“እንግሊዛዊ ብሆን የኢትዮጺያ ሚዲያ ብዙ ያወራልኝ ነበር”

ጋዜጠኞች ቁጭ ብለው የሞሪኒሆን ፈረስ ሲጠብቁ ገንዘቤ 3 ሪኮርዶችን ሰበረች:: ከአድዋ ድል ቀጥሎ የኢትዮጺያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገው አትሌቲክስ ነው:: አትሌቶቻችን በሄዱበት ውድድር ሁሉ ድልን ተጎናፅፈው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን አለም ላይ ከፍ አድርገው ያውለበልቡታል::

እንግሊዞች እግር ኳስን በፍቅር ይወዱታል:: አለም ላይም ሊጋቸው ተወዳጅ እንዲሆን በሚዲያቸው በመጠቀም ተፅኖ አሳድሮዋል:: በአትሌቲክስም ከሀገራቸው አንድ አትሌት ትንሽ ውድድር ካሸነፈ ብዙ ያወሩለታል:: አለም ላይ ያሉ ተርጓሚ ጋዜጠኞችም እዬንኑ ግነት አግንነው ያወሩታል::

በእንግሊዝ ሚዲያ ቀኝ ከተገዙ ሀገራት መካከል የኢትዮጺያ ሚዲያ አንዱ ነው:: ስለ ቀነኒሳ 2ኛ መውጣት ይልቅ ስለ ሞፋራ ሰባተኛ መውጣት ብዙ ይወራለታል:: “የእንግሊዝ ሚዲያ ጅራፉን ያነሳል የኢትዮጺያ ሚዲያ ጅራፉን ያጨዋል”

ገንዘቤ ዲባባ ሰሞኑን አለም ላይ በ15 ቀን 3ሪኮርዶችን እንደ ከረሜላ ኮረሻሽማለች:: የኢትዮጺያ ኔትዎርክ ሳይስተካከል እሷ 3 ሪኮርዶችን ጨፈላልቃለች:: ገንዘቤ በኢትዮጺያ ሚዲያ ሽፋን በበቂ ሁኔታ አልተሰጣትም ብዬ አስባለው:: የሞሪኒሆ ስለ ፈረስ ወሬ በትንታኔ እየቀረበ የገንዘቤ 3 ሪኮርዶች እንደ ዜና ብቻ ቀርበው ሲታለፉ ያስተዛዝባል:: ኢትዮጺያ ውስጥ የእግር ኳስ ጋዜጠኞች እንጂ የስፖርት ጋዜጠኞች ዬሉም የሚለውን ያረጋግጣል::

“ውድድሩ የግል ነው ሀገርን አይወክልም” የሚል ክርክር ሊመጣ ይችላል…. ግን ደደቢት እኮ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የግል ውድድር ነው ሲጠራ የኢትዮጺያው ደደቢት ተብሎ ነው:: በአትሌቲክስም ተመሳሳይ ነው:: “ኢትዮጺያዊቷ (ዲባባስ ፋሚሊ) ገንዘቤ ዲባባ አለም ላይ ነገሰች” ነው የሚባለው::

ገንዘቤ እንደ ምንያህል በጋዜጣ “እንግሊዛዊ ብሆን የኢትዮጺያ ሚዲያ ብዙ ያወራልኝ ነበር" ብትል የእግር ኳስ ጋዜጠኞች እኮ ተሰደብን ብለው በማህበራቸው በኩል መግለጫ ያወጡ ይሆናል:: ምነው ባለች ያስብላል::

ገንዘቤ አቦ እንኳን ተወለድሽ…. እንኳን ሰባበርሽ…. እንኳንም ደስ አለሽ…. ኢቲ ፉፋ

“ሪኮርዱ ቦሌ ፈረሱ ጉለሌ”
የቡና ቁርስ – በEphrem Amare