል። እያንዳንዱ አባል በአሸባሪዎች ፕሮፓጋንዳ ሳይዘነጋ ጠንክሮ እንዲሰራም ትእዛዝ ተላልፎለታል።

“ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ወጣቶች ባላይ የአማራ ክልል ወጣቶች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ አለኝ” ያለው ኢህአዴግ በክልሉ እነዚህን ወጣቶች የመቆጣጠርና የመከታተል ዘመቻ በዘርፈ ብዙ ስልቶች ታጅቦ መካሄድ እንዳለበት አሳስቧል።

“በመሰረተ ቢስ አሉባልታዎች ከኢህአዴግ የኮበለሉና ወስጣቸው የሸፈተ የብአዴን አባላትም ሀቁን ተገንዝበው ከኢህአዴግ ጋር እንዲቀጥሉና ሀገሪቱን ወደ ላቀ እድገት እንዲያሸጋግሩ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊዎች በስብሰባው ላይ ተናግረዋል፡፡

የመወያያ አጀንዳዎች ትምህርትና የመኖሪያ ቤት ሊዝ ጉዳይ ቢሆኑም የስብሰባው ውሎ ግን ከአጀንዳዎች ውጭ አሸባሪዎች በሚሏቸው አካላት ላይ ነበር ያሉት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የድርጅት አባላት፣ መንግስት በመኖሪያ ቤት ሊዝ ያቀረበው ጉዳይ ግን ከፍተኛ ተቀዋውሞ አስነስቷል ብለዋል፡፡ ህጉ የማንንም ኢትዮጵያዊ ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ያላገናዘበ፣በአሰራር ውጣ ውረድ የተበተበና በዘፈቀደ እንዲወጣ የተደረገ ይመስላል ያሉት አባላቱ በተለይ የመንግስት ሠራተኞችን ከጨዋታ ውጭ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከብአዴን እየኮበለለ የሚጠፋውንና ለአሸባሪዎች መጠቀሚያ እየዋለ ነው ያሉትን ሃይል እንቅስቃሴ ለመግታት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአማራ ክልል የሚገኙ ወጣቶችና የብአዴን አባላት ” ብአዴን የህወሀት በቅሎ መሆኑ ያብቃ” በማለት ጥያቄዎችን እያነሱ ነው።

በክልሉ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና አፈና መባባስ አባላቱን ለተስፋ መቁረጥ መዳረጉንም ወጣቶች ይናገራሉ።

“መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ”

መቼም በኢትዮጲያ ብጥብጥና ሁከት የሚባለውን አባባል የማያቅ አለ ለማለት ያሰቸግራል። ምክንያቱም የመብትና የፍትህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር የህወሃት መንግስት “ ብጥብጥና ሁከት ሊያሰነሱ ሲሉ” ማለቱ የተለመደ ነው። ምንም አይነት መብትን የተመለክቱ ጥያቄዎች በድርጅት ወይም በግለሰብ በተነሱ ቁጥር “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ሲሉ ይባልና እስር ቤት ይወረወራሉ። እዚህጋ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ይታያል። በኢትዮጲያ መብት ማለት ምንድነው? አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የመብት ጥያቄዎቹን ለመንግስት እንዴት ነው ማቅረብ ያለበት? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ግን አንድ መራራ እውነት አለ እሱም መብት ማለት በኢትዮጲያ መንግስት መጥኖና ለክቶ ለራሱ በሚስማማ መልኩ ለማህበረሰቡ መብቶች ብሎ የተዋቸው ናቸው። መብት ሲባል በወያኔ ካድሬ አመለካከት ያው ሁሌ ንፅፅሩ ከዛ ከፈረደበት ደርግ ነው “በደርግ ጊዜ ሰአት እላፊ ነበር አሁን ግን የለም” ፣ “በደርግ ጊዜ ብሄራዊ ውትድርና ነበር አሁን ግን የለም” ስለዚህ ወያኔ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንባላለን።
ብጥብጥና ሁከት ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ነገር ግን በአሁኑ ሰኣት በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙት ወጣቶች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ነው እንጂ በጥብጠው እንዳልሆን ለማንም ግልፅ ነው። ደሞ ሌሎች አባባሎች አሉ “የተወሰኑ” ፣ “አንዳንድ” የሚባሉ ለምሳሌ ባለፈው ምስኪኖቹ የኢትዮጲያ መምህራን ደሞዝን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋነት የተሞላው የመብት ጥያቄ ሟቹ አቶ መለስ “አንዳንድ ብቃት ያነሳቸው መምህራን ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ሲሉ” ብለው በአነስተኛ ገቢ በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩትን ምስኪን የኢትዮጲያ መምህራን በሃዘን አንገታቸውን አስደፏቸው። እብሪት ከተሞላው ስድብና ማስፈራሪያ ውጪ ላነሱት ጥያቄ በአግባቡ እንኳን ማብራሪያ አልተሰጣቸውም።
የኢትዮጲያ ሙስሊም ማህበረሰብም ከህፃን እስከ ሽማግሌ እምነታቸውን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋ የመብት ጥያቄ “አንዳንድ ብጥብጥና ሁከት ፈጣሪዎች” እየተባለ ይዘገባል። ባለፈው የብራዚል ማህበረሰብ ላነሳው የመብት ጥያቄ ፕሬዝዳንቷ ዲልማ ሩሴፍ የተናገሩት ንግግር እጅግ ያስቀናል “መብታችሁን ለማስከበር በመነሳታቹ ኮራሁባቹ” ነበር ያሏቸው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው በወያኔ አገዛዝ ይህንን በፍፁም አንሰማም። ለምን? የኢትዮጲያ ህዝብ በጥባጭ ስለሆነ? ወይም መንግስትን አጉል ጥያቄ ስለሚጠይቅ? አይደለም። ህወሃት ራሱ የሰራውና እየሰራ ያለው ኢሰባዊ የሆን ግፍና የመብት ረገጣ ስለሚያስበረግገው ሰው ሲሰብሰብ አይወድም። እጅግ በሚያስገርም መልኩ በቅርቡ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጲያዊያን ላይ ያደረሰውን አስከፊ ግፍና የመብት ረገጣ ለመቃወም የወጣውን ህዝብ እንኳን “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ተብሎ እየተደበደቡ ተበተኑ። ኧረ ሌላም ብዙ አይተናል።
ነፃና ዲሞክራሲያዊ መንግስትማ የህዝቡን የመብት ጥያቄ እንዴት እንደሚመልስ እናያለን። እንደውም የኢትዮጲያ ህዝብ ሲበዛ የዋህ ነው ባለፈው ውጥንቅጡ በወጣውና መላቅጡ በጠፋው የኢትዮጲያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የተነሳ ተሰደው በሳውዲ ሲሰቃዩ ቆይተው ወደሃገራቸው ከተመለሱት ስደተኞችጋ አንድ ሁለት ፎቶ ስለተነሱ ብቻ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የሚያደንቁም ተነስተው ነበር። ምን ስላደረጉ? ምንም። እንደው ህዝባችን ትንሽ ሲያረጉለት ወዲያው ለምስጋና አንገቱን ስለሚያጎነብስ ነው እንጂ። ይህን የመሰለ የዋህ ምስኪን ህዝብ በዘርፈብዙ ችግር ሲሰቃይ ማየት እጅግ ያበሳጫል።
ለምሳሌ የመብት ጥያቄ ማንሳት “ብጥብጥ” መባሉ ቀርቶ ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ ተፈቀደ እንበልና ምስኪኑ የኢትዮጲያ ህዝብም “ኧረ ተው ከዚህ ሀገር ንቀለኝ” እያለ አማልክትን ከማስቸገር መብቱን ለማስከበር ቢነሳ ምን ያህሉ የሃገራችን ህዝብ የመብት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሁላችንም መገመት አያቅተንም።
አንዳንዴ ሳስበው መንግስት ዝም ሲባል የተወደደ ይመስለዋል መሰለኝ ምናልባትም አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ቦታ የሚሰሩ ካድሬዎች የህዝቡን ሮሮ ትተው “ህዝቡ ለመንግስት ፍቅር አለው” ብለው ሪፖርት ስለሚያቀርቡ ይሆናል። እውነታው ቢገለፅ ግን ሪፖርታቸው የሚሆነው “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ” ነበር።
ታስታውሱ እንደሆን አቶ መለስ “ይህ ማዕበል” ብለው አለወትሮአቸው ድምፃቸውን ሞቅ አርገው የተናገሩት መንግስታቸው የተወደደ መስሏቸው ነበር ወዲያው በነጋታው መልሱን አገኙት እንጂ። ግን እንዴት እንደዛ አሰቡ? በትክክል ቁጥሩን የማያውቁትን ህዝብ ፣ መንግስት በስርአቱ መዝግቦ ያልያዘውን ህዝብ ፣ በኑሮ ውድነት ፣ በነፃነት እጦት እያሰቃዩት ያለውን ህዝብ እንዴት ይወደኛል ብለው አሰቡ። ያስገርማል።
ወደዋናው ሃሳቤ ስመለስ ማንኛውም የሰው ልጅ መብቱን መጠየቅ ማስከበር አለበት ማንኛውም ኢትዮጲያዊም እንድዚሁ። ይህን ስል ግን የግድ መስቀል አደባባይ መሰብሰብ ላይቻል ይችላል ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚኖርበት ፣ በሚሰራበት ፣ በሚማርበት ፣ አገልግሎት በሚያገኝበት ቦታ መብቱን ማስከበር አለበት። ባገኘው አጋጣሚ እምቢ ማለት አለበት።
ናትናኤል ካብቲመር ኦስሎ ኖርዌይ 5 ጥር 2006

በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታር መሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችን ጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስት ብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎ መታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉ አስረድተዋል።

በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራር መሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።

የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብ ባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ም መጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።

በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉ ይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎች ወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብም ስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታ አቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።
ሰንደቅ ጋዜጣ

የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸው ያታወሳል።

ኦዴፍም በኢትዮጵያ አንድነት እንደሚያምን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮዮጵያዉያን ሁሉ እንቆማለን የሚል አቋም ፣ ድርጅቱ በተመሰረተ ሰሞን በስፋት ሲያንጸባርቅ ነበር። እንደዉም በፓልቶክ በተደረጉ ዉይይቶች፣ የኦዴፉ አቶ ሌንጮ ባቲ፣ «ካስፈለገም፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተነጋግረን፣ ኦሮሞ ከማለት ኢትዮጵያ የሚል ስም ለመያዝን እንሞክራለን » እንዳሉም የሚረሳ አይደለም።

ሰሞኑን ኦዴፍ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በመጪው ምርጫ ሊወዳደር እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች በስፋት እየተነገሩ ነዉ። የኦዴፍ ሊቀመንበር ፣ ነዋሪነታቸዉ በኖርዌይ የሆኑት፣ አቶ ሌንጮ ለታ (ሌንጮ ባቲ አይደለም) «ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ሊገባ ነዉ» በተባለውና በሌሎሽ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በጀርመን ድምጽ ራዲዮ ቀርበዉ በአማርኛ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ሌንጮ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉ በዘር ላይ የተመሰረተዉ ፌደራል አወቃቀር መቀጠል እንዳለበት አጠንክረዉ ይናገራሉ። «ችግሩ በአፈጻጸሙ ላይ እንጂ በፌደራል አወቃቀሩ ችግር የለም » ያሉት አቶ ሌንጮ፣ ኦዴፍ በተመሰረተ ጊዜ በፌደራላዚም ዙሪያ ፣ ኦዴፍን ወክለው ዶር በያን አሴቦ፣ በፓልቶክ፣ ከሰጡት አስተያየት ጋር ይቃረናሉ። በወቅቱ ዶር በያን፣ «አንዴ ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ መንግስት በተቀየረ ጊዜ የማይለወጥ፣ ሁሉም የሚስማሙበት አዲስ ፌደራል አወቃቀር እንዲኖር ነው ኦዴፍ የሚፈልገው» የሚል አስተያየት ነበር የሰጡት።

የአቶ ሌንጮ በፌደራል አወቃቀሩ ዙሪያ በጀርመን ድምጽ የተናገሩትን ያዳመጡ፣ ኦዴፍ በፖለቲካ አቋሙ ፣ ከኦህዴድ ጋር በጣም የሚቀራረብ እንደሆነ በመግለጽ ኦዴፍ በአገር በት ገብቶ ምን የተለየ ነገር ሊያመጣ እንደሚችል ይጠይቃሉ።
የአገሪቷ ችግሮች በሰላምና በዉይይት እንዲዲፈታ ድርጅታቸው ፍላጎት እንዳለዉ አክለው የገለጹት አቶ ሌንጮ « እኔ እዚህ ኖርዌይ ተቀምጬ ምን አደርጋለሁ ? ሕዝቡ ጋር ሆን ካልታገልን በዉጭ ሆነ የምናደርገዉ ምንም ነገር የለም» ሲሉ ከሕዝብ ርቆ በዉጭ የሚደረግ ትግል ዋጋቢስ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል። ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ፣ አገር ዉስጥ ገብተዉ፣ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት አቶ ሌንጮ፣ በዚያ ዙሪይ ከኢሕአዴግ ጋርም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመወያየት ድርጅታቸው ዝግጁ እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ ዙሪያ፣ ከኦዴፍ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ ምሁር፣ ኦዴፍ ከጅምሩ አገር ዉስጥ ገብቶ በሰላም ለመታገል ፍላጎት እንዳለው ሚስጠር እንዳልሆነ ካስረዱ በኋላ፣ ኦዴፍ ለመደራደር ጥያቄ ያቀረበዉ፣ ኢሕአዴግ ለምርጫ የሚያስፈልጉ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንዲያስተካክልና ለፍትሃዊ ምርጫ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች መሆኑን ይገልጻሉ። «በኦዴፍ ዘንድ ኢትዮጵያ የመግባትና ለምርጫ የመወዳደር ዉሳኔ በፍጹም የለም» ያሉት እኝሁ ምሁር ኦዴፍ አገር ቤት ሊገባ ነዉ ተብሎ የሚዘገበዉን «ከእዉነት የራቀ» ብለዉታል።

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ፣ ኦዴፍ ኢትዮጵያ የመግባት ፍላጎትና አላማ እንዳለው እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሆነ አያመላከትም።

በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።

የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን በርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳዩን በተመለከተ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መረጃ እንደሌለው ገልፀዋል። ነገር ግን በግል በሁመራ ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃውን ለማጣራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በሁመራ የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰብ ነዋሪዎች “መሬቱ ለሱዳን ይሰጣል” ተብሎ እየተወራ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል። በተጨማሪም የአካባቢው ባለስልጣናትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውንም የሚገልፁት አቶ አብርሃ ባለስልጣናቱም “የምናውቀው ነገር የለም” እንዷላቸውም ነው የገለፁት።

ፓርቲው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እያጣራ መሆኑን የገለፁት አቶ አብርሃ፤ ከስርዓቱ ባህሪ በመነሳት በድንበር ማካለሉ ላይ እምነት መያዙ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። “ሥርዓቱ ለስልጣን ብሎ እንጂ የሀገር ድንበር ለመጠበቅ አይደለም። ከዚህ ጉዳይ ተነስቶ የኤርትራን ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የሱዳንም ጉዳይ ሊያጠራጥር ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ያለው ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አለን። ሥርዓቱ ዳርድንበር ከመጠበቅ ባለፈ፤ የውጪ ኃይሎችም ጋር ቢሆን በስልጣን የሚቆይበትን መንገድ ሊያፈላልግ ይችላል” በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል።

የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ በመደገፉ በምትኩ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ተሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬም በተመለከተ አቶ አብርሃ ሲመልሱ፤ “የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩ ነው። ነገር ግን የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ ቢደግፈውም፣ ባይደግፈውም የእኛ ግድብ ነው። የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩና የምንፈልገው ቢሆንም፤ ስለደገፈ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ሊኖር አይገባም። ከአባት፣ አያቶቻችን የተረከብነው መሬት ለሌላ አካል ሊሰጥ አይገባም። ድርጊቱ ተፈፅሞ ከሆነ እንታገለዋለን” ሲሉ መልሰዋል።

“መንግስት በጉዳዩ ላይ ግልፅ መሆን አለበት” የሚሉት አቶ አብርሃ፤ በጉዳዩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግልፅ መደረግ አለበት ብለዋል። ድንበሩ ሲካለልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።

“የድንበር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ኢህአዴግ በመንግስትነቱ ሳይሆን በፓርቲነቱ ስለሚሰራ ጥርጣሬ አለን” የሚሉት አቶ አብርሃ ስለሆነም ለጉዳዩ ማረጋገጫ የሚሆን ግልፅ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ቀጠናው የተረጋጋ ባለመሆኑ የድንበር መካለል እንደሌለበት የጠቀሱት አቶ አብርሃ የድንበር ማካለሉ ሂደት ተጀምሮም ከሆነ መቆም አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች መረጋጋት በሌለበት በድብብቆሽ ወደ ድንበር መካከል መገባት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ታደሰም እንደ አቶ አብርሃ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ነገር ግን መንግስት በውጪ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ጠንከር ያለና ኢትዮጵያውያንን ለሚጠቅም ተግባር ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የድንበር ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንደመሆኑ ግልፅ አሰራርን መከተል አለበት ብለዋል። ከመንግስት ባለፈ ሚዲያውም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

አቶ ጫኔ በመንግስት በኩል የሀገር ድንበርን በተመለከተ የመድበስበስ አካሄድ መኖር የራሱ አደጋ እንዳለው ይገልፃሉ። ፓርቲያቸውም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያሳስበው እንደሆነና በጉዳዩም ላይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት እየጣረ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ፓርቲም በአካባቢው ከሚገኙ አባሎቹም መረጃ የማሰባሰብ ስራም እያከናወነ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ልዩነት እንዳለውም ጠቅሰዋል። ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘም ያሉ ችግሮች የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ችግሮች የሚመነጭ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም በመንግስት በኩል የኢትዮ ሱዳንን ድንበር ማካለል ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጎዳ መልኩ የሚፈፀም ከሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመን የማጋለጥና የመቃወም ስራ እንሰራለን ብለዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ አቋም መወሰዱን ይናገራሉ። ፓርቲው የወሰደው አቋም፤ ጉዳዩን የማጋለጥና ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡ ጀርባ ሆኖ ድንበር የማካለል ስራ እየተሰራ በመሆኑ እንቃወመዋለን። ጉዳዩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውቀው አይመስለንም። ምን ያህል መሬት ለሱዳን ይሰጣል? ለምንስ ይሰጣል? ታሪካዊ ባለቤትነቱ የማነው? የሚለው መታየት አለበት የሚሉት አቶ ስለሺ፤ ድንበሩን በድብብቆሽ የማካለሉ ተግባር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ፓርቲው ከልዩ ልዩ ምሁራንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሰዎች እንደተረዳው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ባለፉት ሰርዓቶች ቢነሳም ጉዳዩ ሳያስተናግዱት መቆየታቸውን አስታውሰው ኢህአዴግ ግን መነሻው ግልፅ ባልሆነ መንገድ የድንበር ማካለል ጥያቄውን አሁን ማንሳቱን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ኢህአዴግ በሱዳን ድንበር አሸባሪ የሚላቸው ወገኖች ተደራጅተው እንዳይመጡበት ገዢ መሬት ለማሳጣት ድንበሩን ለድርድር አቅርቦ እንደሚሆንም እንገምታለን ብለዋል።

ፓርቲውም ይሄንኑ ጉዳይ እንደ አጀንዳ በመያዝ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ከፓናል ውይይቱ በሚነሳው ኀሳብ ደግሞ ሕዝቡ አቋም እንዲይዝና እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ወደ አካባቢው በማቅናት በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።

“በአሁኑ ወቅት መሬቱ በእርግጥም ለሱዳን አልተሰጠም” ያሉት አቶ ስለሺ፤ ሆኖም ግን በድንበር ማካለሉ ላይ ድርድር ተካሂዶ በወረቀት ደረጃ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም በኀሳብ ደረጃ ተስማምቶ በመጪው መጋቢት የመሬት ርክክብ እንደሚፈፀም የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሆነም ተናግረዋል።

“ጉዳዩን እየደበቀው ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው” የሚሉት አቶ ስለሺ፤ “ነገሩ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነው” ብለውታል። የድንበር ማካለል ጉዳይ የሉአላዊነት በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሊፈፀም አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል። ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ሉአላዊነት ደንታቢስ በመሆኑም የድንበር ማካለሉን ለስልጣኑ ብሎ ከመፈፀም ወደኋላ አይልም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ፓርቲያቸው ሕዝቡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ከማድረግ ባለፈ ኢህአዴግ በድርድር የተስማማባቸው ስምምነቶች በመጪው ትውልድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ነው ጨምረው የገለፁት።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪም እንደሌሎቹ የፓርቲ አመራሮች ጉዳይ የሚያሳስበው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል። አጣሪ ቡድኑ በሚያመጣው መረጃ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ መኢአድ እንደ ፓርቲ ድንበሩ በቅድመ አያቶቻችን አባቶቻችን የተካለለ በመሆኑ እንደገና መከለል የለበትም የሚል አቋም እንዳለው ገልፀዋል። የፓርቲው አቋም የአከላለል ሂደቱ ግልፅ ይሁን አይሁን ከማለት ባለፈ ድንበሩ እንደገና መከለል አይገባውም የሚል እንደሆነ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ድንበር ማካለል ቀደም ሲል በነበሩ ስርዓቶች ሳይነሳ አሁን የተነሳበት ምክንያት የአማራውን ብሔር በመልከአምድር እና በቁጥር ለማሳነስ የሚደረግ ሴራ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ሁሉ ሊቃወመው ይገባል ብለዋል።

በመንግስት በኩል የድንበር ማካለሉን ሂደት ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ በተለይ ጎንደር አካባቢ ሱዳኖች ይገባናል ስለሚሉት መሬት ግልፅ አቋም መያዝ አለበት የሚሉት አቶ አበባው፤ “ሕዝቡ ድምፁ ሊሰማና የታሪክ አዋቂዎችና አባቶች በጉዳዩ ሊጠየቁ ይገባል። ሽፍንፍን ባለ ሁኔታ ድንበር ማካለል ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ ለሱዳንም ሆነ ለኢህአዴግ አይጠቅምም” ሲሉ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን አድርጎ እና እያደረገ ከሆነም እንደገና ነገሩን እንዲያጤነው” ሲሉ አሳስበዋል።

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው የፓርቲው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እየተወያየባቸው ካሉ ሦስት አስቸኳይ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማከለል ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የላላ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጐዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱ አሁንም በዚህ ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ከዚህ በፊትም የሀገሪቱን ታሪካዊ ባለቤትነት በጣሰ መንገድ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መደረጓን አቶ ሀብታሙ አስታውሰዋል። አሁንም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም ስለሚችል ከፍተኛ ሰጋት አድሮብናል ብለዋል።

“በሱዳን በኩል እየተጠየቀ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ነው” የሚሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይሄንን ሉአላዊ ግዛት ለሱዳን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ እንደገና ከተደራደረበት ከሕዝብ ጋር በመሆን የምንታገለው ነው ብለዋል።

እስካሁን በመንግስት በኩል ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲያቸው ደጋግሞ እያሳሰበ መሆኑን የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ የድርድሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ለህዝቡ ግልፅ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

“ከዚህ በፊት ከ60ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የረገፉበት የባድመ ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። የአሰብ ወደብን በተመለከተም ኢህአዴግ ቸልተኛ አቋም በመከተሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ጎድቷል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ አሁንም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል በተመለከተ ኢህአዴግን እንድንጠራጠረው አድርጎናል ብለዋል።

ኢህአዴግ በተፈጥሮአዊ ባህሪውን እና ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚመነጭ አስተሳሰብ መረዳት እንደሚቻለው ግንባሩ በሉአላዊነት ላይ የተዛባ አቋም ያለው በመሆኑ አሁንም የሀገሪቱን ሉአላዊነት በመጠበቅ ላይ ስጋት አለን ሲሉ አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።

“ሀገር ማለት ሕዝብ ነው ነው ብለው ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 60 ሺህ ሰው አስጨርሰዋል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግና የአባይን ግድብ መደገፉን ተከትሎ መሬት ቆርጦ ለመስጠት ከታሰበ ተገቢም፣ ትክክል አይደለም ብለዋል። ድንበር እየሰጡ ግድብ መገደብ ሰጥቶ መቀበል አይደለም በማለት ተቃውመውታል። ግድብ መገደብ የሀገሪቱ መብት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።

በዚሁ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ለማነጋገር ጥረት አድርገናል። ነገር ግን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦፊሴላዊ ጉብኝት ጋር በተያያዘ ስራ ስለበዛባቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በተመሳሳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች በኩልም መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። በመስሪያ ቤቱ አሰራር በቃል አቀባዩ በኩል መረጃ ስለሚሰጥ ሊሳካልን አልቻለም።

በተጨማሪም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ቴሌፎናቸው ስለማይሰራ ልናገኛቸው አልቻልንም። በጠቅላይ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋውን አነጋግረን አቶ ሽመልስን ወይም አምባሳደር ዲናን ብቻ ማነጋገር እንደምንችል ገልፀውልናል። በቀጣይ ሳምንት የመንግሥትን ምላሽ ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡

ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡

ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሆነው ህወሃት በሀገራችን ሰላምና ፍትህ፣ ልማትና እድገት እየመጣ ነው እያለ የተረጋጋ መሆኑን በማስመሰል በየጊዜው ይናገራል። ነገርግን የሀገሪቱን ገንዘብ በተዘዋዋሪ በውጪ በሚኖሩ የስርአቱ አግልጋዮች ስም የቦታና የንግድ ግዢ በውጪ ሀገር የማድረግ ስራ በሰፊው እየተፋፈመ መሆኑን የውስጥ ዜና ምንጮቻችን ገልፀዋል።

በተለይም በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች በጉብኝት ስም ታማኝ ሰዎችን በመላክ የሀገሪቱን ገንዘብ በማሸሽ ቦታና የንግድ ማእከሎችን እንዲገዙ እየተደረገ ነው። ህወሃት ራሱ ያልተረጋጋ እና አደጋ ያንጃበበት በመሆኑ ውስጣቸው መረጋጋት እንደሌለበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ታዲያ ይህንን ፍርሃት በመሸፈን በበላይነት የህወሃት ኤፈርት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን ገንዘብ የማሸሽን ዘዴ እንደ አንድ አማራጪ ወስደው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለማሸሽ እየተዘጋጁ ነው ሲል መረጃውን የላከልን ዘጋቢያችን አስታውቋል። በቅርቡ ከሁለት ወር በፊት የኤፈርት ልኡክ ቡድን ወደ አሜሪካ ተልእኮ እንደነበርም አስረድቷል። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የህወሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው ሲል የግንቦት 7 ሬዲዮ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል። (አባይ ሚዲያ)

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ሀገራትን የወከሉት የህብረቱ ዲፕሎማቶች አሁን ስለሳለው አጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ፣አንድነት እንደ ፓርቲ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፓርቲው ፕሬዝደንት በፕሮጀክተር የታገዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድነት ከግንኙነት ስትራቴጂ አንፃር በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ማለትም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራና ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት የተብራራ ምላሽ ተሰጥቷቻዋል፡፡

ኢንጅነት ግዛቸው አንድነት በሚመለከት ባቀረቡት ገለፃ የፓርቲውን ርዕይ፣ተልዕኮና አላማ በሰፊው አብራርተዋል፡፡በመቀጠልም ስለአንድነት ፖሊሲዎችና መርሆዎች ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የአንድነት ፓርቲን ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከት ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትም የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት አመታት አንዳችም አይነት የለውጥ አዝማሚያ እንዳላሳየ ይልቁኑም ተቋማዊ የአፈና ስርአትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳቱ ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት የተዘፈቀበትን ሙስና ግዝፈት የዘረዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፀረሽብር ህጉ ከመንግስት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለማጥቃት የተቀመጠ መሆኑን በአንድነት አመራሮችና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ላይ የደረሰውን እስርና እንግልት በማሳያነት አስረድተዋል፡፡ አንድነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና በበርካታ ሀገራትም የተቋቋሙ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች እንዳሉጠቁመዋል፡፡

ወደፊትም በተጠናከረ ደረጃ በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን መንገድ እንደተቀየሰና የዲያስፖራው አባላትን በአባልነትና በድጋፍሰጪነት በንቃት ለማሳተፍ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ጋር የተገኙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ አያሌውና የውጪ ግንኙነት ሀላፊው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠታቸውም ታውቋል::

የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ «ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል» ብለዋል። «የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው» በማለት አቶ በረከት ገለጽዋል።

አቶ በረከት አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመተካቱ በፊት ፣ ግንባሩ ለ3 ተከፍሎ እንደነበር ገልጸዋል። አንደኛው የአመራር ወገን «ችግራችን የውስጥ ነው እና በቅድሚያ የውስጥ ችግራችንን እንፈትሽ የሚል» አቋም ሲይዝ ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ዋናው ችግራችን ሻዕቢያ በመሆኑ በቅድሚያ ሻዕቢያን እንውጋ የሚል አቋም ይዞ እንደነበር፣ እና ሻእቢያን ከወጋን በኋላ ወደ ውስጥ ችግራችን እንመልከት የሚለው ሶስተኛው አማራጭ አሸንፎ መውጣቱን ገልጸዋል። «በ1997 ዓ.ም ዋናው የአመጽ ሀይል የነበረው ስራ ያጣውና ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው» በማለት የገለጹት አቶ በረከት ለወጣቱ ስራ ካልተፈጠረለት በመንግስት እና በአገር ላይ እንደሚያምጽ ገልጸዋል። መንግስት የምርጫ 97ትን አመጽ ያስነሱት ተቃዋሚዎች ናቸው ብሎ ሲከስ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢህአዴግ ከባለሀብቱ ነጻ የሆነ መንግስት ለመመስረት መነሳቱን የገለጹት አቶ በረከት፣ ስልጣን ላይ የሚያመጣን አርሶአደሩና በከተማ ያለው ጭቁኑ ህዝብ ነው እንጅ ባለሀብቱ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በባለሀብቱ ገንዘብ የሚተዳደር አይደለም ያሉት አቶ በረከት፣ ገንዘብ ከፈለገ ከባላሀብቱ በግብር መልክ መውሰድ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ መንግስት ለህልውናው የራሱ የገቢ ምንጭ እንዳሉት የጠቀሱት አቶ በረከት፣ አየር መንገድን ባንኮችን እና መብራት ሀይልን በምሳሌነት አንስተዋል። የመንግስትን አስተዳደር ያለምንም ችግር ለማስኬድ የባለሀብቱም የውጭ ድጋፍም እንደማያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል።

አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ ምርጫውን ያለባለሀብቶች ድጋፍ ማሸነፍ እንደሚችል እየገለጹ ባለበት ጊዜ በድንገት የመንግስት ተቋሞችን በመግለጽ በቂ ገንዘብ አለን ማለታቸው ተሰብሳቢዎችን ማስገረሙን ስብሰባውን የተከታተሉት አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራር ገልጸዋል። አመራሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለምርጫ ማስኬጃ ከመንግስት ገንዘብ እንደሚወሰድ የአቶ በረከት ንግግር በቂ ማሳያ ነው ።

መንግስት የራሱ ገንዘብ ከሌለው እንደምእራብ የአፍሪካ አገራት ይሆናል ያሉት አቶ በረከት፣ የኮትዲቩዋር ሚኒስትሮች ደሞዛቸውን የሚወስዱት ኮትዲቯር ከሚገኘው የፈረንሳይ ኢምባሲ ነው ይላሉ። በኬንያም ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን አቶ በረከት አክለዋል ኢህአዴግ በ2002 በተደረገው ምርጫ ከግል ባለሀብቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወቃል። በባቡር ግንባታ፣ በመንገድ ቁፋሮና በትራንሰፖርትና እጥረት የተነሳ በአዲስ አበባ መኖር ያስጠላል ያሉት አቶ በረከት ያም ቢሆን ግን ህዝቡ ልማት ነው በሚል እንደሚቀበለው ገልጸዋል።ኢሳት ዜና

መንግስት የግል መጽሄቶች የህትመት ቁጥር መጨመር ስጋት ላይ እንደጣለው ታወቀ::

መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአሁኑ ወቅት በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ስር በአንድ መመሪያነት የሚሰራውና በአዋጅ በፈረሰ ስም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እየተባለ የሚጠራው ድርጅቶች በጋራ አጥንተናል ባሉትና ሰባት ያህል መጽሄቶች ሕግና ስርዓትን በመተላለፍ እየሰሩ መሆኑን የሚያውጀው ጥናት መነሻ የመጽሄቶቹ ቁጥር መጨመር ገዢውን ፓርቲ ስጋት ላይ በመጣሉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደጠቆሙት በጽንፈኝነት ከተፈረጁት ሰባቱ መጽሔቶች ማለትም ሎሚ፣ፋክት፣አዲስጉዳይ፣ዕንቁ፣ቆንጆ፣ሊያ እና ጃኖ መጽሔቶች መካከል አብዛኛዎቹ ሳምንታዊ የህትመታቸው መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣትና የሚጽፉአቸውም ርዕሰ ጉዳዮችም ገዥውን ፓርቲ አጠንክረው የሚተቹ መሆን በተለይ ከመጪው ዓመት አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግን ስጋት ላይ ጥለውታል፡፡

መጽሄቶቹ ለጥናት ሲመረጡ ቀድሞውኑ ውጤቱ ይታወቅ ነበር ያሉት ምንጮቹ ፣ በጥናቱ ተገኘ የተባለው ውጤት ባለስልጣናቱ በየጊዜው ሲሉት የነበረና በአዲስዘመን ጋዜጣ አጀንዳ ኣምድ ላይ በተከታታይ ሲጻፉ የነበሩ ትችቶች ናቸው ብለዋል፡፡ መንግስታዊ ተቋማቱ የጀመሩት ጥናት ገና አለመጠናቀቁንና ከጅምሩ ተቆንጥሮ እንዲለቀቅ የተደረገው በሁዋላ መንግስት ለሚወስደው እርምጃ ከወዲሁ ህጋዊነትን ለማላበስ ታስቦ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ጥናቱ ገና ሳይጠናቀቅና ድምዳሜው ሳይታወቅ ውጤቱ ይፋ መደረጉም መንግስት ሚዲዎቹን ለመወንጀል የቱን ያህል እንደቋመጠ የሚያሳይ ነውም በማለት አክለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በአዲስዘመን ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ የታተመው ዘገባ እንደሚሳየው ሰባቱ መጽሔቶች ከመስከረም እስከ ህዳር 30/2006 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ባወጡዋቸው ዘገባዎች የጽንፈኛ ድርጅቶች ልሳናት መሆናቸውን፣ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ፣ሽብርተኝነትን እንደሚያበረታቱ፣የተሳሳቱ መረጃዎች ሕዝቡ በስርዓቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ እንደሚደርጉ በጥናት ደርሰንበታል መባሉና ኢሳትም ይህንኑ በዕለቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የብሮድካስት ባለስልጣን በታህሳስ ወር 2006 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፋክት መጽሔት በወር 62 ሺ ኮፒ በማሳተም የሚመራ ሲሆን ሎሚ 55ሺ፣ አዲስጉዳይ 51 ሺ ኮፒዎችን በማሳተም ይከተላሉ፡፡ ቆንጆ 7ሺ፣ ዕንቁ 6ሺ 400፣ጃኖ 4ሺ ሲያሳትሙ ሊያ የተባለችው መጽሔት በታህሳስ ወር ምን ያህል ኮፒ እንደታተመች ባለስልጣኑ በመረጃው አላካተተም፡፡
ምንም አይነት ግሳጼ ካልደረሰባቸው ሳምንታዊ ጋዜጦች መካከል ሪፖርተር የእሁድ እትሙ 11 ሺ፣ ፣ አዲስ አድማስ 8 ሺ 700፣ ሰንደቅ 1 ሺ 933፣ ኢትዮ ቻናል፣ 1 ሺ 737 ያሳትማሉ። ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

የመከላከያ መኮንኖች በአ.አ ፖሊስ ተመደቡ::
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ::
በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ ::

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስሩ ክፍለ ከተሞች የመከላከያ መኮንኖች ተዛውረው መመደባቸውን ታማኝ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባላት የሆኑትና ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ደረጃ ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በአስሩም ክፍለ ከቶሞች የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች “ኮሚኒቲ ፖሊስ” በሚል አዳዲስ የፌደራል ፖሊሶች እንደመተደቡ ምንጮቹ አያይዘው ገለፀዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ሃይል እምነት ያጣው ገዢው ፓርቲ ሕወሐት/ኢህአዴግ ታማኝ በሚላቸው መኮንኖችና የፌደራል ፖሊሶች እየተካና አፈናውን እያጠናከረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም አሁን በተጀመረው የክልሉን ፖሊስ የማፍረስ ተግባር በቅርብ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።

ገዢው ፓርቲ ራሱ በደነገገው ሕገ-መንግስት ላይ ፖሊስ ፀጥታውን እንደሚቆጣጠር እንዲሁም መከላከያ ገለልተኛ ሆኖ የአገሩን ሉአላዊነት እንደሚጠብቅና ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሆኖ እንደሚቆም አዋጁ የሚገልፅ ቢሆንም ነገር ግን ራሱ ላወጣው ሕገ መንግስት ተገዢ መሆን እንዳልቻለ የሕወሐት መኮንኖች ከመከላከያ ተዛውረው የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ መመደባቸው የህግ ጥሰት እያካሄደ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው ብለዋል ምንጮቹ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች አጋልጠዋል። በአዲስ አበባ የካና አራዳ ክፍለ ከተሞች “ኬርና ፕላን” በተባሉ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተሰሩት ጤና ጣቢያዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀይረው እስረኞች እየታሰሩባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06/07 ቤላ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ቀበሌ 11 እንዲሁም ጃንሜዳ ቀበሌ 05 የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በከፊል እንደሚጠቀሱ ያስታወቁት ምንጮቹ በተጠቀሱት ቦታዎች እስረኞች በብዛት ታስረው እንደሚገኙ አያይዘው ገልፀዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ኣስታወቀ። ‪የግንባሩ ፕሬዝደንት አቶ ሌንጮ ለታ እንደገለጹት ግንባሩ ከምስረታው ኣንስቶ ወደ ኣገር ቤት ለመመለስ ግልጽ አቐም ይዟል። ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ ኣለኝ የሚለው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው ኣገራዊ ኣንድነትን ለመመስረት እንደሚሰራም ኣስታውቐል። «ኦ ዲ ኤፍ» በይፋ ከተመሰረተ ገና ኣንድ ዓመቱ ሲሆን ፕሬዝደንቱ አቶ ሌንጮ ለታ ለረጅም ጊዜ የዓማጺው ኦሮሞ ነጻነት ግንብር ከፍተኛ ዓመራር አባል እንደነበሩ ኣይዘነጋም።

object Podcast

Image

«በሕገ መንግስቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም።ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገዉ ስርዓቱን ወይንም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም ፣ ነገም ፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነዉ።»ኢቲቪ በቅርቡ በ«ሽብርተኝነት» ላይ፣ በቅርቡ ባቀረበዉ አሳዛኝ ዶኩሜንተሪ ላይ ፣ የፌደራል መንግስት አቃቤ ሕግ፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ የተናገሩት ነበር።

እኝህ የሕግ ባለሞያ እየደጋገሙ ሕግን ስለማክበርና ስለ ሕገ መንግስቱ ነግረዉናል። ስለሕገ መንግስት ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ጣል ላድርግ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 4 «በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይንም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል» የሚል ድንጋጌ ያካትታል። ኢቲቪ በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደር እንደመሆኑ ይህ የሕገ መንግስት አንቀጽ ይመለከተዋል። ነገር ግን ኢቲቪ በቀጥታ፣ ሕግ መንግስቱን ሲንድ፣ ገለልተኛነት በጎደለው መልኩ የአንድ ድርጅትን የፖለቲክ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ሲሆን ነው እያየን ያለነዉ። እነ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ኢቲቪ የአንድ ወገንን አቋም የያዘ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያዥጎደጉድ፣ ቢያንስ ቢያንስ ጥቂት ሰኮንዶች፣ የአንዷለምን ጠበቃዎች፣ ወይንም ቤተሰብ፣ አሊያም የትግል አጋሮቹ የሆኑት የአንድነት አመራር አባላትን ለማነጋገር አልተሞከረም። እንግዲህ ከዚህ የምንረዳዉ፣ ሕግን በማክበር አኳያ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎችና ኢቲቪ፣ አንድ ጣታቸዉን ወደሌሎች ሲጠቁሙ፣ አራቱ ጣቶቻቸው ወደ እነርሱ መዞራቸውን፣ ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ያሉ እነርሱ መሆናቸውን ነዉ።

«አንዱዋለም አራጌን በተመለከተ፣ የግንቦት ሰባትን ተእልኮ ለማስፈጸም አገር ዉስጥ በሕቡእ (ስዉር) ይንቀሳቀሳል በሰላማዊ ትግል እንታገላለን የሚሉ የፓርቲዎችን ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አቅርበናል» ሲሉ ነበር የፌደራል አቃቤ ሕጉ ለኢቲቪ አክለው የገለጹት። ምን አይነት መረጃ እንዳቀረቡ ግን አልነገሩንም። ለምን ቢባል ምንም ስለሌለ።

አንዱዋለም ያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሲያደርግ የነበረው በግልጽና በገሃድ ነዉ። ለተለያዩ ፓልቶክ ክፍሎች፣ አገር ዉስጥና በዉጭ ለሚገኙ ሜዲያዎች በርካታ ቃለ መጠይቆችን ሰጥቷል። በአገር ቤት፣ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ዉይይቶችና ስብሰባዎች ያቀረባቸው ንግግሮች በሙሉ የተደበቁ አይደሉም። ዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር (አንዱም እኔው ነበርኩ) ፣ ብዙ ጊዜ በስልክ ሃሳቦችን ተለዋዉጧል። በስልክ ያደረጋቸው ንግግሮችም፣ 24 ሰዓት የሰላማዊ ተቃዋሚ መሪዎችን ስልክ በሚጠልፈው ቴሌ ዘንድ የተሰሙ ናቸው። ቤቱና ቢሮዉ ከላይ እስከ ታች ተበርብረዉ ፣ የሚስጥራዊ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች፣ ቦምቦች፣ ፈንጂዎች፣ ሚስጥራዊ ሰነዶች አልተገኙም። ኤሜሎቹ በሙሉ ተነበዋል። አንዱዋለምን ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያገናኝ፣ በሕቡእ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ የሚያመለክት አንዳች መረጃ አቃቤ ሕግ አላቀረበም። መረጃዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ «እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደተባለ፣ ዜጎችን በማዋረድና በማሳነስ የሚታወቀዉ ኢቲቪ፣ ይሄን ጊዜ በስፋት ያወራልን ነበር።

ኢቲቪ ግን አንዱዋለምን ለመክሰስ ያቀረበው፣ አንድ የአንድነት አባል የነበሩ፣ ተስፋሁን አናጋዉ የተባሉ ሰው የተናገሩትን ነዉ። አንዱዋለም ከታሰረ በኋላ አቃቤ ሕጎች መረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ የዉሸት መረጃዎች ማሰባሰቡ የግድ ሆነባቸው። የታሰሩ ሌሎች የአንድነት አባላትን ማግባባት ጀመሩ። «በአንዱዋለም ላይ እኛ ተናገሩ የምንላችሁን ከተናጋራችሁ እንፈታቹሃለን» ብለው እጆቻቸዉን ጠመዘዙ። ብዙዎች በአንዱዋለም ላይ የዉሸት መረጃ ማቅረቡ ሕሊናቸውን ስለከበደው ፍቃደኛ አልሆኑም። ነገር ግን እንደ ተስፋሁን አናጋው፣ የሚባሉ ደካማ ሰዎች ተገኙና የዉሸት ምስክርነት ቀረበ። እንግዲህ በአገዛዙ ካድሬዎች ተቀናብረው ከቀረቡ የዉሽት ምስክርነቶች ዉጭ፣ ቅንጣት የምታክል፣ አንዱዋለምን ሽብርተኛ ወይንም ከግንቦት ስባት ጋር የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ አልቀረበም።

«ግንቦት ሰባት ፣ ግንቦት ሰባት ……» እንባላለን። ከጅምሩ በግንቦት ሰባት ላይ ጠንካራ ተቃዉሞ ያለኝ ሰው ነኝ። የግንቦት ሰባት ፖለቲካ አይመቸኝም፣ ለአገርም ይጠቅማል ብዬ አላስብም። ግንቦት ሰባቶች ከያዙት የተሳሳተ መንገድ እንዲመለሱ፣ በሻእቢያ ድጋፍ ሳይሆን፣ በሕዝብ ጉልበት በመተማመን ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲመጡ መክሪያለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ለአንባቢያን ያቀረብኳቸውን ጽሆፍችን መመልከት ይቻላል።

ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በአገር ዉስጥ በሰላም ለዉጥ ለማምጣት የሚሰሩ ድርጅቶችን ደግፊያለሁ። በተለይም የአንድነት ፓርቲ በጣም የሚመቸኝ ፓርቲ እንደመሆኑ፣ አንዱዋለም አራጌን ጨምሮ፣ ከፓርቲዉ አመራር አባላት ጋር ሃሳብ የተለዋወጥኩባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ። አንዱዋለም አራጌ፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ፣ የልጆች አባት፣ የሰላማዊ ትግል አርበኛ ነዉ። አንዱዋለም ስለ ትጥቅ ትግል ያለዉን አመለካከት አውቃለሁ። በየትኛዉም መድረክና ፍርድ ቤት፣ መጽህፍ ቅዱስ ላይ እጄን ጭኜ የምመሰክረዉ ነዉ። አንዱዋለም አራጌ የግንቦት ስባት አባል ወይንም ሽብርተኛ ነው የሚለውን፣ በምን መስፈርትና መልኩ ልቀበለው አልችልም። በርግጥ አንዱዋለም የግንቦት ሰባት አባል ከተባለ፣ እኔም የግንቦት ሰባት አባል ነኝ እንደ ማለት ነዉ።

በጣም ያሳዝናል። እንደ አንዱዋለም አራጌ አይነት አገር ወዳድ ዜጎች፣ አገራቸዉን በመዉደዳቸው፣ የሕዝብ መብት ይከበር በማለታቸው፣ «ሽብርተኞች» በሚል አሳዛኝ ክስ ሲታሰሩ ማየት፣ አገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ቀና ብለው የሚራመዱባት ሳይሆን ፣ አሳፋሪ ድራማ የሚካሄድባት፣ ሕግ መቀለጃ የሆነባት አገር መሆኗ፣ በርግጥ ልብን የሚያደማ ነው።

እንግዲህ፣ ሁሌ እንደማደርገዉ፣ ጥሪ ለኢሕአዴጎች አስተላልፋለሁ። ኢሕአዴግ ዉስጥ፣ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስቡ ካሉ፣ በድርጅታቸው ዉስጥ እየተደረገ ያለውን አፈናና ግፍ በቃ የማለት አቅምና ጉልበት ሊኖራቸው ይገባል ባይ ነኝ። ድርጅታቸው ዉስጥ ያሉ ጥቂቶች ድርጅታቸውን ይዘው ገደል እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነ አንዱዋለምን በማሰር ኢሕአዴግ ምንም የሚጠቀመው ነገር የለም። እነ አንዱዋለምን በዉሸት ክስ ከሶ፣ በቴለቭዥኝ ደግሞ ስማቸውን ማጉደፍ፣ ነዉር ነዉ። ኢሕአዴግ የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ ነዉ። የአረና ትግራይ አመራር አባል አብርሃ ደስታ አንዴ ሲጽፍ፣ የሕወሃት እምብርት በነበረችው የትግራይ ክልል፣ አንዱዋለም አራጌ በጣም ተወዳጅ ፖለቲከኛ እንደሆነ ገልጾ ነበር። አንዱዋለም አራጌ፣ በክልሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያውቀዉ ጀግና መሪ ነዉ። በርሱ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ፣ የበለጠ አንዱዋለምን ከፍ የሚያደርግ፣ ኢሕአዴግን ደግሞ የሚያሳንስ ነዉ። አንዱዋለምን እና ሌሎች የሕሊና እስረኞች፣ አለመፍታት በቀጥታ ከሕዝቡ ጋር እንደመላተም ነው። አይጠቅምም። ጉዳት አለው።

ለኢሕአዴጎች ጥሪ ባቀርብም፣ የነአንዱዋለም ጉዳይ፣ የኢሕአዴጎች ጉዳይ ብቻ ግን አደለም። ኢሕአዴጎች ወደ ሕሊናቸው ተመልሰው መልካም ነገር ያደርጉ ዘንድ እነርሱን ማነጋገርና ለማሳመን መሞከር፣ ማበረታታት ተገቢ ነዉ የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ ሁሉንም ነገር ከነርሱ ጠብቆ ቁጭ ማለቱ ግን፣ እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። እነርሱ ቢሰሙ መልካም ነዉ፤ ካልሆነ ግን እያንዳንዳችን መብታችንን የማስከበር ሃላፊነት ያለብን ይመስለኛል። ዛሬ እነ አንዱዋለም ናቸው። ነገ እያንዳንዳችን ቤት ይንኳኳል ። ዛሬ ሊመቸን ይችላል። ነገር ግን ለሕይወታችን ምንም ዋስትና አይኖረንም። አንድ የመንግስት ባለስልጣን ፊታችንን አይቶ ከጠላን፣ በቀላሉ ወደ ወህኒ ሊወረወረን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አለብን። አለን የምንለውን ቢዝነስ አንዱ ከፈለገዉ፣ «ያለ የሌለዉን እያመጡ፣ ይሄን ያህል ግብር ክፈል» ተብለን ከጨዋታ ዉጭ በቀላሉ ልንሆን የምንችልበት አገር ነዉ ያለችን። አቤት የምንልበት የሕግ ስርዓት የለም። አብዛኞቹ ዳኞች በመመሪያ የሚፈርዱ ካድሬዎች ናቸው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያ፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ለሁሉ ዜጎቸ እኩል የሆነች፣ ኢትዮጵያዊያን ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉባት፣ መቀባባል፣ ይቅርታ፣ ፍቅር፣ ሰላም ፣ ፍትህና ወንድማማችነት የሰፈነባት፣ የበለጸገች አገር እንድትሆን፣ እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት አለብን። ዳር ሆኖ ተቀመጦ ማውራት ይብቃ። ሌሎች ለምን እንዲህ አላደረጉም ብሎ መክሰስ ይብቃ። ሌሎች ሞተው በነርሱ አስክሬን ላይ ተረማመደን ለመሻሻል መሞከር ይብቃ። አገራችን የእስክንደር፣ ወይንም የአንዱዋለም፣ ወይንም የበቀለ ገርባ፣ ወይንም የርዮት አለሙ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት፣ ሁላችንም ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን ሳንጠብቅ፣ የድርሻችንን እንወጣ።

መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች እያቀረቡላቸው መሆኑ ታወቀ::

የሃያሰዎስተኛ ክ/ጦ ኣዛዥ ብ/ጀነራል በላይ ስዩም፤ የሰላሳ ኣንደኛ ክ/ጦ ኣዛዥ ብ/ጀነራል ድሪባና፤ የሰላሳ ሰዎስተኛ ከ/ጦር ኣዛዥ ብ/ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እኛ ኣዲስ ቶሻሚ በመሆናችን ብዙ ተቀባይነት የለንም::

የማእከላዊ እዝ የበላይ ኣመራሮች በተገኙበት ስብሰባ ላይ እንደ ኣንድ ትልቅ ኣጀንዳ ሆኖ የቀረበ። ኣብዛኛው የሰራዊቱ ኣባል ማግኘት የሚገባው ጥቅም ባለማግኘቱ በሰራዊቱ ውስጥ የመቀጠል ፍላጎቱ ያበቃና የሞተ በመሆኑ ምክንያት ክውትድርና ኣለም ተሰናብቶ የግል ሂወቱ መምራት እንደሚፈልግ ላቀረቡት ጥያቄ በስብሰባው ውስጥ የተካፈሉት የበላይ ኣመራሮች የቀረበው ጥያቄ ሰምተው እንዳልሰሙ በመምሰል ተገቢ መልስ ሳይሰጡበት እንዳለፉ ለማወቅ ተችለዋል::

መረጃው በማስከተል በስብሰባው ውስጥ የተገኙ የሃያሰዎስተኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል በላይ ስዩም፤ የሰላሳ ኣንደኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ድሪባና፤ የሰላሳ ሰዎስተኛ ከፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እኛ ኣዲስ ቶሻሚ በመሆናችን ብዙ ተቀባይነት የለንም ኣታስቸግሩን ብለው መልስ እንደሰጥዋቸው ለማወቅ ተችለዋል::

ይህ በንዲህ እንዳለ ከሰራዊቱ ውስጥ ለመኪና ሾፌርነት ስልጠና ተመልምለው ኣዲ ቡኽራይ ወደ ተባለው ቦታ የታላኩ ወተሃደሮች ስልጠናውን በመተው ወደ ክፍላቸው ተመልሰው የ 7 ኣመት ኣገልግሎታችን ስለ ጨረስን ከሰረዊት የመሰናበት መብታችን ይረጋገጥልን ብልው ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ::

ወደ ስልጠናው ከተላኩ ቦሃላ ተመልሰው ወደ ክፍላቸው ከተመለሱ ምልምል ወተሃደሮች ስም ለመጥቀስ። ወ/ር ማእርግ ሰፍየ፤ ወ/ር ተሻለ ኣየነው፤ ወ/ር ክብሮም ኣስረስና ሌሎች ሲሆኑ። በተለይ ከ 1990 ኣ/ም ባሃላ የተቀጠሩ የሰራዊቱ ኣባላት የደሞዝ ይሁን የማእርግ እድገት መብታቸው እንዳላገኙና በላዩ ላይ ለኣባይ ግድብ፤ ለትምህርት ቤትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እየተባለ ደሞዛቸው እየተቆረጠ በመሆኑ ምክንያት ተማርረው ከሰራዊቱ ለመልቀቅ ስንብት እየጠየቁ መሆናቸው መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል::

የኢሕኣዴግ ፍራቻ የወለደው እቅድ ምርጫውን ሊያጭበረብር ነው::የድምጽ ማጭበርበሮች እንኳን ቢከሰት ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም።
ኢህአዴግ ከምርጫ 2007 በሁዋላ ረብሻ ሊነሳ ይችላል አለ::

ኢትዮጵያን ላለፉት 23 ዓመታት የገዛው ኢህአዴግ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በአዲስ አበባና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ረብሻዎች ሊነሱ እንደሚችሉ ፓርቲው ድምዳሜ ላኢ መድረሱን አስታውቋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁት በተለይ ግንቦት7 እና ኦነግ ምርጫውን ተከትሎ በምርጫ 97 የታየውን አይነት የህዝብ አመጽ ለማስነሳት እየሰሩ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰው ኢህአዴግ፣ ከአሁኑ ጀምሮ በአንድ ለአምስት አደረጃጀትና የከተሞችን ነዋሪዎች ስለ አሸባሪዎች አላማ እና ግብ በማስረዳት ህዝቡ በአመጹ ተሳታፊ እንዳይሆን እንደሚያስተምር አስታውቋል።

አሸባሪ የተባሉ ድርጅቶች በመልካም አስተዳደር፣ በሙስና እና በኢኮኖሚ ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ተጠቅመው ህዝቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ሊያደርጉ ይችላሉ አለው ኢህአዴግ፣ ለዚህ አላማ እንዲረዳቸው ደግሞ ኢሳትንና ቪኦኤን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙሀንን በአገር ውስጥ ደግሞ አንዳንድ ጽንፈኛ አስተሳሰብ ያላቸውን መጽሄቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ ብሎአል። በአገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ ለአመጽ ጥሪው ህጋዊ ሽፋን ለማሰጠት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ ።

በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ የአሸባሪዎች ኢላማ እንዳይሆን ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ኢህአዴግ ገልጿል።

በሚቀጥለው አንድ አመት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በሽብረተኝነት ዙሪያ ተከታታይ ትምህርት የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ግንባሩም ከእዚህ ስልጠና የአካባቢ የሰላም ጠባቂዎችን እንደሚመለምል ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ገዢውን ፓርቲ አይደግፉም የሚባሉትን የመለየት ስራም እንደሚሰራ ታውቋል።

ኢህአዴግ ምርጫውን ተከትሎ ሊነሳ የሚችል ማንኛውም ተቃውሞ ሽብርተኝነት ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። በምርጫ ሂደቱ ላይ ፍትሀዊ ያልሆኑ አሰራሮች እንዲሁም የድምጽ ማጭበርበሮች እንኳን ቢከሰት ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም። ኢሳት ዜና

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እሁድ ጥር 4 ቀን 2006 ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እና አብረዋቸው የታሰሩትን የኢስላም ልጆች መዘየራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በዚያራውም ከኮሚቴው አባላት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የፓርቲው አመራሮች በኮሚቴው አባላት ላይ የሚታየውን ፅናት አድንቀዋል፡፡

በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ የተመራው የከፍተኛ አመራር አባላት
– የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር አቶ ተክሌ በቀለ
– የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ
– የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው
– የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ
በማረሚያ ቤቱ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ከኮሚቴው አባላት ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ ከሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የቅሊንጦ እስረኞች –
1-ሼህ መክት ሙሄ – የሼሪዓ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ
2- አቡበከር አህመድ
3- ካሚል ሸምሱ
4- አቡበከር አሊ
5- ሙባረክ አደም
6-አህመድ ሙስጠፋ
7- አብዱራዛቅ አክመል
እና ሌሎችም ሲሆኑ እነ አቡበከር ከፍተኛ የመንፈስ ጥንካሬ የሚታይባቸው ዛሬም ዛሬም ከፊታቸው ፅናት የሚነበብባቸው እንደነበር የአንድነት አመራሮች ገልፀዋል፡፡
የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠንከር ያለ ምክርና መልዕክትም አስተላልፏል፡፡ ሀገሪቷ በነፃነት ደረጃ እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ መድረሷ እንዳሳዘናቸውም ለፓርቲው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

ኮሚቴዎቻችንን ህጋዊ ወኪሎቻችን መሆናቸውን ሳር ቅጠሉ የመሰከረው ጉዳይ ቢሆንም ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ግን በእስር ቤት እንዲማቅቁ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

አላህ ፍትህን ያስፍንላቸው!!!
ፍትህ ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች !!!

ቁጥራቸው ወደ 40 የሚጠጋ የእሕኣፓ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሰራዊት ጎንደር እና ጎጃምን በተቆጣጠረ ጊዜ በውጊያ ከተማረኩ በኋላ በ1983/84( በ1991)ከተረሸኑ በኋላ በጣና በለስ ፕሮጀክት አቅራቢያ በጅምላ መቀበራቸውን ምንጮች ለኢትዮ ሚዲያ ገልጸዋል::

የጅምላ መቃብሩን የቆፈረው ቡልዶዘር የጣና በለስ ፕሮጀክት ንብረት የነበረ ሲሆን ቡልዶዘሩን ሲያንቀሳቅስ የነበረውም ኦፕሬተር ግድያውን እና የጅምላ መቃብሩን በተመለከት ህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ምስጢር ለመጠበቅ ሲባል ወዲያው የተገደለ መሆኑ ምንጮቹ ገልጸው የግድያው ትእዛዝ የሰጡት እና እንዲፈጸም ያደረጉት ሟች መለስ ዜናዊ እና አኦ ስብሃት ነጋ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ ሁኔታ ስምንት የኢሕኣፓ ሰራዊት አመራሮች የነበሩት በሕወሓት ሰራዊት ተይዘው በ ባዶ 6 እስር ቤት ትግራይ መታሰራቸው እና የግድያ ቅጣት ተላልፎባቸው እንደነበር ይታወሳል:: ይህ የኢሕኣፓ ከፍተኛ አመራሮች ጸጋዬ ደብተራው ሃጎስ በርሄ ይሳቅ ደብረጺሆን እና ሌሎችም የተላለፈባቸው የግድያ ቅጣት የተፈጸመው በትግራይ ይሁን በጎንደር አሊያም በጎጃም እስካሁን መረጃው እንዳሌላቸው ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
http://www.ethiomedia.com/14store/5563.html

የምርጫ 97ን ቀውስ ተከትሎ ወደ እስር ቤት ከገቡት የቀድሞዎቹ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣ በቅርቡ የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ስለአዲሱ ሊቀመንበርነታቸው፣ ስለመጪው ዓመት ምርጫና ሌሎች ጉዳዮች ነአምን አሸናፊ አጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን አመራሩ ላይ ወጣቶች አይታዩም በማለት የሚተቹ አሉ፡፡ የእርስዎን ዳግም ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥንም እንደ ምሳሌ ያነሱታል፡፡ ለምንድነው ወጣቶች ወደ አመራር የማይመጡት?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ያለባቸው መራጮች ናቸው፡፡ መራጮችንና የአንድነት አባላትን መጠየቅ ነው፡፡ በመሠረቱ አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው፡፡ ባለፈው ሥራ አስፈጻሚም ሆነ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የወጣቱ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር፡፡ በጠቅላላ ጉባዔው ሰባ በመቶ አካባቢ ወጣት ነው፡፡ የተወዳደርኳቸው ሰዎችም ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ነገር መጠየቅ ያለባቸው አባላትና ጉባዔው ናቸው፡፡
መጠየቅ ያለበት እኔ ፍላጎት ኖሮኝ ወጣቶችን ወደታች ገፍቼ ድርጅታዊ ሥራ ሠርቼ ብመጣ ኖሮ ነበር፡፡ ወጣቶችን ወደታች ተጭነሃል ማለት ይቻል ነበር፡፡ ዋናው ማየት ያለብን ጠቅላላ ጉባዔውና አጠቃላይ ሒደቱ ዲሞክራሲያዊ ነበር ወይስ አልነበረም ነው፡፡ በእኔ ግምት አንድነት ፓርቲ ለዲሞክራሲያዊ አሠራር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ፓርቲዎች የሚበልጠው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለዚህም የምገልጸው በምክር ቤታችንም በሕገ ደንባችን መሠረት የምንሰበሰበው በሦስት ወር አንዴ ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ግን በዓመት እስከ 20 ጊዜ ይሰበስባል፡፡ ምክንያቱም የጀመርነውን አጀንዳ በምናደርገው ሰፊ ውይይት መጨረስ አንችልም፡፡ አጀንዳ ጨርሰን አናውቅም፡፡ አራት አጀንዳዎች ቀርበው እንደሆን ሁለቱን ጨርሰን ሁለቱን ደግሞ ለሚቀጥለው ጊዜ እናስተላልፋለን፡፡ ይህ ደግሞ የዲሞክራሲያዊ ውይይት ነፀብራቅ ነው፡፡
እኔ እንዲያውም ቅስቀሳ አላደረግኩም፡፡ የእኔ ተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ወይም አይደለም? የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ነበር፡፡ ለምን ወጣቶች አልመጡም ለሚለው የእነሱ ምርጫ ነው፡፡ እኔ በአብዛኛው የተመረጥኩት በወጣቶች ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊትም እንዳደረግኩት ወጣቶችን የማሳተፍ አመለካከትና ባህሪ አለኝ፡፡ እኔ አመራር በነበርኩበት ጊዜ በሕገ ደንቡ መሠረት በሥራ አስፈጻሚ 13 አባላት ነው የሚኖሩት፡፡ እኔ ግን ወጣቶች ወደፊት እንዲቆጠሩ ስድስት አባላት ድምፅ የመስጠት ሥልጣን ሳይኖራቸው አስገብቻለሁ፡፡ ደንቡ ስለማይፈቅድልኝ ነው እንጂ ባለድምፅ ሆነው መግባት ይችሉ ነበር፡፡ ደንቡ ግን አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ ድምፅ አልባ ከመሆናቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ የአመራር አባል ነበሩ፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉም የዚያ አባል ነበሩ፡፡ ሌላው ወጣቱን ለዚህ ቦታ ማንም አልከለከለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ ሜካኒካል ይሆናል፣ ኮታ ይሆናል፡፡ ወጣቶች መምጣት አለባቸው፡፡ የኮታ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ የመብት ጉዳይ ነው እንጂ የሚሰጣቸው ስጦታ አይደለም፡፡ ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ ለወጣቶችም ሜዳው ክፍት ነው፡፡ ነገ ጠዋት የላቀ ከመጣ ምክር ቤቱ በወጣት ሊተካ ይችላል፡፡ ከፖለቲካም አንፃር መታየት ያለበት ስብጥሩ ነው፡፡ ከወጣቶችም፣ ከጐልማሶችም፣ ከአዛውንትም ያ ስብጥር ነው መሆን ያለበት፡፡ ወጣትም ሆኖ ሽማግሌም ሆኖ የራሱ የሆነ ችግር አለበት፡፡ ያንን የሚያቻችለው መቀላቀሉ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በተቃዋሚውም ሆነ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉት የ60ዎቹ ትውልድ አባላት አመራርነት የሚያበቃውና ወጣቶች በሰፊው ወደ መሪነት የሚመጡት መቼ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- በእኔ በኩል በአመዛኙ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ የሚለው አይሠራም፡፡ ባለፈው አላየነውም አሁንም አይታይም፡፡ የአንድነት ዕድሜ ስድስት ዓመት ነው፡፡ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ፕሬዚዳንቶችን ለውጧል፡፡ የመጀመሪያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የወጣቶች ተወካይ ነበረች፣ የ60ዎቹ አይደለችም፡፡ ከዚያ እርሷ ስትታሰር እኔ ተጠባባቂ ሆኜ ኃላፊነቱን ተረከብኩ፡፡ ከዚያ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሆነ፣ አሁን እኔ መጣሁ፡፡ ማንም ፓርቲ በስድስት ዓመት ውስጥ አራት ፕሬዚዳንት የቀየረ የለም፡፡ ይህ የሚያሳየው የአንድነትን ዲሞክራሲያዊነት ነው፡፡ በመሠረቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቃት ባለው ከ60ዎቹ በኋላ ባለው ትውልድ መተካት አለበት፡፡ ያ የእኔ እምነት ነው፡፡ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች መጪውን ትውልድ አብቅተው መተካት እንዳለባቸው እምነቴ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን አንድነትን እንደ ምሳሌ ከወሰድነው መጀመሪያ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወጣት መሪ ነበሩ፡፡ ከዚያ እሳቸው ሲታሰሩ እርስዎ መሪ ሆኑ፡፡ ቀጥሎ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አሁን ደግሞ ተመልሰው እርስዎ መጡ፡፡ በአንድነት ውስጥ ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ውጪ ያው የ60ዎቹ ትውልድ አባላት ስለሆናችሁ ከዚያ አንፃር ለማለት ፈልጌ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ትክክል ያልሆነ ምዘና ነው፡፡ ምንድነው የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቅድም እንዳልኩህ ስብጥሩን ነው ማየት ያለብን፡፡ ብርቱካን በነበረችበት ጊዜም ሆነ አሁን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ጥቂት ናቸው፡፡ ምናልባት በጣት የሚቆጠሩ [እኔ፣ ነጋሶ፣ አስራት]፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩት አብላጫዎቹ ከ60ዎቹ በኋላ የመጡ ትውልዶች ናቸው፡፡ በአሁኑ ብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ ከ35 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉት 72 በመቶ ናቸው፡፡ የ60ዎቹ አሉበት፡፡ ነገር ግን በአብላጫው ወጣቶች ናቸው፡፡ በእኔ ካቢኔ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ያለነው ሁለት ሰዎች ነን፡፡ ከ15 ሰዎች አንድ ሰው የ60ዎቹ ሆኖ ላይ ስለተቀመጠ የ60ዎቹ ተፅዕኖ አለ ለሚባለው ምዘናው ትክክል አይመስለኝም፡፡ መታየት ያለበት ይዘቱ ነው፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ አባላት እንዲያውም የት እንዳሉ ግራ ይገባኛል፡፡ አንዳንድ ቦታ መሪ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲው መዋቅር መፈተሽ ካለበት የ60ዎቹ የፖለቲካ ተሳፊዎች ወጥተው ዳር የቆሙ ይመስለኛል፡፡ ደግሞም የተፈጥሮ ሒደት ነው፣ የፖለቲካም ሒደት ነው፣ የታሪክም ሒደት ነው፡፡ መታየት ያለበት የግለሰቦች የ60ዎቹ ትውልድ መሆን ሳይሆን ስብጥሩ ውስጥ ስንት አሉ የሚለው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን እንደ አዲስ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መጥተዋል፡፡ ለፓርቲው ምን አዲስ ነገር ይዘው መጡ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኛ ፓርቲያችንን የምንመራው በሥርዓት ነው፡፡ ፓርቲው በ2002 ዓ.ም. የስትራቴጂ ዶክመንቱንና የአምስት ዓመት ዕቅዱን በመጽሐፍ መልክ አውጥቶታል፡፡ የአነድነት ፓርቲ መሠረታዊ ራዕይና ግብ በዚያ ውስጥ ነው የሚታየው፡፡ እዚያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ነው ሁላችንም በቀጣይነት እየገነባን የምንሄደው፡፡ ነገር ግን በ2002 እና በ2003 ዓ.ም. ያወጣነው የስትራቴጂ ግንባታ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መዛመድ አለበት፣ መቀነባበር አለበት፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ አንዳንድ ለየት ያሉ ሙከራዎች አካሂዳለሁ፡፡
የመጀመሪያው ሙከራዬ አንድነት ምናልባት ካሉት ፓርቲዎች በጉልህ ጠንክሮ የሚታይና መዋቅሩ ታች ድረስ የወረደ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲያው እንደ ሌላው ጉልበት ወይም አቅም አለን ባንልም በቂ የመንቀሳቀስ ችሎታ አለን የሚል ግምት አለኝ፡፡
ይህንን የአመራር መርህ ከአንድነት አቅምና ሕዝባዊ ገጽታ አንፃር የተለየ (Rebranding) እንዲሆን አደርጋለሁ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ያደረግኩት ሥራ አስፈጻሚውን በአብዛኛው ወጣትና አዲስ ነው ያደረግኩት፡፡ በትምህርታቸው ብቁ የሆኑ ናቸው፡፡ በትምህርት ብትሄድ አሁን ከ15 ሰዎች ስድስቱ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሰባቱ የመጀመርያ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ አሁን ይኼ አዲስ ምልክት (New Branding) ነው፡፡ ሁለተኛ እነዚህን ሰዎች ስመድብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ችሎታ እንዲኖራቸው አንዱ መሥፈርት ነበር፡፡ አሁን ዘመኑ ወደዚያው እያመራ ነው፡፡ ስለዚህ በኢንፎርሜሽን ግንኙነታችን ከውጭው መረጃ እኩል አንድነት መራመድ አለበት፡፡
ሌላው ትኩረት የምሰጠው ወጣቶችን የማብቃት ሥራ ነው፡፡ ወጣቶች በቅተው ፓርቲውን እንዲመሩ አደርጋለሁ፡፡ አሁን እኔ እዚህ ሆኜ ወጣቶችን ነው ወደፊት እንዲሮጡ የማደርገው፡፡ ይህን ካደረግኩ በኋላ በእኔ እምነት ክርክርም መካሄድ አለበት፡፡ እስካሁን የተካሄደው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ውጤት አላስገኘም፡፡ ይኼ ምንም የምንክደው አይደለምና ይህ ለምንድን ነው የሚለው ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል፡፡ ወይ ማቆም አለብን ወይ መሥራት አለብን፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተበጣጠሱ ዘጠና ፓርቲዎች አሉ፡፡ ከዘጠናዎቹ ደግሞ ጉልህ የሆኑት አሥር አይሆኑም፡፡ አሥሩም አብረው መሥራት አልቻሉም፡፡ በጥምረትም በግንባርም አልተቻለም፡፡ ለምንድን ነው? ለአሥሩም ቢሆን አሥር መሪዎች አሉ፣ አሥር ፕሮግራሞች አሉ፡፡ አሥሩም እንግዲህ አሥር መሪ ኖሮዋቸው ፖለቲካ ይመራሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ በብሔራዊ ምክር ቤትና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስገኛለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡
በእኔ እምነት እንግዲህ አንድነት ፓርቲ ግንባርና ጥምረት ውስጥ አይገባም፡፡ ወደ ውህደት አንድ አመራር አንድ ፕሮግራም ወዳለው እንቅስቃሴ እንገባለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የእኔ ሐሳብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ስብሰባ ላይ ፈንጥቄያለሁ፡፡ ይህ መሆን አለበት፡፡ የተጀመሩት ውህደቶች በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ማለቅ አለባቸው ብሎ ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ወይ እንዋሀዳለን ወይ እንለያያለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ አንድ የማየው እስከ 2007 ዓ.ም. ወይም በዚህ ዓመት ለእኔ የውህደት ዓመት ነው ብዬ የምገምተው፡፡ ወይ እንዋሀዳለን አለበለዚያ በሰላም ተለያይተን ሁላችንም ጉልበታችንን በየአካባቢው በትብብር እናጠናክር የሚል አመለካከት አለኝ፡፡
ይህን ካደረግኩ በኋላ ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) እንዲኖረን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደ ሽብርተኛ ነው፡፡ ይኼንን ነገር ለሚያስብ ሰው እኮ በጣም ነው የሚያስደነግጠው፡፡ በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አውሬ ነው፡፡ ምናልባት የሠራውን ሥራ ሁሉ ዋጋ (Credit) ያለመስጠት አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖአል፡፡ ያ መቆም አለበት፡፡ ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገው እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለውን የፖለቲካ ምኅዳር ለሁላችንም እኩል ማድረግ አለበት፡፡ ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ለምንድነው የኢሕአዴግ ብቻ የሚሆነው? መብት እኮ አለን፡፡ ለኢቴቪ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ የጻፍነው ምንድነው የኢሕአዴግን ኮንፈረንስ ከባህር ዳርና የኢሕአዴግን ብሔራዊ ምክር ቤት በቀጥታ ስታስተላለፉ ነበር፡፡ የእኛን ግን አልዘገቡም፡፡ ለኢሕአዴግ 99 በመቶ ሰጥተው ለእኛ ግን አንድ በመቶ እንኳን አይሰጡንም፡፡ ይኼ ሁሉ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳየው የኢሕአዴግን ድክመትና ስህተት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ለብዙ ፓርቲዎች የእንዋሀድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደታየው ብዙ ውህደቶች ምርጫ ሲደርስ ከመሰባሰብ በዘለለ ብዙም ሲገፉበት አይስተዋልም፡፡ የ97ቱን ቅንጅት ማስታወስ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እርስዎ የሚያቀርቡት ሐሳብ በምን ይለያል? ከዚህ ቀደም ተሞክረው እንደከሰሙት እንደማይሆንስ ማረጋገጫው ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የቅንጅት ራሱን የቻለ ጉዳይ አለው፡፡ ቅንጅት አልተዋሀደም ነበር፡፡ ለዚህም ነው ቅንጅት ግንባር ደረጃ አልደረሰም የሚባለው፡፡ ለቅንጅት ከፍተኛውን ድቀት ያስከተሉት የኢሕአዴግና የቅንጅት መሪዎች ናቸው፡፡ በወቅቱ ኢሕአዴግ ያልጠበቀው የፖለቲካ አድማስ ነው የመጣበት፤ በ97 ምርጫ አልጠበቀውም ነበር፡፡ አራቱ ፓርቲዎች ማለትም መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ቀስተ ደመናና ኢዴሊ ሆነው ቅንጅት የተመሠረተው ኅዳር ላይ ነበር፡፡ ኅዳር ላይ ተመሥርተን ግንቦት ላይ ነው ከፍተኛ ዕርምጃ ያሳየነው፡፡ ያ ሁኔታ ኢሕአዴግ ያለውን ግምት በጣም ነው ያዛባው፡፡ ኢሕአዴግ አቅም አይፈጥሩም የሚል ግምት ነበረው፡፡ ገና ስንፈጠር በምርጫው አካባቢ አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርን፡፡ የምርጫው ዕለት ምሽት በአጠቃላይ የምርጫው ሒደት ተናጋ፡፡ በዚያ ምክንያት ቅንጅት ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ገባ፡፡ ኢሕአዴግ ትኩረት አደረገብን፡፡
በዚያ ምክንያት እኛም ወደ እስር ቤት ገብተን ከዚያ ደግሞ ወጣን፡፡ ያው ነገሩ ትክክል ስላልነበር መውጣት እንደነበረብን እኔ አምናለሁ፡፡ ከወጣን በኋላ ደግሞ እኛ አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ብሶት ተፈጠረ፡፡ እንደገና ቅንጅትን ለአቶ አየለ ጫሚሶ ሰጡት፡፡ በዚያ በዚያ በመካከላችን ችግሩን በሰከነ ሁኔታ ለማራመድ አልቻልንም፡፡ በዚህ በኩል የራሱ የኢሕአዴግም የእኛም ድክመት ነበር፡፡ ከዚያ በፊትም በተፈጠሩት ስብስቦች እንደዚሁ የመሪዎች ብዛት ነው ችግሩ፡፡ አሁን እኔ የምለው ውህደት ከሆነ አንድ መሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ውህደቱም መፈጸም ያለበት በዲሞክራሲያዊ መርሆዎች መሆን አለበት፡፡ ውህደት ላይ ዲሞክራሲያዊ ባህል መፍጠር አለብን፡፡ አመራር አንድ መሆን አለበት፡፡ ሕግ፣ ሥነ ሥርዓትና ደንቡ መታየት አለበት፡፡ እናም ዲሲፕሊን ሊኖረን ይገባል፡፡ የባህሪ ለውጥም ያስፈልገናል፡፡ ከዚህ አንፃር አንደኛ እኛ አመራሮች የባህሪ ለውጥ ያስፈልገናል፡፡ ያ እስከሆነ ድረስ እኔ ውህደት ይወድቃል ብዬ አላስብም፡፡ አልተሞከረም፡፡ በተጨባጭ ብሔራዊ ዕይታ ያለው ውህደት እኮ እስካሁን አልተካሄደም፡፡
ሪፖርተር፡- ከዚህ ከውህደቱ ጋር በተያያዘ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይስ እንዴት ነው የሚታየው? ብሔራዊ የሆነ ፓርቲ ይኖራል፤ ኅብረ ብሔራዊ የሆኑ ፓርቲዎችም ይኖራሉ፡፡ ይህስ ለውህደቱ እንቅፋት አይሆንም?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኔ ሁላችንም ወደ ብሔራዊ ምክክር መምጣት አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለምሳሌ ብሔር ተኮር የሆነ ፓርቲ ከእኛ ጋር ሲዋሀድ ብሔራዊ ቅርፅ መያዝ አለበት፡፡ አለበለዚያ ብሔር ተኮርና ኅብረ ብሔር ሊዋሀዱ አይችሉም፡፡ ምንድነው ጠቃሚው ነገር? ዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ ለምሳሌ የእኛ ፕሮግራም የግለሰብንም የቡድንንም መብት ያከብራል፡፡ የብሔረሰብ ጉዳይ ከሆነ የቡድን ጉዳይ ነው፡፡ ያ እስከተጠበቀ ድረስ ማንኛውም የብሔር ፓርቲ እኛን ይቀላቀላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ያ ነው ጠቃሚው ነገር፡፡ የፕሮግራሙ ዕይታ ብሔር ተኮር የሆኑትን ፓርቲዎች ፍላጐት ማሟላት አለበት፡፡ የብሔረሰቡ ቋንቋ፣ የብሔረሰቡ የመወሰን መብትና ባህል ማሟላት አለብን፡፡ ይኼ የኢትዮጵያ ነፀብራቅ ነው፡፡ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች የምንልበት ጉዳይ አይደለም፡፡ እኩልነት እስካለ ድረስ የብሔረሰብ ጉዳይ አይነሳም ባይ ነኝ፡፡ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እስካሉ ድረስ ችግር ያለ አይመስለኝም፡፡
ሪፖርተር፡- አንድነት አሳካዋለሁ ወይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አመጣዋለሁ የሚለው የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የእኛ ሊበራል ዲሞክራሲ ነው፡፡ ሊበራል ዲሞክራሲ ሆኖ የቡድንና የግለሰብ መብትን አንድ ላይ እናከብራለን፡፡
ሪፖርተር፡- በሊበራል ዲሞክራሲ የቡድንም የግልም መብት ይከበራል ብለዋል፡፡ ነገር ግን የፍላጐት መጋጨት አይኖርም? በቡድን መብትና በግለሰቦች መብት መካከል ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው የሚወሰነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንት ሰዎች ናቸው እንደዚህ የሚሉት? ሊኖርም ይችላል፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አሥር ሰዎች ሁለቱን አባረው ማካሄድ አይችሉም የሚል ይኖራል፡፡ 90 በመቶ ከደገፈው የ90 በመቶ ይሆናል ለሚለው የዲሞክራሲ ውሳኔ ነው የሚጠይቀው፡፡ እኛም ተወያይተንበታልና የሚወሰነው በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ አገር አቀፍ ምርጫ አለ፡፡ አንድነት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫው ለመሳተፍና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ምን ምን ሥራዎችን እየሠራ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አንደኛ የራሳችንን አቅም እየገነባን ነው፡፡ ከጠቅላላ ጉባዔያችን ዕይታ አግኝተናል፡፡ በዚያ ዕይታ ለምሳሌ የውህደቱ አንዱ ዓላማ በምርጫ የማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድነት ብቻውን ከሚሮጥ ሦስትና አራት ፓርቲ ሆነን ልክ እንደ ቅንጅት ብንሮጥ የተሻለ ውጤት እናገኛለን በማለት፣ በውህደቱ ለምርጫው አንድ የጐለበተ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁለተኛው ፕሮግራማችንንና ርዕዮተ ዓለማችንን ልክ እንደ ሚሊዮኖች ንቅናቄ ወደታች እናወርደዋለን፡፡ አንድ የሕዝብን ዕይታ የሚስብ ከምርጫ 2007 ጋር የሚገናኝ ፕሮግራም እናወጣለን፡፡ ሕዝብን ለማንቀሳቀስ ከዚህ በተጨማሪ አንድነት የዲሞክራሲ ምርጫ ፓርቲ ነው፡፡ ለማንኛውም ሁልጊዜ ለምርጫ ይዘጋጃል፡፡ አሁን ስትራቴጂያችንን ከልሰን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አማራጭ ፖሊሲዎችን እንቀርፃለን፡፡ ከአማራጭ ፖሊሲዎች በመነሳት የምርጫ ማኒፌስቶ እናዘጋጃለን፡፡ በእኔ ዕይታ እስከ ሰኔ ድረስ ካለፈም እስከ ነሐሴ ድረስ አንዱና ትልቁ ሥራችን ይህንን የምርጫ ፖሊሲና ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ነው፡፡ ከዚያ ብቁ የሆኑ ዕጩዎችን ከካቢኔያችን ውስጥ እንመለምላለን፡፡ ከየቦታው ብቁ የሆኑ ታዛቢዎችንም እንመርጣለን፡፡ ይህ ሒደት ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባ እናካሂዳለን፡፡ እንደዚሁም ሕዝባዊ ንቅናቄ ይኖረናል፡፡ እየሄድን ራሳችንን ወደ ሕዝብ የምናወርድበት፡፡ ይህን ሁሉ ለማድረግ ግን የምርጫ ፓርቲ ብንሆንም ምርጫ ውስጥ ጥልቅ ብለን አንገባም፡፡ ሜዳው ለሁላችን እኩል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት ለዚህ ነው ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) ከገዥው ፓርቲ ጋር የምናደርገው፡፡ ይኼ ሜዳ ለሁላችንም እኩል እንዲሆን ነው የምንፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን ነች፡፡ ኢሕአዴግ አንድ ፓርቲ ነው፡፡ እኛም አንድ ፓርቲ ነን፡፡
የምርጫው ሕግ በሕገ መንግሥቱና በምርጫ ቦርድ ሕግ መሠረት መካሄድ ስላለበት ያንን እንጠይቃለን፡፡ ምርጫ ቦርድ የኢሕአዴግ ከሆነ፣ ሚዲያው የኢሕአዴግ ከሆነ፣ የፍትሕ አካላቱ የኢሕአዴግ ከሆኑ እኛ ያን ጊዜ የምንወስነው ውሳኔ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከትዝብትም ጭምር እስካሁን ያሉት ተቋማት ለእኔ ዲሞክራሲያዊ አልነበሩም፡፡ የ2002 ምርጫ በጣም ያዘንኩበት ምርጫ ነበር፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን 99.6 በመቶ የሚያገኝ ፓርቲ የለም፡፡ በዓለም ላይ ዲሞክራሲያዊ በሆነና ውድድሩ በእኩል ሜዳ ላይ ተካሂዶ በእዚህ ውጤት ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በዓለም ዙሪያ በአብዛኛው መንግሥት በቅንጅት እየተፈጠረ ነው፡፡ እንግሊዝን ውሰድ የኮንሰርቫቲቭና የሌበር ፓርቲ ቅንጅት ነው፡፡ ጀርመን፣ ጣሊያንና ኖርዌይም እንዲሁ ቅንጅት ነው፡፡ ምክንያቱ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ውድድሩ ነፃ ነው፡፡ እናም ስለዚህ 99.6 በመቶ በጭራሽ ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያለ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና የኅብረተሰብ ክፍል ባህሪ ባለበት አገር ይኼ አይቻልም፡፡ ይኼ ነገር መለወጥ አለበት፡፡ እናም ለምርጫ እንዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን ሜዳው ሁላችንንም እኩል ማስተናገድ አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- የመጫወቻ ሜዳው ለሁላችሁም እኩል መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ለምሳሌ በምርጫ 97 ሚዲያው ትንሽ ወደ ኢሕአዴግም ቢያደላ ተከፍቶ ነበር፡፡ እንዲያውም የእነሱ ሜዳ ከፍ የእኛ ሜዳ ዝቅ ቢልም፣ ነገር ግን የመወዳደርያ ቦታ ነበረው፡፡ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ክርክሮች ለሕዝብ የወጡት በ97 ምርጫ ነበር፡፡ በ2002 ምርጫ ሚዲያው ታፍኖ ነበር፡፡ ሚዲያው የሕዝብ ጥያቄ አላስተናገደም፡፡ ዝም ብሎ ለይስሙላ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተሂዶ አንዳንድ ነገሮች መነጋገራችንን ሕዝብ ሊሰማው ይችላል፡፡ ነገር ግን በሆነ እጅ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነበር፡፡ ያ መሆን የለበትም፡፡ እናም ትልቁ ምሳሌ የ97 ምርጫ የሚዲያ ጉዳይ ነበር፡፡ ሚዲያው ያን ጊዜ ተከፍቶ ነበር፡፡ በእኩልነትም ባይካሄድም ያን ጊዜ እንደ እኩል ነው የወሰድነው፡፡ እንደዚያ መሆን አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ አንድነት የፀረ ሽብር ሕጉ ይሰረዝ የሚል አቋም ይዞ እየተከራከረ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በመላው ዓለም ሽብርተኝነት ትልቅ ሥጋት ሆኗል፡፡ በእኛ አገር የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አጠቃቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማሰኘት ነው የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት እንደ ፓርቲ አማራጭ የፀረ ሽብር ሕግ አለው ወይ ይሰረዝ ሲል ምን ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- መጀመርያ ሽብርተኝነትን መዋጋት የኢሕአዴግ ብቻ አይደለም፡፡ የማንኛውም ዜጋ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይኼ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴው አስከፊ፣ ከሰው ልጅ ባህሪ በተለየ የሰው ልጅን መንፈስ የሚሰብር፣ የሰው ልጅነትን የሚቀንስ ነው፡፡ አንድነትም ሆነ እኔ እንደ አንድነት አመራር እንደዚሁም እንደ ዜጋም እንዋጋለን&#496

በአሁኑ ወቅት 30 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀውና በሦስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ፣ ‹‹ቴክኒካዊ›› በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ድርድሮች እየተደረጉ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ድርድር ከሚስተዋሉ አቋሞች ግን ለዘመናት የቆዩ ሴራዎች መልካቸውን ቀይረው እየመጡ ይመስላል፡፡

በታላቁ የዓባይ ግድብ ላይ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት ውጤት የያዘው ሪፖርት አሁን እየተደረጉ ላሉት ድርድሮች መሠረት የሚጥል ነው፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው፣ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ ምንም መሠረታዊ ምክንያት ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን በታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊያስከትለው የሚችለው የውኃ ፍሰት መጠን መቀነስና ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሦስቱም አገሮች ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በጋራ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ነው፡፡ በተረፈ የግድቡ ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ሪፖርቱ አጽንኦት ይሰጣል፡፡

የግብፅ ዥንጉርጉር አቋሞች

ኢትዮጵያና ሱዳን ሪፖርቱን በፀጋ የተቀበሉት በመሆናቸው ሚስጥርነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይም የሚቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በሪፖርቱ ላይ የተዘበራረቀ አቋም እያንፀባረቀች በመሆንዋ ሪፖርቱ ይፋ በሆነበት ወቅት በተጠራው ብሔራዊ ምክክር፣ በተለይ የግብፅ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ጦር ኃይሉ እንዲዘምት ድምፃቸው ተሰምቷል፡፡ ግብፅ ባጋጠማት ቀውስ ምክንያት እየተደረጉ ያሉት የባለሥልጣናት መቀያየር የግብፅ መንግሥት አቋም ለትንተና የማይመች ቢሆንም፣ አንዱ የሌላውን ስህተት እየደገመ ይመስላል፡፡ አንዱ ከሌላው ስህተት እየተማረ አይመስልም፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የሽግግር መንግሥት ከአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ ጊዜ በኋላ የተባረረውን የፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ መንግሥት በኢትዮጵያና በዓባይ ግድብ ላይ የተለሳለሰ አቋም መያዙ ለውድቀቱ ምክንያት መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡

ሁለተኛ ከላይ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያለው ቢሆንም፣ ግብፅ በአንድ በኩል የባለሙያዎቹ ሪፖርትን አለመቀበልዋና በሌላ በኩል የቡድኑን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር ድርድር እንዲደረግ መስማማቷ እርስ በርስ የሚጣረሱ አካሄዶች ናቸው፡፡

ሦስተኛ ሪፖርቱን በተመለከተ በሚስጥር ተይዞ መቀመጥ በነበረበት ጊዜ አንዳንድ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ ተብለው ለሚገመቱ አገሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተላልፎ እንዲሰጥ ማድረጓ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ዋሽንግተን ፖስትን ጨምሮ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሪፖርቱን ድምዳሜ በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ በአገር ውስጥ የሚደረገውን አሉታዊ የሚዲያ ቅስቀሳን ጨምሮ ማለት ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ግብፅ የሪፖርቱን ውጤት መቀበሏን በግልጽ ባታሳውቅም፣ የባለሙያዎች የቡድንን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር በቅርቡ ያለውጤት የተበተነውን ጨምሮ ሦስት ጊዜ ድርድር ተቀምጣ ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግና ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ለማቋቋም በሁለቱም የመጀመርያ ድርድሮች ግብፅ ተስማምታ ነበር፡፡

በኮሚቴው አወቃቀር ላይ አንዳንድ ውዝግቦች የነበሩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በኮሚቴው ውስጥ ሦስቱን አገሮች የሚወክሉ ዜጐች ብቻ እንዲካተቱ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ ይህ የኢትዮጵያ አቋም ነበር፡፡ ኮሚቴውም ምክረ ሐሳቡን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የውጭ አማካሪ ድርጅትን የመቅጠርን ሥራ ጨምሮ አማካሪው የሚያቀርበውን ሐሳብ ይገመግማል ይላል፡፡

ባለፈው ሳምንት በካርቱም በተደረገው ሦስተኛው የድርድር ዙር ግን የግብፅ ተወካዮች ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እንዲቀጠር ይጠይቃሉ፡፡ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ግብፆች እንዲቀጠር የፈለጉት የውጭ አማካሪ ድርጅት ቀደም ሲል ስምምነት ከተደረሰበት መንፈስ ውጪ የሚቋቋመውን ኮሚቴ በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዲኖረው የሚል ድብቅ አጀንዳ የያዘ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ድርድሩ ያለውጤት ሲበተን በቀጣይነት ግን ለመነጋገር ቀጣሮ ተይዟል፡፡

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል የሆኑት በዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ላይ ግንባር ቀደሙ ተመራማሪው ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በግብፅ የቀረበው የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን እንዲመሠረት ብትቀበልም በሁለት ነገሮች አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡ አንደኛው የባለሙያዎቹ ቡድን በሦስቱ አገሮች የጋራ መግባባት (ሙሉ በሙሉ) መመሥረት አለበት የሚል የኢትዮጵያ አቋምን ግብፅ መቀበል አለመቻሏ ነው፡፡

ሁለተኛው የባለሙያዎቹ ቡድን የሚመሠረተው ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ አባላትን ያቀፈው የምክረ ሐሳቡን አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለሙያዎች ቀጥሮ ሥራውን ሲያስፈጽም ድንገት አለመግባባት ከተፈጠረ እንጂ፣ አሁን የሚመሠረትበት አመክንዮ የለም የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ነው፡፡

ሌላው ስብሰባው ያለ ውጤት እንዲበተን ምክንያት የሆነው ሦስቱም አገሮች የጋራ መግባባት እንዲኖራቸው ግብፆች ሰባት መርሆች ይዘው መቅረባቸው ነበር፡፡ የመግባባት ሰነድ መፈራረም የዚሁ ስብሰባ አጀንዳ ካለመሆኑም ባሻገር፣ ቀደም ሲል በተለይ የውኃ አጠቃላይ የስምምነት ማዕቀፍ ላይ ሲፈራረሙ፣ ከአሥር ዓመት በላይ ከቆዩ በኋላ አሁን እንዲህ ዓይነት አጀንዳ ላይ መነጋገር ዋናውን ጉዳይ ወደ ጐን ለመግፋት ያለመ በመሆኑ ኢትዮጵያ ያልተቀበለች ምክንያት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ዶ/ር ያዕቆብ እምነት፣ ጥያቄው ሒደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የተደረገውን የሚቃረን መርህ ነው፡፡

ዴይሊ ኒውስ የተባለ ጋዜጣን ጨምሮ አብዛኞቹ የግብፅ ሚዲያዎች ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ዋቢ አድርገው የዘገቡት ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ‹‹ከሦስቱም አገሮች የተውጣጣ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ግብፅ ያቀረበችው ሐሳብ በኢትዮጵያ ተቀባይነት አላገኘም፤›› በሚል፡፡

ምን ማለት ነው?

ዓለም አቀፍ የውኃ ኤክስፐርቶች ያሉበት ቡድን ግድቡን አጥንቶ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ያቀረበውን የምክረ ሐሳብ ለመተግበር ተደጋጋሚ ድርድር እየተደረገ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ድርድሩ እንከን እያጋጠመው ይመስላል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፣ ‹‹ወደፊት ድርድሩ ምን የሚሆን ይመስልዎታል?›› በማለት ከሪፖርተር ለቀረብላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አሁን እየተሠራ ያለው ሥራ በባለሙያዎች ደረጃ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት እንዲደረግ ነው፡፡ በቁጥር ተለክቶ ተወስኖ የሚገለጽ ነገር ነው፡፡ ግብፆች ያንን ነገር መቀበል አይፈልጉም፤›› ብለዋል፡፡

እንደተደራዳሪም እንደ የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪም የጀመሩትን ምላሽ በመቀጠል፣ ‹‹በቴክኒክ ደረጃ ያለውን ነገር ወደ ላይ ወደ መሪዎች ግብፆች ተመልሶ እንዲሄድና ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ እስካሁን የተሠራውንና የተለፋበትን መና የሚያስቀር ነው፡፡ እንዳልተሠራ ሆኖ ወደ ኋላ የሚመለስ ከመሆኑም በላይ፣ በዚያውም ግብፆች የፖለቲካ ውዝግቡን ለሚዲያ ቀልብና ትችት ይዳርጋሉ፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል እያንዳንዷ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ የምትታይ መሆኗን፣ ድርድሩ በዝርዝርና በቴክኒክ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ እንጂ ወደ ፖለቲካ ተመልሶ የሚሄድበት መንገድ በሩ ዝግ ነው ብለዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህርና በዓባይ ውኃ ውዝግብ ላይ ጥናት ያካሄዱት አቶ ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው፣ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ተደራዳሪውን ዶ/ር ያዕቆብ ሐሳብ ይደግፋሉ፡፡ ‹‹በግብፅ በኩል ለማድረግ የሚፈለገው አንድና አንድ ነው፡፡ የግድቡ ሥራ እንዲቋረጥ ወይም በጣም ትንሽ ሆኖ እንዲገነባ ነው፡፡ ያ እስካልተሳካላቸው ድረስ ጉዳዩ ሁሌም ፖለቲካዊ መልክ ይዞ በሚዲያ እንዲራገብና ኢትዮጵያን ለማስተቸት ይፈልጋሉ፤›› ብለዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ ፍላጐታቸው ቀደም ሲል በብቸኝነት የተፈረመውን እ.ኤ.አ. የ1959 ‹‹ውል›› ማሽከርከር እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንደ አቶ ዘሪሁን ገለጻ፣ ግብፆች በአንድ በኩል የተፋሰሱን አገሮች የውኃ ትብብር ማዕቀፉን በጀርባ እየመጡበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው መንገድ እንዳለ ሆኖ፣ በዓባይ ተፋሰስ አገሮች ሥራ ላይ የዋለውንና ሕግ ሆኖ የፀደቀውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በፈራሚ አገሮች ፓርላማ እንዳይፀድቅ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

የተመናመነው የመደራደር አቅም

በዓባይ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች በሦስት አገሮች መካከል ብቻ የሚደረጉ የሦስትዮሽ ድርድር ሆነዋል፡፡ ቀደም ሲል በግድቡ መገንባት ተቃውሞ ቢጤ አሰምታ የነበረችው ሱዳን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቋሟን ለመከለስ ተገዳለች፡፡ በመሆኑም አሁን በጉዳዩ ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ጐልተው እየወጡ ያሉት ጫፍ የረገጡ ውዝግቦች በሁለቱ አገሮች ማለትም በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ሆነዋል፡፡ ይኼውም ከ80 በመቶ በላይ የዓባይን ውኃ ጥቅም ላይ በምታውለው ግብፅና ለዓባይ ውኃ 86 በመቶ አስተዋጽኦ በምታደርገው ኢትዮጵያ መካከል ነው፡፡ ውዝግቡ በተለያዩ መንገዶች የሚገለጽ ሲሆን፣ የሱዳን አቋም መለወጥ የግብፅን የመደራደር አቅም እየተመናመነ እንዲመጣ ምክንያት መሆኑን አንድ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዲገለጽ የማይፈልጉ የውኃ ዲፕሎማሲ ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የግብፅ የመደራደር አቅም የተመናመነው ግብፅ ውስጥ ባለው ቀውስ ምክንያት ብቻም አይደለም፡፡ እንዲያውም ሚዲያዎቻቸው ከሚዘግቡት ማስተዋል እንደሚቻለው፣ የግብፅ ፖለቲከኞች አገራቸው ከገባችበት ቀውስ መውጣት የምትችለው አንድ ትልቅ ውጫዊ የሆነ አጀንዳ በመፍጠር መሆኑን የተስማሙ ይመስላሉ፡፡ እሱም የዓባይን ጉዳይ በማቀንቀን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የተባለችውን ‹‹ነባር ጠላት›› ማስቀደምና የውስጥ ጉዳያቸው በድርድር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡ እንደ ዲፕሎማቱ እምነት ሱዳን በግድቡ ላይ የነበራት አቋም ሲለወጥ በግብፅ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ነበር የፈጠረው፡፡

የዓባይን ግድብ በተመለከተ የሱዳን አቋም መለወጥ ብቻ ሳይሆን፣ የግድቡን ተፅዕኖ ያጠኑት የውኃ ባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት የግብፅ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩትን ሴራ አክሽፎባቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርጉት ጉትጐታ ተቀባይነት እንዳይኖረው አድርጐታል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያን አቋም በይፋ ሙሉ ለሙሉ ተሰሚነት አገኘ ባይባልም፣ አንዳንድ ትልልቅ መገናኛ ብዙኃን ሚዛኑን በጠበቀ አኳኋን መዘገብ ጀምረዋል፡፡ አሁን ቴክኒካዊ የሆነ ድርድር ወደ ፖለቲካ ደረጃ ከፍ ብሎ ውዝግብ እንዲፈጥር የሚፈለግበት ምክንያት ይኸው ነው፡፡

ቀደም ሲል ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን የማዳከም ስትራቴጂ የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡን ሙሉ ለሙሉ በራሱ ወጪ ለመገንባት ነበር ያቀደው፡፡ በመሆኑም በፕሮጀክቱ ተፈጥሮም ሆነ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፍ ሪፖርት ግብፅ በውጭው ዓለም ልታሳርፍ የነበረውን ተፅዕኖ በእጅጉ ቀንሶታል፡፡

‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ፣ በቅርቡ ለግብፅ የውጭ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ እንዳትውል ትሰጋ የነበረችው ሱዳን አቋም መለወጥ ብዙ ነገሮችን በግብፆች ላይ ያወሳሰባቸው ይመስላል፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ማስታወስ ግድ ይላል፡፡

አንደኛው ከሁለት ዓመት በፊት የአሜሪካ አንድ የደኅንነት ድርጅት (Stratford) እና ዊኪሊክስ ይፋ እንዳደረጉት፣ ግብፅንና ሱዳን ኢትዮጵያንና ታላቁን ግድብ ለማጥቃት ሐሳብ ነበራቸው ተብሎ ነበር፡፡

ሁለተኛው ሱዳን ሥጋት በሚፈጥረው የሁለቱ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ ትሳተፋለች የሚል ግምት ያልነበረ ቢሆንም፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የቅርብ ጐረቤት የሆነችው የሱዳንን ግዛት እንደ መንደርደርያ ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ግምት ነበር፡፡

ግብፅ የዓባይን ውኃ በብቸኝነት ለመጠቀም ታዋቂና በአብዛኛው የውኃው ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ ውጪ የተደረጉት እ.ኤ.አ. የ1929ና የ1959 አሮጌ ስምምነቶች በአዲሱ ሁለገብ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ (CFA) በስድስት አገሮች ፈራሚነት መተካታቸውና ሕግ ሆነው መፅደቃቸው ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር

በሃገራችን ውስጥ እየተከሰተ ያለው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እኛ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የአለም ህዝብ ትኩረት በመሳብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በገሃድ እየታየ ነው:: ይህ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የሚፈጸመው ቁልፍ ባለስልጣናት የፖሊስ መኮንኖችን በመጠቀም የህዝብን ሰላም ማደፍረስ እና ሽብር መንዛት የእለት ተግባራቸው አድርገው ተያይዘውታል::

ብልሃት በሌለው መልካም አስተዳደር የፖሊስ ባለስልጣናት የሚፈጽሙት ኢሰብኣዊ ተግባራት የህዝብን የመኖር ሁኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከቶታል::ከጥያቄ ምልክትም አልፎ ከባባድ ወንጀሎች በህዝብ የእለት ተለት ሂደት ውስጥ ራሱን መንግስት ያሰኛው ሕወሓት እየፈጸመ ነው::የኢትዮጵያ ህዝቦች ሃይማኖት እና የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይለያቸው በጋራ የሚያቀርቡትን ጥያቄ
ላይ መልስ መስጠት እየተቻለ በጉልበት እና በማስፈራራት በመግደል እና በማሰር የሚመጣ ለውጥ የለም:; የህዝቦች ትግል በየፈርጁ እየቀጠለ ይሄዳል::ማንኛውም ህዝብ ለለውጥ እስከተነሳ ድረስ የሚሞትለት አላማ እንዳለውም ማሰብ ያስፈልጋል::

ባለስልጣናት ህጋዊ የሆኑ ዜጎች እንዲታሰሩ እንዲገላቱ የሚያደርጉት ከተጠያቂነት አያድናቸውም:; ህገመንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ዜጎችን በአገራቸው እና ህጋዊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማዋከብ ስልጣን ላይ ያለው ጁንታ ህግን እንደማያከብር ፍንትው አድርጎ ያሳየበት ህገወጥ ተግባር በተደጋጋሚ እያየን ነው:: ራሳቹህ ያወጣችሁትን ህግ ያላከበራችሁ እኛ እንዴት እናክብርላችሁ?? መጀመሪያ አንድ መንግስት ባለስልጣኖቹ ህግን አክብረው ለህዝቡ አርኣያ መሆን አለባቸው:: እያየን ያለነው ግን ሕግ አውጪው እና አስፈጻሚው አካል ህግን እየጣሰ መሆኑን ነው:: ስለዚህ ብልሃት አልባ ዲሞክራሲ በሞላባቸው እና የሰውን ልጅ መብት ትርጉም በማያቁ ባለስልጣናት ከመመራት ሞትን መርጦ መታገል አማራጭ እየሆነ ያለበት ዘመን ላይ ደርሰናል::

ከማናችንም ኢትዮጵያውያን በፊት ባለስልጣናት ህግ አውጪዎች ህግ አስፈጻሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች ለህግ ተገዢ ይሁኑልን::ለእኛም አርኣያ ይሁኑ::በጉልበት እና በሃይል በብልሃት አልባ ዲሞክራሲ ሽብር እየነዙ ሃገር አይመራም!!!ምንሊክ ሳልሳዊ

በወያኔ ዘርኝነት፤ ጎጠኝነትና ወደር የለሽ ጭቆና ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ጀርባዉ የጎበጠዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት ሁለት ወራት ዉስጥ በሁለት እጅግ አስቀያሚና ዘግናኝ በሆኑ የታሪክ ምዕራፎች ዉስጥ አልፏል። ለወትሮዉ በወርሃ ህዳርና ታህሳስ፤ ህዳር ሚካኤልንና የገና በዐልን እያከበረ አጆቹን ወደ ፈጣሪዉ የሚዘረጋዉ የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ዘንድሮ ከእነዚህ ሁለት የቆዩ ባህሎቹና ወጎቹ ፈቀቅ ብሎ በሁለት ክብሩን ባዋረዱና ማንነቱን ጥያቄ ዉስጥ በከተቱ ከስተቶች ልቡ ቆስሎ ከራሱ ጋር ሲነታረክ ሰንብቷል። የፈጠረዉን አምላክ መለምን እንጂ በፈጣሪዉ አማርሮ የማያዉቀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ . . . የሚያስብልኝ መንግስት እንደለሌለኝ አዉቃለሁ፤ አምላኬ ግን በፍጹም አይረሳኝም። ምነዉ ቅዱስ ሚካኤል አንተና ሰይፍህ እያላችሁ እንዴት እንዲህ ይደረጋል አንዴ . . . እያለ በምድራዊዉም በሰማያዊዉም መንግስታት ላይ የመረረ ጩኸቱን አሰምቷል።
በህዳር 2006 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ አገራቸዉ ዉስጥ የስራ ዕድል ተነፍገዉ ስራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ የተሰደዱ ወገኖቹ በሳዑዲ ፖሊስና ህዝብ ከፍተኛ በደል ሲፈጸምባቸዉ ተመልክቶ በኃዘንና በቁጭት ልቡ በግኗል። በተለይ ወንዶች ልጆቹ ፈለጊ እንደሌለዉ እንስሳ በየአደባባዩ ሲረገጡና ሲደበደቡ፤ ሴቶች ልጆቹ ደግሞ በየማጀቱ ሲደፈሩ ተመልክቶ ለህዝብና ለአገር ለሚያስቡ አስተዋይና ጨዋ መሪዎች ባለመታደሉ በባዕድ አገር ዉስጥ በደረሰበት ዉርደትና መከራ በአለም አቀፍ ደረጃ ጩኸቱን አሰምቷል።በዚሁ በ2006 ዓም በታህሳሰ ወር አጋማሽ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ የተጣለ የሰዉ ልጅ አጽም ቀርቶ በስመአብ ተብሎ የታረደ በሬ ስጋም ማየት በማይፈልግበት በገና ፆም ወቅት የገዛ ወገኖቹ አጽም በመንገድ ቆፋሪዎች ከመሬት ዉስጥ እየተጎተተ ሲወጣ አይቶ በቆሰለ ልብና በነደደ አንደበት “እባክህ ፈጠሪ ወይ ዉረድ ወይ ፍረድ” እያለ ከወያኔ ጋር ከመኖር የፈጣሪን ፍርዱን አለዚያም ዳግም ምጽአቱን ተመኝቷል።
ባለፉት ሁለት ወራት ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉ ግፍና መከራ ድፍን ህዳርንና ታህሳስን በአለም ዙሪያ በአራቱም ማዕዘን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ያሰባሰበ፤ ያነጋገረ፤ ያበሳጨ፤ ያስቆጨና አንጀት ያሳረረ ጉዳይ ነበር። አዎ የ2006 ህዳርና ታህሳስ አገር ዉስጥም ካገር ዉጭም ለምን መጡ የሚያሰኙ የቀን ጎደሎዎች ነበሩ። የወገኖቹ በባዕድ አገር አላግባብ መታሰር፤መደብደብና መገደል ያበሳጨዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ሀዘኑና ብስጭቱ ሳይላቀቅ ነበር ባለፈዉ ታህሳስ 18ትና 19 ቀን ሌላ አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና የጭንቅና የመከራ ጓዳ የሆነችዉን መዲናችን ከአዲስ አበባን አንደ ሐምሌ ጨለማ የከበባት። ደርግን አሸንፈዉ ስልጣን ሲይዙ ደርግ ገድሎ የቀበረዉን አስከሬን መቃብር እየቆፈሩ ያወጡት የወያኔ መሪዎች እነሱም በተራቸዉ በጅምላ ገድለዉ በብርድ ልብስ እየጠቀለሉ የቀበሯቸዉን ኢትዮጵያዉያን አስከሬን ዬት እንደቀበሩት እንኳን ሰለማያዉቁ እነሱ እራሳቸዉ እየቆፈሩ አዉጥተዉ ወንድሞቹና እህቶቹ እንደወጡ የቀሩበትን የኢትዮጵያን ህዝብ አንጀት እንደገና አቁስለዋል።
እዚህ ላይ አንድ እጅግ በጣም ሊያሳስበንና ሊያስጨንቀን የሚገባ ነገር ቢኖር ባለፈዉ ሳምንት ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ አካባቢ በብርድ ልብስ እንደተጠቀለለ የተገኘዉ የ6 ሰዎች አጽም ሊገኝ የቻለዉ ሆን ተብሎ የጅምላ መቃብር ለማግኘት በተደረገ ቁፋሮ ሳይሆን በአጋጣሚ ነዉ። ይህ የሚያሳየን አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ የአገራችን አካባቢዎች ዉስጥ መረጃ የተሰበሰባበቸዉንና የሚጠረጠሩ ቦታዎችን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ተባብሮ እየቆፈረ መፈተሽ ቢጀምር ወያኔ ጭካኔዉን ሊያሳየን ከሞከረዉ ከደርግ ስርዐት ጋር ምንም የማይለያይ ጨካኝና አረመኔ ስርዐት ለመሆኑ ማንም ማስተባበል የማይችለዉ ተጨባጭ ማስረጃ ይገኛል ብለን እናምናለን።
የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን በተቆጣጠሩ ማግስት ስራችን ብለዉ የጀመሩት ደርግ የሰለበዉን የኢትዮጵያን ህዝብ ሞራል ማደስ ወይም በሶሻሊዝም ስም የደቀቀዉን የአገራችንን ኤኮኖሚ መገንባት አልነበረም። የደርግ ሰርዐት አንደ ገለባ ሲበተን አብሮት የተበተነዉ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያሰራዊትም ቢሆን እንደጠላት የሚመለከቱት ኃይል ስለነበር ይህ ለእናት አገሩ ዳር ድንበር መከበር ደሙን ያፈሰሰ ሰራዊት የሚበላና የሚቀመስ አጥቶ ወደ መንገድ ላይ ለማኝነት ሲቀየር ሌላ ቢቀር ጡረታዉን እንኳን ለማስከበር ያደረጉለት ምንም ነገር አልነበረም። ወያኔዎች ስልጣን እንደጨበጡ የደረጉት አቢይ ነገር ቢኖር ከክፍለ ሀገር ክፍለ ሀገረ እየዞሩ ደርግ በቀይ ሽብርና በሌላም ሌላ ግዜ ገድሎ የቀበራቸዉን ሰዎች መቃብር እየቆፈሩ አጽም መሰብሰብ ነበር። በወቅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተከታታይ እንደተመለከትነዉ የወያኔ ጉድጓድ ቆፋሪዎች የሰነበተ መቃብር እየከፈቱና አጽም እየሰበሰቡ ደርግ ምን አይነት ጨካኝ ነብሰ ገዳይ እንደሆነ ለአመታት የምናዉቀዉን እዉነት እንደገና እንድናዉቀዉ አድርገዉናል። በዚህ ከአንድ አመት ከመንፈቅ በላይ በዘለቀዉ የወያኔ መቃብር ቁፋሮ ወያኔ የቀድሞዉን ንጉስ የቀዳማዊ ኃ/ስላሤን ጨምሮ የብዙ ሰዎችን የመቃብር ቦታ እየቆፈረ እሱ ለፖለቲካ ፍጆታዉ የሚፈልጋቸዉንና በተለይ ደግሞ የኔ ናቸዉ የሚላቸዉን ሰዎች አጽም እየለቀመ አንደገና በክብር እንዲቀበሩ ሲያደርግ ሌሎቹን የደርግ ሰለባዎች ደግሞ ምሶ ያወጣዉን አፈር አንደገና መልሶባቸዋል። እንደዚህ አይነት ጉድ የተመለከትነዉ ከሃያ ሁለት አመታት በፊት ወያኔ ኢትየጵያን ሲቆጣጠር ነበር።
ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ዉስጥ መንገድ የሚሰሩ ሰዎች ለራሳቸዉ ጉዳይ መሬት ሲቆፍሩ ከተጠቀለሉበት የደብረ ብርሀን ብርድ ልብስ ዉስጥ እየዘለሉ ወጥተዉ “የፍትህ ያለህ” እያሉ ሲጮኹ የሰማናቸዉ አጽሞች ወያኔ በእኔ ዘመነ መንግስት ሰዉ በሰዉነቱ ይከበራል እንጂ እየተጎተተ አየገደልም ብሎ ከማለ በኋላ በራሱ በወያኔ በግፍ እየተጎተቱ ተገድለዉ የተጣሉ ዜጎች አጽም ነዉ። ይህንን በታሪካችን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ በስፍራዉ ተገኝተዉ የተመለከቱ የአይን ምስክሮች እንደተናገሩት ቦታዉ ዘመናዊ የመቆፈሪያ ማሽኖች በመቆፈር ላይ እያለ በመጀመሪያ አራት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለዉ ወደላይ ሲወጡ የታዩ ሲሆን፤ በሁኔታዉ የተደናገጡት ቆፋሪዎች ስራቸዉን አቋርጠዉ ወደ ቤታቸዉ ከሄዱ በኋላ በነጋታው ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ሌላ ቁፋሮ ሲያደርጉ አሁንም እንደገና በተመሳሳይ ሁኔታ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ ስድስት አስከሬኖች አግኝተዋል።
አንድ አስከሬኖቹ በተገኙበት አካባቢ በብዛት ተገኝቶ ሁኔታዉን ይመለከት የነበረዉን ህዝብ ለማባረር ወታደሮቹን አስከትሎ የመጣ ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንን “ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ አይቻልም፤ ሆኖም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው” በማለት የዘረኞቹን የወያኔ መሪዎች አይን ያወጣ ወንጀል ለመደበቅ ሲሞክር ተደምጧል። ሆኖም ሁኔታዉን በቅርብ ሆኖ የተከታተለዉም ሆነ በርቀት ሆኖ በምስል የተመለከተ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወንጀሉ የሌሎቹ መንግስታት ሳይሆን የወያኔ መሆኑን ለመገንዘብ ግዜ አልወሰደበትም። አስከሬኖቹ በጅምላ የተጠቀለሉበት የደብረ ብርሀን ብርድ ልብስም ቢሆን እንኳን መሬት ዉስጥ ተቀብሮ ምስጥ፤ እርጥበትና ዘመን ተፈራርቀዉበት፤ አልጋ ላይ ህያዉ ሰዉ ለብሶትም ቢሆን ሃያ አመት ቀርቶ አምስት አመትም የሚቆየዉ የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎች ለብሰዉት አንደመጡት ቁምጣ በመርፌ ከተጠቋቆመ ብቻ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት አርብና ቅዳሜ አስር አስከሬኖችን እንዳቀፈ ከመሬት ዉስጥ ሲወጣ ያየነነዉ ብርድል ልብስ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያዉያንን በሚስጢር እየገደለ እንደ ቆሻሻ ዕቃ ዬትም ቦታ መጣሉን እንዳማያቆም ነዉ።
የአገራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀይማኖት የሚሰጠዉ ቦታ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ። በእስልምናዉ፤ በክርስትናዉም ሆነ በአይሁድ ሀይማኖቶች አስተምህሮ በሀይማኖት ዉስጥ ሁለቱ ዋና ዋና አካሎች እግዚአብሄርና ሰዉ ናቸዉ፤ ይህ የሚያሳየን ሰዉ ክቡር ፍጡር መሆኑን ነዉ። ወደዚህ አለም ሲመጣም ሆነ ይህችን አለም ሲለይ በከብር መጥቶ በክብር የሚሸኝ የሰዉ ልጅ ብቻ ነዉ። የኢትዮጵያ ክርስትና እምነት መሰረት ከሆነችዉ ከትግራይ ክልል የመጡት የዛሬዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ግን ክርስትናዉን ብቻ ሳይሆን የራሳቸዉንም ሰዉ መሆን የረሱ ይመስላል። ሰዉን የመሰለ ክቡር ፍጡር በጅምላ ተገድሎ፤ በጅምላ ከተቀበረበት ቦታ በኮንስትራክሺን ሠራተኞች ከመሬት ዉስጥ እየተጎተተ መዉጣቱን የሰሙ የወያኔ መሪዎች ጉዳዩን አስመልክቶ አንድም ትንፍሽ ያሉት ቃል የለም። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በእነሱ ቁጥጥር ስር ያሉት የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥንም እነማን እንደሆኑ፤ መቼ እንደሞቱና ማን እንደገደላቸዉ የማይታወቅ ሰዎች አስከሬን በብርድልብስ ተጠቅልሎ ሲገኝ ያንን ለስድብና ህዝብን ለመኮነን ቀኑን ሙሉ የሚከፍቱትን አፋቹዉን መክፈት አልፈለጉም። የሚገርመዉ እንደ አለባሌ ነገር ከተጣሉበት ቦታ ተጎትተዉ የወጡት አስከሬኖች ሁኔታና የተጠቀለሉበት ብርድልብስ ሙሉ በሙሉ ወንጀሉን ወያኔ ላይ ስለሚያመለክት ነዉ እንጂ የእነሱ እጅ የሌለበት ወንጀል ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሳምንት ሙሉ ሌላ ዜና አይሰማም ነበር።
አገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገሮች የሚኖረዉ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ባለፈዉ ሳምንት እንደ ዋዛ ከመሬት ዉስጥ እየተጎተቱ የወጡ ወገኖቹን አስከሬን ጉዳይ በቀላሉ መመልከት የለበትም። ወያኔ ስልጣን እጁ ከገባ ጀምሮ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን እያፈነ በየማጎሪያ ቤቱ አጉሯቸዋል። ከሰሞኑ ጃንሜዳ አካባቢ ያየነዉ ዘግናኝ ክስተት ስለእነዚህ ወያኔ በየድብቅ አስር ቤቶች አስሮ አድራሻቸዉ ስለጠፋ ዜጎቻችን ብዙ የሚለዉ ነገር ያለ ይመስለናል። እኛ ነን አድራሻቸዉ የጠፋ ሰዎች እያልን የምንጨነቀዉ እንጂ እነዚህ ወያኔ አስሯቸዉ አድራሻቸዉ የጠፋ ሰዎች ዬት እንዳሉ ጃንሜዳ አፉን ከፍቶ ነግሮናል። አዲስ አበባና በየከተማዉ የሚኖረዉ ህዝብ ስለወያኔ የጅምላ ግድያ የሚያዉቀዉ ብዙ ሚስጢር ይኖራል፤ በጅምላ ተገድለዉ በጅምላ የሚቀበሩ ሰዎችንም ጉዳይ በተመለከተ ማንም ሰዉ ሳያየዉና ሳያዉቀዉ የሚፈጸም ነገር አይመስለንምና ከአሁን በኋላ ጥረታቻን ሁሉ የወያኔ የጅምላ ግድያዎች በብሄራዊና በአለም አቀፍ አካላት እንዲመረመሩና ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ መሆን አለበት። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ያላቸዉ ዜጎች መረጃዎቻቸዉን ማሰባሰብ፤ማደራጀትና ለሚመለከተቸዉ አካላት መስጠት ይኖርባቸዋል። ዬት እንደደረሱ ሳናዉቅ ባለፈዉ ሳምንት ሳይተሳብ በደብረህርሃን ብርድ ልብስ እንደተጠቀለሉ ከመሬት ዉስጥ የወጡ ዜጎቻችን ፍትህ ሳያገኙ ማንም ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ ሊወስደዉ አይገባም።

ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው።

እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።

በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።

ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።

ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል። ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።

ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ። የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል።

ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው።

የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡ የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው።

በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!

ነገርግን በህብረት ለሀገር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ የትዉልድና የሀገር ክብር ነዉ!!!

ከጎልጉል የተወሰደ

ኢትዮጵያዊነት የሚለው ቃል እኮ የኢያንዳንዳችን መከበሪያ እና መኩሪያ እንጂ ማፈሪያ አይደለም::ለአመታት ታገልን የሚሉ ከወያኔ ጎን እየፈሉም ያሉ እና የከሰሙ የብሄር ድርጅቶች በታገሉባቸው አመታቶች ከወሬ ውጭ ለሃገሪቱም ይሁን ለሚጠሩት ብሄር ምንም የፈየዱት ነገር የለም:: ያመጡትም ነጻነት የለም ይብሱኑ እርስ በእርስ ከማጨፋጨፍ ውጪ እና ህዝብን ለእልቂት ከመዳረክ ውጪ ምንም ያመጡት ውጤት የለም:: በብሄር ስም መታገል እና ዘረኝነት ማራመድ ለብሄራዊ ጭቆና በር መክፈት ነው :: ገዢው ፓርቲን ሕወሓትን እንኳን ብትመለከቱት ለትግራይ ህዝብ የፈጠረው አዲስ ነገር የለም:: የትግራይ ህዝብ በዘመናዊ ጭቆና ፍዳውን እያየ ነው::

እኛ በጋራ እስካልታገልን ድረስ ለውጥ አይመጣም:: ከሃገር ሲወጡ የወያኔን ጽዋ ጠጥተው እዚህ ከመጡ በኋላ የሚከረበቱ አስመሳይ ተለጣፊ ፖለቲከኞችን ማስወገድ ግዴታችን ነው:: ኢትዮጵያዊነት የሚለው ቃል እኮ የኢያንዳንዳችን መከበሪያ እና መኩሪያ እንጂ ማፈሪያ አይደለም:: ከሌላው አለም የምንወስደው ትምህርት ምንድን ነው??ሌላው ዜጋ ሃገሩን እና ሌላውን ወገኑን እንዴት ነው የሚወደው?? የዘር እና የቀለም ልዩነት እየተወገደ በሚሄድበት በዚህ በሰለጠነው አለም ላይ ትላንትን እያሰብን የምንኖር ሰዎች ግንዛቤያችንን ማስፋት ይጠበቅብናል::

ኢትዮጵያ ምን አደረገችልኝ የሚል አነጋገር የሚናገሩ ጠባብ ብሄርተኞች አላማቸው የት ላይ እንደሚያርፍ ራሳቸው አያውቁትም::ኢትዮጵያ እኮ አንዲት ግኡዝ አካል ነች :: ተንቀሳቅሳ ላንተ ላንቺ እና ለእናንተ የምትፈይደው ነገር የለም ምድሯን እየረገጥን እየተማርን እየኖርን ያለነው እኛ ነን ::የእኛ ስራ ደሞ አገርን ከክፉ ገዢዎች አድነን ራሳችንን ነጻ በማውጣት የወገንን እምባ ማበስ እንጂ በወገን እንባ እና ደም መነገድ አላስፈላጊ ኪሳራ ያስከትልብናል ለኢትዮጵያ ምን ሰራሁላት ለወገኔ ምን አደረኩለት ብለህ ጠይቅ እንጂ እንደ ከብት አታጓራ:: በህዝብ ጥያቄ ስም ተደብቆ ጠባብነትን ማራመድ ክሽፈትን ያመጣል እና እንጠንቀቅ:: በየትኛውም አገር ያለን ኢትዮጵያውያን በጡት ነካሾች የታሰበውን ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ልንቃወም ይገባል::ምንሊክ ሳልሳዊ

አምስተኛው ዙር አገር አቀፍ ‹‹ምርጫ›› እንደወትሮው ሁሉ በቀጣዩ ዓመት ሊደረግ በዕቅድ ተይዟል፤ ወሬውም ከወዲሁ ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው፤ ኢህአዴግም በበኩሉ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ከቀደመው በበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሴራ ፈትሎ በመግመድ ውሎ ማደሩን ገና በማለዳ እያቀላጠፈው መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ (ከልቡ ባይሆንም) በ1996 ዓ.ም ወርሃ ሐምሌ ላይ በተደረገ የግንባሩ ጉባኤ ‹‹የሚቀጥለው ምርጫ እንከን-አልባ ይሆናል›› ሲል ‹ቃል› ገብቶ የነበር ቢሆንም፣ ከስድስት ዓመት በኋላ በተካሄደው አራተኛው ዙር ‹‹ምርጫ›› በግላጭ ‹እንከን-አልባ ድል› በሚል ሲቀይረው ቅንጣት ታህል ሀፍረት

አልተሰማውም ነበር፡፡ ግና! ‹አንድ ለእናቱ› እንዲል አቤ ጎበኛ፣ የተቃውሞውን ስብስብ የምትወክል አንዲት ወንበር ሾልካ ወደ ምክር ቤቱ በመግባቷ፣ ፓርቲው ዛሬም ድረስ እንደ እግር እሳት እያንገበገበችው መሆኑን በተለያየ መንገድ እያሳየን ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ኢህአዴግ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረግው ‹‹ምርጫ›› እንዲህ አይነት ‹እንዝህላልነትን› ለማረም በከፍተኛ ዝግጅት መጠመዱን የሚጠቁሙ መረጃዎች እያፈተለኩ ነው፡፡ መቼም የጉዳዩ እውነትነት ከተረጋገጠ፣ ምናልባትም በ2012 ዓ.ም ልክ እንደ ኤርትራ ወይም እንደ ቻይና ‹ልማታዊ መንግስት እንጂ ምርጫ የሚባል ነገር አያስፈልግም! የምርጫ ፖለቲካ የኒዎ-ሊበራሊስቶች አጀንዳ ነውና!!› ከማለት የሚመለስ አይመስለኝም፡፡ ማን ያውቃል? …እንዲህ እንደዛሬው የሶስት ሺ ዓመት ታሪክ ያላትን እና የዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ አገርን ፍርሃት በመንዛት አሸንፎ ከቆየ የምናየው ይሆናል፡፡

ከዚህ ባለፈ ቀጣዩን ‹‹ምርጫ›› በፍፁማዊ ጠቅላይነት ለመጨረስ እያደረገ ያለው መሰናዶ በሶስት የተከፈለ ነው፤ የመጀመሪያው ለመላው የድርጅቱ አባላት (የመንግስታዊ ተቋማት ኃላፊዎችን ጨምሮ) የተዘጋጀው ፓኬጅ ነው (ሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች ስለ ‹አውራ ፓርቲ› አስፈላጊነት እና የ‹ልማታዊ መንግስት›ን ጠቀሜታ በተመለከተ እየተሰጠ ያለው ሥልጠናም የዚሁ አካል እንደሆነ ሰምቻለሁ)፤ ሁለተኛው መራጩ ሕዝብ ላይ በተናጥል አተኩሮ ለመተግበር እየተሞከረ ካለው ቀመር ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ ይህም እንደ ቀድሞው ሁሉ ለአቅመ-ምርጫ የደረሰውን ህዝብ በኮንዶሚንየም፣ በመልካም አስተዳደር እና በማይጨበጡ የተስፋ ፕሮፓጋንዳዎች ማማለልን የሚያካትት ነው፤ የመጨረሻው ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የግሉ የህትመት ሚዲያ ላይ ያነጣጥራል፤ በዚህ ፅሁፍም አጀንዳ የምናደርገው አገዛዙ በዚህኛው ግንባር ከሚያስወነጭፋቸው የ‹ጦር መሳሪያዎች› በዋነኛነት በዘጋቢ ወይም በዶክመንተሪ መልክ የሚያዘጋጃቸው ፊልሞችን የተመለከተ ነው፡፡

ስውሩ አጀንዳ…
በርግጥ ይህ አይነቱ አሰራር ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ ባለፉት ሃያ ዓመታት በሙሉ ሲተገበር የነበረ ነው፡፡ በተለይ ሕዝባዊ ተቃውሞን

የመሰለ ለሥልጣን የሚያሰጋ ድንገቴ አጋጣሚ ሲከሰት የሚመረቱት ፊልሞች ቁጥርም እንዲሁ ይጨምራል፤ እንደ ምሳሌም የ1993ቱን የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ በየአካባቢው የሕዝብ ማጉረምረም በበረታበት ወቅት፣ የሰሜን አፍሪካ አብዮት በጋመበት ማግስት እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ሕገ-መንግስታዊው የኃይማኖት ነፃነት እንዲከበርላቸው በአደባባይ በጠየቁባቸው ጊዜያት በ‹‹ዘጋቢ ትዕይንት›› ስም የተሰራጩትን ብቻ መመልከቱ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ (በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ጭብጥ ያላቸው ፊልሞች ደራሲያን፣ የስርዓቱ ዋነኞች ‹ኤጲስ-ቆጶሳት› እንጂ ተቋሙ የሰበሰባቸው ብላቴና ልማታውያን ጋዜጠኞች አይደሉም)

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት ‹ዶክመንተሪ ፊልሞች› የሚዘጋጁት በሁለት መንገድ ነው፤ የመጀመሪያው በኢቲቪ ባልደረቦች ሃሳብ አመንጪነት በፕሮፓጋንዳ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ይሁንታን ሲያገኝ እንዲተላለፍ የሚደረግ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ በጉምቱ የፓርቲው መሪዎች የጭብጥ አሰናጅነት ሙሉ ድራማው አልቆለት በቀጥታ አየር ላይ እንዲውል ወደ ጣቢያው የሚላከው ነው፡፡ በዚህ ዘውግ የሚመደቡት አብዛኛዎቹ ፊልሞች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ በግል ሚዲያ ላይ የተሰማሩ ጋዜጠኞችን፣ የኃይማኖት መሪዎችን እና ዓለም-አቀፍ ተቋማትን በመወንጀልና በመዝለፍ ላይ የሚያውጠነጥኑ ናቸው (የቅርቦቹን እንኳ ለማስታውስ ያህል ብንጠቅሳቸው ይህንኑ ያስረግጣሉ፡- ‹አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ›፣ ‹አኬልዳማ›፣ ‹ጀሀዳዊ ሀረካት›፣ ‹ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ› እና የመሳሰሉት)

በጥቅሉ እስከ 2004 ዓ.ም መገባደጃ ድረስ የእነዚህ ፊልሞች ደራሲ አቶ መለስ ዜናዊ የነበረ ሲሆን፤ ከእርሱ ህልፈት በኋላ የኮሚኒኬሽን መ/ቤት (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪዎች) በደህንነት እና ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ስም

እንደሚያዘጋጁት ውስጥ-አወቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ኢቲቪ በእንዲህ አይነት ጭብጥ ዙሪያ በሚያውጠነጥኑ ፊልሞች ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ አያደርግም፤ ሳይቀንስና ሳይጨምር ለሕዝብ ማስተላለፍ አማራጭ ያልተተወለት ብቸኛ ግዴታው ነው፤ የህወሓቱ ሰው ገራገሩ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ዘርዓይ አስግዶምም ቢሆን ይህ ኃላፊነት ሲሰጠው ትጉህ አገልጋይነቱ ለማን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቀዋልና፣

በፍፁም ፈቃደኝነት ሥራውን ከማሳለጥ በቀር የሚቃወምበት ወይም የኤዲቶሪያል ነፃነቴን አላስገፋም ብሎ የሚቀብጥበት አንዳች ምክንያት የለውም፡፡ በግልባጩ ውዳሴ መለስ፣ ስደት፣ የአባይ ቁጭት፣ የኮንዶሚንየም ቤቶችንና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ ሩቅ አላሚዎቹ ‹‹ልማታዊ ጋዜጠኞች››፣ እንቅልፍ አጥተው የሚጨነቁበትና እርስ በእርስ ለመቀዳደም የሚተጉበት አጀንዳ ስለመሆኑ ራሱ በረከት ስምዖንም ገና ድሮ የገባው ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በየጊዜው ጥቂት የጣቢያው የተለያዩ ፕሮግራም አዘጋጆች እና የዘጋቢ ፊልም ባለሙያዎች የቻይናን የሚዲያ ተሞክሮ አጥንተው እንዲመጡ እንደሚደረግ ይታወቃል)

ለዚህ ፅሁፍም እንደ ማሳያ የምጠቅሰው፣ ባለፈው ሳምንት ‹‹ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ለተመልካች የቀረበው ዘጋቢ ፊልም፣ ሙሉ በሙሉ በብሔራዊ መረጃ መ/ቤት ስም የተዘጋጀ ሲሆን፣ በንባብ የተሳተፉት ሁለቱ ‹‹ጋዜጠኞች››ም የኢቲቪ መደበኛ

ባልደረቦች እንዳልሆኑ ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ፡፡ ምንም እንኳ የፊልሙ ‹ባለቤት› የሆነው የደህንነት ቢሮ በሽብርተኝነት ዙሪያ የሚያውጠነጥን ነው ቢለንም፣ እንዲተላለፍ የተፈለገው ዋነኛ መልዕክት በቀጥታ ከቀጣዩ ምርጫ ጋር የተያየዘ ነው ወደሚል ጠርዝ የሚገፉንን ማሳያዎች መምዘዝ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ እንዴት ሆኖ? የሚለውን ጥያቄ በአዲስ ርዕስ ሥር እናፍታታው፡፡

ከፍርሃት ጋር ወደፊት!

በዚህ ፊልም ላይ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው የቀረቡት ሶስት ሰዎች ናቸው፤ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሽመልስ ከማል (ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በእንዲህ አይነት ፊልሞች ላይ የመሪ-ተዋናይነትን ገፀ-ባህሪ ወክሎ መጫወቱን እየተካነው እንደሆነ እኔም ራሴ እመሰክርለታለሁ¡)፣ የፌደራሉ ዋና ዓቃቢ-ሕግ ብርሃኑ ወንድማገኝ እና አቶ ዘሪሁን ተሾመ (ይህ ሰው ደግሞ አሉባልታና ጠቀሜታቸው ረብ-የለሽ የሆነ ወሬዎችን በማቅረብ የሚታወቀው የ‹ዛሚ-90.7› ሬዲዮ ባለቤት ሚሚ ስብሃቱ የትዳር አጋር ነው) ከትዕይንቱ መካከል የሚታወሱ ፊቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ድራማው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ተሰፍሮ የተሰጣቸውንና በፈጠራ ታሪክ የተሞላውን ‹ስክሪፕት› ቃል-በቃል ሸምድደው መምጣታቸውን በግልፅ በሚያሳይ መልኩ ሲያነበንቡ ላስተዋላቸው ተመልካች ‹‹ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች›› የጣሉባቸውን ግዴታ በቁርጠኝነት ለማስፈፀም ‹ቀራኒዮ› ድረስ የሚጓዙ ሊመስለው ቢችል አይፈረድበትም¡ መቼም አገዛዙ ዓለማዊ ፍላጎታቸውን እስካሟላላቸው ድረስ ሀገር፣ ሕገ-መንግስት፣ ሕሊና… ደንታ ሳይሰጧቸው ሕዝብን በማሸበር የስርዓቱ ዕድሜ ይረዝም ዘንድ ‹ከፍርሃት ጋር ወደፊት!!› ለማለት የማያመነቱ ሰዎችን በዙሪያው የኮለኮለው ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ፊልሙ ከቀድሞዎቹ አንፃር እንኳ ሲመዘን የወረደና አሰልቺ ቢሆንም፣ ያን ያህል ከተደሰኮረለት የ‹‹ሽብርተኝነት ጉዳይ›› ባሻገር ሁለት ያደፈጡ ስውር ዓላማዎች ያሉት ይመስለኛልና፣ እነርሱን ነጣጥለን እንመልከት፡፡

የቀደሙ ልምዶችን ተንተርሰን ስናብሰለስለው፣ የዘጋቢ ትዕይንቱ ድብቅ ዓላማ ተደርጎ ሊጠቀስ የሚችለው የመጀመሪያው የቢሆን ሃሳብ፣ ኢህአዴግ ከምርጫው መዳረሻ በፊት በተቃውሞ ፖለቲካው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የተወሰኑ የአመራር አባላትን እና ጥቂት ጋዜጠኞችን እንደተለመደው ከግንቦት 7 ጋር አቆራኝቶ ለማሰር እየተዘጋጀ ነው የሚል ይሆናል፡፡ በርግጥም ይህንን መከራከሪያ ከመቀበል ሌላ አማራጭ የሚያሳጡ ሁለት ገፊ ምክንያቶች አሉ፤ አንዱ ፓርቲው ቀጣዩን ምርጫ ከትግል ዘመኑ ጀምሮ ይመራው ከነበረው ጉልበታሙ አቶ መለስ ውጪ የሚያደርገው መሆኑ ያሳደረበት ስጋት ወደ ጭፍን አምባገነንት እንዲቀየር ከማስገደድ አልፎ፣ ይህንኑ የሰውየውን ህልፈት ተከትሎ የተከሰተው የኃይል መከፋፈል ያነበረው የመሳሳት ተፅእኖ ይመስለኛል፤ እነዚህ ኩነቶችም ስርዓቱ ህልውናውን ካፀናበት አምባገነናዊ ባህሪው አኳያ ድንገቴ እርምጃ እንዲወስድ መግፋታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ካደረ ተሞክሮው የሚነሳ ነው፤ ይኸውም በ2002ቱ ምርጫ ዋዜማ በተልካሻ ምክንያት የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ሊቀ-መንበር የነበረችውን ብርቱካን ሚደቅሳን እስር ቤት በመክተት ፓርቲውን እና የተቃውሞ ደጋፊ ኃይሉን እስረኛ በማስፈታት አጀንዳ እንዲጠመድ ያደረገበት ስልት እና ሁነቱ የፈጠረው ማሕበረሰባዊ የፍርሃት ድባብ ያስገኘለት ጠቀሜታን ሊከልሰው መሞከሩ አይቀሬ መሆኑ ነው፡፡ በአናቱም በወቅቱ ከፍተኛ ተነባቢነት የነበራትን የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ አዘጋጆች ምርጫው አራት ወር ብቻ ሲቀረው በግልፅና ስውር ጫና ጋዜጣውን ዘግተው ከሀገር እንዲሰደዱ ያደረገበት መንገድም የዚሁ አፈና ጉትያ እንደነበረ አለመዘንጋቱ፣ በቅርብ ከሚፈጠሩ ተመሳሳይ ክስተቶች ጋር ለማያያዝ ያስችላል፡፡

ሌላኛው የዘጋቢ ፊልሙ ዓላማ በቀጣዩ ምርጫ ለውጥ ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል ወደ ተቃውሞ ጎራ ሊያሰባስብና መነቃቃት ሊፈጥር ይችላል የሚል ብርቱ ጥርጣሬ ያሳደረበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጣቢያን በመርገም (በሽመልስ ከማል አነጋገር ‹‹ውጉዝ ከመአርዮስ›› በማለት) የተቀናቃኝ ድምፆች በተከበበላቸው ሞገድ ብቻ እንዲሰሙ ማስገደድ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ አገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና ጋዜጠኞች ለጣቢያው ቃለ-ምልልስ እንዳይሰጡ በፍርሃት ቆፈን መሸበብንም ያከተተ ነው፡፡ አስደንጋጩ ጉዳይ ደግሞ መከራከሪያ ሆኖ የቀረበው ሕገ-መንግስታዊው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሳይሆን፣ ለሚዲያ ተቋሙ የብሶት መግለጫዎችን መስጠትም ሆነ ኢ-ፍትሀዊ አሰራርን ማጋለጥ በሽብርተኝነት እንደሚያስከስስ የሚተርክ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም››

መሆኑ ነው፡፡ በርግጥ ለዚህ ማስፈራሪያ እንደ መደገፊያ የተጠቀሙት ፀረ-ሽብር ሕጉ በግብረ-አበርነት ተጠያቂ የሚያደርግበትን የተለጣጭነት ባህሪውን አፅንኦት በመስጠት እንደነበረ ታዝበናል፡፡

በፊልሙ ላይ አቶ ዘሪሁን ምሬት በዋጠው ድምፅ ‹‹ኢሳት የግንቦት 7 ወፍጮ ነው!›› የሚል መፈክር ሲያሰማ፣ ሽመልስ ከማል ደግሞ የአዋጁ ዋነኛ ዓላማ ከዚህ ቀደም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ‹አሸባሪ› ተብለው ከተፈረጁት ድርጅቶች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖር ለማድረግ እንደሆነ ምሎ-እየተገዘተ ተመልካቹን በፍርሃት ለማንበድበድ ሲሞክር ተስተውሏል፡፡ ይሁንና የአቶ
ሽመልስን እርግጠኛነት ለማመን አመክንዮ መጠቀም የግድ ይሆናል፤ እናም ኢሳት የእነዚህ ድርጅቶች ዓላማ አራማጅ መሆኑን ለማሳየት ምን ተጨባጭ ማስረጃ አቀረባችሁ? ለሚለው ጥያቄ እየነገሩን ካለው እንቶ-ፈንቶ ባለፈ በማስረጃ የተደገፈ መልስ መስጠት የሚኖርባቸው ይመስለኛል፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የኤርትራ መንግስት ከሰጠው አምስት መቶ ሺህ ዶላር ውስጥ ሁለት መቶ ሺውን ለኢሳት ሥራ ማኪያሄጃ እንዲውል መወሰኑን በስልክ ሲናገር ከማሰማት በዘለለ ማለቴ ነው፡፡

እግረ-መንገድ ለመጥቀስ ያህል የዚህ ፅሁፍ ዓላማ ኢሳትን መንግስት ለምን ወነጀለው በሚል ግብረ-መልስ መስጠት አለመሆኑን ማስገንዘቡ አስፈላጊ ይመስለኛል፤ መነሻ ምክንያቴ እንደ ሚዲያ ተቋምነቱ ከእኔ ሞያ ጋር በቀጥታ መገናኘቱ ሲሆን፤ ለምን ይህ ሆነ? ያልኩበት ተጠየቅም የሕግ የበላይነት ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም የተመለከትነው ፕሮግራም ኢሳት እስከ ዛሬ ባሰራጨው ዘገባ ላይ ‹አሸባሪ› ሊያስብለው የሚያስችል ትዕዛዝ ያስተላለፈበትን ወይም ንፁሃን ኢትዮጵያውያንን በተጠመደ ፈንጂ ዶግ-አምድ እንዲሆኑ መቀስቀሱን የሚያጋልጥ ሳይሆን፣ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ከተደራጁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ጋር ያደረገውን ቃለ- መጠይቅ ብቻ በመደጋገም ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የዘጋቢ ፊልሙ ድብቅ ዓላማ ስርዓቱ በሀገር ውስጥ ያሉትን ጥቂት የግል የሕትመት ሚዲያዎች በፈርጣማ የፖለቲካና ቢሮክራሲ ክንዱ ደቁሶ ካኮሰመነ በኋላ፣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ድምፅ ላጡት ድምፅ መሆን እየቻለ የመጣውን እና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አማራጭ የሚዲያ ምህዳር የፈጠረውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተለመደው የአፈና መንገድ /ጃሚንግ/ በተለየ ስልት ከጨዋታ ውጪ ለማድረግና በቀጣዩ ምርጫ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ለማስጠበቅ የሚያደርገው ዝግጅት ነው እንድንል የተገደድነው፡፡

ከዚህ ቀደም እነ እስክንድር ነጋ በግንቦታ 7 አባልነት ተወንጅለው በታሰሩበት ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ለፓርላማው ‹‹ክምር ማስረጃ አለን›› ቢልም፣ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ግን በጨበጣ እንደገባበት ማየታችን አደባባይ የወጣ ሀቅ ነበር፤ በርግጥም ማስረጃ ሆኖ የተቆጠረው ራሱ ያዘጋጀው ‹‹አኬልዳማ›› የሚል ‹‹ዘገቢ ፊልም›› እንደነበረ ስንመለከት፣ ይህ ስርዓት አስቀድሞ የተናገረበት ጉዳይ ስህተት መሆኑ እንዳይጋለጥ ምንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለስ እንታዘባለን (በነገራችን ላይ በወቅቱ በፍትህ ጋዜጣ ‹‹አኬልዳማው! የአይሁድ ወይስ የኢህአዴግ?›› በሚል ርዕስ የዘገባውን ፈጠራነት በተጠናከረ ማስረጃ ለማጋለጥ ከተሞከረ በኋላ እንዲህ የሚል ምክር አዘል ቁም-ነገር ተላልፎ እንደ ነበር አይዘነጋም፡-

‹‹ሆሊውድ የሚሰሩ አስፈሪ (ሆረር) ፊልሞች እንኳ ቢያንስ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች እንዳያዩአቸው የሚከለክል ሕግ አለ፣ ኢቲቪ ግን የተበጠሰ አንገት፣ የተገነጠለ ክንድ፣ የተቆረጠ እጅ፣ የተፈረከሰ ጭንቅላት… እያሳየ፣ ‹13 ዓመት የሞላው ሕፃን በሙሉ ሊያየው ይችላል› ማለቱ ኃላፊነት የጎደለው አሰራር ነው››

ባለፈው ሳምንት በቀረበው ፊልም ላይ ቢያንስ ይህ ሁኔታ ታርሞ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ሊያዩት እንደማይገባ ከሚያስጠነቅቅ መልዕክት ጋር መተላለፉ ስርዓቱ ምክር መስማት ጀመረ እንዴ? እንድንል የሚያጭር ነው፡፡ በርግጥም በሌሎች ጉዳዮችም እንዲህ ቢያዳምጡን ኖሮ፣ እየዋጣቸው ካለው ጥልቅ ጨለማ ራሳቸውን መታደግ የሚችሉበት በርካታ ዕድል ነበር፡፡)

የሆነው ሆኖ በዚህና መሰል ፊልሞች ላይ የሚነሳው ሌላው ለትዝብት የሚያጋልጠው ጉዳይ የደህንነት ተቋሙ ሁሉንም ዜጋ አብጠርጥሬ አውቃለሁ የሚለው ማንአህሎኝነቱ ነው፡፡ አስቂኙ ጉዳይ ግን በአዋጅ የተቋቋሙት የመረጃው መስሪያ ቤት እና የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል፣ ያሻቸውን ዜጋ ቤት (በስውርም በግልፅም) መበርበር፣ ስልክ መጥለፍ፣ የኢ-ሜል እና የማሕበራዊ ሚዲያዎችን አካውንት ‹የሚስጥር ቁልፍ ቃላት› ሰብሮ መፈተሽ… ከሚያስችል ያልተገደበ ሥልጣን ጋር የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እንደ አዋጭ መፍትሄ የወሰዱት ‹ዶክመንተሪ ፊልም›ን እስኪመስል ድረስ በሳምንት አንዴ መመልከቱ የተለመደ መሆኑ ነው፡፡ ርግጥ እንዲህ አይነት ትዕይንቶች ተጨማሪ ስርዓታዊ ጠቀሜታቸው ማህበራዊ ተቀባይነታቸው የጎላ ዜጎችን በስቅየት (ቶርቸር) እያንበረከኩ በቴሌቭዥን መስኮት አንገት አስደፍተው በማቅረብ ትውልዱ ተጠራጣሪና ድንጉጥ እንዲሆን ያላቸው አስተዋፆኦ አንዱ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ይህው ቃል በሚከሰሱት ንፁሀን ላይ ተመልሶ እንደ ማስረጃ ተቆጥሮ፣ ከአስር ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ የሚደርስ ቅጣት በ‹ካንጋሮው› ፍርድ ቤት እንዲጣልባቸው የሚያደርገው ግፈኝነት ነው፡፡ ለዚህም ቅጥ ያጣ አምባገነንነት አይደፈሬ ሥልጣኑ የሰጠውና ገና ሲረቅቅ ጀምሮ ጠንካራ ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረውን የፀረ-ሽብር አዋጅን የሕጋዊነት ከለላ አድርጎ እየተባባሰ በመጣ መልኩ መጠቀሙን መቀጠሉ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የታተመው ‹‹ኒውስ ዊክ›› መፅሄት ‹‹Ethiopia declares war on [deleted] men›› በሚል ርዕስ ባስነበበው አደገኛ መጣጥፍ አዋጁን ያብጠለጠለበት ሀረግ የትችቶቹን ሙሉ መንፈስ የሚጠቀልል ይመስለኛልና እዚህ ጋር ልጥቀሰው፡-

‹‹የፀረ-ሽብር ሕጉ መንግስት ሽብርተኝነት ብሎ የሚያስበውን ጉዳይ በ‹መፃፍ፣ ማቀናበር፣ ማተም ወይም ማሰራጨት› የሚከሰውን ዜጋ በሃያ ዓመታት እስር እንዲቀጣ ፈቅዶለታል፡፡››

እነዚህን ነገሮች ጠቅልለን ስንመለከት ገዥው ፓርቲ ለሀገሪቱ ስጋት እንደሆነ የሚነግረንን ሽብርተኝነት ራሱ ባዘጋጀው ሕገ-መንግስት ሳይሆን፣ በዶክመንተሪ ፊልም ጎርፍ ለመግታት ነው የተዘጋጀው ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ በርግጥ የፓርቲው አላማ ሥልጣኑን መጠበቅ ነውና ሕገ-መንግስቱን ወዲያ ጥሎ ዘጋቢ ፊልሞች ላይ ቢንጠለጠል እንዴት ልንገረም እንችላለን?!

ወደ የፍርሃት ‹ሪፐብሊክ›

ይህች መከረኛ ሀገር በደርግና በኢህአዴግ ከተሠጣት ቅጥያዎች አንዱ ‹‹ሪፐብሊክ›› የሚል እንደሆነ ይታወቃል (የደርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሲል፤ ይህኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነች ይለናል)፡፡ ዝርዝር ሃተታውን

ትተን ከዚህ ፅሁፍ አውድ አንፃር የሪፐብሊክን ብያኔ ሕዝባዊ መንግስትነት የሚል ትርጓሜ ሰጥተን ማለፍ ይበቃል፡፡ ይሁንና የተሻገርናቸው ሁለት አስርታት የሚያስረግጡት ብቸኛ እውነት ቢኖር ሀገሪቱ ከዚህ የተጠያቂ መንግስት ምስረታ ተፃራሪ የሆነውን መንገድ መምረጧን ነው፡፡ ከላይ ለማሳያነት የጠቀስኩት ዶክመንተሪ ፊልምም ሆነ ተያያዥ አፋኝ ሕጎቹ እና ፖለቲካዊ አተገባበራቸው በፍርሃት የሚርድ ማሕበረሰብ በመፍጠር፣ ቀጣይ አስርታቱን ካለአንዳች መደነቃቀፍ ረግጦ መግዛትን ዋነኛ ግብ ያደረጉ ናቸው፡፡ ይህን ተቋማዊነትን ተደግፎ የሚካሄደው መንግስታዊ ሽብር፣ በአንዳች ክስተት ብርክ በሚያናውጣቸው ዜጎች ማሕበረሰቡ እየተሞላ እንደሚሄድ ግልፅ ነው፤ ከፌደራላዊ ወደ ፍርሃት ሪፐብሊክ እየተደረገ ባለው በዚህ ጉዞ፣ ሀገሪቱን ከዝግመታዊ ሞት ለመታደግ የበረቱ መዳረሻቸውን ስርዓቱ አዘጋጅቷል፡፡ እናም ዋጋው ምንም ቢሆንም በአደባባዩ ላይ የሚደረግ የተቃውሞን እንቅስቃሴ፣ ኢህአዴግን ከሥልጣን የማውረድ ብቻ ከመሆን መታለፉን በሚገባ ልናስብበት እንደምንገደድ ይሰማኛል፡፡ እነርሱ ከሚቀጥለው ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ ሕዝባዊ ምህዳሩን ምንም አይነት የተቃውሞ ድምፅ የማይሰማበት ምድረ-በዳ ለማድረግ ይህን ያህል ርቀት መጓዛቸውን ስንመለከት ምርጫችን ሁለት ብቻ ይሆናል፡፡ ቀጣዩን ትውልድ በፍርሃት ሪፐብሊክ ውስጥ ትቶ ማለፍ፣ አሊያም አደባባዩን በጨኸት መሙላት፡፡

ኢትዮሚድያ

ይሄ አደጋ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የግዲያ ሙከራ ይሁን አሊያም በአጋጣሚ የተፈጠረ የእሳት ቃጠሎ ይሁን ማወቅ አልተቻለም።

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት እና የዓረና ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የውብማር አስፋው ጋር በመሆን በመኪና እየሄዱ እያለ ድንገት መኪናቸው በእሳት መያያዟን የተመለከቱ ሰዎች ባደረጉላቸው ጥቆማና ርብርብ ከእሳቱ ቃጠሎ ለጥቂት መትረፋቸውን ማወቅ ተችሏል። በመኪናዋን ግን እዚያ የነበረው ሰው ሁሉ ብዙ ርብርብ ቢያደርግም ከቃጠለው ማተረፍ አልተቻለም። በእውነቱ ይህን መረጃ እንደደረሰኝ አላመንኩም ነበር፤

በመሆኑም ወዲያው ወደ አቶ ገብሩ አስራት ስልክ ደውዬ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ነገር ግን የአቶ ገብሩ ባለቤት ወ/ሮ የውብማር አስፋው ህወሃት ባካሄደው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ከነበራቸው ጥቂት ሴት ታጋዮች ውስጥ የሚመደቡ እና “ፊኒክስዋ ሞታም ተነሳለች፥ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ትግል” የሚለውን መፅሐፍ የፃፉ ናቸው።
ለማነኛውም ለአቶ ገብሩ አስራት እና ለባለቤታቸው ወ/ሮ የውብማር አስፋው እንኳን በህይወት አተረፋችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።

ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

እርግጥ ነው። እኔም አፄነትና መስፍንነትን እንደ ስርዓት አልቀበልም። ምክንያቱም አፄነትና መስፍንነት (እንደ ስርዓት) ላሁኗ ኢትዮጵያ አይመጥኑም። የአፄነትና መስፍንነት ስርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ እዚ ግባ የሚባል ለውጥ አላመጣም። ስለዚህ እኛ የሚያስፈልገን ዘመናዊ (ከዘመኑ ንቃተ ህሊናችን ጋር አብሮ የሚሄድ) የህዝብ አስተዳደር (ዴሞክራሲ) እንጂ ንጉስነት (የሰው ገዢነት) አይደለም። የምንፈልገው የሕግ የበላይነት እንጂ የንጉስ የበላይነት አይደለም።

ግን አፄነትና መስፍንነት እንደ ስርዓት ባልቀበለውም የንጉሳውያን ቤተሰቦችና መሳፍንቶች መጥፋት አለባቸው ብዬ ግን አላምንም። እኔ ብሆን እነኚህ የንጉስ ቤተሰቦችና መሳፍንት ቁልፍ የመንግስት ስልጣን አልሰጣቸውም ነበር። በሀገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ግን እፈቅድላቸው ነበር። ምክንያቱም እንደማንኛውም ሰው ዜጎች ናቸው፤ ለሀገራቸው በተቻላቸው መጠን አስትዋፅዖ አድርገዋል። ስለዚህ ንጉሳዊ ቤተሰብና መሳፍንት ስለሆኑ ብቻ መጥፋት አለባቸው ብዬ አልፈርድም። እንደ ጠላትም አላያቸውም፣ እንደ ዜጎች እንጂ።

ህወሓት ግን በመፈክር ደረጃ በጠላትነት ፈረጃቸው። በተግባርም አጠፋቸው፣ ገደላቸው። በንጉሳዊ ቤተሰብና መስፍንነት ዝንባሌዎች ሰበብ ብዙ የተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ዓድዋ፣ ሽረ፣ አክሱም ወዘተ መሳፍንቶች እንዲጠፉ ተደረገ። ‘ትግራይ ከመሳፍንቶች ነፃ ወጣች’ ተባለ። እውነታው ግን ‘ትግራይ ተገደለች’ መባል ነበረበት። መሳፍንቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ምን አመጣው (ህወሓቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ለምን ያስፈልጋል)?

ባጠቃላይ መሳፍንቶቹ ሲወድሙ ትግራይ ወደመች። አሁን በትግራይ የተቃውሞ መንፈሱ የተዳከመው በመስፍንነት ሰበብ ብዙ ብቁ ሰው ስለተፈጀብን ነው የሚል እምነት አለኝ። በህወሓት የተገደሉብንን ያህን በሌላ ስርዓት አልተገደሉብንም። ስለዚህ መሳፍንቶች ከስልጣን በማውረድ (መሳፍንቶችን ሳይሆን መስፍናዊ ስርዓቱ) ከህወሓቶች ጋር እስማማለሁ። መስፍናዊ ስርዓቱ ለማጥፋት መሳፍንቶቹ ማጥፋት ከሚል የህወሓት መፈክር ወይ መርህ ግን አልስማማም።

ሌላውና መሰረታዊ የህወሓት ችግር “የአማራ የበላይነት ይውደም!” የሚል መፈክር ነው። እኔም ብሆን የማንም ሰው ወይ ብሄር ወይ ሌላ አካል የበላይነት አልቀበለም። የቴድሮስ ወይ ዮሃንስ ወይ ምኒሊክ ወይ ኃይለስላሴ ወይ መንግስቱ ወይ መለስ ወይ ኃይለማርያም ወይ አማራ ህዝብ ወይ ትግራይ ህዝብ ወይ ኦሮሞ ህዝብ ወይ ሌላ … የበላይነት አልቀበልም። እኔ የምቀበለው የበላይነት ‘የሕግ የበላይነት’ ብቻ ነው። የሌላ የማንም የበላይነት አልቀበልም።

እንደ ፖለቲካ ድርጅት አንድን ህዝብ ዒላማ አድርጎ መነሳት ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን በሽታ ነው። ህወሓት (ተሓህት) የአማራን ህዝብ ዒላማ አድርጎ ሲነሳ፣ ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎች ደግሞ በህወሓት ምክንያት የትግራይን ህዝብ ዒላማ ሲያደርጉ ዉጤቱ ምን ይሆናል? አንድን ህዝብ ከሌላ ህዝብ ጋር የማጣላት ስትራተጂ የፖለቲካ ዕብደት ነው። ህዝብና ገዢው መደብ አለመለያየት (አንድ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብ) የፖለቲካ እውቀት ማነስ ዉጤት ነው። ስርዓቱ መቃወምና መታገል እየተቻለ ህዝብን ዒላማ አድርጎ በህዝቦች ላይ መተማመን እንዳይኖር መትጋትና በህዝቦች መካከል ጥላቻ እንዲነግስ መስራት ጠባብነት ነው።

አንድን ህዝብ የበላይነት ሊይዝ አይችልም። አንድን ቡድን ግን በአንድን ህዝብ ስም በመነገድ ሌሎችን ሊበድል ይችላል። የሰው የበላይነት (በህዝቦች ላይ) ሊተገብር ይችላል። ህዝብ እንደ ህዝብ ግን ሌላውን ህዝብ ሊበድል አይችልም። ህወሓት የትግራይን ህዝብ እንደሚወክል ይነግረናል። የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ እያለ ሌሎች ህዝቦች (የትግራይን ጨምሮ) ይበድላል። ሌሎች ህዝቦች (የትግራይ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን) ደግሞ በህወሓት ስርዓት ሲበደሉ በትግራይ ህዝብ የተበደሉ አድርገው ያስባሉ። ግን ስህተት ነው። መታረም አለበት። የትግራይ ህዝብ ለራሱ በህወሓት አገዛዝ የሚበደል ነውና።

“የአማራ የበላይነት” የሚባለው የህወሓት በሽታ እስካሁን ፈውስ አላገኘም። በመርህ ደረጃ ህዝብን ዒላማ አድርጎ ህዝብን ለመታገል መነሳት ስህተት ነው ብያለሁ። በፖለቲካ ህዝብን ዒላማ አይደረግም። ምክንያቱም የፖለቲካ ዓላማ ህዝብን ማገልገል እንጂ ህዝብን መጨቆን አይደለም። ስለዚህ ህዝብን የመበደል ዓላማ መያዝም መተግበርም የህሊና ወንጀል ነው። ህወሓቶች ይህን በሽታ (“የአማራ የበላይነት” መፈክር) አልተዋቸውም። አሁንም “ፀረ አማራ” እንቅስቃሴዎች አሉ። የህወሓት የአሁኑ ስትራተጂ “እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ ከአማራ ጋር አብረን አንቀጥልም” የሚል ገንጣይ አስተሳሰብ እያራመዱ ይገኛሉ። “እኔ ከሌለሁ ሠርዶ አይብቀል …” ዓይነት ስትራተጂ መሆኑ ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ፀረ ብአዴንም መነሳታቸው ነው። ለነሱ ከስልጣን ከሚወርዱ ኢትዮጵያ ብትበታተንና ትግራይን አስገንጥለው ትግራይን እየጨቆኑ ቢገዙ ይመርጣሉ።

ግን ይህን “አማራ” የሚባል ህዝብ መቼ ይሆን የበላይነት ይዞ ሌሎች ህዝቦችን የበደለው? አንድን ህዝብ እንዴት ሌላውን ህዝብ ይበድላል? ህዝብ ህዝብን ሊበድል አይችልም። ምክንያቱም አንድን ህዝብ ሌላውን ህዝብ መበደል ከጀመረ (ከቻለ) ህዝብ መሆኑ ቀርቶ ገዢ መደብ (elite) ሁነዋል ማለት ነው። ገዢ መደብ ከሆነ ደግሞ ህዝብ አይደለም። ገዢ መደብ ስርዓት ነው። ህዝብና ስርዓት ደግሞ ይለያያሉ።

ምናልባት የህዝብ የበላይነት አለ የምንለው ህዝብን የሚያስተዳደር (የሚገዛ) ስርዓት ከህዝቡ የወጣ ሲሆን ይሆን? ይህም አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም ገዢ ሁሌ ከህዝቡ ነው የሚወጣው (የቅኝ ግዛት ካልሆነ በስተቀየር)፤ ገዢ ከህዝቡ እንጂ ከማርስ አይመጣም። የኢትዮጵያ መሪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይወጣል። በኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ። ስርዓቱ ከሁሉም ህዝቦች ሰዎች ይኖሩታል። መሪ ግን አንድ ነው የሚሆነው። ያ አንድ ሰው (መሪው) ከአንድ ብሄር ሊሆን ይችላል። ያ አንድ ሰው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሌሎች ህዝቦችን ሊበደል (ወይ ሊጠቅም) ይችላል። ሰውየው የፈጠረው ስርዓት ለህዝቡ ቢጎዳም ቢጠምም ከስርዓቱ ይገናኛል እንጂ መሪው ከመጣበት ብሄር ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ገዢዎች የሚወክሉት የፈጠሩትን ስርዓት እንጂ የመጡበትን ብሄር አይደለም።

የደርግ ስርዓት ሲበድለን፣ “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የኃይለስላሴ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የምኒሊክ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” አሉን። የህወሓት ስርዓት ሲበድለንስ ማን በደለን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ? አይሆንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይበድላል? አንድን ህዝብ ራሱን ይበድላል? በደል ሁሉ ወደ አማራ ህዝብ ለምን? ስርዓትና ህዝብ ማገናኘት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል።

ግን እስቲ ይሁን፤ መሪዎች የመጡበትን ብሄር ይወክላሉ እንበል (ስህተት ቢሆንም)። እነሱ (መሪዎቹ) ሲበድሉ የመጡበት ብሄር በበዳይነት ተፈርጆ እንደ ጠላት ይቆጠር እንበል። የአማራ ህዝብ መቼ ይሆን በመሪዎቹ አድርጎ ሌሎች ህዝቦችን የገዛ (የበደለ)? ያለፉ ጨቋኝ ስርዓቶች አማራ ነበሩ ያለው ማነው? አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። እስቲ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሪዎች እንመልከት።

ብዙ ግዜ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ቴድሮስ ነው (ወይም ከዚሁ እንጀምር! ምክንያቱም ከአፄ ቴድሮስ በፊት ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች ነበር የምትተዳደረው። በዘመነ መሳፍንት መሳፍንቶች የራሳቸውን ህዝብ (ብሄር) ይገዙና ይበድሉ ነበር)። “አማራ” ተብሎ ከተሰየመው አከባቢ የሚወለድ ገዢ ቴድሮስ ነው። አፄ ቴድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ በዛን ግዜ የነበሩ መሳፍንቶች ተዋጉ። አፄ ቴድሮስ ዉግያው የጀመሩት በአማራ መሳፍንቶች (የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር) ነበር። ቴድሮስ “ከአማራ ስለመጣሁ፣ አማራ ስለምወክል፣ የአማራ መሳፍንቶች ማጥፋት የለብኝም” አላሉም። (ህወሓት ለትግራይ መሳፍንቶች እንዳደረገው ሁሉ)። ስለዚህ አፄ ቴድሮስ አማራን ወክለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አልበደሉም (ከበደሉም ለሁሉም ነው)። ስለዚህ “በአማራ ህዝብ ተገዛን” የሚለው ክስ “በአፄ ቴድሮስ ተገዛን” የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

የአማራ ተወላጅ የሆነ የኢትዮጵያ ገዢ ቴድሮስ ብቻ ነው ብዬ አስባለሁ (ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው እንዳልሳሳት፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)። ዮሃንስ አማራ አልነበረም፣ ምኒሊክ አማራ አልነበረም፣ ኃይለስላሴ አማራ አልነበረም፣ መንግስቱ አማራ አልነበረም፣ መለስ አማራ አልነበረም፣ ኃይለማርያም አማራ አይደለም። ማነው አማራ?

ምናልባት “የአማራ ገዢዎች” የምንለው ግለሰቦቹ (ንጉሶቹና መሪዎቹ) ሳይሆን ስርዓቱ ነው ካልን ያው ስርዓቱማ ከሁሉም ህዝቦች ተወካዮች አሉበት። አማራ ለብቻው ገዥ ነበር ማለት አንችልም። ምናልባት ገዢዎቹ አማርኛ ስለሚናገሩ ነው ካልን ደግሞ አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። አቶ መለስም አማርኛ ይናገር ነበር። አፄ ዮሃንስም አማርኛ ይናገሩ ነበር (አማርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሽየላዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የወሰኑት አፄ ዮሃንስ ናቸው የሚል መረጃ አለኝ፤ ‘መረጃ’ እንጂ ‘ማስረጃ’ አላልኩም)።

የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ገዢዎች ሲሰቃይ የነበረ ነው። ባልበላበት በልተሃል፣ ባልገዛበት ገዝተሃል ሲባል ይገርማል፤ ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ። የትግራይ ህዝብ ሳይበላ በልተሃል፣ ሳይገዛ ገዝተሃል ይባላል፤ ህወሓት በበላው፣ ህወሓት በገዛው። ህወሓት ትግርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም (በፖለቲካ መልኩ)። ያለፉ ገዢዎች አማርኛ ስለሚናገሩ ከአማራ ህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። ህዝብ ሌላ ገዢ ሌላ።

ባጭሩ ፀረ ህዝብ አቋም መያዝ ተገቢ አይደለም (ለማንኛውም ህዝብ)። ሰው የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ ይችላል። “የቀድሞ ስርዓት አባላት …” ምናምን እያልን አንፈርጅ። የህወሓት አባላት ለሌሎች ሰዎች የቀድሞ ስርዓት አባላት፣ ናፋቂዎች ወዘተ እያላቹ ስትፈርጁ እናንተም ራሳችሁ ከህወሓት ስርዓት በኋላ “የቀድሞ ስርዓት አባላት ..” ምናምን እየተባላቹ ስማቹ ይጠፋል፣ የፈለጋችሁን የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብታቹ ይገደባል። አሁን በሌሎች ላይ የምትፈፅሙትን ስም የማጥፋት ተግባር በናንተ (በራሳቹ) ይፈፀማል።

ስለዚህ እናስተውል። ከጥላቻ ፍቅር ይሻለናል። ጥላቻ ይውደም። አሜን!

It is so!!!

ምንሊክ ሳልሳዊ:-የትርፍ ሰአት ፖለቲካ በህዝብ ላይ የሚሴር ያልታወቀ እና ያልተነቃበት ሴራ ነው::ይህ ማለት ፖለቲከኞቹ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በሃሊዮ ወላ በገቢር የህዝብን የመኖር ደህንነት አደፍርሰዋል ::ራሳቸውንም ኢእውቀታዊ ወደሆነ የፖለቲካ ኪሳራ አዘቅት ልከውታል:: ታዲያ ለእነዚህ የትርፍ ሰኣት ፖለቲከኞች ወይም ሴረኞች እንበላቸው ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሰላም የሚል ታርጋ ይነሳቸው = ወያኔን አሸባሪ ማፊያ አድፍጦ ገዳይ አፋኝ ወዘተ ስንለው እነዚህን ታቃዋሚ እና ታማኝ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ሂደታቸው ላይ ያልነቁ ደበኞች ብንላቸው ሲያንሳቸው ነው::

ተቃዋሚ ፖለቲከኝነት በብዛት የትርፍ ሰአት ስራ የሆነባት ኢትዮጵያ አንድም ከወያኔ ቅጥረኝነት ሌላም ከፖለቲካ ከሚገኘው ጥቅም የተትረፈረፈ የህይወት ስኬት ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ አስመስሎታል::ያለፉት 22 አመታት መለስ ብለን ስናስበው የሽግግር ወቅት እንዲመሰረት ወያኔ ከፈጠራቸው የአናሳ ድርጅቶች እና በኋላም በተቃዋሚ ስም እንዲንቀሳቀሱ ተደርገው የምክር ቤት ወንበር እስከመያዝ የደረሱት ፖለቲከኞች አንድም የዩንቨርስቲ መምህር ናቸው አሊያም የግል ስራቸውን የሚያሯሩጡ እና በትርፍ ሰኣታቸው ገንዘብ ላለማጥፋት ወደ ፖለቲካው ያዘነበሉ አሊያም ከገዢው ፓርቲ ዳጎስ ያለ ጉርሻ አግኝተው የሚኖሩ ግለሰቦች ናቸው::

የትርፍ ሰአት ፖለቲካ የሚመነጨው ከግለኝነት ስለሆነ በሃገር ላይ የሚደረጉ ህዝባዊ አብዮቶችን እና ለውጦችን በምናገባኝነት ስሜት(አስመሳይነት) እንዲመለከቱት ያደርጋል;ፕሮፓጋንዳን ብቻ ለፖልቲካ ፍጆታነት የመጠቀም ስልት ማለትም ነው::ግለኝነት ስንል ፖለቲከኛው በፖለቲካው ረገድ መጫወት ያለበትን ሚና ረስቶ ከፖለቲካው ከሚገኘው ጥቅም ላይ ስለሚያተኩር ሲሆን ህዝባዊነትን ገደል ይከተዋል:: ወያኔዎች እያንዳንዳቸው ፖለቲካውን ስራዬ ብለው ስለያዙት በፖለቲካው መስክ ያላቸው ስኬት በዲሞክራሲ ስም ወደ አምባገነንነት አድጓል::

የትርፍ ስራ ፖለቲካ ሌላ ያዋጣቸው ለታማኝ ተቃዋሚዎች ነው::ታማኝ ተቃዋሚዎች ከተቃሚነት ሌላ የፖለቲካ ስለላ ያካሂዳሉ:: የፈለጉትን የትምህርት ዘርፍ ይማራሉ::አስፈላጊው የውስጥ እና የቅርብ ርቀት ጥበቃ ይደረግላቸዋል::በዚህ ላይ በስልጣን እርከን እንደመምሪያ ሃላፊ የመሳሰሉትን ስልጣኖች ይሰጣቸዋል:: ከዛም ስልጣን ሰበብ ለማስመሰል ይባረራሉ::አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የህዝብ ጥያቄ ሲነሳ ከትርፍ ስራ ተቃዋሚነት ወደ ቋሚ ፖለቲከኝነት በጊዜያዊነት ተመሳስለው ገብተው እንዲያከሽፉት ይደረጋል:: አቤት ታማኝ ተቃዋሚዎች የመንግስትን ወንበር ከያዙት ይልቅ እኮ እነሱ የተመቻቸው ናቸው::

የትርፍ ሰአት ፖለቲካ እያራመዱ ሃገርን እና ህዝብን የፖለቲካ ኪሳራ ላይ የጣሉ የ22 አመታት የፈጠራቸው ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሁን አሁንማ የኪሳራቸው ውጤት ስድብ ብቻ ሆነ::የትም ላይደርሱ እየተፈራገጡ:: ባለፉት 22 አመታት ጫካ ገብተው ቢሆን እስካሁን የመንግስትን ስልጣን ይዘው ባናፉብን ነበር::በጎረሩብን ነበር:: እኛም ወያኔ ጭራቁን አስወገዱ ብለን ባከበርናቸው ነበር:: እነ ሽማግሌዎቹ ጡረተኛ ፖለቲከኞችም ቢሆኑ በቋሚነት ስላለባቸው ደምብዛት እና ሰኳር ማስታመም ጋዜጣ ማንበብ እና መጻፍ በትርፍ ሰኣታቸው ህዝቡ ትዝ ሲላቸው ተነስተው ይህችኑ ፖለቲካቸውን ይተነፍሱብናል::

ገና በጠዋቱ “ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?” የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።

መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ ‘የዓሰብ ወደብ የማነው?’ የሚል ነው። ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።
ሁለተኛ ጉዳይ ዓሰብ የኛ ቢሆንም አሁን ያለው ግን በኤርትራ ቁጥጥር ስር ነው። ንብረት ሃብታችን ተነጥቀናል ማለት ነው። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘ዓሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል?’ የሚል ነው። መልሱ: ‘አዎ! ያስፈልጋታል’ ነው። የባህር በሯን የተነጠቀች ብቸኛዋ ትልቅ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። በአሁኑ ግዜ የባህር በር የአንድ ሀገር የህልውና በር ነው። የህልውና በሩ መዘጋት የለበትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ንብረቷ (ወደቧ) የማስመለስ መብትም ታሪካዊ ግዴታም አለባት።

ሦስተኛ ‘እንዴት ነው ወደቡን ማስመለስ የምንችለው?’ የሚል ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ዓሰብ የኢትዮጵያ ቢሆንም በመሪዎቻችን ሐላፊነት የጎደለው ዉሳኔ ምክንያት ለኤርትራ ተሰጥቶ ይገኛል። ‘ወደባችን አለ አግባብ ለኤርትራ በመሰጠቱ ምክንያት ዓሰብን የማስመለስ ጉዳይ ከባድ ሊያደርገው ይችላል’ የሚል ሐሳብ ቢነሳ አግባብነት አለው። ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ሊቀቅ ይችላል።
ግን ማትኮር ያለብን ስለ ጦርነት አይደለም፤ ስለ ዓሰብ ንብረትነት እንጂ። ዓሰብ የኛ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማረጋገጥ (ማሳመን) ይኖርብናል። በዓሰብ ጉዳይ ፅኑ አቋም ይዘን የኢትዮጵያም የኤርትራም ህዝብ እንዲገነዘበው መጣር አለብን። የዓለም ህዝብ ይሁን መንግስትታት ይደግፉናል። ምክንያቱም የባለቤትነት መከራከርያ ነጥባችን ጠንካራ ነው። የዓለም አቀፍ ሕግም ይደግፈናል። ዓሰብ የኢትዮጵያ ስለ መሆኑ የሚመሰክግሩ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችም አሉ።
አራተኛ ዓሰብ የኛ መሆኑ ቢናረጋግጥና ለዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ቢናሳውቅ እንኳ እንዴት ዓሰብን መመለስ እንችላለን? የኤርትራ መንግስትኮ ፍቃደኛ አይሆንም፣ ጦርነት ሊነሳ ይችላል … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ግን ችግር የለውም። ዓሰብ የኛ መሆኑ ካረጋገጥን ‘ንብረታችን መልስልን’ ብለን የመጠየቅ መብት አለን። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ላይሆን ይችላል። ጦርነትም ሊከፍት ይችላል።
እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም።
ጦርነት ስለማንፈልግ ዓሰብን በሰለማዊ መንገድ የምንረከብበት መንገድ እናመቻቻለን። የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል ብለን ግን ሃብት ንብረታችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ጦርነት ተፈርቶኮ የሀገር ግዛት አሳልፎ አይሰጥም። ጦርነት ተፈርቶኮ ልአላዊ ግዛትን ከማስከበር ወደኋላ አይባልም። በባድመ ጉዳይ ጦርነት ዉስጥ የገባነው ጦርነት ስለምንፈልግ ሳይሆን ልአላዊ ግዛታችን የማስከበር፣ ሀገራችን ከወራሪዎች የመከላከል ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ነው። ጦርነት ፈርተን እጃችንና እግራችን አጣጥፈን የባድመን መሬት ለሻዕቢያ ወራሪዎች አሳልፈን አልሰጠንም።
(በኋላ በፖለቲካዊ ዉሳኔ፣ በመሪዎቻችን ግድየለሽነት ምክንያት ባድመን መስዋእት ከፍለን በደም አስመልሰን ሲናበቃ በእስክርቢቶ ለወራሪዎች ተላልፎ ተሰጠ እንጂ። በጦርነት የተመለሰ ንብረት በድርድር ሲከሽፍ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ነው። የባድመ ጉዳይ …!)
ምንም እንኳ ጦርነት ባንፈልግም ሃብት ንብረታችን ግን አሳልፈን አንሰጥም። ጦርነት መስዋእት ይጠይቃል። ግን ለሀገራችን መስዋእት ብንከፍል ችግሩ ምንድነው? ለሀገራችንኮ መሞት አለብን። በምንክያት መስዋእት መሆን እንቻላለን። ደግሞኮ ኢህአዴጎች የዓሰብን ጉዳይ ስናነሳባቸው ‘ጦርነት ናፋቂዎች’ ይሉናል። እኔ ግን ለሀገር መስዋእት ብንከፍል ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። እንኳንም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶማሊያም እየሞትን ነው። ይቅርታ ለሶማሊያም እየሞትን አይደለንም። ምክንያቱ ላልታወቀ ጉዳይ ነው በሶማሊያ እየሞትን ያለነው። ወታደሮቻችን በሀገረ ሶማሊያ እየሞቱ ያሉ ለምን ዓላማ ነው? ዜጎቻችን ዓላማው ለማይታወቅ ጉዳይ በሶማሊያ ከሚሞቱ ለሀገራችን ቢሞቱ አይሻልም ነበር? ኢህአዴጎች ‘ጦርነት ጥሩ አይደለም’ ይሉናል። ጦርነት ጥሩ አለመሆኑ ቢያውቁ ኑሮ ለምን በሶማሊያ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው አያስገቡም?
አዎ! ጦርነት ጥሩ አይደለም። በተቻለ መጠን ጦርነትን ማስወገድ አለብን። ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም።
አሜን!

Image

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።
በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።
የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።
ሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!
ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።

ሕወሓት መራሹ ገዢ መደብ ኢሕኣዴግ በድርጅቱ ውስጥ ባደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ መሰረት ከተቃዋሚው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ቁርኝት አላቸው ግንኙነት ፈጥረዋል ለዲሞክራሲያዊ ስርኣቱ እንቅፋት ሆነዋል የድርጅቱን መረጃ አቀብለዋል ያላቸውን አባሎቹን ሊያባርር መሆኑን ከአዲስ አበባ የኢሕኣዴግ ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::

በዚሁም መሰረት የተደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ የተገኘ ማስረጃን መሰረት በማድረግ የሚባረሩትን አባላት እና ከተባረሩ በኋላ ሊወሰድባቸው የሚገባ እርምጃ እየተጠና መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጦር ሰራዊቱ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል::ከሻለቃ ማእረግ ጀምሮ ወደላይ እስከ ጄኔራሎች ድረስ የሚደረገው ግምገማ አጀንዳው ሙስናን ያጠቃል/አያጠቃል ባይታወቅም በዚህ ሰሞን በሕወሓቱ ጄኔራል ሳሞራ ቢሮ የተሰበሰቡት ጄኔራሎች በከፍተኛ መኮንኖች ላይ ግምገማ እንዲደረግ መወሰናቸው ሲታወቅ በግምገማው ላይ የሚገመገሙ መኮንኖች ስም ዝርዝር እንዲዘጋጅ ለወታደራዊ ደህንነት ክፍል ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቀሱ መኮንኖች እንደማይገመገሙ ሆኖም እንደሚገመግሙ ታውቋል::ምኒልክ ሳልሳዊ

በበደኖ አርባጉጉ አሰቦት አበምሳ እና በቀሪው የኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ ዜጎች የማን ትእዛዝ ነበር?
“ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው::” ሀጅ ቃሲም (ኣርባጉጉ)
ምንሊክ ሳልሳዊ
የፕ/ር ዓስራት ወልደየስ የመአሕድ ፕሬዝደንት ሰኔ 1ቀን 1984ዓ.ም ቁጥር መአሕድ /48/84 ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ የጻፉት ደብዳቤ ኦሕዴድ እን ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ ነው::
አንድ መቶ አመት ወደኋላ ተመልሰን ዛሬም አእምሮኣችንን እርቃኑን ከማስቀረት ከ100 አመት በፊት ከነበሩ ያልተማሩ መሪዎች ያነሰ የሚያስቡ ባዶዎች በዚህ በሰለጠነ ዘመን የፈጸሙት ወንጀል በትውልዳችን መጠየቅ ሊኖርበት ነው ብንል ባያስኬድም ለሁሉ የሚበጀው ግን መልካሙን ይዞ ማደግ ተመራጭ ነው::

በኣርባጉጉ የአውራጃ የኦህዴድ ተወካይ አቶ ዲማ ጉርሜሳ ግንቦት 26/1984 በአበምሳ ከተማና በኣካባቢው የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆችን ስብሰባ ከጠሩ በሆላ “ኣሼ :ኦዴ:ዒመና :ኣቡሌ በሚባሉ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ ” በማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ ከተሰበሰቡት የኦሮሞ ተወላጅ መካከል ሀጅ ቃሲም የተባሉ እጃቼውን ኣውጥተው
“ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው ” የሚል አስተያየት በማቅረባቼው
የኦህዴዱ ተወካይ በመናደዱ ሽጉጡን ኣውጥቶ “የነፍጠኛ እረዳት ነህ በማለት ማስፈራራት ሲጀምሩ ስብሰባው የሀጅ ቃሲምን ሀሳብ በመከተል ተበተነ ::
ይህንን ባለ 6 ገጽ የፕሮፌሰር አስራትን ፊርማ የያዘ ደብዳቤ ይመልከቱ::
Image

Image

Image

Image

Image

Image

#MinilikSalsawi

Image
“ፓርቲው ወደ ፊት ተራመደ ወይስ ወደኋላ” – በተቃዋሚ ፓርቲዎች ካምፕ የአመራር ንጥፈት ማሳያ
“የፖለቲካ ኃይሌ ተሟጦ አልቋል” በማለት ከፖለቲካው መድረክ የተገለሉት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ውስብስቡን የውህደት ማመልከቻ የመመርመር ታሪካዊ ኃላፊነት የወደቀባቸው ይመስላል። ኢንጂነር ግዛቸው የወጣቶች ሚና መጉላት እንዳለበት ደጋግመው ቢገልፁም፤ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ፓርቲው በእጃቸው ላይ እንዲወድቅ ሆኗል። ……የኢህአዴግ ፋሽን የሆነው “መተካካት” በተቃዋሚው ጎራ ውጤታማ እንዳልሆነም የሚገልፁ አልጠፉም። በተመሳሳይ መንገድ የእነ አቶ አዲሱ ለገሰን ወደ አመራር መመለስ በማየት በገዢውም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ “መተካካት” ሳይሆን በስልጣን “መመላለስ” አድርገው የተገነዘቡም ይመስላል።የሀገሪቱን ፖለቲካ በትውልድ መነፅር የሚለኩ ወገኖች ዛሬም ቢሆን “የ60ዎቹ ትውልድ” የሀገሪቱን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥሯል የሚል ቅሬታ እየተደመጠ ነው። አንድነትም ቢሆን የወጣት አመራር በማጣቱና በመቸገሩ በኢንጂነር ግዛቸው ስር መጠለሉን እንደመረጠና አማራጭም እንዳጣ በመግለፅ በማሳያነት የሚያቀርቡ አሉ።
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html

በፍራቻ የተዋጡ የመንግስት ሰራተኞች = የፍትህ ያለህ ….
ጥቅማ ጥቅምን ሽፋን አድርጎ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ ደባልቆ መስራት ከባድ አደጋ አለው::

መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በኢያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ሁሉንም ፖለቲካኛ የማድረግ እና ለፖለቲካ ፍጆታው ለመጠቀም የሚፈልገው ሕወሓት መራሹ መንግስት ህገመንግስታዊ የዜጎችን የመስራት/ሰርቶ የመኖር መብት እየደፈጠጠ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል:; ይህ ዜጋ በተለያዩ አስተሳሰቦች እና እምነቶች የራሱ በሆነ ሂደት ውስጥ የሚጓዝ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው::በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረቁ መንግስታት ኢላማ የሆነው የመንግስት ሰራተኛው ዛሬም የፍትህ ያለህ የነጻነት ያለህ በማለት ላይ ነው::

በየትኛውም የአለም ክፍል ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የሚያገለግለው ለቀጠረው ህዝባዊ አካል ሲሆን በመንግስት ሰራተኛው መሃል የተላያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ድጋፎች እና ተቃውሞዎች የመኖራቸውን ያህል ለፖለቲካ ግድ እስከሌለው ጀምሮ ፖለቲካ መስማት እስከማይፈልጉ እና ስራቸው ላይ ብቻ ማተኮር የሚፈልጉም ዜጎች አሉ :: ይህ ደሞ ህገመንግስታዊ መብታቸው እስከሆነ ድረስ ሊከበርላቸው ይገባል::

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ አለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ድርጅቶችም ይህንን በመንግስት ሰራተኞች ላይ የሚፈጸመውን በመስራት/በመኖር ላይ ያነጣጠረ ደባ አሳሳቢነት በይፋ ገልጸዋል::ከመንግስታዊ ጥቅማ ጥቅምም እንዲታገዱ እየተደረገ እንደሆነም ጩኸታችንን አሰምተናል::መንግስት ስንል ህዝብ ማለታችን መሆኑን ይገንዘቡልን..መንግስት የሚለው ቃል ወያኔን አይወክልም::

ወያኔ በህዝቦች ላይ የሚያራምደው አደገኛ የአገዛዝ ስልት የሚመለከቱ አብዛኛዎች የፓርቲው አባላት እና ካድሬዎች የትግል ቁርጠኝነታቸው ከመላሸቁም ሌላ ከፓርቲ ስራዎች ይልቅ በጥቅማዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው ያሳሰበው ወያኔ አንድ ለአምስት በሚባል አደረጃጀት የፓርቲውን ስራ ከመንግስት ስራ ጋር ጎን ለጎን ለመተግበር ደፋ ቀና በማለት የዜጎችን ህልውና አደጋ ውስጥ ጥሎታል::የወያኔን ድርጅታዊ ስራ ከመንግስት ስራዎች ጋር ቀይጦ ለመተግበር መሞከር አደጋው ወደማይወጡበት አዘቅት ሊከት እንደሚችል መታወቅ አለበት ::

ወያኔ የስልጣን ጊዜውን ለማስረዘም ብቻ በሚያደርገው መፍጨርጨር በህዝብ እና በሃገር ላይ ሊመጡ የሚችሉትን አደገኛ እንቅፋቶች ከግንዛቤ አለማስገባቱ በላይ ማንጫውን ዜጋ ህዝብን በሚያገለግልበት የመንግስት ስራዎች ላይ መፈጸም የሚገባውን እንዳይፈጽም እና በድርጅታዊ ስራ ስፋን ለቢሮክራሲ ለሙስና ለህዝቦች እንባ በር መክፈት መሆኑን ልብ አለማለቱ የወያኔ ዝቅጠት ገሃድ አድርጎታል::
በልማት ስም እየተፈጸሙ ያሉት ደባዎች እና ሴራዎች አልበቃ ብሎት በኢኮኖሚ ድቀት እየተንገፈገፍ ያለን ህዝብ በድርጅታዊ ስራ ለመወጠር ማሰብ የፈነዳ እለት የሚያስከትለውን ችግር ማንም ሊወጣው እንደማይችል ለማረጋገጥ እንወዳለን ስለዚህ በመንግስት ሰራተኞች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው እሽክርክሪት ሊታሰብበት ይገባል::

የ ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው
KING MENELIK HAS INVESTMENTS HERE; Abyssinia’s Ruler Said to be a Heavy Buyer of American… ታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –

– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።
የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

http://query.nytimes.com/mem/archive-fr … 5B898CF1D3

ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው
ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ አብዮቶች (የተሳኩትም ሆነ የከሸፉት) ሰላማዊውንና ህጋዊውን መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸው ዛሬም ይዘገንናሉ፤ ለወደፊቱም ባልተደገሙ ያሰኛሉ፡፡ ስለምን ቢሉ? ግድግዳው ላይ የተቸከቸከው ፅሁፍ እንዲህ የሚል ምላሽ ያስነብባልና፡- በጭቁን ሕዝብ ስም የብዙሀኑን ቤት አፍርሰዋል፤ ሀገርና ታሪክ ለመቀየር የማይሳናቸው አፍላ ወጣቶችን እርስ በእርስ አጫርሰዋል፤ ‹አንቱ› ሊባሉ የሚችሉ ምሁራንን በአንድ ጀንበር ወደ ትንታግ ነፍሰ-ገዳይነት ቀይረዋል፤ ክስረቱም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳ ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሷል…

በርግጥም ያ ወቅት መደማመጥ፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ መቻቻልን… የመሳሰሉ ምክንያታዊ እሴቶች ህቡዕ ገብተው፤ መጯጯኽ፣ መነቋቆር፣ መፈራረጅ፣ መገዳደል… የገነኑበት ነበር፤ ለዚህም ይመስለኛል ሀገር ሊረከብ የተዘጋጀ አንድ ትውልድ፣ በተኮረጀ ርዕዮተ-ዓለም፣ ባልጠራ ፕሮግራም እቅሉን ስቶ ‹ማርክስ እንደፃፈው›፣ ‹ሌኒን እንዳብራራው›፣ ‹ማኦ እንዳስተማረው›፣ ‹ሆጃ እንደመከረው›… በሚል ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ስቶ-በማሳት፣ ሀገር ምድሩን የጦር አውድማ አድርጎ ማለፉ የትላንት የቁጭት ትዝታ የሆነብን፡፡ በአናቱም ዛሬ ‹‹ነፃ አወጣናችሁ›› እያሉ ጃሎታ የሚመቱት የኢህአዴግ መሪዎች ከዚሁ ምንጭ የተቀዱ፣ ግና በቃላት ስንጠቃና በጎሳ ጠባብ አስተሳሰብ የተለዩ የትውልዱና የመንፈሱ ተጋሪ በመሆናቸው፣ የሁነቱ ‹ታሪክ›ነት ለተሰዉት እንጂ፣ ለእነርሱ ‹ሀገር እየመራንበት ነው› የሚሉበት ‹ፖለቲካ› ነውና፣ የነገይቷ የምንወዳት ኢትዮጵያችን መፃኢ ዕድል ገና ከእርስ በእርስ ግጭት ስጋት አለመላቀቁን ያመላክታል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የምንዘመርለት የ‹አትነሳም ወይ?› ድምፅ አደገኛውን ስርዓት የመቀየሪያው ጊዜ አሁን በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ግን እነኢህአፓ ተቸንፈው የተሰናበቱበትም ሆነ ኢህአዴግ ድል አድርጎ የመጣበት መንገድ ለዘመኑ መልካም ተሞክሮ ሊሆን ይችላል እንደማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በእኔ እምነት የእነርሱ ‹ፋኖተሰማራ…› ጊዜው በበየነበት ሙዚየምና የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ብቻ ካልተገደበ ጉዳቱ በቀላሉ የሚጠገን ካለመሆኑም ባለፈ፣ የምንመኘውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልምና ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ለትውልዱ ክቡድ ጥያቄ ስኬታማነት መንገድ መሪ አብርሆት መሆን የሚችሉ የደም ግብር ያልጠየቁ፣ ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ በከተሞች ተካሂደው ሀገርና ህዝብ ያለ ብዙ ኪሳራ በአሸናፊነት የወጡባቸው በርካታ አብነታዊ አብዮቶች (እንደ አረቡ ፀደይም ሆነ እንደ አውሮፓውያኑ ጆርጂያና ዩክሬን ብርቱካናማ-አብዮቶች) መኖራቸው እውነት ነው፤ እንዲሁም በእነርሱ መንፈስ መቀደስ፣ በእነርሱ ፀበል መጠመቅ የአምባገነኑንና የበደለኛውን ሥርዓት እድሜ ለማሳጠር የሚያበረታ ኃይል ማስረፁ እውነት ነው፡፡

ከተማን እንደ ጠላት

የ‹ያ ትውልድ› የጠብ-መንጃ ትንቅንቅን በድል የተሻገረው ኢህአዴግ (ከልቡ አምኖበት ባይሆንም) ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለው በተለይም ለአርሶ አደሩ ጥቅም መሆኑን በአገኘው አጋጣሚ ሳይናገር አያልፍም፡፡ በግልባጩ ደግሞ የከተማ ነዋሪዎችን ‹ጠላት› አድርጎ በመፈረጅ ሲገነግን ተደጋግሞ ተስተውሏል፤ በርግጥ የዚህ መግፍኤ በብሔር እና በሀይማኖት የከፋፈለውን ሕዝብ፣ በመደብም ለያይቶ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እና በየአምስት ዓመቱ በሚያካሄደው የይስሙላ ‹ምርጫ› ኮረጆ ገልብጦ ሲያበቃ የፈረደበት ምስኪን አርሶ አደር ‹መርጦኛል› ለሚለው የተለመደ ሰበቡ ‹ይጠቅመኛል› በሚል ለማመቻቸት ‹አዛኝ ቅቤ…› ተቆርቋሪ በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ድርጅቱ ይህንን የማጭበርበሪያ ስልት በደደቢት በረሃ ራሱ የቀመረው ነው ብሎ ለመከራከር የሚያስችል ገፊ ጭብጥ ይኖራል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም በአንዳንድ የዓለማችን ሀገራት የፖለቲካውን ኃይል ከጨበጡ በኋላ በሕዝባቸው ላይ ነጋሪት ጎስመው ሞትን ከነዙ፣ ስቃይን ከረጩ እርኩሳን መሪዎች (ፓርቲዎች) ድርሳናት ቃል-በቃል የተገለበጠ መሆኑን የሚያስረግጡ (በስነ-አመክንዮ) የተቀኙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላልና፤ እንደምሳሌም አንዱን በአዲስ መስመር እንምዘዘው፡-

የ‹ኬመር ሩዥ› መንገድ

በተለምዶ ‹ኬመር ሩዥ› (Khmer Rouge) በመባል የሚታወቀውና አክራሪ ኮምኒስታዊ የገበሬዎች ድርጅት እንደሆነ የሚነገርለት ‹‹Communist Party of Kampuchea /CPK/›› እ.ኤ.አ ከ1975-1979 ዓ.ም ድረስ፣ በወጣት የገበሬ ሠራዊት ታግዞ በካምቦዲያ መንግስታዊ ሥልጣን ተቆናጥጦ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ጨካኝና አፍቃሪ ቻይና የሆነው የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፖል ፖትም (Pol Pot)፣ ማኦ ዜዱንግ ‹‹የሀገሬን ኢኮኖሚ ያሳድግልኛል›› በማለት ያረቀቀውንና በግብርና ላይ የሚያተኩረውን ‹‹Great Leap Forward›› ፕሮግራም፣ ‹‹Super Great Leap Forward›› በሚል ተቀጥላ እንደወረደ በመኮረጅ ‹‹ሙሉ የካምቦዲያን ሕዝብ ወደ ‹እርሻ መር-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian Society) እቀይራለሁ›› ብሎ ያደረገው ሙከራ ወጪ-ኪሳራን ያወራረደው ሁለት ሚሊዮን ዜጎቹንለህልፈት በመዳረግ እንደ ነበር የታሪክ መፃህፍት ያትታሉ፡፡

ከሁሉም የከፋው ግን ፖል ፖትና ጓዶቹ ‹‹እውነተኛ ዜጋ ገበሬ ብቻ ነው›› በማለት የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ከፈረጁ በኋላ ‹‹ማህበረሰባችንን ለማንፃት›› በሚል የቁም-ቅዠት ምዕራባዊ አስተሳሰብ የተንፀባረቀበትን ማንኛውንም ጉዳይ፣ የከተማ ሕይወትን፣ ኃይማኖትን፣ ትምህርትን፣ አንድ ብርም ቢሆን በግል መያዝን… በአዋጅ ማገዳቸው ነበር፤ እንዲሁም ኢምባሴዎችን፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘግተዋል፤ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን በማፈናቀል ወደ ገጠር አግዘው፣ በግዳጅ የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተዋል፤ ከዋና ከተማዋ ‹ፈኖሞ ፔንህ› (Phnom Penh) ብቻ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ወደገጠር በእግር እንዲጓዙ በመገደዳቸው ሃያ ሺህ የሚሆኑት በጉዞ ላይ ወድቀው እንደወጡ ቀርተዋል፤ ገጠር የደረሱትንም ቢሆን ‹የግድያ ወረዳዎች› እያሉ በሚጠሯቸው የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተው ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ በየሁለት ቀኑ አንዴ 180 ግራም ሩዝ ብቻ በመስጠት በረሀብ፣ በበሽታ፣ ብስቅየት እና በግድያ እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም አገዛዙ በቬትናም ጣልቃ ገብነት እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም በኃይል በመወገዱ፣ ፖል ፖት ከእነተከታዮቹ ሀገሩ ከታይላንድ ወደምትዋሰንበት ጠረፍ አካባቢ በመሸሽ፣ የትጥቅ ትግል እንደአዲስ ጀምሮ ለረዥም ዓመታት ከታገለ በኋላ፣ እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም እርጅና ተጭኖት በህግ ቁጥጥር ስር በዋለ፣ በዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል (በነገራችን ላይ ይህ ድርጅት የሽምቅ ውጊያ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በኋላ የተጠናከረበትን ምስጢራዊ መንገድ ጨምሮ የተከተለው ስልት ከሞላ ጎደል ከኢህአፓና ህወሓት አፈጣጠር ትርክት ጋር ተመሳሳይነት አለው)

ኢህአዴግ እንደ ‹ኬመር ሩዥ›

ከሁለት አስርተ ዓመታት የሥልጣን ቆይታም በኋላ፣ የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ካሰፈረበት ጥቁር መዝገቡ ላይ መሰረዙ ያልሆነለት ኢህአዴግ ‹እንደ ኬመር ሩዥ ሁሉንም የጭካኔ ተግባራት በአደባባይ ፈፅሟል› ተብሎ ባይወነጀልም፣ ተመሳሳይ ስልቶችን በመኮረጅ በረቀቀ መንገድ አለዝቦ መተግበሩን ግን መካድ አይቻልም፡፡ እንዲሁም የሁለቱ ድርጅቶች ዋነኛ ልዩነት ወደ እንዲህ አይነቱ የጥላቻ ጠርዝ
የተገፉበት ምክንያት ይመስለኛል፤ ይኸውም ፈላጭ ቆራጩ ፖል ፖት በከተሜው ላይ የከፋ ቂም የቋጠረበት መነሾ፣ ከገበሬ ቤተሰብ መገኘቱን ጨምሮ፣ ከአስተዳደጉ ጋር በሚያያዙ ‹ህመማቸው-ህመሜ› በሚል ሲባጎ የተቋጠረ ሲሆን፣ መለስና ጓዶቹ ደግሞ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም በማስላት ብቻ መሆኑ ነው፤ መቼም መሬት የረገጠውን እውነታ ተመልክቶ የሀገሬ አርሶ አደር ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ፣ ከከተሜው የተለየ የመልካም አስተዳደርም ሆነ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑን መረዳቱ አዳጋች አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ ‹ፀረ-ከተሜነት› እንዲህ በግላጭ አፍጥጦ የወጣው ከምርጫ 97 በኋላ ነው፤ በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ፣ ድርጅቱ በከተሞች መሸነፉን ከገለፀ በኋላ፣ በገጠር ሙሉ በሙሉ ስለተሳካለት መንግስት ለመመስረት የሚያስችል የመራጭ ድምፅ ማግኘቱን አውጇል፤ ይህንንም ተከትሎ ግንባሩን ያልመረጡ የከተማ ነዋሪዎች በተቀነባበረ ሴራ የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን የሚያመላክቱ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ በተለይም በድህረ-ምርጫው ከተሜውን ዒላማ ያደረጉ በስራ ላይ የዋሉ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ በደባ የተፈፀሙ መንግስታዊ ጥፋቶችን ዘርዘር አድርገን እንያቸው፡፡

መሬትን በተመለከተ የወጣውን የሊዝ አዋጅ በቀዳሚ ምሳሌነት እናንሳው፤ ፓርቲው በ1987 ዓ.ም ባፀደቀው ህገ-መንግስት የመሬት ፖሊሲውን አንዱ ዕማድ አድርጎ በማካተቱ፣ የመንግስት ጭሰኝነትን (Tenants of the state) በገጠሩ ክፍል ሲያሰፍን፣ የመሬት ከፊል ባለቤትነትን ደግሞ ለከተሞች እንዲፈቅድ አድርጎት ነበር፡፡ እናም የግል ይዞታን መሸጥ (መንግስት ለሚፈልጋቸው ‹‹ልማቶች››ም ሆነ
በሊዝ ለመቸብቸብ ዜጎችን የማፈናቀል መብት ከማግኘቱ ውጪ) እስከ 97ቱ ድህረ-ምርጫ ድረስ ተፈቅዶ የዘለቀበት ሂደት፣ በዚህ የሊዝ አዋጅ በመሻሩ የተነሳ፣ ነዋሪው መሬት በመሸጥ ሊያገኝ ይችል የነበረው ገቢ ተጨምቆ ወደ መንግስት ካዝና እንዲሻገር ሆኗል፡፡ የዚህን አዋጅ ‹ፖለቲካዊ ንባብ› ውስጥ የምናገኘው ጭብጥ፣ በከፊልም ቢሆን መሬት ላይ የቆመውን የሀብት መሰረት በመናድ፣ የተቃውሞ ኃይሉ የድጋፍ መዕከል እንደሆነ ያመነውን የማህበረሰብ ክፍል ክፉኛ ማድቀቁን ስንረዳ ነው፡፡ አዋጁን እንለጥጠው ካልን ደግሞ ግንባሩ በገጠሩ ያነበረውን የዜጎች የመንግስት ጭሰኝነት በጠመዝማዛ መንገድ፣ በተለይም በአዲስ አበባ የመፈጸም ዕቅዱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡

የኢህአዴግ ከተማንና ከተሜዎችን የመፍራት አባዜ ከጫካ ትግሉ ጋርም በረዥሙ የሚተሳሰር ነው፡፡ በወቅቱ በጥላቻ ከመተያየት አልፎ ደም የተቃባቸው ኢህአፓን መሰል ኃይሎች መሰረታቸው ከተሞች ላይ እንደነበረ ይታወቃል፤ በአናቱም በትግሉ መጠናቀቂያ ዋዜማ እና ማግስት ሊገዛለት ያልቻለው (ማማለሉ ያልተሳካለት) ልብ በተለይ የአዲስ አበቤዎችን ነበር፤ በ1980ዎቹ መጀመሪያም ፓርቲው አንገት ላይ ታንቆ ሊደፋው የነበረው ዋነኛ ጉዳይ፣ ብሔር ተኮር ስርዓቱ ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ ሲያገኝና የብሄር ፖለቲካ ብቸኛው የድጋፍም የተቃውሞም ተዋስኦ እንዲሆን መደረጉ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያዊብሔርተኝነት መንፈስ ከተገራው የአዲስ አበቤ ብሔር ዘለል ማንነት ጋር እንዲህ በፊት ለፊት መጋጨቱ፣ ከተማይቱን በወረራ የያዛት እስኪመስል ድረስ በጥላቻ እንዲዘምቱበት አነሳስቷል፡፡

ሁለተኛው ምዕራፍ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የመጣው የአሰብ ወደብን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲካለል የመፈለግ የከተሜዎቹ ግፊት ነው፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃና የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ሲገደዱ የነዋሪው ቁጣ ብርቱ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህ እውነትም ሌላኛው ፓርቲውን ቂም ያስቋጠረ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ በድህረ-ምርጫ 97 የፀደቀውና አፋኝነቱ በተግባር የተረጋገጠው የሲቪል ማህበረሰቡን የሚመለከተው አዋጅም ‹የብዙዎች ተቋማት ዋናመቀመጫ አዲስ አበባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወጣ ነው› በማለት ከየአቅጣጫው ይነሳ የነበረውን የተቃውሞ ውግዘት አጣጥሎ፣ በሥራላይ ባዋለበት ዓመት በርካታ ተቋማትን ከማፈራረሱ አኳያ፣ መጀመሪያውንም ለእንዲህ አይነቱ ክፉ እርምጃ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ወደሚል ጥርዝ ይገፋል፡፡ በተጨማሪም ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት ሙሉ በአይኑ መዓት የሚያያቸው ምሁራን፣ የነፃው ፕሬስ አባላት እና በየዘመኑ ከባድ ተግዳሮት የፈጠሩበት የተቃውሞ ስብስቦች ጠንካራ መሰረት በከተማይቱ ውስጥ መሆኑ ጥላቻ እና የጭካኔ እርምጃዎቹን አብዝቶታል፡፡

ሌላው አገዛዙ በከተሜዎች (በሸማቾች) ላይ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ የሚያሳዩት፡- ከምርጫው በኋላ ጤናማ ያልሆነ የዋጋ ንረት በከፋ ደረጃ ማሻቀቡ፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የተለያዩ የግብር ህጎች በእንጀራ እና ሽንኩርት ቸርቻሪዎች ላይ ሳይቀር መተግበራቸው ነው፡፡ በተለይም ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዋነኛ አባባሽ ኃይል የምግብ ዋጋ መናር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ
የምግብ ዋጋ መናር በዋነኝነት ቋሚ ደሞዝ ተከፋዩ የከተማ ነዋሪው ተጎጂ መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናትም ይቀበላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከሁለት ወራት በፊት በ‹‹አዲስ ዘመን›› መፅሄት የተጠየቀው የፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ‹‹በ2006 ዓ.ም የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም›› ከማለቱ ባለፈ ‹‹ነገ ይችን አገር ወደተሻለ የሚያደርስ በጎ መስዋዕትነት ነው›› ሲል በከተሜው መከራ ላይ አላግጧል፡፡ በርግጥ ይህ ሁሉ መዓት ከመውረዱ በፊት በ1998 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ራሱ አቶ መለስ በደቡብ ክልል ወደምትገኘው ይርጋለም ከተማ ድረስ ሄዶ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮችን ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ፣ እንዲህ ለፍተው የሚያገኙትን ምርት ለከተሜው በርካሽ መሸጣቸው አግባብ አለመሆኑን ቀስቅሶ ዋጋውን በአራት እጥፍ እንዲጨምሩ በማድረጉ የተፈጠረው የገበያ እጥረት፣ ምንም እንኳ መልሶ አምራቾቹን ሰለባ ቢያደርግም፣ ኩነቱ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቀጣይ ዕቅድ የሚያመላከት ነበር፡፡

በከተሞች ውስጥ እየተደረገ ያለው ‹‹የሰፈራ ፕሮግራም››ም (Urban Resettlement) አንዱ ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ዕቅድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሻለ የመኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ እንደሆኑ ማየት እንችል ይሆናል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ግን፣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎችን ከሌሎች የፈረሱ የከተማዎቹ ክፍሎች ከሚመጡት ጋር በአንድ አዳብሎ በኮንዶሙኒየም ቤቶች አጥሮ የማስቀመጡ አንደምታ ላይ ነው፡፡ የዚህ ዕቅድ ክፉ ገፅ የሚገባን በረዥም የአብሮነት መስተጋብር (ሶስት መንግስታትን መሻገር የቻለ የአንድ አካባቢ ነዋሪነት) የተገነባው የጋርዮሽ ፖለቲካው አረዳድ እና የእርስ በእርስ ፍፁም መተማመን፣ 97ን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተነሱ ተቃውሞዎች ወጥ ምላሽ እንዲሰጡ ማደፋፈሩን (አራት ኪሎን የመሳሰሉ አካባቢዎች) አስታውሰን፣ በመልሶ ማስፈሩ ደግሞ የአንዱን አካባቢ ነዋሪ በታትኖ ወደተለያዩ ሳይቶች መውሰዱን ስንመለከት ነው፤ ይህ መራራ እውነታም የገዥዎቻችን ጥላቻ ስር የሰደደ መሆኑን እና የአምባገነናዊ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም ያለመ እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡

(ስርዓቱ በከተሜዎች ላይ የሰረፀበትን ጥልቅ የጥላቻ ፅንፍ እንዲህ ከተመለከትን፣ የከተማ አብዮት፣ ማኦኢዝም ከሚያዘው ከገጠር ከሚነሳው ብረታዊ ትግል ጋር ያለውን ልዩነት፣ በአረቡ ፀደይ ተሞክሮ በመንተራስ መፈተሹን፤ እንዲሁም የኢህአዴግ ግድፈቶች (Achilles’ heel) የከተማ አብዮትን ለማስነሳት ያላቸውን አስተዋፅኦ፣ በአደባባይ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ቢሆኑ የተሻለ ነባራዊውን እውነት ያንፀባርቃሉ… የሚሉትን ጉዳዮች እና መንገዱን ስለሚመሩ የሚችሉትን መልከአ-ቡድኖች ማንነት ሳምንት እመለስበታለሁ)

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሁለት ሳምንት በፊት በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።በእዚህ ጉብኝት ላይ አቶ ኃይለማርያም ”እጅግ ለም የሆነ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተስማምተዋል አሁን የቀረው ችካል ማስቀመጥ ነው” የሚል ዜና በኢሳት ሲዘገብ ቀናት ነጉደዋል።ትናንት ታህሳስ 16/2006 ኢሳት በአለም አቀፍ ራድዮ ስርጭቱ ላይ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ የሚከታተሉ ‘የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴ’ የተሰኘ ኮሚቴ አባላትን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።እንደ ኮሚቴው ገለፃ ከሆነ አሁን መንግስት ለሱዳን መንግስት ለመስጠት መስማማቱ የሚነገረው መሬት ከቀድሞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ያለ አሁንም ገበሬዎች የሚገኙበት እና ባዶው ቦታን ጨምሮ በትንሹ ካለምንም ማጋነን 15 ሚልዮን ሕዝብ አስፍሮ መመገብ የሚችል ቦታ ነው።15 ሚልዮን ልብ በሉ!

በሕዝብ ስም የሚደረግ ማንኛውም ውል ከህዝብ ሊደበቅ አይገባውም።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።ይህ ደም ደግሞ ለዘመናት የኢትዮጵያ አባቶች እና እናቶች ያፈሰሱት ደም ነው።ማንም መንግስት በሕዝብ ደም ሊደራደርም ሆነ ድንበር ሊሰጥ አይችልም።ለአንድ ‘ኩርማ’ መሬት ለባድሜ በሺዎች ያረገፈ ጦርነት ክተት ያወጀ መንግስት 15 ሚልዮን ሕዝብ የሚያሰፍር መሬት ለሱዳን ስለመስጠቱም ሆነ ስለ ውሉ ጉዳይ ዝርዝር ማብራርያ ለሕዝብ ሊሰጥ ይገባል።በትዊተር በብዛት የሚታዩት ባለስልጣናት ከሌላው ዜና ይልቅ የእዚህ አይነቱን ቅድምያ ሊሰጡት በተገባ ነበር።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።

http://www.youtube.com/watch?feature=pl … 86uyLReLdE

http://gudayachn.blogspot.no/2013/12/blog-post_26.html

የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ, ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ።

አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና

ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

አቶ ባልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፤ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት በከፊል ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ሊያስረድዋቸው ሞክረዋል፤ ስለመስፋፋቱና እንዲያውም አማራውን እንደገፋው ለአቶ ባልቻ መረጃ ላቅርብ

ጥንት ሌላ ስም የነበራቸው በኦሮሞ ከተያዙ ማግስት ስማቸው የተቀየረ፤ ደዋሮ- ጨርጨር, ጋፋት-ሆሮ, ገራሪያ- ሰላሌ, ዳሞት- ወለጋ, አበቤ- በቾ, ሽምብራ ኩሬ- ሞጆ…(የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ገጽ 50 በጥላሁን ገ/ስላሴ) በቅኝ ተገዛ የሚሉት ኦሮሞ ተጨማሪ ቦታ እንደያዘ እንጂ እንደተወሰደበት አይደለም ታሪኩ የሚመሰክረው፤

አቶ ባልቻ የኦሮሞን ታሪክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ፤ ኦሮሞም እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲረገጥ የኖረ ሕዝብ አድርገው ያቀርቡታል። መፈትሄውንም ሲጠይቁ reconciliation እርቅ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ የተቀረው ይቅርታ ጠያቂ በተለይም የፈረደበት አማራ ለዚህ ወንጀል ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፤ ባለፉት አስተዳደሮች ስህተቶች አልተሰሩም ብሎ የሚከራከር የለም፤ ጥያቄው እንዴት አብረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው?

እንደቅኝ ተገዛን የሚሉት ቡልቻ ደመቅሳ አገሪቱን በእርሻ ሚኒስቴርነትና በምክትል ገንዘብ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል- ቸር ቅኝ ገዢ ነበር የነበራቸው፤ እኛ ቅኝ እየተገዛን ስለሆንን በሚኒስቴርነት ቅኝ ገዢዬን አላገለግልም ብለው አላንገራገሩም፤

ኦሮሞ በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊው ክንፉ ታላቅ የሚባሉትን ስልጣኖች ይዞ የኖረና ያለ የህብረተሰብ ክፍል ነው፤ አገሪቱ ውስጥ ለነበሩትና ላሉትም ደግ ነገሮችም ሆነ ክፉ ነገሮች ተጠያቂነቱ እኩል ነው፤ አቶ ባልቻ ቅኝ ገዢ የሚሉትን የአማራውን ክፍለሀገር ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ያስተዳድሩት ነበር- (ምሳሌ የሚያቀርብበት ደቡብ አፍሪካ የማስተዳደር ቅንጦት ይቅርና ነጭ በሚዝናናበት ቦታ ጥቁር መግባት አይፈቀድለትም ነበር)

ስለኦሮሞ ባለስልጣናት እስቲ እንመልከት

ምኒሊክ በሸዋ ሲነግሱ የረድዋቸው አብሮ አደግ ባልንጀራቸው ጎበና ዳጬ ናቸው፤ የወለጋውም አስተዳዳሪ ኩምሳ ምኒሊክን በደጃዝማችነት አግልግለዋል፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶም የማይረሱ ታልቅ ኢትኆጵያውያን ናቸው

የአጼ ሃይለስላሴ አባት ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (ጉዲሳ) አባታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤ እናታቸውም ወ/ሮ እመቤት እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤

ራስ ዳርጌ የሸዋው ንጉስ ሳህለስላሴ ከወለድዋቸው አራት ወንዶች መሃከል አንዱ ሲሆኑ ጥናታቸው አርሲ ውስጥ የአንድ አካባቢ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ነበሩ (አባ ቦራ በታቦር ዋሚ ገጽ 9)

ራስ አበበ አረጋይ መከላከያ ሚኒስትር

አቶ ይልማ ዴሬሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር, የገንዘብ ሚኒስትር

ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳደር

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የእርሻ ሚኒስትርን ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር

ሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የክብር ዘበኛ አዛዥና I,ባህል ሚኒስትር

ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ የኢሊባቡርና I,ጎሙገፋ አስተዳዳሪ

ሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቲ የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ

ሌ ጀኔራል ጃጌማ ኬሎ የአራተኛው ክፍለጦር አዛዥና የባሌ አስተዳደር

ፊታውራሪ ለማ ወልደጻድቅ የሲዳሞ ምክትል አስተዳደር

ሜ ጀኔራል አበራ ወልደማርያም የአየር ሓይል ምክትል አዛዥ

ደጃዝማች በቀለ ወያ የጨቦና ጉራጌ አስተዳደር ከዛም የጨርጨር አስተዳደር

ደጃዝማች ካሳ ወልደማርያም የአዲስ አበባ ዩኒጸርሲቲ ፕሬዘዳንትና የእርሻ ሚኒስቴር

አንባቢያን መረዳት ያለብን ሁላችንም በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያውያን መሆናችን ነው፤ ሕዝባችን በጋብቻ, በእምነት በባሕል የተሳሰረ በመሆኑ መሰረት የሌለው ታሪክ እያነበነቡ ሊበታትኑን የሚያስቡትን ታሪካዊ መረጃ እያቀረብን ወግዱ ልንላቸው ይገባል፤ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው፤ ምኒሊክም ያስተማሩን መቻቻልን አንድነትንና ፍቅርን ነው፤
Moresh Info.

Image

ዛሬ ላስነብባችሁ ያሰብኩት ቀደም ሲል የጥራት እና ደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተብሎ ይጠራ ስለነበረው አሁን ለአራት ተከፋፍሎ እንዲጠፋ ስለተደረገ ተቋም ነው፡፡ መስሪያቤቱ ምርት እና አገልግሎችን በመቆጣጠር የሸማቹን ደህንነት እና ጤንነነት ማስጠበቅ ፤ የገቢና ወጪ ምርቶችን ጥራት በመከታተል ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡መስሪያቤቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት ይመሩ የነበሩት አቶ መሳይ ግርማ ሲባሉ በውስጡ የፍተሻእናካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የሰርተፊኬሽ አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የደረጃዎች ዝግጅት ዳይሬክትሬት፣ የስልጠናአገልግሎት ዳይሬክትሬት እና የፋይናንስ ዳይሬክትሬት እና ሌሎች የአገልግጎች ዘርፎች ነበሩት፡፡አቶ መሳይ መስሪያቤቱን ከ16 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል፡፡ድንገት ባልተጠበቀ ሰዓት ከአቶ መሳይ እውቅና ውጭ 3 ሰዎች አቶ ተክኤ ብርሀኔ ከመቀሌ፣አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ከጅማ እና አቶ ዳንኤል ዘነበ ከሀረርጌተመልምለው ወደ መስሪያቤቱ ተመደቡ፡፡ሰዎች ሳይፈለጉ መመደባቸው ብቻ ሳይሆን በወቅቱ እንዲከፈላቸው የተፃፈላቸው የደመወዝ መጠንም በመስሪያቤቱ የደመወዝ ስኬል የሌለ፤ ካላቸው የትምህርት እና የስራ ልምድ ጋር ምንም አይነት ዝምድና ስለሌለው አቶ መሳይ መክፈል አልችልም በማለት አንገራገሩ፡፡እነሱ መች የዋዛ ቢሆኑ እና እስከ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተዘረጋ ሰንሰለት ስለነበራቸው በስልክ ተደውሎላቸው ሳይወዱ በግድ መክፈል ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በ2002 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ ከየክልሉ ተፈልገው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀዋርያ ሁነው ወደ ፌዴራል መንግስት የመጡ ናቸው፡፡ተክኤ በስፓርት ፣ደቻሳ በሂሳብ እና ዳንኤል በማኔጅሜንት ተመርቀዋል፡፡ሲመጡ የሚያርፉበት የኪራይቤቶች የሚያስተዳድረው ሰፋፊ ግቢየተዘጋጀላቸው ሲሆን ዳንኤል ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት አጠገብ፤ተክኤ እና ደቻሳ ደግሞ 22 አካባቢ ባለ ሰፋፊ ግቢ እንዲኖሩተመቻችቶላቸዋል፡፡ዋናው የቅርብ ጊዜ አላማቸውም በ2002 ለሚደረገው ምርጫ የመንግስት ሰራተኛውን ከኢህአዴግ ጎን ማሰለፍ እና ቀጣይ አመራሮችን ማዘጋጀትነው፡፡በዚህም መሰረት ባሉበት ቀበሌ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊነት ተመድበው ይሰራሉ፡፡በተጨማሪም መንግስት በቢ.ፒ.አር.(business process reengineering) ብሎ ወደፊት ሊዘረጋ ላቀደው የሰራተኞች ማፈኛ መንገድ የራሱን ታማኝ የስለላ ሰዎች ወደመሲሪያቤቱ ያስገባል፡፡የአዲሶቹን ተመዳቢዎች አመጣጥ ተከተሎ በመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፍረሃት ድባብ ተፈጠረ፡፡እነሱ ሰራተኞችን ወደሚጭነው ሰርቪስ ሲገቡ አንድም ሰው ትንፍሽ አይልም፡፡የአውቶቡሱ ሰው ሁሉ በጸጥታ ይዋጣል፡፡ጆሮ ጆሮ እያሉ ያንሾካሽካሉ፡፡በእረፍት ሰሀት እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ አብሮ ተቀምጦ ሻይ ቡና የሚል የለም፡፡ሲመደቡ የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ተብለው ሲሆን ከመስሪያቤቱ እውቅና ውጭ ከነአቶበረከት ሰምኦን ጋር በየሳምንቱ ስብሰባ እና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ከሳይንስና ቶክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ከፈለጉ በአካል መኪና አዝዘው ካልፈለጉ በስልክ በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡አቶ መሳይ እና ሌሎች የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የማያውቁት መረጃ ከነሱጋ ይገኛል፡፡በዚህ የአንድ አመት ቆያታቸው በመስሪቤቱ ደጋፊዎችን ማፍራት አልቻሉም፡፡
በ2003ዓ.ም የቢ.ፒ.አር ጥናት ሲጀመር አዲስ የመጡት ካድሬዎች የጥናት ቡድን መሪ እየተባሉ ተመደቡ፡፡ቢ.ፒ.አር ለመስራት ቀርቶ ስለመስሪቤቱ አሰራር በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች መስሪያቤቱን አፍርሶ እንደአዲስ የማደራጀት ስራ በእነዚህ ሰዎች ስር ወደቀ፡፡በዚህም ተቀራራቢ ስራዎችን በጋራ ማደራጀት በሚል ሰበብ ከብሄራዊ የጨረር መከላከያ አንዱን መምሪያ በማፍረስ፤የክሊነር ፐሮደክሽን መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ፤የሳይንስ መሳሪያዎች መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው አነዚህን መስሪያቤቶች ከደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መስሪያቤት ጋር በማዋሀድ አራት የተለያዩ መስሪያቤቶችን ለመፍጠርጥናቱ ተጀመረ፡፡አዲስ የተጠኑት መስሪያቤቶች1.Meterology institute, 2.Accreditation biro, 3 .Standards agency4. Conformity assessment enterpriseይባላሉ፡፡ እነዚህ መስሪያቤቶች በተጠኑበት ወቅት ለጥናት ቡድኑ በየሳምንቱ በጣም ውድ በሆኑ ሆቴሎች የእራት ግብዣ እየተዘጋጀ ለ6 ወር ያክል ተደከመበት፡፡ወደመጨረሻው ምእራፍ ሲቃረብ የጥናት ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ናዝሬት ውስጥ ከ10 ቀን በላይ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው እንዲሰሩ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የጥናቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ በአቶ ጁነዲን ሳዶ አማካነት አርባምንጭ ለሶስት ቀናት ድል ያለ ግብዣ ተደረገ፡፡ከአርባምንጭ መልስ ሁሉም በሳይንስ እና ቴክኔሎጂ ሚ/ር ስር የሚገኙ ሰራተኛ ለገሀር በሚገኘው የመንገድ እና ትራንስፖርት መሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተካሄደ፡፡በስብሰባው የየጥንት ቡድኑ ሀላፊዎች የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አደረጉ፡፡የሀገራችን ችግሮች ተዳሰሱ፡፡ለችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉ አማራጮች ከየአቅጣጫው ጎረፉ፡፡አብዛኞች ወጣቶች ተስፋ ያደረጉትን በየመስሪያቤቱ ያለውን ብልሹ አሰራር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡በዚህ ውይይት ከተነሱት ውስጥ እስካሁን የማሰታውሳቸው አቶገብረጊዳን ገብረመስቀል በቅጽል ስሙ(GG) “በየመስሪያቤቱ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ለምሳሌ እንደኢንጅነር ቅጣው እጅጉ አይነት ሰዎች ነበሩዋት ሌሎችም እንዲህ አይነቶች ይኖራሉ ብሎ ተናገረ፡፡”በእረፍት የንግድሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሐይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሳይ ይህን የተናገረውን ልጅ ጠራቸው እና ስሙን ጠይቃ “አንተማ የእኛው ነህ እየውልህ ኢ/ር ቅጣው በመንግስታችን ላይ ሊሰራ አቅዶት የነበረውን ስለማታውቅ ነው እንዲህ ያልከው፡፡በቶሎ ቀጨው እንጂ ቢቆይ በጣም አደገኛ ነበር፡፡እንዲህ አይነቱን ሰው ስሙን መጥራት የለብህም” አለችው፡፡ይቅርታ ወ/ሮ አልማዝ እኔ እሱን አላውቅም ነበር ሲል መለሰላት፡፡ሌላው ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት የመጣ አቶ ጸጋዬ የሚባል አንድ ተናጋሪ በንግግራቸው መሀል ጣል ያደረጉዋት ቀልድ መሰል መልክት ሁሌም ትከነክነኛለች፡፡አቶ ጸጋዬ “አማርኛ እጅዋን አገኘች በግል ትምህርት ቤት ውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል ተብሎ በጉልህ ተጽፎ አንድትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አንብቤያለሁ” ብለው አረፉ፡፡ሌላው ጠያቂ አብዲ ዱጋ ይባላል፡፡አብዲ ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ነው፡፡ጥያቄው “ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አየተካሄደ ያለው የአበባ እርሻ ልማት የአካባቢውን አፈር እና ውሃ እየበከለው ነው፡፡በዚህም የተነሳ እንስሳት ይሞታሉ ሰዎች ይታመማሉ፡፡የሰራተኞችም ህይወት አደጋ ውስጥ ነው የሚከፈላቸውም ገንዘብ እዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡እንዲያውም ባለ ሀብቶች ከሌሎች ሀገሮች ሲባረሩ ነው ወደዚህ ሀገር የመጡት ይባላል እና ይህን እንዴት ያዩታል? ሲል ጠየቀ፡፡አብዲን የገጠመው ከፍተኛ ውግዘት ነው፡፡ለውግዘቱ መነሻም በወቅቱ የአበባ እርሻ ልማት ሲጀመር አቶ ጁነዲን የኦሮሚያ ርእሰመስተዳድር ስለነበሩ እሳቸውን እንደተቃወመ ተቆጠረ፡፡አብዲም ያጠናው ባዮሎጂ ስለነበር ሙያዊ ትንታኔ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ክርክሩ እየከረረ ሲሄድ ጓደኞቹ ዝም እንዲል አደረጉት፡፡ስልጠናው ለ5 ቀናት በፍረሃት እንደተዋጠ ተጠናቀቀ፡፡ከዚህ ሰብሰባ መልስ በቀጥታ ሁሉም መስሪያቤት ወደ ሰው ኃይል ምደባ እንዲገባ መመሪያ ተላላፈ፡፡
ስብሰባው አርብ ተጠናቆ ሰኞ ጠዋት አቶ መሳይ ከመስሪያቤቱ በፍቃዳቸው እንዲለቁ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ለሚቀርቡዋቸው ሰዎች ሲናገሩ የኮሚኒኬሽን ሰራተኞቹ እነ ተክኤ ደግሞ ምደባውን እንዳያስተጉዋጉል በማሰብ አስቀድሞ መባረሩን በየቢሮው እየዞሩ ያውጃሉ፡ይህን ተከትሎ መስሪያቤቱ ሰው የሞተ ያክል በኡኡታ በልቅሶ ታመሰ፡፡አብዛኖች መልካም ተግባሩን ለሰራተኛ አዛኝነቱን እያሰቡ አባታቸውን በሞት የተነጠቁ ያክል ከልብ አዘኑ፡፡በዚሁ እለት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶታደሰ ሀይሌ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ካህሣዬ መስሪያቤቱን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ፡፡የተለያዬ ዳይሬክተሮችን ሹመት ሰጡ፡፡በዚህ ወቅት ቀደም ሲል ወያኔን እንደሚቃወሙ የሚታወቁት እና ከአቶ መሳይ ጋር ቀረቤታ አላቸው የተባሉ ነባር ዳይሬክተሮች ተነስተው በምትካቸው የኢህአዲግ አባላትንመመደብ ተጀመረ፡፡ምደባውም የሚካሄደው እያንዳንዱ ሰራተኛ እየተገመገመባለው ችሎታነው ይባል እንጅ ነገር ግን አስገራሚው እና ያን ያክል የተደከመበት ጥናት የግምገማውን 75% የሚይዘው ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አመለካካት የሚባል ነገር ነው፡፡ሰራተኞች በወቅቱ ያነሱት የነበረው ጥያቄ አመለካከት በምን ሊለካ ይችላል የእኔን አመለካካት ምን እንደሆነ ማን ያውቀዋል የሚል ነበር፡፡ግምገማውን የሚሞሉት ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው እነ ተክኤ፣ደቻሳ እና ዳናኤል ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች እንደመሰላቸው የግምገማ ነጥቡን መስጠታቸው ሳያንስ ምደባውን በዋናነት የሚመሩት እነሱ ናቸው፡፡ወደደረጃ መዳቢ መስሪያቤት የመጡትን የሌላ አዳዲስ መስሪያቤት ሰራተኞች መልካቸውን ሳይቀር የማያውቁዋቸውን ሰዎች ግምገማ በድፍረት ይሞሉ ነበር፡፡በመሀል በተቃዋሚነት ያልተፈረጁትን እና አባል መሆን የሚፈልጉ ካሉ በምደባ እና በእድገት አያባበሉ ወደድርጅቱ የማግባባት ስራ ተከናወነ፡እኔ ስራየን እንጂ የፓርቲ አባል መሆን ፍላጎት የለኝም ያሉት ደግሞ ቀደም ሲል በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ ስልጠናዎችን ተከታትለው ስራቸውን በብቃት ሲወጡ የነበሩ በርካታ ባለሙያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባለመቀበላቸው ብቻ ዘራቸው እየታየ ከስራቸው ከተባረሩትመካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለማሳያ ያክል የቀረቡ ሲሆኑ አንድም የትግራይ ብሄር ተወላጅ አለመባረሩን አንባቢያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ሌላው እና አስገራሚው ነገር በወቅቱ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን እያገለለ እየተካሄደ ያለው ምደባ ያሳሰባቸው የኢህዴድ አባላት ጥያቄያቸውን ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ቢያቀርቡም ወ/ሮ አላማዝ ካህሳይ እያንዳንዱን ኦሮሞ እቢሮአቸው ጠርተው አርፈው እንዲቀመጡ አለዚያ እንደሚባረሩ በዛቻ ገልጸውላቸዋል፡፡በወቅቱም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው አቶ ሙሉጌታ መኮነን ያለስራ ለአንድ ዓመት ደመወዝ ብቻ እየተከፈለው ሊሰራ በማይችል ዘርፍ የቡድን መሪ ሁኖ ሲመደብ በስሩ ግን ምንም ሰው አልነበረም፡፡
ተ.ቁ ስም የነበራቸው ሀላፊነት ብሄር
1 አቶ መሳይ ግርማ የጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ኦሮሞ
2 አቶ ጋሻው ወርቅነህ የጥራት እና ደረጃ መ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አማራ
3 አቶ ተፈራ ማሞ የኤሌክትሪክል ላብራቶር ሃላፊ ኦሮሞ
4 አቶ ሀይሉ የመሳሪያ ጥገኛ አገልግሎት ሃላፊ ኦሮሞ
5 አቶ ደሬሳ ፉፋ የሰርተፊኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር ኦሮሞ
6 አቶ መስፍን የስልጠና አገልግሎት ዳይሬክተር አማራ
7 አቶ አዱኛው መስፍን የጥራት ማኔጅሜንት አሰልጣኝ አማራ
8 አቶ እንዳ የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሀላፊ አማራ
9 አቶ አመሃ በቀለ የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ አማራ
10 አቶ ሂርጳ የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ ኦሮሞ
11 አቶ መረሳ የሰርትፊኬሽን ኤክስፐርት ኦሮሞ
12 አቶ ቴወድሮስ ዘካሪያስ የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት አማራ
13 አቶ ልኡል የባህርዳር ቅርንጫፍ ሀላፊ አማራ
14 የሰርትፊኬሽን ሲስተም ኦዲተር የነበሩት ኦሮሞ
15 የድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት አማራ
16 የናዝሬት ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት ኦሮሞ
17 የሀዋሳ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት ደቡብ
ታማኝ የህወአት አባላት በባትሪ ከሌላ ቦታ ተፈልገው ያለ ልምድ እና ችሌታቸው በከፍተኛ አመራርነት ሲመደቡ የተለሳለሰ አቋም ያላቸውን እና የአባልነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው ጥያቄውን የተቀበሉ ነባር የመስሪያቤቱ ሰራተኞች የፍርፍሪው ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡በዚህ ምደባ እስከቡድን መሪ ያለው ሀላፊነት ያለ ፓርቲ አባልነት ወይም ያለ ትግራይ ተወላጅነት በምንም መልኩ ለተራው ሰራተኛ አይሰጥም፡፡

ተ.ቁ ስም ቀደም የነበራቸው ሀላፊነት አሁን የተሰጣቸው ሀላፊነት ብሄር
1 ወ/ሮ አልማዝ ካህሳየ የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክተር የደረዳዎች ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

2 አቶ ወንዶሰን ፍስሃ የካሊብሬሽን አገልግሎት ሀላፊ የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

3 አቶ አርአያ መከላከያ ኢንጅነሪንግ የአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ

4 አቶ ጋሻው ተስፋዬ የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ትግሬ
አቶ ገብሬ ኝግድ እና ኢንዱስትሪ ኤክስፐርት በደረጃዎች ኢጀንሲ ዳይሬክተር ትግሬ

6 አቶ ብርሀኑ ተካ ረዳ የፋይንነስ አስተዳደር ዳይሬክተር የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፋይናንስ ዳይሬክተር ጉራጌ

7 ወ/ሮ ገነት ገ/መድህን የፍተሻ እና ካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር የአክረዲቴሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር ትግሬ

8 ወ/ሮ ብርሀን ብሂል የአዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጸሀፊ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰው ሀብት እስተዳደር ሀላፊ ትግሬ

9 አቶ ብርሀኑ ተካ የሰርቪስ ሹፌር የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ ትግሬ

10 አቶ ተክኤ ብርሀኔ የኮሙኒክሽን ሰራተኛ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ትግሬ

11 አቶ ዳዊት የሰርቪስ ሹፌር የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የትራንትፖርትመምሪያ ሀላፊ ትግሬ

12 አቶ ጸጋዬ ኢንስፔክተር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሀላፊ ትግሬ

13 አቶ ዘነበ ኢንስፔክተር የገበያ ጥናት ሀላፊ ትግሬ
ቀደም ሲል እንደማናኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚታዩ ችግሮች ቢኖሩም የተወሰደው እርምጃ ግን የወቅቱን የትግሬዎች የንግድ እንቅስቃሴ ያላንዳች ተቆጣጣሪ እንደፈለጉት ለማሽከርከር ታስቦ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ለዚህም መነሻ የሚሆነው በተለያዩ ጊዜያት በቆርቆሮ፣በብረታብረት፣በማዳበሪያ፣በሳሙና፣በከብሪት፣በሲሚንቶ ፣በዘይት፤በጨርቃ ጨርቅ ፣ በባትሪ ድንጋይ፣በኤሌክትሪክ ገመዶች የመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተከስቶ በበላይ አካል የስልክ ትእዛዝ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ ተደርጉዋል፡፡ለአብነት ያክል የአቢሲኒያ ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዳያመርት አገዳ መስሪያቤቱ ሲያስተላልፍ በወቅቱ የከተማ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ካሱ ኢላላ ፍተሻውን ያከናወኑ ባለሙያዎችን በግላቸው ቢሮ ድረስ በማስጠራት ትክክል አደላችሁም፤ልማታችንን እያደናቀፋችሁ ነው፤ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን እየመጡ እንዳይሰሩ መሰናክል እየፈጠራችሁ ስለሆነ አቁሙ ሲባሉ የመስሪያቤቱ ሀላፊዎች እገዳውን ባስቸኩዋይ አንዲያነሱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈዋል፡፡መስሪያቤቱም እንዲፈርስ የተደረገው ባለሞያዎችም የተፈናቀሉት ሆን ተብሎ ያለ አግባብ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለው ራሱን የሚያዳምጠው ወያኔ
ስብሰባ ስብሰባ ስብሰባ…..ይቀጥላል ይህ ወያኔያዊ የአውሬ ወለድ በሽታ

ምንሊክ ሳልሳዊ…የህዝብ ጥያቄዎች አለመደመጣቸው ውጤቱ የችግሩን ጥልቀት ስፋት እና እያስከተለ ያለውን ቀውስ ሊታየው ያልቻለው ወያኔ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ህዝቡን ወደባሰ የድህነት አረንቋ እየከተተው ነው:: ይህ ደሞ ወያኔ እንደ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች አትኩሮት አለመስጠቱ ነው::ሕዝብ ችግሩን የሚናገረው በስብሰባ ብቻ አይደለም፡፡ በየቀበሌው፣ በየክፍለ ከተማው፣ በየከተማ አስተዳደር እርከኖች፣ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በየክልሉ፣ ወዘተ በማመልከቻ፣ በቃልና በጽሑፍ በየደቂቃውና በየሰኮንዱ አቤት እያለ ነው፡፡ የሰሚ ያለህ እያለ እየጮኸ ነው፡፡ መብቴ ተረገጠ፣ ንብረቴ ተቀማ፣ ጉቦ ካልሰጠህ ችግርህ አይፈታልህም ተባልኩ፣ አድልዎ ተፈጸመብኝ፣ ወዘተ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ የሚያዳምጠው የሚያዳምተው አላገኘም ካድሬዎች ከህዝብ ጥያቄዎች በፊት ፖለቲካውን እና ተቃዋሚዎችን ወደ ማሳደድ አዘንብለዋል::

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እናዳምጣቹ በሚል ሰበብ ችግራችሁን ተወያይተን እንፍታ በሚል ሰበብ የተለያዩ ስብሰባዎች የህዝብን ጭንቅላት ለመስረቅ በጀት ለአበል ተመድቦ እበማካሄድ ምንም ፋይዳ ያሌላቸው እና ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል የሚደረጉ ከመሆናቸውም በላይ ወያኔ ግን የሚወስነው ጉዳይ ለህዝብ እንቅፋት የሆነ እና ከስብሰባው እና ከተሰብሳቢ ምልክታ ውጪ የፖለቲካ አጀንዳውን ለማስፈጸም ብቻ ነው::

በስብሰባ ስም የሰበሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጠሩበት አጀንዳ ውጪ ራሱ ተናግሮ ራሱ እንደፈለገ አውጥቶ እና አውርዶ ራሱ ወስኖ የራሱን ድምጾች እንደገደል ማሚቱ የሚያዳምጠው ወያኔ ምንም አይነት መንግስታዊ እና ህዝባዊ ፋይዳዎችን ሲፈጽም አልታየም::ህዝብን ማዳመጥ አለመቻሉ ህዝብ ጥያቄ ሲያነሳ እንደ ጭራቅ መመልከቱ የመብት ጥያቋ ያለሳ ሁሉ እንደ ጠላት እና እንደ ተቃዋሚ መፈረጁ ወያኔ ህዝብን ለማዳመጥ ጊዜ እንዳሌለው የሚያሳዩ ጉዳዮች ናቸው::ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አውቅልሃለሁ ከተባለው ውጭ ጥያቄ አንስቶ ቢገኝ ህገወጥ ነው:: የፖለቲካ ፓርቲ ሰልፍ ቢጠራ ህዝብ በአደባባይ የአገልግሎት መብቱን ቢጠይቅ በስብሰባ ላይ የተሰማውን ቢተነፍስ ወዘተ…ህገወጥ ነው::

በአለማችን ላይ አንዱ አንዱን ካዳመጠ የማይፈታ የማይቀረፍ ችግር የለም:: በሰለጠነ ዘመን እኔን ብቻ ስሙኝ ብሎ ድርቅ ያለ አስተሳሰብ ማንጸባረቅ ተቀባይነት የለውም:: ህዝብን ማዳመጥ የቻለ መንግስት ነኝ የሚል ሁሉ ሃገራዊ ስኬቶቹ ጉልህ ናቸው::ህዝብን ማዳመጥ ያልቻለ በጉልበት የሚኖር መንግስት የግእዜ ጀግና ስለሆነ ይወድቃል:: ወያኔም እኔ ብቻ ነኝ ህዝባዊ ሌላው ህገወጥ ነው ቢልም ለህዝብ ችግሮች ግን ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች በስፋት እየጨመሩ መተዋል::

በየስብሰባው ገበሬው ነጋዴው መምህሩ ተማሪው ፖለቲከኛው ጋዜጠኛው ….ባጠቃላህ ህዝቡ ብሶቱን አሰምቷል::የህዝብን ችግር እናዳምጣለም በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦ ስብሰባዎች በየፈርጁ ተጠርቷል::ሁሉም ችግሩን ተንፍሷል:: …መፍትሄ ግን የለም:: የህዝብን ጥያቄ ግን ወያኔ ሊያዳምጥ አልፈቀደም ….ይልቁኑ ለሚዲያ ፍጆታ እና ለፖለቲካ አጀንዳነት ተጠቅሞበታል:: በየስብሰባው አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ተናግረዋል የተባሉ ታፍነዋል ታስረዋል ተሰደዋል ተገድለዋል ከስራ ተባረው ቤተሰባቸው እንዲበተን ተደርገዋል::ታዲያ ህዝብን ማዳመጥ ተብሎ የሚጠሩ ስብሰባዎች ወያኔ ራሱን እያዳመጠ ህዝቡን እየደፈጠጠ ነው::

ህግ አለ ህገመንግስት እናስከብራለን የሚለው ወያኔ መጀመሪያ ራሱ ህገ መንግስቱን እና ያወጣውን ህግ ማክበር አለበት::አንድ መንግስት ህዝብን ያዳምጥ ሲባል መለመን ወይንም ምጽዋት መጠየቅ አይደለም:; ህዝብም ማዳመጥ የማንኛውም አመራር ህጋዊ ግዴታ ነው::ህዝቦች ከህግ እና ከመብት አንጻር ተደምጠው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል::መንግሥት ሕዝብን የሚያዳምጠው በሕገ መንግሥቱ ግዳጅነት አይደለም፡፡ የሕዝብ ሰራተኛ ነኝ የሚል ሥልጣን የያዘ ፓርቲና መንግሥት፣ ሕዝብ መረጠኝ የሚል ፓርቲና መንግሥት፣ የሕዝብ ከበሬታና አመኔታ ሊያገኝና ዓላማውን በተግባር ላይ ሊያውል የሚችለው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የሚቆየው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ህዝብን የማያዳምጥ ራሱን የሚያዳምጥ የማይደመጥ ይሆናል፡፡

ነጻ አውጪ እስከመች???
የትግራይ ህዝብ ነጻ አልወጣምን??? ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው?
እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ?

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከአነሳሱ ሲጠነሰስ የትግራይ ህዝብን ነጻ በማውጣት ሲሻው በመገንጠል ሲሻው ታላቋን ትግራይ በመመስረት ….በሚሉ የመከኑ ይሁኑ ገና ያልተሳኩ አሊያም (በፕሮሰስ ላይ ባሉ ?)ባልታወቁ መርሃግብሮች ላይ ተነድፎ ወደ ጫካ መግባቱ እውን ቢሆንም ያላሰለሱ ድሎች መገኘት የጀመሩት ግን በ1980ዎቹ የሃገራዊ ፋይዳው ታይቶ ከተፈጠሩት ሁሉን አቀፍ የጦር አውድማዎች በኋላ ነው::…ሕወሓቶች ኢሕዴንን እና ኦሕዴድን አጣምረው ኢሕኣዴግ በሚል ተሰይመው የነበሩት የዛኔዎቹ ታጋዮች ለዲሞክራሲያዊ ምስረታ እና ለህዝባዊ እኩልነት የታገሉ መሆኑ እሙን ቢሆንም የተነሱበት አላማ የተሰዉለት ይህ ነጥብ ግን ከአፈር ጋር ደባልቀውታል:: የሰምዓታቱንም ፍሬ እዛው በረሃ ጥለውት መተዋል::

የዳግማይ ወያኔ አነሳስ የትግራይን ህዝን ነጻ ለማውጣት ነው እስካለ ድረስ እና ራሱን የትግራይ ህዝቦች ነጻ አውጪ ብሎ ከሰየመ በኋላ ደርግን መፋለሙን ተከትሎ ከደርግ ጭቆና የትግራይን ህዝን ነጻ እንዳወጣው እየነገረን ነው::አሁንሳ ሕወሓት ማንን ነጻ ለማውጣት ነው በዚህ ስሙ የቀጠለው? እውን አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የተንሰራፋ የጨቋኝ ቡድን አለ? ወይንስ ነገሩ ከወዲሁ ነው የቀድሞዎቹ ጨቋኝ መደቦች እነእንትና ካልወደሙ የህ ሕወሓት የሚለው ስሙን አይቀይርም??/

ሕውሓት የትግራይን ህዝብ ነጻ ወተሃል ካለው 22 አመት አልፎታል:: የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ገዢዎች ግን አሁንም ይህንን ስም ይዘው ቀጥለዋል::ለምን ግን …? የትግራይ ህዝብ ነጻነቱ የሚረጋገጠው ሕወሃትም ስሙን ቀይሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የሚባልበት ቀን ይናፍቃል:: ኢህዴን እንኳን መዐሕድን ተከትሎ /ቀንቶ ብኣዴን ተብሏል…ሕወሓት ግን እስከመቼ ድብቅ አላማ ይዞ እንደሚጓዝ አልረዳ ብሎናል:: ወይስ ይህን ስም የሚጠቀመው አንድ የትግራይን ነጻነት እንደኤርትራ በሪፍረንደም እስኪያስረግጥ ነው ወይንስ እነእንትና…እንስም አይጠሬ የድሮዎቹ የጨቋኝ መደቦች የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን ዘራቸው ከምድረ እትዮጵያ ተጠራርጎ እስኪጠፋ…???? የህገመንግስቱ አንቀጽ 39 ባለበት የሚቆየው ምን እስኪመሰረት ድረስ ነው? የመጀመሪያው የሆነው ኢትዮጵያዊነትን ከአያት ቅድመ አያቱ የወረሰው የትግራይ ህዝብን በአምባገነኖች ጭቆና ስር ለማስቀጠል ይሆን??/ስላልገባን ይነገረን::

ዲይስፖራ ፖለቲከኞች እና ወያኔ = ለሃገር የማይበጁ የጥላቻ አንጃዎች
የህዝብን አንደበት እንተነፍሳለን::

ምንሊክ ሳልሳዊ ሁለቱን በየፈርጃቸው በትግል አካሄዱ ዙሪያ ስንመለከታቸው የፖለቲካ አጀንዳቸውን በኢኮኖሚ በደቀቀው ህዝብ እና በነጻነት ጥያቄ በሚያነባው ህዝብ ላይ ለመጫን እየተራወጡ የሚሄዱ በጥላቸ የተሞሉ አንጃዎች ናቸው:: የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ የህዝብን አንደበት ግን እንተነፍሳለን::ምናልባት ወያኔን ተወት አድርጓት እና ዲያስፖራ ፖለቲከኛ ነኝ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ጣማማ እና በጥላቻ የሚያነክስ ይህ ነገር ላይዋጥለት ይችላል::
===== መዋጥ ከቻለ ይዋጥ መወጥ ካልቻለ ያስመልሰው የራሱ ጉዳይ::=======

እኛ አንዴ በሃገር ውስጥ አንዴ በውጭው በስራ ጉዳዮች የምንኖር ዜጎች ከወያኔ በባሰ መልኩ እያንገበገብን ያለው በአውሮፓ እና በአሜሪካ ተደብቆ መሰሪ እና በሃገር ላይ የጥላቻ ድብቅ አጀንዳውን እያራመደ ያለው ፖለቲከኛ ነውሃገር ወዳድ በሰው አገር የሚከራተቱ ዜጎችን ከግራ ቀኝ በተደቋቆሰ ፖለቲካ የሚያላትመው እና የዲያስፖራውን ሃገራዊነት ካለሞሶሶ ለማስቀረት የኢቶጵያን ህዝብ ትግል የሰው ሃገር የመኖሪያ ፍቃድ ማስገኛ ያደረገው የዲያስፖራ ፖለቲከኛ የጥላቻ ፖለቲካ ተሞልቶ ዘላለሙን በወሬ ትግሉን እየገደለው ይገኛል:: በሃገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በከፍተኛ ፍጋት ውስጥ ሲያሳልፉ ግማሹ ትግሉን መጦሪያ ሲያደርገው የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆና አገዛዝ ማላቀቅ አልተቻለም::

የወያኔ ካድሬዎች ከሕወሓት መራሹ መንግስት የሚያገኙትን ጥቅም ለማስጠበቅ በከፍተኛ ጥላቻ ተሞልተው በሃገር ውስጥ በህዝብ ስቃይ ሲደሰቱ የተቃወመውን ሁሉ በማፈን በመግደር ወደ ኢስር ቤት በመወርወር የተቃወመ ሁሉ ጠላት ነው በሚል የእኛ እናውቅላቹሃለን አስተሳሰብ ተሞልቶ ህዝብን ሰቆቃ ውስጥ ከቶታል በፍራቻ አንገቱን ሰብሯል:: ውስጥ ለውስጥ በሚነዛ ሽብር የህዝብ ሚዲያዎችን ለፓርቲ ፍጆታ በማዋል በሚደረጉ የፕሮፓጋንዳ ሩጫዎች ለሃገር የማይበጁ መጥፎ ምግባራት በስፋት እየተፈጸሙ ነው::

ወያኔ የሚያራምደው የጥላቻ ፖለቲካ በጋራ ህዝቦች ለሃገራቸው በየመስኩ አስታውጾ እንዳያደርጉ በሃገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ እያደረገ ሲሆን ዲያስፖራው በተቃራኒ የሚያራምደው የጥላቻ ፖለቲካ ቁም ነገር አላባ ትግሎችን በመፍጠር ለወያኔ የስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ በሩን ከፍቶለታል:: ዲያስፖራው የእርስ በእርስ መኮራኮም የበዛበት ፖለቲካ የሚያራምድ እና ዘላለሙን የአምባገነኖችን የማውደም ትግል ሳይሆን የወያኔን ጥላቻ የሚሰብክ አንዱ ከፍ ብሎ ሲያይ እዛው የፖለቲካ ጥጉ ላይ ጎትቶ ገደል ለመክተት የሚራወጥ ለሃገር የማይበጁ በጥላቻ የተሞሉ ስብከቶችን የሚያበዛ ትግሉን ያደነዘዘ የህዝብ እንቅፋት ነው::

ዲያስፖራው የሞላበት የጥላቻ ፖለቲካ ማስወገድ ከትግሉ በፊት ቅድሚያ ተግባሩ ነው:: አብዛኛው ዲያስፖራ በየስብሰባው እንደምናየው ሊያጨበጭብ የሚመጣው በወያኔ ላይ ያለውን የጥላቻ ፖለቲካ ተመርኩዞ እንጂ በትግል ስልቱ ላይ ያለውን ግንዛቤ ይዞ ነው:: አጨብጭቦ ዶላሩን አፍሶ የመኖሪያ ፍቃዱን የሚያድስበት የትብብር ደብዳቤ ተከብሎ ከዛ ሃገር የራሷ ጉዳይ:: ጠንከር ያለ ትግሉን የሚያጧጡፍ ሃተታ የማይዋጥላቸው ጋዜጠኞችም አንደኛው የትግሉ እሾህ ናቸው::በፖለቲካ ሽፋን ሃገር እና ህዝብ ይበዘበዛሉ ዲያስፖራው በቅንጦት ይኖራል::ይህ የጥላቻ ፖለቲካ የወለደው ጎል ነው:: ዲያስፖራው ለሃገር የሚበጅ እንቅስቃሴ የሚያደርግበትን ጊዜ እንናፍቃለን::

የወያኔ አገዛዝ እንደ እሳት የፈጀን ዜጎች የዲያስፖራው የተልፈሰፈሰ ትግል ደሞ እያንገበገን ይገኛል::ስለዚህ የህ ለሃገር የማይበጅ የጥላቻ ፖለቲካ ተወግዶ በጋራ ሃገር ከአምባገነኑ የወያኔ አገዛ የምትላቀቅበትን የጋራ ስልት መንደፍ ተገቢ ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ…ትናንትና ማታም ኢቲቪ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ የተመሰከረውን ቆረጠው፡፡ ያ በ1984 ቤተሰቦቻቸውን ያጡትና አሳዛኝ ሰውዬ ትናንትናም በኢቲቪው ዶክመንተሪ እያለቀሱ ታዩ፡፡ እነ ዶክተር መረራ ጊዲና፣ ፕሮፌሰር መስፍን፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ግርማ ሰይፉ በሽብርተኝነት ስም መንግስት እያሸበረን ነው በማለታቸው ተብጠልጥለዋል፡፡

በሌላ በኩል ያ መከረኛ ሰውዬ የሰጡት ምስክርነት አሁንም ተቆርጧል፡፡ ባይቆረጥ ኖሮ ሰውየው ‹‹ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው!›› ነበር የሚሉት፡፡ ማን ይናገር የነበረ ቢሆንም የአሁኖቹ ወጣት የኢቲቪ ካድሬዎች ግን ቆርጠውታል፡፡ አዎ! ኢቲቪ አሁንም ዳግመኛ ቆረጠው፡፡ በእነ ዶክተር መረራና በእነ ፕሮፌሰር መስፍን ላይ ደግሞ የሌለውን መረጃ ቆርጦ ቀጥሏል፡፡ እነ አንዱ ዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ይህን ነው የሚባል ምስክር ሳይቀርብባቸው እስር ቤት ውስጥ ታጉረዋል፡፡ ቤተሰባቸው ላይ ማን ጥቃት እንዳደረሰ፣ ማን ተጠያቂ እንደሆነ የተመሰከባቸው አቶ መለስ ግን ምስክርነቱ ተቆረጠላቸው፡፡ እነ አንዱ ዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ መፍትሄ አፈላላጊ እንዲህ እያለቀሰ ‹‹ቤተሰቦቼን ፈጁብኝ! ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው›› የሚል ቢገኝ መስካሪው ካለው ባሻገር ሆድ አደር ‹‹ተንታኞችና ተመራማሪዎች፣ ጋዜጠኞች›› ለጥጠው፣ ጨምረውበት ስንት ሰቅጣጭ ፊልም ይሰራበት ነበር፡፡

አንዳንዴ ሳስበው ካድሬዎቹና ኢቲቪ (ያው ካድሬ ነው) አቶ መለስን ከአምላክ በላይ ይፈሯቸዋል/ያከብሯቸዋል፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ መጽሃፉ፣ የእምነት አባቶች እግዚያብሄር ሰውን በውሃም ሆነ በሌላ ነገር ማጥፋቱን አይደብቁም፡፡ እስኪ ስለ ይሁዳም ሆነ ሌላ ከየትኛውም መላክ በተቃራኒ ስለሚገኙት አካላት የምታወቁ ንገሩኝ? ተከታዮቹ ጥፋታቸውን ይደብቁላቸዋል እንዴ?

ምስክር ምስክር ነው፡፡ ደግሞም ከኢቲቪ፣ ከኢህአዴግ፣ ከአቶ መለስ ይልቅ ዶክተር መረራ፣ ፕሮፌሰር መስፍን፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ግርማ ሰይፉ ያሉትን አምነዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እነ አንዱ ዓለም፣ አቡበክር፣ እስክንድር፣ ርዕዮት ሳይሆኑ የሚያስሸብሩን ካድሬዎቹ፣ ባለስልጣናቱ፣ ኢህአዴግ፣ ኢቲቪም ናቸው፡፡

ያን መከረኛ ሰውዬ ደግሞ ከምንም በላይ አምናቸዋለሁ፡፡ እንዴት አልመናቸው? እሳቸው ስለ ሽብር ሲያወሩ በቅርብ ስለሚያውቋቸው ቤተሰቦቻቸው ጭፍጨፋ እንጅ ስለ ስልጣን አይደለም፡፡ እናም ኢቲቪ የቆረጠውን እኔም አልቆርትባቸውም፡፡ ልክ ነዎት! ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ኦነግ ፈጸመው ለተባለው ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ ቤተሰቦቻቸው እንዳያዩዋቸው ተደርገው ጨለማ ቤት ውስጥ ለሚታጎሩት ሰላማዊ ታጋዮች፤ ኑሮ፣ ካድሬ፣ የመለስ ራዕይ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ የአቅርቦት እጥረት……ለሚያሸብረው የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠያቂው፤ ሽብርተኝነትን በመንግስት ደረጃ አዋቅረው ያለፉት አቶ መለስ ናቸው፡፡ የፈለጋችሁ ሙት ወቀሽ በሉኝ፡፡ ይህን የአቶ መለስ ‹‹ሌጋሲ›› አልረሳውም፡፡ ቢያንስ ኢህአዴግ ራሱ አምኖ ‹‹ተሳስተን ነበር፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መለስ ዜናዊ ነው፡፡ እኛም ሆድ አደር ሆነን አብረን አጥፍተናልና ተጠያቂዎች ነን›› እስኪል ድረስ!

ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:; ቤቱን ገዛሁት የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::

ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::

ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖለኢሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል:: Minilik salsawi

Image

በእስር ከሚገኙ የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የተሰጠ መግለጫ
ሰኞ ታህሳስ 14/2006
Image
ኢትዮጵያ ከአንድ ሺህ አራት መቶ አመታት በፊት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ማህበረሰብ ካሰፈነው ፍትህ የላቀ ፍትህ ማስፈን ችላ ነበር። የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ በነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት ‹‹በሐበሻ አንድም ሰው የማይበደልበት ንጉስ አለ›› ተብሎለታል። እንዲህ አይነት ፍትህ በዚህ መልኩ ለማስፈን ምን ያህል ፍትሀዊ፣ እውነተኛ እና የሰለጠነ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚጠይቅ ግልፅ ነው። በሀገራችን የነበረው ፍትህ በጊዜው ነፃነት እና ፍትህ ፍለጋ ይዋትቱ የነበሩትን ማስጠለል የቻለ እና ዘመናትን ተሻጋሪ ነበር። ግና የዛሬው አሳዛኝ እውነታ ‹‹ሰዎች ስለ ፍትህ ግንዛቤ ባልነበራቸው በዚያ ዘመን የፍትህ ጥግ የደረሰችው አገራችን ሰዎች ሁሉ ወደ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ፊታቸውን ሲያዞሩ ለምን ጀርባዋን ሰጠች?›› ብለን እንድንጠይቅ አስገዳጅ ሆኗል።

ፍትህ ዘመን፣ ቦታና ሁኔታ የማይገድበው፣ በሃይማኖት፣ በሃገርና በብሔር ልዩነት የማይደረግበት፣ ሁሉም ለሁሉም እውን ሊያደርገው መጣር ያለበትና ሰው የመሆናችን ሚስጥር የሚፈታበት ጥልቅ እውነታ ነው። ግና ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ህጎች ፍትህን ቢደግፉትም ቅሉ በተጨባጩ ዓለም ግፍና በደል ተንሰራፍቶ ይገኛል። ቀደም ሲል አምባገነኖች በአደባባይ ይፈፅሙት የነበረውን ግፍ በዘመናችን ቅርፁን ቀይረው ፍትህ፣ ነፃነት እና እኩልነትን እየሰበኩ በተግባር ግን የህዝባቸውን ኑሮ የስቃይ ያደርጉታል።

መንግስት በሚዲያና በየስብሰባው ስለፍትህና ዴሞክራሲ በተደጋጋሚ ቢያነሳም መሬት ላይ ያለው ተጨበጭ ፍፁም ለማመን አዳጋች ነው፡፡ በማንኛውም ዘመን አምባገነኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሰብዓዊነት የጐደለው ኢ-ፍትሃዊ ተግባር እየፈጸመ ሳለ ‹‹ህዝቡ ቦታ የሚሰጣቸው ሥነ-ምግባሮች፣ ህግጋትና መልካም እሴቶችን ለማስጠበቅ›› ሲባል የተሰራ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል። በመብት ትግላችን ሂደት ለሃይማኖታቸው ታማኝ በመሆን የፍትህና የነፃነት ጥያቄ ያነሱ ወገኖቻችን ሁሉ በመንግስት አካላት ስደት፣ እስራትና ሞት የደረሰባቸው ህብረተሰቡ የሚያከብራቸውን ስነ-ምግባሮች፣ እሴቶችና ህግጋት ሽፋን በማድረግ መሆኑ በእርግጥም ምጸት ነው።

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸውና በወከላቸው ኮሚቴዎች አማካኝነት ለመንግስት ያቀረባቸው ጥያቄዎች ግልጽ፣ ቀላል፣ ሃይማኖታዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች መሆናቸውን መላው ኢትዮጵያዊና ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ያውቀዋል። መንግስት ግን ለሰው እምነት ከባለቤቱ በላይ ተቆርቋሪ፣ ለሃገር ደህንነትና ሰላም የሚያስብ ብቸኛ አካል እና ህገ-መንግስቱን አክባሪና አስከባሪ እንደሆነ በመደስኮር የመብት ጥያቄያችንን የሀሰት ቅርፅ ሊያስይዘው ሞክሯል። በመሰረቱ መንግስት ኃይልና ጉልበት ያለው አካል ሆኖ ሳለ በተቃራኒው ደግሞ ህዝብ ጉልበት ስለሌለው ሰላምንና ደህንነትን አጥብቆ የሚፈልገው ከመንግስት በላይ ህዝብ ነው። ህገ-መንግስት ደግሞ መንግስት ያለውን ኃይል በመጠቀም ህዝብ ላይ ግፍ እንዳይፈፅም የሚገድብ ህግ እንደመሆኑ በመንግስት እንጂ በህዝብ ሊጣስ አይችልም።

ከጅምሩ መንግስት የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ከጀርባው ምንም ሴራ እንደሌለው የሚያውቅ መሆኑን ብንረዳም በአባላቱም ሆነ በማህበረሰቡ ላይ ብዥታ እንዳይፈጥር ዓላማችንን እና ጥያቄዎቻችንን ለሁሉም ግልፅ አድርገናል። ይህም ሆኖ ግን በተለያዩ ብሄሮችና ሃይማኖቶች መካከል መከባበር እንዲኖር የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት መንግስት ሙስሊሙን እርስ በእርስ፣ እንዲሁም ሙስሊሙን እና የሌላ ሀይማኖት ተከታዩን ህብረተሰብ ለግጭት የሚዳርጉ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። አሁንም እያደረገ ይገኛል። ይህ አደገኛ አካሄድ ሊከሽፍ የቻለው በህዝባችን ብስለት እና ጨዋነት ብቻ ነው። ኩሩው የኢትዮጵያ ህዝብ ከህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የመረጠው በሳል አካሄድ ሊመሰገን የሚገባው ነበር። ይህ በሳል የህዝብ ምላሽ ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ሊያጋጭ ይችል የነበረውን የመንግስት እንቅስቃሴ ቀልብሶ የህዝባችንን ጨዋነት፣ ተከባብሮ የመኖር ብቃት እና አስተዋይነት ዳግም ማሳየት ችሏል። ክስተቱም በታሪክ መዝገብ ውስጥ በወርቃማ ጽሁፍ የሚሰፍርበትና ለትውልድ የሚተረክበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጸማቸው በደሎች በህዝቡ ብስለት የከሸፉ ቢሆኑም ለህዝቡ ደንታ የሌለውና ስህተቱን አምኖ መቀበልን ውርደት አድርጐ የሚቆጥረው መንግስት ግን ህዝብ እየተቃወመው ህገወጥነቱን ቀጥሎበታል። በዚህም ምክንያት ‹‹መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን! ያልመረጥናቸው ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ወርደው ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ! የማናምንበት እምነት በግድ አይጫንብን!›› ብሎ የጠየቀውን ህዝብ ከነወኪሎቹ ለእስር፣ ለስደት፣ ለእንግልት እና ለሞት ዳርጓል።

የኢፌደሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 2 ‹‹ማንኛውም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም›› ይላል። ነገር ግን ለፀጥታ ተግባር የተሰማሩት አካላት ህጉን በመጣስ ሰላማዊ ግለሰቦችን ሲይዙ የታጠቀ የጠላት ኃይል ላይ እንኳ ሊፈፀም የማይገባውን ግፍ፣ ድብደባ፣ ወከባ እና ስቃይ ይፈፅማሉ። ከፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ሳያገኙና ለባለቤቱ ሳይሰጡ ያስራሉ። ህግ ጥሰው ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት በኋላ የግለሰቦች ቤት ላይ ብርበራ ያካሂዳሉ። በብርበራው ወቅት በሚፈጥሩት ሁከት በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ስጋት እና ድንጋጤ ይፈጥራሉ። ይህ ሁሉ የሚካሄደው ህዝቡ በፍርሃት ከመብት ጥያቄው ወደ ኋላ እንዲል ቢሆንም ውክቢያውና እንግልቱ ግን የመብት ጥያቄው ይበልጥ እንዲፋፋም፣ ህዝቡ ፍርሃቱ ለቅቆት ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ያለውን ልዩ ጣዕም እንዲያጣጥም እና ሙሉ መብቱን ወደ መጠየቅ እንዲሸጋገር ነው ያደረገው።

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀፅ 1 ‹‹ማንኛውም ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው›› ይላል። ህገ-መንግስቱ ይህን ቢልም ዜጐች መሆናችንን ጥርጣሬ ውስጥ በሚከት መልኩ ከያዙን በኋላ በማእከላዊ በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳን ቅዝቃዜው በማይቻለው ‹‹ሳይቤሪያ›› ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል ለ3 ወራት አጉረውናል። መቋቋም የሚያዳግተውን የማሰቃያ ስልታቸውን በመጠቀም ያላሰብነውንና ያልሰራነውን ‹‹እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ!›› ብለው አስገድደውናል።

ለቀጠሮ ፍርድ ቤት ስንቀርብ የደረሰብንን ሰቃይ አሳይተን ቢያንስ ፍርድ ቤቱ ስቃዩን እንዲያስቆምልን ጠይቀን ነበር። ያገኘነው ውጤት ግን ወደ ማዕከላዊ ስንመለስ ከመርማሪዎቹ በቀልና ተጨማሪ ስቃይ ነበር። ፍርድ ቤቱ የደረሰብንን ስቃይና የተከሰስንበትን ጉዳይ አግባብ እንዳልሆነ አይቶ ዋስትና ሰጥቶን ሳለ ፖሊስ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ጥሶ ዋስትናውን በመከልከል ክስ መስርቶብናል። አሰቃዮቻችን ስለ ህገ-መንግስት እና መብት ስንናገር ‹‹ህገ-መንግስቱን ቀደህ ጣለው!›› እና ‹‹እኛ መሰዋዕትነት ከፍለን ነው እዚህ የመጣነው!›› ወ.ዘ.ተ በማለት ለህግም ሆነ ለሰው ክብር ደንታ እንደሌላቸው አሳይተውናል። ይህ ሁሉ መከራ በተቃራኒው ህገ-መንግስቱን ለማስከበር መታገል የሚያስፈልግበት ትክክለኛ ወቅት ላይ መሆናችን እንዲሰማን፣ እውነተኛ ፅናትና ወኔ እንዲኖረንም አድርጎናል።

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 5 ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ፣ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም። በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም›› የሚለውን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ እዚያው ማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት እያለን የደረሰብንን ስቃይና እንግልት ገልፀን ክስ አቅርበን ነበር። በምርመራ ጣቢያው ቃላችንን የሰጠነውም ሆነ የፈረምነው ተገደን መሆኑን ገልፀን ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀናል። ሆኖም ግን ክሳችን ተዳፍኖ እና ተድበስብሶ እንዲቀር በመደረጉ በጊዜው ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል። ክስ ተመስርቶብን ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበን በኋላም በድጋሚ ጉዳዩን ያስረዳን ሲሆን አሁንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ የሚያደምጥበትንና ምላሽ የሚሰጥበትን ቀን እየተጠባበቅን እንገኛለን።

ከቤተሰብ፣ ከጠበቃና ከሀኪም ጋር እንዳንገናኝ አድርገው የፈፀሙብን የህግ-ጥሰት እና አስገድደው በማስፈረም እና ድምፅና ምስላችንን በመቅረፅ የፈፀሙብን በደል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 424 መሰረት እስከ አስር አመት የሚያስቀጣ ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ነው። ነገር ግን የፖሊሱም፣ የዐቃቤ ህጉም፣ የፍርድ ቤቱም አለቃ በሆነውና የፍትህ ስርዓቱን ሰብስቦ በያዘው ገዚው ፓርቲ አምባገነንነት በተቃራኒው እኛ ተከሳሾች ሆነን ጉዳያችን ‹‹በፍርድ ቤት›› በመታየት ላይ ይገኛል።

በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል። ከአስራ አራት ሰዓታት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና ዓይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና ድብደባ እንቅልፍ በመንሳት፣ ሃይማኖታችንንና ክብራችንን በመንካት፣ ፂማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ እንዲሁም ሰላት በመከልከል፣ ቤተሰብ፣ ጠበቃ፣ ሀኪምና የሃይማኖት አባት እንዳናገኝ በማድረግ፣ ከአቅም በላይ የሆነን ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ‹‹ልጅህን እንገለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ ሀይላንድ በማንጠልጠል መሀን እናደርግሃለን!›› ሲሉ በማስፈራራት ከፍተኛ የሆነ እንግልትና ስቃይ አድርሰውብናል።

ይህም አልበቃ ብሏቸው በሃገሪቱ የቅጣት ጣሪያ የመጨረሻ የሆነውን የወንጀል አንቀፅ ጠቅሰው ከሰሱን። ‹‹ህገ-መንግስት ይከበር!›› ብለን በጠየቅን ህገ-መንግስትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ወነጀሉን። ተቃውሟችን ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ሳለ ‹‹ከእኛ ውጪ ያሉ እምነቶች ከሃገሪቱ መጥፋት አለባቸው ብለዋል›› ሲሉ ከሰሱን። ሃይማኖታዊ የመብት ጥያቄያችንን ‹‹ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ነው›› በሚል ሊያጠለሹ ሞከሩ። ‹‹ህዝብ ያልመረጣቸው የመጅሊስ አመራሮች በህገ-ወጥ መንገድ መጥተው አይመሩንም! ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ!›› ባልናቸው ‹‹መንግስት ይውረድ! መንግስት አያስተዳድረንም! ብለዋል›› በሚል ወነጀሉን።

ያዘጋጁት ክስ የህግ ባለሙያ ቀርቶ ማንም የህግ ግንዛቤ የሌለው ሰው በሚረዳው ደረጃ በህግ ስህተቶችና አመክኖአዊነት በጐደላቸው ሃሳቦች የተሞላ፣ በህግ ወንጀል ያልሆኑ አረፍተ ነገሮች እና ቃላት ወንጀል ተደርገው የተጠቀሱበት ፍፁም ተራ እና የሃገሪቷን የፍትህ ሁኔታ የሚያስገምት ክስ ነው። ምንም እንኳን ‹‹ክሱን ዳኞች ስርዓት ሊያስይዙት ይገባል›› በሚል የፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም እና ክሱ ላይ ያሉ ስህተቶችን ሁሉ ነቅሰን በማውጣት የክስ መቃወሚያ ያቀረብን ቢሆንም የዳኞች ብይን ክሱን ይበልጥ የማይገባና ውስብስብ አደርጎታል።

ከታሰርን ጀምሮ የደረሱብን የህግ ጥሰቶች እና የፍትህ እጦቱ ከፍርድ ቤት ሂደት ራሳችንን ሙሉ ለሙሉ እንድናገል የሚገፉ ነበሩ። ሆኖም ግን የተወነጀልንበት ክስ ምን ያህል ከእውነት የራቀ፣ ጥያቄያችን ሃይማኖታዊ እና ህገ መንግስታዊ መሆኑን እና እንቅስቃሴያችንም ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ለህዝባችን በፍትህ አደባባይም ጭምር ለማሳየት ስንል የፍርድ ሂደቱ ውስጥ መግባቱ የተሻለ መሆኑን በማሰብ ሃሳባችንን ቀይረናል።

መንግስት በአግባቡ ሊተውነው ያልቻለውን አሳፋሪ የፍርድ ቤት ድራማውን ህዝብ እንዳያይበት ለመሸሸግ በመገደዱ ‹‹የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለህዝብ ግልፅ በሆነ ችሎት የመስማት መብት አላቸው›› የሚለውን ህገ-መንግስታዊ መብት በመጣስ ችሎቱ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ቆይቷል። በዝግ ችሎቱ የምስክር መስሚያ ጊዜ ብዙ አስገራሚ ድራማዎችን አይተናል። ዓቃቤ ህጎች ዳኞች የሚሰጡትን ብይን እንደማይቀበሉ እስከመግለጽ የደረሱበትን እና ምስክሮችን ማለት ያለባቸውን አሰልጥነዋቸው እንደሚያመጡ አምልጧቸው የተናገሩበትን አጋጣሚ ታዝበናል። በወቅቱ ‹‹ጋዜጠኞች፤ ዲፕሎማቶች እና ህዝባችን ምነው ይህንን አይተው በነበር?›› ብለን ከመመኘት ውጭ ምርጫ አልነበረንም።

ማንኛውም ታራሚም ሆነ ተጠርጣሪ በማረሚያ ቤት ሊያገኛቸው የሚገቡ በህግ የተደነገጉ መብቶች አሉ። መብቶች ግን እንደተለመደው ከወረቀት ዘለው መሬት ጠብ ማለት አልቻሉም። የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ላይ ሲሆን ደግሞ መብቶች በቅጣት ይተካሉ። ካለው የጋራ ችግር በተጨማሪ በእኛ ላይ በተለየ መልኩ በጥላቻ እና በበቀል ስሜት የደረሰብን እንግልት ህሊና ያለውን ሁሉ የሚጎዳ ነው። ከቤተሰቦቻችን መካከል ከጥቂቶች ጋር በስተቀር እንዳንገናኝ ተደርጓል። የምንጠየቅበትንም ሰዓት ከእስረኞች ሁሉ በመለየት በቀን ለሃያ ደቂቃ ብቻ እንዲሆን በማድረግ አድሎ እና መገለል ተፈፅሞብናል። በመካከላችን ልጆቹና ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት የተደረገም አለ። ከሁሉም በላይ ከባድ ህመም ያለባቸው፤ ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ የታዘዘላቸው፤ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላቸው የተመራላቸው እና በማእከላዊ የደረሰባቸውን ድብደባ ለመታከም የጠየቁ ለዓመት ከአራት ወር በላይ መፍትሄ ሳያገኙ ስቃዩን ይዘው ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ይገኛሉ። ማረሚያ ቤት የደረሱብን እና እየደረሱብን ያሉ አድሎዎችንና እንግልቶችን ሁሉ ዘርዝረን ጉዳያችንን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ብናቀርብም የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ፍርድ ቤት እንኳ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ሶስት ጊዜ ቀጠሮ አሳልፈዋል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴውን ከጀመረ በኋላ መንግስት በነጋዴውና በተማሪው፣ በመንግስት መዋቅር ውሰጥ በሚሰሩ አካላት፣ በሃይማኖት አባቶች እና በአስተማሪዎች፣ እንዲሁም በኢስላማዊ ተቋማት ላይ ሰብዓዊነት የጎደለው እና ህገ-መንግስቱን የሚጻረር የመብት ጥሰት መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በበርካታ የክልል ከተሞችና ሙስሊሙ ደስታውን በሚገልጽበት የዒድ ዕለት በአዲስ አበባ ፈጽሞ ልንረሳው የማንችለውና ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ፈጽሞብናል። የምንሳሳላቸው እና የምንወዳቸው ወገኖቻችንን እና ቤተሰቦቻችንን ለእስር፣ ለሞትና ለአካል ጉዳተኝነት ዳርጎብናል። ይህ ሁሉ ስቃይ እና መከራ በአንድ በኩል የመንግስትን ግፍ እና ለህግ ተገዢ አለመሆን ሲያጋልጥ በሌላ በኩል የህዝባችንን ፅናት እና ቁርጠኝነት አሳይቶናል። በየትኛውም ሃይማኖት፣ ባህል እና ልማድ ግፍ የተጠላ ሲሆን ለመብት ሲሉ መሰዋት ደግሞ ክብር ነው። ስለዚህ ለሃይማኖታችሁ፣ ለክብራችሁ እና ለደህንነታችሁ ለተሰደዳችሁ፣ ለታሰራችሁ፣ ለተደበደባችሁ እና ቤተሰቦቻችሁን ላጣችሁ ሁሉ ያለንን ክብር እንገልጻለን፤ በሀገራችን ለሚሰፍነው የሃይማኖቶች ነፃነት እና እኩልነት የመሰረት ድንጋይ የሚሆነው ዛሬ እናንተ የከፈላችሁት መስዋእትነት ነውና!

ለሁለት ዓመታት ያለ ምንም መሰላቸት እንግልቱ፣ ማስፈራሪያው፣ እስሩ፣ ድበደባው እና ግድያው ሳይበግራቸው እና ሰላማዊውን የተቃውሞ መስመር ሳይለቁ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ፍቅር ላሳዩ፣ እንዲሁም ይህን ድንቅ ታሪክ ለሰሩ አባቶች፣ የሃይማኖት መሪዎችና አስተማሪዎች /በተለይ ደግሞ ወጣቶች እና ሴቶች/ ያለንን ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ልናቀርብ እንወዳለን። በሰራችሁት ሁሉ ተደስተናል፤ ኮርተንባችኋልም!

መንግስት የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ያደረገውን ሙከራ ንቆ በመተውና ጉዳዩን በብስለትና በሰከነ መንፈስ በማየት፣ እንዲሁም እውነታውን ለመረዳት ጥረት በማድረግ ረገድ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣ በተለይም ህዝበ ክርስትያኑ ላደረጋችሁት ትብብር ሳናመሰግን አናልፍም። በእውነቱ የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደን በህዝብ ደረጃ ተከባብረን ስለመኖራችን ከተነሱ ምሳሌዎች ሁሉ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ያሳየነው መከባበር እና አንድነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ይህ ብሄራዊ አንድነት የበለጠ ተጠናክሮ በጋራ ለምንገነባት ሃገራችን ታላቅ ብርታት እንደሚሆን ጠንካራ እምነት አለን።

በተጨማሪም የፕሬስ ነፃነት በተነፈገበት ተጨባጭ የመብት ጥያቄያችንን እውነታ ለመገንዘብ ማስፈራሪያዎችን እና ዛቻዎችን አልፋችሁ፣ የመንግስትን የተሳሳተ እና ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ ለይታችሁ ሂደታችን ላይ አዎንታዊ አስተያየቶች እና ገንቢ ትችቶችን ለሰጣችሁ ጋዜጠኞችና በሚዲያው ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ወገኖቻችሁ ያጡትን ፍትህ እና ነጻነት በሃገራችሁ ለማየት በመጓጓት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ለማበርከት የምትጣጣሩ በስደት የምትገኙ ሙስሊሞችና የሌሎች ሀይማኖቶች ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ ላደረጋችሁት ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። በሀገር ውስጥ ለተጠናከረው የአጋርነት ስሜት የእናንተ አስተዋጽኦ የመጀመሪያውን ድርሻ ይይዛል።

በአጠቃላይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ነጋዴው፣ አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ፣ ተማሪው፣ ሴቱ፣ ወንዱ፣ ወጣቱ፣ አዛውንቱና ሌላውም፣ እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ስር ሆናችሁ የመንግስትን የተሳሳተ አካሄድ ስትቃወሙ የነበራችሁ ዳኞች፣ ዓቃቤ ህጎች፣ አባቶች፣ ፖሊሶች፣ የጦር ሰራዊትና የፓርላማ አባላት በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን። የጥረታችሁን ፍሬ በቅርቡ ያሳያችሁ ዘንድም አላህን እንለምናለን!

መልእክታችን

1/ በሙስሊሞች መካከል እና በሙስሊሙና በክርስትያኑ መካከል የታየውን አንድነትና መከባበር ሁላችንም በጋራ እንድንጠብቀው፣ እንዲሁም መሰረቱ የፀና ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ እንድንጥር አደራ እንላለን። ሀገራችን ከእርስ በእርስ ሽኩቻዎች ወጥታ የእድገትና ብልጽግና ጉዞ እንድትጀምር ከተፈለገ ትክክለኛ የሃይማኖት ነፃነት፣ እኩልነት እና መከባበር በቅድሚያ እውን መሆኑ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው። የሃገራችንን እድገት የጋራ አላማ አድርገን፣ የጋራ ተጠቃሚ ሆነን መኖር የምንችለው ስጋትና ጥርጣሬውን በፍቅርና መተማመን ስንተካው ነው።

2/ በፅናት ሰላማዊ የመብት ትግሉን የምንቀጥል መሆኑንና የሚያስከፍለንን መስዋዕእትነት ሁሉ ለመክፈልም ዝግጁ መሆናችንን ለህዝባችንም ሆነ ለመንግስት መልእክት ለማስተላለፍ እንወዳለን። ለቀጣዩ ሰላማዊ የመብት ትግል እርከንም እኛም ህዝባችንም በሙሉ ዝግጅት ላይ መሆናችንንና ለመብታችን ተግተን ሰርተን መስዋዕት ከመሆን ወደኋላ የማንል መሆኑን ስንገልጽ በከፍተኛ ወኔ ተሞልተን ነው!

3/ መንግስት እየፈጸማቸው ያላቸውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ተግባራት፣ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈጸመ ያለውን እስራት፣ ግፍ፣ መስጂድ ነጠቃ፣ የሀሰት ውንጀላና የሃይማኖት ሰዎችን፣ ጋዜጠኞችንና የመብት ጠያቂዎችን በሽብርተኝነት መፈረጅና መሰል ህገ መንግስታዊ የመብት ጥሰቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን። በማእከላዊና በተለያዩ እስር ቤቶች የሚፈጸሙት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዲቆሙና የህሊና እስረኞችም መለቀቅ እንደሚገባቸው ለመግለጽ እንወዳለን። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእውነተኛ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ እና ልማት ባለቤት ሆኖ ማየት የዘወትር ህልማችን መሆኑንም ሳንገልጽ አናልፍም፡፡

በመጨረሻም በቃል ኪዳናችን ጸንተንና መነሻው ላይ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተንቀሳቅሰን ፍጹም በሰለጠነና በተጠና መልኩ የተሟላ ፍትህ እና ነፃነት ለማግኘት በጽናት እና በቆራጥነት ሁሉም ባለድርሻ አካል እንቅስቃሴውን ከዳር እንዲያደርስ አደራ ለማለት እንወዳለን። የእንቅስቃሴው ማብቂያ ድልና ስኬት እንደሚሆን አንጠራጠርም!

አላሁ አክበር!

ግልባጭ፡- እዚሁ አገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ለሚገኙ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች

Image

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››
እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡
ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ
በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡
የህወሓት ኃይል
ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡
በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡
በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡
ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡

ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ
ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)

የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)

ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡››
መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡
የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)

ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡
ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።

የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል
የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡
ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡
ምን እንጠብቅ?
ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁ&#4

ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በሃዘን ሲመታ ፣ ደመናው ሲጠለሽ ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ ፤
የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው …….. የክፉው ቀን ጅማሮ ፣ የውርደት ሃሌታ ፣ የሃገር አልባነት ስሜትና የዜግነት
ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር ።

ውርስ ከአባት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ካልቻለ ፤ አባት የጀመረውን ልጅ ካልቋጨው ፤ አዲስ መንግስት ሲቀየር
የድሮውን በጐ ነገር ሁሉ ብትንትኑን አውጥቶ ካጠፋ ፤ የትውልድ ቅብብሎሽ ገደል ገባ ማለት አይደል ? እናም
በአገሬ ምድር ላይ የእርግማን ዘመን ያኔ “ በ1991 “ “ ሀ “ ብሎ ጀመረ ።

ሌባው ከሳሽ … ቀማኛው ፈራጅ የሆነበት ፤ አባት ተቀምጦ ልጅ የሁሉ ነገር አዛዥ ሲሆን ፤ አህያ ወደ ሊጥ …
ውሻም ወደ ግጦሽ ከተሰማራ …. እነሆ ዘመነ ብልሹ ላይ መድረሱን ያልተረዳ ካለ … እሱ ባይፈጠር …. እናቱ ሆድ
ውስጥ ውሃ ሆኖ ቢቀር ይሻለው ነበር ።

አገር ሲገነጠል ዝምታ ፤ ንብረት ከመሃል አገር ተግዞ ሲያልቅ ዝምታ ፤ ገዳማት ሲታረሱ ፣ ቤተ ክርስቲያናት
ሲዘረፉና ታቦታት በየገበያው ሲቸበቸቡ ዝምታ ፤ ደን ሆን ተብሎ በሰደድ እሳት እንዲወድም ሲደረግ ዝምታ ፤
ግዙፉ የአገር መከላከያ ኃይል እንደተረት አይናችን ስር ሲበተን ዝምታ …….. የምንወደው ዝነኛው የአየር
ኃይላችንም አብሮ ተደርምሶ እንዳልነበረ ሲሆን ዝምታ ነገሰ ። የሚቆጭ ፤ የሚመክር ፤ የሚቆጣና ሃይ የሚል
ወንድ ጠፋ ። የአድዋና የማይጨው አርበኞቻችን የክብር ሃውልቶች ሲፈርሱም ዝምታ ፣ የጦር ካምፖቻችንም
ታሪካዊ ስያሜ በማን አለብኝነት ለጐጠኞች ስያሜ ሲውልም ዝምታ ነገሰ ።

ዛሬ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዋሺንግተን በሚመላለሱና ከዘመነኞቹ ጊዚያዊ የይሁኝት ፈገግታ በተቸራቸው የኛና የኔ
ቢጤዎች አማካኝነት የቬተራን አሶሴሽን እናቋቁማለን ፤ የአየር ኃይሉንም ታሪክ እንፅፋለንና ለዕርዳታ እጃችሁን
ዘርጉ የምትል የኢሜል መልዕክት ደርሳን በትዝብት ተደምመናል ። እስኪ ከበጐ መንፈስ የመነጨ ነው ብለን
እንመን ። ግን ሥጋት አለን !

የአየር ኃይላችንን ታሪክ ለትውልድ ዘግቦ ማስቀመጥ ምንኛ የተቀደሰ ዓላማ ነው ! የአቭዬሽን ቬተራን ማህበርን
ማቋቋምስ እንዴት ትልቅ ራዕይ አለው ? ነገር ግን የአንድ መንደር ልጆችን ዓላማ አድርጐ በጐጠኝነት ማማ ላይ
እየተንጠለጠለ እኛ እና እነሱ ፤ የቀድሞውና አዲሱ ፤ ዲሞክራቲኩና የአንድነት አርበኛ እያለ ሊለያየንና
ሊከፋፍለን ሌት ተቀን የሚተጋው ጐጠኛና ሽፍታ መንግስት የሚገነባውን ከእውነተኛው አየር ኃይል በቅጡ
መለያየት ያስፈልጋል ።

ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል በማምሺያ እድሜ መባጀት ጉልበት ማባከን እንዳይሆን ! የነፃነት አርበኛው ጀ/ል ተጫነ
መስፍንና የሽፍቶቹ ጀ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቤ) በምን ተዓምር ለአንድ ዓላማ ሊሰለፉ ይችላሉ ?
በምንስ ሂሳብ የህ.ው.ሃ.ቱ. አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) የቬተራን አሶሴሽን መስራች ሆኖ በሸራተን አዲስ ይደግሳል ?
እነዚህ ሁለት ፍጥረታት ውሃና ዘይት ናቸው ። በዓላማም በራዕም አንድ አይደሉም ….. አሳዳጅና ተሳዳጅ !
ወንጀለኛና ወንጃይ … አርበኛና ባንዳ .. ውሃና ዘይት ናቸው ። ሊዋሃዱ አይችሉም ።

የእኛው አየር ኃይል በጅምላ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ተብሎ እንደ ጉም በተበተነበት ዘመን ላይ ተቆሞ ….. ለአገር
የደሙ ከያሉበት ታድነው በውርደት በየማጐሪያው ተወርውረው ልባቸው ተሰብሮና ጥሪት አልባ ሆነው በሰው
እጅ ላይ እንዲወድቁ በተበየነበት ዘመን ላይ ፤ ዛሬ ከሲሶው በላይ እውነተኛው አርበኛ አገር አልባ ሆኖና ተዋርዶ
አልጋ ላይ እየዋለ ያለ ደጋፊና አጋዥ ቀና ማለት ባቃተው ሰዓት ላይ የቬተራን አሶሴሽን እያቋቋምን ነው ሲሉንና
ግባታውን በገንዘብ እንድንደግፈው ስንጠየቅ እውን ለእውነተኛው የአየር አርበኛ አገልግሎት እንዲመስለን ይሆን ?

በእርግጥ ጥቂቶች ደም የተገበረበትን አርበኝነታቸውን ሳይሆን የሽንፈት ታሪካቸውን አሜን ብለው በመቀበል
በውርደት በጅምላ የተለጠፈብንን የጨፍጫፊነት ማንነት ፤ በተጨማሪም ለአገር በመሞታችንና ደማቸንን
በማፍሰሳችን ምክንያት እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች መሆናችንንና/መሆናቸውን
ዘንግተው “ ማምሻም እድሜ ነው “ በሚል የመሰንበት ጉጉት በድለላ እያግባቡን ማየታችን ከላይ በበጐ መንፈስ
ተነሳስተው ነው የሚለውን አቋማችንን እየሸረሸረብን ተቸገርን ።

ለመሆኑ በማን አየር ኃይል ….. በነማንስ ደም ይቀለዳል ?
የእነ ሚሽካ ባቢቼቭ አየር ኃይል …. የእነ ባህሩ ካባ አየር ኃይል …. የእነ ጀነራል አበራ ወ/ማሪያም …. የእነ ጀነራል
አሰፋ አየነ … የእነ ጀነራል አሰፋ ገ/እግዚ …. የነ ጀነራል ታዬ ጥላሁን ….. አየር ኃይል እንዴት ሆኖ ከዚህኛው ዘመን
ጋር ይዋሃዳል ?

እነ ጀ/ል ለገሰ ተፈራ ፣ ኰ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ፣ ኰ/ል ታደለ አለሙ ፣ ኰ/ል ትርሲት ፣ ኰ/ል ወርቁ ፣ ሻ/ል
ጥላሁን በዛብህ ፣ መ/አ አባይነህ ኃይሉ ፣ መ/አ ደመላሽ መኰንን የመሳሰሉት በምርኰና በእስር መስዋዕትነት
የከፈሉበት ፤
የነ መርዕድ ዳጨው ደም …. የነ አማኑኤል አምደ ሚካኤል …. የነ ጥላሁን ኃይሉ ፤ የነ ለዊ ደሬሳ …. የነ መንግስት
ዓለሙ … የእነ ሊ/ካዴት ይኩኖ ታደሰ ጨቅላና አድገው ያልጨረሱ ልጆች ደም ፤ የነ ተስፋዬ ብ/ሥላሴ …. የነ
ማ/ቴክ ደገፋ ሆራ …. የነ ኰ/ል ጥላሁን ቦጋለ ….. የነ ሰለሞን መክብብ …. የነ አብረሃም ስንቄ ደም ላይ እንዴት
ዳንኪራ ይጨፈራል ?

እነ ጀ/ል ፋንታ በላይ …. ጀ/ል አመሃ ደስታ …. ጀ/ል ሰለሞን በጋሻው …. ጀ/ል ተስፉ ደስታ … ጀ/ል ንጉሴ ዘርጋው
… ጀ/ል ገናናው መንግስቱ …… እንዲህ ደማቸው ደመ ከልብ ይሁን ? ለአፍታ ቀና ብለው ቢያዩስ ምንኛ
በባልንጀራቸው ያፍሩ ይሆን !

ዘመናቸውን ሙሉ ለአገራቸው የአየር ክልል መከበር ጨርቄን ማቄን ሳይሉ …… ንብረት ማፍራት …. ሃብት ማካበት
…. ሚስት ማግባትና የአብራካቸውን ፍሬ ለማየት ሳይጓጉ እድሜያቸውን የጨረሱ የአየር ኃይሉ ጌጦችና የአገር
አለኝታዎች እንደ ወሮበላ ማጅራት መቺ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ በተሆነባት አገር ላይ እንዴት አይነቱ የአየር
ኃይል የአቪየሽን ቬተራን አሶሴሽን ይገነባል ?

እነ ኰ/ል ታከለ አበበ ፣ ሻ/ቃ አለማየሁ እሳቱ ፣ ሻ/ቃ ከበደ ጫኬ ፣ በላይነህ ተገኝ ፤ ደበበ ሞላ …. ደሳለኝ
ስሜነህ … …. ወዘተ በጉልበት ከአገር ተሰደው በበረሃ ላይ ያለ አልቃሽና ቀባሪ ነፍሳቸውን እንዲሰጡ ላደረገ ሽፍታ
፤ እነ ሻ/ል ፍሰሃ መለስን በእስር ቤት ለገደለ ወንበዴ እንዴት ብለን ክብራችንን ዝቅ አናደርጋለን ?
እነ ኰ/ል ብርሃነ መስቀል ፤ ኰ/ል ሰለሞን ከበደ ፤ ኰ/ል ግርማ አስፋው ፤ ሻ/ል ክፍሌ ውቤ ከእድሜያቸው ከሩብ
በላይ በእስር የገበሩበት ምክንያት ምን ይሆን ? ዘንግተነውስ ይሆን ?

እነ ማ/ቴክ ሽብሩን .. እነ ማ/ቴክ ፀጋዬ ሁሉቃን … እነ ማ/ቴክ ግርማ ሰቦቃንና የመሳሰሉትን በአጠቃላይ
አፕሬንቲሱን ፣ ኤርሜኑን ፣ ቴክኒሻኑን ፣ የአየር ፖሊሱን ፣ በራሪውን ፣ መኰንኑን ፣ ባሌ ላላ ማዕረግተኛውን
እንደ አሮጌ ቁና ሜዳ ላይ በትኖ በስተ እርጅና የሰው እጅ እንዲያዩ የተደረጉበትን እንደ ጨዋታ ቆጥረነው ይሆን ?

እነ ኰ/ል ብርሃኑ ከበደን ፤ ኰ/ል ብርሃኑ ውብነህ ፤ ኰ/ል ጣሰው ወዳጄነህን ….. ኰ/ል ጌታቸው መንገሻን ….
ኰ/ል መንገሻ ሁንዴን …. ኰ/ል የሺጥላ መርሻን ….. ኰ/ል ይልቃልን … አለማየሁ አጐናፍርን …. አለማየሁ ኃይሌን
…. ስንታየሁ አሽኔን … መስፍን መንግስቴን ….. በኃይሌ ደግፌን … ጂልቻ ዱራን …. ኰ/ል ነብዩን …. አሰፋ ተገኝን ፤
አቦነህ ነጋሽን … ዳዊት ወንዲፍራውን ፤ መስፍን ግርማን ……. በአጠቃላይ ስማቸው ያልተዘረዘሩትን የተዋጊውን ፣
የትራንስፖርትና የሄሊኮፕተር ስኳሮኖች በራሪና የቴክኒክ ባለሙያ ሲቪል ሰራተኞችን ሁሉ አገር አልባ አድርጐ …
እንዴትስ አይነት የአቪዬሽ ቬተራን ማህበር ሊመሰረት ይችላል ?

ጀነራል ተጫኔ መስፍን ደም ገብረው በአቀኑት አየር ኃይል ውስጥ አበበ ተ/ኃይማኖት አንዳችም የአየር ኃይል
ትምህርትና ዕውቀት ሳይኖረው የቬተራኖቹ አየር ኃይል አዛዥ ሆኖ በራሪ ተማሪዎችን ሲሸልም በአፍሪካ ውስጥ
በበረራ ሰዓታቸው ተወዳዳሪ የሌላቸው የተዋጊ አውሮፕላን በራሪና ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜ የተቃጣባትን ወረራና
ጥቃት በጀግንነት የመከቱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጅ ጀነራል ተጫነ መስፍን በዚህ አይነት በአሳላፊነት
መታየታቸው ምን ያክል አገር አልባ እንደሆንን አያሳይ ይሆን ? እውን ታዲያ ይሄ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ነው ?
እንደዚህ አይነት አገር የማታከብረው ቬተራንስ የት አገር ነው ያለው ?

ጀነራል ተጫኔም በዚህ አይነቱ ሁኔታ እራሳቸውን ለማሳነስ ባይፈቅዱ እንዴት ጥሩ ነበር ? እነ ጀነራል መስፍን …
ጀነራል ተሻለ … ኰ/ል ጥላሁን ነብሮን የመሳሰሉት ባለ ወርቅዬ ታሪክ ባለቤቶች እንደ አገር አልባና ሁለተኛ ዜጋ
ተገልለውና ተጥለው ያለ ፎቶ ግራፍ ይኖሩ የለ ?
በእርግጥ በዚህ ዘመን ጀ/ል ተጫነ ከአቻዎቻቸው በተለየ ሁኔታ ከነ ሙሉ ክብራቸውና ጥቅማቸው በአገራቸው
በቬተራን ማዕረግ እየኖሩ ያሉ ብቸኛ ሰው ናቸው ። ቀደም ሲልም እንደ ጀ/ል ተጫኔ ሁሉ ጀ/ል ሰለሞን በየነ
በዚሁ በተንቆጠቆጠው ማማ ላይ ተሰቅለው እንዳሉ እናውቃለን ፤ ይህ እንግዲህ የልደታ አየር ምድብ አዛዥ
ተደርጐ ተሹሞ የነበረውን ሻለቃ ተስፋዬ ተገኝን ሳንዘነጋ ፣ የሚሊታሪ አታቼውንና ጀ/ሉን ኃይለ ሥላሴ ገብሩንም
ማ/ቴክ ረዳዕይና ማ/ቴክ ክንድያን እንዲሁም ካላዩ አፅበሃንም በማሰብ ነው …….. ። በእርግጥ አድሎው አይን
ያወጣ ቢሆንም ከወደ ኰረም ፣ አዲግራትና አድዋ የመወለድ ጣጣ ነው እያልን ቆይተናእነሆ ምክር እንለግሳለን …….

የአየር ኃይላችንን ታሪክ መፃፉን እናበረታታለን ። ይሁን እንጂ …….
ዛሬ የሚፃፍ ካለ … አየር ኃይሉ እንዴት እንደተመሰረተ ብቻ ሳይሆን እንዴትም እንደፈረሰ ፤ ለአገር የደሙና የሞቱ
እንዴት እንደወንጀለኛ በየማጐሪያው እንደተጋዙ … ህብረ ብሄሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እንዴት ወደ አንድ ዘር
የሽፍቶች ስብስብነት እንደተቀየረ የሚተርክ ካልሆነ …. ጀ/ል ተጫነ መስፍን ፣ ኰ/ል አስፋው አየልኝንና
የመሳሰሉትን የትውልድም የታሪክም ተወቃሽ ፤ የአገርም ክህደት እንዳይሆን ይታሰብበት ።

የአቭዬሽን ቬተራን አሶሴሽንም ከመመስረቱ በፊት አርበኛውን ከጐጠኛው መለየት ፤ እውነተኞቹን የአየር
አርበኞችና ቬተራኖች ከብቀላ ፍርደኝነታቸው ነፃ ማድረግና ዝነኛውን አየር ኃይል በጅምላ ከተለጠፈበት
የጨፍጫፊነት ስያሜ እንድናላቅቅ የየበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል ።

ጨረስን ።
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ ።

ትብብር ለመልሶ ማቋቋም
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል
Source-ethioforum.com
Image